Biomedical Engineer III

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 6

የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ


I. አጠቃላይ መግለጫ
የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባዮሜዲካል ኢንጂነር III ባዮሜዲካል

የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ


XIII
መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ
በየደረጃው ባሉ ጤና ተቋማት
II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡
 ከፍተኛ የህክምና መሳሪያዎችን ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ፤ የህክምና መሳሪያዎች ከመገዛታቸው በፊትና ከተገዙ
በኋላ የተከላና ጥገና ምርመራና የግምገማ ሥራን በመስራት፣ መሳሪያዎችን በመትከልና ለአገልግሎት ዝግጁ
በማድረግ እንዲሁም በመሳሪያዎች አጠቃቀም ዙርያ ለጤና ባለሙያዎች፣ ለቴክኒሺያኖች እና ለኢንጅነሮች ሥልጠና
በመስጠትና የጤና አገልግሎቱን ሥራ መደገፍ ነው፡፡
2.2.ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1፤ የከፍተኛ የህክምና መሳሪያዎችን ፍላጎት ጥናት የማካሄድ እና የማማከር፣ የመደገፍ ሥራዎችን ማከናወን፣ ተከላ
በማከናወን ለአገልግሎት ዝግጁ ማረግ፡፡

 የሚፈለገውን የህክምና መሳሪያዎችን ፍላጎት ለማወቅ የዳሰሳ ትንተና ያካሂዳል/ይገመግማል፣


 ለመለዋወጫ የሚዉሉ መሳሪያዎች ግዢ ጥያቄዎችን ይመረምራል፣ ያጸድቃል፣
 የከፍተኛ ህክምና መሳሪያዎችን የግዥ እቅድ እና ሰነድ ያዘጋጃል፣
 ከፍተኛ የህክምና መሳሪያዎች የጨረታ ቴክኒካል ግምገማ ያካሂዳል ያደርጋል፣
 ከፍተኛ የህክምና መሳሪያዎች ከመገዛታቸው በፊትና ከተገዙ በህዋላ የምርመራና የግምገማ ስራን ይሰራል፣
 በከፍተኛ ህክምና መሳሪያዎች ዙሪያ አስፈላጊውን የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፣
 የከፍተኛ የህክምና መሳሪያዎችን ዝርዝር መስፈርት (technical specification) ያዘጋጃል፤
 ከህክምና መሳሪያዎች አቅራቢዎች ጋር ያሉ ስምምነቶችን ያስተዳድራል፣
 የህክምና መሳሪያዎች መለዋወጫዎችና አላቂዎች በግዢ ትዕዛዙ መሰረት መሆኑና ያረጋግጣል፣
 በእርዳታ የሚሰጡ መሳሪያዎችን በአገር አቀፍ ህግ መሰረት ተሟልተው መቅረባቸውን ያረጋግጣል፤
 በድርጅቱ ለተገዙም ሆነ በእርዳታ ለተሰጡ መሳሪያዎች የተሰጡ የተከላ ማንዎሎችን በመከተል ተገቢውን የተከላ ቦታ

1
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

መመቻቸቱንና ተከላው መከናወኑን ይከታተላል ያጸድቃል/ክፊያ እንዲፈጸም ሪፖርት ያደርጋል


ውጤት 2፤ የከፍተኛ የህክምና መሳሪያዎችን የጥገና ስራዎችን በመስራት ለአገልግሎት ዝግጁ ማረግ፤

 የአነስተኛ እና መካከለኛ ቅድመ ጥገና ፕሮግራም መዘጋጀቱን ይከታተላል ፤ሲዘጋጅም ያጸድቃል


 የአነስተኛ እና መካከለኛ መሳሪያዎች የጥገና እና ካሊብሬሽን ሥራ በተገቢው ሁኔታ መከናወኑን ይከታተላል፣
 መሰረታዊ የኤሌክትሪክ ደህንነት ቁጥጥር የአሰራር መመሪያዎችን ያዘጋጃል፤
 ለእያንዳንዱ የህክምና መሳሪያዎች የተዘጋጁ የቁጥጥር የጥራት የደህንነት እና የአስተዳደር መርሆችን
መተግበራቸውን ይከታተላል
 የድህረ-ገበያ መሳሪያ ቁጥጥር ላይ ይሳተፋል፤ በመሳሪያው አማካኝነት የሚከሰቱ ችግሮችን ሪፖርት ያደርጋል
 የአገልግሎት ግዚያቸው የጨረሱ ከፍተኛ የህክምና መሳሪያዎችን ተገቢውን መመርያ በመከተል ማስወገድ
 የአነስተኛ እና መካከለኛ ህክምና መሳሪያዎችን የጥገና አገልግሎቶች በአጠቃላይ ይገመግማል፤ ተገቢው የማስተካከያ
እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል
ውጤት 3፤ በፍተኛ የህክምና መሳሪያዎች አጠቃቀምና አሰራር ዙርያ ለቴክኒሺያኖች፤ለኢንጅነሮች እና ለጤና ባለሙያዎች
ሥልጠና መስጠትና እና መጃዎችን መያዝ
 ለከፍተኛ የጤና መሳሪያ ተጠቃሚ የጤና ባለሙያዎች፣ ለቴክኒሺያኖች እና ለኢንጅነሮች የአጠቃቀም ሥልጠና
ይሰጣል ተገቢውን ደጋፍና ክትትል ያደርጋል፣
 ለኢንጅነሮችና ቴክንሺያኖች ስልጠና ለመስጠት የሚያስችሉ ማኑዋሎችን ያዘጋጃል፡፡
 የመሳሪያዎችን አጠቃላይ መረጃ በሶፍት ኮፒና በሃርድ ኮፒ መያዙን ክትትልና ግምገማ ያደርጋል
 የተሰሩ የጥገና መሳሪያዎችን መረጃ መደራጀቱን፣ ሪፖርት በጊዜ መቅረቡን ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፣

III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች


3.1 የሥራ ውስብስብነት
 ሥራው ከፍተኛ የህክምና መሳሪያዎችን ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ፤ የከፍተኛ ህክምና መሳሪያዎችን የግዥ እቅድ
ማዘጋጀትና ግዥ ሲፈፀም ማመከር፤ ቴክኒካል ስፔስፍኬሽን ማዘጋጀት፤ በርዳታ የሚሰጡና አዳዲስ የሚገዙ
መሳሪያዎችን በመመርመር መትከል፣ የቅድመ ጥገና ፕሮግራም ማዘጋጀት፤ ተገቢውን የጥገና እና ካሊብራሽን ሥራ
ማከናወን፤ በከፍተኛ ህክምና መሳሪያዎች ዙሪያ አስፈላጊውን የማማከር አገልግሎት መሥጠት፣ ዝርዝር የመሳሪያ
technical specification ማዘጋጀት፣ በእርዳታ የሚሰጡ መሳሪያዎችን በአገር አቀፍ ህግ መሰረት ተሟልተው
መቅረባቸውን ማረጋገጥ፤ መሰረታዊ የኤሌክትሪክ ደህንነት ቁጥጥር የአሰራር መመሪያዎችን ማዘጋጀት እና
የአገልግሎት ጊዜያቸውን የጨረሱ ከፍተኛ የህክምና መሳሪያዎችን ማስወገድ ሲሆን በስራ ሂደትም ምቹ የተከላ ቦታ
ማግኘት አስቸጋሪ መሆን፣ ሥለመሳሪያዎች አተካከልና አጠጋገን የሚያስረዳዉ ማንዋል አለመቅረብ፣ ስለመሳሪያ
ተከላና አጠጋገን ከአምራቹ ወይም ከአቅራቢው ድርጅት በቂ ስልጠና አለማግኘት፣ የመረጃ እጥረት፣ የቴክኖሎጅ

2
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

በየግዜው መቀያየር እና የመለዋወጫ እቃዎች የአቅርቦት ችግር መከሰት የሚያጋጥም ሲሆን የተለያዩ አማራጮችን
ወስዶ የመሳርያ መትከያ ቦታዎችን በማዘጋጀት፣ ስለመሳርያው አጠቃላይ ሁኔታ የሚያስረዱ ማንዋሎች እንዲቀርቡ
በማድረግ፣ ከመሳሪያ አቅራቢው ድረጅት ሥልጠና በመውሰድ፣ የመለዋወጫ እቃዎች የሚገኙበትን አማራጭ
በማየትና ተግባራዊ እንዲሆኑ በማድረግ፣ የተልያዩ የመረጃ ምንጮችን በመጠቀም እና እራሱን በየጊዜው ከቴክኖሎጅ
ጋር በማስተዋወቅ መፍታትን ይጠይቃል፡፡
3.2 ራስን ችሎ መስራት
3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 ሥራው የመሳሪያዎች የአጠቃቀም ደንብና በመመሪያ ከቅርብ ሃላፊ በሚሰጥ አጠቃላይ መመሪያ በአሰራር
መመሪያዎች እንዲሁም የአሰራር መርሆዎችን መሰረት በማድረግ የሚከናወን ነው፡፡
3.2.2 ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
 የህክምና መሳሪያዎች ጥገናና ተከላ ሥራው አስፈላጊውን ውጤት ከማምጣቱና ከለሌች የህክምና ሥራዎች ጋር
ካለው ውህደት አኳያ በመጨረሻ ይገመገማል፡፡
3.3 ተጠያቂነት
3.3.1 ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት፣
 የፍተኛ የህክምና መሳሪያዎችን ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ባያካሂድ፤ የግዥ እቅድ ባያዘጋጅና ግዥ ሲፈፀም ባያማክር፤
ቴክኒካል ስፔስፍኬሽን ባያዘጋጅ፤ በርዳታ የሚሰጡና አዳዲስ የሚገዙ መሳሪያዎችን በመመርመር ተከላ ባያከናውን፣
የቅድመ ጥገና ፕሮግራም በማዘጋጀት ተገቢውን የጥገና እና ካሊብራሽን ሥራ ባያከናውን፤ በከፍተኛ ህክምና
መሳሪያዎች ዙሪያ አስፈላጊውን የማማከር አገልግሎት ባይሰጥ፣ በእርዳታ የሚሰጡ መሳሪያዎችን በአገር አቀፍ ህግ
መሰረት ተሟልተው መቅረባቸውን ባያረጋግጥ፤ መሰረታዊ የኤሌክትሪክ ደህንነት ቁጥጥር የአሰራር መመሪያዎችን
ባያዘጋጅ እና የአገልግሎት ግዚያቸውን የጨረሱ ከፍተኛ የህክምና መሳሪያዎችን ባያስወግድ ደረጃቸውን ያልጠበቁ
መሳሪያዎች እንዲገዙ ያደርጋል፤ መሳሪያው የሚጠበቅበትን ያክል ጊዜና አገልግሎት ሳይሰጥ ከጥቅም ውጭ እንዲሆን
ያድርጋል፣ በድርጅቱ የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ያስተጓጉላል፣ በመሳርያው ተጠቃሚ የጤና ባለሙያና በህሙማኑ
ላይ አደጋ ያስከትላል እንዲሁም በተቋሙ ዕቀድ አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡
3.3.2 ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣
 የለበትም
3.4 ፈጠራ
 ሥራው የጤና አገልግሎት መስጫ መሳሪያዎችን ተከላ ማከናወንና ሲበላሹም ጥግና ማድረግ እንዲሁም ማስወገድ
ሲሆን የመሳሪያዎች አጠቃላይ ሁኔታ የሚያስረዳ ማንዋል ባልተገኘበት ወቅት እና በጥገና ወቅት የመለዋወጫ እጥረት
ቢገጥም የመሳሪያውን ባህሪ ተረድቶ ስራውን ማከናወን፣ አዳዲስ ሲስተሞችን ፈጥሮ ትግባራዊ በማድረግ እና
ከፍተኛ የሞዲፊኬሽን ስራዎችን በመስራት ስራውን ውጤታማ ማድረግን ይጠይቃል፡፡

3
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

3.5. የሥራ ግንኙነት፣


3.5.1 የግንኙነት ደረጃ
 ሥራው ከቅርብ ሃላፊው፣ከባልደረቦቹ፤ ከፋይናንስና ግዢ፤ ከተገልጋዮች እንዲሁም ከመሳሪያው ሻጭ ድርጅት ጋር
የሥራ ግንኙነት ማድረግን የጠየቃል፡፡
3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ
 ሪፓርት ለማቅረብ ፣ለማማከር ፤ ስለ ስራው መረጃና ድጋፍ ለመስጠት፤ ሥራን በጋራ ለመስራትና፣ የተለያዩ
የመላዋወጫና የመገልገያ ቁሶች እንዲገዙለት ለማድረግ እንዲሁም ከመሳሪያው አቅራቢ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ
ለመወያየት፣ ስምምነት ላይ መድረስ፣ መደራደርና አጥጋቢ ስምምነት ላይ ለመድረስ ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡

3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ


 ከስራ ጊዜው እስከ 40 በመቶ ይሆናል
3.6 ኃላፊነት
3.6.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት
 የለበትም
3.6.1.1 በኃላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት
 የለበትም
3.6.1.2 የኃላፊነት አይነትና ደረጃ
 የለበትም
3.6.2 ኃላፊነት ለንዋይ
 የለበትም ፡፡
3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት
 ሥራው ለተከላ፤ለጥገና እንዲሁም ለካሊብሬሽን የሚያገለግሉ የዎርክሾፕ መሳሪያዎችን እና የቢሮ መገልገያ
ቁሳቁሶች (computer, laptop, printer….) የመያዝ ሃላፊነት ያለበት ሲሆን ግምቱም እስከ ብር 5,000,000 ብር
ይሆናል፡፡
3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
 ከፍተኛ የህክምና መሳሪያዎችን ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት የማካሄድ፤ የግዥ እቅድ የማዘጋጀትና ግዥ ሲፈፀም የማመከር፤
ቴክኒካል ስፔስፍኬሽን የማዘጋጀት፤ በርዳታ የሚሰጡና አዳዲስ የሚገዙ መሳሪያዎችን የመመርመር፣ የቅድመ ጥገና
ፕሮግራም የማዘጋጀት፤ ተገቢውን የጥገና እና ካሊብራሽን ሥራ የማከናወን፤ በከፍተኛ ህክምና መሳሪያዎች ዙሪያ
አስፈላጊውን የማማከር አገልግሎት የመሥጠት፣ ዝርዝር የመሳሪያ technical specification የማዘጋጀት፣ በእርዳታ

4
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሚሰጡ መሳሪያዎችን በአገር አቀፍ ህግ መሰረት ተሟልተው መቅረባቸውን የማረጋጥ፤ መሰረታዊ የኤሌክትሪክ
ደህንነት ቁጥጥር የአሰራር መመሪያዎችን የማዘጋጀት እና የአገልግሎት ግዚያቸውን የጨረሱ ከፍተኛ የህክምና
መሳሪያዎችን ማስወገድ የአዕምሮ ውጥረት የሚጠይቅ ሲሆን ይህም ከስራ ጊዜው እስከ 65 በመቶ ይሆናል፡፡
3.7.2.ስነልቦናዊ ጥረት
 ሥራው በተደጋጋሚ ከቅርብ ሀላፊው፤ከባልደረቦቹ፤ከሂሳብና ፋይናንስ ክፍል፤ ከመሳሪያው ተገልጋዮቹ እንዲሁም
ከመሳሪያው አቅራቢ ጋር በሚያደርጋቸው ግኑኝነቶች የሚነሱ የተለያዩ አለመግባባቶችን(ትችት፤ማጥላላት ወዘተ)
ተቋቁሞ ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የስነ ልቦና ዝግጁነትና ቁርጠኝነት ይጠይቃል፡፡
3.7.3 የዕይታ ጥረት፣
 ስራው ከኢንተርኔት የከፍተኛ መሳሪያዎችን አተካከልና አጠጋገን የሚያስረዳ ማንዋልና መረጃዎችን መፈለግን እና
ጨረር አመንጭ የሆኑ የህክምና መሳሪያዎችን መትክልና መጠገን የሚጠይቅ ሲሆን ይህም የእይታ ጥረትን ይጠይቃል
ይህም ከስራ ጊዜው እስከ 50 በመቶ ይወስዳል፡፡
3.7.4 የአካል ጥረት
 ሥራው 40% በመቀመጥ፤ 20% በመቆም፣20% በመንቀሳቀስ፣10 በመቶ በመንጋለል የሚከናወን ነው፡፡
3.8. የሥራ ሁኔታ
3.8.1. ሥጋትና አደጋ
 በሥራው ወቅት በጋሉ የመሳሪያ ክፍሎች አማካኝነት ለቃጠሎ፣ የህክምና መሳሪያዎች አማካኝነት የመቆረጥና በከፊል
የሰውነት ክፍልን ማጣት እንዲሁም በአግባቡ ባልተዘረጉ የመብራት መስመሮች ለሚከሰት የኤሌክትሪክ ንዝረት
ይጋለጣል፡፡
3.8.2. የሥራ አካባቢ ሁኔታ
 ሥራው ጎጂ ለሆኑ በሽታ አምጭ ተዋስህያን፤ ጨረርና መርዛማ ኬሚካሎች ባሉነት የሚከናወን ሲሆን ይህም በቆዳ
በአይን እንዲሁም የመሃንነት ችግር በማስከተል ለከፍተኛ ለጤና መታወክ ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡
3.9. እውቀትና ክህሎት፣
3.9.1. ትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት አይነት
መጀመሪያ ድግሪ ባዮሜዲካል ኢንጅነሪንግ
3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ
የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
6 ዓመት በባዮሜዲካል ኢንጅነሪንግ

የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

5
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like