Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 15

ፖሊሲ JK-R- የተማሪ ፀባይ እና ሥነ ምግባር መመሪያዎች

መግቢያ
የሚከተሉት የተማሪ ፀባይ እና ሥነ ምግባር መመሪያዎች ለት/ቤት ቦርድ ፖሊሲ JK - የተማሪ ሥነ ምግባር አፈጻጸም የተዘጋጁ
ናቸው። እነዚህ መመሪያዎች የተቀረጹት በፖሊሲ JK ውስጥ እንዲሁም በፌደራል እና የስቴት ሕጎች እና በአካባቢ መመሪያዎች ውስጥ
ከተቀመጡ ጠቅላላ ዓላማዎች እና መርሆች ጋር እንዲጣጣሙ ተደርገው ነው።

ክፍል አንድ፦ የት/ቤት ሥነ ምግባር አስተዳድር


1-1 የሥነ ምግባራዊ ተሞክሮዎች መገለጫ ባሕርያት
ሀ. መልካም/ውጤታማ ሥነ ምግባራዊ ልምዶች የሚከተሉት ባሕርያት ይኖሯቸዋል:-
1. ግልጽ፣ ምክንያታዊ እና ሰዓት አካባሪ መሆን
2. አመዛዛኝ፣ ፍትሃዊ፣ ወጥ መሆን እና እድሜን የሚመጥን ውጤቶችን የሚያስከትሉ ይሆናሉ።
3. የተለያዩ የመከላከያ እና የእርምት እርምጃዎችን ያካትታሉ
4. በበቂ ሁኔታ የወላጅ/የአሳዳጊ እና የተማሪ ተሳትፎን ይፈቅዳሉ
5. በተማሪዎች ሀሳቦች እና ስሱነት/ስሜታዊነት ውስጥ ለግለሰብ ልዩነቶች ምላሽ ይሰጣሉ
6. ለተማሪዎች ትምህርት የማግኘት ዕድልን ያረጋግጣል።
7. በመጥፎ ሥነ ምግባር ተሳታፊ የሆኑ ተማሪዎች ፍላጎቶችን፣ በመጥፎ ሥነ ምግባሩ ተጎጅ የሆኑ ተማሪዎች ፍላጎቶችን፣ እና
የአጠቃላይ የት/ቤቱ ማኅበረሰብን ፍላጎቶችን ያስተናግዳል።

1-2 የሠራተኞች ስልጠና


ሀ. የሠራተኞች ስልጠና በእያንዳንዱ ት/ቤት ውስጥ የሥነ ምግባር ፕሮግራም ውጤታማ መሆኑን ለማረጋገጥ እና አግባብነት ያላቸው
ፖሊሲዎችና መመሪያዎች በፍትሃዊነት/በእኩል ሁኔታ ሥራ ላይ መዋላቸውን ለማረጋገጥ እንዳስፈላጊነቱ ይሰጣል።

1-3 ከአድሎ የነፃ መሆን


ሀ. ይህን ፖሊሲ ለማስፈጸም ኃላፊነት ያለበት የት/ቤት ዲስትሪክት ሠራተኛ በብሔር፣ በዘር፣ በቀለም፣ በሃይማኖት፣ በመጡበት ቦታ፣
በዘር ግንድ፣ በፆታ፣ በፆታ ምርጫ፣ በእድሜ፣ ወይም በአካል ጉዳተኝነት ምክንያት ያለማዳላት ማስፈጸም ይገባቸዋል።
ለ. የአካል ጓዳተኛ ተማሪዎች ሥነ ምግባር በታየት ያለበት ከተማሪው የግል ትምህርት ፕሮግራም (IEP)፣ ከባሕርይ እርማት እቅድ፣
ከእቅድ 504፣ እና ከJKF ቦርድ ፖሊሲ (የአካል ጓዳተኛ ተማሪዎች ሥነ ምግባር ) አንፃር ይሆናል።

1-4 በት/ቤት ሥነ ምግባር ውስጥ የዘር ልዩነቶችን እና ሌሎች የጥብቅ መደብ ልዩነቶችን ማስተካከል/ማረም
ሀ. በት/ቤት ሥነ ምግባር ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የዘር ልዩነትን ለማጥፋት ጥረቶች ማድረግ ይገባል። የሠራተኞች አባላት ከታገዱት፣
ከተባረሩት፣ ወይም ለህግ ተላልፈው ከተሰጡት ተማሪዎች መካከል በታሪክ ከፍተኛ ውክልና የነበራቸው በዘር እና በብሔር ቡድኖች
ወይም ሌሎች ጥበቃ የሚደረግላቸው መደቦች ተማሪዎች ላይ የሚያደርጓቸውን ድርጊቶች ያለውን ተጽዕኖ የመቆጣጠር የተለየ ኃላፊነት
አለባቸው።

1-5 የሥነ ምግባር እርምጃ ሊወሰድበት የሚገባው ተማሪ ፀባይሀ. ተማሪው በክፍል ውስጥ፣ በት/ቤት ህንፃዎች ውስጥ፣ በት/ቤት
መጫዎቻ ቦታዎች፣ ወይም በት/ቤት መኪኖች ላይ በአጠቃላይ በዋና ትምህርቶች ወይም ተኳዳኝ ትምህርቶች ጊዜ የሚያደርጋቸው
እንቅስቃሴዎች በት/ቤቱ ውስጥ አደናቃፊ ሊሆኑ የሚችሉ ወይም ለሌሎች ተማሪዎች ወይም የት/ቤቱ ሠራተኞች ጤናማነት ወይም
ደህንነት አስጊ ከሆነ የሥነ ምግባር እርምጃ የሚወሰድባቸው ይሆናል።

1-6 የአንድ ት/ቤት የተናጥል ፖሊሲዎች


ሀ. ከዚህ ፖሊሲ ጋር የሚጣጣሙ እስከሆኑ ድረስ፣ ት/ቤቶች የራሳቸው የት/ቤት ህጎች እና መተዳደሪያ ደንቦች ለማውጣት
ይችላሉ። በአንድ ት/ቤት በተናጥል የወጡ ደንቦች ወይም ሕጎች በዋና ተቆጣጣሪው ወይም በተወካይ የዲስትሪክት ባለስልጣን መጽደቅ
ይኖርባቸዋል። ከዚያም ሥራ ላይ ከመዋላቸው በፊት በዚህ ፖሊሲ ክፍል 1-6 ጋር በሚጣጣም መልኩ ለተማሪዎች እና
ለወላጆቻቸው/አሳዳጊዎቻቸው መሰጠት ይኖርባቸዋል።

1-7 ስርጭት
ሀ. ዲስትሪክቱ ይህን ፖሊሲ በዲስትሪክቱ ድር ጣቢያ እና በእያንዳንዱ ት/ቤት ውስጥ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ይለጥፋል። ይህን
ፖሊሲ እና የት/ቤት ሕጎች ቅጅዎች ለሚጠይቅ ተማሪ እና ወላጅ/አሳዳጊ የሚሰጡ ይሆናል፤ እንዲሁ በጥያቄ ወላጁ/አሳዳጊው በሚረዳው
ቋንቋ የሚተረጎሙ ይሆናል።
ለ. ት/ቤቶች በተናጥል ተማሪዎቻቸውን በዚህ ፖሊሲ እና ባጸደቋቸው ሌሎች የት/ቤት ሕጎች እና መተዳደሪያ ደንቦች ላይ
ተማሪዎቻቸውን እንዲያሰለጥኑ ይበረታታሉ።
ክፍል ሁለት፦ የእርምት እርምጃዎች እና ውጤቶቻቸው
2-1 አጠቃላይ
ሀ. ውጤታማ የት/ቤት ሥነ-ምግባር ፖሊሲዎች በሚቻለው መጠን የተማሪን ትምህርት ከማቋረጥ የሚገቱ ሥነ-ምግባራዊ ምላሾችን
ያበረታታሉ። ት/ቤቶች የመንግስት ሕጎችን፣ የአካባቢ ደንቦችን እና አስገዳጅ ሪፖርት የማድረግ ሕጎችን እስካልተጻረሩ ድርስ ከት/ቤት-
ውጭ የማቆየት ቅጣትን፣ በማባረር ለመቅጣት መሞከርን እና ወደ ሕግ መውሰድን መቀነስ አለባቸው።

2-2 ተመጣጣኝ ቅጣቶች


ሀ. ቅጣቶች ተመጣጣኝ፣ ትክክለኛ፣ በዕድሜ-መሠረት፣ የተማሪውን የጥፋት ዓይነት ጋር የሚጣጣም እና በተጎጂው ግለሰብ እና/ወይም
ማኅበረሰብ ላይ የደረሰ ጉዳትን ያገናዘቡ መሆን አለባቸው። ትርጉም ካላቸው ትዕዛዝ እና መመሪያ ጋር የተሳሰሩ ቅጣቶች (የእርምት
ግብረ-መልስ እና መልሶ ማስተማር) ተማሪዎች ከስህተታቸው እንዲማሩ እና ለት/ቤቱ ማኅበረሰብ መልሰው የሚያበረክቱብትን ዕድል
ይሰጧቸዋል። እናም ተማሪዎች ተመልሰው በትምህርታቸው ላይ በይበልጥ እንዲያተኩሩ የማድረጋቸው ዕድል ከፍተኛ ነው።
ለ. ከፍተኛ ጥቅም እና በደንብ የታወቀ ውጤት ያስገኝ ዘንድ ማንኛውም ቅጣት በጥንቃቄ ሊታቀድ ይገባል። አዎንታዊ ቅጣቶች ለተገቢ
ፀባይ ስልታዊ ዕውቅና መስጠትን ያካትታል፣ ይህም ያ ተገቢ ፀባይ እንዲጎለብት ይረዳል። አሉታዊ ቅጣቶች አንድ ተማሪ ፀባዩ
ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ለማሳወቅ እና ድጋሜም እንዳይፈጽም ለማድረግ የሚነደፉ ናቸው።

2-3 በሥነ ምግባር ጥፋት ላይ እርምጃ በሚውሰድ ጊዜ ሊታዩ የሚገባቸው ጠቃሚ ነገሮች
ሀ. ለተማሪዎቸ ምግባረ-ብልሹነት ቅጣቶችን በመምረጥ ጊዜ መምህራን፣ አስተዳደሮች እና ሠራተኞች የዲስትሪክቱን የት/ቤት ውስጥ
ረብሻዎችን ማጥፋትን እና የተማሪዎችን የትምህርት ጊዜ ማብዛት ዓላማዎችን ማመዛዘን/ማጣጣም ያስፈልጋቸዋል። ተማሪዎችን ሥርዓት
ከማስያዝ/ከመቅጣት አስቀድሞ፣ የሚከተሉት ጉዳዮች ግንዛቤ ውስጥ ይገባሉ፦
1. የዕድሜ፣ የጤና፣ እና የአካል ጉዳተኝነት ወይም የልዩ ፍላጎት ትምህርት ሁኔታ2.
2. የተማሪው አካዳሚያዊ ምደባ ተግቢነት
3 የተማሪው ቀደምት ፀባይ እና የፀባይ ማህደር (ሪከርድ)
4. የተማሪው አመለካከት
5. የወላጅ/አሳዳጊ የትብብር እና የተሳትፎ ደረጃ
6. ጉዳትን ለመጠገን/ለማረም የተማሪው ፈቃደኝነት
7. የጥፋቱ ከባድነት እና ያስከተለው የጉዳት መጠን
8. የክስተቱ በአጠቃላይ የት/ቤቱ ማኅበረሰብ ላይ ያደረሰው ተጽዕኖ
ሀ. ተማሪዎችን ሥርዓት ከማስያዝ/ከመቅጣት አስቀድሞ የተማሪዎችን ምግባረ-ብልሹነት ለማስተካከል የተቀረጹ መከላከያ እና
ማስተካከያ ፕሮግራሞች መኖራቸውን ማየት ያስፈልጋል።

2-4 የእርምት እርምጃዎች


ሀ. ጥፋት በሚከሰትበት ጊዜ፣ ት/ቤቶች ሁኔታዎችን መመርመር እና በተማሪው ላይ ተገቢውን የእርምት እርምጃና ቅጣት ለመወሰን
የሚያስችሉ መረጃዎችን ማሰባሰብ አለባቸው። ይህ ሲሆን ግን ትኩረቱ በተቻለ መጠን በአነስተኛ የት/ቤት ወጭ እና ሀብት የተማሪውን
ብልሹ ምግባር ለማረም/ለማስተካከል ላይ መሆን አለበት። የእርምት እርምጃዎች ለተማሪዎች ከስህተታቸው እንዲማሩ እድል
በመፍጠር መልሰው ትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ ማድረግ አለባቸው። ሁሉም የየእርምት እርምጃዎች የተማሪዎችን ፍላጎት፣
በፀባያቸው በቀጥታ የተጎዱትን ፍላጎት፣ እንዲሁም የአጠቃላይ የት/ቤት ማኅረሰቡን ፍላጎት ያመዛዘኑ ሊሆኑ ይገባል።
ለ. በመምህራን እና በአስተዳድሮች ሊወሰዱ የሚችሉ ሦስት ዓይነት የእርምት እርምጃ ስልቶች አሉ፦ አስተዳደራዊ፣ አገጋሚ/አረጋጊ
/Restorative/፣ እና ክህሎት-ተኮር/ወጌሻዊ (ቴራፒዩቲክ)።
1. አስተዳደራዊ ስልቶች በሕግ የፀደቁ፣ ሕግን መሠረት ያደረጉ፣ ወይም በኮንትራት ደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወሰዱ ስልቶች ሲሆኑ
እንደሚከተሉት ያሉ ናቸው፦
ሀ. ከክፍል ማስወጣት
ለ. በአንድ ውስን ቦት ማቆየት /Detention/
ሐ. እገዳ
መ. ማባረር.
2. አገጋሚ/አረጋጊ /Restorative/ ስልቶች ከአጥፊው ጋር በመሆን የሚደረጉ ችገር ፈቺ እርምቶች ናቸው። በተቻለ መጠን በፍትሕ
ይመራሉ እንዲሁም በደረሰው ጉዳት ላይ እና ሊጠገን/ሊታረም የሚቻልበት ዘዴ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። ስኬታማ የአገጋሚ/አረጋጊ
ፍትሕ ስልት ለእርምት ከሌሎች አጋር ኤጀንሲዎች እና ባለሙያዎች ጋር ትብብርን ሊጠቀም ይችላል። የክስተቱ/የፀባዩ ግምገማ
ይደረጋል፣ ከዚያም ከሁሉም አካላት ጋር የፊት-ለ-ፊት ስብስባ ማደረግ ተገቢ መሆን አለመሆኑን በት/ቤቱ ወይም በዲስትሪክቱ
ይወሰናለ። ለምሳሌ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፦
ሀ. የቤተሰብ ቡድን ስብሰባ
ለ. የተበዳይ እና በዳይ እርቅ
ሐ. የክፍል ውስጥ የሰላም ቡድኖች
መ. የጉዳት ካሳ ክፍያ
3. ቴራፔውቲክ/ሪሶርስ ስልቶች የሚፈጸመው 'በ' በዳዩ ሲሆን የውስጥ መነሳሳትን እና የፀባይ መለወጥን ይጠይቃል። እነዚህ
እርምቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
ሀ. የአዕምሮ ጤና ካውንስሊንግ
ለ. የቁጣ ስሜቶች አያያዝ/አጠባበቅ ትምህርቶች
ሐ. ኢመደበኛ የምክር እና የባሕርይ ስልጠና
ሐ. መምህራን እና አስተዳደሮች የፀባይ ችግሮችን በተለይ የ2ኛ ወይም 3ኛ ጊዜ ጥፋቶችን ለማረም የተለያዩ የስልት ዓይነቶችን ወይም
በርካታ ስልቶችን በአንድ ጊዜ መጠቀምን ማሰብ አለባቸው። ለምሳሌ፣ ሦስቱም የእርምት እርምጃዎች፣ ከሞሊሲው ጋር ተስማምተው፣
በሚከተሉት መንገዶች ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፦
1. በተናጥል (ለምሳሌ፣ ለ1 ቀን ከትምህርት ሰዓት በኋላ አግቶ/ይዞ ማቆየት)
2. አንዱ ለአንዱ ተለዋዋጭ በመሆን (ለምሳሌ፣ የእርቅ ወይም የ1 ቀን)
እገዳ ምርጫ)
3. አንዱ ካአንዱ ጋር በመጣመር (ለምሳሌ፣ ቁጣን የመቆጣጠር ትምህርት እና ግልግል ጋር 2-ት/ቤት ውስጥ ማገት)።
መ. የእርምት እርምጃዎች ከማስታዎሻዎች፣ ትክክለኛ መንገድን ማሳየት፣ የተማሪ/አስተማሪ ስብስባዎች (ኮንፈረንስ) ጀምሮ እስክ ከክፍል
ማስወጣት፣ የፀባይ ኮንትራቶች፣ እገዳዎች፣ የማባረር ማስጠንቀቂያዎች፣ እና/ወይም ለሕግ አሳልፎ እስከመስጠት ድረስ ይጠቀሳሉ።
ሠ. ለተለያዩ የእርምት እርምጃ ዓይነቶች ምሳሌዎች አባሪ «ሀ»ን ይምልከቱ።

ክፍል ሦስት፦ ሥነ ምግባራዊ ወንጀሎች/ጥፋቶች


3-1 ወንጀሎች/ጥፋቶች እና ውጤቶች
ሀ. ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ወንጀሎች/ጥፋቶች ሁለቱንም የደንብ ጥሰቶችን እና የሕግ ጥሰቶችን የያዙ ናቸው። የደንብ ጥሰቶች ከዚህ
በላይ በክፍል 2.4 ውስጥ በተገለጹት የእርምት እርምጃዎች የሚፈቱ ሲሆኑ የሕግ ጥሰቶች ደግሞ በእነዚሁ የእርምት እርምጃዎች ወይም
የወጣት አጥፊዎች እና የወንጀለኛ መቅጫ ሕጎች ሊታዩ ይችላሉ።
ለ. ዲስትሪክቱ እና የትምህርት ቦርዱ አንዳንድ የት/ቤት ውስጥ ጥፋቶች ሌሎች ተማሪዎች ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ ያውቃሉ፣ ስለሆነም
በጥፋቶቹ የተጎዱ ሰዎችን መብቶች ያከብራሉ። ተማሪ ተጥቂ የሆነበት የሕግ ጥሰት ሲፈጸም፣ ት/ቤቱ ለተማሪው ወላጅ/አሳዳጊ
ወዲያውኑ ስለሁኔታው ማሳወቅ እና ት/ቤቱ ምን ምላሽ እየሰጠበት እንደሆን መግለጽ አለበት። በዚሀ ሁኔታ፣ ወላጁ/አሳዳጊው ወደ ሕግ
አካላት መሄድን ሊመርጡ ይችላል፤ ት/ቤቱንም ይህን እንዲያመቻችለት መጠየቅ ይችላል። እነዚያን መብቶች ሙሉ በምሉ እያከብሩ
ዲስትሪክቱ እና የትምህርት ቦርዱ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ክስተቱን በተመለከተ የወጣት አጥፊ እና የወንጀለኛ መቀጫ ሕጎችን
ከመጠቀም ይልቅ እንደ የማረጋጋት/ ይማስተካከል /restorative/ ፍትሕ፣ ግልግል እና ሌሎች የእርምት እርምጃዎች ያሉ አማራጮችን
እንዲጠቅሙ ያብረታታሉ።
1. ለዚህ ክፍል ዓላማ፣ ከዚህ በታች በክፍል 3-1(ሸ) ውስጥ የተዘሩት እና ሌሎችን ተማሪዎች ተጠቂ የሚያደርጉ ጥፋቶች ዓይነት ሁለት
/Type Two/ ትብለው ተመድባልዋል። አንድ የት/ቤት የቢሮ ሰራተኛ አንድ የተወሰነ የሥነ-ምግባር ነክ ጥፋት የሕግ ጥሰት ባሕሪ
ይኑረው አይኑረው እርግጠኛ ካልሆነ የDPS ድህንነት እና ፀጥታ ክፍልን ማማከር ይኖርበታል።
ሐ. የሕግ ጥሰት ተጠቂው ት/ቤቱ ወይም ዲስትሪክቱ በሚሆን ጊዜ ወይም ተጠቂ በማይኖርበት ጊዜ፣ የሚቻል ሆኖ ሲገኝ ለሚከተሉት
ቅድመ-ሁኔታዎች ተገዥ በሆን መልኩ ችግሮች ያለ ሕግ ጣልቃ ገብነት የሚፈቱ ይሆናል።
መ. ሊወሰዱ የሚችሉት ከዚሀ በታች የተዘረዘሩት ቅጣቶች/የእረምት እርምጃዎች ጥፋቱ ማባረርን ያስከትል እንደሆን ወይም «ከት/ቤት
ውጭ መረጃ መጠየቅ /school referra/» ያስከትል እንደሆን ብሥነ-ምግባር መሰላሉ ክፍል 2-3 ውስጥ ተገቢውን ማጣቀሻ
አካቷል። «ከት/ቤት ውጭ መረጃ መጠየቅ /school referral/» የሚያመለክተው በጥፋቱ የተነሳ ከት/ቤቱ ውጭ የሆን ግለሰብን
ወይም አካልን ማነጋገርን (መረጃ መጠየቅን) ያመለክታል። አምስት ዓይነት የውጭ ግለሰብን ውይም አካልን መረጃ ለመጠየቅ አስገዳጅ
መጠይቆች (ሪፈራሎች) አሉ፦
1. ለሕግ አስከባሪ አካል ለማሳወቅ አስገዳጅ ሁኔታዎች
ሀ. ለሚከተሉት ወንጀሎች/ጥፋቶች ተማሪው/ዋ ወደ ሕጋዊ አስፈጻሚ አካል መላክ ይኖርባቸዋል።
i. ት/ቤቱ የተማሪን ሥነ ምግባር ብልሹነት አስመልክቶ ለፖሊስ በሚያሳውቅ ጊዜ ለዚያ ተማሪ ወላጅም/አሳዳጊም ወዲያውኑ
ለማሳወቅ መጣር ይኖርበታል። ተማሪው በሕግ አስፈጻሚ አካላት ቃለ መጠይቅ በሚደረግለት ጊዜ ስለሚኖረው መብት ለማወቅ
ፖሊሲ JIHን ይመልከቱ።
ii. ስለተጠረጠሩ የልጆች ጥቃት፣ ሕገወጥ ፆታዊ ባሕርይ፣ ሕገወጥ ፆታዊ ግንኙነት፣ ወይም ጸያፍ ራቁትነት ፖሊሲ JLF፣ JLF-R፣ እና
የDPS የልጆች ጥቃት እና መተው ፕሮቶኮል መጽሔትን ይመልከቱ። ከ10 ዓመት በታች ያሉ አጥፊዎች የሚላኩት ወደ ዴንቨር የሰብዓዊ
አገልግሎት ዲፓርትመንት /Denver Department of Human Services/ ይሆናል። 10 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ልጆች
ወደ ሕግ አስፈጻሚ አካላት ይላካሉ።
ለ. እነዚህ ወንጀሎች/ጥፋቶች ከዚህ በታች የአስትሪክስ ("*") ምልክት የተደረገባቸው ናቸው።
2. ለሕግ አስከባሪ አካል ለማሳወቅ አማራጭ ሁኔታዎች
ሀ. ለሚከተሉት ወንጀሎች/ጥፋቶች ተማሪው/ዋ ወደ ሕግ አስፈጻሚ አካል ሊላኩ ይችላሉ። ሆኖም፣ ከተቻለ እነዚህ ክስተቶች ያለሕግ
አስከባሪ አካል ጣልቃ ገብነት ሊፈቱ የሚችሉ ናቸው። የት/ቤቱ ባለስልጣን በራሱ ኃላፊነት ለሕግ አስከባሪ አካላት የማሳወቅ ስልጣን
የተለያዩ ጉዳዮችን ግንዛቤ ውስጥ ማካተት ይኖርበታል። እነዚህም ጉዳዮች በእነዚህ ብቻ ባይወሰኑም የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
i. የሥነ ምግባር ጉድለቱ በተለይ የከፋ ዓይነት መሆን አለመሆኑ፤
ii. ተማሪው ባሕርይውን እንዲተው ወይም እንዲያቆም ተነግሮት ሳያቆም በጥፋቱ በመቀጠል የሌሎችን ጤና፣ ደንነት ወይም ሰላም
አደጋ ላይ የሚጥል መሆን እና አለመሆኑን፤
iii. በጥፋቱ ተሳታፊ ሆኖ የተገኘው ተማሪ እድሜ (ለምሳሌ፦ ከ10 ዓመት በታች ያሉ ተማሪዎች ለሕግ አስፈፃሚ መላክ የለባቸውም)፤
iv. ተማሪው ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው መሆን አለመሆኑ፤
v. የተማሪው ጥፋት ሆን ተብሎ ወይም በእንዝላልነት ሌሎች ላይ የአካል ጉዳት ወይም ጤናቸው፣ ሰላማቸው፣ ወይም ደህንነታቸው
አደጋ ላይ ለመጣል የተደረገ መሆን አለመሆኑን፤
vi. ጥፋቱ ሌላ ሰውን መጉዳት አለመጉዳቱን እና ያ ሰው ለሕግ አስከባሪ አካል ማሳወቅ መፈለግ አለመፈለጉን።
ለ. የት/ቤት ባለስልጣን ለፖሊስ ስለማሳወቅ አለማሳወቅ ማንኛውም ጥያቄ ቢኖረው፣ ለፖሊስ ከማሳወቁ በፊት የDPS ደህንነት እና
ፀጥታ ክፍልን ምክር መጠየቅ ይኖርበታል።
ሐ. ት/ቤቱ የተማሪን ሥነ ምግባር ብልሹነት አስመልክቶ ለፖሊስ በሚያሳውቅ ጊዜ ለዚያ ተማሪ ወላጅም/አሳዳጊም ወዲያውኑ
ለማሳወቅ መጣር ይኖርበታል። ተማሪው በሕግ አስፈጻሚ አካላት ቃለ መጠይቅ በሚደረግለት ጊዜ ስለሚኖረው መብት ለማወቅ
ፖሊሲ JIHን ይመልከቱ።
መ. እነዚህ ወንጀሎች/ጥፋቶች ከዚህ በታች ሁለት የአስትሪክስ ("**") ምልክት የተደረገባቸው ናቸው።
3. ለደህንነት እና ፀጥታ ክፍል በግዳጅ መላክ
ሀ. እነዚህ ጥፋቶች ለሕግ አስከባሪ አካላት መመራት እንዳለባቸው ወይም እንደሌለባቸው ለመወሰን ት/ቤቱ የDPS ደህንነት እና ፀጥታ
ክፍልን ማማከር ይኖርበታል።
ለ. እነዚህ ወንጀሎች/ጥፋቶች ከዚህ በታች በሦስት የአስትሪክስ ("***") ምልክት የተደረገባቸው ናቸው።
4. ለአንቀጽ /Title/ IX መኮንን /Officer/
ሀ. ለእነዚህ ጥፋቶች በDPS ፖሊሲ JBB መሠረት የዲስትሪክቱ አንቀጽ IX መኮንን /District Title IX Officer/ መክር መጠየቅ
ይኖርበታል።
ለ. እነዚህ ወንጀሎች/ጥፋቶች ከዚህ በታች በአራት የአስትሪክስ ("****") ምልክት የተደረገባቸው ናቸው።
5. ለእሳት አደጋ ለማሳወቅ አስገዳጅ ሁኔታዎች
ሀ. ለሚከተሉት ወንጀሎች/ጥፋቶች ተማሪው/ዋ ወደ እሳት አደጋ መላክ ይኖርባቸዋል።
ለ. እነዚህ ወንጀሎች/ጥፋቶች ከዚህ በታች አምስት የአስትሪክስ ("*****") ምልክት የተደረገባቸው ናቸው።

የሥነ ምግባር ጥፋት እርምጃዎች

የሥነ ምግባራዊ ጥፋቶች እርምጃዎች


ዓይነት አንድ ጥፋቶች ለዓይነት አንድ ጥፋቶች የት/ቤት ባለስልጣናት በሥነ ምግባር
· የክፍል ውስጥ ረብሻ እርከኑ ውስጥ ደረጃ "ሀ"ን መጠቀም ይኖርባቸዋል (የዚህን ፖሊሲ
· የበዛ አርፋጅነት ክፍል 3-2ን ይመልከቱ)። በአንድ የትምህርት ዘመን ውስጥ
· ሌሎች ተማሪዎችን ማንቋሸሽ፣ ማስጨነቅ ወይም መረበሽ ተመሳሳይ ጥፋቶች ቢከሰቱ፣ የእርምት እርምጃው በእርከኑ ላይ
· ሀይማኖትን/አምላክን የሚያንቋሸሽ ወይም የብልግና ንግግር አንድ ደረጃ ከፍ ይላል (ለምሳሌ ከደረጃ "ሀ" ወደ ደረጃ "ለ" እና
ማድረግ ወዘተ ከፍ እያለ ይሄዳል)።
· የአለባበስ ደንብን መጣስ - ፖሊሲ JICAን ይመልከቱ
· የት/ቤት እንቅስቃሴን በመጠኑ ማቋረጥ ለዓይነት አንድ ጥፋቶች ተማሪዎች ከት/ቤት እንዲባረሩ
· ለባለስልጣን ዝቅተኛ የሆነ አለመታዘዝ (ለምሳሌ፦ ሆን ብሎ አይመከረም። ለዚህ ብቸኛው ልዩነት ለእገዳ የሚያበቃ ተደጋጋሚ
መመሪያን አለመከተል) ጥፋት ተማሪው "የዘወትር አጥፊ" ተብሎ እንዲታወቅ እና
· የቃል ስድቦች ወይም ማዋረዶች እንዲባረር የሚያበቃው በሚሆን ጊዜ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ
· የሞባይል ስልኮችን፣ ተንቀሳቃሽ የኮምፒውተር መጫዎች እና የዚህን ፖሊሲ ክፍል 6-7 ይመልከቱ።
ተመሳሳይ የኤሌክትሪካዊ መሳሪያዎችን ባልተፈቀደ ጊዜ መጠቀም
· የት/ቤት ንብረት ላይ መለስተኛ ጉዳት ወይም ብልሽት
· የትንባሆ ጥፋቶች - ፖሊሲ JICGን ይመልከቱ
· የት/ቤት እቃዎችን ያለፈቃድ መጠቀም
· ቁማር
· አነስተኛ/መለስተኛ የሆነ ከሌላ ተማሪ ጋር የሚደረግ ጠብ
አጫሪነት (ለምሳሌ፦ መገፋፋት፣ መገፍተር)
· በትምህርት ላይ አለመታዘዝ
· ሌሎች በት/ቤት ውስጥ የሚደረጉ መለስተኛ ጥፋቶች/ሥነ
ምግባር ጉድለቶች
ዓይነት ሁለት ጥፋቶች ለዓይነት ሁለት ጥፋቶች የት/ቤት ባለስልጣናት በሥነ ምግባር
· ሐሰተኛ የእሳት አደጋ ደወል መደወል***** እርከኑ ውስጥ ደረጃ "መ"ን መጠቀም ይኖርባቸዋል (የዚህን ፖሊሲ
· ርችቶችን ይዞ መገኘት ክፍል 3-2ን ይመልከቱ)። በአንድ የትምህርት ዘመን ውስጥ
· ትንኮሳ:- ደረጃ I (ለምሳሌ፦ የቃል እና የጽሑፍ ጠብ-አጫሪነት ተመሳሳይ ጥፋቶች ቢከሰቱ፣ የእርምት እርምጃው በእርከኑ ላይ
ወይም ማሸማቀቅ)- ፖሊሲ JICDEን ይመልከቱ አንድ ደረጃ ከፍ ይላል (ለምሳሌ ከደረጃ "መ" ወደ ደረጃ "ሠ" እና
· በዘር፣ በብሔር፣ በፆታ ምርጫ፣ በፆታ ማንነት፣ በአካል ወዘተ ከፍ እያለ ይሄዳል)።
ጉዳተኝነት፣ ወይም በሃይማኖት ምክንያት ማዋከብ/ጭቆና፦ ደረጃ I
(ለምሳሌ፦ የቃል እና የጽሑፍ ማዋከብ/ጭቆና) - ፖሊሲ JBBAን ለዓይነት ሁለት ጥፋቶች ተማሪዎች ከት/ቤት እንዲባረሩ
ይመልከቱ አይመከረም። ለዚህ ብቸኛው ልዩነት ለእገዳ የሚያበቃ ተደጋጋሚ
· ፆታዊ ማዋከብ/ጭቆና፦ ደረጃ I (ለምሳሌ፦ የቃል እና የጽሑፍ ጥፋት ተማሪው "የዘወትር አጥፊ" ተብሎ እንዲታወቅ እና
ማዋከብ/ጭቆና)**** - - ፖሊሲ JBBን ይመልከቱ እንዲባረር የሚያበቃው በሚሆን ጊዜ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ
· በስምምነት የተደረገ ነገር ግን ልክ ያልሆነ አካላዊ ግንኙነት የዚህን ፖሊሲ ክፍል 6-7 ይመልከቱ።
· (ከ$500 በታች የሆነ) የት/ቤት ንብረት ውድመት ወይም
ስርቆት፣ የግድግዳ ላይ ጽሑፍን /graffiti/ ጨምሮ አንድ ተማሪ በሌሎች ደግነት ያላግባብ የመጠቀም ጥፋት ካጠፋ
· በከባድ ሁኔታ ለባለስልጣን እምቢተኝነት/አለመታዘዝ ("trespassing") ወደ ሕግ አካል ሊወሰድ ይችላል፣ ይህ
(ለምሳሌ፦ ለት/ቤት ሠራተኞች በጥቅሉ ክብር አለመስጠጥl) የሚደረገው ግን ተማሪው ግቢውን ለቆ እንዲወጣ ከተጠየቀ በኋላ
· በሌሎች ደግነት ያላግባብ መጠቀም /trespassing/ እምቢ ካለ ይሆነል።
· (ከ$500 በታች የሆነ) ንብረት ከግለሰብ መስረቅ
· የት/ቤቱን አካባቢ የሚረብሽ/ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሚያውክ
ሌላ ምግባረ ብልሹነት/ጥፋት
· ተደጋጋሚ ዓይነት አንድ ጥፋቶች (በሥነ ምግባር እርከኑ ውስጥ
በደረጃ "ሀ" እስከ ደረጃ "ሐ' ውስጥ ካለፉ በኋላ (የዚህን ፖሊሲ
ክፍል 3-2 ይመልከቱ))
ዓይነት ሦስት ጥቃቶች ለዓይነት ሦስት ጥፋቶች የት/ቤት ባለስልጣናት በሥነ ምግባር
· ትንኮሳ-: ደረጃ II (ለምሳሌ፦ አካላዊ የጠብ-አጫሪነት ወይም እርከኑ ውስጥ ደረጃ "ሠ"ን መጠቀም ይኖርባቸዋል (የዚህን ፖሊሲ
ማሸማቀቅ ድርጊቶች)- ፖሊሲ JICDEን ይመልከቱ ክፍል 3-2ን ይመልከቱ)። በአንድ የትምህርት ዘመን ውስጥ
· በዘር፣ በብሔር፣ በፆታ ምርጫ፣ በፆታ ማንነት፣ በአካል ተመሳሳይ ጥፋቶች ቢከሰቱ፣ የእርምት እርምጃው በእርከኑ ላይ
ጉዳተኝነት፣ ወይም በሃይማኖት ምክንያት ማዋከብ/ጭቆና፦ ደረጃ አንድ ደረጃ ከፍ ይላል (ለምሳሌ ከደረጃ "ሠ" ወደ ደረጃ "ረ" እና
II (ለምሳሌ፦ አካላዊ የማዋከብ ወይም የማሸማቀቅ ድርጊቶች እና ወዘተ ከፍ እያለ ይሄዳል)።
የደረጃ I ባሕርይ መድገም )- ፖሊሲ JBBAን ይመልከቱ
· ፆታዊ ትንኮሳ/ውከባ:- ደረጃ II (ለምሳሌ፦ አካላዊ የማዋከብ ለዓይነት ሦስት ጥፋቶች ተማሪዎች ከት/ቤት እንዲባረሩ
ወይም የማሸማቀቅ ድርጊቶች እና የደረጃ I ባሕርይን መድገም)**** አይመከረም። ለዚህ ብቸኛው ልዩነት ለእገዳ የሚያበቃ ተደጋጋሚ
- (የተማሪው ባሕርይ ጥፋት ወደሚባል ደረጃ ያደገ እና ለሕግ ጥፋት ተማሪው "የዘወትር አጥፊ" ተብሎ እንዲታወቅ እና
አስከባሪ አካል ወይም ለዴንቨር የሰብዓዊ አገልግሎቶች እንዲባረር የሚያበቃው በሚሆን ጊዜ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ
ዲፓርትመንት ሪፖርት መደረግ ያለበት መሆን አለመሆኑን የዚህን ፖሊሲ ክፍል 6-7 ይመልከቱ።
ለመወሰን ፖሊሲዎች JBB እና JLF መታየት ይኖርባቸዋል።)
ድብድብ፦ ደረጃ I (እንደ መቆረጥ/መሰንጠቅ፣ መጫር እና
የአፍንጫ መድማት ዓይነት ቀለል ያሉ ጉዳቶችን ሊያካትት ይችላል።
)
· በእፆች/መድሃኒቶች ወይም በአልኮል ተጽዕኖ ስር መውደቅ -
ፖሊሲዎች JICH እና JICH-R ን ይመልከቱ
· አልኮል ወይም ያልተፈቀዱ (ግን ሕጋዊ የሆኑ)
እፆች/መድሃኒቶችን ይዞ መገኘት
· ሕገ ወጥ የሆኑ እፆች/መድሃኒቶችን ይዞ መገኘት**
· የ (ከ$500 - $5000 የሆነ) የት/ቤት ንብረት ውድመት
ወይም ስርቆት፣ የግድግዳ ላይ ጽሑፍን /graffiti/ ጨምሮ**
· (ከ$500 - $5000 የሆነ) ንብረት ከግለሰብ መስረቅ
· በከፍተኛ ሁኔታ የት/ቤቱን አካባቢ የሚበጠብጡ በት/ቤት ግቢ
ውስጥ/አካባቢ የሚደረጉ ሌሎች ጥፋቶች ወይም የሥነ ምግባር
ግድፈቶች
· ተደጋጋሚ የዓይነት ሁለት ጥፋቶች
ዓይነት አራት ጥፋቶች ለዓይነት አራት ጥፋቶች፣ የት/ቤት ባለስልጣናት የሥነ ምግባር
ርከኑን ደረጃ "ረ"ን የሚመለከቱ/የሚያጣቅሱ ይሆናል። የሥነ
· ሕንፃን ለማቃጠል ሆን ብሎ እሳት መለኮስ /Arson/ ምግባር ግድፈቱ/ጥፋቱ የሌሎች ት/ቤቶችን ወይም የት/ቤት
· ድብድብ:- ደረጃ II (እንደ ደረጃ አምስት ጥፋት "1ኛ ወይም ሠራተኞች ጤናማነት ወይም ደህንነት በአደገኛ ሁኔታ ሥጋት ላይ
2ኛ ደረጃ ጥቃቶች" የማይቆጠሩ ነገር ግን በመጠኑ ከፍተኛ የሆኑ የሚጥል ከሆነ እና የተማሪው በት/ቤት ውስጥ መገኘት መቀጠል
ጉዳቶች ጨምሮ)*** (ማሳሰቢያ:- ለሪፖርት ለማድረግ ሲባል እንደ ከበድ ያለ ሥጋት ካለው ተማሪው እንዲባረር ሊደረግ ይሆናል።
3ኛ ደረጃ ጥቃት ይቆጠራሉ)
· (ከ$5000 በላይ የሆነ) የት/ቤት ንብረት ውድመት ወይም ለመታገድ የሚያበቃ ተደጋጋሚ ጥፋት አጥፊው ተማሪን "የዘወትር
ስርቆት፣ የግድግዳ ላይ ጽሑፍን /graffiti/ ጨምሮ** አጥፊ" ሊያስብለው ይችላል። "የዘወትር አጥፊ" ማለት አንድ
· (ከ$5000 በላይ የሆነ) ንብረት ከግለሰብ መስረቅ የተናጥል ጥፋት አይደለም፣ ነገር ግን በስቴት ሕግ መሠረት
· ሌሎች ተማሪዎችን ወይም የት/ቤት ሠራተኞችን ጤናማነት ተከታታይ ምግባረ ብልሹነት በየትኛውም ደረጃ ቢሆን ተማሪው
ወይም ደህነት በከፍተኛ ሁኔታ አደጋ ላይ የሚጥሉ (ርችት ያልሆኑ) "የዘወትር አጥፊ" ተብሎ ሊፈረጅበት እና ሊባረርበት የሚችል
ፈንጅ ነገሮች ይዞ መገኘት* ምድብ ነው። ለበለጠ መረጃ ፖሊሲ JK-R ክፍል 6-7
· እያወቁ/ሆን ብሎ በት/ቤት ሠራተኛ ንብረት ላይ ጉዳት ይመልከቱ።
ማድረስ*
· ጥቃት፣ ወከባ/ትንኮሳ ወይም የት/ቤት ሠራተኛን በውሸት
ጥቃት አድርሶብኛል ብሎ መክሰስ*
· ግልጽ ያልሆኑ /Hazing/ እንቅስቃሴዎች (ለምሳሌ፦ በአንድ
የተማሪ ቡድን ላይ ለማነሳሳት በማለም አንድን ግለሰብ የአካላዊ
ድርጊት ለረጅም ጊዜ እንዲሰሩ ማስገደድ፣ ማንኛውንም
እፅ/መድሃኒት /substance/ በብዛት መጠቀምን ማስገደድ፣
ለረጅም ጊዜ እንቅልፍ፣ ምግብ ወይም መጠጥ መከልከል፣ ወይም
ሌላ ጥንቃቄ የጎደለው እና አደጋ ሊያስከትል የሚችል ማንኛውም
ሌላ ባሕርይ) **
· የልጆች ብዝበዛ *
· ሕገወጥ ፆታዊ ባሕርይ እና/ወይም ፆታዊ ግንኙነት፣ እና/ወይም
ጸያፍ ራቁትነት *
· ምስክርን ማስፈራራት ወይም መበቀል*
· ለት/ቤት ማኅበረሰብ ጤናማነት ወይም ደህንነት ዝግጁ ወይም
ቀጣይ የሆነ አደጋ የያዘ የሌላ ተማሪ ባሕርይ *
· ተደጋጋሚ ዓይነት ሦስት ጥፋቶች**

- የዘወትር አጥፊ (የዚህን ፖሊሲ ክፍል 4-3 ይመልከቱ፤


የዘወትር አጥፊ ተማሪዎች ለሕግ አስከባሪ አካላት ተላልፈው
ባይሰጡም የሚባረሩ ናቸው)

አይነት አምስት ጥፋቶች ለዓይነት አምስት ጥፋቶች የሥነ ምግባር እርከኑ


· ዝርፊያ* አይሠራም/የሚተገበር አይሆንም። እነዚህን ጥፋቶች የሚፈጽሙ
· አንደኛ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት፣ እና የፆታዊ ጥቃት* ተማሪዎች ከ3-10 ቀናት የከት/ቤት ውጭ እገዳ ይጣልባቸዋል፤
· ያልተፈቀዱ እፆች/መድሃኒቶችን ወይም ቁጥጥር እንዲሁም የስቴት ሕግ በሚፈቅደው መሠረት የሕግ አስፈጻሚ
የሚደረግባቸው እፆች/መድሃኒቶችን ማሰራጨት፣ ወይም ለመሸጥ አካል እንዲያውቀው ይደረጋል። ት/ቤቶች የማረር ስብሰባ/ችሎት
ወይም ለማከፋፈል ማሰብ* መጠየቅ ይችላሉ።
· ያለት/ቤቱ ወይም ዲስትሪክቱ ፈቃድ/እውቅና ቢላ ወይም
አደገኛ የጦር መሳሪያ መሸከም፣ ማምጣት፣ መጠቀም፣ ወይም ይዞ
መገኘት (ይህም ከትክክለኛው የእጅ ጠመንጃ ጋር ሊመሳሰል
የሚችል የእጅ ጠመንጃ፣ ተስፈንጣሪ ነገር፣ ወይም እንደ BB
ጥይቶች ያሉ በእምቅ ጋዝ የሚሰሩ፣ ከ3 ኢንች በላይ የሚረዝም
ስለት ያላቸው ቢላዎች፣ ከ3.5 ኢንች በላይ የሚረዝም ስለት ያለው
የኪስ ጩቤ፣ ተስፈንጣሪ ያላቸው ጩቤዎች፣ እና የሞት አደጋ
ወይም ከባድ የአካል ጉዳት ለማድረስ የሚውሉ ወይም ሊውል
የታሰቡ ሌሎች እቃዎች)*
ለዓይነት ስድስት ጥፋቶች የሥነ ምግባር እርከኑ
አይሠራም/የሚተገበር አይሆንም። እነዚህን ጥፋቶች የሚፈጽሙ
ተማሪዎች ከ3-10 ቀናት የከት/ቤት ውጭ እገዳ ይጣልባቸዋል፤
ዓይነት ስድስት ጥፋት እንዲሁም የስቴት ሕግ በሚፈቅደው መሠረት ት/ቤቶች የማረር
በት/ቤት ግቢ ውስጥ የእጅ የጦር መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት* ስብሰባ/ችሎት መጠየቅ እና የሕግ አስፈጻሚ አካል እንዲያውቀው
እንዲያደርጉ ይፈለጋል። በስብሰባው/ችሎቱ ላይ ለተረጋገጠ
የዓይነት ስድስት ጥፋት ቅጣት ለአንድ ዓመት ያህል ከት/ቤት
ማባረር ነው። ይህ ቅጣት ሊሻሻል የሚችለው በዋና ተቆጣጣሪው
ወይም በተወካያቸው ደብዳቤ ብቻ ይሆናል።

ሠ. የDPS ደህንነት እና ፀጥታ ዲፓርትመንት ወንጀል የሚባሉ የት/ቤት ውስጥ ጥፋቶች ዝርዝር ያዘጋጃል። እነዚህ ወንጀሎች የሕግ
መስፈርቶችን ያሟሉ ዘንድ ለሕግ አስከባሪ አካል ሪፖርት መደረግ አለባቸው። እያንዳንዱ ት/ቤት በርዕሰ መምህሩ እና/ወይም በተወካይ
አማካኝነት ስለሁሉም እንዲህ ዓይነት ወንጀሎች ወይም የተጠረጠሩ ወንጀሎች የጽሑፍ ሪፖርት ያቀርባሉ። የሁሉም ሪፖርቶቹም
በዲስትሪክት አቀፍ ተጠናቅሮ በፍጥነት ለሕግ አስከባሪ ሪፖርት ይደረግ ዘንድ ለDPS ደህንነት እና ፀጥታ ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ረ. ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የሥነ ምግባራዊ ጥፋቶች እና የሚያስከትሏቸው ውጤቶች ናቸው፦

3-2 የሥነ ምግባር እርከን


ሀ. በሥነ ምግባር እርከኑ ሥር ስድስት የእርምት እርምጃ ደረጃዎች ተተንትነዋል። አንድ ሥነ ምግባራዊ እርምጃ እንደ ጥፋቱ
ባሕርይ/ሁኔታ እና በተቻለ መጠን በዝቅተኛ ደረጃ መጀምር እና መፈታት አለበት። ተመሳሳይ ጥፋቶች መፈጸም ቢቀጥሉ፣ የእርምት
እርምጃው በእርከኑ ላይ አንድ ደረጃ ከፍ እያለ ይሄዳል (ለምሳሌ ከደረጃ "ሀ" ወደ ደረጃ "ለ")። ሥነ ምግባራዊ ጥፋቶች ወይም
ወንጀሎች የአንድ የትምህርት ዘመን እንዲጠራቀሙ የዚህ ፖሊሲ ፍላጎት ነው። በአንድ የትምህርት ዘመን ውስጥ ለተፈጸመ ጥፋት
ወይም ወንጀል ከፍተኛውን የቅጣት ልክ ወይም የእርከን ደረጃን ለመወሰን ያለፉ የትምህርት ዘመናት ሪፖርቶች እንደ አጠቃላይ ጥቅም
ላይ ሊውሉ አይገባም።
ለ. የሥነ ምግባር እርከኑ ተማሪዎች ወደፊት ጥፋቶችን ማስወገድ እንዲችሉ እገዛ ለመስጠት የሚጠቅም ነው። ለሁሉም የጥፋት
ሪፖርት የማድረጊያ እርከኑ ደረጃዎች የሚሰጡ የእርምት እርምጃዎች በዚህ ፖሊሲ ክፍል 2-4 የተጠቀሱትን ማናቸውንም የእርምት
ዓይነቶችን ሊያካትቱ ይችላሉ።
ሐ. ለተለያዩ የእርምት እርምጃዎች ምሳሌዎች አባሪ "ሀ"ን ይመልከቱ፣ ቀለል ተደርጎ ለተዘጋጀው የሥነ ምግባር ሠንጠረዥ /Matrix/
አባሪ "ለ"ን ይመልከቱ፣ እንዲሁም ቀለል ተደርጎ ለተዘጋጀው የሥነ ምግባር እርከን አባሪ "ሐ"ን ይመልከቱ።

የሥነ ምግባር እርከን

ደረጃ 'ሀ' - መምህር/ተማሪ


• ተማሪው ስለአደጋው/ስለድርጊቱ ከራሱ አንጻር እንዲናገር ዕድል ይሰጠዋል።
• መምህሩ ወይም ተወካይ ሠራተኛ ተማሪው ጋር ይማከራል።
• እንደአስፈላጊነቱ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የእርምት ሂደቶች ይጀመራሉ።
• ማንኛውም የእርምት ሂደት ተሰንዶ (ዶኩመንት ተደርጎ) ይያዛል።

ደረጃ 'ለ' - መምህር/ተማሪ/ወላጅ


• ተማሪው ስለአደጋው/ስለድርጊቱ ከራሱ አንጻር እንዲናገር ዕድል ይሰጠዋል።
• መምህሩ ወይም ተወካይ ሠራተኛ ለተማሪው ወላጅ/አሳዳጊ ያሳውቃል።
• መምህሩ ወይም ተወካይ ሠራተኛ ተማሪው ጋር፣ ከተቻለም ከወላጁ/አሳዳጊው ጋር ይማከራል።
• እንደአስፈላጊነቱ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የእርምት ሂደቶች ይጀመራሉ።
• ማንኛውም የእርምት ሂደት ተሰንዶ (ዶኩመንት ተደርጎ) ይያዛል።

ደረጃ 'ሐ' - መምህር/ድጋፍ ሰጭ ሠራተኛ/ተማሪ/ወላጅ


• ደረጃ 'ለ' ላይ የተወሰዱት የእርምት እርምጃዎች ውጤታማ ካልሆኑ፣ የማኅበራዊ ሕይወት ባለሙያን (ሶሻል ወርከር)፣ ነርስን፣
አማካሪን (ጋይዳንስ ካውንስለር)፣ የሥነ ልቦና ባለሙያን (ሳይኮሎጅስት) ወይም ከት/ቤቱ ደጋፊ ሠራተኞች ሌላ ባልደረባን ማሳተፍ
ያስፈልግ እንደሆነ መምህሩ ወይም ተወካይ ሠራተኛ መወሰን ይችላል።
• ተማሪው ስለአደጋው/ስለድርጊቱ ከራሱ አንጻር እንዲናገር ዕድል ይሰጠዋል።
• ወላጁ/አሳዳጊው ስለግዳዩ እንዲያውቅ ይደረጋል።
• መምህሩ እና ማንኛውም ተሳታፊ የድጋፍ ሠራተኞች አባል ከተማሪው እና (ከተቻለ) ከወላጁ/አሳዳጊው ጋር የተማሪውን ምግባረ
ብልሹነት ስለማረም ስብሰባ ያደርጋሉ። ከተቻለም ሁሉም የተማሪው መምህራን በስብሰባው ላይ የሚገኙ ይሆናል።
• እንደአስፈላጊነቱ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የእርምት ሂደቶች ይጀመራሉ።
• ማንኛውም ለሕግ አስከባሪ ወይም ሌላ አካል የሚደረጉ ሪፖርቶች ወይም የእርምት ሂደቶች ተሰንደው (ዶኩመንት ተደርገው)
ይያዛሉ።

ደረጃ 'መ' - በአስተዳደር ደረጃ የሚደረጉ እርምጃዎች


• ተማሪው ወደ ተገቢው አስተዳዳሪ ወይም ተወካይ ይላካል።
• የተማሪውን ባሕርይ ለማረም የተወሰዱ እርምጃዎች ተሰንደው (በጽሑፍ) ይቀርባሉ።
• ተማሪው ስለአደጋው/ስለድርጊቱ ከራሱ አንጻር እንዲናገር ዕድል ይሰጠዋል።
• አስተዳዳሪው ወይም ተወካይ ሠራተኛ ከወላጁ/አሳዳጊው ጋር አንድ ስብሰባ ያመቻች እና በተጨማሪም ከድጋፍ ሰጭ ሠራተኛ ጋር
መማከር ያስፈልግ እንደሆነ ይወስናል።
• እንደ አስፈላጊነቱ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የእርምት ሂደቶች ይጀመራሉ።
• አስፈላጊ ከሆነ እስከ ሦስት ቀን የሚደርስ የት/ቤት-ውስጥ እገዳ ሊጣልበት ይችላል (ለበለጠ ዝርዝር የዚህን ፖሊሲ ክፍል 6-2 ን
ይመልከቱ)።
• የት/ቤት ባለስልጣናት ለተማሪው የባሕርይ እርምት እቅድ ማዘጋጀትን ማሰብ ይኖርባቸዋል (በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲህ
ዓይነቱ እቅድ አስገዳጅ ሊሆን ይችላል፤ የዚህን ፖሊሲ ክፍል 5-3 ይመልከቱ)።
• ማንኛውም ለሕግ አስከባሪ ወይም ሌላ አካል የሚደረጉ ሪፖርቶች ወይም የእርምት ሂደቶች ተሰንደው (ዶኩመንት ተደርገው)
ይያዛሉ።

ደረጃ 'ሠ' - የእገዳ አማራጮች


• ተማሪው ወደ ተገቢው አስተዳዳሪ ወይም ተወካይ ይላካል።
• የተማሪውን ባሕርይ ለማረም የተወሰዱ እርምጃዎች ተሰንደው (በጽሑፍ) ይቀርባሉ።
• ተማሪው ስለአደጋው/ስለድርጊቱ ከራሱ አንጻር እንዲናገር ዕድል ይሰጠዋል።
• አስተዳዳሪው ወይም ተወካይ ሠራተኛ ከወላጁ/አሳዳጊው ጋር አንድ ስብሰባ ያመቻች እና በተጨማሪም ከድጋፍ ሰጭ ሠራተኛ ጋር
መማከር ያስፈልግ እንደሆነ ይወስናል።
• እንደ አስፈላጊነቱ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የእርምት ሂደቶች ይጀመራሉ።
• ቀደም ሲል የተወሰዱት የእርምት እርምጃዎች ውጤታማ ካልሆኑ፣ ርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ ከ1 እስከ 3 ቀናት የሚደርስ የት/ቤት-
ውስጥ እገዳ ወይም የአንድ ቀን የት/ቤት-ውጭ እገዳ ሊጥሉበት ይችላሉ (ስለ እገዳዎች አጠቃቀም የዚህን ፖሊሲ ክፍል 6-2፣ 6-3 እና
6-4ን ይመልከቱ)።
• የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ለዓይነት አንድ ጥፋቶች የት/ቤት ውጭ ቅጣት አይጣልባቸውም።
• የት/ቤት ባለስልጣናት ለተማሪው የባሕርይ እርምት እቅድ ማዘጋጀትን ማሰብ ይኖርባቸዋል (በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲህ
ዓይነቱ እቅድ አስገዳጅ ሊሆን ይችላል፤ የዚህን ፖሊሲ ክፍል 5-3 ይመልከቱ)።
• ከእገዳ በኋላ ወደ ት/ቤት ሲመለሱ አዎንታዊ ባሕርይዎችን ለማበረታታት ተጨማሪ እርምጃዎች መውሰድ ሊታሰብበት ይገባል።

ደረጃ 'ረ' - ተጨማሪ የእገዳ አማራጮች


• ተማሪው ወደ ተገቢው አስተዳዳሪ ወይም ተወካይ ይላካል።
• የተማሪውን ባሕርይ ለማረም የተወሰዱ እርምጃዎች ተሰንደው (በጽሑፍ) ይቀርባሉ።
• ተማሪው ስለአደጋው/ስለድርጊቱ ከራሱ አንጻር እንዲናገር ዕድል ይሰጠዋል።
• አስተዳዳሪው ወይም ተወካይ ሠራተኛ ከወላጁ/አሳዳጊው ጋር አንድ ስብሰባ ያመቻች እና በተጨማሪም ከድጋፍ ሰጭ ሠራተኛ ጋር
መማከር ያስፈልግ እንደሆነ ይወስናል።
• እንደ አስፈላጊነቱ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የእርምት ሂደቶች ይጀመራሉ።
• ቀደም ሲል የተወሰዱት የእርምት እርምጃዎች ውጤታማ ካልሆኑ፣ ርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ ተጨማሪ ከ1-3 ቀናት የሚደርስ
የት/ቤት-ውስጥ እገዳ እና/ወይም ከ1-3 የሚደርሱ ቀናት የት/ቤት-ውጭ እገዳ ሊጥሉበት ይችላሉ (ስለ እገዳዎች አጠቃቀም የዚህን
ፖሊሲ ክፍል 6-2፣ 6-3 እና 6-4ን ይመልከቱ)።
• የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ለዓይነት አንድ ጥፋቶች የት/ቤት ውጭ ቅጣት አይጣልባቸውም።
• የት/ቤት ባለስልጣናት ለተማሪው የባሕርይ እርምት እቅድ ማዘጋጀትን ማሰብ ይኖርባቸዋል (በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲህ
ዓይነቱ እቅድ አስገዳጅ ሊሆን ይችላል፤ የዚህን ፖሊሲ ክፍል 5-3 ይመልከቱ)።
• ተደጋጋሚ ጥፋት አጥፊው ተማሪን "የዘወትር አጥፊ" ሊያስብለው ይችላል። ይህም ለመባረር የሚያበቃው ሊሆን ይችላል። ለበለጠ
መረጃ የዚህን ፖሊሲ ክፍል 6-7 ይመልከቱ።
• ከእገዳ በኋላ ወደ ት/ቤት ሲመለሱ አዎንታዊ ባሕርይዎችን ለማበረታታት ተጨማሪ እርምጃዎች መውሰድ ሊታሰብበት ይገባል።

ክፍል አራት፦ የክፍል ውስጥ ረባሽ ተማሪዎች


4-1 ከክፍል ማስወጣት
ሀ. በውጤታማ የተማሪዎች ሥነ ምግባር አያያዝ ውስጥ መምህራን ያላቸውን ሚና እና ኃላፊነት ዲስትሪክቱ በሚገባ ያውቃል።
ከረብሻ የጸዳ መማሪያ ክፍል ለመማር ማስተማሩ ሂደት እጅግ አስፈላጊ ነው። አንድ መምህር የመማር ማስተማሩ ሂደቱን ለመከላከል
ሲል አስፈላጊ ነው ብሎ ከገመተ ረባሽ ተማሪን ወደ ሌላ አማራጭ ቦታ ሊያዛውረው ይችላል። የትምህርት ቦርዱ የ"ክፍል ውስጥ
ረብሻ"ን ሆን ብሎ እና ከፍተኛ የሆነ አለመታዘዝ ወይም ግልጽ እና ቀጣይ የሆነ እምቢተኝነት፣ ወይም የት/ቤቱን ወይም የመምህሩን
ተገቢ የሆነ የመማር ማስተማር ሁኔታን የማቅረብ ችሎታ ተደጋጋሚ የሆነ እና በውጤታማ የክፍል አያያዝ እና/ወይም በዚህ ፖሊሲ
ውስጥ በተለዩት የእርምት ስልቶች ሊታረም የማይችል ጣልቃ ገብነት/ማደናቀፍ ሲል ተንትኖታል/ፈትቶታል።
ለ. አንድ ተማሪ ከክፍል እንዲወጣ በሚደረግበት ጊዜ፣ ተማሪው የመማሪያ መጽሐፍቶቹን እና አሳይንመንቶችን ማጠናቀቅ
የሚያስችሉትን የክፍል ሥራዎችን መያዙን መምህሩ ያረጋግጣል። እያንዳንዱ የት/ቤት አመራር ቡድን ("SLT") በመምህር ከክፍል
ውስጥ ለሚባረሩ ተማሪዎች አማራጭ ቦታ(ዎች)ን በማመቻቸት ረገድ ከት/ቤቱ ርዕሰ መምህር ጋር መተባበር ይኖርባቸዋል። ተማሪው
ወደክፍሉ የሚመለሰው መምህሩ ከተጠየቀ እና ከተማሪው ጋር ስብሰባ ከተደረገ በኋላ ብቻ ይሆናል። መምህሩ ወይም የት/ቤቱ ርዕሰ
መምህር (ወይም ተወካይ) የተማሪውን ወላጅ ወይም ሕጋዊ አሳዳጊ በተቻለ ፍጥነት የተማሪውን ከክፍል መባረር አስመልክቶ ማነጋገር
ወይም ተገቢ ከሆነም በስብሰባ ላይ እንዲገኙ ይጠይቃሉ።
ሐ. በዚህ ጊዜ የባሕርይ/የሥነ ምግባር ዕቅድ ሊዘጋጅ ይችላል፣ ነገር ግን ተማሪው ለሁለተኛ ጊዜ ከክፍል ከተባረረ የባሕርይ/የሥነ
ምግባር ዕቅዱ የግድ መዘጋጀት አለበት። እቅዱ ከገንቢ የሥነ ምግባር እቅዱ ጋር ተጣጣሚ መሆን ይኖርበታል። ተማሪው ከመመለሱ
በፊት ማለፍ ያለበትን የጊዜ ገደብ ጨምሮ ለሁለተኛ ከክፍል ከተባረሩ በኋላ ተማሪዎች ወደ ክፍላቸው የሚመለሱባቸው ቅድመ-
ሁኔታዎች የሚዘጋጀው የባሕርይ/የሥነ ምግባር እቅድ አካል መሆን ይኖርባቸዋል። ለት/ቤቱ የሥርዓት አስከባሪ ቡድን (ከበቂ ሰነዶች
ጋር) መላክ/ማሳወቅ ተገቢ ነው። ተማሪው ወደክፍሉ የሚመለሰው መምህሩ ከተጠየቀ እና ከተማሪው ጋር ስብሰባ ከተደረገ በኋላ ብቻ
ይሆናል።
መ. ለሦስተኛ ጊዜ ከክፍል የተባረረ ተማሪ (አሁን የሚሰራ IEP ካላቸው ተማሪዎች በስተቀር) ለቀሪው ወሰነ ትምህርት (ተርም)
በሙሉ ከዚያ መምህር ክፍል ሊወገድ ይችላል። ለት/ቤቱ የሥርዓት አስከባሪ ቡድን (ከበቂ ሰነዶች ጋር) መላክ/ማሳወቅ ተገቢ ነው።
ተማሪው የተለየ የትምህርት አደረጃጀት ቢፈጠርለትም አልያም ቢታገድ ከዚህ ፖሊሲ እና ከIDEA ደንቦች ጋር በተጣጣመ መልኩ
መሆን ይኖርበታል።
ሠ. በሥነ ምግባር እቅዱ ውስጥ SLT (ወይም ተወካይ) በመምህር ላይ የተዛባ ፀባይ ማሳየትን፣ አንድ መምህርን ማዋከብን
እንዲሁም ሆን ብሎ በሕፃናት ብዝበዛ መክሰስን በተመለከተ የCRS 22-32-109.1 እና የየፖርድ ፖሊሲ መስፈርቶች ማካተት
ይኖርባቸዋል። የሥነ ምግባር እቅዱን በማስፈጸም ሂደት ውስጥ አንድ መምህር በCRS 22-32-109.1 (9) ውስጥ እንደተመለከተው
የሰብዓዊ መብት ወይም የወንጀል ሕጎች ተጠያቂነት እንዳይኖርበት ጥበቃ የሚደረግለት ይሆናል።
ረ. አንድ ርዕሰ መምህር አንድ መምህር በሥነ ምግባር ግድፈት ምክንያቶች እጅግ ብዙ ተማሪዎችን ከክፍል እያስወጣ ስለመሆኑ
ርዕሰ መምህሩ ማስረጃ ካለው፣ ርዕሰ መምህሩ ከመምህሩ ጋር በመሆን የክፍል ውስጥ ተሞክሮውን መገምገም እና የመምህሩን የክፍል
ውስጥ ትግበራ ተሞክሮ በመለወጥ የተሻለ መከላከል የሚቻል እንደሆነ፣ ወይም መምህሩ በስልጠና መለወጥ የሚችል እንደሆነ ለመወሰን
ይሞክራል። ሆኖም ግን፣ እንዲህ ዓይነት ሥጋት/ሀሳብ በመምህሩ ከክፍል ተባርሮ የነበረ ተማሪን ከላይ የተጠቀሰው ስብሰባ ሳይደረግ
ወደ ክፍሉ ለመመለስ እንደ ምክንያት የሚያገለግል አይሆንም።

ክፍል አምስት፦ እገዳን እና ማባረርን መከላከል


5-1 አጠቃላይ
ለ. ለመታገድ ወይም ለመባረር የቀረቡ ተማሪዎች እነዚህ እርምጃዎች ከመወሰዳቸው በፊት የሚያረጋጉ /restorative/ ወይም
የሚያክሙ /therapeutic/ አማራጭ እርምጃዎችን መጠቀም ያስፈልጋል።
ለ. የእያንዳንዳንዱ ት/ቤት ርዕሰ መምህር ወይም ተወካይ የመታገድ ወይም የመባረር አደጋ ያንዣበበባቸው ተማሪዎችን ለመለየት
ከሙያተኛ የት/ቤቱ ሠራተኞች ጋር መሥራት ይገባቸዋል። የመታገድ ወይም የመባረር አደጋ ያንዣበበባቸው ተማሪዎች ሊባሉ ከሚችሉ
ተማሪዎች ውስጥ የዘወትር ፎራፊ ወይም የዘወትር ረባሽ የተባሉ ወይም ሊባሉ የሚችሉ ናቸው።
ሐ. የመታገድ ወይም የመባረር አደጋ ያንዣበበባቸው ተማሪዎች ተብለው ሊለዩ የሚችሉት ባለፈው የትምህርት ዘመን በየትኛውም
ጊዜ ውስጥ የባሕርይ ችግር የነበረባቸው ወይም ታግደው የነበሩ፣ ተባርረው የነበሩ ወይም ከክፍል እንዲወጡ ወይም እንዲቀይሩ
ተደርገው የነበሩ ተማሪዎች ናቸው።
5-2 የባሕርይ እርምት/ማስተካከያ እቅዶች
ሀ. ተደጋጋሚ የሥነ ምግባር ችግሮችን ለመከላከል ወይም ለማስተካከል የባሕርይ እርምት/ማስተካከያ እቅዶችን መጠቀም በከፍተኛ
ሁኔታ የሚበረታታ ነው። የእቅዱ ግቦች የተማሪን ልክ ያልሆነ ባሕሪን እና የትምህርት ፍላጎቶች ማስተካከል እና የልጁን በት/ቤት ውስጥ
የመቀጠል አስፈላጊነት ማጉላት ናቸው።
ለ. እቅዱን ለማዘጋጀት፣ ርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ ከተማሪው፣ ከተማሪው ወላጅ/አሳዳጊ፣ እና ርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ
መሳተፍ አለበት ብሎ ካመነበት የት/ቤቱ ሥራ ባልደረቦች ጋር ስብሰባ ያዘጋጃል። የስብሰባውም ዓላማ የተማሪውን ምግባረ ብልሹነት
ምክንያቶች ለመመርመር እና ባሕሪውን ለማሻሻል በትብብር ግቦችን፣ ዓላማዎችን እና የጊዜ ሰሌዳዎችን ለማውጣት ይሆናል።
ሐ. የተማሪውን የሥነ ምግባር ጉድለት፣ የትምህርት ፍላጎቶች፣ እና ልጁን በት/ቤት ውስጥ እንዲቀጥል አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎች
የሚዳስስ የጽሑፍ እቅድ ይዘጋጃል። እቅዱን በማዘጋጀት ሂደት ውስጥ ተግባራዊ የባሕርይ ዳሰሳዎች /Functional behavioral
assessments/ (አባሪ 'መ'ን ይመልከቱ) ይበረታታሉ። እቅዱ ለመልካም ባሕርይ ማበረታቻዎችን እና እቅዱን በመጣስ ተማሪው
ለሚያሳየው ጥፋት ደግሞ ቅጣቶችን ያካትታል። የባሕርይ ማሻሻያ እቅዱ ተማሪው ወደፊት እገዳዎች እና መባረር እንዳይገጥመው
ት/ቤቱ የሚያደርግለትን ድጋፎች እና ትምህርታዊ አገልግሎቶችን ይገልጻል።
1. እነዚህን አገልግሎት ለመስጠት ዲስትሪክቱ ከተማሪው ወላጅ ወይም አሳዳጊ ጋር በመተባበር መሥራት አለበት።
2. አገልግሎቶቹ አግባብነት ካላቸው የአካባቢ መንግስታዊ ኤጀንሲዎች፣ ማኅበረሰብ አቀፍ ድርጅቶች፣ እና የከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት ጋር በስምምነት የሚሰጡ ሊሆኑ ይችላሉ።
መ. ኮንትራቱን በማዘጋጀት ሂደት ማንኛውም ጥረት የሚደረገው የወላጅ/አሳዳጊን እና የመምህር(ራን) ግብዓት እና ተሳትፎ
ለመጠቀም ይሆናል። እቅዱን የማስተዋወቁ ሥራ ወላጁ/አሳዳጊው ሊረደው በሚችል ቋንቋ የሚደረግ ይሆናል።
ሠ. ኮንትራቱ ላይ ወላጁ/አሳዳጊው፣ ተማሪው፣ እና ርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ መፈረም ይኖርባቸዋል።
ረ. በድንገተኛ ጊዜ የት/ቤቱን እና የማኅበረሰቡን ደህንነት ለማረጋገጥ መውሰድ ከሚያስፈልግ ሥነ ምግባራዊ እርምጃ በስተቀር
አንድን ተማሪ ከማገድ ወይም ከማባረር አስቀድሞ የአገልግሎት እቅድ መኖሩን እና ሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ማንያውም ጥረት
ይደረጋል።

5-3 አስገዳጅ የባሕርይ እርምት/ማስተካከያ እቅዶች


ሀ. የባሕርይ እርምት/ማስተካከያ እቅድ የግድ መዘጋጀት ያለባቸው ሁለት ሁኔታዎች አሉ፤ አንድ ተማሪ ረባሽ ተብሎ ከክፍል ለሁለተኛ
ጊዜ በሚባረር ጊዜ፣ እና አንድ ተማሪ እንደ "የዘወትር ረባሽ" ሊያስቆጥረው የሚችል እገዳ በሚጣልበት ጊዜ።
1. በ"የዘወትር ረባሽ ተማሪዎች" ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ክፍል 6-7ን ይመልከቱ።

ክፍል ስድስት፦ እገዳዎች ወይም ማባረሮች


6-1 አጠቃላይ
ሀ. የት/ቤት-ውስጥ እና የት/ቤት-ውጭ ሁለቱም እገዳዎች በዚህ ፖሊሲ ክፍል 3-1 መሠረት ብቻ የሚጣሉ ቅጣቶች ናቸው።
ለ. የተማሪው ጥፋት በከፍተኛ ሁኔታ የት/ቤቱን አካባቢ የረበሸ ወይም የሚረብሽ ካልሆነ ወይም የሌሎች ተማሪዎችን ወይም
የት/ቤት ሠኞች ጤናማነትን ወይም ደህነንትን በከፍተኛ ሁኔታ አደጋ ላይ የሚጥል ካልሆነ በስተቀር አንድ ተማሪ ከት/ቤት ንብረት ውጭ
እና ከትምህርት ቀናት ውጭ ለሚያደርጋቸው የሥነ ምግባር ጥፋት ከት/ቤት ሊታገድ አይችልም። በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ በዚህ ፖሊሲ
ክፍል 3-1 ሥር የተሰጡ መመሪያዎችን መከተል ያስፈልጋል።
ሐ. የታገዱ ተማሪዎች በእገዳቸው ወቅት በተጓዳኝ ትምህርቶች ወይም በት/ቤት ስፖንሰርነት የሚዘጋጁ ዝግጅቶች ላይ ሊሳተፉ
አይችሉም። ሆኖም ግን፣ የስቴት ፈተናዎች በሚሰጡበት ጊዜ ፈተናውን የመፈተን እድል ሊሰጠው ይገባል። ስለሆነም በርዕሰ መምህሩ
ወይም ተወካዩ ፈቃድ ተያያዥነት ያላቸው ለፈተና የመዘጋጀት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ይሳተፋል።
መ. ት/ቤቱ በእገዳ ላይ ያለ ተማሪ በእገዳው ወቅት ወይም እገዳዎን ባጠናቀቀ በአጭር ጊዜ ውስጥ የማካካሻ ፈተናዎችን እና የማጠቃለያ
ፈተናዎችን የመውሰድ፣ የክፍል እና የቤት ሥራዎችን ያለቅጣት የመሥራትና የማስረከብ፣ እና ከሌሎች ተማሪዎች ጋር እኩል ውጤት እና
ነጥቦች /credits/ የማግኘት እድልን ሊሰጠው ይገባል። የዚህ መመሪያ ዓላማ ተማሪው የተጣለበትን እገዳ ከጨረሰ በኋላ ወደ
ትምህርት ፕሮግራሙ በሚገባ እንዲዋሃድ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ነው።

6-2 የት/ቤት-ውስጥ እገዳዎች


ሀ. በተከታታይ አስቸጋሪ ባሕሪ ያላቸው ተማሪዎች የትምህርት ሂደቱን እንዲያደናቅፉ ሊፈቀድላቸው አይገባም፤ ዳሩ ግን እንዲህ ዓይነት
ተማሪዎችን ከት/ቤት ማገድ ብዙውን ጊዜ ለሌሎች ተማሪዎች፣ ለት/ቤቱ እና ለማኅበረሰቡ ተጨማሪ ችግር መፍጠር ይሆናል። ስለዚህ
ዲስትሪክቱ እና የትምህርት ቦርዱ የት/ቤት-እገዳ የሚል ጽንሰ ሀሳብን አጽድቀዋል።
ለ. የት/ቤት-ውስጥ እገዳ ዓላማ ከትምህርት ሰዓት በኋላ ከማገት /detention / ወይም ከት/ቤት-ውጭ እገዳ የተሻለ ውጤታማ የሥነ
ምግባር መፍትሄ ማቅረብ ነው። የት/ቤት-ውስጥ እገዳን በመጠቀም፣ ተማሪዎች ከትምህርታቸው ወደ ኋላ አይቀሩም፣ ነገር ግን
ከስህተታቸው እና ከመጥፎ ባሕርያቸው መማር አለባቸው። ሁሉም የት/ቤት-ውስጥ እገዳዎች በዚህ እና በሌሎች ፖሊሲዎች ውስጥ
በተዘረዘሩት የተማሪዎች ተገቢ መብቶችን ባከበረ መልኩ መሆን ይኖርባቸዋል። የሚከተሉት መመሪያዎች መጠበቅ ይኖርባቸዋል፦
1. ካለ፣ ተማሪዎቹ በሁሉም ጊዜያት በቂ ክትትል/ቁጥጥር ሊደረግላቸው በሚችሉበት ልዩ መማሪያ ክፍል ውስጥ መመደብ
ያስፈልጋቸዋል። የት/ቤት-ውስጥ እገዳ ተቆጣጣሪው እያንዳንዱ ተማሪ ከመደበኛ መምህሩ የቤት ሥራዎችን እና ተገቢውን ትምህርት
እያገኘ መሆኑን ይከታተላል።
2. ልጃቸው የት/ቤት-ውስጥ እገዳ ከተጣለበት የት/ቤቱ ርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ ለወላጆች/ለአሳዳጊዎች ወዲያውኑ በስልክ
ማሳወቅ አለባቸው። ወላጁ/አሳዳጊው በስልክ መገኘት ካልቻሉ፣ ወይም በወላጁ/አሳዳጊው የተጠየቀ ከሆነ፣ በሚረዱት ቋንቋ የጽሑፍ
ደብዳቤ መላክ ይኖርበታል። ለት/ቤት-ውስጥ እገዳው ምክንያቶች መገለጽ ይኖርባቸዋል፤ ተማሪው ወደ መደበኛ ክፍሉ ከመመለሱ
በፊትም ስብሰባ ሊደረግ ያስፈልጋል።

6-3 የከት/ቤት-ውጭ እገዳዎች


ሀ. ተማሪዎች ከት/ቤት-ውጭ እገዳ የሚጣልባቸው ዓይነት ሦስት፣ ዓይነት አራት፣ ዓይነት አምስት፣ ወይም ዓይነት ስድስት ጥፋትን
ከፈጸሙ (የዚህን ፖሊሲ ክፍል 3-1ን ይመልከቱ)፣ ወይም በሥነ ምግባር ርከኑ ደረጃ "ሠ" ከደረሱ (የዚህን ፖሊሲ ክፍል 3-2ን
ይመልከቱ) ብቻ ይሆናል።
ለ. የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ለዓይነት አንድ ጥፋቶች የት/ቤት-ውጭ እገዳዎች ሊጣልባቸው አይገባም (የዚህን ፖሊሲ
ክፍል 3-2ን ይመልከቱ)።

6-4 የት/ቤት-ውጭ እገዳዎች አፈጻጸም ሂደቶች


ሀ. እያንዳንዱ የት/ቤት ርዕሰ መምህር ወይም በርዕሰ መምህሩ በጽሑፍ የተወከለ ሰው ከዚህ ፖሊሲ ጋር በተጣጣመ ሁኔታ ተማሪ ላይ
የት/ቤት-ውጭ እገዳ እንዲጥሉ የትምህርት ቦርዱ ስልጣን ሰጥቷቸዋል። ርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ ይህን ስልጣን ሲተገብሩ
ተገቢውን ሂደት መከተላቸውን ለማረጋገጥ የተሰጧቸውን አፈጻጸም ሂደቶች መከተል አለባቸው።
ለ. ተማሪ ከመታገዱ በፊት ከርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ ጋር ኢ-መደበኛ የሆነ ስብሰባ የማካሄድ መብት አለው። በስብሰባው
ላይ ተማሪው፦
1. ወላጅ ወይም አሳዳጊ እንዲጠራ እና ወላጁ ወይም አሳዳጊው ከቻሉ በስበሰባው በተወሰነ ጊዜ ውስጥ እንዲገኙ እንዲያደርግ
ይፈቀድለታል።
2. የተከሰሰበትን ጥፋት ሊነገረው ይገባል።
3. ለክሶቹ በቃል ወይም በጽሑፍ ምላሽ ለስጠት እና ስለክስተቱ/ድርጊቱ ከራሱ አንፃር ለማቅረብ ይፈቀድለታል።
4. የጽሑፍ መግለጫ ከተፈልገ የጽሑፍ መግለጫውን ያለማቅረብ መብት እንዳለው ይነገረዋል።
5. ምስክሮቹ በርዕሰ መምህሩ ወይም በተወካዩ እንዲጠየቁ የማድረግ መብትን ጭምሮ ራስን ለመከላከል ማስረጃዎችን የማቅረብ
መብት አለው።
ሐ. እገዳዎችን ለመጣል ውሳኔ ከመወሰን በፊት ሁሉንም የሚታወቁ ምስክሮች ቃለ-መጠይቅ ማድረግ እና ሁሉንም ማስረጃዎች
መገምገም ለርዕሰ መምህሩ ወይም ለርዕሰ መምህሩ ተወካይ በጣም ጥሩ ልምድ/ተሞክሮ ነው።
መ. ከኢ-መደበኛው ስብሰባ በኋላ ርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ ተማሪውን የት/ቤት-ውጭ እገዳ እንዲጣልበት ከወሰኑ፣ ት/ቤቱ
የተማሪውን ወላጅ/አሳዳጊ በስልክ ለማነጋገር በቂ ጥረት ማድረግ አለበት። በተጨማሪም ት/ቤቱ ለወላጁ/አሳዳጊው በሚረዱት ቋንቋ
እገዳውን በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት። የቃል እና የጽሑፍ ማስታወቂያዎች ሁለቱም ተማሪው እገዳ እንደተጣለበት፣ የእገዳው ምክንያቶች
ምን እንደሆኑ፣ የእገዳው ጊዜ ምን ያህል እንደሆነ ለወላጁ/አሳዳጊው መግለጽ መቻል አለባቸው። በተጨማሪም ተማሪው ከመመለሱ
በፊት ወይም በተመለሰ ጊዜ ወላጁ/አሳዳጊው ከርዕሰ መምህሩ ወይም ከተወካዩ ጋር እንዲገናኙ ጊዜ እና ቦታን መያዝ
አለበት። እንዲሁም በእገዳው ጊዜ የማካካሻ ሥራዎች ለተማሪው እንደሚሰጡት እና ስለእገዳው አቤቱታ የማቅረብ መብት እና እንዴት
አቤት ማለት እንዳለበት የማወቅ መብትን መግለጽ አለበት።
ሠ. ድንገተኛ ሁኔታ ተማሪው በቶሎ ከት/ቤት እንዲወጣ/እንዲወገድ ቢያስገድድ፣ ኢ-መደበኛው ስብሰባ ተማሪው ከተባረረ በኋላ
እንደአመችነቱ የሚደረግ ይሆናል። ተማሪውን በአስቸኳይ ከት/ቤት ማስወጣት አስፈላጊ ከሆነ፣ የተማሪውን ጥበቃ እንዴት በተሻለ
መንገድ ለወላጁ/አሳዳጊው ለማስተላልፍ እንደሚቻል ለመወሰን ት/ቤቱ ወዲያውኑ ለወላጁ/አሳዳጊው ማሳወቅ ይኖርበታል።
ረ. እገዳው ተማሪውን እንደ "የዘወትር ረባሽ" የሚያስቆጥረው ከሆነ በዚህ ፖሊሲ ክፍል 6-7 እንደተብራራው ለወላጁ/አሳዳጊው
እና ለተማሪው በጽሑፍ እንደዚያ ተብሎ ሊገለጽላቸው የግድ ያስፈልጋል።
ሰ. ማንኛውንም ተማሪ ከእገዳ በሚመለስበት ጊዜ ተጨማሪ የሥነ ምግባር ግድፈቶችን ለመከላከል የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር ወይም
ተወካይ ከተማሪው ወላጅ ወይም ሕጋዊ አሳዳጊ ጋር ተገናኝቶ ስለተማሪው ባሕርይ እና ሊያስፈልግ ስለሚችል የባሕርይ
እርምት/ማስተካከያ እቅድ (በክፍል 5-2 እና 5-3 እንደተብራራው) መወያየት አለባቸው።
ሸ. ለዓይነት ሦስት ጥፋቶች (የዚህን ፖሊሲ ክፍል 3-1ን ይመልከቱ) የተማሪው በት/ቤት መገኘት ለት/ቤቱ እና ለማኅበረሰቡ
አደጋ ወይም ከፍተኛ ረብሻ ያለው ከሆነ ወይም አደጋውን/ክስተቱን የበለጠ ለማጣራት ተጨማሪ ጊዜ ካስፈለገ፣ ርዕሰ መምህሩ በክፍል
3-1 የሚገኘውን የት/ቤት-ውጭ እገዳን ቢበዛ ለአንድ ቀን የማራዘም፣ በድምሩ ሦስት ቀናት የማድረግ አማራጭ አለው።
ቀ. ለዓይነት አራት ጥፋቶ (የዚህን ፖሊሲ ክፍል 3-1ን ይመልከቱ)፣ በዚህ ፖሊሲ ክፍል 6-6 አማካኝነት ለዋና ተቆጣጣሪው
ወይም ተወካዩ ተማሪው እንዲባረር ጥቆማ የቀረበ ከሆነ፣ ወይም እገዳ ጊዜው እንዲራዘም የቀረበ ጥያቄ ካለ፣ ለት/ቤቱ ደህንነት አስፈላጊ
ሆኖ ከተገኘ ርዕሰ መምህሩ በክፍል 3-1 የሚገኘውን የት/ቤት-ውጭ እገዳ ቢበዛ እስከሁለት ቀን የማራዘም እና በድምሩ አምስት ቀን
የማድረግ አማራጭ አለው።
6-5 ስለ ከት/ቤት-ውጭ እገዳ ይግባኝ የማለት መብቶች
ሀ. በእገዳው ማስታወቂያ ውስጥ ተማሪው ለርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ ይግባኝ የማለት መብት እንዳለው ሊገለጽለት ይገባል።
ለ. ስለእገዳው ይግባኝ በማለት ሂደት ውስጥ ተማሪው የሚከተሉት መብቶች አሉት፦
1. ከርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ ጋር ስብሰባ ለማድረግ የመጠየቅ። 2. በስብሰባው ተወካይ የማቅረብ መብት።
3. ተማሪው፣ ወላጁ/አሳዳጊው እና/ወይም ተወካይ ጠበቃው ርዕሰ መምህሩን ወይም ተወካዩን ስለማስረጃዎቹ እና ስለቅጣቱ
አግባብነት የማነጋገር መብት አላቸው።
4. እገዳውን አስመልክቶ የመቃወሚያ ሀሳብ የማቅረብ ወይም ወላጅ፣ አሳዳጊ፣ ወይም ተወካይ ጠበቃ እንዲያቀርብ እና በተማሪው
የሥነ ምግባር ፋይል እንዲካተት የማድረግ መብት።
5. በእገዳው ውሳኔ ሂደት ውስጥ ግንዛቤ ውስጥ የገባውን እና ለመታየት አግባብነት ያለውን ማንኛውንም ማስረጃ የመገምገም ወይም
ወላጅ፣ አሳዳጊ፣ ወይም ተወካይ ጠበቃ እንዲገመግም የማስደረግ መብት። የቤተሰብ ትምህርት መብቶች እና የግላዊነት አዋጅን
/Family Education Rights and Privacy Act/ በመጣስና ያለግለሰቡ(ቦቹ) ስምምነት ፈቃድ ዲስትሪክቱ ማስረጃዎችን የማቅረብ
ግዴታ አይኖርበትም።
ሐ. ርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ፦
1. ሁሉንም የጽሑፍ ሰነዶች ይገመግማሉ/ይመረምራሉ።
2. የሚከተሉትን ለማረጋገጥ በቂ ማስረጃ መቅረቡን ውሳኔ ይሰጣሉ።
ሀ. የተባለው ወንጀል/ጥፋት መፈጸሙን፣ እና
ለ. የተጣለው ቅጣት አግባብ መሆኑን።
3. ስብሰባ በተካሄደ በአምስት ቀናት ውስጥ የጽሑፍ ውሳኔ ይሰጣሉ።
4. ምንም ጥፋት/ወንጀል አልተፈጸመም ተብሎ ከተወሰነ፣ እገዳውን የሚመለከቱ ሁሉም ሰነዶች/ማኅደሮች ከተማሪው ፋይል
ይሰረዛሉ/ይፋቃሉ። ከዚያም የተስተካከለው የተማሪው ፋይል ቅጅ ለተማሪው ወላጅ ወይም አሳዳጊ በፖስታ ይላክላቸዋል።
5. የተጣለው ቅጣት ከጥፋቱ/ከወንጀሉ አንፃር አግባብ ያልሆነ ሆኖ ከተገኘ፣ ሁሉም የት/ቤት ሰነዶች/ማኅደሮች በርዕሰ መምህሩ ወይም
ተወካዩ የተሻሻለውን ቅጣት እንዲያሳዩ ለማድረግ ይከለሳሉ።
መ. ርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ የይግባኝ ጥያቄውን ካልተቀበሉት፣ ተማሪው ሁለተኛ ይግባኝ ለዋና ተቆጣጣሪው ተወካይ
ማቅረብ የሚችል ይሆናል።
ሠ. ለሁለተኛ ጊዜ ይግባኝ በሚልበት ሂደት ውስጥ ተማሪው የሚከተሉት መብቶች ይኖሩታል፦
1. ከዋና ተቆጣጣሪው ተወካይ ጋር ስብሰባ ለማድረግ የመጠየቅ።
2. በስብሰባው ተወካይ/ጠበቃ የማቅረብ መብት።
3. ተማሪው፣ ወላጁ/አሳዳጊው እና/ወይም ተወካይ ጠበቃው የዋና ተቆጣጣሪውን ተወካይ ስለማስረጃዎቹ እና ስለቅጣቱ አግባብነት
የማነጋገር መብት አላቸው።
4. እገዳውን አስመልክቶ የመቃወሚያ ሀሳብ የማቅረብ ወይም ወላጅ፣ አሳዳጊ፣ ወይም ተወካይ ጠበቃ እንዲያቀርብ የማድረግ መብት።
ረ. የዋና ተቆጣጣሪው ተወካይ፦
1. ሁሉንም የጽሑፍ ሰነዶች ይገመግማል/ይመረምራል።
2. የሚከተሉትን ለማረጋገጥ በቂ ማስረጃ መቅረቡን ውሳኔ ይሰጣል።
ሀ. የተባለው ወንጀል/ጥፋት መፈጸሙን፣ እና
ለ. የተጣለው ቅጣት አግባብ መሆኑን።
3. ስብሰባ በተካሄደ በአምስት ቀናት ውስጥ የጽሑፍ ውሳኔ ይሰጣል።
4. ምንም ጥፋት/ወንጀል አልተፈጸመም ተብሎ ከተወሰነ፣ እገዳውን የሚመለከቱ ሁሉም ሰነዶች/ማኅደሮች ከተማሪው ፋይል
ይሰረዛሉ/ይፋቃሉ። ከዚያም የተስተካከለው የተማሪው ፋይል ቅጅ ለተማሪው ወላጅ ወይም አሳዳጊ በፖስታ ይላክላቸዋል።
5. የተጣለው ቅጣት ከጥፋቱ/ከወንጀሉ አንፃር አግባብ ያልሆነ ሆኖ ከተገኘ፣ ሁሉም የት/ቤት ሰነዶች/ማኅደሮች በዋና ተቆጣጣሪው
ተወካይ የተሻሻለውን ቅጣት እንዲያሳዩ ለማድረግ ይከለሳሉ።

6-6 የት/ቤት-ውጭ እገዳዎችን ማራዘም


ሀ. የትምህርት ቦርዱ ለዋና ተቆጣጣሪው ወይም ተወካዩ የተማሪን ከት/ቤት-ውጭ እገዳ በርዕሰ መምህሩ ጥቆማ መሠረት እስከ አስር
(10) ቀናት ድረስ የማራዘም ስልጣን ተሰጥቷቸዋል። አጠቃላይ የእገዳ ጊዜው ከሃያ አምስት (25) ቀናት መብለጥ የለበትም።
ለ. እገዳ ሊራዘም የሚችለው ተማሪው ዓይነት አራት ወይም ዓይነት አምስት ጥፋትን ከፈጸመ (የዚህን ፖሊሲ ክፍል 3-1ን
ይመልከቱ)፣ የተማሪው በት/ቤት መገኘት ለት/ቤቱ እና ለማኅበረሰቡ አደጋ ወይም ከፍተኛ ረብሻ የሚፈጥር ሆኖ ከተገኘ ወይም
አደጋውን/ክስተቱን የበለጠ ለማጣራት ተጨማሪ ጊዜ ካስፈለገ፣ ወይም ለዋና ተቆጣጣሪው ወይም ተወካዩ ተማሪው እንዲባረር ጥቆማ
ከቀረበበት ብቻ ይሆናል።
ሐ. እገዳው እንዲራዘም ጥቆማ የሚደረግ ከሆነ፣ ርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ ለወላጅ/ላሳዳጊ ወዲያውኑ በስልክ ለማሳወቅ
ለማሳወቅ እና አስከትለውም ወላጁ/አሳዳጊው በሚረዳው ቋንቋ ደብዳቤ ለመላክ መጣር ይኖርባቸዋል። ርዕሰ መምህሩ ወይም ተወካዩ
በዚህ የቃል እና የጽሑፍ ማስታወቂያ አማካኝነት እገዳው የተራዘመበትን ምክንያት ለወላጁ/ለአሳዳጊው ለማስረዳት የስብሰባ ቀጠሮ
ለማስያዝ መሞከር አለባቸው።
መ. የእገዳው መጠን በድምሩ አሥር (10) ቀናት ወይም ከዚያ በላይ እስኪደርስ ድረስ እገዳው ከተራዘመ እና ተማሪው እንዲባረር
ጥቆማ ካልቀረበ፣ ተማሪው በዚህ ፖሊሲ ክፍል 6-8 ከዚህ በታች እንደተገለጸው አንድ ዓይነት የመሰማት /hearing/ መብት
ይኖራቸዋል።
ሠ. የተማሪው እገዳ በድምሩ ከአሥር (10) ቀናት በላይ ከተራዘመ፣ ተማሪው ከሌሎች ተማሪዎች ጋር እኩል ውጤቶችን እና
ነጥቦችን /credits/ ማግኘት እንዲችል በእገዳው ጊዜ የሚያጠናበት/የሚዘጋጅበት አማራጭ የትምህርት ሁኔታ ሊቀርብለት ይገባል።

6-7 የዘወትር ረባሽ ተማሪዎች


ሀ. አንድ "የዘወትር ረባሽ ተማሪ" በአንድ የትምህርት ዘመን ውስጥ በክፍል ውስጥ፣ በት/ቤት ግቢ ውስጥ፣ በት/ቤት መኪኖች፣ በት/ቤት
እንቅስቃሴዎች ወይም ማዕቀብ/ክልከላ በተጣለባቸው ዝግጅቶች ላይ ብጥብጥ/ረብሻ በማስነሳት በርዕሰ መምህሩ ወይም በተወካዩ ለሦስት
(3) ጊዜ ያክል ከት/ቤት-ውጭ እገዳ የተጣለበት ተማሪ ማለት ነው።
ለ. እንደ የዘወትር ረባሽ ተማሪ ሊያስቆጥሩ የሚችሉ ጥፋቶች/ወንጀሎች፣ የተማሪውን የጊዜ ሰሌዳ መለውጥ ረባሽ/በጥባጭ
ባሕሪውን ያስተካክለው እንደሆነ የሚታይ ይሆናል።
ሐ. ተማሪውን እንደ የዘወትር ረባሽ ተማሪ ሊያስቆጥር ስለሚችል እያንዳንዱ እገዳ ለተማሪው እና ለወላጁ/ለአሳዳጊው በጽሑፍ
ማሳወቅ ያስፈልጋል። ስለ "የዘወትር ረባሽ ተማሪ" ፍቺ/ትንታኔ እና እንዲህ ዓይነት ተማሪዎችን ለማባረር የጥቆማ አማራጭ በጽሑፍ
እና በስልክ ወይም በሌላ መንገድ በቤታቸው ወይም በወላጁ/አሳዳጊው የሥራ ቦታቸው ለተማሪው እና ለወላጁ/ለአሳዳጊው
ሊገለጽላቸው ይገባል። የጽሑፍ ማስታወቂያው ወላጁ/ሕጋዊ አሳዳጊው ሊረዳው በሚችል ቋንቋ ሊሰጣቸው ይገባል።

6-8 የማባረር ሂደቶች


ሀ. የትምህርት ቦርዱ ለዋና ተቆጣጣሪው አንድ የቅበላ መስፈርቶችን ያላሟላ ወይም በዲስትሪክቱ የሕዝብ ት/ቤቶች ለመቀጠል
የማይችልን ተማሪ እስከ አንድ (1) ካላንደር ዓመት ድረስ የማባረር ስልጣን ተሰጥቶታል።
ለ. የማባረር ሂደቱ የሚጀምረው የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር ለዋና ተቆጣጣሪው ወይም ተወካዩ በሚቀርበው ጥቆማ ይሆናል። ርዕሰ
መምህሩ እንዲህ ዓይነት ጥቆማ በሚያደርግበት ጊዜ ለተማሪው እና የተማሪው ወላጅ/አሳዳጊ ስለጥቆማው በሚረዱት ቋንቋ በጽሑፍ
ማሳወቅ አለበት። ማስታወቂያው የሚከተሉትን ይይዛል፦
1. እንዲወሰድ ለተጠየቀው እርምጃ (ለጥቆማው) ምክንያቶች።
2. ተማሪው ወይም ወላጁ/አሳዳጊው ካላነሱት/ካልተውት በስተቀር፣ የማስታወቂያው ደብዳቤ በተሰጠ አሥር (10) ቀናት ውስጥ
ስለማበረር ውሳኔውና ምክንያቶቹ ችሎት /hearing/ እንደሚሰየም/እንደሚደረግ የሚገልጽ ዐረፍተ ነገር።
3. ተማሪው የቀረቡበትን ማስረጃዎች ለመስማት፣ አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎች ለማቀረብ በችሎቱ መገኘት እንደሚችል፣ ሲገኝም
ከወላጅ/አሳዳጊ እና ከመረጠው ተወካይ/ጠበቃ ጋር ሊሆን እንደሚችል የሚገልጽ ዐረፍተ ነገር።
ሐ. ተማሪው ወይም ወላጁ/አሳዳጊው ለችሎት /hearing/ ያላቸውን መብት በግልጽ ካላነሱት/ካልተውት በስተቀር፣ ዋና
ተቆጣጣሪው ወይም ተወካዩ ወላጅ፣ ጠበቃ ወይም ወላጁ/አሳዳጊው የመረጠው ተከራካሪ ልጁን ወክለው ማስረጃዎችን የሚያቀርቡበት
ችሎት/ስብሰባ ሳያደርጉ አንድም ልጅ ማባረር የለባቸውም።
መ. ችሎት የሚካሄደው በወቅቱ የት/ቤቱ፣ የዲስትሪክቱ፣ ወይም የትምህርት ቦርዱ ሠራተኛ ባልሆነ የችሎት ባለሙያ /hearing
officer/ ይሆናል። በችሎቱ፣ ምስክርነት እና መረጃ የሚቀርቡት በመሃላ ይሆናል። የማስረጃ ቴክኒካዊ ደንቦች /Technical rules of
evidence/ አይተገበሩም። ተማሪው፣ ወላጁ/አሳዳጊው ወይም ተወካዩ/ጠበቃው መረጃዎችን የሚያቀርቡ ግለሰቦችን ጥያቄዎችን
መጠየቅ ይችላሉ።
1. በተማሪው የተፃፉ መግለጫዎች ተማሪው ጽፎ ሲፈርምባቸው ወላጁ/አሳዳጊው ካልተገኙ ወይም የት/ቤት ባለስልጣናት በፊርማ ጊዜ
ወላጁ/አሳዳጊው እንዲገኙ በቂ ጥረት ካላደረጉ በስተቀር እንደማስረጃ ጥቅም ላይ ሊውሉ አይችሉም።

2. ለደረጃ ስድስት ጥቃት፣ የችሎት ባለሙያው /hearing officer/ተማሪው በት/ቤት ግቢ ውስጥ የእጅ ጠመንጃ /firearm/ ይዞ
ተገኝቷል ብሎ ከወሰነ፣ የሚከተለው ቅጣት ለአንድ ዓመት ማባረር ይሆናል።
ሠ. ዋና ተቆጣጣሪው ወይም ተወካዩ የተጠቆመውን እርምጃ እና የችሎት ባለሙያውን ሪፖርት ከመረመሩ በኋላ በቀረበው
የማባረር ሃሳብ ላይ እርምጃ ይወስዳሉ። ስለተወሰደው እርምጃ ተማሪውን እና ወላጁን/አሳዳጊውን የሚያሳውቅ የጽሑፍ ደብዳቤ ችሎቱ
ከተያዘበት ቀን አንስቶ በአምስት (5) ቀናት ውጥ መላክ አለበት። ዋና ተቆጣጣሪው ወይም ተወካዩ ለደረጃ ስድስት ጥፋት የአንድ
ዓመት ማባረር አይገባውም ብሎው ከወሰኑ፣ የጽሑፍ ሀሳቡ ልዩ የሆነባቸው ምክንያቶችን ይዘረዘራል። ማስታወቂያው ወላጁ/አሳዳጊው
ሊረዳው በሚችል ቋንቋ ሊሰጣቸው ይገባል።
ረ. ዋና ተቆጣጣሪው ወይም ተወካዩ ለተማሪው እና ለወላጁ/ለአሳዳጊው ማስታወቂያ ደብዳቤው በደረሳቸው በአሥር (10) ቀናት
ውስጥ ውሳኔውን ለትምህርት ቦርዱ ይግባኝ የማለት መብት እንዳላቸው ያሳውቃሉ። ማስታወቂያው ወላጁ/አሳዳጊው ሊረዳው
በሚችል ቋንቋ ሊሰጣቸው ይገባል።
ሰ. ይግባኝ በሰዓቱ ከተጠየቀ፣ የትምህርት ቦርዱ ማኅደሩን ይገመግም እና የዲስትሪክቱ ተወካዮች እና ተማሪው መግለጫዎችን
ለትምህርት ቦርዱ እንዲያቀርቡ ዕድል ይሰጣቸዋል። የትምህርት ቦርዱ፦
1. የሚከተሉትን ለማረጋገጥ በቂ ማስረጃ መቅረቡን ውሳኔ ይሰጣል።
ሀ. የተባለው ወንጀል/ጥፋት መፈጸሙን፣ እና
ለ. የተጣለው ቅጣት አግባብ መሆኑን።
2. ስብሰባ በተካሄደ በአምስት ቀናት ውስጥ የጽሑፍ ውሳኔ ይሰጣል።
3. ምንም ጥፋት/ወንጀል አልተፈጸመም ተብሎ ከተወሰነ፣ እገዳውን የሚመለከቱ ሁሉም ሰነዶች/ማኅደሮች ከተማሪው ፋይል
ይሰረዛሉ/ይፋቃሉ። ከዚያም የተስተካከለው የተማሪው ፋይል ቅጅ ለተማሪው ወላጅ ወይም አሳዳጊ በፖስታ ይላክላቸዋል።
4. የተጣለው ቅጣት ከጥፋቱ/ከወንጀሉ አንፃር አግባብ ያልሆነ ሆኖ ከተገኘ፣ ሁሉም የት/ቤት ሰነዶች/ማኅደሮች በትምህርት ቦርዱ
የተሻሻለውን ቅጣት እንዲያሳዩ ለማድረግ ይከለሳሉ።
ሸ. እያንዳንዱ ተማሪ በተባረረበት ወቅት ስለሚኖሩት የትምህርት አማራጮች ለወላጁ/አሳዳጊው መረጃ
ይሰጣል። ወላጁ/አሳዳጊው የቤት ውስጥ የትምህርት ፕሮግራምን ከመረጡ፣ የሚፈለገው የክፍል ደረጃ ሥርዓተ ትምህርቶች
ይቀርቡላቸዋል።

ክፍል ሰባት፦ የአመታዊ ግምገማ እና ሥነ ምግባር ኮሚቴ


7-1 አመታዊ ግምገማ እና ሪፖርት
ሀ. ት/ቤቶች በተናጥል እና ዲስትሪክቱ በተማሪ ዘር፣ ብሔር እና ፆታ በተነጣጠለ የት/ቤት የሥነ ምግባር ዳታ በመጠቀም የት/ቤቱን ሥነ
ምግባር እቅድ ውጤታማነት ሁለቱም በአንድ ላይ ይገመግማሉ ይቆጣጠራሉ። ይህም ት/ቤቶች እና ዲስትሪክቱ መሞላት
የሚያስፈልጋቸው ክፍተቶችን ለመለየት፣ የሥጋት መስኮች ላይ ለማነጣጠር፣ የሙያዊ ልማትን፣ ድጋፎችን፣ እና አገልግሎቶችን ተደራሽ
ለማድረግ፣ እና የት/ቤት መመሪያዎችን እንደተፈለገው ለመከለስ ያስችላል።
ለ. ት/ቤቶች የት/ቤታቸውን ሁኔታ በየአመቱ በመገምገም ለትምህርት ቦርዱ፣ ለዋና ተቆጣጣሪው እና ለዲስትሪክቱ የት/ቤት
ማሻሻያ እና ተጥያቂነት መማክርት የጽሑፍ ሪፖርት ያስገባሉ፤ በግምገማው መሠረት ት/ቤቶች ከዚህ እና ከሌሎች ፖሊሲዎች ጋር
የሚጣጣሙ ለውጦችን ያደርጋሉ።
ሐ. ግምገማው የሚከተሉትን ያካትታል፦
1. የእርምት እና የመከላከያ ስልቶችን፤
2. ለበላይ አካል አስተላልፎ መስጠት (ሪፈራል)፣ የት/ቤት-ውስጥ እገዳዎች፣ የት/ቤት-ውጭ እገዳዎች፣ የማባረሮች፣ የቲኬቶች እና
የእስሮች ቁጥር በተማሪው ዘር፣ ብሔር፣ እድሜ፣ ክፍል ደረጃ፣ አካል ጉዳተኝነት ሁኔታ፣ እና ፆታ ተለይቶ፤
3. ከሠራተኞች አባላት መካከል ለበላይ አካል አስተላልፎ በመስጠት (በሪፈራል) ያሉ ልዩነቶችን፤
4. የሥነ ምግባር እርምጃን ጨምሮ ነገር ግን በዚህ ሳይወሰን ፖሊሲው በምን ያህል መጠን ለሁሉም ተማሪዎች በወጥነት ተተግብሯል
የሚለውን ይይዛል።
መ. በግምገማው መሠረት ት/ቤቶች ከዚህ እና ከሌሎች ፖሊሲዎች ጋር የሚጣጣሙ ለውጦችን ያደርጋሉ።

7-2 የሥነ ምግባር ኮሚቴዎች


ሀ. የት/ቤትን የሥነ ምግባር ፖሊሲን እና የት/ቤትን ሁኔታ ለማጎልበት፣ ለመከታተል እና ለመገምገም ት/ቤቶች የት/ቤት ሠራተኞችን፣
ወላጆችን እና ተማሪዎችን የያዘ የሥነ ምግባር ኮሜቴ እንዲያቋቁሙ ይበረታታሉ። በዚህ ሂደት ውስጥ የት/ቤት የሥነ ምግባር ዳታ
መጠቀም የሚመከር ነው።

መተግበር የተጀመረበት ቀን
ኦክቶበር 1፣ 1996
የፀደቀበት ቀን፦ 19፣1996
የተከለሰበት ቀን:- ኦገስት 21፣ 2008
የተከለሰበት ቀን:- ኦክቶበር 15፣ 2008
የተከለሰበት ቀን:- ሴፕቴምበር 15፣ 2011

ሕጋዊ ማጣቀሻዎች፦
C.R.S. 22-32-109.1 (የተማሪ ፀባይ፣ ደህንነት እና ጤናማነት)
C.R.S. 22-32-126(5) (የሥነ ምግባር ነክ መረጃዎች አያያዝና አሰጣጥ)
C.R.S. 22-33-105 (እገዳ፣ ማባረር፣ እና ቅበላ/ምዝገባ መከልከል)
C.R.S. 22-33-106 (የእገዳ፣ የማባረር፣ እና ቅበላ/ምዝገባ የመከልከል ምክንያቶች)
C.R.S. 22-33-106.3 (በማባረር ችሎት ላይ ጥቅም ላይ የሚውሉ የተማሪ መግለጫዎች)
C.R.S. 22-33-202 (በአደጋ ወይም ሥጋት ውስጥ ያለ ተማሪን መለየት)
C.R.S. ከ18-3-202 እስከ 204 (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ እና ሦስተኛ ደረጃ ጥቃት)
C.R.S. ከ18-8-704 እስከ 706 (ምስክርን ማስፈራራት እና መበቀል)
C.R.S. 19-3-304 (ስለ ህፃናት ብዝበዛ/መተው ወይም ትኩረት መነፈግ ሪፖርት እንዲያደርጉ የሚጠበቅባቸው ሰዎች)
C.R.S. 19-1-103 (የህፃናት ብዝበዛ)
C.R.S. 16-22-102 (ሕገ ወጥ የሆነ ፆታዊ ባሕርይ፣ ሕገ ወጥ የሆነ ፆታዊ ግንኙነት፣ ጸያፍ ራቁትነት)
የቤተሰብ የትምህርታዊ እና የግላዊነት መብቶች (FERP) 20 U.S.C. 1232g(h))

You might also like