AWA 2012 Annual Plan 2

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 34

በአማራ ሴቶች ማህበር

የ 2012 በጀት ዓመት እቅድ

ሰኔ 2011 ዓ.ም

ባ/ዳር፣

መግቢያ
የአማራ ሴቶች ማህበር የክልሉን ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት
ለማረጋገጥ ዓላማ አድርጐ በመስራት ላይ ያለ ማህበር ነው፡፡ በክልሉ የልማት የመልካም አስተዳዳርና
የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አባላት የሚጠበቅባቸውን የበኩላቸውን ሚና በመወጣት በሂደቱም ተሳትፎና
ተጠቃሚነታቸው እያደገ እንዲሄድ አልሞ በመስራቱ በርካታ ለውጦች በመታየት ላይ ይገኛል፡፡

1
ማህበሩ ከተቋቋመበት ዓላማ አኳያ የአባላቶቹን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በማህበሩ ከሚታቀዱ
ግቦች በተጨማሪ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት ጋር በመቀናጀት የአባላቱን ግንዛቤ በመፍጠርና በማነሳሳት
ግንባር ቀደም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረግ ባለፈ ሌሎች ሴቶችም ተሳትፏቸው እንዲጨምር በማነሳሳት
የአረያነት ተገባር እየተወጣ ያለ አደረጀጀት ነው፡፡ የማህበሩን የመፈፀም አቅም የመገንባትና የማብቃት ስራ
ለማጠናከር በየደረጃው ባለው አመራር የሚታየውን የአመለካከት፣ የክህሎት፣ የአሠራር፣ አደረጃጀትና
የግብአት ችግሮችን የሚፈታ ተከታታይ የሆነ የአቅም ግንባታ ሥራ በመስራትና ተቋማዊ አሰራሩን ለመገባት
ተግባራትን በምእራፍ በመከፋፈል በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ፣ በተግባር ምዕራፍና በማጠቃለያ ምዕራፍ
ለማከናወን በሚደረገው ጥረት የማህበሩ የመፈፀም ብቃት በአንፃራዊነት ለማሻሻል ጥረት ተደርጓል፡፡

ማህበሩ አገራዊ እና ክልላዊ ለውጡን ተከትሎ ገጠሙትን በሰፊው የአመራር መለዋወጥ ችግሮች እና የስራ
መፋዘዞችን ሊፈታ በሚችል መንገድ በ 2012 ዓ/ም የበጀት አመት ሊፈታ በሚችል መንገድ አቅዶ መስራት
ስላለበት እና የመንግስት 2 ኛው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የመጨረሻ አመት በመሆኑ በቅንጅት
በመስራት ሴቶችን ተጠቃሚነት የበለጠ በሚያረጋግጥ መንገድ መስራት ይኖርብናል፡፡

በአጠቃላይ የማህበሩን የ 2 ዐ 11 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም በመገምገም ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን፣ እንደመነሻ
በመውሰድ የማህበሩ የ 2 ዐ 12 ዓ.ም የመነሻ እቅድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል፡፡ ዕቅዱ የመነሻ ሁኔታዎችን፣
የማህበሩን ራዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች፣ የቁልፍ ተግባር እና አበይት ተግባራት ዕቅድ፣ የማስፈፀሚያ ስልቶች
እና የክትትልና ግምገማ ስርዓት ያካተተ ነው፡፡

ሀ. የእቅድ መነሻ ሁኔታ

1. የ 2 ዐ 11 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም እንደመነሻ

በ 2011 ዓ/ም በጀት አመት የአባላትን ብሎም የመላ ሴቶችን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከቅድመ ዝግጅት
ስራችን ጀምሮ እስከ ማጠቃለያ ስራወች በቁልፍ እና አብይ ተግባር እቅዶቻችን አፈጻጸም ያስመዘገብናቸው ስኬቶች
እንዲሁም ጥንካሬ እና ድክመቶቻችን እንደመነሻ በመውሰድ የ 2012 እቅድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል፡፡

1.1 መዋቅራዊ አደረጃጀት

1.2 ማህበሩ ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ


1.2.1 የክልሉ ስራ አስፈጻሚ ያለበት ሁኔታ

እንደሚታወቀው የማህበሩ እስትራቴጅካዊ አመራር፤ ለማህበሩ አሰራር መመሪያወችን እና ደንቦችን


የሚያወጣ፤ የተሻሉ አሰራሮችን የሚያዘጋጅ እና እስከታችኛው ያለውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጠናከር
ለተፈጻሚነቱ ክትትል በማድረግ ማህበሩ ከተቋቋመበት አላማ አንጻር ግቡን እንዲመታ በማድረግ በኩል
2
ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው የበላይ አመራር የሆነው የክልሉ ስራ አስፈጻሚ መሆኑ ያታወቃል፡፡ የክልል ስራ
አስፈጻሚ ኮሚቴው የተቋሙ የበላይ አመራር እንደመሆኑ መጠን ማህበሩ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት
የተቋሙን ስትራቴጅክ እቅድ ከማቀድ ጀምሮ በየደረጃው ለሚገኙ ፈጻሚ አካላት ብቁ ኦረንቴሽን በመስጠትና
በመስራት እንዲሁም ተፈጻሚነቱን ትኩረት ሰጦ በመከታተል ረገድ የሰራዉ ስራ አበረታች ነው፡፡ ይህ
እንደተጠበቀ ሆኖ አንዳንድ የክልሉ ስራ አስፈጻሚ አባላት የአማራ ሴቶች ፌዴሬሽን አመራሮችም ስለሆኑና
ማህበራችን የአማራ ሴቶች ፌዴሬሽን አባል ስለሆነ ይህንን ሁኔታ እንደ ምቹ አጋጣሚ በመዉሰድ ፕሮጀክት
ቀርጸዉ ያገኙትን በጀት በመጠቀም ማህበሩ ወደፊት እንዳይረመድ በማድረግ ረገድ አንቀው የያዙትን
አመለካከቶች በመድረክ ታግለው ለማስተካከልና ይህንን መሰረት አድርጎ በማህበሩ ዉስጣዊና ዉጫዊ
መነሳሳት በመፍጠር ማህበሩን ወደፊት ለመሳብ ጥረት የሚያደርጉ የስራ አስፈጻሚ አባላት መኖራቸው፤
ማህበራችን በጥሩ የገመገመው ሁኔታ ነው፡፡ ሌላው በጣም ፀጉራቸው ስስ የሆነ እና ሌትና ቀን የማህበሩ ሁኔታ
እያሳሰባቸው በተደራጀ መንገድም ባይሆን ለቢሯቸው ስራ ወደ መስክ ሲሄዱ የማህበሩን ስራም በደረሱበት
አጋጣሚ ደግፈውና አመራር ሰጠው የሚመጡ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መኖራቸው በበጎ መንገድ
የሚወሰድ ተግባር ነው፡፡ በተጨማሪም በማህበሩ የተሰጣቸው ድርብ ተልኮም ቢሆን ፅ/ቤቱ አንዳንድ ወቅታዊና
ጊዜ የማይሰጡ ተግባራት ሲገጥሙት 3 ወሩን ሳይጠብቁ ትርፍ ጊዜያቸውን ጭምር ተጠቅመው በሳል ዉይይት
በማድረግ አቅጣጫዎችን በመስጠት ማህበሩን የሚደግፉበት ሁኔታ መኖሩ አስተማሪነቱ የጎላ ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሰው ጥንካሬ እንደተጠበቀ ሆኖ አገራዊ ብሎም ክልላዊ ፖለቲካዊ ለውጡን ተከትሎ
በሃገራችን የመንግስት፤ የድርጅት እና የተለያዩ ህዝባዊ አደረጃጀቶች አሰራሮቻቸውን ወቅታዊ፤ ለውጡን
ሊመጥን በሚችል መንገድ ለማድረግ መዋቅራዊ ማሻሻያወች፤ የአሰራር፤የአደረጃጀት እና የእስትራቴጅ
ለውጦች እንዲሁም አደረጃጀቶችን እና ለውጡን ሊመጥን በሚችል የሰው ሃይል የማደራጀት ስራዎች
እንዲሰሩ በየጊዜዉ አቅጣጫ እየተቀመጠ የመጣ ቢሆንም ማህበሩ እንደ አንድ የክልል የህዝብ ተቋም ለውጡ
የሚመለከተው እና ወቅታዊ አሰራሮችን በማዘጋጀት የአባሎቹን ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተቋማዊ
አደረጃጀቱ በየጊዜዉ እየተፈተሸ በአዳዲስ አሰራሮች እንዲጠናከር ከማድረግ ይልቅ ማህበሩ ሲመሰረት ጀምሮ
ይዞት በተነሳዉ የአሰራር መመሪያዎች ታጥሮ የዛሬ 21 አመት በነበረ የአስር ስርዓት ዉስጥ እራሱን እያነሳ
እየጣለ ሲሄድ ቆይቶ ከለዉጡ ማግስት ተሸሎ መዉጣት ሲገባዉ እንደገና በኃልዮሽ ጎዳና ራሱን እያራመደ
ይገኛል፡፡ ለዚህ ደግሞ የክልል ስራ አስፈጻሚው ስትራቴጅክ አመራር በመሆን ነባራዊ ሁኔታወችን በመረዳት
እንደ ህዝባዊ አደረጃጀት የተፈጠሩልንን መልካም አጋጣሚወችን ተጠቅሞ ማህበሩን ከልማዳዊ አሰራር
ለማውጣት ህገ ደንቡን አሻሽሎ ወቅታዊ በማድረግ በኩል፤ ለማህበሩ አሰራር የሚያመቹ ልዩ ልዩ የአደረጃጀት
እና የአሰራር መመሪያወችን በማዘጋጀት በኩል፤ ለታችኛው አደረጃጀት ለማጠናከር ድጋፍ እና ክትትል
በማድረግ ሙያተኛዉን ወይም በጎፈቃደኛዉን ሊያነሳሳ የሚችል ስርዓት በመዘርጋት፣ የተጠያቂነት አሰራር
እንዲፈጠር እና ተቋሙ ከነበረበት የ 20 አመት ጉዞ ለውጥ እንዲያሳይ በማድረግ በኩል፡እየተደረገ ያለዉ እገዛ
እዚህ ግባ የሚባል ባለመሆኑ ወደታች ያሉ አደረጃቶችን ለመምራት እና ችግሮችን ለመፍታት በልማዳዊ

3
መንገድ መሄዱ ውጤት አለማስገኘቱ ብቻ ሳይሆን ማህበሩን ከመቸውም ጊዜ በላይ የመፍረስ አደጋ
እንዲጋረጥበት፤ በሌሎች አጋራ እና ባለድርሻ አካላትም የለውጥ ተቋም እንዳልሆነ እየተተቸ አጋዥነት
ሚናቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ አድርጓቸዋል፡፡ እንዲሁም የክልሉ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ስብሰባ ላይ
በመገኘት በየጊዜው የሚያስቀምጣቸውን አቅጣጫወች መልካም ቢሆኑም አቅጣጫ ከመስጠት በተጨማሪ
ስለመፈጸሙን መከታተልና ሳይፈፀም ሲቀር የተጠያቂነት አሰራርን መዘርጋት የሚጠየቅበት አግባብ
አልነበረም፡፡ በመሆኑም በቀጣይ ከዚህ ችግር ለመውጣት የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት ተግባራዊ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡ የማህበሩን ጽ/ቤት የሚመሩ አመራሮች ነጻ ሁነው አሰራሩን በመከተል በራሳቸው እየወሰኑ
እንዲሰሩ በአሰራር መመሪያ ባለመፍቀዱ ወይም ሁሉንም የተቋም ጉዳይ ስራ አስፈጻሚው ሳያውቀው እና
መልካም ፍቃዱ ካልሆነ መስራት አለመቻሉ፤ መገፋፋቶች መኖራቸው፤ በተቋሙ አመራሮች መካከል ግልጽ
የሆነ የሃላፊነት ልዩነት አለመኖር፤ እና የሰው ሃይል ጉድለት ሲኖር ማሟላት አለመቻሉ( ሊ/ር፤ ፋይናንስ
ኃላፊ፤ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ) እንዲሟላ ባለማድረጉ ተቋሙን ከነበረበት ወደ ኋላ እንዲመለስ እና
እንዲቆም አድርጎታል፡፡

በመሆኑም የክልሉ ስራ አስፈጻሚ ከስራ አስፈጻሚው አደረጃጀት ጀምሮ ለማህበሩ እድገት ቅድሚያ
ትኩረት በመስጠት ወቅቱን ሊመጥን የሚችል፤ ከተደራራቢ ሃላፊነት ነጻ የሆኑ፤ የማህበሩን ሃገራዊ እና
አለምአቀፋዊ ግንኙነት ሊያሳድግ የሚችሉ፤ የተቋሙን አፈጻጸም በቅርበት በመከታተል አስተዋጽኦ ሊያደረጉ
የሚችሉ ተጽኖ ፈጣሪ እና ከውክልና ይልቅ ለሴቷ ተጠቃሚነት ቅድሚያ የሚሰጡ እና በዚህ አመለካከት
የተቃኙ እንዲሁም ወደታች ያለውን የማህበሩን አደረጃጀት ተቆራርጦ በተለያዩ ስልቶች ክትትል እና ድጋፍ
በማድረግ አደረጃጀቱን ሊያስተካክል እና ሊያጠናክር የሚችል የለውጥ ሃሳቦችን የሚቀበል ከወቅታዊነት ጋር
አገናዝቦ ተከታትሎ ሊመራ በሚችል መንገድ ተደራጅቶ ማህበሩን ከተቋቋመበት አላማ አንጻር ወደ
ትክክለኛው መስመር በማስገባት ስራ አስፈጻሚው ሓላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል፡፡

1.2.2 የክልሉ ጽ/ቤት ያለበት ሁኔታ

ማህበሩ በበጀት አመቱ ከፍተኛ የሆነ የአመራር ፍልሰት በየጊዜው ያጋጠመው ሲሆን በአዲስ ሃላፊነት እና ውክልና
የተሰጣቸው አመራሮችም ቢሆን ተግባሩን በቶሎ በመላመድ በተሰጣቸው ሃላፊነት ልክ የክልሉን ስራ አስፈጻሚ እና
የተቋሙን አፈጻጸም በየጊዜው እየገመገሙ፤ ችግሮችን እየለዩ ውሳኔ እንዲሰጣቸው በማድረግ በኩል፤ወደታች ላለው
መዋቅራችን አቅም በመሆን በኩል እንዲሁም ወቅታዊ ሁኔታወችን ተረድቶ አጀንዳወችን በየጊዜው እየቀረጹ ለስራ
አስፈጻሚው በማቅረብ ለተቋሙ አደረጃጀት መሻሻሎች የተሰሩ ስራወች የሉም፡፡ እንዲሁም የተቋሙን ሰራቶኞችን ተግባርን
ቆጥሮ ሰጥቶ በመቀበል፤ ሰረተኛው ተነሳሽነትን እንዲፈጥር አቅም በመሆን በኩል፤ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለይቶ
አፈጻጸማቸውን በመገምገም እና በዘርፉ የአባሎቻችን ብሎም የመላ ሴቶች ተጠቃሚነት ምንላይ ነው ብሎ የስራ አካል
በማድረግ በኩል፤ ተቋሙ የተሻለ እውቅና እና የህዝብ ግንኙነት በማህበረሰቡ ብሎም በሚዲያ አካላት በማስተዋወቅ በኩል
በአጠቃላይ በክልሉ ስራአስፈፃሚ ላይ ተፅዕኖ ፈጥሮ አዳዲስ አሰራሮችን ወደ ተቋሙ በማምጣት ለተቋማዊ አደረጃጀት
ለውጥ ከመስራት ይልቅ የተለመደዉን የአሰራር ስርዓት ተከትሎ የመጓዝ እንዲሁም በተለያዩ ቤተሰባዊ ጫናዎቸ ምክንያት

4
በተሟላ ሁኔታ ራስን ወደ ስራ አለማስገባትና ብቁ አመራር አለመስጠት፤ ብሎም የሚገኙ መልካም አጋጣሚዎችን ተጠቅሞ
ለማህበሩ አደረጃጀት መጠናከሪያ አድርጎ ያለመጠቀም /የፌደሬሽን መድረክ/ ችግሮች ገጥመዋል፡፡ ስለሆነም ወደፊት ከላይ
የተዘረዘሩ ችግሮችን ሊፈታ በሚችል መንገድ ተግባራትን ቆጥሮ አመራር በመስጠት፤ ሰራተኛውን ወደ ስራ በማስገባት
ዘመናዊ እና ወቅታዊ አደረጃጀት እና አሰራር እንዲፈጠር በማድረግ ለተሻለ አፈጻጸም መትጋትን ይጠይቃል፡፡

እንዲሁም በክልል ያለው የማህበሩ ፅህፈት ቤት ሞያተኛ ቁጥር አንስተኛና አንድ ሰው ሁለትና ከዛ በላይ
ሃላፊነት በመሸከም ማህበሩ የተቋቋመበትን አላማ ዳር እንዲደርስ በሃላፊነት ስሜት እንዲሰሩ ሆኖ የተደራጀ
ቢሆንም ሃላፊነትን ለመወጣት በተለመደው መንገድ በአለው የአሰራር ማዕቀፍ ውስጥ ሁነው በሚፈለገው
አግባብ ባይሆንም የሚጥሩ ሰራተኞች ያሉ ቢሆንም ፤እንዲሁም ከራስ ተነሳሽነት ችግርም እቅድን አውቆ
በመስራት በኩል ችግር ያለባቸው ሰራተኞች መኖራቸው፤ የጠባቂነት ስሜት መኖር ፣ቢሮ መግባት መውጣትን
እንደ ስራ የሚቆጥሩ፤ከተሰጣቸዉ ሃለፊነት ጋር የማይመጣጠኑ የራሳቸዉን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ የነሱ
ተግባር የሆነዉን ሁሉ በሃላፊ እንዲያልፍ የሚፈልጉ፤ ከሰራተኛ ጋር ተቆራርጦ ተግባር መምራት፤ የማይፈልጉ
ሃላፊነታቸዉን ከፁሁፍ በዘለለ በተግባር የማያዉቁ ሙያተኞችም አሉ፡፡ እንዲሁም አንዳንድ ሰራተኞች ደግሞ
ማህበሩን እንደመቆያ የሚያዩ፣ከስራቸዉ ይልቅ ማህበራዊ ህይወታቸዉ የሚያስጨንቃቸዉና በየጊዜዉ
የተለያዩ ሰበቦች እየፈጠሩ ፈቃድ የመዉጣት፣ የሰራተኛዉ የርስበርስ የመተጋገል ባህል ደካማ መሆን፤ ነገሮች
አይቶ ዝም የማለት አልፎ አልፎም የማህበር ሃብት የሚያባክኑ ሰራተኛ መኖሩ ፣የማህበሩ ኃብት ሲባክን እያዩ
አሰራሩ እንዲስተካከል፤ አለመታገል እና ለተቋም አመራር ጥቆማ የመስጠት ችግር መኖሩ፤ የሚጠበቅባቸውን
ሃላፊነት ሁሉ በተሟላ ሁኔታ የማይወጡ የስራ ክፍል መኖራቸው እና ይህንንም በውጤት እየመዘኑና
እያበረታቱ በትግል ያለመመራት ችግር መኖሩ ተገምግሞዋል፡፡ በመሆኑም በቀጣይ ይህን ችግር የሚቀርፍ
ሰራተኛውን በውጤት የሚለካበትንና ለውጤታማነት አሰራር መርህ እና ተጠያቂነት ስራት በመዘርጋት
ጠንካሮች የበለጠ የሚበረታቱበትን ደካሞች ደግም ወደ ጠንካሮች አፈጻጸም የሚመጡበትን የጽ/ቤት
ሃላፊወች አመራር የመስጠት ተልኮን በአግባቡ መወጣት ይኖርብናል፡፡

1.2.3 የዞን ስራ አስፈጻሚያችን ያለበት ሁኔታ

የዞን ስራ አስፈጻሚያችን በአብዛኛው ያልተሟላ ሲሆን በቁጥር ደረጃ የተሟላ ስራ አስፈጻሚ ያላቸውም
ቢሆኑም እነ ምስራቅ ጎጃም፤ ምዕ/ጎጃም፤ አዊ፤ ባህርዳር ከተማ ፤ማዕከላዊ ጎንደር፤ኦሮሞ ዞኖች በአግባቡ
ሃላፊነትን ለመወጣት የሚያደርጉት ጥረት በተለያዩ ሰበቦች ምክንያት(ማለትም ተደራራቢ ሃላፊነት አለብን
በማለት፤ ጠባቂነት በመኖሩ) የተሰጣቸውን ሃላፊነት በመወጣት በኩል ከፍተኛ ችግሮች ይታያሉ፡፡ እንዲሁም
ደቡብ ጎንደር ዞን ከአንድ አመት በላይ ስራ አስፈጻሚ የሌለው፤ ደቡብ ወሎ ዞን በቁጥር ደረጃ የተሟሉ
ቢሆኑም ሁለቱ ስራ አስፈጻሚወች ስራውን በስልክ ካልሆነ በአካል ተገኝተን ለመገምገምም ይሁን ለመደገፍ
ካለን የመደበኛ ስራ ጫና አንጻር አንገኝም በማለት በሙሉ አቅም ወደ ስራ አለመገባቱ፤ደሴ ከተማ፤ ሰ/ሸዋ
ዞን፤ ሰሜን ወሎ ዞን አንድ እና ሁለት ስራ አስፈጻሚ ይዞ ለማሟላትም ፈጥኖ ወደ ስራ በመግባት በኩል በዞኑ

5
በእራሱም እንዲሁም በክልሉ በኩልም ችግር መኖሩ፤ከስራ ውጭ ሁነው ቆይተዋል፡፡ ዋግ ልዩ ዞን ለድጋፍ ሲኬድ
ለቀናል አንሰራም ማለት በተለያዩ መድረኮች ግን ማህበሩን ወክሎ መገኘት/በአመለካከት የተሟሉ አለመሆን፤
ስራው እየተሰራ ያለው በሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ተቋም ብቻ መሆኑ፤ ጎንደር ከተማ ማህበሩ ሙሉ በሙሉ
የፈረሰ መሆኑ እና አዳዲስ ዞኖች በራሳቸው አደረጃጀት እየሰሩ ያለ ቢሆንም ተቋሙን ከማደራጀት እና
እውቅና ከመስጠት አንጻር የክልሉ ጽ/ቤት ቀርቦ ያላገዛቸው በመሆኑ በሚፈለገው አግባብ እየሰሩ አይደለም፡፡
እንዲሁም የሁሉም ዞኖች ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊወች በተቋማችን አማካኝነት ከማህበሩ እገዛ
እራሳችሁን አስወጡ ተብለናል በማለት የተቋቋሙበትን አደረጃጀቶችን የመፍጠር እና የማቋቋም እና
የመደገፍ አላማ ወደ ጎን በመተው ጣልቃ አትግቡ ተብሎ በመድረክ የተግባባንበትን አትድረሱ ተብለናል
በማለት የአጋዥነት ሚናን በአግባቡ የመወጣት ችግሮች ስላሉ የክልሉ ስራ አስፈጻሚ እና ተቋሙ ከቢሮው ጋር
በመሆን ችግሮችን መፍታት እና የተሳሳተውን ግንዛቤ በማስተካከል የአጋዥነት ሚናቸውን እንዲወጡ ማድረግ
ይኖርብናል፡፡

እንዲሁም ለአስተባባሪወች የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እና ክትትል አለማድረግ እና የታችኛው መዋቅር


አለማጠናከር፤የማህበሩን የፋይናንስ እንቅስቃሴወችን አለመከታተል፤ ተጠያቂነት ያለው አሰራር እንዲሰፍን
በማድረግ በኩል ከፍተኛ ችግሮች መኖራቸው እና አጠቃላይ የማህበሩን እንቅስቃሴ በየደረጀው በእውቀት
እንዲመራ በማድረግ በኩል ሰፊ ውስንነቶች ይታያሉ፡፡

በመሆኑም በአጠቃላይ የሁሉም ዞኖች ስራ አስፈጻሚወች ያልተሟሉ እና ወደ ስራ ያልገቡ ወደታች ያለውን


መዋቅራቸውን በማገዝ በኩል ከፍተኛ ችግር ያለባቸው በመሆኑ የክልሉ ጽ/ቤት እንዲሁም የክልሉ ስራ
አስፈጻሚ አስቸኳይ ውሳኔ በመስጠት አደረጃጀቶችን ፈትሾ ማስተካከያ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

1.2.4 በየደረጃዉ የሚገኘው የአማራ ሴቶች ምክር ቤት ያለበት ሁኔታ፡-

ምክርቤቱ ከጉባኤተኛው ቀጥሎ የተቋሙ የበላይ አመራር ሆኖ የተደራጀ ነው፡፡ አገራችን እየገነባች ባለችው
የዴሞክራሲ ስርኣት ሲቪክ ማህበራት ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡ የማህበራችን አባላት በራሳቸው ማህበር
ዉስጥም ሆነ በአስፈጻሚዊ ተቋም የሚታዩ አሉታዊ አሰራሮችን ታግለዉ ለማስተካከል እንዲሁም የሴቶችን
ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መልካም ጅምሮችን ለይተው በማዉጣት መላ አባላት ከመንግስት ጎን
በመሆን ደጋፊነት ሚናዉን እንዲወጡ ለማድረግ ሴቶች በፆታቸው ተደራጅተው በራሳቸው ጉዳይ ላይ ነፃ
ሆነው እንዲወያዩ የሚያደርግና መንግስት የሴቶችን የተደራጀ ተሳትፎ ለማረጋገጥ እንዲችል ምቹ
አደረጃጀት በመሆን የሚያገለግል ነው፡፡ ከዚህ ተግባርና ሃላፊነቱ በመነሳት ምክር ቤቱን ስናይ አንጻራዊ
በሆነ መንገድ የክልል ምክር ቤቱ 6 ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ተከትሎ የሁሉም ዞኖች ዉክልናን
ባረጋገጠ መንገድ የተዋቀረ ከመሆኑም በተጨማሪ ከተዋቀረ 4 ጊዜ የክልሉን ሪፖርት ገምግሞ የተጓደሉ

6
አመራሮችን አሟልቷል፣የቀረቡ አጀንዳወችንም ተዎያይቶ ከማጽደቅ ጀምሮ በውይይቱ ተሳትፎ ተገቢ
ማደማደሚያ ላይ እንዲደረስ አድርጓል፡፡

ኪህም በተጨማሪ ልክ እንደ ክልሉ ሁሉ በወረዳና በቀበሌም ምክርቤቶቻችን መደራጀታቸውና በውስን


ወረዳወች ለምሳሌ ደንበጫ ወረዳ ምክር ቤቱ የተቀመጠውን አሰራር በመከተልና ተግባርና ሃላፊነቱን
ለመወጣት ዉይይት ማድረጋቸው በጥሩ መንገድ የሚገለፅ ተግባር ነው፡፡ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከምክር
ቤቱ ተግባርና ሃላፊነት በመነሳት ሁሉንም ምክርቤቶቻችንን ስንመለከት ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡
ከምክር ቤት አባላት መረጣ ብንነሳ በአግባቡ የሴቶችን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ ታታሪና
ሞጋች ሴቶችን አብሮ በማደራጀት በኩል ሰፊ ችግር ያለበት ነው፡፡ በተጨማሪ ይህንን ምክርቤት
እንዲያስተባብሩ ሃላፊነት የተሰጣቸው አካላትም በተቀመጠው አሰራር መሰረት አጀንዳ እየቀረጹ
አለማወያየት፣ የማህበሩ ምክር ቤት ከመንግስት ምክር ቤት ለይተው የማያውቁ በተለይ በቀበሌ ደረጃ
ማህበሩ ምክር ቤት ስለመኖሩ የግልጽነት ችግር በአብዛኛው የሚስተዋል ችግር ነው፡፡ እንዲሁሙ
የምክር ቤት አባላት ተለይተው የማይታወቁበትና የአባላት መረጃም በሰነድ ያልተያዘበት ሁኔታ አለ፡፡
የምክር ቤት አባላትም አብዛኛዎቹ ይህንን አሰራር ባለመገንዘባቸውና የተገነዘቡትም ሞጋቾች ስላልሆኑ
አመራሮች ሲደክሙ የሚደክም በአመራሮች ጥንካሬና ድክመት ላይ ብቻ የተንተለጠለ ምክር ቤት ሆኖ
እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡የክልል ምክር ቤት አባላት ሲዋቀሩ ታሳቢ ያደረገው አካባቢያቸውን እንዲዎክሉና
የተፈጠረላቸውን ግንዛቤ መሰረት አድርገው በአሉበት አካባቢ ማህበሩን ከማጠናከር አኳያ አቅም
እንዲሆኑ ታስቦ ቢሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች እንደምናየው ምክር ቤት አባላት ሚናቸው ክልሉ
ስብሰባ ሲጠራ ብቻ ተገኝተው ጉባኤው እንዲካሄድ ከሰው አኳያ መሟላት ያለበት ቁጥር እንዲሟላ
ማድረግ ላይ ብቻ የተመሰረቱ ሁነዋል፡፡

1.2.5 የመላው አባላችን ሁኔታ

የማህበራችን አባላት ቁጥራቸው 1.76 ሚሊየን የሚሆን ሲሆን በመደራጀት እድሜ ክልል ውስጥ
ከሚገኙት 3 ሚሊየን ሴቶች አኳያ ሲነጻፀር 58% የሚሆኑት ሴቶች በአማራ ሴቶች ማህበር የተደራጁ
ሲሆን ከቁጥር አኳያ አብዛኞቹ የማህበሩ አባላት ለማድረግ መሰራት ቢኖርበትም አሁን ያላቸው
ሽፋንም በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡እኒህ አባላት ስማቸው የተደራጁ ቢያስብላቸውም አብኛዎቹ
አባላት ሲደራጁ በቂ ግንዛቤ እየተፈጠረላቸው ወደውና ፈቅደው አባል እንዲሆኑ ያልተደረገበትና
ስለተደራጁበት ማህበር እዉቅና የሌላቸው ጠንከር ያሉትን መርጦ ሲፈለግ በወቅቱ ለተፈለገው
አደረጃጀት ወካይ ተደርገው የሚወሰዱና ከሞቀው አብረው የሚዘፍኑ አባላት ናቸው፡፡ ይህ በእንዲህ
እያለ መንግስት በሚጠራቸው የልማት ጥሪዎችም ሆነ ግንዛቤ ለመፍጠር መድረኮችን ሲያመቻች
በእኒህ ጥሪዎች በመገኘት፣ በመሳተፍ ራስንም ሆነ ቤተሰብን ለመጥቀም ከመሞከር ይልቅ አደባባይ
7
የሚወጡ ሴቶች ትዳር የሌላችው አለፎም የገቢ ምንጭ የሌላቸው ሴቶች ብቻ የሚደራጁበት
እንደሆኑ ለራስ በመንገር ቤት መቀመጠና ችግር ሲደርስ ብቻ ያዉም ነገሩ ካለቀና ከተበላሸ በኋላ
በስሚ ስሚ ወደማህበሩ ሲመጡ ይታያል፡፡ ስለዚህ አባላት ተደራጅተው ፀረ ዲሞክራሲያዊ አሰራርን
ይታገላሉ ለሌሎች ላልተደራጁ ሴቶችም ብርሃን ይሆናሉ ተብሎ ታስቦ እንዲደራጁ ቢደረግም
አይደለም ለሌሎች ለራሳቸውም ያልሆኑበትን ሁኔታ ከሚገጥሙን ጉዳዮች እና በአጠቃላይ
ከምናስተዉለው የማህበሩ እንቅስቃሴ መረዳት ችለናል፡፡

በተጨባጭ ያለንን የአባል ቁጥር ለማረጋገጥ መረጃዉ በተደራጀ መንገድ በሃርድና ሶፍት ኮፒ በክልል
ደረጃ እንዲኖርንና በየጊዜው እየታደሰ እንዲላክልን ዞን ላሉ የማህበሩ ፅ/ቤት አስተባባሪዎች ብንልክም
እስካሁን አንድም ዞን ይህንን መረጃ ሰርቶ መላክ አልቻለም፡፡ ከዚህ መረዳት የምንችለው በቁጥር
ደረጃ አሉ ተብለው የሚላኩልንን አባላት በዉል ለይተን የማናዉቃቸውና አንዴ ያፈራናቸው አባላት
በተለያየ ችግር ክፍያ ሲያቋርጡ ያጋጠማቸውን ችግር ተከታትሎ ፈቶ አባልነታቸው እንዲቀጥል
ከማድረግ ይልቅ ቀጣይነት የሌላቸውን በአጋጣሚ በሆነ መድረክ ያገኘናቸውን ሴቶች ብቻ አባል
ዕያደረጉ የመሄድ ሁኔታ በማህበራችን ውስጥ ያለ ግን ደግሞ ትክክለኛ ያልሆነ አሰራር ነው፡፡ኪህ
በተጨማሪ አንዳንድ አባላትን አባል ለማድረግ ያልተገባ ቃል ስለምንገባላቸው አባል በሆኑ ማግስት
ማህበሩ ከአቅም አኳያ በአጭር ግዜ ሊመልስ የማይችላቸውን ጥያቄወች እንዲወጠርና ሌሎችም
አባላት በዚህ ሁኔታ ተወዛግበው ከማህበሩ ሲወጡ ይስተዋላል፡፡

1.2.6 የዞን ጽ/ቤት አስተባባሪወች ያሉበት ሁኔታ

በዞን ደረጃ ያሉ የጽ/ቤት አስተባባሪዎች የዞኑን ስራ አስፈፃሚ ሊያሠራ የሚችል አጀንዳ ቀርፆ
የዉይይት መድረክ በማዘጋጀትና በማስተባበር እንዲሁም በስራቸው ለሚገኙ ወረዳዎች ከእቅድ ዝግጅት
ጀምሮ ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ወረዳዎች ወደ ተመሳሳይ አፈጻጸም እንዲመጡ እና አባላትን ተሳታፊ እና
ተጠቃሚ እንዲሆኑ በአሰራሩ ዙሪያ እራስ ግልጽ በመሆን ተልዕኮውን በመረዳት ሌሎችን በማስተባበር በኩል
አፈጻጸማቸው የሁሉም ዞኖች እየወረደ የመጣ እና በአብዛኛው ችግሮችን ከወቅታዊ ሁኔታው ጋር የማያያዝ
እና ፈጥኖ ለማሻሻል እና አፈጻጸማችንን ለማሳደግ የሚደረጉ እንቅስቃሴወች ባለመኖራቸው አስተባባሪወች
ባሉበት እና በሌሉበት ዞኖች ልዩነት እስከአለመኖር ድረስ ታይተዋል፡፡

እንዲሁም ሁሉም አስተባባሪወቹ የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናወች፤ ማበረታቻወች፤ አዳዲስ አሰራሮች
ስላልፈጠሩላቸው፤ ስራ አስፈጻሚውም ውክልናውን በአግባቡ ስለማይወጣ፤ለአስተባባሪወች አቅም የሚሆን
ድጋፍ ስለማያደርግ፤ በአብዛኛው ስራ አስፈጻሚ ኃላፊነትን አስተባባሪወችን መገምገም ላይ ብቻ በማተኮር፤
የአመለካከት እና የቁርጠኝነት ችግር በመኖሩ እና በክልል ተቋሙ ጠያቂነት፤ በቂ ድጋፍ እና ክትትል አለመኖሩ
አስተባባሪወች በሚፈለገው መንገድ እየሰሩ አይደለም፡፡ እንዲሁም (ደቡብ ጎንደር፤ማዕከላዊ ጎንደር፤ደሴ
8
ከተማ፤ኦሮሞ ዞን፤ ምዕራብ ጎጃም፤ባህርዳር ከተማ) በእራሳቸውም የአቅም ችግር የማህበሩን ራዕይና ተልእኮ
ተረድተዉ፤ የማይንቀሳቀሱ፣ መረጃ በወቅቱ የማይለዋወጡ ማህበሩን እንደመቆያ/አማራጭ/ማፈላለጊያ
አድርገዉ የሚመለከቱ፣በስራ ገበታቸዉ ላይ የማይገኙ፣ የወረዳ አስተባባሪወችን የማይከታተሉ እና ወደ ስራ
ማስገባት ያልቻሉ፤ (በወረዳ ደረጃ አስተባባሪ በተመደበበት እና ባልተመደበበት ያለውን ልዩነት መመዘን
ያልቻሉ) በተገቢዉ የማይመሩ፣ለትግል ምቹ ያልሆኑ፣ በየጊዜዉ የሚላኩ
እቅዶች፣ግብረመልሶች፣ቸክሊስቶችን የስራ መመሪያ የማያደርጉ፣በተለያዩ መድረኮች የሚያገኙዋቸውን ግባት
እንደ አቅም ማጎልበቻ አለመጠቀም፤ በተለያዩ መድረኮች ሌሎች ስራ አስፈጻሚወችን የማሳተፍ ችግር፤
ተልኮን በአግባቡ አለመውስድ እና ያለመረዳት ችግሮች፤ የተጠያቂነት ስርዓት የለም ብሎ በማሰብ መረጃ
ሲጠየቁ እና ሪፖርት በወቅቱ አለመላክ፤ የማህበሩን መሰረታዊ መረጃወች አሟልቶ ያለመያዝ፤ የአባላትን
መረጃ በአግባቡ በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ የማይዙ፤ የጽ/ቤቱን አደረጃጀት መረጃ በተሟላ አግባብ የማይዙ፤
ለስራ አስፈጻሚወች የበሰለ አጀንዳ ቀርጾ በማቅረብ ችግሮች እንዲፈቱ ከማስተባበር ይልቅ ይሄን ሳይሰሩ፤ ስራ
አስፈጻሚው እያገዘን አይደለም ብሎ በማማረር ብቻ መቆየት የሚፈልጉ፤ ብቻን ሲሆኑ ስራ አስፈጻሚውን
አያግዘንም ብለው የሚኮንኑ በጋራ ሲሆኑ ደግሞ የማይታገሉ፤ የጠባቂነት ስሜት ያለባቸዉ፤ የማህበሩን ሚና
ሊያጎላና ማህበሩን በላቀ ደረጃ ሊሸጥ በሚችል አግባብ የማይንቀሳቀሱ ይልቁንም ሁሌም ስራ አስፈፃሚዉ
አያግዘንም እንዲሁም የሚከፈለን ደመወዝ ትንሽ ነዉ ብሎ የሚቆዝሙ መኖራቸው ተገምግሟል፡፡
እንዲሁም በዚህ ችግር ውስጥም ቢሆን ሁና ስራ አስፈጻሚውን ወደ አንድ አምጥታ በሙሉ አቅም መስራት
ባትችልም እንኳ በራሷ ጥረት ተግባራት በመፈጸም እና ወረዳወች በማስተባበር በኩል የደቡብ ወሎ ዞን
አስተባባሪ የተሻለ እየተንቀሳቀሰች ያለች ሲሆን የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተባባሪ የአቅም ችግር ባይኖርም
በቁርጠኝነት ማነስ፤ ሆን ብሎ ስራወችን በመተው እየሰራች እንዳለሆነ ተገምግሟል፡፡ ቀሪወቹ ዞኖች ግን
አስተባባሪ ስላልነበራቸው መረጃ መለዋወጥም በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ ጽ/ቤቱ ተከታትሎ እንዲቀጠሩ
ማድረግ ይኖርበታል፡፡

2. የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም

ግብ.1. በየደረጃው ያሉትን የማህበሩን አመራሮች የመፈጸም ብቃት 50% ማሳደግ

የማህበሩ ዋናው ቁልፍ ተግባር ጠንካራ የሆነ መዋቅራዊ አደረጃጀት መፍጠር ሲሆን የማህበሩን አደረጃጀት እና
አሰራር በማጠናከር ጠንካራ የሆነ መዋቅራዊ ተቋም በመፍጠር መፈጸም የሚችሉ አመራሮችን ማብቃት
በየደረጃው ትኩረት ተሰጥቶት የሚከናወን ተግባር ነው፡፡

በመሆኑም በየደረጃው የሚገኙትን አመራሮች የመፈጸም ብቃት ለማሳደግ ከእቅድ ዝግጅት እና ፈጻሚን
ከማዘጋጀት ተግባሮቻችን ጀምሮ ተሳታፊ በማድረግ እና አመራሩ እቅዱን በባለቤትነት አውቆ እና የስራ
መመሪያ አድርጎት በእምነት እንዲይዘው ማድረግ የመጀመሪያው እና ዋናው ተግባር ይሆናል፡፡ ይሄን ግብ
ለማሳካትም በበጀት አመቱ ለማከናወን ካቀድናቸው ዝርዝር ተግባራት ውስጥ፤ እንደ ክልል የ 2010 በጀት

9
አመትን አፈጻጸም በመገምገም የ 2011 ዓ/ም ክልላዊ የሆነ እቅድ በማዘጋጀት እስከታች ድረስ ፈጻሚወቻችን
በማዘጋጀት አጠቃላይ እውቅናቸውን በመጨመር የመፈጸም አቅማቸውን ማሳደግ ግብ ተጥሎ እየተሰራ
ሲሆን በአጠቃላይ እቅዱን ለ 12 ዞኖች፤ለ 3 ከተማ አስተዳደሮች፤ለ 184 ወረዳወች፤ ለ 3494 ቀበሌወች፤
ለአዲስ አበባ ከተማ፤ እና በየደረጃው ለሚገኙ መላ አባሎቻችን፤ለ 3494 የግብርና እና
የቴ/ሙ/ባለሙያወች፤ለ 3494 የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያወች፤ለ 3494 የቀበሌ ስራ አስኪያጅ እና
ሊቀመንበሮችን በብቃት በማሳተፍ በቁልፍ እና አባይ በአጠቃላይ 10,482 አስፈጻሚወችን የመፈጸም
አቅማቸውን ለማሳደግ እና በ 184 ወረዳወች እቅድ ኦሬንቴሽን ለመስጠት ታቅዶ፤

እንደ ክልል ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታውን መነሻ ያደረገ፤ ያሉንን ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮችን የቀደምት
አፈጻጸም እና የተፈጥሮ ጸጋቸውን መነሻ ያደረገ፤ሊፈጸም እና ሊለካ የሚችል እቅድ በማዘጋጀት ለሁሉም
ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች ኦሬንቴሽን በመስጠት፤ ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮችም የክልሉን እቅድ
በመነሻነት በመውሰድ የየራሳቸውን እቅድ እነዲያዘጋጁ በቅርበት በመደገፍ፡ የተሰራ ሲሆን ዞኖችም ይሄን
ተግባራዊ በማድረግ፤ ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ ፤ ምስራቅ ጎጃም ዞን በ 19 ወረዳወች፤ ምዕራብ ጎጃም ዞን
በሁሉም ወረዳወች፤ አዊ ዞን በ 10 ወረዳወች፤ ባህርዳር ከተማ በከተማ አስተዳደር ደረጃ፤ ደቡብ ጎንደር ዞን
በ 6 ወረዳወች፤ ማዕከላዊ ጎንደር በ 7 ወረዳወች ፤ ደቡብ ወሎ ዞን በ 17 ወረዳወች፤ ደሴ ከተማ በ 5 ቱም
ክፍለከተማ ደረጃ ኦሮሞ ዞን በ 2 ወረዳወች እና ዋግ በ 8 ወረዳወች በአጠቃላይ በ 97 (52%) ከሴቶች እና
ህጻናት ጋር በጋራ፡ 84 የዞን አመራሮች በዞን ደረጃ፤234 የወረዳ አመራሮች ዞን ላይ በመገኘት 1011 የቀበሌ ስራ
አስፈጻሚወች ወረዳ ላይ በመገኘት እና 1617 የቀበሌ አስተዳደር እና ስራ አስኪያጆች 1971 የግብርናና
ቴ/ሙ/አደራጅ ባለሙያወች፤እና 2107 ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያወች እና አመራሮች በአጠቃላይ 7024
(67%) አስፈጻሚወች በእቅድ ኦሬንቴሽን እንዲሳተፉ ተድርጓል፡፡

የእቅድ ዝግጅት ስራችን ከክልል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ አካባቢያዊ የሆነ እቅድ የማዘጋጀት ክህሎታችን ከጊዜ
ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ቢሆንም በእቅድ ዝግጅታችን ልክ ፈጻሚ አካሉ በአግባቡ አውቆት እና የስራ
መመሪያው አድርጎ እንዲጠቀምበት በማድረግ በኩል፤ ሁሉም ባለድርሻ እና አጋራ አካሎቻችን በኦሬንቴሽኑ
እንዲሳተፉበት በማድረግ በኩል አሁንም ቢሆን ከፍተኛ እና ያልተሸገርነው ችግር ነው፡፡ በዞን ደረጃ በቅድመ
ዝግጅት ስራችን በሁሉም ዞኖች ባለው ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ የእቅድ ትውውቁን በአግባቡ መስጠት
አልተቻለም፡፡ በአንጻራዊነት ደቡብ ወሎ፤ ምስረቅ ጎጃም፤ ደቡብ ጎንደር፤ ምዕራብ ጎጃም፤ አዊ እና ባህር ዳር
ከተማ አስተዳደር ኦሬንቴሽኑን በዞን ደረጃ እራሱን አስችለው እቅድ ኦሬንቴሽን የሰጡ ሲሆን ዞን በተግባቡበት
ደረጃ ግን እስከ ታች ድረስ ኦሬንቴሽኑን ማስኬድ አልተቻለም፡፡ እንዲሁም የእቅድ ኦሬንቴሽኑ በዚህ አግባብ
ተሰጠ ቢባልም ተግባባን በተባለው ልክ የአብይ ተግባራት አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆኑ በቅድመ ዝግጅት ላይ
ትኩረት ተሰጥቶ መግባባት ላይ አለመደረሱን ያሳያል፡፡ ቀሪ ዞኖች ግን በተለመደው አግባብ የእቅድ ትውውቁ
ከሴ/ህ/ወ/ጉ ጋር በቅንጅት ተሰጠ ቢባልም እንደ አጠቃላይ የቅድመ ዝግጅት ስራችን የተንጠባጠበ እና

10
ውጤታማ ያልነበረ መሆኑ እንደማሳያ የሌሎች ተግባሮቻችን የአፈጻጸም ዝቅተኝነት መኖሩ እና በቅድመ
ዝግጅት ወቅት መከናወን የነበረበት የአባላት ገቢ አሰባሰብ ስራችን አሁን ላይም ዝቅተኛ መሆኑ ማሳያ ነው፡፡

ግብ፡2. 75% የማህበሩን አባላት በተልኮወቻቸው ላይ ያላቸውን ግልጸኝነት ማሳደግ

እንደሚታወቀው በበጀት አመቱ ማንኛዋም አባል እና በየደረጃው የሚገኘው ስራ አስፈጻሚ በማህበሩ


አደረጃጀትና ተልኮ ዙሪያ ግልጸኝነት ለመፍጠር ልዩ ትኩረት በመስጠት ታቅዶ እየተሰራ ያለ ተግባር ነዉ፡፡
በአብዛኛው የቀበሌ፤ የወረዳ እና የዞን ስራ አስፈጻሚወች ከመንግስት ሃላፊነት ጋር ተደረበው የተያዙ ስለነበሩ፤
በወቅታዊ ሁኔታው ምክንያት የመንግስት ኃላፊነታቸውን በተለያየ ምክንያት ሲለቁ፤ የማህበሩን ኃላፊነትም
ጭምር ሰለለቀቁ በየደረጃው ያለው የማህበሩ አመራሮች ከመቸውም ጊዜ በላይ በአዲስ ስራ አስፈጻሚወች
የተደራጁበት ጊዜ ነው፡፡ ስለሆነም በክልል በአጠቃላይ የማህበሩ ተግባራት ዙሪያ ቸክ ሊስት በማዘጋጀት በዞን
ደረጃ፤ ለምዕ/ጎጃም፤ ለምስራቅ ጎጃም፤ ለአዊ ብሄረሰብ ዞን፤ ለባህርዳር ከተማ፤ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን፤
ለደ/ጎንደር ዞን፤ ለሰ/ሸዋ ዞን፤ለዋግ፤ ለኦሮሞ ዞን፤ለደሴ ከተማ አስተዳደር እና ለደቡብ ወሎ ዞን፤ እንዲሁም
በወረዳ ደረጃ ለደላንታ፤ወረባቦ፤ደሴ ዙሪያ፤ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ፤ ሸዋ ሮቢት፤ ምንጃር ሸንኮራ፤ ሞረት
እና ጅሩ፤ ሃብሩ፤ መርሳ ከተማ ደብረ ብርሃን ከተማ፤ ወልደያ ከተማ፤ ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ እና ሰቆጣ ከተማ
አስተዳደር ፤ ቆቦ ከተማ አስተዳደር፤ እና ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ከቀበሌ ጀምሮ አጠቃላይ ለስራ
አስፈጻሚወች እና ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ በተለኮው ዙሪያ ግልጸኝነት ለመፍጠር
የተሞከረ ሲሆን ዞኖች ግን ሌሎች ቀሪ በአዲስ የተደራጁ ወረዳወችን ወርዶ ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ በኩል
ከፍተኛ ክፍተት መኖሩን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ይሁን እንጅ ከእቅዳችን አንጻር የአባሎቻችንን ግንዛቤ ለማሳደግ
አሁንም ቢሆን ያልተሰሩ ስራወች በመኖራቸው አላማውን በሚፈለገው መንገድ ማስረጽ አልተቻለም፤
በመሆኑም የማህበሩ አባል የሆኑ እና ያልሆኑትን ሴቶች በልማት ቡድን አማካኝነት መረጃ ለይቶ በመያዝ፤
መረጃውን በሃርድ እና በሶፍት ኮፒ በሚፈለገው መነገድ በመያዝ በኩል፤ መላ አባላትን በአደረጃጀታቸው
አማካኝነት ስለማህበሩ አላማ፤ህገ ደንብ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞችን ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራወች፤ተሞክሮን
የማለዋወጥ ስራወች በአብዛኛው ዞኖቻ ያልተከናወኑ ሲሆን እስከዚህ ሩብ አመት 1‚300,000 አባሎቻችን
ግንዛቤ ለመፍጠር ታቅዶ ግንዛቤ የተፈጠረላቸው 675,000 ሴቶች አፈጻጸሙም(52%) ብቻ ናቸው፡፡ በዚህም
የተሸለ አፈጻጸም ያላቸው ዞኖች ከሪፖርታቸው በመነሳት ሰ/ሸዋ፤ ምዕራብ ጎጃም፤ ደሴ ከተማ አስተዳደር፤
ምስራቅ ጎጃም ሲሆን ተፈጠረ የተባለው ግንዛቤና የዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም ተቃርኖ ያለውና በተጨባጭ
ውጤት ያልተረጋገጠ ከመሆን አልዘለለም፡፡ ለምሳሌ የአባልነት ክፍያን አውቆ በመክፈል በኩል ግንዛቤ ፈጠርን
ያሉ ዞኖች የግማሽ አመቱ አፈጻጸም ዝቅተኛ ነው፡፡ በመሆኑም የግንዛቤ ፈጠራ ስራው ታርጌትን ያለየ፤
በአግባቡ ያልተሰጠ እና ግንዛቤ በተፈጠረላቸውና ባልተፈጠረላቸው መካከል ምንም አይነት ልዩነት መፍጠር
ያልቻለ በመሆኑ የሪፖርቱን ታማኒነት የሚያጠራጥረው ይሆናል፡፡ እንዲሁም የአባላትን መረጃ በዞን ደረጃ
በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ በማዘጋጀት በየልማት ቡድኑ አባል የሆኑ እና አባል ያልሆኑትን በመለየት መረጃውን
በየጊዜው ወቅታዊ በማድረግ ለክልሉ ጽ/ቤት መላክ እንዳለበት ባለፉት አመታት ጀምሮ መግባባት ላይ
11
የተደረሰና ተግባሩ የእቅድ አካል ሆኖ የወረደ ቢሆንም፤ በተደረገው ድጋፍ እና ክትትል መሰረት አንድም ዞን
የተሟላ እና በስሩ ያሉትን ሁሉንም ወረዳወች ያካተተ በሶፍት ኮፒ የተጠናከረ መረጃ ያለው ዞን አለመኖር እና
በእጅ ጹሁፍ (በሃርድ ኮፒ) የመጣውን ዝርዝር እንኳ ወደፊት ወደ ሶፍት ኮፒ ልንቀይረው አንችለም ብሎ
በአመለካከት የያዙ ዞኖች(ደቡብ ወሎ፤ ምስራቅ ጎጃም፤ አዊ፤ ምዕራብጎጃም፤ማዕከላዊ ጎንደር) መኖራቸው
ትክክል ስላልሆነ ወደፊት ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ አመለካከቱን አስተካክሎ ወደ ስራው ማስገባት
ይኖርብናል፡፡ስለሆነም ቁጥር ላይ ብቻ በመንጠልጠል በየአመቱ በሪፖርት ብቻ የሚገለጸው የአባላት መረጃ
በተጨባጭ በእጃችን ያሉትን አባላት ጥርት አድርገን እንድናዉቃቸው የማያደርግና ቁጥር ላይ ብቻ
የተንጠለጠለ በመሆኑ በስም ዝርዝር ተለይቶ በየግዜው እየተገናዘበ እስካልሄደ ድረስ ታማኒነቱ አጠያያቂና ወደ
ስህተት የሚወስድ ስለሆነ ወደፊት ከችግሩ ለመውጣት ትኩረት መስጠትና የመፍትሄ እርምጃ በመውሰድ
መስተካከል ያለበት ተግባር ነው፡፡

የመንግስት ሰራተኛ እና ሙህራን አባላትን ለማፍራት በተለይም የክልል ተቋማትን ትኩረት በመስጠት የ 53 ቢሮ
እና ሌሎች ተቋማትን ስርአት ጾታ ባለሙያወች እና ፎካል ፐርሰኖች መረጃ በመለየት ስለማህበሩ የግንዛቤ
ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ማህበሩን የማስተዋወቅ እንዲሁም በየቢሯቸው ያሉ ሴት የምንግስት
ሰራተኞችን አጠቃላይ ፕሮፋይል እንዲልኩልን ተልኮ የሰጠን ሲሆን ከነዚህ ተቋማት ውስጥ ለሰባት (ሲቪል
ሰርቪስ ኮሚሽን፤ማረሚያቤቶች ኮሚሽን፤ ቴክኒክ እና ሙያ ቢሮ፤ንግድ ቢሮ፤አብቁተ፤ ፍትህ ማሰልጠኛ እና
ገጠር መንገድ ቢሮ) ተቋማት ደግሞ ለብቻ እራሳቸው ተቋሞቹ ባዘጋጁት መድረክ ባለሙያ በመመደብ ስልጠና
በመስጠት ወደ አደረጃጀቱ እንዲገቡ ለማድረግ ሰፊ ስራ እየተሰራ ያለ ሲሆን ሁሉም ቢሮወች ተቋሙ እየሄደ
ግንዛቤ እንዲፈጥርላቸው ፍላጎት ስላለ ስራ አስፈጻሚውም ቢያንስ ባለበት ቢሮ እና በሌሎች መድረኮችም
ለሙህራኑ ግንዛቤ ለመፍጠር እገዛ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ 15 ቢሮወች እና ተቋማት ደግሞ በተሰጣቸው ተልኮ
መሰረት የሴት ሰራተኞቻቸውን ፕሮፋይል በተላለፈላቸው ፎርም መሰረት ሞልተው አሳውቀውናል፡፡ በዚህ
ሂደትም ማህበሩ ከሙህራን አባላት ጋር ቀርቦ መወያየት በመቻሉ እስካሁን የነበረው የሙህራን ተሳትፎ
ክፍተት ማህበሩ ተቀራርቦ ባለመስራቱ የመጣ እንጅ ሙህራን ተደራጅተው ለመሳተፍ እና ለማገልገል
ያላቸውን ተነሳሽነት ያየንበት፤ የቢሮ ሃላፊወች ሙህራኑ በጾታቸው እንዲደራጁ ድጋፍ የሚያደርጉ እና ምቹ
ሁኔታ እንዲፈጠር እገዛ እንደሚያደርጉ ትምህረት ተወስዶበታል፡፡ ይሁን እንጅ አሁንም ቢሆን በቢሮ ደረጃ ያሉ
ሴት የመንግስት ሰራተኞችን ወደ አደረጃጀቱ ለማምጣት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ያለ ቢሆንም ሴቶቹን
በየትኛው መዋቅር አባል አድርጎ ማለትም(በቀበሌ፤በዞን፤በከተማ አስተዳደር፤ በክልል ደረጃ ወይስ
በተቋማቸው ውስጥ) አደረጃጀት ይፈጠርላቸው የሚል ግልጽ የሆነ እነሱን ሊያስተናግድ የሚችል መዋቅር
ባለመኖሩ ወደ አፈጻጸም ለመግባት እንደችግር ስለሆን ስራ አስፈጻሚው በትኩረት አይቶ መፍትሄ
ሊያስቀምጥለት ይገባል፡፡ እንዲሁም ጥረት ኮርፖሬት፤ መገናኛ ብዙሃን እና አንዳንድ ተቋማት ከአባላቶች
የአባልነት ክፍያ ማሰባሰብ መጀመራቸው ፤ለሌሎች አረያ መሆናቸው የሚበረታታ ሲሆን ከአላማው አንጻርም
ሙህራኖቹ ከዚህ ባደገ መንገድ ለአባላቶች ተጠቃሚነት በሌሎች ተግባራቶች ላይም መሳተፍ ይኖርባቸዋል፡፡

12
ግብ፡3. የማህበሩን ገቢ ከአባላት የአባልነት ክፍያ ገቢ(9,520,292 ብር የዘመኑ፤ 5,006,846 ውዝፍ) በድምሩ
የአባላት ገቢ 14,527,138 ብር፤ ፕሮጀክት በመቅረጽ ከለጋሽ ድርጅቶች 10 ሚሊዮን ብር እና ለማህበሩ ህንጻ
ግንባታ 458 ሚሊዮን ብር በድምሩ 482,527,138 ብር በማሰባሰብ የማህበሩን የመፈጸም አቅም ማሳደግ

የአባላት ገቢ በበጀት አመቱ የውዝፍ እና የዘመኑን የአባልነት ክፍያ እስከ ታህሳስ 30/2011 ዓ/ም ድረስ በቅድመ
ዝግጅት ስራችን በንቅናቄ ለማጠናቀቅ የታቀደ ቢሆንም በበጀት አመቱ መፈጸም ወይም ማሰባሰብ የተቻለው
ግን ብር 3,151,764 ብር (33%) ብቻ የዘመኑን ማሰባሰብ ተችሏል፡፡ አፈጻጸሙ ሲታይም እጅግ በጣም
ዝቅተኛ፤ የአቀድናቸውን የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን ለማከናወን እንቅፋት የሚሆን፤
የአጋር እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የሌለበት እና ማህበሩም እንደ ተቋም በአግባቡ ያልመራው ተግባር
መሆኑን ማየት ተችሏል፡፡ እንዲሁም በአብዛኛው ሃብቱ ከሴቷ እጅ የተሰበሰበ እና በየደረጃው ባለው አመራር
እና ባለሙያ እጅ የተቀመጠ መሆኑንም ለኦዲት ስራወች ካሪኒወች እንዲሰባሰቡ የማድረግ ስራ ሲሰራ
ለማረጋገጥ ተሞክሯል፡፡ ይህ ተግባሩ አሁን ላይ አፈጻጸሙ ከባለፉት አመታት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር
በጣም ዝቅተኛ እና ወደ ኋላ የቀረ፤ እስካሁን የተሸለ አፈጻጸም የነበራቸው ዞኖች ጭምር አሁን ወደኋላ
የቀሩበት ሲሆን በዋናነት እንደ ችግር የሚነሳው የመጀመሪያው የዞን አስተባባሪወች በደመወዝ ጥያቄ ምክንያት
መቆዘም እና ወደ ስራ በሙሉ ተነሳሽነት ያለመግባት፤ወቅታዊ ክልላዊ ሁኔታው( በሁለት መንገድ ማለትም
አንደኛው በተለይም ሰ/ዎሎ፤ ደ/ወሎ፤ ደሴ ከተማ፤ ኦሮሞ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ላይ በቀጥታ ማህበሩ ካርኒ
በትኖ የአባላት ገቢ እንዳይሰበስብ በአንዳንድ ወረዳወች ካርኒ እስከመቀማት ድረስ ችግሮች መፈጠራቸው
ሲሆን 2 ኛው መንገድ ደግሞ ለውጡን ምክንያት በማድረግ አብዛኛው ስራ አስፈጻሚወች ከመንግስት እና
ድርጅት ሃላፊነት ጋር ደርበው ይዘው ስለነበር ሃላፊነታቸውን ሲለቁ ከማህበሩ አመራርነትም በመነሳታቸው፤
የተተኩት ስራ አስፈጻሚወች አዲስ በመሆናቸው ስራውን ባለማወቅ ወደ ስራ ባለመግባታቸው) ቢሆንም
ይሄንን ችግር ሊቋቋም የሚችል ጠንካራ የሆን መዋቅር ያለው ተቋም እና በየደረጃው ጠንካራ አመራር
ባለመኖሩ፤ ለአንዳንድ ዞኖች ደግሞ የዘመኑን ስራ ማስኬጃ ክልሉ ያለባቸውን ችግር ፈትቶ መላክ ሲገባው
በወቅቱ ባለመላኩ(ደ/ጎንደር፤ሰ/ጎንደር፤) ዞኖች የሰበሰቡትን ሃብት አንልክም ማለታቸው፤ እንዲሁም ፤ የክልል
ጽ/ቤቱ የገቢ ማሰባሰቢያ ካርኒወችን በወቅቱ አሳትሞ ባለማቅረቡ በቅድመ ዝግጅት ወቅት ለወረዳወች እና
ቀበሌወች ማሰራጨት ባለመቻሉ የገቢ ማሰባሰብ ስራውን አፈጻጸም ዝቅተኛ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
እንዲሁም ዞን የጽ/ቤት አስተባባሪወችም ለተግባሩ ተፈጻሚነት ድጋፍ እና ክትትል አለማድረግ ተግባሩን አንድ
ጊዜ አቅደው ካወረዱ በኋላ እንዴት እየተፈጸመ እንደሆነ፤ ወረዳወች እና ቀበሌወች ምን ችግር
እንዳጋጠማቸው፤ የትኞቹ የተሻለ እንደፈጸሙ በግብረ መልስ አለማሳወቅ፤ በየወረዳው ሃብቱ ከሴቷ እጅ
ከተሰበሰበ በኋላ ገቢ እንዲያደርጉት ያለመከታተል እና ለስራ አስፈጻሚው አቅም በመሆን እና የደጋፊነት
ሚናቸውን እንዲወጡ በማድረግ በኩል በትኩረት ያለመስራት ችግሮች ይታያሉ፡፡ ይህ በመሆኑም አስተባባሪ
ያላቸው ዞኖች እና የሌላቸው ዞኖች ተቀራራቢ እና አንዳንድ ዞኖች ደግሞ(ደቡብ ጎንደር፤ ማዕከላዊ ጎንደር፤
ባህርዳር ከተማ፤ ደሴ ከተማ) አስተባባሪ ከሌላቸው ዞኖች በታች የሆነ አፈጻጸም ማስመዝገባቸው በቦታው

13
ቢኖሩም ስራውን በአግባቡ እየተወጡ እንዳልሆነ ያሳያል፡፡ በተመሳሳይ ጎንደር ከተማ አስተዳደርም ምንም አይነት
ሃብት ገቢ ማድረግ አለመቻሉ ያለው የስራ አስፈጻሚ ለማህበሩ ትኩረት የሰጠ አለመሆኑን ያሳያል፡፡

የማህበሩን የገቢ ማስገኛ የህንጻ ግንባታ ለማሳካት የሴቶች የልማት ቡድንን መሰረት በማድረግ በ 2010 ዓ/ም ከታቀደው
እና መሰብሰብ ያልቻለ 28 ሚሊዮን ብር እንዲሁም በ 2011 ዓ/ም የዘመኑን 30 ሚሊዮን ብር በድምሩ 58 ሚሊዮን ብር
ለመሰብሰብ ታቅዶ፤ ከባለፈው አመት መገባደጃ ጀምሮ በንቅናቄ መድረኮችን በመፍጠር፤ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ዞን ድረስ
ውይይት በማካሄድ፤ ለሁሉም ዞኖች እኩል ኦሬንቴሽን በመስጠት፤የገቢ ማሰባሰቢያ ካርኒወችን በማሳተም ለሁሉም
ዞኖች በማሰራጨት ወደ ስራ የተገባ ሲሆን አፈጻጸሙ ሲታይ ግን ከባንክ ሪፖርት እና እኛም በሁሉም ዞኖች እና ወረዳወች
በመስክ ባረጋገጥነው መሰረት ስራው ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ አለመሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ አፈጻጸማችንም
509,593.51 ብር(0.9%) ከዞኖች ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ደግሞ 2,364,128.61 ብር ማሰባሰብ ተችሏል፡፡
በአጠቃላይ እስከ ወለዱ 3,028,463.21 ብር ማሰባሰብ ተችሏል፡፡ አፈጻጸሙ ሲታይም በየደረጃው ያለው አመራር
በመቀናጀት ድጋፍ እና ክትትል ያልሰጠበት ለጽ/ቤቱ እና ለዞኖች ብቻ የተተወ በመሆኑ በሁሉም አካባቢወች እኩል ግንዛቤ
ያልተያዘበት ለምሳሌ ምስራቅ ጎጃም እና ኦሮሞ ዞን በእምነትም ያልተቀበሉት ሲሆን አመራሩም ይሄን አመለካከት
ተከታትሎ ማስተካከል ያልተቻለ በመሆኑ እንዚህ ዞኖች ወደስራው መግባት አልቻሉም ፡፡ስለሆነም ሁሉም ዞኖችን እና
ወረዳወችን ወደ ስራ ማስገባት በየደረጃው ያለው አመራር እና ባለሙያ የቀጣይ ሃላፊነት ይሆናል፡፡

እንዲሁም ዞኖች ከልዩ ልዩ የማህበሩ ገቢ የሚሰባሰበውን ሃብት ወደ አንድ ማክል በማሰባሰብ ለታለመለት አላማ
በማዋል በኩል በምክር ቤቱ በተወሰነው መሰረት ወደ ስራ ገብተው ተግባራዊ እንዲያደርጉ በ 2010 ዓ/ም
የተወሰነ ቢሆንም የክልሉ ጽ/ቤት የምክር ቤቱን ውሳኔ እንደ ስራ መመሪያ በመጠቀም አስፈላጊ የስራ
መመሪያወችን እና ጋይድ ላይን በማዘጋጀት ዞኖችን ተከታትሎ ወደ ስራ ለማስገባት በመዘግየቱ(አካውንት
የተከፈተው እና ጋይድ ላይን የተሰራጨው በዚህ ሩብ አመት ነው) በአፈጻጸሙ ላይ ለውጥ ማምጣት
አልተቻለም፡፡ ምንም እንኳን ይሄ ችግር ከላይ ጀምሮ ያለ ቢሆንም የዋግህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በስሩ
የሚገኙ እና ሃብት ያላቸውን ወረዳወች (ሰቆጣ፤ ጋዝጊብላ እና ደሃና) ወረዳወችን በማሳመን በዞን ደረጃ የልዩ
ልዩ ገቢ አካውንት በመክፈት፤ ወደ ዞኑ በተለያየ ጊዜ የተላኩ የገቢ ማስገኛ ብድሮችን ወደ ዞኑ አካውንት ገቢ
እንዲሆኑ በማድረግ እና ገቢው ያላቸው ወረዳወች በተዘዋዋሪ ብድር እንዲጠቀሙበት ማድረግ መቻሉ
ለሌሎች ዞኖች ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው፡፡ በሌሎች ዞኖች ግን የተግባባንበትን እና የምክር ቤት ውሳኔውን
ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ችግር መኖሩን በአንዳንድ ዞኖች ማለትም በምስራቅ ጎጃም ዞን፤ በምዕራብ ጎጃም
ዞን፤ በሰሜን ሸዋ ዞን፤ በኦሮሞ ልዩ ዞን፤ በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን፤ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ስራው
ያልተሰራ እና በዞን ደረጃ እንኳ የልዩ ልዩ አካውንት ያልተከፈተ፤ በአመለካከት ደረጃም በምክር ቤቱ ቁጭ
ብለው ከወሰኑ በኋላ ለወረዳወች ስለ ሃብት አስተዳደሩ ግልጸኝነት ፈጥሮ ወደ ስራው ከመግባት ይልቅ
ወረዳወችን ብንጠይቃቸው እንቢ ብለውናል በማለት እንዲሁም በደቡብ ጎንደር ዞን ደግሞ አካውንቱ
ቢከፈትም (በደ/ታቦር ከተማ የሚገኘውን የካፍተሪያ ኪራይ ከመሰብሰብ ውጭ የሌሎች ወረዳወችን ወደ
አንድ ማዕከል ማምጣት አለመቻሉ እንዲሁም የተሰበሰበውም ገቢ ቢሆን ለብክነት የተዳረገ መሆኑ)
በአጠቃላይ ተግባሩን በእምነት ባለመያዝ ወደ ስራው ያልገቡ ዞኖች ናቸው፡፡ ደቡብ ወሎ ዞን ከደሴ ከተማ
አስተዳደር ጋር በጋራ በተከፈተ አካውንት ሃብቱን ወደ አንድ ማዕከል የማሰባሰብ ስራ ተጀምሮ የቆየ ቢሆንም
ሙሉ በሙሉ ግን ሁሉም ወረዳወች ወደ አንድ ማዕከል ሃብቱን እየላኩ አለመሆኑ ማለትም ኩታበር፤ ሳይንት
፤መሃል ሳይንት እና ተውለደሬ ወረዳወች የሚያገኙትን ልዩ ልዩ ገቢ ወደ ዞን አካውንት አንልክም በማለት
በራሳቸው አካውንት በመክፈት ሃብቱን እያባከኑት ስለሆን ወደፊት ጥብቅ ክትትል በማድረግ ዞኑ ማስተካከል
ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም ደቡብ ወሎ ዞን እና ደሴ ከተማ አስተዳደር በዞን ደረጃ አቋም ይዘው ሃብቱን ወደ ክልል
14
አንልክም አባሉን ሳናወያይ የሚል አቋም በስራ አስፈጻሚው መያዙ ስህተት ስለሆነ መስተካከል እና ወደ ስራ
መገባት ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም የተሻለ አሰራር የፈጠሩ ዞን እና ወረዳወች ያሉትን ያክል ከፍተኛ ሃብት
ያላቸው አንዳንድ ወረዳወች ደግሞ(ለምሳሌ ሰ/ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ፤ ምስራቅ ጎጃም ዞን ቡብኝ
ወረዳ) ያላቸውን ገቢ ያላግባብ በቀበሌ እና በወረዳ ደረጃ እየተጠቀሙበት ስለሆን በየደረጃው ያለው አካል
ጥብቅ ክትትል በማድረግ ወደ ህጋዊ አሰራሩ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ዞን
ድረስ የሚገኘውን ልዩ ልዩ ቋሚ ሃብቶች በአግባቡ መዝግቦ እና ከሶስተኛ ወገን ነጻ በማድረግ የራሳቸው የይዞታ
ማረጋገጫ የሌላቸውን እንዲኖራቸው በማድረግ በኩል በሁሉም ዞኖች ከፍተኛ ውስንነት ስላለ ወደፊት
ትኩረት በመስጠት ሃብቶችን ለተባለላቸው አላማ እንዲውሉ ማድረግ፤ ተከታትሎ የይዞታ ማረጋገጫ
እንዲሰራላቸው ማድረግ ይኖርብናል፡፡

3. የአብይ ተግባራት አፈጻጸም እንደ መነሻ ሁኔታ

3.1 የአባላት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ያለበት ሁኔታ

3.1.1 የአባላት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት


ግብ .1 በተለያዩ የግብርና ዘርፎች የማህበሩ አባላትን 70% ወደ ላቀ ደረጃ እንዲደርሱ የተሟላ ግባት
እንዲጠቀሙ ማድረግ እና 30% በአዲስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ

ማህበሩ አርሶ አደር የማህበሩ አባላትን መንግስት በዘረጋቸው የልማት ፖሊሲ እና የልማትና የለውጥ ፖኪጅ እንዲሁም
በግብርና ኤክስቴንሽን በቂ እውቀትና ግንዛቤ ኖሯቸው የተሻሻሉ አሠራሮችንና ቴክኔዎሎጆችን እንዲጠቀሙ በማድረግ
ዘመናዊ አሠራርንና የግብርና ኤክስቴንሽኑን በቀላሉ ወደ አባል አርሶ አደር ሴቶች ለማስረጽ በየደረጃው ባለው
መዋቅራችንን በመጠቀም በመወያየት እና የግብርና ኤክስቴኝሽን ሥራው ወደ አባላት ብሎም ለሴቶቹ በቀላሉ
እንዲሸጋገርና የገጠር ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ከፍተኛ የሆነ ሚናውን እየተወጣ
ይገኛል፡፡ ሁሉም አባላት ወደ ላቀ ደረጃ እንዲደርሱ ቀጣይነት ያለው የቴክኖሎጅ ተጠቃሚነትን በማጎልበት ፤እማውራ
አባላት መሬታቸውን በአነስተኛ ዋጋ ከማከራየት ይልቅ እራሳቸው እንዲያለሙ ተከታታይ ግንዛቤ በመፍጠር፤
ምክርቤቶቻቸውን እና የሴቶች የልማት ቡድንን በማጠናክር የአባላትን ሰብል ምርት ለማሳደግ የሚያስችሉ የግብርና
ቴክኖሎጆችን በመጠቀም ምርታቸውን እንዲያሳድጉ በግብርና ባለሙያ ትምህርት እንዲሰጣቸው በማድረግ ፍላጎት
እንዲፈጥሩ በማነሳሳት በበጀት አመቱ ለ 150,000 አባላት ስለ ስራ ፈጠራ እና የገቢ ማስገኛ ስራወች ግንንዛቤ በመፍጠር
ግንዛቤ ከተፈጠረላቸው ውስጥ በልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ዘርፎች ማለትም በእንስሳት ማድለብ 102,546፤ በእንስሳት
እርባታ 420,500፤ በሰብል ልማት 1,000‚000፤ በአትክልት እና ፍራፍሬ ልማት 115,500፤ በንብ ማነብ 2,500፤ እና በደሮ
እርባታ 75,500 አባላት እንዲሰማሩ በማድረግ በበጀት አመቱ 70% አባላትን ወደላቀ ደረጃ ማድረስ እና 30% አባላት
ደግም በአዲስ የተሟላ ግባት እንዲጠቀሙ ለማድረግ ግብ ተጥሎ ሲሰራ ቆይተቷል፡፡

በመሆኑም በአመቱ ውስጥ ለ 81,894 (55%) አባላት ግንዛቤ በመፍጠር እና 24‚298 አባላት ደግሞ ተገቢውን የስራ ፈጠራ
ክህሎት ስልጠና በመስጠት 842,421 (50%) አባላት ደግሞ በግብርና ኤክስቴንሽን የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ
በማድረግ በልዩ ልዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ማለትም (ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በመጠቀም፣ ሰብል በመስመር በመዝራት፣
የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎችን በመጠቀም) እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት በአመቱ ውስጥ በእንስሳት
ማድለብ 38,564(38%) ፣ በእንስሳት እርባታ 268,758(64%)፣ በሰብል ልማት 718,260(72%)፣ በአትክልትና ፍራፍሬ

15
ልማት 56,326(49%)፣ አባላት በዶሮ እርባታ 19,427(26%)፤ እንዲሁም በንብ ማነብ ስራዎች, 961(38%) አባላት
እንዲሳተፉ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል፡፡ በዚህም የዞኖችን አፈጻጸም ስንመለከት በአንጻራዊነት የተሻለ
አፈጻጸም ያላቸው ዞኖች፣ ምዕራብ ጎጃም፣አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን፣ ደ/ወሎ፤እና ሰ/ሸዋ እንዲሁም በመካከለኛ
ደረጃ ደ/ጎንደር፣ እና ኦሮሞ ዞን ሲሆኑ በዝቅተኛ ደረጃ ማ/ጎንደር፣ ዋግምህራ፣ ደሴ እና ባህር ዳር ከተማ ይገኙበታል፡፡
ሰ/ወሎ፤ጎንደር ከተማ በበጀት አመቱ በሪፖርት መገናኘት አልተቻለም፡፡በአጠቃላይ ከአፈፃፀሙ መረዳት እንደሚቻለው
አባላት በልዩ ልዩ የግብርና ፓኬጆች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር ከተያዘው ዕቅድ አኳያ ሲታይ
ዝቅተኛ ሲሆን አባላት ዘመናዊ አሰራሮችን በተሟላ ሁኔታ እንዲከተሉ ከማድረግ አኳያ እና አባላት በአብዛኛው
ተጠቃሚ የሆኑት ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ ብቻ በመሆኑ ወደፊት ደግሞ ሁሉንም ቴክኖሎጅዎች አቀናጅተው
እንዲጠቀሙ ለማድረግ መስራት ይኖርብናል፡፡

1) በጥቃቅንና አነስተኛ የሥራ ዘርፍ

የከተማ አባላችን የሥራ እድል ሊፈጠረላቸው የሚገቡትን ቤት ለቤት በመዘዋወር እንዲለዩ የማድረግና በዘርፉ
የተሰማሩ አባላት የሚያጋጥማቸውን የስልጠና፣ የብድር እና የመስሪያና የመሸጫ ቦታ ችግራቸውን
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት ለመፍታት ጥረት ተደርጓል፡፡ በዘርፉ 199‚360 አባላትን ተጠቃሚ
ለማድረግ ታቅዶ 105‚498 ከአመታዊ ግባችን(58%) አባላትን በልዩ ልዩ የጥቃቅንና አነስተኛ የስራ ዘርፎች
ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ በበጀት ዓመቱ 1228,933 አባላት 3‚689‚799000 ብር ብድር እንዲያገኙ ለማድረግ
ታቅዶ ለ 873924 አባላት 248567285 ብር (7%) ብድር እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

3.1 የአባላትን ማህበራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማሳደግ


ግብ 4. የአባላትን የትምህርት ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በ 2010 ዓ/ም ከነበረበት 43% ወደ 70% ማሳደግ

እንደሚታወቀው በክልላችን ከሚገኘው ያልተማሩ የህ/ሰብ ክፍሎች ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዙት ሴቶች
በተለይም አ/አደር ሴቶች ናቸው፡፡ ካሉን አጠቃላይ የማህበር አባላት ውስጥ ከ 90 በመቶ በላይ የሚሆኑት አ/አደር
ሴቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ከፍተኛ ድርሻ ይዞ የሚገኘውን ያልተማሩ ሴቶች ቁጥር ለመቀነስና ሁሉንም አባላት ማንበብና
መፃፍ የሚችሉና የተቀናጀ ተግባር ተኮር ትምህርት ተሳትፎ ለማረጋገጥ በዚህ አመት በ 2010 ከነበረበት 43% ወደ
70% ለማሳደግ ግብ ተጥሎ እየተሰራ ያለ ሲሆን በጠቀሜታው እና አስፈላጊነቱ ዙሪያ እስከዚህ ሩብ አመት ለ 250,000
አባላት ግንዛቤ ለመፍጠር ታቅዶ ለ 273,326 (100% በላይ) አባላት ግንዛቤ በመፍጠር 200,000 አባላትን በአዲስ
የተ/የተ/ተ/የጎ/ት/ት እንዲማሩ ለማድረግ ዕቅድ ተይዞ 31,692(16%) አባላትን በአዲስ የተ/ተ/የጎ/ት/ት እንዲማሩ
ማድረግ ተችሏል፡፡ በአመቱ ልናሳከው ካስቀመጥነው ግብ የጀመሩትን ማስቀጠል እና ማስመረቅ ሙሉ በሙሉ የቆመ
ሲሆን በአዲስ እንዲማሩ ማድረግ አፈጻጸማችን ከአመቱ ግብ (16%) ላይ እንገኛለን፡፡ አፈጻጸማችን ዝቅተኛ ቢሆንም
ትምህርቱን ተከታትለዋል ተብሎ በምዕ/ጎጃም፤ ኦሮሞ፤ማእከላዊ ጎንደር፤ደቡብ ጎንደር፤ ባህርዳር እና ደሴ ከተማ ዞኖች
ሪፖርት የተላከውም ቢሆን በመስክ ድጋፍ በአረጋገጥነው መሰረት በአብዛኛው ከመመዝግብ በዘለለ ተከታታይነት ባለው
ሁኔታ በመማር በኩል ከፍተኛ ችግር ያለበት ፕሮግራም መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ከዚህም ባለፈ የተመዘገቡ አባላት
ወጥ በሆነ መንገድ ሳያቆራርጡ ትምህርቱን እንዲከታተሉና እንዲመረቁ ክትትልና ድጋፍ ከማድረግ፣ ባለፈው በጀት
ዓመት ትምህርት የጀመሩ አባላትንም ቢሆን መቅሰም ያለባቸውን ት/ት በአግባቡ ተከታትለው ደረጃው የሚፈልገውን
16
ዕውቀት እንዲይዙ ከማድረግ፣ ትምህርቱ በተቀናጀ አግባብ እንዲሰጥ እንዲሁም አባላትም ከመመዝገብ አልፎ ለሌሎች
ሴቶች ግንባር ቀደም የዐረያነት ሚናቸውን ለመወጣት በሚያስችል መልኩ የልማት ቡድን አደረጃጀታቸውን መሰረት
አድርጎ በመሳተፍ በኩል በአጠቃላይ በመማራቸው ያመጡትን ለውጥ ቀምሮ ሌሎች እንዲማሩበት በማድረግ በኩል
የሚታዩ ክፍተቶች አጽንኦት ተሰጥቶ ሊሰራባቸው የሚገቡ ናቸው፡፡

ግብ.5. በጤና ልማት ተግባራት የአባላትን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማሳደግ፣

የእናቶች እና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ በተለይ ነፍሰጡር እናቶችን እንዲመዘገቡ የወሊድ ክትትል እንዲያደርጉ በጤና
ተቋማት በሰለጠነ አዋላጅ ወይም በጤና ኤክስቴሽን እዲወልዱ ፖኬጁን እንዲያሟላ የተቀናጀ ስራ እየተሰራ ሲሆን
አባላት በቅድመ ወሊድ፣ ወሊድና ድህረ ወሊድ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑና አንድም አባል ቤቷ ውስጥ
እንዳትወልድና በወሊድ ምክንያት እንዳትሞት እራሳቸው ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን በአደረጃጀቶቻቸው
በመወያየት ሰፊ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በበጀት አመቱ 325‚000 ነብሰጡር አባላትን/እናቶችን ለመመዝገብ ታቅዶ
81,776(25%) እናቶችን በመመዝገብ 325‚000 አባላት የመጀመሪያ ዙር የቅድመ ወሊድ አገልግሎት እንዲያገኙ ታቅዶ
81,052(81%) አግኝተዋል፣ እንዲሁም 81,052(25%)አባላት ደግሞ የ 4 ኛ ዙር የቅድመ ወሊድ አገልግሎት
አግኝተዋል፣ 81,052(25%) ነብሰ-ጡር አባላት የኤች.አይ.ቪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን 58,037(18%) አባላት
በሰለጠነ ባለሙያ፣ 532 አባላት(አዊ 5፤ደቡብ ወሎ 485 እናዋግ 45) ደግሞ በቤታቸው ወልደዋል፡ እንዲሁም
51,880(89%) አባላት ደግሞ በድህረ-ወሊድ አገልግሎት ተጠቃሚ እዲሆኑ ማድረግ ተችሏል፡፡ አፈፃፀሙም ከዕቅዱ
አንፃር ሲታይ ዝቅተኛ ነው፡፡ ማለትም ከተመዘገቡት 81,776 ነብሰ ጡር እናቶች መካከል በሰለጠነ ባለሙያ የወለዱት፣
የ 4 ኛ ዙር የቅድመ ወሊድ ክትትል ያደረጉት እና ቫይረሱ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የኤች .አይ.ቪ/ኤድስ ምርመራ
ያደረጉት አፈጻፀም ዝቅተኛ በመሆኑ በቀጣይ በትኩረት ተይዞ ሊፈጸም ይገባል፡፡

ግብ 6. የሴቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት የሚገድቡ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችንና የሃይል ጥቃት መቀነስ

በሴቶች ላይ አካላዊ፤አእምሮአዊ፤ስነ-ልባናዊ ማህበራዊ ዕድገት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድርና ለረጅም ጊዜ


ለችግርና ለአካል ጉዳት የሚዳርጉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲቀንሱ መከላከሉ ላይ ትኩረት በመስጠት
የችግሩ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን እና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፍ የመከላከል ስራ እየተሰራ
ይገኛል፡፡ በመሆኑም የመጀመሪያው ተግባር የሆነውን በየደረጃው ላለው የህብረተሰብ ክፍል ግንዛቤ መፍጠር እና
በመከላከሉ ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ለማስቻል በበጀት አመቱ ለ 3,000,000
(ወንድ 1,500,000 ሴት 1,500,000) ለሚሆኑ የተለያዩ የህ/ሰብ ክፍሎች በጎጅ ልማዳዊ ድርጊትና የሀይል ጥቃት ዙሪያ
እንደዚሁም በሀገራዊ የጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ማስወገድ ስትራቴጂ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ታቀዶ 839,462 (ወንድ
282,814፣ ሴት 556,648) ለሚሆኑ ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፡፡ አፈፃፀሙም 28 በመቶ ነው፡፡

በአጠቃላይ ሴቶችን ለችግርና ለአካል ጉዳት የሚዳርጉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲቀንሱ የተፈጠረው ግንዛቤ
ቢኖርም እንኳን ግንዛቤ በተፈጠረባቸው አካባቢወች እንኳ ሳይቀር አሁንም ተግባሩ የአፈጻጸም ስልቱን
እያቀያያረ እየተፈፀም እና እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ለችግር እያጋለጠ በመሆኑም በፈጠርነው ግንዛቤ
ልክ የመጣውን ውጤት እየለኩ መሄድ ይጠበቃል፡፡

በፖለቲካዊ ተሳትፎ እና ውሳኔ ሰጭነት

17
ግብ 7. የአባላትን ውሳኔ ሰጭነት በመልካም አስተዳደር እና ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመታገል ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ
ማህበሩ ከተቋቋመበትና ከሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት ውስጥም የሴቶች እኩልነት እንዲረጋገጥ
መታገልና ሴቶች የሃብትና ንብረታቸው ባለቤት እንዲሆኑ ማድረግ አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም አባላት ስለህግ አገልግሎት
በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በበጀት አመቱ ለ 1‚000,000 ሴቶች የንቃተ-ህግ ትምህርት ለመስጠት ታቅዶ
ለ 421,428(42%) ሴቶች የንቃተ ህግ- ትምህርት እንዲሰጣቸው ተደርጓል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በየደረጃው ባሉ የፍትህና
የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተጎጅ የሆኑ ሴቶችን ችግር ለመፍታት ማህበሩ በየደረጃዉ ካሉ የፍትህ አካላት ጋር
በመቀናጀት የድሃ ድሃ የሆኑ ሴቶችን የነጻ የህግ ድጋፍ ተሰጥቶአቸዉ የመሬትና ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ከማድረግ
በተጨማሪ በክልሉ ዉስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የኢኮኖሚ አቅም ለሌላቸዉ ሴቶች ነጻ የህግ የምክር
አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በዚህም በዞኖች ደረጃ 71 ሴቶች የመሬት ባለቤትነት መብታቸውን ለማረጋገጥ የነፃ ህግድጋፍ
ሲያገኙ 315 ሴቶች ደግሞ ልዩልዩ የመብት ጥሰትና የመል/አስ/ችግሮችን በተመለከተ ነፃ የህግ ምክር አገልግሎት እንዲያገኙ
ተደርጓል፡፡ በተመሳሳይ በክልል ማእከሉ በሚገኝ የዩኒቨርስቲው የህግ ድጋፍ ማእከል 134 ሴቶች የህግ ድጋፍ ያገኙ ሲሆን የመሬት
ክርክርና የቤተሰብ ጉዳዮች ከተሰጧቸው የህግ የምክርና የጽህፈት አገልግሎት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ በህግ ድጋፉም የመሬት
ክርክር ቅድሚያውን የሚይዝ ሲሆን የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ለታመነበት 31 ሴቶች 28,844.44 ብር
የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ ሆኖም የዞን እና የወረዳ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ማህበሩ በየደረጃው ባለው አሰራር
የፈታቸው ችግሮችና የተደረጉ የገንዘብ ድጋፎች፣ በዩኒቨርሲቲዎች የተቋቋሙ ማእከላት የመጡ አገልግሎት
ፈላጊዎች፤ የችግሮች አይነት፣የሰጧቸው የህግ ድጋፍና ውጤት በዝርዝር ሪፖርት መደረግ ቢገባቸውም
እየተደረጉ ባለመሆኑ በሴቶች ላይ ለሚደርሱ በደሎችና ለሚገጥሟቸው የፍትህ መጓደሎች ማህበሩ ያደረገው
አስተዋጽኦ ካለመታየቱም ባለፈ የችግሮችን ምንጭ ለማድረቅ በሚደረገው ርብርብ ላይ የእራሱን አሉታዊ
ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡

ግብ 2. የማህበሩን የሃብት አስተዳደር እና አጠቃቀም በዞን ደረጃ 40% እና በወረዳ ደረጃ 50% ኦዲት ማስደረግ እና
የማህበሩን የሃብት አጠቃቀም ስርዓት ማሻሻል

አባላት ሴቶች ያሉባቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታትና በማንኛውም ዘርፍ ያላቸውን
ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ይበልጥ ለማሳደግ ከአባላት ከሚሰበሰበው ሃብት ብቻ በቂ ስለማይሆን ከተለያዩ የሀብት
ምንጮች ሀብት ማሰባሰብ በተቋማችን ከሚከናወኑ ተግባራት አንዱ ነው። በዚህም መሠረት በአለፉት አመታት
ከወረዳ ጀምሮ እስከ ክልል ባለው መዋቅራችን የማህበሩን የሃብት አጠቃቀምና የሂሳብ አያያዝ ስርዓት በየጊዜው ኦዲት
ማስደረግ አለመቻሉ የማህበሩን ሃብትና ንብረት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዳይውልና አባላት በማህበሩ ላይ አመኔታ
እንዳይኖራቸው እያደረገ ነው፡፡የማህበሩ የሂሳብ አያያዝ በማይቆራረጥ መንገድ በየአመቱ ኦዲት እየተደረገ ያለው
በክልል የማህበሩ ጽ/ቤት ብቻ ነው፡፡ ይህም የማህበሩን የፋይናንስ እና ንብረት አያያዝ እና አስተዳደር ስርዓት ለብልሹ
አሰራር እና ለከፍተኛ ብክነት ሊዳርገው እንደሚችል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ጥሎታል፡፡ የማህበሩን የሃብት አጠቃቀምና
የሂሳብ አያያዝ ስርዓት በየጊዜው ኦዲት ማስደረግ ሲመከርበት የነበረና የማህበሩን አቅም ለማጠናከርም የሚረዳ
በመሆኑ በዚህ በጀት ዓመት ካሉን ዞኖች ክልሉ 40% እና ካሉን ወረዳወችም በተመሳሳይ ዞኖች 50% ኦዲት
ለማስደረግ ግብ ጥለን እየሰራን ሲሆን አፈጻጸማችን ሲታይ በዞን ደረጃ ደቡብ ጎንደር ዞን ብቻ እንዲሁም
በወረዳ ደረጃ ደቡብ ወሎ ዞን 4(አራት)፤ምዕራብ ጎጃም አንድ ወረዳ ኦዲት ያስደረግን ሲሆን በሌሎች
18
ወረዳወች እና ዞኖች ግን በተለይ በወረዳ ደረጃ ካርኒወችን እንዲያሰባስቡ እና ለኦዲት ምቹ እንዲሆኑ ድጋፍ
እና ክትትል እየተደረገ ያለ ቢሆንም እስካሁን ድረስ አስፈላጊውን አሟልቶ ለኦዲት እራሱን ምቹ ያደረገ ወረዳ
የለም፡፡ ይህ የሚያሣየው የማህበሩ ሃብትና ንብረት ለተባለለት ዓላማ እንዲውል እና ግልፀኝነት ያለው አሰራር ተግባራዊ
እንዲሆን በማድረግ በኩል ከፍተኛ ውስንነት ያለ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም እንዲህ አይነት አሰራር እየተለመደ መምጣቱ
የማህበሩን ህልውና የሚፈታተን በመሆኑ ሁሉም ወረዳዎች ወቅቱን ጠብቀው ኦዲት እንዲደረጉ በየደረጃው ያለው
አመራሩ በተለይም ደግሞ የክልል አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይኖርበታል፡፡

4 የማህበሩ ራዕይ

በ 2017 ሁሉንም የክልሉ ሴቶች ያቀፈና የተጠናከረ ማህበር ተፈጥሮ፤የአባላት ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና
ፖለቲካዊ ችግሮች ተፈትቶ ማየት፣

5 የማህበሩ ተልዕኮ

የተጠናከረና ሁሉም የክልሉ ሴቶች አባል የሆኑበት ማህበር በመፍጠር ሴቶች ከጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች
እንዲላቀቁ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲዊ ችግሮቻቸዉ እንዲፈቱና ከማንኛዉም ፆታዊ ጥቃትና ትንኮሳ
ነጻ እንዲሆኑ ሴቶችና ህብረተሰቡን ማስተማር መቀስቀስና ከሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት
ጋር ተቀናጅቶ መስራት።

V. የማህበሩ እሴቶች
 ስርዓተ ጾታ እኩልነትና ፍታሃዊነት እናሰፍናለን
 ለጋራ ፍላጐትና ጥቅም እንሰራለን
 ሕግና አሰራርን እናከብራለን
 በመደራጀት እናምናለን

6 የዕቅዱ ዓላማዎች፣ ዝርዝር ግቦችና የማስፈጸሚያ ስልቶች

6.1 አጠቃላይ ዓላማ

የማህበሩን ተቋማዊ አደረጃጀት በማጠናከርና የመፈጸም አቅሙን በማሳደግ የአባላትን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና
ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣

6.2 ቁልፍ ተግባር

የማህበሩን ተቋማዊ አቅም መገንባት

19
ዓላማ 1. የማህበሩን አደረጃጀትና አሰራር በማጠናከር ጠንካራ መዋቅራዊ ተቋም በመፍጠር የአባላትን
ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤

ግብ.1. በየደረጃው ያሉትን የማህበሩ አመራሮች የመፈጸም ብቃት ወደ 50% ማሳደግ

 የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
የ 2011 ዓ/ም የተግባር አፈጻጸም ግምገማ መነሻ በማድረግ በ 2012 ዓ/ም የሚኖሩን ዋና ዋና ተግባራት ለመፈጸም
የሚያስችል ዝርዝር እቅድ ማዘጋጀት
በየደረጃው የሚዘጋጀውን አቅድ መሪ እቅዱን መሰረት በማደረግ የአካባቢን ነባራዊ ተጨባጭ ሁኔታ የዳሰሰ የፈጻሚ እና
የባለድርሻ አካላት ትስስር በትክክል በማስቀመጥ የሚታዩትን የአመለካከት፤የአሰራር፤የክሎት እና የአደረጃጀት ጥንካሬ
እና ድክመት በመለየት ለእቅድ ዝግጅት በግባትነት ተጠቅሞ እንዲዘጋጅ ይደረጋል፡፡ በመሆኑም የ 2012 ዓ.ም እቅድ
ማህበሩን የሚያጠናክር እና የሚያሰራ እቅድ በሁሉም ዞኖች፤ ከተማ አስተዳደሮች እና ቀበሌወች እንዲሁም በአዲስ
አበባ ከተማ እቅድ የማዘጋጀት ስራ በቅርበት እየተመራ ግብረመልስ በመስጠት ጸድቆ የተግባር መመሪያ በማድረግ
በእቅድ መመራት ዲሲፕሊን እየጎለበተ እንዲሄድ ይደረጋል፡፡
በመሆኑም እቅዱን ለአባሎቻችን ማወያየት እና ግልጽነት በመፍጠር የአባላት ተሳትፎ የማጎልበት የማብቃት ስራ ይሰራል፡፡
ይሄንን በብቃት ለመፈጸም እቅዱን በብቃት ሊያወያዩ የሚችሉ የማህበሩ አባላት ሁነው በሌሎች ሴቶች አደረጃጀት
እና በተለያየ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ ጠንካራ አመራሮች እና አባላት በመለየት ኦሬንቴሽን በመስጠት ፈጻሚውን
በማሳመን ለእቅዱ ተፈጻሚነት የተሸለ ዝግጁነት እንዲፈጠር በጥብቅ የሚሰራ ይሆናል፡፡
በዚሁ መሰረት የማህበሩን እቅድ ለ 4953 አመራሮች፤ለ 4000 የግብርና እና የጥቃቅን አደራጅ ባለሙያወች፤ ለ 4000
የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያወች፤ ለ 4000 የቀበሌ ስራ አስኪያጆች እና ለ 1.76 ሚሊዮን አባሎቻችን በብቃት
በማሳተፍ በቁልፍ እና አባይ ተግባራት፤ በአፈጻጸም አቅጣጫወች ፤ በትግበራ ሂደቱ በሚያጋጥሙ ችግሮች እና
መፍቴወቻቸው ላይ በመግባባት በላቀ ቁርጠኝነት ለማስፈጸም የሚያስችል ወኔ በመፍጠር ማሰማራት ይሆናል፡፡
በየደረጃው ለሚገኙ (የዞን፣ ወረዳ እና የቀበሌ) የማህበሩ አመራሮች የአመለካከት እና የክህሎት ግንባታ ስልጠና መስጠት፣
በክልልና በዞን ደረጃ ያሉ የጽ/ቤቱን የሰው ሃይል የመፈፀም አቅም መገንባት፤
በየደረጃው ያለውን የማህበሩን አመራር 100% ወደ ስራ ማስገባት
በየደረጃው ያለውን አመራር በተሻለ የሰው ኃይል የማደራጀት
የ 4000 የቀበሌ አመራሮችን በማህበሩ ተግባራት፣ አሰራሮች፣ ደንቦች ዙሪያ ሁለንተናዊ እዉቀት
እንዲኖራቸዉ ስልጠና በመስጠት ወደ ተጨባጭ ተግባር ማስገባት፣
ለማህበሩ አጠቃላይ አባላት ስለማህበሩ አላማና ተልኮ፣ ስለማህበሩ ህገ-ደንብ እና ዝርዝር አሰራሮች ግንዛቤያቸውን
ማሳደግ፣
ክልል ለዞንና ዞን ለወረዳ በየሩብ አመቱ እንዲሁም ወረዳ ለቀበሌዎች በየወሩ የአካል ድጋፍና ክትትል
ማድረግ፣
የክልል ባለሞያውን አቅም ማሳደግ

20
በዓመቱ የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ዞኖች ወረዳዎችና አመራሮች እውቅና መስጠት፣

ግብ 2- 75% የማህበሩን አባላት በተልኮወቻቸው ላይ ያላቸውን ግልጽነት ማሳደግ

 ግቡን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራት


የማህበሩ አባል የሆኑና ያልሆኑትን ሴቶች በልማት ቡድኑ አማካኝነት መረጃ ለይቶ መያዝ፣
መላ ሴችን በአደረጃጃታቸዉ አማካኝነት ስለማህበሩ አላማ፣ ህገ-ደንብ፣ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ግንዛቤ
ማስጨበጥ፣
የማህበሩንና የሴቶችን የልማት ቡድን አደረጃጀት ትስስር በማጠናከር በአደረጃጃቱ አማካኝነት ስለ
ተልኮወቻቸው በልማት ቡድን ውስጥ ለተደራጁ አባላት ግንዛቤውን መፍጠር
ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ብሮሸር በማዘጋጀት ለቀበሌወች ተደራሽ ማድረግ እና
ውይይት እንዲካሄድበት ማመቻቸት
የዞን እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች የልምድ ልዉዉጥ የሚያደርጉበትን ፕሮግራም
በክልል ማዘጋጀት፤
የዞን አመራሮች በየዞኑ ስር ለሚገኙ የወረዳ አመራሮች ተመሳሳይ መድረክ እንዲያዘጋጁ
ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል፤
በተመሳሳይ የወረዳ አመራሮች የልምድ መለዋወጫ መድረክ እንዲያዘጋጁ የዞን አመራሮች
ተገቢዉን ድጋፍ እንዲያደርጉ ክትትል ይደረጋል፤
በየደረጃዉ የጋራ እየተደረገ የመጣ ምርጥ ተሞክሮና የአሰራር ስርአት በወረዳና በቀበሌ ደረጃ
ለአባላትና ለአመራሮች ግንዛቤ እንዲወሰዱ ይደረጋል፤
ከየዞኑ የመጡትን ሪፖርቶችና የመስክ ግኝቶች መሰረት በማደራጀትና በመለየት
ተገቢዉ ግብረ መልስ እንዲሰጥ ይደረጋል፤

ግብ 3- የማህበሩን ገቢ ከአባላት የአባልነት ክፍያ ገቢ (9,520,292 ሚሊን የዘመኑ+6,368,528 ውዝፍ)


ውዝፍ)
15,888,820 ብር ፕሮጀክት በመቅረጽ ከለጋሽ ድርጅቶች 10 ሚሊዮን ብር እና ለማህበሩ ህንጻ
ግንባታ 458 ሚሊዮን ብር በድምሩ 483,888,820 ብር በመሰብሰብ የማህበሩን የመፈጸም አቅም
ማሳደግ

 ግቡን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራት


የአባላትን መረጃ በሁሉም ወረዳዎችና ቀበሌዎች በጥራት እንዲሰበሰብ ማድረግ እና የአባላት ክፍያ ስራውን
በመረጃዉ መሰረት የማህበሩንና የሴቶችን የልማት ቡድን አደረጃጃት ትስስሩን በማጠናከር በልማት
ቡድኑ አማካኝነት ሁሉንም አባላት የዘመኑን የአባልነት ክፍያ ግዴታቸዉን እንዲወጡ ማድረግ፣

21
ውዝፍ ክፍያ ያለባቸውን አባላት በመለየት የአባልነት ግዴታቸውን እንዲወጡ በማድረግ የውዝፍ
ክፍያ ዜሮ ማድረግ፣
የአባላት ክፍያን የመሰብሰብ ስራን በንቅናቄ በዝግጅት ምዕራፍ ማጠናቀቅ፣
የመንግሰት ሰራተኛ እና ተባባሪ አባላት አመታዊ ክፍያ በአግባቡ ማሰባሰብ
ልዩ ልዩ ረጅ ድርጂቶችን ማፈላለግና መለየት፤
ድጋፍ ሊያደርጉ ከሚችሉ ለጋሽ ድርጅቶች ጋር የምክክር መድረኮችን ማዘጋጀት እና አጋርነትን
ማጠናከር፣
የማህሩን የገቢ አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ 10 የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎችን በመቅረፅና በማዘጋጀት
ለተለያዩ ረጅ ድርጅቶች ማቅረብ፣
ከተቀረፁት ፕሮጀክቶች ውስጥ ቢያንስ 8 ቱን ተግባራዊ እንዲሆኑ በማድረግ 10 ሚሊየን ብር በክልል
ደረጃ ብቻ መሰብሰብ፣
ከፕሮጀክቶች በሚገኘው ገቢ የአባላትን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶችን መተግበር፣
ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ፕሮጅከቶችን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እና ቀጣይነታቸውን ማረጋገጥ፣
የማህበሩን የህነፃ ግንባታ ለማሳካት የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዘዴወቸንበመጠቀም 458 ሚሊዮን ብር
መሰብሰብ-
ከአባላት 58 ሚሊዮን ብር ልማት ቡድኖችን መሰረት በማድረግ ማሰባሰብ
4 ፕሮጀክት በመቅረፅ ለለጋሽ ድርጅቶች በመስጠት ከልዩ ልዩ ረጅ ድርጅቶች (ከመንግስት፤ከልማት
ድርጅቶች፤መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት) 400 ሚሊዮን ብር በክልል ደረጃ ብቻ መሰብሰብ
የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሎቶን ይዘጋጃል
ስለ ህንጻ ግንባታው አስፈላጊነት ከአባላትና መላ ሴቶቸ ጋር በአስፈላጊነቱ ላይ በመግባባት በኩፖን
ሽያጭ ገቢ ማሰባሰብ

22
6.3 አበይት ተግባራት

ዓላማ 1. የአባላትን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳታፎና ተጠቃሚነት ማሳደግ

6.3.1 በኢኮኖሚያዊ ልማት ተግባራት

ግብ 1. በተለያዩ የግብርና ዘርፎች የማህበሩን አባላትን 70% ወደላቀ ደረጃ እንዲደርሱ የተሟላ ግብአት እንዲጠቀሙ
ማድረግና 30% በአዲስ ተጠቃሚ እነዲሆኑ ማድረግ፣

 ግቡን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራት


ሁሉም አባላት ወደላቀ ደረጃ እንዲደርሱ ቀጣይነት ያለዉ የቴክኖሎጅ ተጠቃሚ እንዲሆኑና እማወራ
ሴቶች መሬታቸውን በአነስተኛ ዋጋ ከማከራየት ይልቅ ራሳቸው እንዲያለሙ ግንዛቤ መፍጠር፤
የሴቶች የልማት ቡድን አደረጃጀቶችን በማጠናከር የአባላትን የሰብል ምርት ለማሳደግ
የሚያስችሉ የግብርና ቴክኖሎጅዎችን በመጠቀም ምርታቸዉን አንዲያሳድጉ በግብርና ባለሙያ
ትምህርት እንዲሰጣቸዉ ሁኔታዎችን ማመቻቸትና ፍላጎት እንዲፈጥሩ ማነሳሳት፤
አባላት በተፈጥሮ ሀብት ስራ እንዲሳተፉ መቀስቀስ፣ ቅስቀሳዉን በየልማት ቡድኖቹ ማድረግና
ለልማት ሲወጡም በተደራጀ መንገድ እንዲወጡ ግንዛቤ መፍጠር፣
በሚለሙ እና በሚያገግሙ ተራሮች የስራ ዕድል ለሌላቸው ሴቶች የስራ ዕድል
እንዲፈጠርላቸው ማድረግ፣

ግብ 2- በተለያዩ የጥቃቅንና አነስተኛ የስራ ዘርፎች ተጠቃሚ የሆኑ 70% ወደላቀ ደረጃ ማድረስ 30%የከተማ
አባላቸን በአዲስ ወደ ዘርፉ ማስገባት፣

 ግቡን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራት


የከተማ አባላት ተደራጅተዉ በተለያዩ የጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፎች እንዲጠቀሙ ግንዛቤ መፍጠር፣
በልዩ ልዩ ኢንተርፕራይዞች አባላት ሙያዊ የሆነ የክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ፣
23
አባላት ያለባቸውን የመነሻ ካፒታል እጥረት ለመቅረፍ ከልዩ ልዩ አበዳሪ ተቋማት ብድር እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ
መፍጠር፣
አባላት ያለባቸውን የመስሪያ እና የመሸጫ ቦታ እጥረት ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር
ተቀናጅቶ መስራት፣
ለዚህም የሚሆን ቁጠባ እንዲያሰባስቡ ተከታታይ የሆነ ግንዛቤ የመፍጠርና የቅስቀሳ ስራ መስራት፤ ከአበዳሪ
ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት፤
የተለያዩ ሀብቶችን በማፈላለግ አባላት በገቢ ማስገኛ የሚሰማሩበትንና የኢኮኖሚ አቅማቸው የሚጠናከርበትን
ሁኔታ ማመቻቸት፡፡
በልዩ ልዩ የጥቃቅን የስራ ዘርፎች ለተሰማሩ የማህበሩ አባላት የገቢያ ትስስር መፍጠር፣

ግብ 3- የማህበሩ አባላት 1,500,000,000 ብር እንዲቆጥቡ ማድረግ፣

 ግቡን ለመፈፀም የሚከናወኑ ተግባራት


ስለቁጠባ ጠቀሜታ እና አስፈላጊነት ለማህበሩ አባላት ግንዛቤ መፍጠር፣
አባላት በቆጠቡት ገንዘብ በልዩ ልዩ የማኑፋክቸሪንግ የስራ ዘርች እንዲሰማሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር
ማስተሳሰር፣
ከአጋር አካላት ጋር በጋራ በመሆን የአባላትን ተጠቃሚነት ያለበትን ደረጃ በጋራ እየገመገሙ መሄድ፣
6.3.2 በማህበራዊ ልማት ተግባራት

ግብ 4. የአባላትን የትምህርት ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ማሳደግ

 ግቡን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራት


በተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት አስፈላጊነትና ጠቀሜታ ዙሪያ ለ 500,000 አባላት ግንዛቤ
መፍጠር፣
የተ/የተ/ተ/የጎ/ት/ት ያልተማሩትን 200,000 አባላት እንዲማሩ ማድረግ፣
አባላት የጎልማሶች ትምህርት እንዲማሩ በሴቶች የልማት ቡድን አማካኝነት የተማሩትንና ያልተማሩትን
ዝርዝር ይያዛል፣ ያልተማሩትን እንዲማሩ ከሚመለከታቸዉ ጋር መስራት፤
በትምህርት ተቋማት በተለይም በየትምህርት ቤቱ በሚኖሩ የአመራርነት ቦታዎች (ወመህ)
የሴቶችን የአመራርነት ሚና ማሳደግ፣
በ 1 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሴት ርዕሳነ መምህራንን እና ሱፕርቫይዘሮችን ቁጥር እንዲያድግ ከባለ
ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት
የተማሪዎች ምዝገባ ስራን በሴቶች የል/ቡድን አደረጃጀት መሰረት መፈፀም፣
ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸዉን እንዳያቋርጡና ጥቃት እንዳይደርስባቸዉ ለወላጆች ግንዛቤ መፍጠር፣

24
አባላት የሚያቋርጡ ተማሪዎችን በአደረጃጀታቸው መሰረት ወደት/ቤት እንዲያስመልሱ
ግንዛቤ መፍጠር፣
ለትምህርት የደረሱ ህጻናትን ወደትምህርት ገበታ እንዲሄዱና አባላት ለልጆቻቸው የጥናት ግዜ እንዲሰጡ
ግንዛቤ መፍጠር፣
ለሴት ተማሪዎች ክበባት ማጠናከሪያ የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣

ግብ 5. የአባላትን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ቁጥር ማሳደግ፣

የጤና ኤክስቴንሽን ፖኬጆችን በጥራት አሟልተው የሚመረቁ አባላትን አሁን ካለበት


ወደ 100%ማድረስና ፓኬጁን ያሟሉትን ቀጣይነት እንዲኖረው መከታተል፣
የእናቶችን ሞት ለመቀነስ በጤና ተቋማት የሚወልዱ እናቶች መጠን አሁን ካለበት ማሳደግ፣
ተመዝግበዉ ከተያዙ ነብሰጡር እናቶች የአራተኛ ዙር የቅድመ ወሊድ አገልግሎት ያገኙ እናቶች ሽፋን
100% ማድረስ፤ የድህረ ወሊድ ክትትል የሚያገኙ እናቶችንም በተመሳሳይ፤
ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፈውን የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ለመከላከል ሁሉም ነብሰጡር እናቶች ምርመራ
እንዲያድርጉ መስራት፣
ቫይረሱ በደማቸዉ ያሉ ሴቶች ሁሉም የጸረ-ኤችአይቪ ኤድስ መድሃኒት እንዲጠቀሙ መስራት ፣
የማህበሩ አባሎች ደም እንዲለግሱ ግንዛቤ መፍጠር
 ግቡን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራት
የጤና ፓኪጁን ያሟሉ አባላት አስፈላጊውን ጥገና እንዲያደርጉ እና እንዲጠቀሙበት ግንዛቤ
መፍጠር፣
በእናቶች ጤና ዙሪያና በጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጁ ላይ ለማህበሩ የቀበሌ አመራሮችና የልማት ቡድን
መሪዎች ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ተግባር ማስገባት፣
በወሊድ ምክንያት አንድም እናት እንዳትሞት የሚያስችል የቅስቀሳና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ስራ
ተቀናጅቶ ይፈጸማል፣
የነፍሰ ጡር እናቶችን መዝግቦ መያዝና በጤና ድርጅት እንዲወልዱ ክትትል ማድረግ፤
የነብሰጡር እናቶች ክትትልም ሆነ ሌሎች የጤና ስራዎች በሴቶች የልማት ቡድን አማካኝነት
በቅንጀት ይፈጸማል፣
በኤች አይቪና በሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ዙረያ ለማህበሩ አባላት ግንዛቤ እንዲያገኙ መስራት፣
አባላት የሴቶች የጤና ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በሚሰሩ ስራዎች የግንባር ቀደምነት
ሚናቸውን እንዲወጡ መቀስቀስ፣
ለእናቶች/አባላት/ ስለ ማህጸን ጫፍ ካንሰር ግንዛቤ መፍጠር እና ወደ ጤና ተቋም ሂደው
እንዲመረመሩ ግንዛቤያቸውን ማሳደግ

25
ግብ 6. የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚገድቡ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችንና የሃይል ጥቃት መቀነስና ማጥፋት፣

 ስለጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶአች እና ፆታዊ ጥቃት ለ 3 ሚሊዮን የማህበረሰብ ክፍል ግዛቤ መፍጠር፣
 በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ያለእድሜ ጋብቻና ሌሎች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲቀንሱ ዘላቂነት ያለው
የመከላከል ስራ መስራት፣
 በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ የጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች (የሴት ልጅ ግርዛት) እንዲሁም ልዩ ልዩ የሃይል ጥቃቶችን
የመከላከል ስራ መስራት፣
 የፊስቱላ ህመምን ከ 0.5% በታች ማውረድ እና የችግሩ ተጠቂ የሆኑት አስፈላጊውን ህክምና
እንዲያገኙ ማድረግ፣
 ግቡን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራት
በጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች፣ በሃይል ጥቃት ዙሪያና በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ስትራቴጂክ ጉዳዩች ለ 3
ሚሊዮን የተለያዩ የህበረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ መፍጠር፣
በየደረጃው ከሚገኘዉ የጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች ጥምረት ጋር በቅንጅት መስራት በክትትልና ድጋፍ
ማጠናከር፣
በሁሉም የማህበሩ ምክር ቤት እና በሴቶች የልማት ቡድን ስለጎጅ ልማዳዊ ድርጊት እና የሃይል ጥቃት
ተከታታይ ውይይት እንዲካሄድ ማድረግ፣
ከጎጅ ልማዊ ድርጊቶች ነጻ የሆኑ ቀበሌወችን እና ልማት ቡድኖችን መፍጠር፣ እውቅና መስጠትና
ተሞክሯቸውን ማስፋፋት፣
የሴቶች የልማት ቡድኖችን ስልጠና በመስጠትና ድጋፍ በማድረግ ማጠናከርና ከጎጅ ልማዳዊ
ድርጊቶች ነጻ የሆኑ የሴቶች ልማት ቡድኖችን መፍጠር፣
የፊስቱላ ተጠቂ የሆኑ ሴቶችን በሴቶች የል/ቡድን አደረጃጀት አማካኝነት በመለየት ህክምና
እንዲያገኙ ማድረግ፣
ታክመው ለዳኑ የፊስቱላ ተጠቂዎች በልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ዘርፎች እንዲሰማሩ ማድረግ፣
6.3.3 በፖለቲካዊ ተሳትፎና ዉሳኔ ሰጭነት

ግብ 7. የአባላትን የዉሳኔ ሰጭነት በመልካምአስተዳደርናሙስናናብልሹአሰራርንበመታገልያላቸዉንተሳትፎማሳደግ፤

 ግቡንለማሳካትየሚከናወኑተግባራት
በየደረጃዉ ያለዉን የማህበሩን ም/ቤቶች በማጠናከር በማህበሩ የስራ እንቅስቃሴዎች ሙሉ እውቀት
እንዲኖራቸው በማሳተፍ የአባላትን የዉሳኔ ሰጭነትና የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደትን
እንዲያዳብሩ መስራት፣ ዉይይት የሚያደርጉና የማያደርጉትን መረጃ ለይቶ መያዝ፣
የክልል እና የብሄረሰብ ዞኖች ሴት የምክር ቤት አባላትን የውሳኔ ሰጭነት አቅም ማጎልበት
በቀበሌ እና በወረዳ ምርጫ ሴቶች የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራቸው መስራት

26
በየደረጃዉ ባሉ የመንግስት ም/ቤቶች የማህበሩ አመራሮች እየተገኙ በአባላት መብትና ጥቅም ጉዳይ
እንዲታገሉ ማደረግ፣
በአመራርና ዉሳኔ ሰጭነት አቅም የፈጠሩ አባላትና አመራሮች በየደረጃዉ ባሉ ኮሚቴዎችና
የመንግስት ሃላፊነት እንዲሳተፉ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
በወረዳና የቀበሌ ምርጫ እንዲሁም በአገር አቀፍ ምርጫ አባላትና መላ ሴቶች በመራጭነት
በአሰመራጭነት በታዛቢነት በመሳተፍ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዲጠቀሙበት
ማድረግ እንዲሁም ብቃት ያላቸው እና ተወዳዳሪ ሴቶችን ማዘጋጀት
በየደረጃው ባሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በንቃት በመሳተፍ በሴቶቸ ላይ የሚደርሱ ተጽኖወችን
መታገል፡፡
በክልል ተቋማት ስር ያሉ የሚገኙ መንግስት ሰራተኛ ሴቶችን አቅም ለማሳደግ ከየ ቢሮው የስርአተ
ጾታ አመቻቾች ጋር በመቀናጀት ይሰራል፤
ስለፍትህ እና መልካም አስተዳደር ለመላ አባላት የንቃተ-ህግ ትምህርት መስጠት፣ያለውን የአገልግሎት
አሰጣጥ ችግር እንዲታገሉ ማስተማር፡፡
ያለአግባብ መሬታቸውን የተነጠቁ አባላት በሴቶች የልማት ቡድኖች አማካኝነት እንዲለይና በአካባቢ መፍትሄ
የሚፈታዉን እንዲፈታ ጥረት በማድረግ ያልተቻለዉን ደግሞ ወደ ሚመለከተዉ አካል መፍትሄ እንዲያገኝ
ማድረግ፣
አባላት የመሬት አስተዳደር ህጉን እንዲያውቁ የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ባለቤት
እንዲሆኑ ወጥተዉ እንዲተቹ አዋሳኛቸውን እንዲያውቁ ማድረግ ማስተማርና ሙስናን በማጋለጥ
ለጥቅሞቻቸዉና ለመብቶቻቸዉ እንዲታገሉ ማዘጋጀት፣
በመንግስት እቅድና ተግባር አፈጻጸም ላይ በየደረጃው በሚፈጠሩ የንቅናቄና የተሳትፎ መድረኮች
አባላትና አመራሮች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ፣
የሴቶችን የውሳኔ ሰጭነት ሚና በማሳደግ ሃብትና ንብረት የማስተዳደር እና በቤታቸው እኩል ውሳኔ
ሰጭነታቸው እንዲረጋገጥ የአባላትን ግንዛቤ ማሳደግ፣
በባልና ሚስት አለመግባባት ንብረታቸውን የሚነጠቁ ሴቶችን ንብረታቸውን እንዲያገኙ በየደረጃው
ካለው የፍትህ አካል ጋር ተቀናጅቶ መስራት፣
በትራንስፖርት እና የገንዘብ እጥረት ምክንያት ፍ/ቤት ቀርበው ተከራክረው ንብረታቸውን ማስመለስ
ላልቻሉ የድሃ ድሃ የሆኑ ሴቶች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣

ግብ 8፡ በማህበሩ አባላት የተደራጀ እንቅስቃሴ የክልላችን ሰላም ለማረጋገጥ ግንባር ቀደም ሚና መወጣት

 ግቡን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራት


ለመላው የማህበሩ አባላት ስለሰላም አስፈላጊነትና ለሴቶች ስላለው ፋይዳ ግንዛቤ መፍጠር፡

27
በየአካባቢው ሰላምን የሚያደፈርሱ እንቅስቃሴዎችን በንቃት የመከታተልና ሰላምን የሚያደፈርሱ
አካላትን በመታገልና በመቃወም እንዲታረሙ መስራት፤
በአደረጃጀታችው በየሰፈራቸው ከወንዶች ጋር በመተባበር አካባቢያቸውን በመጠበቅ ስራ ላይ
እንዲሰማሩ ማድረግ፤
አባላት ስለሰላምና መልካም አስተዳደር ጠቀሜታ ልጆቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን እንዲያስተምሩ
ማድረግ፣

ዓላማ 3. የማህበሩን ሃብትና ንብረት የተደራጀ መረጃ መያዝና ለተባለለት አላማ ማዋል

ግብ 1. የማህበሩን ሃብትና ንብረት ዘመናዊ በሆነ የመረጃ ስርዓት ማደራጀትና በጥራት መጠቀም

 ግቡን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራት


 ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ ወጥ የሆነ የመረጃ መሰብሰቢያ ቅፆችን ማዘጋጀት፣
 የማህበሩን ሃብትና ንብረት ለመመዝገብ የሚያስችል ዳታ ቤዝ ማደራጀት፣
 ቀጣይነት ያለውና ወቅታዊ መረጃ መሰብሰብ፣
 መረጃዎችን በሃርድ እና በሶፍት ኮፒ አደራጅቶ መያዝ፣
 የማህበሩን ሃብትና ንብረት በአግባቡ አደራጅቶ መያዝና ጥቅም ላይ ማዋል (መሬት፣ የከተማ ቦታ፣ ደን፣
የሰብል ምርት፣ ቤት፣ ሆቴልና የመሳሰሉት ንብረቶች)
 የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለሌላቸው የማህበሩ ንብረቶች የባለቤትነት ማረጋገጫ ማሰራት፣
 የማህበሩን የገቢ ማስገኛዎች በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችል የአሰራር መመሪያ ማዘጋጀት እና
መተግበር፣

ግብ 2. የማህበሩን የሃብት አስተዳደር እና አጠቃቀም በዞን ደረጃ 100% እና በወረዳ ደረጃ 50% ኦዲት
ማስደረግ እና የማህበሩን የሃብት አጠቃቀም ስርአት ማሻሻል

 ግቡን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራት


 ካሉን ወረዳወች 50% እና 100% ዞኖችን በአመት አንድ ጊዜ የማህበሩ ሂሳብ አያያዝ፣ የንብረት
አጠቃቀም እና የህገ-ደንብ አተገባበር ኦዲት እንዲያደርጉ ማድረግ፣
 በየደረጃው በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት ያልተመለሱና ያልተወራረዱ ሰነዶች ወደ ክልል ፋይናንስ
እንዲወራረዱ/ገቢ እንዲደረጉ ማድረግ፣
 ለሃብት ብክነትና ጉድለት የሚዳርጉ አሰራሮችን በመለየት ክፍተቶችን መሙላት፣
 ስለሃብት አያያዝና አስተዳደር ለማህበሩ አመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣
 ኦዲት ስርኣቱን ለማቀላጠፍ በየደረጃው ካሉት ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ተቋማት ጋር በቅንጅት
መስራት፣
28
ዓላማ 4፡- የማህበሩን የህዝብ ግንኙነት ስራ በማጠናከር የማህበሩን ገጽታ መገንባት፣

ግብ 1. የማህበሩን የህዝብ ግንኙነት ስራ በማሻሻል ተደራሽነቱን ማስፋት

 ግቡን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራት


 ማህበሩ የሚሰራቸውን የአባላትን እና የማህበረሰቡን የንቅናቄ ስራወች በህዝብ ግንኙነት ስራወች ማጀብ
 ማህበሩ የሰራቸዉና ያስመዘገባቸዉ ዉጤቶች ላይ በማህበሩ አመራር መግለጫ መስጠትና በሚዲያ እንዲተላለፉ
ማድረግ፣
 የማህበሩን መልካም ተሞክሮዎች ለማስተላለፍ የህዝብ ግንኙነት መድረኮችን መፍጠር/ማመቻቸት፣ የሚዲያ ሽፋን
እንዲያገኝ ማድረግ፣
 በየደረጃው በሚገኙት የማህበሩ ጽ/ቤቶች ያለው የስራ እንቅስቃሴ በህዝብ ግንኙነት እንዲታጀብ ማድረግ፣
 ምርጥ ተሞክሮዎችን አደራጅቶ ለሁሉም አካባቢዎች እንዲደርስ ማድረግ፣
 የማህበሩ መልካም ተሞክሮዎች በልዩ ልዩ ሚዲያዎች እንዲተላላፍ ማድረግ፣
 የማህበሩን ድህረ-ገፅ ማልማት እና ማህበሩ ያስመዘገባቸዉን መልካም ዉጤቶች በማህበሩ ድህረ ገጽ እንዲወጡ
ማድረግ፣
 የማህበሩን የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች በአግባቡ ማልማት እና ለህዝብ ተደራሽ ማድረግ፣
 በየደረጃው ባሉት የማህበሩ ጽ/ቤቶች የሚከናወኑ ተግባራት እና መልካም ተሞክሮዎች በአካባቢው ያሉ የተለያዩ
የማህበረሰብ ሚዲያዎችን በመጠቀም ለህዝብ እንዲደርሱ ማድረግ፣ አፈፃፀማቸውን መከታተልና መደገፍ፣
 በምስልና በፎቶ ግራፍ መረጃዎችን አደራጅቶ መያዝ፣
 የአባላትን እና የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ በራሪ ፅሁፎችን፣ ብሮሸር እና
ቡክሌቶችን እያዘጋጁ ማሰራጨት፣

7 እቅዱን ለመፈጸም የምንከተላቸዉ ዋና ዋና አቅጣጫዎች

 ስራችን ቁልፍ ተግባሩን መሰረት በማድረግ በተደራጀ በተደራጀ አግባብ መፈፀም፣

 ሁሉም አመራርና አባላችን ወደ ስራ በማስገባት አቅሙ የሚገነባበት እና ብቃት ያላቸው ሰዎች


የምንለይበት፤ ተደግፎ መምራትና ከድክመት መውጣት ያልቻሉትን የምናሸጋሽግበት፤ በተቆጠረ ተግባር
የተቆጠረ ውጤት ይዘን የምንመዝንበት ሁኔታ በመፍጠር የመዋቅርና፤ የአመራራችንን ብቃትና አቅም
ማሳደግ፤
 ከእያንዳንዱ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚገኝ በጎ ትምህርት በማስፋት ስኬትና ድክመት ለመማር የሚያስችል
የውድድር መንፈስ በማሳደግ ተቀራራቢ የማስፈጸም አቅም እንዲፈጠር በማድረግ አቅም መጨመር
 የ 2012 ዓ.ም እቅድ በየደረጃው ለመዋቅሩ ኦረንቴሽን በመስጠት መግባባት ላይ በመድረስ እና እቅዱ በጊዜ
ሰሌዳ በመከፋፈል ተግባራዊነቱን ለማረጋገጥ የድጋፍና ክትትል ቡድን በማዋቀር በየደረጃው

29
ሜትሮፖሊታንት ከተሞችን እና ወረዳወችን በመከፋፈል ወርዶ ችግር ፈቺ ድጋፍ በማድረግ የማገዝ እና
የማብቃት አቅጣጫ መከተል፣
 ማንኛውም የማህበሩ ገንዘብ (ገቢዎች) ከኪራይ ሰብሳቢነት ነጻ በሆነ መልኩ በደረሰኝ ብቻ እንዲሰበሰብ
የማድረግ አቅጣጫ በመከተል ግልጽ አሰራር ፣ለመቆጣጠር እና ለኦዲት ምቹ የሆነ፣ የማህበሩ አባላት
በማህበሩ የጀመሩት አመኔታ የማሳደር ስራ አጠናክሮ መቀጠል ይሆናል፡
 የማህበራችን አባላት ጊዜና ጉልበት በመቆጠብ ጊዜያቸውና ጉልበታቸውን ኢኮኖሚያዊ ዋጋ ባላቸው
ስራዎች ላይ እንዲያሳልፉ የሚያግዙ ተስማሚ ቴክኖሎጂ ጠቀሜታዎችን ለማስተዋወቅ ከሚመለከታቸው
አካላት ጋር በቅንጅት መስራት
 የተለያዩ ማህበራዊ ጎጂ ልማዶችን እና ድርጊቶች በሴቶች ላይ የሚደርሱ የሃይል ጥቃቶች የሴቶችን
ተሳትፎና ተጠቃሚነት ሊጎዱ የሚችሉ የወንዶች የበላይነት እና የሴቶች የበታችነት አስተሳሰቦችን፣ ኪራይ
ሰብሳቢነት አመለካከቶችን በተጠናከረ መልኩ መታገል
 ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስትራቴጂዎች በመንደፍ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን አጠናክረን መቀጠል፡፡
 በ 2012 ዓ.ም አቅም በፈቀደ መጠን በማቴርያል (የስቴሽነሪ፣ ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ኮምፒይተር እና
የመሳሰሉት) በጎደሉት በሰው ሃይል የሟሟላት ፣የአቅም ክፍተት ለመሙላት ስልጠና የመስጠት እና
በአመለካከት ያለው ክፍተት የመሙላት ስራ ትኩረቱ ሜትሮፖሊታንት ከተሞች እና ወረዳወች ላይ
የማድረግ አቅጣጫ በመከተል የተሻለ ስራ መስራት፤

 የሴቶችን የልማት ቡድን አደረጃጃት ለስራዎችችን ማሰለጫ ዋና መሳሪያ አድርጎ መጠቀም እና በተግባር
የማህበሩ የመጨረሻ ተቋም ማድረግ፣
 በየደረጃው ያለውን የማህበሩን አመራር አቅም መገንባት እና የሰው ሃይል ልማት ላይ ትኩረት
ማድረግ፣
 ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በትብብርና በቅንጅት መስራት፣
 የንቅናቄና የተሳትፎ መድረኮች ለአባላት ንቅናቄ መፍጠሪያ ዋና አቅም አድርጎ መዉሰድ
 ስራዎቻችን በህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራዎች ማጀብ፣

8 የሚያጋጥሙ ችግሮችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች

8.1 የሚያጋጥሙ ችግሮች

ዞንና ወረዳ ላይ መነሻ እቅዱን መሰረት ያደረገ ጥራት ያለው ከባቢያዊ እቅድ አለማቀድ፣
ዋናዉን ቁልፍ ተግባር ትቶ በጥቃቅን ስራዎች ብቻ መባዘን፣
በየደረጃው ያለው የማህበሩ አመራር ለስራው እኩል ትኩረት አለመስጠት፣

30
በዝግጅት ምዕራፍ ወቅት የሚፈጠሩ መድረኮች የመጣውን የአመለካከት ለውጥ ሳይሆን የመድረኮችን
መጠናቀቅ እንደ ግብ መውሰድና የተፈጠሩትን ምቹ ሁኔታዎች በብቃት አለመጠቀም፣
በየደረጃዉ ያሉ አመራሮች በክልሉ የግምገማ አቅጣጫ መሰረት በአግባቡ ገምግሞ የሚወሰድን
ትምህርት ወስዶ ወደ ተግባር አለመቀየር፣
የአመራር በየጊዜው መቀያር እና ለስራው አዲስ መሆን በተለይ ወረዳ ላይ፤
የማህበሩ አመራሮች በተለይም ስራዉ ያለበት ወረዳ ላይ አመራሩ ትርፍ ጊዜዉን ለማህበሩ
አለመስጠት የተነሳሽነትና የቁርጠኝነት ችግሮች፤
በተፈለገዉ መንገድ የአባላት ገቢ ባለመሰብሰቡ ለተግባራት ማከናወኛ የበጀት እጥረት መኖር፣

8.2 የመፍትሄ አቅጣጫ

ፈጻሚን የማዘጋጀቱ ስራ መለካት ያለበት በአመለካከት የተፈጠረን ዝግጁነት መሆን እንዳለበት፤


በእያንዳንዱ እርከን የሚካሄድ ግምገማ ነክ ስልጠና በዝርዝር ከተገመገመና የአመለካከት ለውጥ
ማምጣቱ ከተረጋገጠ ብቻ ወደ ቀጣዩ መድረክ መግባት ፤
የወቅታዊ ስራን ከማህበሩ ስራ ጋር በማቀናጀት እንዲፈጸም በማድረግ ስራን ቆጥሮ ሰጥቶ ቆጥሮ
በመቀበል ወረዳዎችን በተገቢዉ መንገድ እየደገፉ በተገቢዉ መንገድ የማይመሩትን አመራሮች እየለዩ
ከሚመለከተዉ አካል ጋር በመሆን በሚሰሩ ሴቶች መቀየር
አዳዲስ አመራሮችን እየለዩ ትኩረት ሰጥቶ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ በየደረጃው ማብቃት፣
የአባላትንና የልዩ ልዩ ገቢን በወቅቱ በመሰብሰብ የገቢ አቅምን ማሳደግ፣

9 የክትትልና ድጋፍ አግባብ

የክትትል እና ድጋፍ አግባባ የደርሶ መልስ ሳይሆን ችግሮችን በለየ እና በተጨባጭ ተግባሩ ያለበትን ሁኔታ
በመገምገም እና አቅጣጫ በማሳየት ሲሆን ክትትሉም በአካል፣ በግብረ-መልስ፣ በቸክሊስት፣በስልጠና
እንዲሁም ተግባሩን መሰረት ያደረገ አጫጭር ግምገማዎችን በማድረግ አቅጣጫዎችን በማሳየት የሚከናዎን
ይሆናል፡፡

በዚህም መሰረት ፣

በክልል ደረጃ የሚገኘዉ አመራር ዞኖችን፤ በዞን ደረጃ የሚገኘዉ አመራር ወረዳዎችን ተከፋፍሎ
ይደግፋል፤ ከሪፖርት ባለፈ በየ እሩብ አመቱ እየተመቻቸ እስከ ቀበሌ ድረስ በአካል ሱፐርቪዥንና
ድጋፍ ይደረጋል፣ በተግባር የተገኙትን ምርጥ ተሞክሮዎችን ወደ ሌሎች የማስፋት ስራ ይሰራል፣
በክልል ደረጃ ወቅታዊ ተግባራትን መሰረት ያደረገ ቸክሊስት በየወሩ እና በየሩብ ዓመቱ እየተዘጋጀ
ለዞኖች ይላካል፣ የስራ አፈፃፀሙን መሰረት ያደረገ ግብረ-መልስ በየሩብ ዓመቱ በክልል ባለሙያዎች
እየተዘጋጀ ለዞኖች ይላካል፣
31
የክልል የማህበሩ አመራር እና ባለሙያዎች ዞኖችን በመከፋፈል አፈፃፀማቸውን ለማቀራረብ
የሚያስችል ተከታታይ የሆነ የአካል ድጋፍ ይደረጋል፤
ሌሎች ተቋማት የማህበሩን አደረጃጀት በአግባቡ መጠቀማቸዉ በየጊዜዉ ይገመገማል፣
የክልሉ ስራ አስፈጻሚዎች ዞኖችን ተከፋፍለዉ የአመራር ድጋፍ በመስጠት በየሩብ አመቱ
ይገመግማሉ ግብረመልስ ለዞን ይሰጣሉ፣
የክልል ባለሙያዎች የተደራጀ መረጃን መሰረት ያደረገ የስልክ እና የአካል ድጋፍ ለዞኖች እና ለተመረጡ
ወረዳዎች ይደረጋል፣
የፕሮጀክት እና የመደበኛ ስራዎችን በማቀናጀት በተለይ ፕሮጀክቶች የሚፈፀሙባቸው ወረዳዎች
ግንባር ቀደም እንዲሆኑ ትኩረት ይደረጋል፤
ዞኖች የዋና ዋና ተግባራትን አጭር ሪፖርት እንደ አስፈላጊነቱ በየሳምንቱ፣ በየሁለት ሳምንቱ እና
በየወሩ እንዲልኩ ይደረጋል፤
በየ 3 ወሩ በማህበሩ በሪፖርት ፎርማቱ መሰረት የተደራጀ ሪፖርት ለክልል ይልካሉ፣ የክልል አመራርም
በዚህ ላይ ተመስርቶ ግብረ መልስ ይሰጣል፣
በየሩብ አመቱ አጠቃላይ ስራዉ በክልል ደረጃ የዞን አመራሮች ባሉበት ይገመገማል፣
የማህበሩ የሪፖርት ግንኙነት መዋቅራዊ አደረጃጃቱን መሰረት በማድረግ ከቀበሌ ጀምሮ የሚደረግ
ሲሆን ይህም አንዱ የግምገማ ተግባር ይሆናል።
10 የተግባራት ማስፈፀሚያ የድርጊት መርሃ ግብር
ከላይ የታቀዱት አላማ እና ግቦች በሶስት ምዕራፎች ማለትም በዝግጅት ምዕራፍ፣ በተግባር ምዕራፍ እና
ማጠቃለያ ምዕራፍ ተከፋፍለው የሚፈፀሙ ሲሆን ዝርዝር የድርጊት መርሃ ግብሩ አባሪ በተደረገው ሰንጠረዥ
በየሩብ ዓመቱ ተከፋፍሎ ታቅዷል፡፡
11 ዕቅዱን ለመፈፀም የሚስፈልግ በጀት
በበጀት ዓመቱ ለመፈፀም የታቀዱ ተግባራትን ወቅቱን ጠብቆ ለመፈፀም በጀት እና የሰው ሃይል ወሳኝ
ግብአቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም ማህበሩ ከላይ የተቀመጡትን አላማ እና ግቦች ለማሳካት የሚያስፈልገው
በጀት እንደሚከተለው ተቀምጧል፡፡

32
የክልልና ዞን የመደበኛ በጀት ወጪ እቅድ /2011/

ተ.ቁ የሂሳብ መደብ የበጀት አርዕስት የተፈቀደ በጀት ምርመራ

1 51100-00-00 የክልል ሰራተኞች ደመወዝ 930,996.00

የዞንና ከተማ/አስ/ሰራተኞች ደመወዝ 714,000.00

2 51200-00-00 ጡረታ 11% የክልል 10,2410.00

ጡረታ 11% ዞንና ከተ/አስ 78,540.00

3 51202-00-00 የቤትና የወንበር አበልና ሌሎች 80,000.00


ጥቅማጥቅሞች

4 51502-00-00 ነዳጅና ቅባት 70,000.00

5 51601-00-00 ለጽህፈት መሳሪያ 150,000.00

6 51704-00-00 ለጽዳት መሳሪያ 10,000.00

7 51705-00-00 ደንብ ልብስ 25,000.00

8 51301-00-00 ለኦዲት አገልግሎት 25,000.00

9 51303-00-00 የባንክ ቸክ ግዥ 500.00

10 51402-00-00 ህትመት 200,000.00

11 51403-00-00 ፎቶኮፒና ጽህፈት 1,000.00

12 51404-00-00 ለሚዲያና ዶክመንቴሽን 50,000.00

13 51405-00-00 ስልክ ፖስታ 70,000.00

14 51406-00-00 ዉሃና መብራት 8,000.00

15 51407-00-00 ለመኪና ቦሎ 6,000.00

16 51408-00-00 ኢንሹራንሽ 40,000.00

17 51410-00-00 ጭነት 4,000.00

18 51411-00-00 መስተንግዶ 30,000.00

33
19 51501-00-00 ለዉሎ አበል 30,000.00

20 51702-00-00 አዳራሽ ኪራይ 5,000.00

21 51706-00-00 ማበረታቻ 10,000.00

22 51707-00-00 ድጋፍ 10,000.00

23 51802-00-00 ተሸከርካሪ ጥገናና መኪና ጎማ ግዥ 250,000.00

24 51803-00-00 ቢሮ ዕድሳት 300,000.00

25 51804-00-00 የቢሮ ቁሳቁስ ጥገና 7,000.00

26 51805-00-00 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ጥገና 8,000.00

27 51708-00-00 ቋሚ ዕቃ ግዥ 50,000.00

28 51807-00-00 ሌሎች ወጪወች 20,000.00

29 ለዞኖች ስራማስኬጃ በቀመሩ መሰረት


የሚላክ
1,871,681.00

30 የክልል ደመወዝና ስራ ማስኬጃ ድምር 2,157,906.00

31 የዞንና ከተማ አስተዳደር ደመወዘወና ስራ ማስኬጃ 2,664,221

32 ጠቅላላ ድምር 4,972,127.00

34

You might also like