Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 6

የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ


I. አጠቃላይ መግለጫ
የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባዮሜዲካል ኢንጂነር IV ባዮሜዲካል
የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ
XIV
መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ
በየደረጃው ባሉ ጤና ተቋማት
II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡
 የህክምና መሳሪያዎችን ፍላጎት ጥናት በማካሄድ፣ የአሰራር መመሪያዎችን በማዘጋጀት፣ የህክምና መሳሪያዎችን
ተከላና ጥገና ስራዎች በመደገፍ በመከታተልና በማረጋገጥ እንዲሁም ሙያዊ ምክር በመስጠት የጤና አገልግሎቱን
ሥራ መደገፍ ነው፡፡
2.2.ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1፤ የህክምና መሳሪያዎችን ፍላጎት ጥናት ማካሄድ እና የአሰራር መመሪያዎችን ማዘጋጀት፡፡

 በሁሉም የህክምና መሳሪያዎች ደረጃ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማደርግ ዉሳኔ መስጠት፡፡
 በእርዳታ የሚሰጡ መሳሪያዎችን መቆጣጠርያ መመርያ በማዘጋጀት እንዲጸድቅ ያደርጋል፡፡
 የሚሰጡ የእርዳታ መሳሪያዎች በህጉ መሰረት ተሟልተው መቅረባቸውን ያረጋግጣል፤
 መሰረታዊ የኤሌክትሪክ ደህንነት ቁጥጥር የአሰራር መመሪያዎችን ያዘጋጃል፤ በአግባቡም መዘጋጀታቸውን ይከታተላል
 ለእያንዳንዱ የህክምና መሳሪያዎች የቁጥጥር፤ የጥራት፤ የደህንነት፤ የአስተዳደር መመሪያዎች ያዘጋጃል፤ በአግባቡ
መተግበራቸውን ይከታተላል
 የአገልግሎት ግዚያቸውን የጨረሱ የህክምና መሳሪያዎች ማስወገጃ መመሪያ ማዘጋጀት፣ ሲወገዱም መመሪያውን
በመከተል መወገዳቸውን ይከታተላል
 ለኢንጅነሮችና ቴክንሺያኖች ስልጠና ለመስጠት የሚያስችሉ የስልጠና ማኑዋሎችን ማዘጋጀት፤

ውጤት 2፡- የህክምና መሳሪያዎችን ተከላ እና ጥገና ስራዎች መደገፍ፣መከታተልና መገምገም

 በድርጅቱ ለተገዙም ሆነ በእርዳታ ለተሰጡ መሳሪያዎች የተሰጡ የተከላ ማንዎሎችን በመከተል ተገቢውን የተከላ ቦታ
መመቻቸቱንና ተከላው መከናወኑን ይከታተላል፣ ያጸድቃል፣ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል

1
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

 የቅድመ ጥገና ፕሮግራም መዘጋጀቱን ይከታተላል፤ ሲዘጋጅም ያጸድቃል


 ተገቢው የጥገና እና ካሊብሬሽን ሥራ በተገቢው ሁኔታ መከናወኑን ይከታተላል፣
 የድህረ-ገበያ መሳሪያ ቁጥጥር ላይ ይሳተፋል፤በመሳሪያው አማካኝነት የሚከሰቱ ችግሮችን ሪፖርት ያደርጋል
 የህክምና መሳሪያዎችን የጥገና አገልግሎቶች በአጠቃላይ ይገመግማል፤ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ
ያደርጋል
 የተሰሩ የጥገና መሳሪያዎችን መረጃ መደራጀቱን፣ ሪፖርት በጊዜ መቅረቡን ክትትልና ግምገማ ያደርጋል
 የተቋሙን የህክምና መሳሪያ ቡድን(ከተለያዩ ክፍሎች የሚዋቀር) ይመራል፤ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል
 በመሳሪያዎች ዙሪያ አስፈላጊውን የማማከር አገልግሎት ይሰጣል
 የመሳሪያዎችን አጠቃላይ መረጃ በሶፍት ኮፒና በሃርድ ኮፒ መያዙን ክትትልና ግምገማ ያደርጋል
ውጤት 3፤ የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት መከታተል እና ሙያዊ ምክር መስጠት
 የህክምና መሳሪያዎችን የግዥ እቅድ ዝግጅት ይከታተላል፣ ይመራል
 ዝርዝር የመሳሪያ technical specification ያዘጋጃል፤ የተዘጋጁትንም ይመረምራል ያጸድቃል
 የህክምና መሳሪያዎች ከመገዛታቸው በፊትና ከተገዙ በኋላ የምርመራና የግምገማ ስራን ይሰራል፤ይከታተላል
 ከህክምና መሳሪያዎች አቅራቢዎቸች ጋር ያሉ ስምምነተችን ያስተዳድራል፤የሚነሱ አለመግባባቶችን ለበላይ ኃላፊ
በማቅረብ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል
 ለመለዋወጫ የሚዉሉ የህክምና መሳሪያዎችን ግዥ ጥያቄ ይመረምራል ያጸድቃል ግዥ እንዲፈፀም ያደርጋል
 ለመሳርያው ተጠቃሚ የጤና ባለሙያዎች ማለትም ለዶክተሮችና ለነርሶች የአጠቃቀም ሥልጠና መሰተጠቱንና
ተገቢው ደጋፍ መደረጉን ይከታተላል፣ ያሰለጥናል፣

III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች


3.1 የሥራ ውስብስብነት
 ሥራው የህክምና መሳሪያዎች የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ፣ በእርዳታ የሚሰጡ መሳሪያዎችን መቆጣጠሪያ
መመርያ ማዘጋጀት፣ መሰረታዊ የኤሌክትሪክ ደህንነት ቁጥጥር የአሰራር መመሪያዎችን ማዘጋጀት፣ ለእያንዳንዱ
የህክምና መሳሪያዎች የቁጥጥር፤ የጥራት፤ የደህንነት፤ የአስተዳደር መመሪያዎች ማዘጋጀት፣ የአገልግሎት
ጊዜያቸውን የጨረሱ የህክምና መሳሪያዎች ማስወገጃ መመሪያ ማዘጋጀት፣ ለኢንጅነሮችና ቴክንሺያኖች ስልጠና
ለመስጠት የሚያስችሉ የስልጠና ማኑዋሎችን ማዘጋጀት፤ የህክምና መሳሪያዎች የተከላ ማንዎሎችን በመከተል
ተከላው መከናወኑን መከታተል፣ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ በመሳሪያዎች ዙሪያ አስፈላጊውን የማማከር አገልግሎት
መስጠት፣ ዝርዝር የመሳሪያ technical specification ማዘጋጀት፤ የተዘጋጁትንም መመርመር እና የህክምና
መሳሪያዎች ከመገዛታቸው በፊትና ከተገዙ በህዋላ የምርመራና የግምገማ ሥራን መስራት ሲሆን በስራ ሂደትም
ሥለመሳሪያዎች አተካከልና አጠጋገን የሚያስረዳዉ ማንዋል አለመቅረብ፣ ስለመሳሪያ ተከላና አጠጋገን ከአምራቹ

2
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ወይም ከአቅራቢው ድርጅት በቂ ስልጠና አለማግኘት እና የመለዋወጫ እቃዎች የአቅርቦት ችግር መከሰት፣
የቴክኖሎጅው በየጊዜው መለዋወጥ፣ የመረጃ እጥረት የሚያጋጥም ሲሆን ስለመሳርያው አጠቃላይ ሁኔታ
የሚያስረዱ ማንዋሎች እንዲቀርቡ በማድረግ፣ ከመሳሪያ አቅራቢው ድረጅት ሥልጠና በመውሰድ፣ በየጊዜው
ከሚሰሩ የህክምና መሳሪያዎች ጋር ራሱን በማስተዋወቅ፣ ወቅታዊና የተሟላ መረጃ የሚያገኝበትን ሥልት በመቀየስ
እና የመለዋወጫ እቃዎች የሚገኙበትን አማራጭ በማየትና ተግባራዊ እንዲሆኑ በማድረግ መፍታትን ይጠይቃል፡፡
3.2 ራስን ችሎ መስራት
3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 የመሳሪያዎች የአጠቃቀም ደንብና በመመሪያ ከቅርብ ሃላፊ በሚሰጥ አጠቃላይ መመሪያ በአሰራር መመሪያዎች
እንዲሁም የአሰራር መርሆዎችን መሰረት በማድረግ የሚከናወን ነው፡፡
3.2.1 ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
 የህክምና መሳሪያዎች ጥገናና ተከላ ሥራው አስፈላጊውን ውጤት ከማምጣቱና ከለሌች የህክምና ሥራዎች ጋር
ካለው ውህደት አኳያ በመጨረሻ ይገመገማል፡፡

3.3 ተጠያቂነት
3.3.1 ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት፣
 የህክምና መሳሪያዎች የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ባያካሂድ፣ በእርዳታ የሚሰጡ መሳሪያዎችን መቆጣጠሪያ መመርያ
ባያዘጋጅ፣ መሰረታዊ የኤሌክትሪክ ደህንነት ቁጥጥር የአሰራር መመሪያዎችን ባያዘጋጅ፣ ለእያንዳንዱ የህክምና
መሳሪያዎች የቁጥጥር፤ የጥራት፤ የደህንነት፤ የአስተዳደር መመሪያዎች ባያዘጋጅ፣ የአገልግሎት ጊዜያቸውን የጨረሱ
የህክምና መሳሪያዎች ማስወገጃ መመሪያ ባያዘጋጅ፣ ለኢንጅነሮችና ቴክንሺያኖች ስልጠና ለመስጠት የሚያስችሉ
የስልጠና ማኑዋሎችን ባያዘጋጅ፤ የህክምና መሳሪያዎች የተከላ ማንዎሎችን በመከተል ተከላው መከናወኑን
ባይከታተል፣ ድጋፍና ክትትል ባያደርግ፣ በመሳሪያዎች ዙሪያ አስፈላጊውን የማማከር አገልግሎት ባይሰጥ፣ ዝርዝር
የመሳሪያ technical specification ባያዘጋጅ፤ በሌሎች ባለሙያዎች የተዘጋጁትንም ባይመረምር እና የህክምና
መሳሪያዎች ከመገዛታቸው በፊትና ከተገዙ በኋላ የምርመራና የግምገማ ሥራን ባይሰራ ደረጃቸውን ያልጠበቁ
መሳሪያዎች እንዲገዙ ያደርጋል፤ መሳሪያው የሚጠበቅበትን ያክል ጊዜና አገልግሎት እንዳይሰጥ ያድረጋል፣ በድርጅቱ
የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ያስተጓጉላል፣ በመሳርያው ተጠቃሚ የጤና ባለሙያና በህሙማኑ ላይ አደጋ ያስከትላል
እንዲሁም በተቋሙ እቅድ አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡
3.3.2 ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣
 የለበትም
3.4 ፈጠራ
 ሥራው አጠቃላይ የጤና አገልግሎት መስጫ መሳሪያዎችን ተከላና ጥገና እንዲሁም ማስወገድ ስራን መስራት፣

3
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

መምራት መክታተልና መደገፍ ሲሆን የመሳሪያዎች አጠቃላይ ሁኔታ የሚያስረዳ ማንዋል ባልተገኘበት እና በጥገና
ወቅት የመለዋወጫ እጥረት ቢገጥም የመሳሪያውን ባህሪ ተረድቶ ስራውን ለማከናወን እና እንዲያከናዉኑ ለማድረግ
አዳዲስ ሲስተሞችንና አሰራሮችን በመፍጠር፣ አለማቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመርና ትግባራዊ እንዲሆን
በማድረግ እና ከፍተኛ የሞዲፊኬሽን ስራዎችን በመስራት ስራውን ውጤታማ ማድረግን ይጠይቃል፡፡

3.5. የሥራ ግንኙነት


3.5.1 የግንኙነት ደረጃ
 ሥራው ከቅርብ ሃላፊው፣ ከባልደረቦቹ፤ ከግዥና ፋይናንስ ፤ ከመሳሪያው ተገልጋዮች እንዲሁም ከመሳሪያው ሻጭ
ድርጅት ጋር የሥራ ግንኙነት ማድረግን ይጠየቃል፡፡
3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ
 ሪፓርት ለማቅረብ ፣ለማማከር ፤ ስለ ስራው መረጃና ድጋፍ ለመስጠት፤ ሥራን በጋራ ለመስራት፣ የተለያዩ
የመላዋወጫና የመገልገያ ቁሶች እንዲገዙለት ለማድረግ እንዲሁም ከመሳሪያው አቅራቢ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ
ለመወያየት፣ ለመደራደር፣ ስምምነት ላይ ለመድረስ፣ በመመሪያዎች ላይ ስልጠና ለመስጠት ነው፡፡

3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ


 ከስራ ጊዜው እስከ 50 በመቶ ይሆናል

3.6 ኃላፊነት
3.6.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት
3.6.1.1 በኃላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት
 የለበትም፡፡
3.6.1.2 የኃላፊነት አይነትና ደረጃ
 የለበትም፡፡
3.6.2 ኃላፊነት ለንዋይ
 የለበትም ፡፡
3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት
 ሥራው ለተከላ፤ለጥገና እንዲሁም ለካሊብሬሽን የሚያገለግሉ የዎርክሾፕ መሳሪያዎችን እና የቢሮ መገልገያ
ቁሳቁሶች (computer, laptop, printer….) የመያዝ ሃላፊነት ያለበት ሲሆን ግምቱም እስከ ብር 5,000,000 ብር

4
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ይሆናል፡፡
3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
 ሥራው የህክምና መሳሪያዎች የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት የማካሄድ፣ በእርዳታ የሚሰጡ መሳሪያዎችን መቆጣጠሪያ
መመርያ የማዘጋጀት፣ መሰረታዊ የኤሌክትሪክ ደህንነት ቁጥጥር የአሰራር መመሪያዎችን የማዘጋጀት፣ ለእያንዳንዱ
የህክምና መሳሪያዎች የቁጥጥር፤ የጥራት፤ የደህንነት፤ የአስተዳደር መመሪያዎች የማዘጋጀት፣ የአገልግሎት
ጊዜያቸውን የጨረሱ የህክምና መሳሪያዎች ማስወገጃ መመሪያ የማዘጋጀት፣ ለኢንጅነሮችና ቴክንሺያኖች ስልጠና
ለመስጠት የሚያስችሉ የስልጠና ማኑዋሎችን የማዘጋጀት፤ የህክምና መሳሪያዎች የተከላ ማንዎሎችን በመከተል
ተከላው መከናወኑን የመከታተል፣ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ በመሳሪያዎች ዙሪያ አስፈላጊውን የማማከር አገልግሎት
የመስጠት፣ ዝርዝር የመሳሪያ technical specification የማዘጋጀት፤ የተዘጋጁትንም የመመርመር እና የህክምና
መሳሪያዎች ከመገዛታቸው በፊትና ከተገዙ በህዋላ የምርመራና የግምገማ ሥራን የመስራት የአዕምሮ ውጥረት
የሚጠይቅ ሲሆን ይህም ከስራ ጊዜው እስከ 75 በመቶ ይሆናል፡፡
3.7.2.ስነልቦናዊ ጥረት
 ሥራው በተደጋጋሚ ከቅርብ ሀላፊው፤ከባልደረቦቹ፤ከሂሳብና ፋይናንስ ክፍል፤ ከመሳሪያው ተገልጋዮቹ እንዲሁም
ከመሳሪያው አቅራቢ ጋር በሚያደርጋቸው ግኑኝነቶች የሚነሱ የተለያዩ
አለመግባባቶችን(ትችት፤ማጥላላት፤አለመታዘዝ፤ወዘተ) ተቋቁሞ ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የስነ ልቦና
ዝግጁነትና ቁርጠኝነት እንዲኖረው ይጠይቃል፡፡
3.7.3 የዕይታ ጥረት፣
 ስራው ከኢንተርኔት የመሳሪያዎችን አተካከልና አጠጋገን የሚያስረዳ ማንዋልና መረጃዎችን መፈለግን እና ጨረር
አመንጭ የሆኑ የህክምና መሳሪያዎችን መትክልና መጠገን የሚጠይቅ ሲሆን ይህም የእይታ ጥረትን ይጠይቃል ከስራ
ጊዜው እስከ 50 በመቶ ይወስዳል፡፡
3.7.4 የአካል ጥረት
 ሥራው 30% በመቀመጥ፤ 30% በመቆም እና 40% በመንቀሳቀስ የሚከናወን ነው፡፡
3.8. የሥራ ሁኔታ
3.8.1. ሥጋትና አደጋ
 በሥራው ወቅት በጋሉ የመሳሪያ ክፍሎች አማካኝነት ለቃጠሎ፣ የህክምና መሳሪያዎች አማካኝነት የመቆረጥና በከፊል
የሰውነት ክፍልን ማጣት እንዲሁም በአግባቡ ባልተዘረጉ የመብራት መስመሮች ለሚከሰት የኤሌክትሪክ ንዝረት
ይጋለጣል፡፡

5
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

3.8.2. የሥራ አካባቢ ሁኔታ


 ሥራው ጎጂ ለሆኑ በሽታ አምጭ ተዋስህያን፤ ጨረርና መርዛማ ኬሚካሎች ባሉነት የሚከናወን ሲሆን ይህም በቆዳ
በአይን እንዲሁም የመሃንነት ችግር በማስከተል ለከፍተኛ ለጤና መታወክ ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡
3.9. እውቀትና ክህሎት፣
3.9.1. ትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት አይነት
መጀመሪያ ድግሪ ባዮሜዲካል ኢንጅነሪንግ
3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ
የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
9 ዓመት በባዮሜዲካል ኢንጅነሪንግ

የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like