Ngo Coordinator III

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

I. አጠቃላይ መግለጫ
የመሥሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
በግብርና ሚኒስቴር የአደጋ መከላከልና የለጋሾች ድርጅቶች አስተባባሪ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያና ፈጣን
ዝግጁነት እና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ባለሙያ III ምላሽ ዳይሬክቶሬት
የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት በሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር/ቢሮ ብቻ የሚሞላ
ለለጋሾች ድርጅቶች ማስተባባሪያ ቡድን መሪ የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ

መሥሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ ውጤቶችና ተግባራት፤


2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-
 ለጋሽ ድርጅቶች የሚያቀርቡትን ፕሮፖዛሎችንና መሠረታዊ ውሎቻቸውን በመመርመርና ፣ የለጋሽ ድርጅቶችን ሥራዎች በተገባው ውልና ግዴታ መሰረት መሆኑን
በመከታተል ድርጅቶች ለሃገሪቱ ማብረከት የሚገባቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማድረግ ነው፡፡
ውጤት 1፡- ለጋሽ ድርጅቶች የሚያቀርቡትን ፕሮፖዛሎችንና መሠረታዊ ውሎቻቸውን መመርመርና
 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ስራ ከመጀመራቸው በፊት የፕሮጀክት ፕሮፖዛልና ዓመታዊ የድርጊት መርሐ ግብር ማቅረባቸውንና ሰነዱ በትክክል
መሟላቱን በማጣራት የተዘጋጀውን ቅፅና የቀረጥ ነፃ ዲክላራሲዮን ይመዘግባል፤
 ድርጅቶች መሠረታዊ ውል እንዲፈርሙ የውል ሰነዱን በማጣራት ያስተላልፋል፤
 የውል ሰነዶች ከተፈረሙ በኋላ፣ በተወሰነ ጊዜ እንዳስፈላጊነቱ ለሚመለከታቸው የመንግስት መ/ቤቶች፣ ክልሎች ወይም የዕርዳታ ድርጅቶች
እንዲደርሱ ያደርጋል፤
 ከበጎ አድራጎትና ማህበራት ኤጀንሲ የሚላኩትን የፕሮጀክት ፐሮፖዛል ሰነዶች ትክክለኛነት ይመረምራል፤
 ለሀገር በቀልም ሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንደየፕሮጀክቱ ዓይነት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፣
 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከውጭ ያገኙት ንብረት በትክክል ለተፈቀደላቸው ዓላማ መዋሉን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤

ውጤት 2 ፡-የለጋሽ ድርጅቶችን ሥራዎች በተገባው ውልና ግዴታ መሰረት መሆኑን መከታተል፤
 መያዶች ከውጭም ሆነ ውስጥ የሚያገኙትን የሀብት አጠቃቀም ሪፖርት መነሻ በማድረግ የኦዲት ምርመራና ግምገማ ማድረጋቸውን ይከታተላል፤
 ŸýaË¡„‹ Ò` kØ ታ ¾e^ Ó”–<’ƒ vKv†¨< ¾e^ SÅx‹ L ይ ¾¨<ß ²?Ô‹ እ”Ç=kÖ\ ¾T>Ák`ቡ ƒ” ØÁo‹ ›Óvw’ƒ ÃS[U^M፤ በአትዮጵያውያን
የሚሸፈንበትን ሁኔታ ላይ ሃሳብ ይሰጣል፣
 ሥራውን በሚመለከት የፕሮጀክት ክተትልና ግምገማ የአሠራር ሂደትን ለማሻሻል ወይም የአሠራር ስልትን ለመቀየስ በሚደረገው የምርጥ ተሞክሮ
ትግበራ ላይ ተሳትፎ ያደርጋል፤ ሥልጠናም ይሠጣል፤
 ለፕሮጀክት ፕሮፖዛልና መሠረታዊ ውሎች የሚረዱ የተሻሻሉ ፎርማቶችን/ቅፆችን ያዘጋጃል፣
 በተገባው ውል መሠረት በሥራ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን የሥራ አፈፃፀም በቦታው ላይ በመገኘት በየጊዜው ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፤
 የየድርጅቶቹ መሠረታዊ ውሎች የሥራ ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት ድርጅቶቹ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲያዘጋጁ ያደርጋል፤የሥራ አፈፃፀም
ሪፖርቱንም ለግምገማ ያቀርባል፤
 የድርጅቶቹ የሥራ ጊዜ ሲጠናቀቅም ስለ ፕሮጀክቱ ግምገማ ያካሄዳል፤
 ስለ ሥራ አፈፃፀሙ ለኃላፊው ሪፖርት ያቀርባል፡፡

III. የሥራው ባህርይ መግለጫዎች፤


3.1. የሥራ ውስብስብነት፡-
 ሥራው ሀገር በቀልም ሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በማስተባባርን ፣ ከውጭም ሆነ ከሀገር ውስጥ የሚገኘውን ንብረትና ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ
መዋሉን መከታተልን፤ የተቀረፁ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎችንና መሠረታዊ ውሎችን መመርመርን፤ ድርጅቶቹ በገቡት ግዴታና ውል መሠረት ሥራቸውን
ስለ ማከናወናቸው መቆጣጠርን የሚጠይቅ ሲሆን ከውጭም ሆነ ከሀገር ውስጥ የሚገኘውን ንብረትና ገንዘብ ፕሮጀክቱ ከታለመለት ዓላማ ውጭ ለሌላ
ዓለማ ማዋል፣ በለጋሽ ድርጅቶች ፕሮጀክት ላይ ደካማ የሆነ የሥራ አፈፃፀም መከሰት፣ በስራ ክንውን ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮች ሲሆኑ እነዚህን
ችግሮች ከድርጅቶቹ ጋር የጋራ ውይይት በማከሄድና ያላሰለሰ የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም ድጋፍ በማድረግ ይፈታሉ፡፡
3.2. ራስን ችሎ መሥራት፡-
3.2.1. ሥራው የሚከናወንበት አግባብ፡-
 ሥራው ለጋሽ ድርጅቶችን ለማስተባበር የወጣውን ድንብና መመሪያ እንዲሁም ከቅርብ ኃፊው የሚሰጠውን አጠቃላይ መመሪያ መሰረት በማድረግ
ይከናወናል፡፡

3.2.2. ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ


 ሥራው ደንቦችና መመሪያዎችን ተከትሎ የጥራት ደረጃውን ጠብቆ ሰለመከናወኑ በመጨረሻ ላይ በቅርብ ኃላፊው ይገመገማል፡፡

3.3. ተጠያቂነት
3.3.1. ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት፡-
 ሥራው ሀገር በቀልም ሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በማስተባባር ፣ ከውጭም ሆነ ከሀገር ውስጥ የሚገኘውን ንብረትና ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ
መዋሉን መከታተል፤ የተቀረፁ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎችንና መሠረታዊ ውሎችን መመርመር፤ ድርጅቶቹ በገቡት ግዴታና ውል መሠረት ሥራቸውን
ማከናወናቸውን መከታተልና መቆጣጠር፤ የሚጠይቅ ሲሆን፣ ይህ በአግባቡ ባይከናወን የዘርፉን፣ የሌሎች ስራ ዘርፎችንና፣ የሌሎች አቻ ተቋማትን

የሥራ መስተጓጎል ያስከትላል፤ በተቋሙ ዕቅድ አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡

3.3.2. ተጠያቂነት ለምስጢራዊ መረጃ፤


 የለበትም፤
3.4. ፈጠራ፡-
 ሥራው የተለያዩ የፕሮጀክት ፕሮፖዛልና መሠረታዊ ውሎችን ለመቅረፅ የሚረዱ ወጥነት ያላቸው ፎርማቶችን ማዘጋጀትና የክትትልና ቁጥጥር
ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ የሚያፍዙ አሰራሮችን ማመንጨት ፣ የውሳኔ ሃሳብ ማመንጨት ፣ ይጠይቃል፡፡

3.5. የሥራ ግንኙነት/work communication/፤


3.5.1. የግንኙነቱ ደረጃ ፤
 በውስጥ ከቅርብ ሃላፊው፣ ከስራ ዘርፉ ባለሙያዎች፣ ከሌሎች የስራ ዘርፎች ባለሙያዎች፣ ከውጭ ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች
ባለሙዎች ጋር ግንኙነት ያደርጋል፡፡

3.5.2. የግንኙነቱ ዓላማ/አስፈላጊነት፤


 የሥራ ትዕዛዝ ለመቀበል፣ የፕሮጀክት ውሎችን በመመርመርና በማቅረብ ሂደት መረጃ ለመስጠትና ለመቀበል፣ በጋራ ለመስራት፣ የፕሮጀክት
ፕሮፖዛልና መሠረታዊ ውሎችን መርምሮ ለማረጋገጥ፣ የውሳኔ ሃሳብ ለመስጠት፣ በሥራ አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ እንዲሁም የፕሮጀክት
ንብረቶችን በማረካከብ ሂደት ላይ ክትትል ለማድረግ ግንኑኘት ያደርጋል፡፡
3.5.3. የግንኙነቱ ድግግሞሽ፤
 ሥራው ከሥራ ሰዓቱ 25 30 % የሚደርስ ግንኙነት ያደርጋል፡፡

3.6. ኃላፊነት
3.6.1. ኃላፊነት ለሰው ሀብት
 የለበትም፡፡

3.6.1.1. በኃላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት


 የለውም፡፡
3.6.1.2 የኃላፊነት ዓይነትና ደረጃ
 የለውም፡፡
3.6.2. ኃላፊነት ለንዋይ
 የለበትም፡፡
3.6.3. ኃላፊነት ለንብረት
 ሥራው በሚከናወንበት ወቅት ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ እንደ ኮምፒዩውተር(ዴስክቶፕና ላፕቶፕ)፣ ፕርንተር፣ ጠረጴዛና ወንበር፣ ሼልፍ፣ ካልኩሌተር
የመሳሰሉትን ዋጋቸው እስከ ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) የሚደርሱ ንብረቶችን በአግባቡ የመያዝና እንዳይበላሹም በጥንቃቄ የመጠበቅ ኃላፊነት
አለበት፡፡
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት፡-
 ሥራው ሀገር በቀልም ሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በማስተባባርን ፣ ከውጭም ሆነ ከሀገር ውስጥ የሚገኘውን ንብረትና ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ
መዋሉን መከታተል፤ የተቀረፁ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎችንና መሠረታዊ ውሎችን መመርመር፤ ድርጅቶቹ በገቡት ግዴታና ውል መሠረት
ሥራቸውን ማከናወናቸውን መከታተል የሚጠይቅ ሲሆን፣ ይህም እስከ 55 % የአዕምሮ ጥረትን ይጠይቃል፡፡

3.7.2. ስነልቦናዊ ጥረት/Emotional effort/


 ለጋሽ ድርጅቶችን ሥራዎች በመከታተል ሂደት እና የፕሮጀክቱን ንብረት ከታለመለት ዓላማ ውጭ አገልግሎት ላይ በማዋላቸው ምክንያት
የሚፈጠሩ አለመግባባቶችና ክርክሮች ስነ ልቦናን የሚፈታተኑ ሲሆኑ ይህንንም በትዕግስትና በተረጋጋ ስሜት ተቋቁሞ መስራትን ይጠይቃል፡፡
3.7.3. የዕይታ ጥረት
 ከምፒዩተር በመጠቀም መጻፍና ማንበብ እይታን የሚያደክም ሲሆን ከሥራ ሣዓቱ 25 በመቶ ይወስዳል፡፡

3.7.4. የአካል ጥረት


 ሥራው በአብዛኛው ጊዜ 80% በመቀመጥና 20% ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ይከናወናል፡፡
3.8. የሥራ አካባቢ ሁኔታ
3.8.1. ሥጋትና አደጋ
 ሥራው ሥጋትና አደጋ የለበትም፡፡

3.8.2. የጤና ጠንቅ፣


 ሥራው በሚከናወንበት ወቅት የጤና ጠንቅ የለበትም፣

3.9. እውቀትና ክህሎት፣


3.9.1. የትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት አይነት
መጀመሪያ ድግሪ፤/ሁለተኛ ዲግሪ በግብርናና በሶሻል ሳይንስ (ማህበራዊ ሳይንስ) ግምገማ፤በዓለም ዓቀፍ ግነንኙነትና
ፖልቲካል ሳይንስ እና በሌሎች በተመሳሳይ የትምህርት መስክ፤

3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ


የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
4 ዓመት መያድን በማስተባበር፣በፕሮጀክት ክትትልና ግምገማ፤እርዳታ
ፕሮገራሞች በዓለም ዓቀፍ ግነንኙነትና ሌሎች ተዛማች የስራ
የሥራ ዝርዝሩን ያዘጋጀው ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like