Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 48

የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ

መጋቢት 2006 ዓ.ም


አዲስ አበባ
ማውጫ

1. መግቢያ.........................................................................................................................4

2. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አስፈላጊነት.............................................................5

3. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዓላማ.....................................................................6


 3.1. አጠቃላይ አላማ................................................................................................................. 6

 3.2. ዝርዝር ዓላማዎች.................................................................................................................. 6

4. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት ድጋፍ የማስተግበሪያ ስልቶች........................7


 4.1. የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ /KAIZEN/ አቅም ግንባታ.................................................................9
4.1.1. የጥራትና ምርታማነት ድጋፍ ማዕቀፍ የሚያካትታቸው የብቃት አሀዶችና ዝርዝር የስራ ተግባራት............9
4.1.2. የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ/ ድጋፍ ተግባራዊ ስናደርግ መከተል ያለብን የአተገባበር ሂደት...................12
4.1.3. የጥራትና ምርታማነት ድጋፍ የክፍተት ዳሰሳ አካሄድ.............................................................................32
4.1.4. ቀጣይነት ያለው የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ሰሌዳ /KAIZEN BOARD/......................................13

 4.2. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ.............................................................................................. 19


4.2.1. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ድጋፍ ከብቃት አሀዶችና ዝርዝር የስራ ተግባራት ጋር የማስተሳሰር ሂደት....19
4.2.2. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ አተገባበር ስልት......................................................................................21
4.2.3. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ድጋፍ አማራጮች....................................................................................23
4.2.4. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ሂደቶች.................................................................................................23
 የምርጥ ተሞክሮ መለየት.................................................................................................................23
 አሁን ያለበትን ደረጃ ማወቅ.............................................................................................................24
4.2.5. የቴክኒካል ክህሎት የክፍተት ዳሰሳ መለያ አካሄድ....................................Error! Bookmark not defined.

 4.3. የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ.................................................................................................. 25


4.3.1. የቴክኖሎጂ የአሰራር ሂደቶች............................................................................................................25
4.3.2. የእሴት ሰንሰለት..............................................................................................................................25
4.3.3. የቴክኖሎጂን ክፍተት መለየት...........................................................................................................26

 ክፍተቱን ለመሙላት የሚወሰዱ አካሄዶች................................................................................................ 26


 አዋጭነት.......................................................................................................................................26
ምርታማነት................................................................................................................................26
ጥራት.........................................................................................................................................27
ጉልበት በስፋት መጠቀም..............................................................................................................27
ዋጋ............................................................................................................................................27
4.3.4. ምርጡን ቴክኖሎጂ መለየት.............................................................................................................27
 ቴክኖሎጂን ማቀብ (ማከማቸት)......................................................................................................28
 ንድፍ ማዘጋጀት..............................................................................................................................28
 ናሙና ማዘጋጀት.............................................................................................................................29
ናሙና መፈተሽ..............................................................................................................................29
4.3.5. የተፈተሸውን ቴክኖሎጂ ማሸጋገር....................................................................................................29
 የአብዢዎችን አቅም ክፍተት መለየት...............................................................................................30
 አብዢዎችን ማብቃት.....................................................................................................................30

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 2
 ድጋፍ በመስጠት የብቃቱን ውጤት መገምገም...................................................................................30
 ገበያ ማፈላለግ...............................................................................................................................30
 4.4. የኢንተርፕርነርሽፕ ክህሎትና ዕውቀት አቅም ግንባታ..............................................................15
4.4.1. የኢንተርፕርነርሽፕ ድጋፍ ማዕቀፍ የሚያካትታቸው የብቃት አሀዶችና ዝርዝር የስራ ተግባራት..................15
4.4.2. የኢንተርፕሪነርሽፕ ድጋፍ ማዕቀፍ የክፍተት ዳሰሳ ጥናት አካሄድ.............Error! Bookmark not defined.

5. ተቀፅላዎች...................................................................................................................36
 የሽያጭ መዝገብ /sales Journal/............................................................................................................. 46

 የሂሳብ ቋት ማሳያ /general ledger/......................................................................................................... 47

 ረዳት ቋት/Subsdiary Ledger/............................................................................................................. 47

 የሂሳብ አያያዝ ኡደት............................................................................................................................... 51

1. መግቢያ

አሁን ያለንበት ዘመን አለምአቀፍ የኢኮኖሚ ትስስር የሰፈነበት ሲሆን ኢትዮጵያም የዚሁ ትስስር አካል ናት፡፡ ከዚህ ጋር
ተያይዞ የሚከሰተው አለምአቀፍ የገበያ ውድድር ደግሞ ድንበር ዘለል ከመሆኑ የተነሳ በመጪው ጊዜ የገበያው

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 3
ባለቤት የሚሆኑት በሂደቱ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው አምራቾችና አገልገሎት ሰጪ ተቋማት ናቸው፡፡ ማንኛውም
ተቋም ከተወዳዳሪዎቹ ልቆ እንዲገኝ ከሚያደርጉት ነገሮች ዋነኞቹ በቂ ቴክኒካል ክህሎትና የኢንተርፕሪነርሽፕ ባህሪይ
የተላበሰ የሰው ሐይል እንዲሁም ምርጥ ቴክኖሎጂና የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ አሰራር ሲኖር ነው፡፡ ይህ አሰራር
ከሌለ በስተቀር ማንኛውም አይነት ግብአት፣ መሰረተ ልማትና ዘመናዊ አደረጃጀት ቢኖርም ለትርፋማነትና ለተወዳዳሪነት
ሊያበቁ እንደማይችሉ የተለያዩ የጥናት ውጤቶች ያመለክታሉ።

ከዚሁ ግንዛቤ በመነሳት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ ተቀርጾ ወደ ስራ ተገብቷል። በዚህ
ስትራቴጂ ላይ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማልማት ከተቀመጡት የድጋፍ ማእቀፎች ውስጥ አንዱ
ለኢንተርፕራይዞቹ ብቃት ያለው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት መስጠት ነው። ይህ አገልግሎት የጥቃቅንና
አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ችግር በፍላጎት ላይ ተመስርቶ የለየና የተሟላ መረጃ የማደራጀትና የመስጠት፣ ስልጠናና
ምክር፣ የቴክኖሎጂ ልማት፣ ግብይት፣ ምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስተላለፍን የሚያካትት ድጋፍ ነው፡፡

በመሆኑም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪነታቸውንና ምርታማነታቸውን አሁን ካለበት ደረጃ በተሻለ
ሁኔታ ለማሳደግ እንዲቻል ይህ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት ድጋፍ ማስተግበሪያ
መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

2. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አስፈላጊነት


በአሁኑ ጊዜ አገራችን የግብርና መር የኢኮኖሚ ስርአት በመከተል ላይ የምትገኝ ቢሆንም ሩቅ በማይባል
ጊዜ ደግሞ የኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ የመሪነቱን ሚና እንደሚይዝ ታሳቢ ተደርጎ እንቅስቃሴ
በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ አገሪቱ ባላት ወቅታዊ የሆነ የኢኮኖሚ ነባራዊ ሁኔታ ደግሞ የኢንዱስትሪው ክፍለ
ኢኮኖሚ እንዲስፋፋ ትኩረት ተደርጎ መሰራት ያለበት በጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንዱስትሪዎች/ኢንተርፕራይዞች ላይ እንደሆነ የአገሪቱ የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ላይ በግልፅ
ሰፍሯል፡፡
በዚህም መሰረት መንግስት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግና
በቀጣይነትም ወደ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪ እንዲያድጉ በማድረግ የአገሪቱ የኢንዱስትሪ ክፍለ
ኢኮኖሚ እንዲጠናከርና እንዲስፋፋ ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም የኢንዱስትሪ ክፍለ
ኢኮኖሚው የመሪነቱን ሚና ውጤታማ በሆነ መልኩ እንደሚወጣ ይጠበቃል፡፡ ለጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንዱስትሪዎች ከሚደረጉትም ድጋፎች መካከል አንዱ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር
አገልግሎት ድጋፍ ነው፡፡
የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት ድጋፍ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ችግር
የለየና በፍላጎት ላይ የተመሠረተ የተሟላ መረጃ የማደራጀትና የመስጠት፣ ሥልጠናና ምክር፣ የቴክኖሎጂ ልማት፣
ግብይት፣ ምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስተላለፍን የሚያካትት ድጋፍ ነው፡፡ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 4
በኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂው በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የኢንተርፕራይዞችን ችግሮች በጥናት ላይ ተመስርቶ በቅድሚያ
በመለየት ችግር ፈቺ የሆነ መፍትሄ በሚሰጥ መልኩ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ይህም
አገልግሎት በአራት ማዕቀፎች እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን እነዚህም የካይዘን/የጥራትና ምርታማነት
ማሻሻያ/ ድጋፍ፣ የቴክኒካል ክህሎት ድጋፍ፣ የቴክኖሎጂ ድጋፍና የኢንተርፕርነርሽፕ ድጋፍ ናቸው፡፡

የካይዘን/የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ/ ድጋፍ የሚሰጠው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ብክነትን


በማስወገድ፣ወጪን በመቀነስና የስራ ቦታን አመቺ በማድረግ ቀጣይነት ያለው የምርታማነትና የጥራት
መሻሻል እንዲያመጡ ለማስቻል ነው፡፡ የቴክኒካል ክህሎት ድጋፍ የሚደረገው የጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በፍጥነትና በየጊዜው ከሚፈጠሩ የቴክኖሎጂና የገበያ መለዋወጥ ምክንያት
የሚያጋጥሟቸውን የቴክኒካል ክህሎት ክፍተቶች ለመሙላት ነው፡፡ የቴክኖሎጂ ድጋፍ የሚደረገው ደግሞ
ለአገራችን ነባራዊ ሁኔታ የሚስማማውንና ተመርጦ መቶ ፐርሰንት የተቀዳውን ቴክኖሎጂ በመውሰድ
ውጤታማ የቴክኖሎጂ አብዢዎች እንዲሆኑና በቴክኖሎጂ ሽግግር ስራ ብቁ ተዋናኝ እንዲሆኑ ለማስቻል
ነው፡፡ የኢንተርፕርነርሽፕ አገልግሎት ድጋፍ የሚሰጠው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የዘመናዊ
ንግድ አሰራርን እንዲተገብሩና ተወዳዳሪ ሆነው እንዲቆዩ ለማድረግ ሲሆን በተጨማሪም ዘርፉ በከተሞች
በዋነኝነት የስራ እድልን በመፍጠር እነዚህ ኢንተርፕራይዞች ለኢንዱስትሪ ልማት መሰረት መጣል
እንዲችሉ ነው፡፡

3. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዓላማ

3.1. አጠቃላይ አላማ

ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት


በመስጠት በገበያ ውስጥ በአገልግሎት/ በምርት ጥራት፣ በቴክኖሎጂ፣ በምርታማነት፣ በአሰራርና በዋጋ ተወዳዳሪና
ትርፋማ እንዲሆኑ፤ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ የላቀ ለውጥ እንዲያመጡ፣ ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩና
ገቢያቸው እንዲሻሻል ማድረግ፡፡

3.2. ዝርዝር ዓላማዎች

 የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞች የመስሪያ ቦታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ማስቻል፣

 የኢንተርፕራይዞችን የምርት ጊዜ ማሻሻልና ምርታማነታቸውን ማሳደግ፣

 የማያቋርጥ የምርትንና አገልግሎት የአመራረት ኡደትን ማሻሻል፣

 የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን የምርት ወጪን በመቀነስና ጥራትን በመጨመር ትርፋማነታቸውን


ማሳደግና የደንበኛን ፍላጎት ሙሉ ለሙሉ ማርካት

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 5
 ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ክፍተት ከብቃት አሀድ ጋር
በማዛመድ ተግባር ላይ እንዲያውሉ በማድረግ የምርታማነታቸውንና የተወዳዳሪነታቸውን አቅም
ማሳደግ፣

 ከአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ የቴክኖሎጂ መረጣና መቶ ፐርሰንት የቴክኖሎጂ መቅዳት


ስራ በመስራት ለጥ/አ/ኢንተርፕራይዞች ማሸጋገር

 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አንቀሳቃሾች የኢንተርፕሪነሪያል አመለካከታቸውን፣ እውቀታቸውንና


ክህሎታቸውን መገንባት

 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ ስርዓትን እንዲተገብሩ በማድረግ


ትርፋማነታቸውን እንዲጨምሩ ማስቻል

 ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የገበያ ልማት እውቀትና ክህሎት እንዲያዳብሩ በማገዝ በገበያ ላይ በምርት
ጥራት፣ ዋጋና አቅርቦት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት መርሆዎች


 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች መፈልፈያና
የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከላት እንዲሆኑ ማድረግ፣

 በገበያ ፍላጎት የሚመራ፣ የተቀናጀና የተዋሃደ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት መስጠት፣

 ግልጽነት፣ተጠያቂነትና ታማኝነት የተላበሰ አገልግሎት መስጠት፣

 የኢንተርፕራይዞች እድገትና ጥቅም የእኔም ጥቅም ነው ብሎ በማመን መንቀሳቀስ፣

 ለነባርና ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ቅድሚያ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት መሰጠት እንዳለበት


አምኖ መንቀሳቀስ፣

 የቴክኖሎጂ አቅምን መገንባት ለኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ መሣሪያ መሆኑን አምኖ መተግበር፣

4. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት ድጋፍ የማስተግበሪያ ስልቶች


“የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ ማለት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ችግር በፍላጎት ላይ
ተመስርቶ የለየና የተሟላ መረጃ የማደራጀትና የመስጠት፣ ስልጠናና ምክር፣ የቴክኖሎጂ ልማት፣ ግብይት፣ምርጥ
ተሞክሮ ቅመራና ማስተላለፍን የሚያካትት ድጋፍ ነው” የማስተላለፊያ ስልቶቹም፤

 የጥራትና ምርታማነት አቅም ግንባታ

 የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ

 የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 6
 የኢንተርፕርነርሽፕ አቅም ግንባታ

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 7
4.1. የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ /KAIZEN/ አቅም ግንባታ
የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ /KAIZEN/ አቅም ግንባታ ማለት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በእለት
ተእለት የስራ እንቅስቃሴዎቻቸው የማያቋርጥ የምርታማነትና የጥራት ለውጦች እንዲያመጡ የሚያስችላቸው
የአቅም ግንባታ ስራ ማለት ነው፡፡

የካይዘን (KAIZEN) አስተሳሰብ የተጀመረውም ሆነ በስፋት ስራ ላይ የዋለው በጃፓን ሲሆን የተገነባውም ከሁለት
የጃፓን ቃላት ነው፡፡ እነርሱም ካይ (KAI) እና ዘን (ZEN) ናቸው፡፡ ካይ ማለት ለውጥ ማለት ሲሆን ዘን ማለት ደግሞ
መልካም (ጥሩ) ማለት ነው፡፡ አጠቃላይ የቃሉ ፍቺም የማያቋርጥ መልካም ለውጥ በሚለው የአማርኛው ቃል ሊመነዘር
ይችላል፡፡ ይህ የማያቋርጥ መልካም ለውጥ በአንድ ድርጅት/ተቋም ውስጥ በሚከናወነው የእለት ተእለት የስራ
እንቅስቃሴ በምርቱና በአገልግሎቱ የሚታይ ይሆናል፡፡

ይህን በጃፓን ለውጥ ያመጣ የካይዘን ተሞክሮ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በተዛመደ መልኩ በጥቃቅንና
አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በድጋፍ መልክ በመስጠት ሲተገበር ኢንተርፕራይዞቹ ሰፊ የስራ እድል
የሚፈጠርባቸው፣ የልማታዊ ባለሀብት መፈልፈያ የሚሆንባቸው፣ አሁን ያለባቸውን ችግር አስወግደው
ለተወዳዳሪነት የሚበቁበት አንዱ ውጤታማ የሆነ የአሰራር ስርአት ይሆናል፡፡

4.1.1. የጥራትና ምርታማነት ድጋፍ ማዕቀፍ የሚያካትታቸው የብቃት አሀዶችና ዝርዝር የስራ
ተግባራት
የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ድጋፍ አገልግሎት መነሻ የሚያደርገው በአገሪቱ የሙያ ደረጃዎች ላይ
በተቀመጡት የካይዘን /የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ/ የብቃት አሀዶችና በነዚህ ስር ባሉ ዝርዝር ስራዎች
ላይ ነው፡፡

ደረጃ 1 (Level I): የአምስቱን “ማ” ዎችን የአሰራር ስርአቶች መተግበር (Apply 5s procedures)

 የጥራት ስርአት ግንዛቤን ማጎልበት (Develop understanding of quality system)

 የሚፈለጉትን እቃዎች ከማይፈለጉት ማጣራት (Sort needed items from unneeded items)

 የተለዩትን እቃዎች በአግባቡ ማስቀመጥ (Set workplace in order)

 የስራ ቦታን ማፅዳት (Shine work area)

 ከላይ የተከናወኑትን ተግባራት ማስቀጠል (Standardize activities)

 አምስቱ “ማ” ዎችን ስርአት አድርጎ ማዝለቅ (Sustain 5S system)

ደረጃ 2 (Level II) ፡ ቀጣይነት ያለውን የማሻሻያ ሂደቶችን መተግበር (Apply continuous
improvement processes (KAIZEN)

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 8
 በእለታዊ የስራ ተግባራት የጥራት ስርአት ተፈላጊውን እርካታ ማምጣት (Satisfy quality
system requirements in daily work)

 ለውጤታማ ተግባር መልካም አጋጣሚዎችን መተንተን (Analyze opportunities for


corrective and/or optimization action)

 ለውጤታማ ተግባር መልካም አጋጣሚዎች ስራ ላይ እንዲውሉ ሀሳብ ማቅረብ (Recommend


corrective and/or optimization actions)

 መልካም አጋጣሚዎች ስራ ላይ በሚውሉበት እንቅስቃሴ ላይ ተሳትፎ ማድረግ (Participate in


the implementation of recommended actions)

 ቀጣይነት ያለውን የማሻሻያ ስትራቴጂዎችን የማጎልበት ስራ ላይ ተሳትፎ ማድረግ (Participate


in the development of continuous improvement strategies)

ደረጃ 3 (Level III) ፡ የጥራት ስርአትና ቀጣይነት ያለውን የማሻሻያ ሂደቶችን ማስጠበቅ (Maintain
quality system and continuous improvement processes)

 በስራ ቦታ ላይ የጥራት ስርአት መዋቅር መዘርጋትና ማጎልበት (Develop and maintain quality
framework within work area)

 የጥራት ሰነድን በአግባቡ መጠበቅ (Maintain quality documentation)

 ደረጃቸውን የጠበቁ የአሰራር ደንቦችን ተግባራዊ የሚደረጉበትን ሁኔታ ማመቻቸት (Facilitate


the application of standardized procedures)

 በጥራት የአሰራር ስርአቶችና የስራ ማሻሻያ ሂደቶችን ላይ ስልጠና መስጠት (Provide training in
quality systems and improvement processes)

 የስራ አፈፃፀምን መከታተልና መገምገም (Monitor and review performance)

 ቀጣይነት ያለው የስራ ማሻሻያ ሂደትን መገንባት (Build continuous improvement process)

 የስራ ማሻሻያ መልካም እድሎችን ማመቻቸትና መለየት (Facilitate the identification of


improvement opportunities)

 አግባብነት ያላቸውን የጥራት ስርአት ክፍሎቸ መገምገም (Evaluate relevant components of


quality system)

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 9
ደረጃ 4 (Level IV) ፡ ቀጣይነት ያለው የስራ ማሻሻያ ስርአትን መምራት (Manage continuous
improvement system)

 ፕሮግራሞችን፤ስርአትችንና ሂደቶችን መገምገም (Review programs, systems and


processes)

 ቀጣይነት ላለው የስራ ማሻሻያ ስርአት አማራጮችን ማጎልበት (Develop options for
continuous improvement)

 አዳዲስና ውጤታማ የስራ ሂደቶችን መተግበር (Implement innovative processes)

ደረጃ 5 (Level V) ፡ ቀጣይነት ያለው የስራ ማሻሻያ ስርአትን መተግበር (Implement continuous
improvement system)

 ወቅታዊ የሆነ የውሰጥ አሰራር ማሻሻያ ስርአት መለኪያ መዘርጋት (Establish parameters of
current internal improvement system)

 የላቀ ለውጥ የሚያመጣ አሰራር ማሻሻያ ስርአት መለየት (Distinguish breakthrough


improvement processes)

 ቀጣይነት ያለው የስራ ማሻሻያ ተግባርን ማጎልበት (Develop continuous improvement


practice)

 ወቅታዊ የሆነ የውጭ አሰራር ማሻሻያ ስርአት መለኪያ መዘርጋት (Establish parameters of
current external improvement system)

 ቀጣይነት ያለው የእሴት ማሻሻያ ሂደቶችን ለማጎልበት መልካም አጋጣሚዎችን ማሰስ (Explore
opportunities for further development of value stream improvement processes)

 ከማሻሻያ ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣሙ የአሰራር ስርአቶችን መገምገም (Review systems for


compatibility with improvement strategy)

4.1.2. የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ/ ድጋፍ ተግባራዊ ስናደርግ መከተል ያለብን የአተገባበር ሂደት

ውጤታማ የሆነ የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ስርዓትን በኢንተርፕራይዞች ስንተገብር ከዚህ በታች
የተዘረዘሩትን የአተገባበር ሂደቶችን መከተል አለብን፡፡

 ካይዘን ከመተግበሩ በፊት የኢንተርፕራይዙን ነባራዊ ሁኔታ የሚገልፁ መረጃዎችን በፅሁፍ፣


በቁጥር፣ በፎቶ፣በቪዲዮና ነባራዊ የስራ ፍሰትን የሚገልፅ ንድፍ በሚገባ ማዘጋጀትና መያዝ

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 10
ለምሳሌ፡- እያንዳንዱን ምርት ለማምረት የሚፈጅበት ጊዜ በሰዓት፣ የሚያመርተው ምርት ጥራት፣
ያለውን የመስሪያ ቦታ ስፋትና አጠቃቀም፣ የሰራተኞች የስራ ቦታ ደህንነትና ጤንነት፣ ሰራተኞቹ
ምን ያህሉን የስራ ሰዓት እሴት በሚጨምሩ፣ እሴት በማይጨምሩና ብክነት ላይ እንደሚያሳልፉና
ወዘተ መረጃዎችን መያዝ፡፡

 ከመረጃው በመነሳት ዋና ዋና ችግሮችን ከላይ ከተገለፁት ነጥቦች አንጻር መለየትና የችግሩን


መንስኤ መተንተንና ማደራጀት፣

 የተለዩትን ችግሮች በምን ያህል አሁን ካለው በጥራትና ምርታማነት ፍልስፍናና መሳሪያዎች
በመጠቀም ማሻሻል እንደሚቻል ግብ ማስቀመጥ፣

 ለተለዩት ችግሮች መፍቻ/መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉትን መሳሪያዎችና አሰራሮች መምረጥና


ለድርጅቱ በሚሆን መልኩ ማዘጋጀት፣

 የተዘጋጁትን የመፍትሄ እርምጃዎች/መሳሪያዎች ተግባራዊ ለማድረግ ዝርዝር የትግበራ እቅድ


ማዘጋጀት

 የተመረጠውን የመፍትሄ እርምጃ መተግበር፣

 የትግበራውን አፈጻጸም ከተቀመጠው ግብ አንጻር ማወዳደር፤ ይህ ማለት ምን ያህል ሰዓት እንደ


ተሻሻለ፣ በቀን የሚመረተውን ምርት ከበፊቱ ምን ያህል እንደጨመረ፣ ምን ያህል የማምረቻ
ወጪን እንደቀነሰ፣ በምርት ጥራት የጨመረ የደንበኛ ብዛት፣ የተገኘን የቦታ ስፋትና
አጠቃቀም፣ጠፍቶ የተገኘ ንብረት፣ የጨመረ የሽያጭና የገቢ መጠን ከበፊቱ አፈጻጸም አንጻር፣
ሰራተኞቹ ምን ያህሉን ሰዓት እሴት በሚጨምር ስራ ላይ እንደሚያሳልፉ፣ የስራ ቦታ ደህንነት
በመጠበቁ የቀነሰ ወጪና ወዘተ…

 ከላይ ከተገለጹት ነጥቦች በመነሳት የተገኘውን ለውጥ/ልዩነት ከበፊቱ አንጻር በማስላት ወደ


ገንዘብ መለወጥ፣

4.1.3. ቀጣይነት ያለው የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ሰሌዳ /KAIZEN BOARD/


የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ/ማትግያ ስርአት ሰሌዳ/KAIZEN BOARD/ የካይዘን ቀጣይነት
ማረጋገጫ ሰሌዳ ሲሆን እያንዳንዱ የኢንተርፕራይዙ ሰራተኛ ብቃቱ እየተገመገመ ያሉበትን የክህሎት
ክፍተት እየታየ የሚሞላበት፣ ምርታማነትን ለማሳደግም ሆነ የአገልግሎት ጥራትን ለማስጠበቅ የማሻሻያ
ሀሳቦች የሚንፀባረቁበት እንዲሁም የተለያዩ ችግሮች ለመፍትሄ የሚቀርቡበትና በተግባር የሚፈተሽበት
የካይዘን ማሻሻያ/ማትጊያ ስርአት ነው፡፡

የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ሰሌዳ /KAIZEN BOARD/

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 11
የሰራተኞች የክህሎት መገምገሚያና ማብቂያ ስኬት

ተ ዝርዝር ክፍ ክፍተት ም
.ቁ ተ ር ጥሩ አፈፃፀም ያሳየ የሰራተኛ ምስል
ስራዎች የለም
ት መ

አለ

ዝርዝር ስራዎች 1 2 3 4 5

የሰራተኛው ስም

ችግር/ሀሳብ የመፍትሄ ሀሳብ

ሀሳብ ሀሳብ
መፍትሄ 1
1 2

አንድ ሳምንት>>> አንድ ሳምንት>>>


ሀሳብ ችግር 1
3
መፍትሄ 2
ችግር 2

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 12
4.2. የኢንተርፕርነርሽፕ ክህሎትና ዕውቀት አቅም ግንባታ

የኢንተርፕርነርሽፕ ክህሎትና ዕውቀት አቅም ግንባታ ማለት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ


ሰራተኞች/አንቀሳቃሾች ከተቀመጠው የሙያ ብቃት አሃድ አንጻር በምርት ዋጋ፣ በምርት ጥራት፣
በትርፋማነት፣በደንበኞች አያያዝ፣በሂሳብ መዝገብ አያያዝ፣በስራ ፈጠራና ተነሳሽነት እንዲሁም
በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ተወዳዳሪ መሆን ያላስቻሉአቸውን ክፍተቶች በመለየት ክፍተቶቹን ለመሙላት
የሚከናወን የአቅም ግንባታ ስራ ነው፡፡

4.2.1. የኢንተርፕርነርሽፕ ድጋፍ ማዕቀፍ የሚያካትታቸው የብቃት አሀዶችና ዝርዝር የስራ ተግባራት

ደረጃ I: የኢንተርፕርነርሽፕ ግንዛቤ ማጎልበት (Developing Understanding of


Entrepreneurship)

 የኢንተርፕሪነርሽፕ መርሆችን ፣ ፅንሰ ሀሳቦችን እና የፅንሰ ሀሳቡን ይዘት መግለፅና


ማብራራት( Describe and explain the principles, concept and scope of
entrepreneurship)

 ኢንተርፕሪነር እንዴት መሆን እንደሚቻል ማብራራት (Discuss how to become


entrepreneur)

 አንድን ድርጅት እንዴት ማቋቋም ይቻላል (Discuss how to organize an enterprise)

 ድርጅትን እንዴት መምራትና ማንቀሳቀስ ይቻላል (Discuss how to operate an


enterprise)

 የንግድ ስራ እቅድ ማዘጋጀት( Develop one’s own business plan)

ደረጃ II: የንግድ ስራ ተግባርን ማጎልበት (Develop Business Practice)

 የንግድ ስራ መልካም አጋጣሚዎችን መለየት (Identify business opportunity)

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 13
 የንግድ ስራ የግል ክህሎቶችን መለየት (Identify personal business skills)

 የድርጅት ስራ እንቅስቃሴ እቅድ ዝግጅት (Plan for establishment of business operation)

 የድርጅት ስራ እንቅስቃሴ እቅድ አተገባበር (Implement establishment plan)

 የድርጅት ስራ እንቅስቃሴ ትግበራን መገምገም (Review implementation process)

ደረጃ III: የንግድ ስራ ተግባርን ማሻሻል (Improve Business Practice)

 የድርጅት ስራ እንቅስቃሴ መመርመር (Diagnose the business)

 የድርጅት ስራ እንቅስቃሴ ለማሻሻል ምርጥ ተሞክሮዎችን መለየት (Benchmark the business)

 የድርጅቱን የስራ አፈጻጸም ለማሻሻል እቅድ ማዘጋጀት (Develop plans to improve business
performance)

 የግብይትና የማስታወቂያ እቅዶችን ማዘጋጀት (Develop marketing and promotional plans)

 የድርጅታዊ የእድገት እቅድን ማዘጋጀት (Develop business growth plans)

 የተዘጋጁ የተለያዩ እቅዶችን መተግበርና አፈፃፀማቸውን መከታተል (Implement and monitor


plans)

ደረጃ IV: የአነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶችን ስራ መምራትና ማስቀጠል (Manage and Maintain
Small/Medium Business Operations)

 እለታዊ ስራ ለማከናወን አስፈላጊ ነገሮችን መለየት (Identify daily work requirements)

 የስራ አፈፃፀምን መከታተልና መምራት (Monitor and manage work)

 ውጤታማ የሆኑ የስራ ልምዶችን ማጎልበት (Develop effective work habits)

 የፋይናንስ መረጃዎችን መተንተን (Interpret financial information)

 የስራ አፈጻጸምን መገምገም (Evaluate work performance)

ደረጃ V A: የንግድ ስራ ግንኙነት መመስረትና መተግበር (Establish and conduct Business


Relations)

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 14
 ከደንበኛ ጋር ለሚኖር ግንኙነት ስልት መንደፍ (Establish contact with customer)

 የደንበኛን ፍላጎት አጥርቶ መለየትና መገንዘብ (Clarify needs of customer)

 ለደንበኞች አስፈላጊውን መረጃና ምክር መስጠት (Provide information and advice)

 የደንበኞች ጋር ያለውን ግንኙነትን ማሳደግና መጠበቅ (Foster and maintain business


relationships)

ደረጃ V B: ለውጥንና ፈጠራን /ግኝትን/ ማበረታታትና ማጎልበት (Facilitate and Capitalize on


Change and Innovation)

 የአሰራር ለውጦችን ተግባራዊ በማድረግና በማላመድ እቅድ ዝግጅት ላይ ተሳትፎ ማድረግ


(Participate in planning the introduction and facilitation of change)

 አዳዲስና ተለማጭ የሆኑ አሰራሮችና መፍትሄዎችን ማጎልበት (Develop creative and flexible
approaches and solutions)

 በድርጅት እንቅስቃሴ ላይ የሚመጡ ተግዳሮቶችና መልካም አጋጣሚዎችን በአግባቡ መምራት


(Manage emerging challenges and opportunities)

ከላይ በዝርዝር የተገለጹት ድጋፎች ኢንተርፕራይዞች ያሉባችውን ችግሮች በመለየት የኢንተርፕርነርሺፕ


ክህሎት አቅማቸውን መገንባት ያስችላል ተብሎ ይታመናል፡፡ ሆኖም ግን በትክክል የተፈለገው ውጤት
መምጣቱን ለማረጋገጥ በውጤት ተኮር የስልጠና ስርዐቱ መሰረት ከስልጠናና ድጋፍ በኃላ አንቀሳቃሾች
የብቃት ማረጋገጫ ምዘና መውሰድና ብቃታቸው መረጋገጥ አለበት፡፡

እንዲሁም በተሰጠው ድጋፍ ያፈሩት ሀብት ሌላው የድጋፉን ውጤታማነት መለኪያ መሳሪያ በመሆኑ
ከድጋፍ በኋላ ያፈሩትን ሀብት መረጃ መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ የደረጃ ዕድገታቸውም ከዚሁ ጋር ተያይዞ
የሚታይ ጉዳይ ይሆናል፡፡

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾችን የማብቃት ኃላፊነት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት


እንደመሆኑ መጠን የኢንተርፕርነርሽፕ አቅም ግንባታ ስልጠና የሚሰጠው በየሙያው አሰልጣኞች ነው።
ይህንንም ለመተግበር የየሙያው አሰልጣኞች በቅድሚያ የኢንተርፕርነርሽፕ ስልጠናን ከሙያ ደረጃ ጋር
አያይዞ ለማሰልጠን የሚያስችል ብቃታቸው መገንባት ስላለበት በየተቋማቱ የሚገኙ የኢንተርፕርነርሽፕ
አሰልጣኞች ሰፊ ስራ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለዚህም የየተቋማቱ አመራር ፕሮግራም በማውጣትና አስፈላጊውን ግብዐት በሟሟላት


የኢንተርፕርነርሽፕ አሰልጣኞች የሌሎች ሙያ አሰልጣኞችን የሚያበቁበትን ሁኔታ ማመቻቸት
ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህንንም በማድረግ አንቀሳቃሾች ሁሉንም (አራቱንም) ድጋፎች በአንድ አሰልጣኝ

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 15
ማግኘት እንዲችሉ ያደርጋቸዋል። በመሆኑም አሰልጣኙም ሆነ ሰልጣኙ የንግድ ሥራ አመራርን ከሙያው
ጋር አያይዞ በቀላሉ እንዲረዳው ያደርጋል፡፡

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 16
4.3. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ
የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ማለት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በገበያ ላይ ተወዳዳሪ
እንዳይሆኑ የሚያደርጓቸውን የክህሎት ክፍተቶችን ነቅሶ በመለየት እነዚህን ክፍተቶች ሊያስወግድላቸው
የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስራ ነው። የተለየ የቴክኒክ ክህሎት ክፍተት ሳይኖር የክህሎት አቅም ግንባታ
ፕሮግራሞችን ማቀድና ማከናወን እንደ ብክነት ሊቆጠር ይገባል። ሰራተኛው ከፕሮግራሙ ባገኘው
ክህሎት የሚያስመዘግበው ምርታማነት ለአቅም ግንባታው ከዋለው ሀብትና በክህሎት አቅም ግንባታ
ፕሮግራሞች ላይ ለመሳተፍ ከስራ ገበታው በተለየበት ጊዜ ባለማምረቱ ምክንያት ከሚከሰቱት
ወጪዎች/opportunity costs/ እና ሌሎችም ግብአቶች በላይ መሆን ይኖርበታል።

4.3.1. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ድጋፍ ከብቃት አሀዶችና ዝርዝር የስራ ተግባራት ጋር
የማስተሳሰር ሂደት

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን የቴክኒካል ክህሎት ድጋፍ አሰጣጥ በአገልግሎት ተቀባዩ ምርጫ መሰረት
በአገልግሎት ሰጪ ክፍተቶቹ ከተለዩ በኋላ ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ አምስት በተለያዩ ሙያዎች ካሉት
የሙያ ደረጃ የብቃት አሀዶች እና ዝርዝር ስራዎች ጋር በማዛመድ ክፍተቶቹ የሚሞሉና ብቃታቸው
በምዘና የሚረጋገጥ ሲሆን ዝርዝር አተገባበሩ በሚከተለው ቅደም ተከተል ይሆናል፡

1. የአንቀሳቀሹን የቴክኒካል ክህሎት ክፍተት መለየት

2. የተለዩ ክፍተቶችን መሙላት የሚያስችል የብቃት አሃድ መምረጥ

3. የተመረጠውን የብቃት አሃድ ሊያስጨብጥ የሚችል የስልጠና መርሀ ግብር ማዘጋጀት፣

4. የስልጠና መርሀ ግብሩን ለመተግበር የሚያስችል ዝግጅት ብቃታቸው በተረጋገጠ አሠልጣኞች


ወይም ባለሙያዎች ማድረግ

5. መርሀ ግብሩን ብቃቱ በተረጋገጠ አሠልጣኝ ወይም ባለሙያ የቴክኒካል ክህሎት ክፍተት
ለታዩባቸው አንቀሻቃሾች መስጠት፣

6. የቴክኒካል ክህሎት ክፍተቱን መሙላት የሚያስችል አቅም መፈጠሩን በምዘና ማረጋገጥ፣

7. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታውን ውጤት መገምገም፡ የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ዋና
የማስፈጸሚያ ስልት የስልጠና ፕሮግራሞችን በማዘጋጀትና በመስጠት ነው። የስልጠናን ፋይዳ
ደግሞ ከታለመለት ግብ ስኬታማነት አንጻር መገምገም ያስፈልጋል።የስልጠና ፋይዳ ግምገማን
በአራት ዋና ዋና እርከኖች ማከናወን ይቻላል፡፡ እነዚህም:-

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 17
 ሰልጣኝ አንቀሳቃሽ ፕሮግራሙ እንደተጀመረ ያለውን ተነሳሽነት፡ ይህ ግምገማ የተለያዩ
መጠይቆችን በቃል ወይም በጽሁፍ በማቅረብ የሚከናወን ሲሆን ይህም ከመጠይቆቹ በሚገኙ
ግብረመልሶች አማካይነት በፕሮግራሙ አሰጣጥ ላይ ቀጣይ ማሻሻዎችን ለማድረግ ያስችላል፡፡

 በፕሮግራሙ ማጠናቀቂያ ላይ ሰልጣኝ አንቀሳቃሹ የተላለፈለትን ክህሎት በሚገባ


ለመጨበጡ የሚደረግ ግመገማ፣

 ሰልጣኝ አንቀሳቃሹወደ ስራ ገበታው ከተመለሰ በኋላ የተላለፈለትን ክህሎት በስራ ላይ


መተግበሩ/application፣

 ሰልጣኝ አንቀሳቃሹ የተላለፈለትን ክህሎት በመተግበሩ ምክንያት በስራው ላይ ያሳየውን


ለውጥ ከምርታማነት አንጻር መገመገም፡፡ ይህ ግምገማ የክህሎት ክፍተቱ ከመሟላቱ በፊት
የነበረውን የምርታማነት ውጤትን ከክህሎት አቅም ግንባታው በኋላ ካለው ምርታማነት ጋር
በማነጻጸር የሚከናወን ይሆናል።

 በማጠቃለያም ስለተለየው የክህሎት ክፍተትና ስለተወሰደው የአቅም ግንባታ ድጋፍና


ድጋፉ በምርታማነት ላይ ያመጣውን ለውጥ በፓኬጅ መልክ ቀምሮ ለሌሎች ተመሳሳይ
የቴክኒካል ክህሎት ክፍተት ላለባቸው ኢንተርፕራይዞች ማስተላለፍ ያስፈልጋል።

በወሳኝ ስራዎች መሰረት በተለየው የክህሎት ክፍተት መሰረት በሙያ ደረጃና የብቃት አሀድ አንጻር
የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ሂደት፡-

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 18
4.3.2. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ አተገባበር ስልት

ያለንን ሀብት በአግባቡ ስራ ላይ ለማዋልና የአቅም ውስንነትን ትኩረት ውስጥ በማስገባት የክህሎት አቅም
ግንባታ ድጋፎችን በምናካሄድበት ወቅት በአካባቢያችን የትኩረት ኢንዱስትሪዎች መሰረትና
በኢንተርፕራይዞች ውስጥ ባሉ ለተወዳዳሪነት ወሳኝ በሆኑ የስራ ሂደቶች ላይ በሚያጋጥሙ የክህሎት
ክፍተቶች ላይ ማተኮር ይኖርብናል።በተጨማሪም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የእድገት ደረጃ
መሰረት ትኩረት በማድረግ የአቅም ግንባታውን ማካሄድ ስልታዊ ጠቀሜታ እንዳለው ይታመናል።

የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታን ቅድሚያ አሰጣጥ ከኢንተርፕራይዞች ፍላጎትና ካለው የክህሎት ደረጃና
ከትኩረት ዘርፉ ወሳኝነትና አስፈላጊነት አንጻር ለመገምገም ይቻል ዘንድእያንዳንዱንስራ ከአስቸጋሪነት
/difficulty፣ ከአስፈላጊነት /importance፣ ከድግግሞሽ /frequency (DIF) አንጻር መተንተንና ቅድሚያ
የሚሰጣቸውን መወሰን ያስፈልጋል። ይህም ውስን ሀብትን በማያስፈልጉ የስልጠና ፕሮግሮሞች ላይ
እንዳናባክንና በተወሰኑ ችግሮች ላይ ብቻ በማተኮር ውጤታማ እንድንሆን ይረዳናል።

ከዚህ በታች በሳጥኖች ውስጥ የተመለከተው በስራው የአስፈላጊነት ደረጃና ባለው የክህሎት ደረጃ መሰረት
እንዴት ቅድሚያ መስጠት እንደሚኖርብን ያሳየናል፡፡

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 19
በጣም አስፈላጊ ስራና የተወሰነ በጣም አስፈላጊ
አስፈላጊ ስራ
ስራ እና
እና በቂ
በቂ
በጣም
ክህሎት = ከፍተኛ ቅድሚያ
ክህሎት =
ክህሎት = ዝቅተኛ
ዝቅተኛ ቅድሚያ
ቅድሚያ
የሚሰጠው
የሚሰጠው
የሚሰጠው
የስራው አስፈላጊነት

አስፈላጊነቱ ዝቅተኛ
አስፈላጊነቱ ዝቅተኛ የሆነ
የሆነ ስራና
ስራና አስፈላጊነቱ ዝቅተኛ የሆነ ስራእና
የተወሰነ ክህሎት=
የተወሰነ ክህሎት= ዝቅተኛ
ዝቅተኛ ቅድሚያ
ቅድሚያ በቂ ክህሎት = ቅድሚያ
የማይሰጠው
የማይሰጠው
የሚሰጠው
የሚሰጠው

የክህሎት ደረጃ

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 20
4.3.3. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ድጋፍ አማራጮች

የቴክኒካል ክህሎት ክፍተት አቅም ግንባታ ድጋፍን በተለያዩ ዘዴዎችና ቦታዎች ማከናወን ይቻላል፡፡
እነሱም፡-

ሀ. የተሻለ የክህሎት አቅም ባለውና ብቃቱ በተረጋገጠ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሽ
አማካይነት በኢንተርፕራይዙ የስራ ቦታ ላይ፣

ለ. በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አሠልጣኝ አማካይነት በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዙ የስራ


ቦታ ላይ፣

ሐ. በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አሠልጣኝ አማካይነት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና


ተቋማት ውስጥ፣

መ. የተሻለ የክህሎት አቅም ባለውና ብቃቱ በተረጋገጠ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሽና
በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አሠልጣኝ በጋራ በሁለቱም ተቋማት ውስጥ፣

ሠ. በአስመጪዎችና አቅራቢዎች ባለሙያዎች በአዳዲስ የአመራረት ዘዴዎችና በአዳዲስ የመሳሪያ


አጠቃቀም ላይ በአስመጪዎቹ ወይም በኢንተርፕራይዙ የስራ ቦታ ላይ፣

ከላይ እንደተመለከተው በተለየው የኢንተርፕራይዙ ቴክኒካል ክህሎት ክፍተት መሰረት አማራጮችን


መጠቀም ይቻላል። ሆኖም ግን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ድጋፉን በማቀድና
የማሰልጠኛ ስነ ዘዴዎችና ማቴሪያሎችን ከማዘጋጀት አንስቶ እስከ ፕሮግራሙ ፍጻሜ ግምገማ ማድረግና
መቀመር ድረስ የሚጫወቱት ሚና በተለይም ከ ’ሀ’ እስከ ‘መ’ ባሉ አማራጮች ላይ ከፍተኛ ነው።

4.3.4. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ሂደቶች

 የምርጥ ተሞክሮ መለየት

ተወዳዳሪ የሚያያደርጉ ቁልፍ አሰራሮችን፣ ስርዓቶችን፣ የስራ ሂደቶችን፣ ወዘተ… መለየት

ከታች የተመለከተው ምሳሌ በባህላዊ ሽመና ላይ የተለየ ቁልፍ ስራን ያሳያል፡፡

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 21
 አሁን ያለበትን ደረጃ ማወቅ

በተለዩ አሰራሮች፣ ስርዓቶች፣ የስራ ሂደቶች፣ ወዘተ… ላይ ያለውን የተወዳደሪነት ክህሎት ደረጃና
ከተቀመጠው የሙያ ደረጃ/የብቃት አሃድ አንጻር መቀመር

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 22
4.4. የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ

የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ማለት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከቴክኖሎጂ ለውጥ ጋር ተስማምተው
እንዲሄዱ የሚያስችል የማያሻማና የተቀናጀ ችሎታ/አቅም እንዲፈጥሩ የማድረግ የአቅም ግንባታ ሂደት
ነው፡፡ የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ማስተግበሪያ ስልቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡፡

4.4.1. የቴክኖሎጂ የአሰራር ሂደቶች

የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ ተፈላጊውን ቴክኖሎጂ በመለየት፣ በማግኘትና


በመኮረጅ በማመሳሰልና አቅምን አዳብሮ ለማሻሻል አዋጪ የሆነ የአሰራር ስርዓት ሂደት ሞዴል ቀርቧል፡፡

ጥ/አ/ኢ
ተወዳዳሪ
የአሰራር
የሚያደርግእሴት አዋጭ
ቴክኖሎጂ
ሰንሰለት
የቴክኖሎጂ ቴክኖሎጂ ቴክኖሎጂ ዕቀባ
ፍላጎት
ብዜትና ሽግግር
አብዥዎችን
ትንተና
ተግባራትን መረጣ
ንድፍ ማዘጋጀት መለየትና
መለየት ማፈላለግ መካከለኛና
ማብቃት
ከፍተኛ
ክፍተትን የአዋጭነት ናሙና መስራት ባለሃብቶችን
መለየት ትንተና ማካሄድ የመሳሪያ
ውጤት ማሳተፍ
አቅርቦት
አላመጣም ናሙና
መፍትሄ ፍተሻውጤት ማመቻቸት
ማስቀመጥ መረጣ ማካሄዴ ‘’አምጥ
ተወዳዳሪነትን
ቷል
የሚያረጋግጥ
ቴክኖሎጂ
4.4.2. የእሴት ሰንሰለት

የእሴት ሰንሰለት ማለት የአንድን ለገበያ የሚቀርብ ምርት ከግብዓቱ ጀምሮ እስከ ፍጆታ (ጥቅም ላይ
እስክዋለበት ጊዜ) ድረስ ያሉና ለምርት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ነገሮች የሚቀነባበሩበት ዓላማ መር ቅደም
ተከተል ነው፡፡ የእያንዳንዱን ኢንዱስትሪ ሥራ ከግብዓት እስከ ውጤት ድረስ መዘርዘር የሚያስፈልግበት
ዓላማ በመጨረሻ ላይ የምርቱን ጥራት የሚወስኑ ነገሮች ከግብዓቱ ወይም ከአሰራሩ ወይም ሌላ ከምን
እንደሆነ ለመወሰን እንዲቻል ነው፡፡

4.4.3. የቴክኖሎጂን ክፍተት መለየት

ከላይ የቴክኖሎጂን ትርጓሜና ክፍሎቹ ላይ በመንተራስ የእሴት ሰንሰለቱ ሲተነተን የቴክኖሎጂ ክፍተቶችን
(ቁሳዊ፣ ዕውቀታዊ፣ ሰነዳዊ፣ ድርጊታዊ) ብሎ በመለየት በምርት ጥራት ላይ ችግር/ ክፍተት ያመጣውንና

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 23
ቢሻሻል ሊያመጣ ይችል የነበረውን ክፍተት መለየት አንድ ትልቁ ሥራ ነው ምክንያቱም ችግርን ማወቅ
የመፍትሄው ግማሽ አካል ነውና፡፡ ለምሳሌ የቆዳ ጫማ የእሴት ሰንሰለት ትንተና ላይ በእያንዳንዱ የአሰራር
ሂደት ችግሮችን በቀላሉ መለየት ይቻላል፡፡

ክፍተቱን ለመሙላት የሚወሰዱ አካሄዶች

ለገበያ በሚቀርቡ ምርቶች ከግብዓት ጀምሮ ምርቱ ጥቅም ላይ እስከሚውልበት ድረስ ያለውን ሰንሰለት
በማጥናትና በምርት ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያመጡ ያስቻሉትን ችግሮች/ ክፍተቶች ከተለዩ በኋላ
የሚወሰዱ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በዝርዝር ማየት ነው፡፡

በመሆኑም የተለያዩ አማራጮችን በመዘርዘር (ለእያንዳንዱ ዝርዝር አሰራር በመፃፍ) የመጨረሻና


አማራጭ የሆነውን ምርጥ ቴክኖሎጂ በግልጽ ማስቀመጥና የተመረጠበትን የአሠራር ዝርዝር ከሌሎቹ ጋር
በአዋጭነት መስፈርት መሰረት ማነፃፀር ያስፈልጋል፡፡

 አዋጭነት

የቴክኖሎጂ ክፍተቶች ያለበትን አንድ የምርት ሰንሰለት ክፍተት ከላይ በተጠቀሰው መሠረት ክፍተቱን
የሚሞሉ አማራጭ ቴክኖሎጂዎች ከተመረጡለት በኋላ የሚቀጥለው ሥራ ለተመረጠት የቴክኖሎጂ
አዋጭነት ግምገማ ማካሄድ ነው፡፡ አዋጭነት ከብዙ መንገድ የሚታይ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ ምርታማነት፣
ጥራት፣ ጉልበትን በስፋት መጠቀምና ዋጋ ናቸው፡፡

 ምርታማነት

የተመረጠው ቴክኖሎጂ በእርግጥ ምርታማነትን ይጨምራል ወይ? ይህም ማለት በተወሰነ ጊዜና የሰው
ኃይል በመጠቀም ቴክኖሎጂው በመምጣቱ ብቻ ምርት ጨምሯል ወይ? ከጨመረስ በምን ያህል?
(በመቶኛ፣ በቁጥር ፣ በክብደት ወዘተ) በሌላ በኩል ደግሞ ለማምረት የወጣ ወጪ መቀነስም ሆነ በምርት
ላይ የጥሬ ዕቃ ብክነት መቀነስ እንደ ምርታማነት ሊቆጠር ይችላል፡፡

 ጥራት

ቴክኖሎጂው በምርቱ ጥራት ላይ ለውጥ አምጥቷል ወይ? (ምንም እንኳን ጥራት የተለያየ ትርጉም
ቢኖረው በተለይ ግን የተጠቃሚዎችን መሥፈርት ማሟላቱ እንደዋና ትርጓሜ መውሰድ ይቻላል)፡፡
ተጠቃሚው ባወጣው መስፈርት አለዚያም በአገር ወይም በዓለም አቀፍ ደረጃ በወጣ መስፈርት
(Standard) መሠረት ምርቱ የሚፈለገውን ጥራት (በተሰጠው መሥፈርት ወይም በተጠቃሚ ምርጫ)
በክብደት፣ በቀለም፣ በርዝመት፣ ወዘተ ምርቱ ላይ ቴክኖሎጂው ለውጥ ማምጣቱ መታየት ይኖርበታል፡፡

 ጉልበት በስፋት መጠቀም

አንዳንድ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ ጊዜና ጉልበትን የሚቆጥብ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ (high


Technology) “Automation” አሰራር ማምጣት ይቻላል፡፡ ይህ ግን በሥራ ላይ የሚሰማራውን ሰው ቁጥር

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 24
ስለሚቀንስ አሁን አገሪቱ ከተያያዘችው ሥራ አጥነትን የመዋጋት ርምጃ ጋር ይቃረናል፡፡ በመሆኑም
የተመረጠው ቴክኖሎጂ ጉልበትን በስፋት የሚጠቀም መሆኑን ማረጋገጥ አሁን ካለው አገራዊ አስተሳሰብ
ጋር አንዱ የአዋጭነቱ ሥራ ነው፡

 ዋጋ

ቴክኖሎጂው በዋጋ ላይ ምን ለውጥ አምጥቷል? ይህም ማለት አንድም ያንኑ ምርት ለማምረት ይወጣ
የነበረው ወጪ በምን ያህል ይቀንሳል ወይም ያንኑ ምርት ለማምረት ይባክን የነበረው የግብዓት ወጭ
በምን ያህል ቀንሷል የሚለው በዋነነት የሚታይ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ቴክኖሎጂው በስራ ላይ ሲውል
የሚያስወጣው የማንቀሳቀሻ ወጪም የኤሌክትሪክ ፍጆታ፣ የነዳጅ ፍጆታ፣ የጥገና ወጪና ወዘተ ከግምት
ውስጥ መግባት ይኖርበታል፡፡

4.4.4. ምርጡን ቴክኖሎጂ መለየት

የአንድን ምርት የዕሴት ሰንሰለት በማየትና ያለበትን ክፍተት ለመሙላት ሊጠቅሙ የሚችሉ
ቴክኖሎጂዎች ከተዘረዘሩ በኋላ የሚቀጥለው ሥራ የእያንዳንዱን አዋጭነት በመተንተን አንድ ቴክኖሎጂ
መምረጥ ነው፡፡ ምርጡን ቴክኖሎጂ በመምረጥ ሂደት ውስጥ ከአዋጭነት በተጨማሪ ሌሎች መታየት
ያለባቸው ነገሮት የአሠራር ደህንነትንና የጤና ጉዳዮች ናቸው፡፡

ቴክኖሎጂን ማቀብ (ማከማቸት)

በኢኮኖሚ ቀጠና ውስጥ ያለ የትኩረት ኢንዱስትሪን የዕሴት ሰንሰለት ትንተና ያገናዘበ ምርጥ ቴክኖሎጂን
ለማስተላለፍና ሌሎች ደረጃውን ጠብቀው እንዲሰሩት ለማድረግ ቴክኖሎጂውን ማቀብ (ማከማቸት)
ያስፈልጋል፡፡

ቴክኖሎጂ በማቀብ ሂደት ውስጥ የተመረጠውን ቴክኖሎጂ ንድፍ (Blue Print) ማዘጋጀትና ናሙና ሰርቶ
ተከታታይ ፍተሻ ማካሄድ ዋና ዋና ሥራዎቹ ናቸው፡፡ የቴክኖሎጂ ተቋማት ቴክኖሎጂ ማቀብ ዋና ስራቸው
በመሆኑ በሳይንሳዊ ትንተናና መረጃ ተመስርተው የቴክኖሎጂ ንድፍ ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡
በተዘጋጀው ንድፍ መሠረት ብቃት ያለው ናሙና ማዘጋጀት፣ የተዘጋጀውን ናሙና በተገቢው ቦታና የሥራ
ምህዳር ደረጃውን ጠብቆ ለመሠራቱ ተከታታይ የፍተሻ ሥራ ማካሄድ፣ በፍተሻ በተገኙ መረጃዎች ላይ
በመመርኮዝ ማስተካከያ/ማሻሻያ አድርጎ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ንድፍ ማዘጋጀት

የተመረጠውን ቴክኖሎጂ አሸጋጋሪዎች በሚገነዘቡበት መልክ የተዘጋጀ ዶኩመንት ሊኖር ይገባል፡፡ ይኸው
የዶኩመንት ንድፍ (Blue Print) የተመረጠውን ቴክኖሎጂ ለማምረት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 25
(Materials)፣ አይነት፣ ልኬትና ምስል (Drawing) በውስጡ የያዘ ነው፡፡ ድሮዊንግ (Drawing) በቴክኖሎጂ
ትግበራ ወቅት የሚዘጋጅ ዝርዝር የተለያዩ አካላት ንድፍ (detail drawing)፣ሙሉ የቴክኖሎጂው ንድፍ
(assembly drawing)፣ ቢቻል three dimensional ድሮዊንግ መረጃዎችን ከተገቢው ስኬልና ልኬት
(Measurment) ጋር ማሟላት ይኖርበታል፡፡

ለቴክኖሎጂ ማምረቻነት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች (Materials) መምረጥ የዕቃ አመራረጥ ሂደት


የተጠቃሚውን ጤና የማይጎዳ፣በአካባቢ በቀላሉ ማግኘት የሚቻል፣ የዕቃው ባህርያት (የዕቃው ጥንካሬ፣
ሜካኒካል ባህርያት፣ ኬሚካል ባህርያት፣ የዕቃው አስተማማኝነትና የቆይታ ጊዜ) ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ
መሆኑን ይኖርበታል፡፡ ሌላው በቴክኖሎጂ ማምረቻ ዕቃዎች (Materials) አመራረጠ ላይ የዋጋ የመገመት
ሂደት (cost estimation) በወዳደቁ እቃዎች ሳይሆን ደረጃውን በጠበቁ አቃዎች ላይ የተመረኮዘ ሊሆን
ይገባል እንዲሁም በቴክኖሎጂ ማምረት ሂደት የወጡ (Direct labour,material,electric etc) ወጪዎች
የቴክኖሎጂውን ዋጋ በሚያስችል መልኩ በዶክመንት ሊያዙ ይገበል::

ናሙና ማዘጋጀት

ለአንድ ቴክኖሎጂ ንድፍ ከተሰራ በኋላ ያንን ንድፍ በተከተለ መልኩ ናሙና ሊዘጋጅ ይገባል፡፡ ይኸ ናሙና
የተመረጠውን ቴክኖሎጂ ውጤታማነት እንዲሁም ድክመቶች ለመገምገም ይረዳል፡፡ በንድፍ ላይ
የተመሰረተ የናሙና ዝግጅት በአሰራር ላይ ሊከሰቱ በሚችሉ የስኬት፣ የቅርፅና የውህደት አለመጣጣም
ሊከተል የሚችለው የገንዘብ የጉልበትና የጊዜ ብክነት ሊያድን ይችላል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም ናሙና
በተዘጋጀው የዲዛይን፣ የማቴሪያልና የጥራት ደረጃ መሰራት ይኖርበታል፡፡ ይህንንም ሂደት ለማገዝ
የአመራረት ሂደቱን ቅደም ተከተል የሚያሳይ የማኑፋክቸሪንግ ፕሮሰስ አብሮ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
ሌላው በናሙና ዝግጅት ወቅት ሊስተዋል የሚገባው ነገር ናሙና ከሞዴል የሚለይ መሆኑ ነው፡፡ ሞዴል
ለአንድ ቴክኖሎጂ ስዕላዊ ምልከታ (Visualization) አገልግሎት እንዲውል ታስቦ መሆን ካለበት ማቴሪያል
ወጪ ከካርቶን፣ ፕላስቲክ፣ ቆርቆሮ ወ.ዘ.ተ ሊዘጋጅ የሚችል ሲሆን በንድፍ ላይ የተጠቀሰው የቴክኖሎጂ
ማምረቻ እቃ ላይጠቀም ይችላል፡፡ ስለዚህ በቴክኖሎጂ ሽግግር ትግበራ ላይ ሞዴል ባይሰራ ይመረጣል
በመሆኑም ናሙና በንድፍ ላይ በተቀመጠው ልኬትና ማምረቻ ዕቃ የሚሰራ ስለሆነ ጥቅም ላይ ሊውል
የሚችል ነው::

ናሙና መፈተሽ

በተሰራው ናሙና ላይ በሚደረግ የመስራት ማረጋገጫ (functionality test) ሙሉ የሆነ የፍተሻ መረጃ
ማግኘት አይቻልም ስለሆነም የተሰራው ናሙና ተፈላጊውን የኢንዱሰትሪ ደረጃ ማሟላቱን
ከቴክኖሎጂው ተጠቃሚ ጋር በመሆን ቴክኖሎጂው ግልጋሎት በሚሰጥበት ቦታ ላይ (ለረጅም ጊዜና
በተደጋጋሚ) ፍተሻ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ለዚህም በቂ አሃዛዊ መረጃ መያዝ አለበት፡፡ በተጨማሪም
ናሙናው ያለበትን ጉድለቶችና ችግሮች በመረጃ አስደግፎ በመያዝና በትንታኔ የተመረኮዘ ማሻሻያ
በማድረግ አጠናቆ ማውጣት ያስፈልጋል፡፡ የናሙና ፍተሻው የተመረጠው ቴክኖሎጂ ትክክለኛነትን፣

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 26
የተዘጋጀው ንድፍ ብቃትንና የተዘጋጀው ናሙና ቴክኖሎጂ የታለመለትን ግብ መምታት መቻሉን
ማረጋገጫ መሳሪያ ነው፡፡

4.4.5. የተፈተሸውን ቴክኖሎጂ ማሸጋገር

አንድ ቴክኖሎጂ ከተለየ፣ ንድፍ ተዘጋጅቶለት የናሙና ስራ ከተከናወነ እንዲሁም በተሠራው ናሙና ላይ
የፍተሻ ስራ ተካሄዶበት ፍተሻውን ካለፈ በኋላ ወደ ማሸጋገር ስራ ይገባል፡ ከናሙናነት አንስቶ አባዝቶ ወደ
ገበያ ለማሸጋገር በመጀመሪያ አብዢዎችን የመለየትና እነሱን የማብቃት ስራ ሊሠራና ከዛም አልፎ
ቴክኖሎጂውን ከገበያ ጋር ማስተሳሰር ይገባል፡፡

የአብዢዎችን አቅም ክፍተት መለየት

አንድ ቴክኖሎጂ የፍተሻ ስራ ከተሠራበትና ፍተሻው ካለፈ በኋላ የማብዛት ስራ ይሰራል፡፡ ቴክኖሎጂውን
ለማብዛት መጀመሪያ አብዢን መለየት ያስፈልጋል፡፡ አብዢዎችን ስንለይ ልንመለከታቸው ከሚገቡን
ነጎሮች መካከል ዋንኛው የአብዢዎቹን አቅም ማወቅ ነው፡፡ የአብዢዎችን አቅም ስንል የሰው ሀይል፣
የማምረቻ ቴክኖሎጂ፣ የገንዘብ አቅምን ከግምት ያካተተ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደት
ውስጥ የማብዛቱን ስራ ሊሠሩ የሚችሉት የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ናቸው፡፡ ከጥቃቅንና አነስተኛ
ተቋማት መካከል የተፈተሸውን ቴክኖሎጂ ለማብዛት አቅሙ ያላቸውን መርጦ የማባዛት ስራውን
እንዲሰራ ማድረግ ይገባል፡፡

አብዢዎችን ማብቃት

አብዢዎችን የማብቃት ስራ ሊሠራ የሚችለው በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ሲሆን


የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ቴክኖሎጂን የማብዛት ስራ እንዲሰሩ ይደረጋል::

ድጋፍ በመስጠት የብቃቱን ውጤት መገምገም

የማብዛት ስራ በሚሰራበት ጊዜ የማብዛቱን ስራ የሚሰራው ተቋም የተለያዩ ድጋፎች ሊያስፈልጉት


ይችላሉ፡፡ ይህ ድጋፍ በገንዘብ፣በሰው ሀይል ወይም ሙያዊ አስተያየትና ልምዶችን ለማካፈል ሊሆን
ይችላል፡፡ ስለሆነም በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ፓኬጅ በተቀመጠው መሰረት አንድ የማብዛት
ስራን የሚሠራ ተቋም ስራውን በትክክል ያከናውን ዘንድ ሊያገኝ የሚገባውን ድጋፍ በሙሉ ማግኘቱን
ሊረጋግጥ ይገባል፡፡

ገበያ ማፈላለግ

በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ፓኬጅ እንደተቀመጠው፣ ቴክኖሎጂ የማብዛት ስራ ከተሠራ በኋላ


የሚቀጥለው ገበያን ወደ ማፈላለግ ስራ መሄድ ይሆናል፡፡ ቴክኖሎጂን ከገበያ ጋር ለማስተሳሰር
የማስተዋወቅ ስራዎች ሊሰሩ ይገባል፡፡ የቴክኖሎጂውን ውጤታማነት ያለውን ተፈላጊነት ገበያው
እንዲረዳው የተለያዩ የገበያ ጥናቶችና የማስተዋወቂያ ስራዎች ሊሰሩ ይገባል፡፡ በዚህ ላይ የመንግስት፣የግል
እንዲሁም ሌሎች በገበያ ነክ ጉዳይ ላይ የተሰማሩ ተቋማት ሊሳተፉ ይችላሉ፡፡

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 27
የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 28
የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ የክፍተት መለያ አካሄድ

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ ለጥ/አ/ኢንተርፕራይዞች እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ይህ የሚሰጠው ድጋፍ


የኢንተርፕራይዙን የአሰራር ሂደት፣አደረጃጀትና የቴክኖሎጂ ክፍተቶች እንዲሁም የአንቀሳቃሾችን ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ
ያደረጉ የቴክኒካል ክህሎት ክፍተቶችና የእነሱን የኢንተርፕሪኒየር እውቀት፣ክህሎትና አመለካከት ክፍተቶች በመለየት
አግባብ የሆነ የአቅም ግንባታ ስራ ከሙያ ብቃት አሀድ ተነስቶ መከናወን አለበት፡፡ ድጋፉም ከተሰጠ በኋላ
የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ብቃታቸው በምዘና ይረጋገጣል፡፡

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 29
ኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ ያደረጉ ክፍተቶች ለመለየት በሚቀጥለው ገፅ የተቀመጠው የክህሎት ሰሌዳ ተዘጋጅቷል፡፡

የኢንተርፕራይዙ ስም_______________________________

የተሰማራበት የስራ መስክ____________________________

የትም/ት ከዚህ በፊት የእዉቀትና ክፍተቱ የሚሞላበት የሚወሰደው


የአንቀሳቃሹ
ተ.ቁ ዝግጅት የወሰደው የክህሎት የብቃት አሀድ መፍትሄ

እድሜ
ስም

ፆታ
ስልጠና ክፍተት

ክፍተቱን የለየው አሰልጣኝ ስም______________________

ፊርማ_______

ቀን_______________

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 |ገጽ 30
የተለዩትን ክፍተቶች ከሙያ ደረጃ የብቃት አህዶች አንፃር መተንተንና በኢንተርፕራይዙ ከሚገኘው ሞያተኛ
ብቃት አንፃር ከታች በተመለከተው ሰሌዳ መሰረት መገምገም

የክፍተት መለያ ሰሌዳ /Skill Gap Identification Matrix/

የድጋፉ ፓኬጅ ስም፡ _________________

ደረጃ፡ _________

የብቃት አህድ፡ _________________

የሰራተኛው ስም ዝርዝር የብቃት አሃዱ ሥራዎች/Elements/

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11

ክፍተቱን የለየው አሰልጣኝ ስም______________________

ፊርማ_______
ቀን_______________

የክፍተት መለያ ሰሌዳው አጠቃቀም

 የእያንዳንዱን አንቀሳቃሽ ከተሰማራበት ስራ አንፃር የአፈፃፀሙን ክፍተት በሙያ ብቃት ምዘና መለየት

 የአንቀሳቃሾችን የአፈፃፀም ክፍተት ከተቀመጠው የሙያ ብቃት አሀድ አንፃር በመገምገም የብቃት አሀድ
ዝርዝር ስራዎችን /elements/ ሙሉ በሙሉ በብቃት ለሚያከናውኑ አንቀሳቃሾች √ ምልክት መስጠትና
ሙሉ በሙሉ በብቃት ለማያከናውኑ አንቀሳቃሾች ደግሞ x ምልክት መስጠት

 በተለዩት ክፍቶተች መሰረት የማሰልጠኛ ሞጁልና ማሰልጠኛ መሳሪያ በማዘጋጀት የአቅም ግንባታ ድጋፍ
መስጠት

 የተሰጠውን ድጋፍ በሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጥ

 ቀጣይነት ያለው ክትትልና ድጋፍ ማድረግ

በተለዩት ክፍተቶች ላይ የማሰልጠኛ ሞጁሎችና የማሰልጠኛ መሳሪያ ማዘጋጀት

የማሰልጠኛ ሞጁል ማዘጋጃ ቅፅ

የቴ/ሙ/ት/ስ/ፕሮግራም ዘርፍ፤

ሞጁሉ የተዘጋጀበት የብቃት አሀድ ፤

ለሞጁሉ የተመደበ ሰአት፤

የሞጁሉ መግለጫ፤

የስልጠናው ውጤት፤

ሰልጣኞቹ ይህንን ሞጁል ካጠናቀቁ በኋላ……………………………

የሞጁሉ ይዘት፡

የስልጠናው አሰጣጥ ዘዴ፤

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 32


የምዘና ዘዴ፤

ምዘናው የሚሰጥበት ቦታ፤

5. የአስፈፃሚ አካላት ሚና
5.1. የፌደራል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ ተግባርና ኃላፊነት

ሀ. የድጋፍ ማዕቀፎችን እንዲቀርጹ ማድረግና በሂደትም ማሻሻል፣

ለ. የዘርፉን ዕቅድ የማጠናቀር፣ አፈጻጻሙን የመከታታልና የመገምገም፣

ሐ. ለኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አመቻቾች የአሰልጣኞች ስልጠና

መስጠት፤

መ. የዘርፉን ልማት የተመለከቱና ልማቱን የሚያፋጥኑ መረጃዎችን ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር ማሰባሰብ፤

ማጠናቀርና ማሰራጨት፣

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 33


ሠ. የቴክኖሎጂ ልማት ስራን በዓይነት ወይም በገንዘብ ሊረዱ የሚችሉ ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች

እገዛና ድጋፍ እንዲያደርጉ ማስተባብር፣

ረ. የክልል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኤጀንሲዎችን መደገፍ አቅማቸውን መገንባት፤

ሰ. የሀገር ውስጥና የኤክስፖርት ገበያ ልማት ሥራዎችን ማከናወን፤

ሸ. የድጋፍ ማዕቀፎችን ለማስፈጸም የሚረዱ መመሪያዎች ማዘጋጀት፤

ቀ. የዘርፉን የልማት ችግሮች ለመለየትና ለመፍታት የሚያስችሉ

ጥናቶችን ማከናወን፣ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን መቀመርና ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት አፈጻጸሙንም

መከታተል፤

በ. በአመት ሁለት ጊዜ ከፈጻሚ አካላትጋር በመሆን በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በአካል

በመገኘት ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡

5.2. የክልል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ ተግባርና ኃላፊነት

ሀ. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አስፈፃሚ አካላትን አቅም ማጐልበት፣

ለ. ከኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ጋር የተገናኙ የወጪ መጋራትንና አሸፋፈንን በተመለከተ

መመሪያዎችን ያዘጋጃል፣ በሚመለከተው ክፍልም ያፀድቃል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣

ሐ. በቴክኖሎጂ አቅርቦት ላይ የሚሰሩ ተቋማት በክልሉ ውስጥ እንዲስፋፉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር

በቅንጅት ይሰራል

መ. የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተፈላጊና አዋጭ ቴክኖሎጂዎችና የማምረቻ መሣሪያዎች

የሚያገኙበትን ሥልት ይቀይሳል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል፣

ሠ. ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚገኙ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች እንዲበረታቱ ያደርጋል፣

ረ. የቴክኖሎጂ ልማት ስራን በዓይነት ወይም በገንዘብ ሊረዱ የሚችሉ ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ

ድርጅቶች እገዛና ድጋፍ እንዲያደርጉ ያስተባብራል፣

ሰ. በክልሉ የሚገኙ የምርምርና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምር ፕሮግራማቸው ውስጥ የቴክኖሎጂ

ልማት ሥራን እንዲያካትቱ ያበረታታል፣

ቀ. በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተፈላጊና አዋጭ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች መረጃ፣ዲዛይኖችና ናሙናዎች

ያሰባስባል፣ በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዳስፈላጊነቱ በሌሎች አምራቾች እንዲመረቱ

ያደርጋል፣

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 34


በ. የተመረቱ ቴክኖሎጂዎች በኤግዚቢሽኖች የሚተዋወቁበት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፣ ሕጋዊ ዕውቅና

የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣

ተ. ለእያንዳንዱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት በየጂኦግራፊ ክልላቸው የሚከታተሏቸውና

የሚያበቋቸው ኢንተርፕራይዞች በክልል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኤጀንሲዎች

ይመደቡላቸዋል።

5.3. በየደረጃው የሚገኙ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ጽ/ቤቶች ተግባርና ኃላፊነት

ሀ. የዞን ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት

1. ስለኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አስፈጻሚ አካላትና

ሠራተኞች ግንዛቤ ማስጨበጥና ሰፊ የማስተዋወቅና የሕዝብ ግንኙነት ስራ መስራት፣

2. በዘርፉ የተሠማሩ ባለሙያዎችን አቅም ማጐልበትና በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና

ሥልጠና ተቋማት ተቀናጅተው ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን

አገልግሎት የሚያቀርቡበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣

3. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት መረጃዎችን ማሰባሰብ፣ማጠናቀር፣ ሪፖርት ማዘጋጀትና

ለሚመለከታቸው አካላት ማስተላለፍ፣

4. የንግድ ምክር አገልግሎቶችን መከታተልና ውጤቱን መገምገም፣

5. በዞኑ ወስጥ ስለሚገኙ ኢንተርፕራይዞች የምክር አገልግሎት የተሰጠበት ሪፖርት (Report on BDS

delivery) ማደራጀትና ሪፖርቱን ለሚጠይቀው አግባብ ያለው አካል ማስተላለፍ፣

ለ. የከተሞች ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት ሚና

1.ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ተቀናጅተው ለተጠቃሚው ኀብረተሰብ የምክር

አገልግሎት የሚሰጡበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣

2.ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ጋር በመቀናጀት የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት

ውጤታማ እንዲሆን ማድረግ፣

3.ሪፖርቶችንና መረጃዎችን ማጠናቀርና ለበላይ አካላት ማስተላለፍ፣

4.በሥራው የተሻለ ብቃት ያላቸውንና ውጤት ያስመዘገቡ ሠራተኞችን ማበረታታት፡

ሐ. የአንድ ማዕከል አገልግሎት ጣቢያ

1. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንዴት፣ የትና በማን

እንደሚሰጥ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት፣


2. የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎችን በመስፈርቱ መሰረት መመልመል፣

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 35


3. ለኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎችን በተሟላ ደረጃ

ያደራጃል፣ለተጠቃሚዎች ያሰራጫል፡፡
4. የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ችግሮች ከለየ በኋላ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት

ድጋፍ የሚፈቱትን ችግሮች ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ያስተላልፋል፣ሌሎቹን

(የብድር፣የቦታ፣የገበያና የመሳሰሉትን) በአንድ ማዕከል አገልግሎት ጣቢያ እንዲቀርብ ያደርጋል፡፡


5. በየወቅቱ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሚሰጡ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን

አገልግሎቶች ይደግፋል፣ ይከታተላል፣ ሪፓርት ይቀበላል፡፡


6. ለኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎቱ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በማገናኘት

አብሮ የሚሰራ የኢንዱስትሪ አክስቴንሽን አገልግሎት አመቻቾች እንዲመደቡ ያደርጋል፣

5.4. የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ተግባርና ኃላፊነት

ሀ. የሥልጠናና የቴክኖሎጂ ልማት ማዕቀፎችን ማዘጋጀት፣

ለ. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምህራንን አቅም መገንባት፣

ሐ. የቴክኖሎጂ ልማት ስራን በዓይነት ወይም በገንዘብ ሊረዱ የሚችሉ ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ

ድርጅቶች እገዛና ድጋፍ እንዲያደርጉ ማስተባበር፣

መ. ለተለዩ ሙያዎች የሙያ ደረጃ ምደባና የብቃት ምዘና መሳሪያዎች እንዲዘጋጁ ማስተባበር፣

ሠ. የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂን በብቃት ለማስፈጸም በክልሎች የሚገኙ የቴክኒክና

ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲዎች አቅም መገንባትና ሥራዎቻቸውን ማቀናጀት፤

ረ. ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎላና የናሙና ወጪያቸው ከፍተኛ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን የመለየት፣ የማከማቸትና

የማሸጋገር ሂደቶችን በመሪነት ማከናወን፣

ሰ. ለኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ኤጀንቶች የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት፤

ሸ. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዋና የስራ ሂደትን ማደራጀትና ባለሙያዎች ማስመደብ፣

ቀ. በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች የሃገር ውስጥና

የውጭ አገር ተሞክሮዎችን እንዲያገኙ ትምህርታዊ ስልጠናዎችና የልምድ ልውውጥ ፕሮግራሞችን

ማመቻቸትና ማስተባበር፣

በ. በአመት ሁለት ጊዜ ከፈጻሚ አካላት ጋር በመሆን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በአካል

በመገኘት ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡

5.5. የክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ/ቢሮ/ኮሚሽን ተግባርና ኃላፊነት

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 36


ሀ. በስሩ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተፈላጊና

አዋጭ ቴክኖሎጂዎች ዲዛይኖችንና ናሙናዎችን እንዲያመርቱ ይደግፋል፣ ያስተባብራል፣ ክትትልና ድጋፍ

ያደርጋል።

ለ. የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ትምህርታዊ ጉብኝቶችና ሥልጠናዎችን የሚመለከታቸው አመራሮችና

ባለሙያዎች እንዲያገኙ ይከታተላል፣ያመቻቻል፣

ሐ. ከሥልጠና ማጠናቀቂያ በኃላ ሰልጣኞች የሙያ ብቃት ምዘና እንዲውስዱ ያስተባብራል፣

መ. በክልል ለሚሰራው የሰው ኃይል ልማት፣ቴክኖሎጂ አቅርቦትና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት

አስፈላጊውን በጀትና የሰው ኃይል ይመድባል።

ሠ. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዋና የስራ ሂደትን ያደራጃል ባለሙያዎች ያስመድባል፣

ረ. በክልል ለሚሰራው የሰው ኃይል ልማት፣ቴክኖሎጂ አቅርቦትና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ማንዋል

ዝግጅት ያስተባብራል፣

ሰ. የቴክኖሎጂ ልማት ስራን በዓይነት ወይም በገንዘብ ሊረዱ የሚችሉ ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ

ድርጅቶች እገዛና ድጋፍ እንዲያደርጉ ያስተባብራል፣

ቀ. ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት መምህራን የክህሎት ክፍተታቸውን በማጥናት ተጨማሪ

ስልጠና የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣

በ. በሥሩ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የንግድ ስራ

አመራርና የቴክኒክ ስልጠና ብቃታቸው በተረጋገጠ ባለሙያዎች እንዲሰጥ ያስተባብራል፣ይመራል፣ ድጋፍና

ክትትል ያደርጋል።

5.6. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ተግባርና ኃላፊነት

ሀ. የተሟላና ለውጤታማነት የሚያበቃ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ይሰጣል፤

ለ. አዋጭ ቴክኖሎጂዎች በመተንተን መምረጥ፣ የዲዛይንና ናሙና ማዘጋጀትና ፈትሾ በማረጋገጥ ለአብዥዎች

ስልጠና በመስጠት ያሰራጫል፣

ሐ. ለሰው ሃይል ልማት፣ለቴክኖሎጂ አቅርቦትና ለኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስልጠና ማንዋል ያዘጋጃል፣

መ. ተለይተውና ተመልምለው የቀረቡላቸውን ሰልጣኞች በተዘጋጀው የስልጠና ማንዋል መሰረት ስልጠና

በመስጠት ስልጠናውን በተገቢው ሁኔታ ላጠናቀቁ የስልጠና ማጠናቀቂያ ማስረጃ ይሰጣል፣

ሠ. ልዩ ፍላጎት ላላቸውና ለሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልዩ የሥልጠናና ምክር አገልግሎት

ይሰጣል፣

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 37


ረ. በኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ መሠረት ተፈላጊ፣ ጥልቀትና ስፋት ያለው ለተወዳዳሪነት የሚያበቃ

የኩባንያ ውስጥ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት ይሰጣል፣

ሰ. ሠልጣኞች ለሙያ ብቃት ምዘና እንዲዘጋጁ ድጋፍ ይሰጣል፣

ሸ. የንግድ ልማት አገልግሎት መረጃዎች በንግድ ልማት አገልግሎት /BDS/ የፋይል አደረጃጀት ስልት

ለእያንዳንዱ የምክር አገልግሎት ተቀባይ ማለትም ድርጅት ወይም ግለሰብ የሚከተሉትን ፎርማቶች

በመጠቀም በተገቢው ማደራጀት፣ የነባራዊ ሁኔታ ትንተና (Situation Analysis) የተግባር መርሀ -ግብር

(Action Planning) የምክር አገልግሎት የተሰጠበት ሪፖርት (Report on BDS Delivery) ያዘጋጃል፣

ቀ. የመሳሪያ ኪራይ አገልግሎት መስጠትና የመለዋወጫ ዕቃዎችን በመሥራት በአካባቢያቸው ለሚገኙ ጥቃቅንና

አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ያደርጋል፣

በ. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ባለሙያዎችም ያስመድባል፣

ተ. በጥገና አገልግሎት ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች በሥራቸው የበቁ ይሆኑ ዘንድ ሥልጠናና ድጋፍ ይሰጣል፣

ቸ. በቴክኖሎጂ አመራረት ሂደት፣ በምርት ጥራትና ምርታማነት፣ በዲዛይን፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ

ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሥራ ላይ ስልጠናና ምክር አገልግሎት ይሰጣል፣

ከ. ለንግድ ስራ አመራርና ለቴክኒክ ስልጠና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች (የሠው ሐይል፣ የፋይናንስ፣ የማሰልጠኛ

መሣሪያዎች) መሟላታቸውን በማረጋገጥ ገበያ መር ሥልጠና ይሰጣል፣

አ. የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከማምረቻ መሳሪያዎችና ቴክኖሎጂዎች ጋር በተያያዘ ያሉባቸውን

ችግሮችና ክፍተቶች በተመለከተ ዝርዝር ጥናት ያደርጋል፣

ነ. ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ስለ ቴክኖሎጂና ማምረቻ መሣሪያዎች አጠቃቀም፣ አያያዝና ጥገና

ሥልጠናና የምክር አገልግሎት ይሰጣል፣

በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ከተጠቃሚዎች የሚጠበቁ ኃላፊነቶች

1. በሙሉ ፍላጎት ብቻ ተመስርቶ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን፣


2. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ሰጪ አካልም ሆነ ለሌላ ከሥራው ጋር ተያያዥነት ላለው አካል

ትክክለኛ መረጃ መስጠት፣


3. ከኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ሰጪው አካል ጋር በተዘጋጀው የድርጊት መርሀ-ግብር እና

የአገልግሎት የውል ስምምነት መሠረት የድርሻውን መወጣት፣


4. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ወጪን በገባው የውል ስምምነት መሰረት የመክፈል፣
5. ህጋዊ ባልሆነ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለመሳተፍ፣

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 38


6. ከኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ኤጀንት ጋር በምክር አገልግሎት ውል ከተቀመጠው ውጪ ተገቢ

ያልሆነ ግንኙነት ያለመፍጠር፣


7. ከኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ኤጀንት ጋር የገባውን ቀጠሮ የማክበር ችግር ካጋጠመውም

አስቀድሞ የማሳወቅ።

6. ተቀፅላዎች
መሰረታዊ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ቅፆች

የሂሳብ አርዕስት /Account Classification/፡-ማለት እያንዳንዱ ሂሳብ በሂሳብ ቋት /ledger/ ውስጥ በሚመዘገብበት ወቅት
የሚሰጠው ስያሜ ነው፡፡

የሂሳብ አርዕስቶች የሚከተሉትን 5 ዋና ዋና አርዕስቶች መያዝ ይኖርባቸዋል::

 የሀብት ዋና መደብ /Assets Division/

 የዕዳ ዋና መደብ /Liabllity Division /

 የካፒታል ዋና መደብ /Capital Division /

 የገቢ ዋና መደብ / Revenue Division /

 የወጪ ዋና መደብ /Expenses Division / ናቸው፡፡

እነዚህ ዋና ዋና መደቦች እያንዳንዳቸው በሥራቸው በርካታ የሂሣብ ርዕሶች ይኖሯቸዋል፡፡

የሂሳብ መዋቅር /Chart of Accounts /

 ዋና መደቦችን፣ የሂሣብ ርዕሶችንና/Account Titles / የሂሳብ መለያ ቁጥሮችን/Account Numbers/ በቅደም ተከተል
በዝርዝር የያዘ ሠንጠረዥ የሂሣብ መዋቅር/ Chart of Accounts / በመባል ይታወቃል፡፡

 የሂሳብ መለያ ቁጥር ማለት እያንዳንዱ የሂሳብ አርዕስት በቀላሉ ለመለየት እንዲቻል የሚሰጥ መለያ ቁጥር ነው፡፡

 የሂሣብ ርዕሶች ማለት በዋና ምድብ ስር ያሉ ዝርዝር የሂሳብ ስሞች ናቸው፡፡

የሂሣብ መዋቅር

የሂሣብ መደቦችና ርዕሶቻቸው የሂሣብ መለያ የሂሣብ መደቦችና የሂሣብ

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 39


ቁጥር ርዕሶቻቸው መለያ ቁጥር

1. ሀብት/Assets/ 100 4.ገቢ /Revenue/ 400

ጥሬ ገንዘብ 101 ሽያጭ ገቢ 401

ያልተሸጠ ዕቃ 102 ልዩ ልዩ 402

ተሰብሳቢ ሂሣብ 103 5. ወጪ /Expenses/ 500

የፅዳት ዕቃ 104 የደመወዝ ወጪ 501

የፅዳት መሣሪያ 105 የፅዳት ዕቃ ወጪ 502

ቅድሚያ ክፍያ 106 የጽሕፈት መሣሪያ ወጪ 503

ቋሚ ዕቃ 107 የጉልበት ዋጋ ወጪ 504

2. ዕዳ /Liability/ 200 የባንክ ወለድ ወጪ 505

ተከፋይ ሂሣብ 201 የዕድሳት ወጪ 506

የባንክ ብድር 202 የእርጅና ቅናሽ ወጪ 507

3. አንጡራሀብት /Capital/ 300 መሰብሰብ ያልተቻለ ወጪ 508

ዕጣ /Share/ 301 ልዩ ልዩ ወጪ 509

ስጦታ /Donation/ 302 510

መጠባበቂያ /Reseve Fund/ 303

በሁለትዮሽ የሂሳብ አያያዝ ስርአት የዋና የሂሳብ መደቦች የሚጨምሩበትን፣የሚቀንሱበትንና የመደበኛ ሚዛናቸውን
አመዘጋገብ የሚያሳይ ሰንጠረዥ

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 40


ተ.ቁ የሂሣብ ዋና መደብ ሲጨምር ሲቀንስ መደበኛ ሚዛን /ኖርማል
ባላንስ/

1 ሀብት /Asset/ ዴቢት ክሬዲት ዴቢት

2 ዕዳ /Liability/ ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት

3 ካፒታል /Capital/ ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት

4 ገቢ /Revenue/ ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት

5 ወጪ /Expenses/ ዴቢት ክሬዲት ዴቢት

የገቢ መዝገብ

የ------------------ ኢንተርፕራይዝ የገቢ መዝገብ ገፅ ገ 001

ቀን ወር ዓ/ም ዝርዝር መግለጫ የገቢ ካርኒ ጥሬ ገንዘብ ሽያጭ ዕጣ መመዝገቢያ


ቁጥር
Cr Cr Cr
በእጅ በባንክ

Dr Dr

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 41


የግዥ መዝገብ/Purchase Journal/

የ------------------ ኢንተርፕራይዝ የገቢ መዝገብ ገፅ ገ 001

ቀን አቅራቢ ማ.ቁ ተከፋይ ሂሳብ


Cr

5.1. የሽያጭ መዝገብ /sales Journal/

የ------------------ ኢንተርፕራይዝ የገቢ መዝገብ ገፅ ገ 001

ቀን ከፋይ ማ. የሚሰበሰብ ሒሳብ

ቁ. Dr

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 42


የጥሬ ገንዘብ መቆጣጠሪያ ቅጽ

ቀን መግለጫ ማ.ቁ ገቢ ወጪ ሚዛን

5.2. የሂሳብ ቋት ማሳያ /general ledger/

የሂሳብ አርዕስት ---------------- የሂሳብ መለያ ቁጥር---------

ቀን መግለጫ ማ.ቁ. ዴቢት ክሬዲት ሚዛን

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 43


5.3. ረዳት ቋት/Subsdiary Ledger/

መቆጣጠሪያ/controlling ledger/ ድርጅቱ ከሁሉም ደንበኞች ምን ያህል እንደሚያሰባስብና እንዲሁም


ለአበዳሪዎቹ ምን ያህል እንደሚከፋፈል ጥቅል መጠኑን የሚያሳይ ሲሆን ረዳት ቋት ግን ከማን ምን ያህል መሰብሰብ
እንዳለበትና ለማን ምን መከፈል እንዳለበት የሚያሳይ በየደንበኛው ስምና አድራሻ በተናጠል የሚዘጋጅ የቋት
ዓይነት ነው።

የተከፋይ/ከፋይ ሥም -----------------------------------

አድራሻ፡- ክ/ከተማ---------------- ወረዳ-------------- ቀበሌ----------------- ስልክ-------------------

ቀን መግለጫ ማ.ቁ. ዴቢት ክሬዲት ሚዛን

--------------------- ጥ/አ/ኢንተርፕራይዝ

የሂሳብ መሞከሪያ ሚዛን

ሰኔ 30/2004 ዓ/ም

ተ.ቁ. የሂሳብ አርዕስት ማመሳከሪያ ዴቢት ክሬዲት

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 44


የ ------------ ኢንተርኘራይዝ
የትርፍና ኪሳራ መግለጫ
ከ ------------ እስከ ----------

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 45


ዕዳና ካፒታል

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 46


5.4. የሂሳብ አያያዝ ኡደት

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 47


ከላይ በዝርዝር የተገለጹት ድጋፎች ኢንተርፕራይዞች ያሉባችውን ችግሮች በመለየት የኢንተርፕርነርሺፕ ክህሎት
አቅማቸውን መገንባት ያስችላል ተብሎ ይታመናል፡፡ ሆኖም ግን በትክክል የተፈለገው ውጤት መምጣቱን
ለማረጋገጥ በውጤት ተኮር የስልጠና ስርዐቱ መሰረት ከስልጠናና ድጋፍ በኃላ አንቀሳቃሾች የብቃት ማረጋገጫ
ምዘና መውሰድና ብቃታቸው መረጋገጥ አለበት፡፡

እንዲሁም በተሰጠው ድጋፍ ያፈሩት ሀብት ሌላው የድጋፉን ውጤታማነት መለኪያ መሳሪያ በመሆኑ ከድጋፍ በኋላ
ያፈሩትን ሀብት መረጃ መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ የደረጃ ዕድገታቸውም ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚታይ ጉዳይ ይሆናል፡፡

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾችን የማብቃት ኃላፊነት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እንደመሆኑ


መጠን የኢንተርፕርነርሽፕ አቅም ግንባታ ስልጠና የሚሰጠው በየሙያው አሰልጣኞች ነው። ይህንንም ለመተግበር
የየሙያው አሰልጣኞች በቅድሚያ የኢንተርፕርነርሽፕ ስልጠናን ከሙያ ደረጃ ጋር አያይዞ ለማሰልጠን የሚያስችል
ብቃታቸው መገንባት ስላለበት በየተቋማቱ የሚገኙ የኢንተርፕርነርሽፕ አሰልጣኞች ሰፊ ስራ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለዚህም የየተቋማቱ አመራር ፕሮግራም በማውጣትና አስፈላጊውን ግብዐት በሟሟላት የኢንተርፕርነርሽፕ


አሰልጣኞች የሌሎች ሙያ አሰልጣኞችን የሚያበቁበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህንንም በማድረግ
አንቀሳቃሾች ሁሉንም (አራቱንም) ድጋፎች በአንድ አሰልጣኝ ማግኘት እንዲችሉ ያደርጋቸዋል። በመሆኑም
አሰልጣኙም ሆነ ሰልጣኙ የንግድ ሥራ አመራርን ከሙያው ጋር አያይዞ በቀላሉ እንዲረዳው ያደርጋል፡፡

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት አተገባበር መመሪያ፣ መጋቢት 2006 48

You might also like