Interpretation of The First Three Gospels

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 43

ሏዱስ ኪዲን

Interpretation to the first three Gospels


Module

መ/ር ወ/ትንሣኤ በዚ

2014 ዓ.ም

አዱስ አበባ
መግቢያ

ሲኖፕቲክ ወንጌሊት

ሲኖፕቲክ /Synoptic/ የሚሇው ቃሌ የግሪክ ቃሌ ሲሆን ከ4ቱ ወንጌሊት ውስጥ ሇ3ቱ ወንጌሊት
የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ ሦስቱ ወንጌሊት የተባለትም የማቴዎስ ወንጌሌ፣ የማርቆስ ወንጌሌና
የለቃስ ወንጌሌ ናቸው፡፡

ሲኖፕቲክ ማሇት በአንዴ ሊይ የሚታይ /Seen together/ ማሇት ነው፡፡ ሦስቱ ወንጌሊት
በይዝታቸው በብዘ ክፍሌ ስሇሚመሳሰለና እርስ በእርስ ማስተያየት ስሇሚቻሌ ይህን ሇማስረዲት
የተሰጣቸው ስያሜ ነው፡፡ ከሦስቱ ወንጌሊት በአንደ ሇተመ዗ገቡት ሇብዘዎቹ የጌታ ታሪኮችና
ሥራዎች በላልቹ ሁሇቱ ወንጌሊት ውስጥ እናገኛቸዋሇን፡፡ ይህ ማሇት እነዙያኑ ክፍሇ ንባባት
ራሳቸውን በዴጋሚ እናገኛቸዋሇን ማሇት ነው፡፡ የእያንዲንዲቸው አገሊሇጥና የቃሊት አጠቃቀም
እንዳት እንዯሆነና በዙያው ክፍሇ ንባብ ውስጥ አንደ የገሇጠው ላሊው የገሇጠው መን እንዯሆነ
ንባቡን በማስተያየት እያጠኑ ማወቅ ያስፈሌጋሌ፡፡ ከዙህም በተጨማሪ ሦስቱ ወንጌሊት ምንም
እንኳን በአብዚኛው ትይዩ ክፍሊት ቢኖራውም ከሦስቱ በአንደ ወይም በሁሇቱ ብቻ የተመ዗ገቡ
ክፍልች እንዲለ መታወቅ አሇበት፡፡

ስሇዙህ ትይዩ የላሊቸው እነዙህ ክፍልች የትኞቹ እዯሆኑና ከሦስቱ በየትኛው ወይም በየትኞቹ
ወንጌሊት ውስጥ እንዯሚገኙ ሇይቶ ማጥናት ተገቢ ነው፡፡
የማቴዎስ ወንጌሌ

ጸሏፊው

የማቴዎስ ወንጌሌን የጻፈው ከ12ቱ ሏዋርያት መካከሌ አንደ የሆነው ቅደስ ማቴዎስ ነው ፡፡

ይህም ሇወንጌለ በተሰጠው ርዕስ ሊይ ተገሌጧሌ፡፡ በግእዘ ሏ.ኪ. ተሰጠው ርዕስ እንዱህ
ይሊሌ፡፡

‹‹ብስራተ የማቴዎስ ሏዋርያ አሏደ እምዏሠርቱወክሌኤቱ ሏዋርያት ›› ከ12ቱ ሏዋርያት


አንደ የሆነው የሏዋርያው የማቴዎስ ብስራት ›› ይሊሌ፡፡

የጥንት ቤተክርስቲያን አባቶች የመጀመሪያው ወንጌሌ ጸሏፊ ሏዋርያው ቅደስ ማቴዎስ


እንዯሆነ በጽሐፎቻቸው አስረዴተዋሌ፡፡ ከሁለም ቀዯም ያሇው መረጃ ከሏዋሪያውን አበው
መካከሌ አንደ የ ኾነው ፓፒስ /60-130 ዓ.ም/ የመ዗ገበው ነው እርሱም፡- ማቴዎስ የጌታን
ነገር /Loggias/ oracles/ በዕብራይስጥ ቋንቋ ጻፈ›› የሚሌነው፡፡

ስም

‹‹ማቴዎስ ማሇት የእግኢአብሓር ስጦታ ማሇት ነው፡፡ ከ12ቱ ሏዋርያትስም ዜርዜር


በሚገኝባቸው በአራቱም ጥቅሶች ውስጥ ማቴዎስ የሚሇው ስሙ ተመዜግቦ
ይገኛሌ፡፡/ማቴ.10፤2-4፤ ማር.3.16-19፤ለቃ.6.የሏዋርያ1.13/ ነገር ግን በመጠራቱ ታሪክ
ምዜገባ ውስጥ የማቴዎስ ስሙ በራሱ ወንጌሌ‹‹ማቴዎስ››ተብል ሲጠራ በማርቆስና በለቃስ
ወንጌሊት ውስጥ በሚገኘው ትይዩ ታሪክ ዯግሞ ‹‹ ላዊ››ተብል ተጠርቷሌ፡፡/ ማቴ.9.9 n
ማር.2.2ለቃ ከጥንት ጀምሮ ባሇው ታሪክና ትውፊት መሠረት ‹‹ማቴዎስ›› እና ላዊ
የዙሁ የአንደ ሏዋርያ ሁሇቱ ስሞች ናቸው፡፡ በዕብራውያን ዗ንዴ በሁሇቱ ስሞች መጠራት
የተሇመዯ ሲሆን ‹‹ላዊ›› ከቀዴሞ ጀምሮ ይተራበት የነበረው ስሙ ፤ ‹‹ማቴዎስ›› ዯግሞ ጌታን
ከተከተሇ በኋሊ የተጠራበት ስሙ የቤ.ክ. ሉቃውንት ያስረዲለ፡፡

1
ቤተሰቡ

ስሇማቴዎስ ቤተሰብና ስሇ ነገደ በመቅዯመ ወንጌሌ የተመ዗ገበው ታሪክ እንዱህ ይሊሌ፡-‹‹--


ወሇማቴዎስ ስሙ ላዊ ወዉእቱ ዗እምነገዯ ይሳኮር ዗እምሀገረ ናዜሬት ስመ አቡሁ ዱቁ ወስሙ
እሙ ካሩትያስ ፤ ማሇት የማቴዎስ ስሙ ላዊ ነው፤ ይኸውም ከይሳኮር ነገዴ የኾነ ከናዜሬት
ሀገር የኾነ የአባቱ ስም ዱቁ የእናቱም ስም ካሩትየስ ነው፡፡

በዙህ ታሪክ መሠረት የማቴዎስ ነገደ ነገዯይሳኮር ሀገሩ ናዜሪት እንዯሆነ ስሇቤተሰቡ
ዯግሞ አባቱ ‹፣ ዱቁ›› እናቱ ዯግሞ ‹፣ ካሩትያስ ›.እንዯምትባሌ ተገሌጧሌ ፡፤ ነገር ግን
በማርቆስ ወንጌሌ ውስጥ የማቴዎስ አባቱ ‹‹እሌፍዮስ››እንዯሆነ ተመዜግቧሌ፡፡-ይኸውም ፡-

ወኀሉፎእምህየ ርእዩ ስላዊ ወሌዯ እሌፍዩስ እን዗ ይነብር ኀበ ምጽባሔ ፤ማሇት ከዙያ
አሌፎም በመቅረጫው የተቀመጠ የእሌፍዮስ ሌጅ ላዊን አየው ›› የሚሌ ነው፡፡/ማር.2.21

ስሇዙህ በመቅዯመ ወንጌሌ የተገሇጠው‹‹ ዱቁ›› የሚሇው ስም ምናሌባት ‹‹የማቴዎስ ››


አባት ‹‹ እሌፍዮስ›› ላሊ ስሙ ሉሆን ይችሊሌ፡፡

መጠራቱ

ማቴዎስ በራሱ ወንጌሌ ውስጥ በሚገኘው የሏዋርያት ስም ዜርዜር ውስጥ ‹‹--ወማቴዎስ


መጸብሏዊ/ ቀራጩ/ ማቴዎስም ›› ተብል ተጠርቷሌ፡፡/ማቴ.0 /ቀራጭ የተባሇውም
በሥራው የሮማውያን ግብር ሰብሳቢ ስሇነበር ነው፡፡ የቀራጭነት ሥራውን ይሠራ የነበረው
በገሉሊው ገዥ በሄርዴስ አንቲጳስ ሥር ሲሆን ቦታውም በገሉሊ ባሔር በምትገኛው በቅፍርናሆም
ከተማ ነበር /ማር. /ምናሌባት ወዯዯማስቆ በሚወስዯው መንገዴ በነበረ የመቅረጫ ቦታ
ተቀምጦ የዓሣ እና የላሊም ነገር ንግዴን እየተቆጣጠረ የቀራጭነት ሥራውን ይሰራ እንዯነበር
የገመቱ ሉቃውንት አለ፡፡

መዴኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዙህ ሲያሌፍ በመቅረጫው ተቀምጦ አገኛውና


‹‹ተከተሇኝ ››ብል ጠራው፤ ማቴዎስም ሁለን ትቶ ተከተሇው፡፤ በቤቱም ብዘ ቀራጮችና
ኃጢአተኞች ባለበት ሇጌታችን ከዯቀመዚሙርቱ ጋር ታሊቅ ግብዣ አዯረገሇት፡፡ ይህ ማቴዎስ
የመጠራቱ ታሪክ በሦስቱ ሲኖፕቲክ ወንጌሌ ተመዜቧሌ /ማቴ.9.9-13፤ ማር 2.13-17፤ ለቃ
5.27-32/ ሇጌታ ግብዣ ያዯረገሇት በራሱ ቤት ውስጥ እንዯኾነ ከላልች ይሌቅ በግሌጽ

2
የሚያሰረዲ ጥቅስ ለቃ 5.29 ነው ፡፡ ከዙያም እንዯምንረዲው ማቴዎስ ጌታችንን በተከተሇ ጊዛ
ቤት ንብረት የነበረው የመንግስት ባሇስሌጣኖች በሥራ ጓዯኞቹ ዯቀ መ዗ሙር መሆኑን ግብዣ
በማዴረጉ ሇሁለም ግሌጽ አዯረገ ፡፡

ማቴዎስ በክርስቶስና በሏዋርያት ዗መን

ቅ.ማቴዎስ በመጠራቱ ታሪክ ላሊ በመጽሏፍ ቅደስ ውስጥ በጌታና በሏዋርያት ዗መን ተሇይቶ
የሚታወቅበት ታሪክ አሌተመ዗ገበሇትም ፡፡ ቢሆንም እስከ በዓሇ ሃምሳ ዴረስ ሏዋርያት ሁለ
ከጌታ ጋር በነበሩበት ጊዛ እንዱሁም በትንሣኤውና በዕርገቱ ጊዛ በበዓሇ ሃምሳ ዯግሞ
ሇሏዋርያት ሁለ መንፈስ ቅደስ በወረዯሊቸው ጊዛ አብሮ እንዯነበር ማወቅ ይቻሊሌ፡፡
/ማቴ.10.1-5 ለቃ.6.13-16 ዩሏ .6.67 ለቃ.18.31 ማር.16.14 የሏዋ.1.6-13፣2.14 ከዙያም
ሰባቱ ዱያቆናት እስከ ተመረጡበትና እስጢፋኖስ እስከተገዯሇበት ዴረስ ከዙያም በኋሊ ሇተወሰነ
ጊዛ 12 ሏዋርያት በእየሩሳላም እንዯነበሩ ስሇምንረዲ ማቴዎስም እስከዙያ ዴረስ በእየሩሳሇም
እንዯነበር ግሌጽ ነው ፡፡ /የሏዋ.6.2/ከዙህ በኋሊ ሏዋርያ ማቴዎስ ወዳት ሓድ አስተማረ

ያስተማረበት አገር

ሏዋርያው ቅደስ ማቴዎስ ስሊስተማረበት አገር የምንረዲው ከታሪካዊና ትውፊታዊ ማስረጃዎች


ነው፡፡ ‹‹ በ4ኛው ክፍሇ ዗መን የነበረውን አውሳብዮስ ዗ቄስርያ የተባሇው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ
ጸሒፊ‹‹ ጽፏሌ፡፡ /አውሳ.3.6/ በመቅዯመ ወንጌሌ ከዙሁ ጋር የሚስማማ ታሪክ ይገኛሌ፡፡
እርሱም ቀጥል የሰፈረው ነው፡፡

‹‹ ወሶበ ተጋብኡ ኀቤሁ ጉባዔ ብዘኀ እምአይሁዴ ዗ጻውኦሙ ወእሇሂ አምኑ ወተጠምቁ
ወኃሠሡ እምኔሁ ከመያስተጻንእ አሌባቢሆሙ ዗አእመኖሙ ቦቱ በቃሌ ወበ መጽሏፍ
዗ዛነዎሙ በሌሳነ ዕብራይስጥ ወተሰጥወ ስእሇቶሙ ››፡፡ ይሊሌ

በገዴሇ ሏዋርያትና በመጽሏፈ ስንክሳር ሊይ አገረ ካህናት በተባሇ ቦታ እና በአካባቢው እንዯሰበከ


ተመዜግቧሌ፡፡ ሇምሳላ ፡- በመጽሏፈ ስንክሳር የተመ዗ገበው ፡-

‹‹ ወበዚቲ ዕሇት አአረፈ ቅደስ ማቴዎስ አሏደ እምዏሠርቱ ወክሌኤቱ ሏዋርት አምዴኅረ ስበከ
ውስተ ሀገረ ካህናት ወሜጦሙ ውስተአእምሮ እግዙአብሓር ›› ይሊሌ /ስንክ.ጥቅ.12/ ከዙህም
ላሊ ስንክሳር ማቴዎስ በኢየሩሳላምና በአካባቢው እንዯስተማረ ጨምሮ ገሌጧሌ ይኸውም ፡-

3
‹‹ . . . ወእምዴኅሬሁ ወጽአ ቅደስ ማቴዎስ ሏዋርያ ወንጌሊዊ ኀበ ኢየሩሳላም ወምዴረ
ይሁዲ ወጸሏፈ ወንጌሇ በዕብራይስጥ ወእምዜ ወጽአ ኀበ ሀገር ዗አፍአ ‹. . . ››ይሊሌ

‹‹ መቅዯመ ወንጌሌ ማቴዎስ ወዯ ህንዴም ሓድ እንዯነበር እንዱህ ሲሌ ይጠቀማ ‹‹ ወወጠነ


ጽሑፎተ ዜንቱ በፍሌስጤኤም ወፈጸማ በህንዴ በዕብራይስጣዊ አመተሰደ አይሁዴ እምዴረ
ይሁዲ ››

. ቅደስ ማቴወስ ኢትዮጵያም መጥቶ አስተምሮ እንዯነበር የተሇያዩ ጥንታዊያን የቤተ


ክርስቲያን ታሪክ ጻሏፊዎች መዜግበዋሌ ፡፡ ከእነዙህ ውስጥ አውሳብዮስ እና ሩፊኖስ
የተባለት ይገኙባቸዋሌ ፡፡

ዕረፍት፡-

ስሇ ቅደስ ማቴዎስ ዕረፍት በመጽሏፈ ገዴሇ ሏዋርያትና በመጽሏፈ ስንክሳር የሚገኘው ታሪክ
ቅ.ማቴዎስ ከኢየሩሳላም ወጥቶ በሄዯበት ሀገር በእስር ቤት ገብቶ የጌታውን ገን዗ብ አጥፍቶ
የታሰረ አንዴ አስረኛ ያዯረገሇት ታምር በተሰማ ጊዛ በዙህ ታምር ብዘ ህዜብ ስሊሳመነ ዮስጦስ
የተባሇው የዙች ሀገር ገዧ ተቆጥቶ አንገቱን በሰይፍ እንዲስቆረጠው ይናገራሌ ፡፡ /ገዴ ሏዋ
ስንክ. ጥቅ 12 ተመሌከት /

መቅዴመ ወንጌሌ ዯግሞ ስሇሞተበት እና ስሇተቀበረበት ቦታ እንዱሁም ስሇ አሟሟቱ ጊዛውን


ጠቅሶ ሲናገር፡-

‹‹ ወኮነ ስምዓ በሀገረ-በስባራ ውጉረ በዕብን አመ 02 ሇጥቅምት ወተቀብረ በቅርጣግና ዗ቂሳርያ


››ይሊሌ በነዙህ ታሪኮች ስሇ አሟሟቱ የተገሇጠውን ስናገናኘው በዴንጋይ ተወግሮ አንገቱን
በሰይፍ እንዯተቆረጠ እንገነ዗ባሇን፡፡

በምዕራባውያን በምስራቃውያን የተመ዗ገበው የማቴዎስ የዕረፍት ታሪክ በጣም የተሇያየ ነው፡፡


ስሇዙህም እዙህ ሊይ ማንሳት አስፈሊጊ ባሇመሆኑ ታሌፏሌ፡፡

ሇምሳላው

ማቴዎስ በገጸሰብእ ይመስሊሌ ፡፡ የዙህም ምክንያት የጌታን ሰው መሆን ከአብርሃም ጀምሮ


ትውሌዴ ቆጥሮ በመጻፍ ስሊሳየ ነው /ማቴ.1.1-17/ ይህንንም ብዘዎች የቤ.ክ.አባቶች

4
አስረዴተዋሌ፡፡ የትርጓሜ ወንጌሌ መግቢያም ይህን ያስረዲሌ፡- ‹‹ማቴዎስ በገጸብእሲ ይመሰሊሌ
ወሌዯ ዲዊት ወሌዯ አብርሃም እያሇ ምዴራዊ ሌዯቱን ይጽፋሌና›› በማሇት ይገሌጻሌ፡፡

የተጻፈሇት ዗መን ቦታና ቋንቋ

የማቴዎስ መንጌሌ የተጻፈበትን ዗መን በተመሇከተ በተሇያዩ ሉቃውንት ዗ንዴ ያሇው አመሇካከት
የተሇያየ ነው፡፡ አብዚኛው አመሇካከት ግን ኢየሩሳላም በ70 ዓ.ም ከመጥፋቷ በፊት የተጻፈ
መሆኑን የማገሌጽ ነው፡፡ ከ4ቱም ወንጌሊት በቅዴሚያ የተጻፈው ‹‹ የማርቆስ ወንጌሌ ነው››
በማሇት ብዘዎች ቢያምኑም ብዘዎች ሉቃውንት ዯግሞ የማቴወስ ወንጌሌ ስሇተጻፈበት ዗መን
በመቅዯመ ወንጌሌ የተመ዗ገበው አስረጁ እንዱህ ይሊሌ ፡፡

‹‹ ወወጠነ ጽሑፎተ ዜንቱ መጽሏፍ በፍሌስጥኤም ወፈጸማ በህንዴ ዕብራይስጣዊ አመተሰደ


አይሁዴ እምዴረ ይሁዲ በቀዲሚት ዓመተ መንግስቱ ሇአቅላንዴዬስ ቄሳር ወይእቲ ተስአት
ዓመት እምዕርገት ቅዴስት፡፡

በማቴዎስ ወንጌሌ ትርጋሜ መዯምዯሚያ ሊይ ዯግሞ እንዱህ ይሊሌ፡፡ ‹‹ መሌአ ጽሔፈተ


ብስራቱ ሇማቴዎስ ሏዋርያ አሏደ እም አስርቱ ወክሌኤቱ ሏዋርያት ወኮነ ዗ጸሏፎ
በፍሌስጤም በሌሳነ ኢብራይስጣዊ በአስተሏምሞ መንፈስ ቅደስ እምዴህረ ዕርገቱ ሇእግዙነ
እየሱስ ክርስቶስ ዗በአጰርግዮን ኀበ ሰማይ ወበቀዲሚት ዓመተ መንግስቱ ሇቀሊውዱዎስ ቄሳር ‹‹
ከነዙህ መረጃዎች ውስጥ የማቴዎስ ወንጌሌ የተረጻፈበት ቦታ ፍሌስጤም ሲሆን ጹሁፉም
የተጻፈበት ቦታ ህንዴ እንዯሆነ እንረዲሇን የተጻፈበት ቋንቋ ዕብራይስጥ መሆኑን ይገሌጣለ
፡፡አንዲንዴ ታሪኮች ግን በአራማይክ ነው ይሊለ፡፡ አራማይክ በዙያ ዗መን ዕብራውያን ይናገሩበት
የነበረው የዕብራይስጥ ዱያላክት ስሇሆነ ክርስቶስም ያስተማረበት ቋንቋ ስሇሆነ የተሇየ ታሪክ
ሉሆን አይችሌም ፤ ማሇት የግእዜ መጻሔፍት በዕብራይስጥ ነው ካለት ጋር ብዘህ አይሇያይም
ዕብራይስጥም አረማይክም ቢሌ አንዴ ነው፡፡ የተጻፈበትን ዗መን በተመሇከተ በግዕዜ መጻሔፍት
ውስጥ ከተገኙት ማስረጃዎች ጌታ ካረገ በኋሊ 8ኛው ዓመት ተፈጽሞ 9ኛው ዓመት ሲጀመር
ቀሊውዱዎስ ቄሳር በነገሰ በመጀመሪያው ዓመት እንዯነበር እንገነ዗ባሇን ፡፡ ይህም ፡-

ከጌታ ዕርገት በፊት 33 ዓመት


ከጌታ ዕርገት በኋሊ 8 ዓመት
ዴምር 41 ዓመት ይሆናሌ

5
ስሇዙህ በዙሁ መረጃ መሰረት የማቴዎስ ወንጌሌ የተጻፈው በ41 ዓ.ም መሆኑ ነው ፡፡ ይህም
዗መን የማቴዎስ ወንጌሌ ከ4ቱም ወንጌሊት እንዱሁም በጠቅሊሊ ከሏ.ኪ.መጻሔፍት ሁለ
በቅዴሚ የተጻፈ እንዯሆነ ያሳያሌ፡፡

የተጻፈሊቸው ሰዎች

በጸሏፊው በማቴዎስ ታሪክ ውስጥ እንዯተመሇከትነው ብዘዎች የግእዜ መጻሔፍት ማቴዎስ


ወንጌለን የጻፈው ከዕብራውያን /ከአይሁዴ/ ወዯ ክርስትና ሇተመሇሱ ሰዎች ነው ፡፡ የትርጓሜ
ወንጌሌ ካስተማራቸው በኋሊ ወዯ ላሊ ሀገር ሉሄዴ ሲሌ በምዴረፍሌስጥኤም ሊለ አይሁዲውያን
ክርስቲያኖች እንዯጻፈሊቸው ሲገሇጥ፡-

‹‹. . . ምዴረ ፍሌስጥኤም ሇማቴዎስ በዕጣ ዯረሰችው ከዙህ ገብቶ ጌታ ከጽንስ ጀምሮ ያዯረገው
ታምራት ያስተማረውን ትምህርት የሠራውን ትሩፋት ቢነግራቸው እሥራኤሌ ናቸውና ከኦሪት
ወዯ ወንጌሌ ከገቢረ ኃጢአት ወዯ ገቢረጽዴቅ ተመሇሱ አመኑ ተጠመቁ ፡፡ ትምህርት
ካሌዯረሱበት ሇማዲረስ ወጥቶ በሚካሄዴበት ጊዛ በቃሌ ያሇ ይረሳሌ በመጽሏፍ ያሇ ይወረሳሌ
ብሇውት በዙህም ምክንያት ነው፡፡ የጻፉት አንዴም እሱ እንዲባትነቱ ከራሱ አንቅቶ
ይጽፍሊቸዋሌ ›› ይሊሌ፡፡ ይህም በመቅዯመ ወንጌሌ ስሇተጻፈሊቸው ሰዎች ከሚገኘው መረጃ ጋር
አንዴ ነው፡፡

ማቴዎስ ወንጌለን የፃፈው ሇዕብራዊያን መሆኑ ከጥንት የቤ/ክ አባቶች መካከሌ ጎራጎርዮስ
዗እንዙናዘ የቅደሳት መጻሔፍትን ቀኖና በገሇጻበት ጽሐፍ ‹‹ ማቴዎስ ሇዕብራውያን
ታምራተኢየሱስን ጻፈ›› ብሎሌ ፡፡የመጻህፍም አጠቃሊይ ይዝታ በዕብራዊያን ክርስትያኖች
የተጻፈ መሆኑን ያሳያሌ፡፡

6
ማቴዎስ ወንጌለን የጻፈው ሇዕብራውያን መሆን ከጥንት የቤ.ክ. ኣባቶች መካከሌ ጎርጎርዮስ
዗እንዙናዘ ቅደሳት መጻሔፍትን ቀኖና በገሇጸበት ጽሐፍ « ማቴዎስ ሊዕበራውያን ተአምራት
ኢየሱስን ጻፈ» ብሎሌ፡፡ የመጽሏፉም አጠቃሊይ ይዝታ ሇዕብራውያን ክርስቲያኖች የተጻፈ
መሆኑን ያሳያሌ፡፡

የተጻፈበት ዓሊማ

የማቴዎስ ወንጌሌኝ ስናጠና ማቴዎስ የጌታኝ ታሪክና ሥራ በወንጌለ ውስጥ ሇዕብራውያን


የጻፈው ሚከተለት ዓሊማዎች መሆኑን እንረዲሇን፡፡

1. ኢየሱስ ክርቶስ ከአብርሃምና ከዲዊት ትውሌዴ የተወሇዯ ፍፁም ሰው መሆኑን ሇማስረዲት


ነው፡፡ ይህንንም ኣብ ትውሌደን በመቁጠር፣ ጌታ ራሱን « የሰው ሌጅ» እያሇ መጥራቱንና
በላልች ሰዎች « የዲዊት ሌጅ» ተብል መጠራቱን በመመዜገብ ያስረዲሌ ፡፡ 1፥1-17፣ 8፥20
6፣9፥27፣ 12፥27፣16፥13፣17፥12፣18፥11፣ 25፥31፣26፥64

2. በሰዎች ዗ንዴ ጌታ ከነቢያት አንደ ሲባሌ እንኳ የእግዙአብሓር ሌጅ መሆኑን እንዱታወቅ


ሇማስረዲት ነው / *17፣8፥29፣11፥25-27፣14፥33፣16፥13-17፣ 17፥5፣27፥40፡43፡54/

3. ይሔግና በነቢያት መጻሔፍት /በብኪ/ ስሇ ክርስቶስ የተነገሩትን ትንቢታዊ ቃሊት እየጠቀሰ


ፍጻሜአቸውን ሇማሳየት ነው:: ማቴዎስ በወንጌለ ውስጥ ከ60 ጊዛ በሊይ የብኪ. ጥቅሶችን
ጠቅሷሌ፡፡ ከእነዙህም ብዘዎቹ ሔግና ነቢያት ስሇ ክርስቶስ /መሲህ/ ምን እንዯተናገሩ
የሚገሌፁ ናቸው:: የማቴዎስ ወንጌሌ ከሏ.ኪ. መጻሔፍት በመጀመሪያ የተ዗ረ዗ረው
የብኪዲንን ፍጻሜ አሳይቶ ወዯ ሑኪ የሚያሸጋግር ዴሌዴይ የሆነ ወንጌሌ በመሆኑ ነው፡፡
ስሇዙህ የማቴዎስ ወንጌሌ ሔግና ነቢያትን በመጥቀስ ኢየሱስ እርሱ እንዯሚመጣ ይጠበቅ
የነበረው መሢህ | ክርስቶስ መሆኑን ሇዕብራውያን ያስረዲሌ፡፡ /1፥22:23፣2፥4፣4፥16፣11፥2-5
12፥17-21፣ 13፥35፣16፥16፣21፥5:42፣ 22፥41-46፣27፥9/

የወንጌለ ጥናት

የማቴዎስ ወንጌሌ 28 ምዕራፎችና 1061 ቁጥሮች ያለት መጽሏፍ ነው በዙህ ክፍሌ ውሰጥ
የነዙህን ምዕፎች ቁጥሮች ቃሌ በማንበብ የወንጌለን ይዝታና አከፋፈሌ እናጠናሇን፡፡

7
• ይዝታው፡-

4ቱም ወንጌሊት ስሇ ጌታችን ስሇ ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ነገሮችን ይ዗ዋሌ፡፡ እነርሱም፡

1. የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ

2. ኢየሱስ ክርስቶስ ያዯረጋቸው ታምራት

3. ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማራቸው ትምህርቶች ናቸው::

28ቱን የማቴዎስ ወንጌሌ ምዕረፋት በማንበብ እነዙህን ሦስት ይዝታዎች እንዯሚከተሇው


እናጠናሇን፡፡

1. የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ ይዞሌ፡፡

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ታምራትና ትምህርቶች በታሪኩ ውስጥ ሉነገሩ ይችሊለ፡፡ ነገር ግን
በዙህ ጥናት ውስጥ « የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ» ስንሌ በማስተማር ዗መኑ ያዯረጋቸውን
ታምራትና ያስተማራቸውን ትምህርቶች ሳያጠቃሌሌ ከሌጅነት እስከ ዕርገቱ የተመ዗ገቡትን
ታሪኮች ያመሇክታሌ፡፡

በማቴዎስ ወንጌሌ ውስጥ ብዘ የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪኮች ተመዜግበዋሌ፡፡ ከብዘዎቹ


ውስጥ በማቴዎስ ወንጌሌ ውስጥ ብቻ የተመ዗ገቡትን 1ዏ ታሪኮች እንመሇከታሇን፡፡

1. ከአብርሃም ጀምሮ የተቇጠረው የክርስቶስ ሏረግ ትውሌዴ / 1፥1-17/

2. የጌታ ሌዯትና በተወሇዯ ጊዛ የሰብአ ሰገሌ መምጣት /1፥18፣ 2፥12/

3. ጌታ በሔፃንነቱ ከእናቱ ከዴንግሌ ማርያም ጋር መሰዯዴ / 2፥3-23/

4. ጌታ የማስተማር ሥራውን ሇመጀመር ወዯ ቅፍርናሆም መሄደ 4፥12-17/

5. በቅፍርናሆም ሇመንግሥት ግብር መገበሩ

6. የአስቆሮቱ ይሁዲ ጌታን አሳሌፎ እንዱሰጣቸው የካህናት አሇቆች 30 ብር እንዯመ዗ኑሇት


/26፥14-16

8
7. የአስቆረቱ ይሁዲ ጌታ እንዯተፈረዯበት ሲያይ ተጸጽቶ 30 ውን ብር በቤተመቅዯስ ጥል
በመሄዴ ታንቆ እንዯሞተ /27፥3-1ዏ/

8. ጲሊጦስ ጌታ እንዱሰቀሌ አሳሌፎ በሰጠው ጊዛ እጁን መታጠቡ 127፥224

9. ጌታ ተሰቅል ከሞተ በኋሊ የካህናት አሇቆችና ፈሪሳውያን የተቀበረበትን መር አትመው


በጭፍሮች እንዲስጠበቁ / 27፥62-66/

10. ጌታ ከሙታን ተሇይቶ ከተነሳ በኋሊ ሇጠባቂዎቹ ገን዗ብ በመስጠት « ዯቀ መዚሙርቱ »


« ስረቁት» ብሇው እንዲስወሩ / 28፥1-15/

2. ኢየሱስ ክርስቶስ ያዯረጋቸውን ታምራት ይዞሌ

በማቴዎስ ወንጌሌ ውስጥ ጌታችን በማስተማር ዗መኑ ብዘ ታምራትን አዴርጉ እንዯነበር


በተሇያዩ ቦታዎች ይገሌጻሌ /4፥23:24፣8፥17፣14፥35:36፡፡/ ነገር ግን በማቴዎስ ወንጌሌ
ታሪካቸው በተሊይ የተመ዗ገበው 21 ታምራት ናቸው ከእነዙህም ውስጥ በማቴዎስ ወንጌሌ ብቻ
የሚገኙት ታምራት ሲሆኑ እነርሱም፡-

1. በመንገዴ ሲያሌፍ የተከተለትን ሁሇት ዕውሮች ወዯ ቤት በገባ ጊዛ ዓይናቸውን በመዲሰስ


አበራሊቸው (9፥27-30

2. ግብር እንዱሰጥ በተጠየቀ ጊዛ ጴጥሮስን መቃጥን ሲጥሌ መጀመሪያ ከሚወጣው ዓሣ አፍ


እታቴር እንዯሚያገኝ በነገረው መሠረት አገኘ፡፡ 7፥24-27

3. በኢያሪኮ የሁሇት ዕውሮችን ዓይን አበራ / 2ዏ፥29-34

4. ጌታ የተሰቀሇ ዕሇት ምዴር ተናወጠች፣ ዓሇቶች ተሰነጠቁ፣ መቃብሮች ተከፈቱ፣ ከቅደሳን


(ብዘ ሥጋዎች ከሙታን ተነሡና እና ከተማ ታዩ /27፥51-53/ ላልች 17 ታምራት
በማርቆስ ወንጌሌ ጥናት ተመሌክቶ ማጥናት ያስፈሌጋሌ፡፡

9
3. ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማራቸውን ትምህርቶች ይዞሌ

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀና ከተፈተነ በኋሊ መጥምቁ ዮሏንስ አሌፎ እንዯተሰጠ በሰማ
ጊዛ በገሉሊ ውስጥ በቅፍርናሆም ከተማ ወንጌሇ መንግሥትን ማስተማር እንዯጀመረ የማቴዎስ
ወንጌሌ ይናገረናሌ / 4 ፥ 12-15/

በዙህ ወንጌሌ የተመ዗ገቡት የጌታ ትምህርቶች ብዘዎቹ በገሉሊ ውስጥ ያስተማራቸው


ትምህርቶች ናቸው፡፡ ቢሆንም በመጨረሻ ጊዛው በይሁዲ አውራጃዎችና በኢየሩሳላም ከተማ
ያስተማራቸው ትምህርቶች ተመዜግበዋሌ/ 19፥1:2/

በማቴዎስ ወንጌሌ ውስጥ የተመ዗ገቡት የጌታ ትምህርቶች ብዘዎች በማርቆስና በለቃስ


ወንጌሊት ውስጥ ይገኛለ፡፡ በተሇይም ከለቃስ ወንጌሌ ጋር የሚያመሊሌሳቸው መሠረታዊ ነጥብ
ከጌታ ትምህርት በስፋት መመዜገባቸው ነው፡፡

ስሇዙህ በዙህ ወንጌሌ የተመ዗ገቡትን ሁለ አሁን ተመሌክተን በዙህም ወንጌሌ ያሌመ዗ገቡትን


ዯግሞ በማርቆስና በለቃስ ወንጌሳት መመሌከቱ የተሻሇ ነው:: የጌታን ትምህርቶች የምናጠናው
በሁሇት ከፍሇን ነው::

ሀ. ጌታ በቀጥታ ራሱ ያስተማራቸው ትምህርቶች

ጌታ ከሔዜብ ወይም ክሔዜብ አሇቆች ወይም ከተማሪዎች ሳይጠየቅ በቀጥታ ራሱ


ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከሌ በማቴዎስ ወንጌሌ ውስጥ 5 ትምህርቶችን ተመዜግበዋሌ፡፡
እነርሱም፡

1. በተራራ ሊይ ሆኖ የስተማረው ረጅም ትምህርት / የተራራው ስብከት ወይም አንቀፀ


ብፁዓን /5፥1-7፥29/ 2.

2. በስምንት ምሳላዎች ያስተማረው ትምህርት /13፥1-52/

3. ሉከተሇው የሚወዴ ራሱን ክድ እንዱከተሇው የሰጠው ትምህርት / 16፥24-28/

4. ሇሌጁ ሠርግ ባዯገ ንጉሥ ምሳላ ስሇመንግሥተ ሰማያት ያስተማረው ትምህረት /22፥1-
14 5 ሇጻፎችና ሇፈሪሳውያን ስሇግብዜነታቸው የሰጠው የተሣጽ ትምህርት /23፥1-23/

10
ሇ. ከሚቀርቡሇት ጥያቄዎች በመነሳት ያስተማራቸው ትምህርቶች

ጌታ ከሚከተለት ሔዜብና ከዯቀመዚሙርቱ እንዱሁም ከተቃዋሚዎቹ ከሚቀርቡሇት ጥያቄዎች


በመነሳት ብዘ ትምህርቶችን አስተምሯሌ፡፡ በዙህ ጥናት መሠረት በማቴዎስ ወንጌሌ ውስጥ
የተመ዗ገቡት በጥያቄዎች መነሻነት ያስተማራቸው ትምህርቶች 15 ናቸው፡፡ እነርሱም፡

1. ዯቀ መዚሙርቱ ስሇምን እንዯማይጦሙ በተጠየቀው ተነስቶ ያስተማረው 9፥14-17

2. መጥምቁ ዮሏንስ በወኅኒ ሳሇ በሳከሇት ጥያቄ መነሻነት ያስተማረው /11፥2-30/

3. ሔዜቡ ‹‹ የዲዊት ሌጅ ይሆንን?» ሲለ ፈሪሳውያን በመቃወማቸው ያስተማረው


[12፥23-37/

4. ፈሪሳዉያን ምሌክትን እንዱያሳያቸው ጠይቀውት ያስተማረው 412፥38-50

5. ፈሪሳውያን ስሇወግ ተቆርቁረው ባቀረቡት ጥያቄ መነሻነት ያስተማረው /15፥1-20/

6. ዯቀ መዚሙርቱ ስሇ ኤሌያስ ጠይቀውት በሰጣቸው መሌስ ያስተማረው /17፥10-13/

7. ዯቀ መዚሙርቱ ጋኔን ያሊወጡት ሇምን እንዯሆነ ጠይቀውት ያስተማራቸው /17፥9-21

8. ዯቀ መዚሙርቱ በመንግሥተ ሰማያት ከሁለ የሚበሌጥ ማን እንዯሆነ ጠይቀውት


ያስተማረው/18፥1-20

9. ጴጥሮስ ስሇ ይቅርታ በጠየቀው ተነሥቶ በምሳላ ያስተማረው 18፥21-35/

10. ፈሪሳውያን ስሇፍቺ ጠይቀውት በሰጠው መሌስ ያስተማረው /19፡3-12/

11. አንዴ ባሇጠጋ ስሇመሌካም ነገር ጠይቆት ያስተማረው !19፥15-20፥16

12. የካህናት አሇቆችና የሔዜቡ ሽማግላዎች ስሇ ሥሌጣኑ ጠይቀውት ያሰተማረው /21፥23-44

13. ሰደቃዉያን ትንሣኤን የሚመሇከት ጥያቄ ጠይቀውት ያስተማረው /22 ፥23-33/

14. ፈሪሳውያን ስሊ ሔግ ጠይቀውት ያስተማረው /22፥34-46/

11
15. ዯቀ መዚሙርቱ ስሇ ምጽአቱ ጠይቀውት ያስተማረው | 24፥1-25፥46/

አስተውሌ:- ጥያቄውን በትምህርት ውሰጥ የተሰጠው መሌስ እንዳት እንዯሚገናኝ


ሇእያንዲንዲቸው የተሰጡትን ጥቅሶች በማንበብ እያስተዋለ ማጥናት ያስፈሌጋሌ፡፡

አከፋፈለ

ወንጌሊትን የምዕራፋቸውን ቅዯም ተከተሌ ጠብቆ በአስተዋጽኦ ወይም በአከፋፈሌ ማጥናት


ይቻሊሌ፡፡ እኛ የምናጠናው በዏበይትና በንዐሳን ክፍልች በመከፋፈሌ ነው። በዙህ መሠረት
28ቱን የማቴዎስ ወንጌሌ ምዕራፉ በ7 ዏበይት ክፍልች ከፍሇን እናጠናቸዋሇን፡፡

1. መግቢያ /1፥1-17/

 የጽሐፉ ርእስ /1፥1/

 ከአብርሃም እስከ ክርስቶስ ማቴዎስ የቆጠረው ሏረገ-ትውሌዴ /1፥2-17/

2. የኢየሱስ ክርስቶስ የሔፃንነቱ ታሪክ /1፥18-2፥23/

 የኢየሱስ ክርስቶስ ሌዯት /1፥18-25/

 በተወሇዯ ጊዛ የሰብአሰገሌ መምጣት /2፥1-12

 ከእናቱ ከዴንግሌ ማርያም ጋር ወዯ ግብጽ መሰዯደ /2፥13-23/

3. ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ከመጀመሩ በፊት የተዯረጉ ነገሮች /3፥1-4፥11/

 የመጥምቁ ዮሏንስ ምስክርነት /3፥1-12/

 በዮርዲኖስ ወንዜ በመጥምቁ ዮሏንስ እጅ መጠመቁ /3፥13-17/

 40 ቀንና 40 ላሉት ከጦመ በኋሊ በዱያብልስ መፈተኑ /4፥1-11/

4. ጌታ በማስተማር ዗መኑ በገሉሊ እና ባካባቢዋ የሠራው ሥራና ያስተማረው ትምህርት


/4፥12-18፥35/

12
 ማስተማር ሲጀመር 4ቱን ዯቀ መዚሙርት እንዯጠራ 4፥12-25/

 በተራራ ሊይ የሰጠው ሰፊ ትምህርት /5፥1-7፥29/

 በገሉሊ ውስጥና ባካባቢዋ ያዯረጋቸው ታምራት /8፥1-9፥38/

 12ቱ ዯቀ መዚሙርትን በሊካቸው ጊዛ የሰጣቸው ሥሌጣንና ትእዚዜ /10፥1-42/

 በተሇያዬ ጊዛያትና ቦታዎች ያስተማራቸው ትምህርቶችና ያዯረጋቸው ታምራት /11፥1-


19፥35/

5. ጌታ በማስተማር ዗መኑ መጨረሻ በይሁዲ አገር የሠራው ሥራና ያስተማረው ትምህርት


/19፥1-26፥46/

 ወዯ ኢየሩሳላም ከመውጣቱ በፊት በይሁዲ ያዯረገውና ያስተማረው /19፥1-20፥16/

 ወዯ ኢየሩሳላም በመውጣት ሊይ ሳሇ ስሇሞቱና ስሇትንሣኤው መናገሩ /20፥ 17-28/

 በኢያሪኮ ያዯረገው ታምር /20፥29-34

 ወዯ ኢየሩሳላም ከገባ ጀምሮ እስከተያ዗ ዴረስ ያዯረገውና ያስተማረው /21፥1-26፥46/

6. የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅሇት / 26፥47-27፥6

 በይሁዲ ሰመጡ ጭፍሮች ተይዝ እንዯተመረመረ 26፥47-27፥26

 በመስቀሌ እንዯሰቀለት 127፥27-56/

 እንዯተቀበረና መቃብሩን እንዲስጠበቁ /27፥57-66

7. የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ /28፥1-20/

 የተነሳ ዕሇት ሇማርያም መግዯሊዊትና ሇሁሇተኛይቱ ማርያም እንዯ ታየ/28፥1-10/

 ጠባቂዎቹ ገን዗ብ ተቀበሇው ስሇ ትንሣኤው የሏሰት ወሬ እንዲወሩ/28፥11-15/

 ኢየሱስ ሇ 11ደ ዯቀ መዚሙርት የሰጠው የመጨረሻው ትእዚዜ /28፥16-20/

13
የማርቆስ ወንጌሌ

ጸሏፊው

የሁሇተኛው ወንጌሌ ጸሏፊ ቅ. ማርቆስ ነው:: ቅ.ማርቆስ ይህንን ወንጌሌ የጻፈው ራሱ


በሚያውቀው መሠረት ብቻ ሳይሆን ከቅደስ ጴጥሮስ በሰማውም መሠረት መሆኑን የሚገሌጹ
ትውፊቶች አለ፡፡ ከእነዙህ መካከሌ ሁሇቱን እንጠቅሳሇን።

1. አውሳብዬስ በቤተ ክርስቲያን ታሪኩ ውስጥ የጠቀሰው የፓፒያስ ቃሌ ነው፡፡ እርሱም


እንዱህ ይሊሌ፡፡

 ‹‹የጴጥሮስ ትርጁማን የነበረው ማርቆስ የክርስቶስን አባባልችም ሆነ ሥራዎች፣


የሚያስታውሰውን ሁለ ትክክሌ ጽፎ አስቀምጧሌ፡፡ ... ጴጥሮስን ተከትሎሌ እንዲሌኩት
ከእርሱ ትምህርት የሚያስፈሌገውን እየወሰዯ የጌታን ነገር ጽፎ አጠናቅቋሌ፡፡ ... »
ብሎሌ / አውሳብ የቤ.ክ.ታሪክ 3፥39/

2. ጽሏፈ ስንክሳር ሊይ የተመ዗ገበው ታሪክ ነው፡፡ ይኸውም፡

ሀ. የቅጴጥሮስን ታሪክ በሚተርክበት ክፍሌ፡ -

« . . ወነገሮ ሇማርቆስ ወተርጉመ ልቱ ወንጌሇ ወአጽሏፎ» ይሊሌ :- ስንክሳር ሏምላ5

ሇ. የቅ.ማርቆስን ታሪክ በሚተርክበት ክፍሌ ዯግሞ፡

 ወኮነ ልቱ ረዴኦ ወበህየ ጸሏፈ ወንጌሌ ዗ተርጉመ ልቱ ጴጥሮስ ወሰበከ ቦቱ ሀገረ ሮሜ


» ይሊሌ /ስንክሳር ያዜያ 30/

ከዙህ የምንረዲው ማርቆስ ወንጌለን የጻፈው ራሱ ባስታወሰው መሠረት እና ከቅደስ ጴጥሮስ


ባገኘው ሠረት መሆኑን ነው:: ይህን አቀናጅቶ ሲጽፍ የመንፈስ ቅደስ መሪነት ያሌተሇየው
መሆኑ ግሌጽ /የታመነ/ ነው::

14
ስሙ

የዙህ ወንጌሌ ጸሏፊ ሁሇት ስሞች አለት:: አንደ « ዮሏንስ» ሉሆን ላሊው ዯግሞ « ማርቆስ›
ነው ይህንን በሚከተለት ጥቅሶች እንረዲሇን፡፡

ዮሏንስ » ተብል የተጠራበት ክፍሌ / ዮሏ.12፥12፥25፥13፡5:13፡፡/ ‹‹ማርቆስ» ተብል


የታጠራበት ክፍሌ / የሏዋ.15፥9/ 2ጢሞ. 4፥11፣1ጴጥ.5፥13/ | ዮሏንስ የቀዴሞ ስሙ ማርቆስ
ዯግሞ በኋሊ የተሰጠው ስሙ እንዯሆነ በሏዋርያት ሥራ ውስጥ» ማርቆስ የተባሇው ዮሏንስ
«ተብል በተጻፈው የማርቆስ የስም አጠራር ሌንረዲ እንችሊሇን፡፡ የዙህ ዓይነቱን አጠራር ሦስት
ጊዛ እናገኛሇን፡፡ እነርሱም፡ ፡ የሏዋ. 12፥12:: 2. የሏዋ.12፥25 3. የሏዋ.15፥37 ናቸው
ዮሏንስ» አይሁዲዊ ስሙ ሲሆን «ማርቆስ» ዯግሞ ሮማዊ ስሙ እንዯሆነ ብዘ መዜገበ ቃሊቶች
ይናረራለ፡፡ ያን ዗መን ብዘዎች አይሁዲዊያን ከአይሁዲዊ ስማቸው በተጨማሪ ሮማዊ ወይም
ግሪካዊ ስም ነበራቸው ሇምሳላ የሏዋ. 1፥23፣ 13፥9፣ ማር. 2፥14፣3፥18 . . . ተመሌክት፡፡
በዙሁ ዓይነት ቅ.ማርቆስ እነዙህ ሁሇት ች ሉኖሩት እንዯቻለ እንገነ዗ባሇን ሆኖም ሇስብከተ
ወንጌሌ ከተሇየ ከተሰማራ ጀምሮ በአብዚኛው የተጠራበት ስሙ «ማርቆስ» የተባሇው ስሙ
ነው:: ማርቆስ ማሇት «ታሊቅ መድሻ» ማሇት እንዯሆነ ኢንተርፕሬተርስ ባይብሌ ዱክሽነሪ
የተባሇው መዜገበ ቃሊት ይተረጉማሌ፡፡ ትርጓሜ ወንጌሌ ግን ማርቆስ ማሇት « ካህን ፣ ሌኡክ»
ማሇት እንዯሆነ ይገሌጣሌ፡፡ ያም ሆነ ይህ ማርቆስ ከ4ቱም ወንጌሊት አጠር ያሇውን ወንጌሌ
የጻፈሌን ወንጌሊዊ ነው:: ታሪኩንም ከሏዱስ ኪዲን “ሔፍትና ከቤ.ክ. ትውፊት እናገኛሇን፡፡
ይህም እንዯሚከተሇው ይቀርባሌ፡፡

ቤተሰቡ በሏዋ.12፥12 ሊይ የቅደስ ማርቆስ እናት በኢየሩሳላም የነበሩት ክርስቲያኖች


ቤቷን እንዱጸሌዩበት ሰጥታ የነበረችው« ማርያም» የተባሇች ቅዴስት ሴት እንዯሆነች እንረዲሇን

ቤቷም ቤተክርስቲያን ተብል ተጠርቷሌ /የሏዋ.12፥5/ ይህ ቤት ጌታችን የመጨረሻውን እራት


ያዯረገበት እንዯሆነ ይነገራሌ ማር.14፥12 16 ይህም ከሆነ በማር.14፥14 ሊይ « የቤቱ ጌታ»
የተባሇው ሰው የማርቆስ አባት መሆኑ ነው፡፡

የማርቆስ አባት በመጽሏፍ ቅደስ ስሙ ባይገሇጥም የባርናባስ ወንዴም እንዯሆነ ግን ከመጽሏፍ


ቅደስ ማወቅ ይቻሊሌ፡፡

15
ምክንያቱም ማርቆስ የባርናባስ የወንዴሙ ሌጅ እንዯሆነ ተገሌጧሌና ነው / ቇሊ.4፥1ዏ በአማርኛ
መጽሏፍ ቅደስ ቅደስ ተመሌከት

በስንክሳርና በገዴሇ ሏዋርያት ሊይ ግን የማርቆስ አባት ስሙ አርስጦ ጳውልስ እንዯሆነ


ተመዜግቧሌ፡፡ በሏዋ.12 ፥ 12 ሊይ የቤቱ ባሇቤት ሆና የተገሇጠችው የማርቆስ እናት ማርያም
ናት ። ከዙህም አንጻር ምናሌባት ያን ጊዛ የማርቆስ አባት ሞቶ ይሆናሌ ተብል ይገመታሌ፡፡

ማርቆስ በክርስቶስ ዗መን

ማርቆስ ከእነዙህ ቤተሰዎች በኢየሩሳላም ተወሌድ ያዯገ አይሁዲዊ ሰው በመሆኑ በጌታና


በሏዋርያት ኢየሩሳላም ውስጥ የተፈጸሙትን ዴርጊቶች ያውቃሌ፡፡ ይህንንም በሚከተለት
ሁለት ትውፊታውያን መረጃዎች እንመሇከታሇን፡፡

1. በመቅዴመ ወንጌሌ ትርጓሜ፣ በትርጓሜ ወንጌሌ መግቢያና በላልቹም የግእዜ መጻሔፍት


ቅደስ ማርቆስ ቁጥሩ ከሰባ አርዴእት መሆኑ ተመዜግቧሌ ሇወንጌለ የተሰጠው ርእስም
ይህንንው ያረጋግጣሌ፣ እርሱም፡- ‹‹ ብሥራተ ማርቆስ ረዴእ አሏደ እምሰብእ ወክሌኤቱ
አርዴእት» ይሊሌ፡፡

2. በማር.14፥51፡52 ሊይ የተገሇጠው ዕርቃኑን በነጠሊ የሸፈነ ጏበዜ፣ ጌታችን በጌቴ ሴማኒ


በተያ዗ ጊዛ እሱንም ጏበዚዜቱ ሉይዘት ሲለ ነጠሊውን ትቶ የሸሽው ጏበዜ ወጣት ማርቆስ
እንዯሆነ ብዘዎች የትርጓሜ ሉቃውንት ይስማማለ፡፡ ትርጓሜ ወንጌሌ ይህንን ሲገሌጥ፡-
«ወተሇዎ አሏደ ወሬዚ ዗ይትአጸፍ ሰንደነ ዕራቆ፣ ዕርቃኑን በበፍታ የሰወረ አንዴ ጎዜ
ተከተሇው:: ሏተታ ራሱን አርቆ ... » ትርጓሜ ወንጌሌ ማር.14፥51:፡ ን ተመሌከት/

ማርቆስ በሏዋርያት ዗መን

ቅደስ ማርቆስ በሏዋርያት ዗መን ስሊሇው ታሪኩ ከመጽሏፍ ቅደስ በግብረ ሏዋርያትና
በመሌእክታት ውስጥ ከላልቹ ይሌቅ በግሌጽ እናገኝሇታሇን፡፡

ሀ. በግብረ ሏዋርያት፣

1. ጳውልስና በርናባስ በሏዋ.11፥28 በተገሇጠው ረሀብ ምክንያት ሇተጏደት የኢየሩሳላም


ክርስቲያኖች ከአንጾኪያ ክርስቲያኖች የተሊከውን ርዲታ አዴርሰው አገሌግልታቸውን ከፈጸሙ

16
በኋሊ ሲመሇሱ ማርቆስን ከኢየሩሳላም ወዯ አንጾኪያ ይ዗ውት እንዯመጡ ተመዜግቧሌ።
/የሏዋ.1፥30፣12፥25/

2. በ1ኛው ሏዋርያዊ ጉዝአቸው የጳውልስና የበርናባስ አገሌጋይ ሆኖ እስከ ጰርጌን ዴረስ


አብሮአቸው ከተጓ዗ በኋሊ ከእነርሱ ተሇይቶ ወዯ ኢየሩሳላም እንዯተመሇሰ ተገሌጧሌ፡፡ / የሏዋ.
13፥5፡13/ ወዯ ኢየሩሳላም ስሇተመሇሰበት ምክንያት ሦሰት አስተሳሰቦች በሉቃውንት ይሰጣለ፡፡

 ሌጅ ስሇሆነ መከራውን ተሰቅቆ ተመሌሷሌ፣

 ሌጅ ስሇሆነ እናቱ ናፍቃው ተመሌሷሌ፣

 በጴርጌን ጳውልስ ታሞ ስሇነበር በሽታውን ፈርቶ ተመሌሶ ይሆናሌ፣ የሚለት ናቸው፡፡

3. ከኢየሩሳላም ጉባኤ በኋሊ ሏዋርያው ቅደስ ጳውልስና በርናባስ 2ኛውን ሏዋርያዊ ጉዝ


ሉጀምሩ ሲለ ማርቆስ እንዯገና በአንጻኪያ ነበር፡፡ በርናባስ በ2ኛው ጉዝአቸው« ማርቆስ »
አብሮአቸው እንዱሂዴ ፈሇገ ጳውልስ ግን ያሇፈው ስህተት እንዲይዯገም በማሰብ ማርቆስ
አብሯቸው እንዱጓዜ አሌፈቀዯም:: በዙህም ምክንያት በጳውልስና በባርናባስ መካከሌ መሇያየት
ተፈጠረ:: ስሇዙህ ማርቆስ በርናባስን ተከትል ወዯ ቆጵሮስ እንዯሄዯ እናነባሇን፡፡ /የሏዋ.15፥36-
39/

ሉ. በመሌእክታት

ከግብረ ሏዋርያት ቀጥል በመጽሏፍ ቅደስ ውስጥ ስሇቅደስ ማርቆስ የሚታወቀው


በመሌእክታት ውሰጥ የሚገኙ 4 ጥቅሶች ነው:: እነርሱም፡

1 ቇሊ.4፥10 « ... ከተገረዘት ወገነ ያለት አብሮ ከእኔ ጋር የታሠረ አርስጥርኮስ


የባርናባስ የወንዴሙ ሌጅ ማርቆስ ኢዮስጦስም የተባሇ ኢያሱ ሰሊምታ ያቀርቡሊችኋሌ
ስሇማርቆስ ወዯ እናንተ ቢመጣ ተቀበለት የሚሌ ትእዚዜ ተቀብሊችሁ፡፡
በእግዙአብሓር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት እነዙህ ብቻ ናቸው እኔንም
አጽናንተውኛሌ» ይሊሌ።

2. ፊሌሞ.2.4:፡ « በክርስቶስ ኢየሱስ ከእኔ ጋር የታሠረ ኤጳፍራ አብረውኝም የሚሠሩ


ማርቆስና አርስጥሮኮስ ዳማስም ለቃስም ሰሊምታ ያቀርቡሌሃሌ» ይሊሌ፡፡

17
አስተውሌ፡- ሏዋርያው ቅደስ ጳውልስ የቇሊስዩስ መሌእክትንና የፊሌሞናን መሌእክት የጻፈው
በሮም ሲሆን በመጀመሪያው የሮም እሥራቱ ጊዛ ነው፡፡ ስሇዙህ በዙያን ጊዛ ቅደስ
ማርቆስ በሮም ከጳውልስ ጋር አብሮ በመሥራት እና በመሌእክተኛነት ያገሇግሌ
እንዯነበር እናያሇን፡፡

ስሇሆነም ቀዯም ሲሌ የነበረው ሌዩነት ጊዛያዊ እንዯነበረና ወዱያውኑ እንዯጠፋ


እንገነ዗ባሇን፡፡

3. 2ጢሞ.4፥11 « ማርቆስ ሇአገሇግልት ብዘ ይጠቅመኛሌና ከኣንተ ጋር አምጣው»

• አስተውሌ 2ኛይቱ የጢሞቴዎስ መሌእክቱ ቅደስ ጳውልስ ሇ2ኛ ጊዛ በሮም ታስሮ ሳሇ በዙያን
ጊዛ በኤፌሶን ሇነበረው ሇዯቀ መዜሙሩ ሇጢሞቴዎስ የተጻፈች ስሇሆነች ማርቆስ በዙያን
ወቅት በኤፌሶን እንዯነበረ እንገነ዗ባሇን፡፡

3. 1ጴጥ.5፥13 « ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢልን ያሇች ቤተክርስቲያን ሌጄም ማርቆስ


ሰሊምታ ያቀርቡሊችኋሌ» ይሊሌ፡፡

• አስተውሌ በዙህ ጥቅስ «ባቢልን » የሚሊት « ሮምን» እንዯሆነ ብዘዎች


ሉቃውንት ይናገራለ፡፡ ስሇዙህ ቅደስ ማርቆስ በሮም ሳሊ ከቅደስ ጴጥሮስ ጋር እንዯነበር
በጥቅለ እንረዲሇን፡፡ በተሇይም « ሌጄ ማርቆስ» የሚሇው የጴጥሮስ አጠራር ማርቆስ ከጳውልስ
ጋር ብዘ የሠራ ቢሆንም ከጴጥሮስ ጋር ሳይሇይ አብሮ ይኖር የነበረ መሆኑን ያስገነዜባሌ።

ያስተማረበት አገር

ቅደስ ማርቆስ ስሊስተማረበት አገር የሚከተለትን ታሪካዊና ትውፊታዊ መረጃዎችን


እናገኛሇን፡፡

1. የቤተክርስቲያን ታሪክ ጸሏፊ አውሳብዬስ ዗ቂሣርያ ቅደስ ማርቆስ በሮም ወንጌለን ከጻፈ
በኋሊ ወዯ እስክንዴርያ ሓድ እንዯሰበከ እና የእስክንዴርያ የመጀመሪያ ጳጳስ እንዯሆነ ጽፏሌ።

2. ገዴለ ሏዋርያትንና ስንክሳር ዯግሞ ቅደስ ማርቆስ ከበርናባስ ዕረፍት በኋሊ ወዯሮም
ወዯ ጴጥሮስ እንዯሓዯና በሮም ወንጌለን ከጻፈ በኋሊ ወዯ እስክንዴርያ ሓድ እንያኖስ
ከተባሇ ጫማ ሰፊ / ፊሏቂ/ እና ከቤተሰቡ ጀምሮ ሇብዘ ሔዜብ ወንጌሌን እንዯሰበከ

18
እና ከእስክንዴርያም ውጭ በዙያው አካባቢ ባለ አምስት የአፍሪቃ ሀገሮች እየተ዗ዋወረ ሇ2
ዓመታት ያህሌ እንዲስተማረ መዜግበዋሌ፡፡ /ገዴሇሏዋ.ስንክሳር ሚያዜያ 30/

ዕረፍቱ

ወንጌሊዊው ማርቆስ ከ5ቱ አገሮች ተመሌሶ ወዯ እስክንዴርያ ከመጣ በኋሊ ፋሲካን


/ትንሣኤ/ ሲያከብር ሳሇ፣ በዙያው ዕሇት « ሰራጵዮስ» የተባሇውን የጣዖታቸውን በዓሌ ያከብሩ
በነበሩት በግብጽ አረማውያን ተያ዗፡፡ በበሬም እየተጏተተ ከተሰቃየ በኋሊ በማግስቱ ሚያዜያ 30
ቀን በሰማዕትነት ዏረፈ፡፡ አረማውያኑ በዴኑን ሉያቃጥለት ሲለ በዕሇቱ መብረቅና ነፋስ ያሇበት
በረድ የተሊቀሇበት ኃይሇኛ ዜናብ ስሇ዗ነበ ባሇመቻሊቸው ክርስቲያኖች ወስዯው ሰቤ.ክ. ቀበሩት፡፡
ይህን ታሪክ ገዴሇ ሏዋርያትና ስንክሳር እንዱሁም የጥንት ቤተክታሪክ ያስረዲለ፡፡ ይህም
የሆነው በ67 ዓ.ም ነው::

 ምሳላው፡- የማርቆስ ምሳላው ‹‹ ገጸ አንበሳ» ነው:: ማርቆስ በገጸ አንበሳ የተመሰሇበት


ምክንያት፡

1. አንበሳ ኑሮው በበረሃ ነው፡፡ በዙያ ሆኖ ሲጮህ ዴምጹ በሩቅ ይሰማሌ፡፡ ማርቆስም
ወንጌለን ሲጻፍ « በበረሃ የሚጮህ ሰው ዴምጽ» የተባሲ የመጥምቁ የዮሏንስ
ሥራና ትምህርት በማስቀዯም ስሇሚጀምር ነው:: /ማር.1፥1-18/

2. አንበሳ ሇሊህም ጌታው ነው ይሰብረዋሌ፡፡ ማርቆስም አምሌኮተ ሊህምን ከምዴረ


ግብጽ ስሊጠፋ ነው፡፡ /የትርጓሜ ወንጌሌ መግቢያ/

የተጻፈበት ቦታ፣ ቋንቋና ዗መን

የማርቆስ ወንጌሌ የተጻፈበት ቦታ ሮም ሲሆን የተጻፈበትም ቋንቋ ሮማይስጥ /ሊቲን ነው፡፡


዗መኑም በኛ ትውፊት እንዯተገሇጠው ጌታ ባረገ 11ኛው ዓመት ተፈጽሞ 12ኛው ዓመት
ሲጀመር ቀሊውዳዎስ ቄሣር በነገሠ ባራተኛው ዓመት ነው:: ይህም በዓመተ ምሔረት ሲታሰብ፡

ከጌታ ዕርገት ሰፊት - 33 ዓመት ከጌታ ዕርገት በኋሊ 11 ዓመት ስሇዙህ በ44 ዓ.ም ተጽፏሌ
ማሇት ነው:: የማርቆስ ወንጌሌ ስተጻፈበት ቦታ፣ ቋንቋና ዗መን ከዙህ ሊይ የተገሇጠውን
የሚያስረደ ታሪካዊና ትውፊታዊ መረጃዎችን ቀጥል እናቀርባን፡፡

19
1. ከቤተክርስቲያን አባቶች መካከሌ ጏርጏርዮስ ዗እንዙናዘ የማርቆስ ወንጌሌ የተጻፈበት
ቦታ ጣሉያን እንዯሆነ ሲገሌጥ አውሳብዮስ ዗ቂሣርያ ዯግሞ የተጻበት ቋንቋ የጣሌያን
/የሊቲን ቋንቋ እንዯሆነ በጽሐፎቻቸው አስረዴተዋሌ፡፡

2. የትርጓሜ ወንጌሌ መግቢያ/ ታሪክ የማርቆስ ወንጌሌ ስሇተጻፈበት አገር ሲናገር « . .


ማርቆስ በግብጽ በሮምም ይሊሌ» ብል ይገሌጣለ፡፡ ስሇተጻፈበት ቋንቋ / ሌሳን (ዯግሞ
ማርቆስ በሮማይስጥ . . . » ሲሌ በሮማይስጥ እንዯሆነ ይናገራሌ፡፡ ስሇመዋዕሇ
ጽሔፈቱ/ ስሇተጻፈበት ዗መን ዯግሞ « ማርቆስ ጌታ ካረገ አሥራ አንዴ ቢለ ሲፈጸም
አሥራ ሁሇት ቢለ ሲጀመር ቀሊውዳዎስ ቄሣር በነገሠ በአራተኛው አመት» ይሊሌ፡፡

3. የማርቆስ ወንጌሌ የትርጓሜው መዯምዯሚያ መርገፍ ዯግሞ ወንጌለ ስሇተጻፈበት ቦታ፣


ቋንቋና ዗መን ሲናገር እንዱህ ይሊሌ፡- « መሌዓ ጽሔፈተ ብሥራቱ ሇማርቆስ ሏዋርያ
አሏደ እም ሰብአ ወክሌኤቱ አርዴአት ወኮነ ዗ጸሏፎ በሀገረ ሮሜ በሌሳነሮም ዗አፍርንጊ
እምዴኅረ ዕርገቱ ሇእግዙእነ ሰዏሠርቱ ወአሏደ ዓመት ወበራብዕት ዓመት ምንግሥቱ
ሇቀሊውዳዎስ ቄሣር» ይሊሌ። ይህም መረጃ የማርቆስ ወንጌሌ የተጻፈሰት አገር « ሀገረ
ሮሜ» ቋንቋው « ሌሳ ነሮም» ዗መኑም ከጌታ ዕርገት በኋሊ በ11ኛው ዓመት እንዯሆነ
ይገሌጻሌ፡፡

4. ዗መናውያን የሏዱስ ኪዲን ሉቃውንት ዯግሞ የማርቆስ ወንጌሌ ከላልቹ ወንጌሊት


ቀዯም ብል በ60 ዓ.ም ገዯማ እንዯተጻፈ ይናገራለ፡፡

የተጻፈሊቸው ሰዎች

ማርቆስ በሮም ውስጥ ሆኖ ወንጌለን የጻፈሊቸው ሇራሳቸው ሇሮማዉያን ነው። ሇሮማውያን


እንዯጻፈ የሚያሳዩ መረጃዎች በወንጌለ ውስጥ ይገኛለ። እነርሱም:-

1. አንዲንዴ የሊቲን ቃሊት በውስጡ ይገኛለ/5፥9፣15፥16/ በጽሐፉ ውስጥ ያስገባቸውንም


አንዲንዴ የአራማይክ ቃሊት ይተረጉምሊቸዋሌ፡፡ 13፥17፣7፥12፣ 7፥34

2. ጌታን ሉሰቅለት በወሰደት ጊዛ በመንገዴ ሊይ አግኝተውት መስቀለን እንዱሸከም


ያስገዯደት ስምዖን ቀሬናዊ የአላክሳንዴሮስና የሩፎስ አባት መሆኑን ይገሌጣሌ፡፡
/15፥21/ ከእነዙህ የስምዖን ቀሬናዊ ሌጆች አንደ ሩፎስ ሩፎን/ የተባሇው በሮሜ እንዯ

20
ነበር ጳውልስ በሮሜ መሌእክቱ ውስጥ ባቀረበሇት ሰሊምታ ይታወቃሌ፡፡ /ሮሜ.16፥13/
ስሇዙህ ማርቆስ« የአላክሳንዴሮስና የሩፎስ አባት ስምዖን የተባሇ የቀሬና ሰው »
አንባቢዎች እንዯሚያውቋቸው አዴርጉ ሲጽፍ የጻፈው ሇሮማዉያን መሆኑን
እንገነ዗ባሇን፡፡

የተጻፈበት ዓሊማ

የማርቆስ ወንጌለን ስናጠና ሌንረዲ እንዯምንችሇው ወንጌለ የሚከተለት ሁሇት ዓሊማዎች


አለት፡-

1. ኢየሱስ እርሱ « የሰው ሌጅ»፣ « ክርስቶስ» ብቻ ሳይሆን /8፥27-31 « የእግዙአብሓር


ሌጅ» ፣«ጌታ » መኾኑን ሇሮማውያን ሇማስረዲት ነው፡፡ ይህም ወንጌለን መጻፍ
ሲጀምር « የእግዙአብሓር ሌጅ» የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌሌ መጀመሪያ ብል በሰጠው
ርእስ ይታወቃሌ፡፡ /1፥1/ በላልችም ክፍልች የእግዙአብሓር ሌጅነቱንና ጌትነቱን
በተዯጋጋሚ ይገሌጣሌ፡፡ 1፥11፣3፥11፣9፥7፣ 12፥35 37፣ 15፥39፣ 16፥19

2. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማስተማር ዗መኑ ካስተማረው ትምህርት ይሌቅ


ያዯረጋቸውን ታምራት እያብራራ በመግሇጥ የጌታን የኃይሌ ሥራውን ማሳወቅ ነው
/1፥21-28፣2፥1-12፣3፥7፣5፥1-2ዏ፣7፥21 37፣ 10፥46-52/ ካረገ በኋሊም ጌታ
ከዯቀመዚሙረቱ ጋር በምሌክትና በዴንቅ /በታምራት/ አብሮ ይሠራ እንዯነበር በዙህ
ወንጌሌ ተመዜርቧሌ /16፥20

የወንጌለ ጥናት

የማርቆስ ወንጌሌ በይዝታውና በአከፋፈለ ይጠናሌ፡፡ በወንጌለ ያለት ምዕራፎች 16 ሲሆኑ


ቁጥሮቹ ዯግሞ 678 ናቸው:: ከ4ቱም ወንጌሊት አጭሩ ይህ ወንጌሌ ነው::

ይዝታው

የማርቆስ ወንጌሌ ይዝታው በማስተማር ዗መኑ ብቻ የተፈጸሙ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ፣
ትምህርትና ታምራት ነው፡፡ በዙህ አቀራረቡም ከላልቹ ወንጌሊት ይሇያሌ። የማቴዎስና የለቃስ
ወንጌሊት የጌታን ነገር ሲጽፉ ከሔፃንነት ታሪኩ ይጀምራለ የዮሏንስ ወንጌሌ ዯግሞ

21
ከቀዲማዊነቱ ጀምሮ ይጽፋሌ፡፡ የማርቆስ ወንጌሌ ግን የሚጀምረው ከመጥምቁ ዮሏንስ ሥራ
እና ከጌታ ጥምቀት ነው:: ከዙያም አያይዝ እስከ ዕርገቱ ዴረስ ያሇውን የጌታ የኢየሱስ
ክርስቶስን ነገር ይዞሌ።

1. የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክ

በማርቆስ ወንጌሌ የሚገኙት የጌታ ታሪኮች ብዘዎች ሰማቴዎስና በለቃስ ወንጌሳት ትይዩ ክፍሌ
አሊቸው:: ነገር ግን ከእነዙሁ ታሪኮች ውስጥ በማርቆስ ወንጌሌ ብቻ በተሇይ የተገሇጡትን
ቀጥል እንመሇከታሇን፡፡

1. በምዴረ በዲ 40 ቀን በሰይጣን ሲፈተን ከአራዊት ጋር እንዯነበር ተሌጧሌ /1፥12፡13/


2. ታምራት ማዴረግ ከጀመረ በኋሊ ወዯምዴረ በዲ ሉጸሌይ ሄድ ሊሊ ሔዜቡ ምን ያህሌ
ይፈሌጉት እንዯነበር ተገሌጧሌ /1፥3539/
3. ቀራጩ ላዊ የእሌፍዮስ ሌጅ መሆኑ ተገሌጧሌ /2፥14
4. አሥራ ሁሇቱን ጠርቶ ሁሇት ሁሇቱን እንዯሊከቸውና እነርሱም ብዘ ዴውዮችን ዗ይት
ቀብተው እንዯፈወሱ ተገሌጧሌ/6፥7፡13/
5. በመጥምቁ ዮሏንስ አሟሟት ታሪክ ውስጥ የተብራሩ ነገሮች አለ፡፡ / 6፥19-29/
6. በረጅም ተራራ ሊይ ክብሩን ሲገሌጥ የነበረው የሌብሱን ንጣት በተሇየ ሁኔታ ተገሌጧሌ
/9፥3/
7. የ዗ብዳዎስ ሌጆች በግራውና በቀኙ መቀመጥን የጠየቁት ራሳቸው እንዯሆኑ ተገሌጧሌ
/ 1፥35-37/
8. የሆሳዕና መዜሙር በተሇየ አንገሊሇጥ ቀርቧሌ /11፥9:10/
9. ጌታ በተያ዗ ጊዛ ነጠሊውን ትቶ ራቁቱን ስሇሸሽው ጏበዜ ተመዜግቧሌ /14፥51:52/
10. በጌታ ሊይ ሉመሰክሩበት የቀረቡት የሏሰት ምሥክሮች ምስክርነታቸው አሇመስማማት
ተገሌጧሌ 14፥56-59
11. ጴጥሮስ 3 ጊዛ ጌታን የካዯው ድሮ 2 ጊዛ ሳይጮህ መሆኑ ተገሌጧሌ /14፥30:66-72/
12. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተፈረዯበት በኋሊ የተሰባሰቡበት ቦታ «ፕራይቶሪዮን»
እንዯሚባሌ ተገሌጦሌ፡፡ /15፥16-20/
13. ሰምዖን ቀሬናዊ የአላክሳንዴሮስና የሩፎን አባት መሆኑ ተገሌጧሌ /15፥21/

22
14. ኢየሱስ ከተነሳ በኋሊ ቅደሱን ወንጌሌ ከፀሏይ መውጫ እስከ መግቢያው ዴረስ
በእጃቸው እንዲዯሊከ ተመዜግቧሌ /16፥8/
15. የጌታ የመጨረሻዎቹ ቃሊት የተሇዩ ናቸው /16፥14-18/
16. ወዯ ሰማይ ዏርጏ በእግዙአብሓር ቀኝ መቀመጡና ከዙያ በኋሊ ዯቀ መዚሙርት
በየሥፍራው ሲሰብኩ አብሯቸው ይሠራ እንዯነበር ተገሌጧሌ /16፥19፥20/

3. ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማራቸው ትምህርቶች


ማርቆስ የጌታን ትምህርቶች የማቴዎስንና የለቃስን ያህሌ አሌመ዗ገበም፡፡ የመ዗ገባቸውም
ብዘዎች በማቴዎስና በለቃስ ወንጌሊት ትይዩ ክፍሌ ያሊቸውና ተመሳሳይ ትምህርቶች ናቸው
ጥቂቶቹ ግን በተሇየ አገሊሇጥ የቀረቡ አለ፡፡ እነዙህን ሌዩ አገሊሇጥ ያሊቸውን ትምህርቶች ብቻ
እንዯሚከተሇው እናቀርባሇን፡፡
ሀ. በቀጥታ ራሱ ካስተማራቸው ትምህርቶች
1. በማቴዎስና በለቃስ ወንጌሊት ከተመ዗ገቡት የምሳላ ትምህርቶች ውስጥ የማይገኝ
እንዴ ምሳላ በዙህ ወንጌሌ ተመዜግቧሌ /4፥26-29/
ሇ. ከሚቀርቡሇት ጥያቄዎች በመነሳት ካስተማራቸው ትምህርቶች
1. ፈሪሳውያንና ጻፎች የጌታ ዯቀ መዚሙርት እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ሲበለ
አይተው ባቀረቡት ጥያቄ ተነስቶ የሰጠው ትምህርት በማቴዎስ ወንጌሌ ከተመ዗ገበው
ይሌቅ በዙህ ወንጌሌ ተብራርቶ ተገሌጧሌ /7፥ 3-23/
2. ዮሏንስ በሰው አጋንንትን ሲያወጣ ያዩትን ሰው እንዯከሇከለት ሇጌታ በነገረው ጊዛ
ያስተማረው ትምህርት በለቃስ ወንጌሌ ከተገሇጠው ይሌቅ በዙህ ወንጌሌ በሰፊው
ተብራርቶ ተገሌጧሌ /9፥38-50/
3. ከጻፎች አንደ ፊተኛይቱ ትእዚዜ የትኛይቱ እንዯሆነች ጠይቆት ያስተማረው
ትምህርት በማቴዎስ ወንጌሌ ከተመ዗ገበው ጋር ሲተያይ በዙህ ወንጌሌ ውስጥ በተሇየ
አገሊሇጥ ቀርቧሌ /12፥28-34/

3. ኢየሱስ ክርስቶስ ያዯረጋቸው ታምራት

የማርቆስ ወንጌሌ አብዚኛው ክፍሌ የተያ዗ው ጌታ ያዯረጋቸውን ታምራት በመግሇጥ ነው፡፡


ማርቆስ በአጻጻፉ ከጌታ ታሪክና ትምህርት ይሌቅ ባዯረጋቸው ታምራት ሊይ ያተኩራሌ።
የመ዗ገባቸው ታምራት /ምሌክቶች/ አብዚኞች በማቴዎስና በለቃስ ወንጌሊት ውስጥም የተመ዗ገቡ

23
ናቸው ነገር ግን ከማቴዎስና ከለቃስ አመ዗ጋገብ ይሌቅ በዙህ በማርቆስ ወንጌሌ ውስጥ በሰፊው
ተብራርቶዋሌ፣ በዙህ ወንጌሌ ብቻ የሚገኙም አለ፡፡

በማርቆስ ወንጌሌ ውስጥ ጌታ ብዘ ታምራትን አዯረጉ እንዯነበር በየሥፍራው ተገሌጧሌ 1፥32-


34፣3፥9-11፣6፥53-56/ ሙለ ታሪካቸው የተመ዗ገበሊቸው ግን አሥራ ዗ጠኝ ናቸው:: የወንጌለ
ዋና ይዝታም የጌታን ታምራት በመግሇጥ ሊይ ያተኮረ ስሇሆነ እነዙህን አሥራ ዗ጠኝ ታምራት
እዙህ ሊይ እናጠናሇን፡፡

1. በቅፍርናሆም ምኩራብ ሲያስተምር የጮኸውን ርኩስ መንፈስ በቃለ አወጣ /1፥21-28/

2. በስምዖን በእንዴርያስ ቤት ገብቶ የስምዖን አማት እጂን ይዝ ከንዲዴ ፈወሳት 1፥29-31/

3. ሇምጻሙን ሰው አጁን ዗ርግቶ ሰመዲሰስ ከሇምጹ አነጻው /1፥40-44/

4. ሰቅፍርናሆም በቤት ሆኖ ሇብዘ ሔዜብ ቃለን በመናገር ሊይ ሳሇ አራት ሰዎች


ተሸክመው ያመጡትንና የቤቱን ጣራ ነዴሇው ያወረደትን ሽባ በቃለ ፈወሰው /2፥1-12/

5. በሰንበት ቀን ወዯ ምኩራብ ገብቶ በዙያ የነበረውን እጁ የሰሇሇችውን ሰው በቃለ አዲነው


/3፥1-5

6. በምሽት በታንኳ ሲሄደ የተነሣውን ማዕበሌ ነፋሱን ገሥጾ አቆመው /4፥35-41/

7. በጌርጌሴኖን ሇጌዎን የነበሩበትን ሰው አዲነው /5፥1-20/

8. ከ12 ዓመት ጀምሮ ዯም ይፈሳት የነበረች ሴት ሌብሱን ዲሰሳ ከርሱ በወጣ ኃይሌ
ተፈወሰች /5፥25-34/

9. የምኩራብን አሇቃ የኢያኢሮስን ሌጅ እቤቱ ዴረስ ሄድ ከሞት አስነሳሇት /5፥21-24፡34-


43/

10. በምዴረ በዲ በምሽት 5 እንጀራና 2 ዓሣ አበረክቶ ከ5ሺህ ሔዜብ ሰሊይ መግቦ የተረፈው
12 ቅርጫት ተነሣ /6 ፥34-44

24
11. ዯቀ መዚሙርቱ ወዯ ቤተሳይዲ በታንኳ ሲሄደ ያስጨነቃቸውን ነፋስ በባሔር ሊይ
እየሄዯ መጥቶ አቆመው:: /6፥43-52/

12. በጢሮስና በሲድና ጋኔን ያዯረበትን ያንዱት ሲሮፊንቄያዊት ሌጅ አዲነ / 7፥24-30/

13. ሰገሉሊ ባሔር ኣካባቢ ዯንቆሮና ኮሌታፋ የነበረውን ሰው « ኤፍታህ» ብል ፈወሰው


/7፥31-35

14. በምዴረ በዲ 7 እንጀራና ጥቂት ዓሣ አበርክቶ ከ4 ሺህ ሔዜብ በሊይ ከመገበ በኋሊ


የተረፈው 7 ቅርጫት ተነሣ /8፥1-9

15. በቤተሳይዲ ወዯ እርሱ ያመጡሇትን አንዴ ዕውር በዓይኑ ሊይ ተፍቶበት ፣እጁንም


ጭኖበት ዓይኑን አበራሇት /8፥22-26/

16. ዯቀ መዚሙርቱ ሉያወጡት ያሌቻለትን ዱዲ፣ ዯንቆሮም መንፈስ በትእዚዜ


አወጣው/9፥17-25/

17. በኢያርኮ የዕውሩ የበርጤሜዎስን ዓይን አበራሇት 10፥46-52/

18. ከቅጠሌ በቀር ፍሬ ያሊገኘበትን በሇስ ሲረግማት ዯረቀች /11፡12-14፣ 20:21/

19. በመስቀሌ ሲሰቀሌ ከ6-9 ሰዓት በምዴር ሁለ ሊይ ጨሇማ ሆነ፣ የቤተ መቅዯሱ መጋረጃ
ከሊይ እስከታች ከሁሇት ተቀዯዯ /15፥33:38/

አስተውለ፡- ከሊይ ከተ዗ረ዗ሩት የጌታ ታምራት ውስጥ በማርቆስ ወንጌሌ ብቻ የሚገኙት


ታምራት ሁሇት ታምራት ናቸው እነርሱም በተራ ቁጥር13 እና በተራ ቁጥር 15
የተገሇጡት ታምራት ናቸው::

አከፋፈለ

16ቱን የማርቆስ ወንጌሌ ምዕራፋት በ6 ዏበይት ክፍልች እንከፍሊቸዋሇን፡፡

1. ጸሏፊው ሇወንጌለ የሰጠው ርእስ /1፥1/

2. ጌታ ወንጌሌን ማስተማር ከመጀመሩ በፊት ጥቂት ቀዯም ብል ያዯረጋቸው ነገሮች /1፥1-13/

25
 የመጥምቁ ዮሏንስ ሥራዎች /1፥2-8/

 ኢየሱስ ከገሉሊና ናዜሬት ወዯ ዮርዲኖስ ወንዜ መጥቶ በክ ብ ቁ /1፥9-11/

 በምዴረ በዲ ከሰይጣን እየተፈተነ 40 ቀን እንዯሰነበተ /1.12፡13/

3. ጌታ በገሉሊና በአካባቢዋ የሰራው ሥራና ያስተማረው ትምህርት /1፥14-9፥50/

 ዮሏንስ አሌፎ ከተሰጠ በኋሊ ንስሏን እየሰበከ ትምህርቱን መጀመሩ /1፥14:15/

 በገሉሊ ባሔር አጠገብ ሲያሌፍ 4ቱን ዯቀ መዚሙርት እንዯጠራ /1፥16-20/

 በቅፍርናሆምና በአካባቢው አያስተማረ ያዯረጋቸው ታምራትና የሠራቸው ላልች


ሥራዎች /1፥21-3፥35፡፡/

 በባሔር ዲር በታንኳ ተቀምጦ በምሳላዎች ያስተማረው ትምህርት /4፥1-34/

 በገዚ አገሩና በመንዯሮቹ እያስተማረ ሲዝር ሏዋርያትን ሥሌጣን አቶ ሉሰብኩ


እንዯሊካቸው /6፥1-31/

 በምዴረ በዲ፣ በገሉሊ ባሔር፣ በጌንሳሬጥ፣ በጢሮስና በሲድና በቤተሳይዲ እያስተማረ


ያዯረጋቸው ታምራት /6፥32-8፥26 /

 ከፊሌጶስ ቄሣርያ ወዯ ቅፍርናሆም እየመጣ ያዯረገውና ያስተማረው /8፥27-9፥50/

4. ጌታ ወዯ ይሁዲ አገር መጥቶ ያዯረገውና ያስተማረው /10፥1-14፡42/

 ወዯ ኢየሩሳላም መውጣት ሳይጀምር በላሊው የይሁዲ ክፍሌ ያዯረገውና ያስተማረው


ነገር /10፥1-31/

 ወዯ ኢየሩሳላም በመውጣት ሊይ ሳሇ የተዯረጉ ነገሮች /10፥32-52/

 በቢታንያ በኩሌ ወዯ ኢየሩሳላም ሲገባ ሔዜቡ ሆሳዕና ብል እንዯተቀበሇው /11፥1-10/

 ወዯ ኢየሩሳላም ከገባ ጀምሮ እስከተያ዗ ዴረስ ያዯረገውና ያስተማረው /11፥11-14፥42/

26
5. የጌታ የስቅሇቱ ታሪክ /14፥43-15፥47/

 በይሁዲ መሪነት በመጡ ሰዎች እንዯተያ዗ /14፥43-52/

 በሉቀ ካህናቱ ግቢ በአይሁዴ ሸንጏ ፊት በሏሰት እንዯተመሰከረበት /14፡53-72/

 በጲሊጦስ ፊት እንዯተመረመረና እንዯተፈረዯበት /15፥1-15/

 በመስቀሌ ተሰቅል እንዯሞተ /15፥16-41/

 የአርማትያሱ ዮሴፍ ከመስቀሌ አውርድ እንዯቀበረው /15፥42-47/

6. የጌታ የትነሣኤወና የዕርገቱ ታሪክ /16፥1-20/

የተነሳ ዕሇት ሇተከታዮቹ በየሥፍራው እንዯተገሇጠ /16፥1-14/ ጌታ ሇዯቀመዚሙርቱ


የተናገራቸው የመጨረሻዎቹ ቃሊት /16፥15-18/

የጌታ ዕርገቱ /16፥19:20/

የለቃስ ወንጌሌ

ጸሏፊው

የሦስተኛው ወንጌሌ ጸሏፊ ቅደስ ለቃስ ነው፡፡ ይህንንም ኤሬኒያስ የተባሇው የቤተ ክርስቲያን
አባት አስታውቋሌ፡፡ ከዙህም ላሊ በጥንታዉያን ጽሐፎች ሁለ የዙህ ወንጌሌ ጸሏፊ ለቃስ
መሆኑ ተረጋግጧሌ፡፡ በግእዘ ሏኪ. ሇዙህ ወንጌሌ የተሰጠው ርእስም ይህን ሲገሌጥ፡
«ብሥራተ ለቃስ ወንጌሊዊ አሏደ እምሰብአ ወክሌኤቱ አርዴእት ማሇት ከሰባ ሁሇቱ አንደ
የሆነው የወነወጌሊዊው ለቃስ ብሥራት ይሊሌ

ስሙ

ለቃስ የሚሇው ስም« ሉካኖስ» ከሚሇው የሊቲን ቃሌ የተገኘ ስም ነው ትርጉሙም መብራት


ማሇት ነው:: በትርጓሜ ወንጌሌ ሊይ ለቃስ ሇሚሇው ስም ዏቃቤ ሥራይ፣ ትንሣኤ፣መበስር
የሚለ ምሥጢራዊ ትርጉሞች ተሰጥተውታሌ። በሏዋ. ሥራ 13፥1 ሊይ « ለክዮስ» እና
በሮሜ /16፥21/ « ለቂዮስ» የተባለት ስሞች ለቃስ ከሚሇው ስም ጋር ባጠራርም ሆነ

27
በትርጉም ይመሳሰሊለ፡፡ ለቃስ ከሏዱስ ኪዲን መጻሔፍት ሁሇት ተከታታይ መጻሔፍት ያለት
ወንጌሊዊ ነው፡፡ እነርሱም ይህ 3ኛው ወንጌሌና የሏዋርያት ሥራ ናቸው::

ሀገሩ

ለቃስ በሶርያ ውስጥ የምትገኘው የአንጾኪያ ሰው እንዯሆነ ብዘ ጥንታዉያን የእጅ ጽሐፎች


ያስረዲለ ሇምሳላ የሙራቶሪዮን ቀኖና / Muratorion Canon / እና ፀረ ማርሲዮናውያን መቅዴም
/Antimarcionate Erologue/ የተባለት ጥንታዉያን የእጅ ጽሐፎች ለቃስ ሀገሩ አንጾኪያ
እንዯሆነች ይገሌጣለ፡፡ በገዴሇ ሏዋርያት የተመ዗ገበው ታሪክ ግን « ወለቃስ እምሀገረ
ዴሌማጥያ» በማሇት ሀገሩ « ዴሌማጥያ» እንዯነበረ ይናገራሌ፡፡ ያም ሆነ ይህ ለቃስ አይሁዲዊ
ሳይሆን ከአሔዚብ መገን የነበረ ሰው መሆኑን እንገን዗ባሇን፡፡

ሙያው

ለቃስ ሁሇት ዓይነት ሙያ እንዯነበረው ታውቋሌ፡፡ እነርሱም፡-

1. ባሇመዴኃኒት |ሏኪም/ ነበር ይህም ሙያው በመጽሏፍ ቅደስ ተመስክሮሇታሌ


ሏዋርያው ቅደስ ጳውልስ « የተወዯዯው ባሇ መዴኃኒት ለቃስ» በማሇት ጠርቶታሌ
ቇሊ.4፥14

2. ሠዓሉ ነበር፡- በብዘ አገሮች የሚነገሩ ትውፊቶች የለቃስን ሠዓሉነት ያረጋገጣለ


እንዱያውም የጌታችን እናት የዴንግሌ ማርያምን ሥዕሌ እንዯሣሇ ይታመናሌ በመሌክአ
ሥዕሌ ሊይም ይህን የሚገሌጽ ቃሌ ይገኛሌ፡፡ ይኸውም « ሰሊም ሇሥዕሌኪ እንተ ሠዓሊ
በእደ ለቃስ ጠቢብ እም ወንጌሊዉያን አሏደ» የሚሌ ነው፡፡

ስሇዙህ ለቃስ በ዗መኑ የነበረውን ጥበብ /ዕውቀት፣ የተማረ ሰው ነበር፡፡ ስሇዙህ ብዘ ጽሏፍት
ለቃስን « ጠቢብ» የሚሌ ቅጽሌ እየሰጡ ይጠሩታሌ፡፡ የተማረበትም ቦታ ሇአንጾኪያ ቅርብ
በነበረች ጠርሴስ በተባሇችው የኪሌቅያ ዋና ከተማ፣ የቅደስ ጳውልስ የትውሌዴ አገር እንዯሆነ
ይነገራሌ፡፡ እንዱያውም ከቅደስ ጳውልስ ውቅ ያዯረጉት ጳውልስ ገና እንዲመነ ከኢየሩሳላም
ተሰድ ወዯ ሀገሩ ወዯ ጠርሴ መጥቶ ሇረጅም ጊዛ በተቀመጠበት ወቅትና ለቃስ ዯግሞ
ሇትምህርት መጥቶ በነበረበት ጊዛ ነው የሚለ አለ፡፡
28
ለቃስ በመጽሏፍ ቅደስ

መጽሏፍ ቅደስ ስሇ ለቃስ ሇይቶ የሚነግረን ሰፊ ታሪክ ባይኖርም የሚታወቀው


ያህሌ መመሌከቱ አሰፈሊጊ ነው፡፡ ከመጽሏፍ ቅደስ ከተሇያዩ ቦታ የተሇቀሙትች ስሇ ለቃስ
የማናገሩ ክፍልች አንዲንድች በሉቃውንት ትርጉም እና በትውፊት መጻሔፍት
እገዚ የምንመሇከታቸው ነው::

በለቃስ ወንገሊ ሰለቃ

ለቃ.24 ፥ 13-35 ሊይ ክርስቶስ ከሞት የተነሣ ዕሇት ወዯ ኤማሁስ ይጓዘ የነበሩ የሁሇት ዯቀ
መዚሙርት ታሪክ ተመዜግቧሌ፡፡ የአንዯኛው ስሙ ቀሇዮጳ እንዯሆነ ሲነገር የላሊው ዯቀ
መዜሙር ስም ግን አሌተገሇጠም፡፡ ይህ ስሙ ያሌተገሇጠው ዯቀመዜሙር ለቃስ እንዯሆነ ብዘ
ትውፊቶች ይናገራለ፡፡ ትርጓሜ ወንጌሌ ይህን ክፍሌ ሲተረጉም ሁሇት ያሊቸው ለቃስና ቀሇዮጳ
ናቸው:: ለቃስንስ ዗ውእቱ ቀሇዮጳ ይሇዋሌ ብል ለቃስና ኒቆዱሞስ ናቸው ይሊሌ። በዙህ
ሏተታ በሁሇተኛው አነጋገር ቀሇዮጳ ራሱ ለቃስ እንዯሆነና ስሙ ያሌሌተገሇጠው ዯቀመዜሙር
ግን ኒቆዱሞስ እንዯሆነ ተገሌጿሌ። ነገር ግን ቀሇዮጳ / Cleopas/ ራሱን የቻሇ ላሊ ዯቀ
መዜሙር መሆኑ ስሇሚታወቅ ከሁሇቱ መንገዯኞች መካከሌ ለቃስ ስሙ ያሌተሇገሇጠው ዯቀ
መዜሙር / Un named disipile/ ነው የሚሇው ሏሳብ የበሇጠ ተቀባይነት አሇው።

እነዙህ ሁሇት ዯቀ መዚሙርት በለቃ.10፥1 ሊይ ከተገሇጡት ከሰባ አርዴእት እንዯሚቆጠሩ ብዘ


ትውፊቶች፣ ትርጉሞችና፣ መዜገበ ቃሊቶች ይገሌጣለ፡፡

ስሇዙህ ለቃስም ከሰባ አርዴእት ይቆጠራሌ፡፡ መጽሏፈ ስንክሳር ይህንን ሲገሌጽ « ... ወበዚቲ
ዕሇት ኮነ ቅደስ ለቃስ ጠቢብ ወሰማዕት፡፡ ወዜንቱ ቅደስ ኮነ እምኁሌቆሙ ሇሰብአ አርዴእት
዗዗ከሮሙ ወንጌሌ ቅደስ» ይሊሌ / ጥቅምት 22 ተመሌከት/ መቅዴመ ወንጌሌ፣ የትርጓሜ
ወንጌሌ የታሪክ ዓምዴ ሇለቃስ ወንጌሌ የተሰጠው ርእስ እና መዯምዯሚያ ሁለ ይህንን
አረጋገጠው ይናገራለ፡፡

29
በሏዋርያት

« የሏዋርያት ሥራ» ለቃስ የጻፈው ሁሇተኛው መጽሏፍ መሆኑ የታወቀ ነው በዙህ መጽሏፍ
ውስጥ ቅ.ለቃስ የቅ. ጳውልስን ሏዋርያዊ ሥራ ሲጽፍ ራሱንም በታሪክ ውሰጥ በመጨመር
በአጃቢነት የሚጽፉአቸው ሦስት ክፍልች / The three we Sections/ አለ፡፡ እነዙህ ሦስቱ «
የእኛ» አገሊሇጥ ክፍሊትም የሚከተለት ናቸው::

1. የሏዋ.16፥10-17 በዙህ ክፍሌ ቅደስ ጳውልስ ሁሇተኛው ሏዋርያዊ ጉዝውን በማዴረግ


ሊይ ሳሇ ለቃስ ከጢሮአዲ እስከ ፊሌጵስዬስ ዴረስ አብሮ እንዯነበር እንረዲሇን፡፡

2. የሏዋ. 20፥5-21፥18፡ በዙህ ክፍሌ ዯግሞ ቅ.ጳውልስ 3ኛውን ሏዋርያዊ ጉዝውን


አጠቃል ከግሪክ ወዯ ኢየሩሳላም ሲሄዴ ለቃስ ኣብሮት እንዯነበር እንረዲሇን፡፡

3. የሏዋ.27፥1-28፥16:- በዙህ ክፍሌ ቅደስ ጳውልስ በቂሳሪያ ሇሁሇት ዓመት ያህሌ ታስሮ
ሳሇ እና ይግባኝ ጠይቆ ወዯሮም በተወሰዯ ጊዛ ሁለ ለቃስ አብሮት እንዯነበር እናያሇን፡፡
በእነዙህ ሦስት ክፍልች ለቃስ በሏዋርያዊ ጉዝዎቹ ሁለ አብሮት የሰራ የቅደስ
ጳውልስ ዯቀ መዜሙር መሆኑን እንገነ዗ባሇን :: መቅዴመ ወንጌሌም ለቃስ የቅደስ
ጳውልስ ዯቀ መዜሙር እንዯነበር ሲያስረዲ « ወክሌኤቱ እምኔሆሙ እምአርዴእት. ..
ወካሌኡ ለቃስ ወውእቱኒ ዗ኮነ ረዴኦ ሇጳውልስ ፤ከሁሇቱ አንደ የጳውልስ ዯቀ
መዜሙር ለቃስ ነው« በማሇት ይገሌጣሌ፡፡ በመሌእክታቱ ውስጥ የምናያቸው
መረጃዎች ይህንንው በበሇጠ የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡

በመሌእክታት

ከመሌእክታት ውስጥ ስሇ ለቃስ የሚያስረደን ሦስት ጥቅሶች ናቸው እነርሱም:-

1. በቇሊ.4፥14 ሊይ « የተወዯዯው ባሇመዴኃኒቱ ለቃስ ዳማስም ሰሊምታ ያቀርቡሊችኋሌ »


ይሊሌ

2. በፊሌሞ.24 ሊይ « በክርስቶስ ኢየሱስ ከእኔ ጋር የታሰረ ኤጳፍራ አብረውኝም የሚሠሩ


ማርቆስና አርስጥሮኮስ ዳማስም ለቃስም ሰሊምታ ያቀርቡሌሃሌ» ይሊሌ::

30
ማስገን዗ቢያ የቇሊስያስና የፊሌሞና መሌእክታት ጳውልስ በመጀመሪያ የሮም አሥርቱ
ጊዛ በሮም ሆኖ የጻፋቸው መሌእክታት መሆናቸው ታውቋሌ ስሇዙህ ለቃስ በዙያ ጊዛ
ስማቸው ከተገሇጠው ከላልቹ የጳውልስ ዯቀመዚሙርት ጋር ሆኖ በሮም ውስጥ
የወንጌሌን ሥራ አብሮ ይሠራ እንዯነበር ከጥቅሶቹ እንገነ዗ባሇን፡፡

3. በ2ጢሞ 4፥10 ሊይ « ዳማስ የአሁኑን ዓሇም ወድ ትቶኛሌና ወዯ ተሰልንቄም


ሄዶሌ፤ ቲኪቆስም ወዯ ገሊትያ ቲቶም ወዯ ዴሌንጥያ ሄዶሌ፡፡ ለቃስ ብቻ ከእኔ ጋር
አሇ» ይሊሌ

መስገን዗ቢያ፡- 2ኛ የጢሞቴዎስ መሌእክት ዯግሞ ጳውልስ ሇሁሇተኛ ጊዛ በሮም ታሥሮ


ሳሇ የጻፋት መሌእክት ናት:: ያን ጊዛ ቅደስ ጳውልስ የወንጌሌ ሩጫውን ጨርሶ ዕሇተ
ሞቱን የሚጠባበቅበት ጊዛ ነበር፡፡ ዯቀ መዚሙርቱ ሁለ በየምክንያቱ ወዯ ላልች
ቦታዎች ሄዯዋሌ፡፡ እሥራቱና መከራው ከመቼውም ይሌቅ በጸናበት በዙያ ጊዛ ከእርሱ
ጋር የነበረው ለቃስ ብቻ ነበር፡፡ ስሇዙህም ለቃስ ሇቅደስ ጳውልስ የነበረው ቀረቤታ
ምን ያህሌ እንዯነበረና እስከ ዕሇተ ሞቱ ዴረስ ከእርሱ ሳይሇይ ያገሇገሇው ታማኝ ዯቀ
መዜሙሩ እንዯነበር ከጥቅሱ እንገነ዗ባሇን፡፡

ያስተማረበት ሀገር

ለቃስ ስሊስተማረበት ሀገር የምንረዲው ከትውፊታውያን መጻሔፍት በምናገኘው ታሪክ ነው::


እነዙህም ታሪኮች ለቃስ ጳውልስን ከመከተለ በፊትና ከጳውልስ ዕረፍት በኋሊ በየትኞቹ
አገሮች እንዲስተማረ ይነግሩናሌ፡፡

በለቃስ ወንጌሌ ትርጓሜ መግቢያ ሊይ ሏዋርያት ዓሇምን ዕጣ በዕጣ ብሇው ተካፍሇው


ሇማስተማር በሚወጡበት ጊዛ ለቃስ ዮሏንስን ተከትል በመሓዴ ዮሏንስ በዕጣ ከዯረሰችው
ከምዴረ ጽርእ ከፍል በሰጠው በመቄድንያ ገብቶ ስሇ ክርስቶስ እንዲስተማረ ይናገራሌ፡፡ ይህም
ቅ.ጳውልስን ከመከተለ በፊት መሆኑ ነው::

31
ገዴሇ ሏዋርያት ዯግሞ ቅደስ ጳውልስ በሰማዕትነት ከሞተ በኋሊ ለቃስ ከሞት ተርፎ በሮሜ
ዲርቻ ባለ አገሮች ያስተምር እንዯነበር ሲገሌጥ « ወኔሮንኒ ንጉሥ ዗ይሰመይ ቄሣር አኃዝ
ሇጳውልስ ወመተሮ ርእሶ ሀገረ ሮምያ ወለቃስ ቅደስ ተርፈ እምገጸ ንጉሥ ወተሰወረ ወኮነ
ይሰብክ ውስተ ኵል በሏውርተ አህጉር ዗ውስተ ይእቲ አጽናፍ» ይሊሌ :: ስንክሳር ዯግሞ
በበኩለ« ወይሰብክ ለቃስ በሀገረ ሮሜ» ይሊሌ፡፡ ስሇዙህ ቅደስ ለቃስ በፊት በመቄድንያ፣
በኋሊም በሮምና በዲርቻዎቿ እየተ዗ዋወረ የክርስቶስን ወንጌሌ አስተምሮ እንዯነበር
እንገነ዗ባሇን፡፡

ዕረፍቱ

ኔሮን ቄሣር ባስነሳው ስዯትና መከራ ቅደስ ጴጥሮስና ቅደስ ጳውልስ በሞቱ ጊዛ የብዘ
ክርስቲያኖች እሌቂት ተፈጽሞ ነበር፡፡ ለቃስ ግን ከኔሮን ቄሣር ተሰውሮ ወንጌሌን በመስበክ ሊይ
ነበር፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተሇያየ ታምራት እያዯረገ ብዘ ሔዜብ ሲያሳምን ያዩ ካህናተ
ጣዖት ወዯ ኔሮን ቄሣር ሄዯው « በሥራዩ ብዘ ሔዜብ እያሳሳተ ነው» ብሇው ከሰሱት:: ከዙያም
ተይዝ በኔሮን ቄሣር ፊት ቀረበ፡፡ ንጉሡ ኔሮንም « እስከ መቼ አንተ ሰዎችን በሥራህ
ታስታሇህ» ባሇው ጊዛ «እኔ መሠርይ አይዯሇሁም የሔያው የእግዙአብሓር ሌጅ የኢየሱስ
ክርስቶስ መሌክተኛ ነኝ እንጂ» ብል መሇሰሇት፡፡ በዙህን ጊዛ ኔሮን ተቆጥቶ እጁን
እንዱቆርጡት አ዗዗ና መጻሔፍት የሚጽፍባትን ቀኝ እጁን አስቆረጠው ለቃስ ግን ጸልት
አዯረገና የተቇረጠችውን እጁን ቀጥል የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይሌ አሳየው፡፡ የጭፍሮቹን አሇቃ
ጨምሮ 270 ነፍሳት ይህን አይተው በክርስቶስ አመኑ፡፡ በዙህ ጊዛ ኔሮን በጣም ተቆጣና
እነዙህ ሰዎችና ቅደስ ለቃስን በሰይፍ እስከገዯሊቸው ለቃስን በሰይፍ ሉገዴለ ከመጡት
ጭፍሮች አንደ አንዴ ዓይኑ ታውሮ ነበር፡፡ ገና ወዯ ለቃስ ሲቀርብ የታወረ ዓይኑ በራሇት፧
በዙህ ተገርሞ በእግሩ ሥር ወዴቆ ለቃስን ይቅርታ ጠየቀውና ንስሏ ገባ፡፡ ላሊው ጭፍራ ግን
ይህን ያመነውን ሰው እና ለቃስን በሰይፍ መትቶ ገዯሊቸው በዙህ ዓይነት ለቃስ በሰማዕትነት
አረፈ፡፡ በዴኑንም ወዯ ባሔር ጣለት፡፡ ነገር ግን እግዙአብሓር ሞገዴን አስነስቶ ወዯ አንዱት
ዯሴት አዯረሰው፤ አንዴ አማኝም አግኝቶ ገነ዗ውና ቀበረው በማሇት ገዴሇ ሏዋርያት እና
ስንክሳር ይተርካለ፡፡ ስንክ ጥቅ.22

ለቃስ የሞተው በ84 ዓመቱ ሲሆን እስከ 84 ዓመቱ ዴረስ ግን ሚስት ያሊገባ ሰው እንዯነበር
ጥንታዊያን መረጃዎች ይገሌጣለ፡፡

32
ምሳላው

 ለቃስ በገጸ ሊሔም ይመሰሊሌ የዙህም ምክንያቱ « አምጽኡ መግዜአ ሊህም


ወጥብሇሐ ንብሊዕ ወንትፌሳሔ ምስላሁ» ብል ሇክርስቶስ ምሳላ የሚሆን የሊህም
የፊሪዲ/ ምሳላ« ስሇየጻፈ ነው /ለቃ.15፥23/ የትርጓሜ ወንጌሌ የታሪክ ዓምዴ
እንዱሁም የጥንት ቤተክርስቲያን አባቶች ጸሏፍት የ4ቱን ወንጌሊት ምሳላ |
Sumbol of figure/ ሲገሌጡ ለቃስ በገጸ ሊህም የተመሰሇው በዙህም ምክንያት
እንዯሆነ አስረዴተዋሌ፡፡

የተጻፈበት ቦታ ቋንቋና ዗መን

የለቃስ ወንጌሌ ስሇተጻፈበት ቦታና ዗መን የተሇያየ አመሇካከት አሇ፡፡ ይኸውም ዗መናውያን
የሆኑ ሉቃውንት የለቃስ ወንጌሌ ከሏዋርያት ሥራ አስቀዴሞ የተጻፈ መሆኑ በሏሥ.1፥2
ስሇተገሇጠ ሏዋርያት ሥራ የተጻፈው ዯግሞ ቅደስ ጳውልስ በሮም ሇሁሇት ዓመት ታሥሮ
ከነበረበት ጊዛ /62-64 ዓ.ም በኋሊ ወዱያውኑ መሆኑን ስሇምንረዲ/ ወንጌለ የተጻፈው ከዙህ
ቀዯም ብል ቅደስ ውልስ በቂሣርያ ታስሮ ሳሇ በ60 ዓ.ም ገዯማ እንዯሆነ ያስገነዜባለ፡፡
የጻፈውም በግሪክኛ ቋንቋ መሆኑን ያስረዲለ፡፡ መቅዴመ ወንጌሌና የትርጓሜ ወንጌሌ የታሪክ
ዓምዴ ዯግሞ ለቃስ ወንጌለን የጻፈበት አገር መቄድንያ፣ የጻፈበት ቋንቋ /ሌሳን/ ዮናኒ
የተጻፈበት ዗መን ዯግሞ ጌታ ካረገ ሃያ አንዴ ዓመት ተፈጽሞ ሃያ ሁሇተኛው ሲጀመር
ቀሊውዳዎስ ቄሣር በነገሠ በአሥራ አራተኛው ዗መን እንዯሆነ ይገሌጣለ:: ዗መኑን ወዯ ዓመተ
ምሔረት ስንሇውጠው: ከጌታ ዕርገት በፊት:- 33 ዓመት ከጌታ ዕርገት በኋሊ 21 ዓመት ዴምር
54 ዓ.ም ይሆናሌ

ስሇተጻፈበት: ቦታ፥ ቋንቋና ዗መን ይህን ሁለ አጠቃል የሚናገረው በለቃስ ወንጌሌ ትርጓሜ
መዯምዯሚያ ሊይ የሚገኘው ቃሌ ነው፡፡ እርሱም በግእዜ እንዱህ ይሊሌ፡፡ « መሌዓ ጽሔፈተ
ብሥራቱ ሇለቃስ ወንጌሊዊ አሏደ እምሰብአ ወክሌኤቱ አርዴእት ዗ጸሏፎ በሌሳነ ዮናኒ ሇሰብአ
ሀገረ መቄድንያ እምዴኅረ ዕርገቱ ሇእግዙእነ ውስተ ሰማይ በእሥራ ወአሏደ ዓመት
ወበዏሠርቱ ወዏርባዕቱ ዓመተ መንግሥቱ ሇአቅላንዴዮን ሇቀሊውዳዎስ ቄሣር»

ከእነዙህ መረጃዎች እንዯተመሇከትነው የተጻፈበትን ቦታና ዗መን በተመሇከተ በኛ ትውፊት


የተገሇጠውና በላልች ሉቃውንት የተነገረው አመሇካከት የተሇያየ ቢሆንም የተጻፈበትን ቋንቋ

33
በተመሇከተ ያሇው አመሇካከት ግን ተመሳሳይ ነው፡፡ ምክንያቱም በኛ ትውፊት « ዩናኒ»
የተባሇው ቋንቋ « ኪኒ» የተባሇው የግሪክኛ /የጽርእ ዱያላክት ስሇሆነ ነው፡፡

የተጻፈሇት ሰው

የለቃስ ወንጌሌ የተጻፈሇት ሰው «ቴዎፍልስ» የተባሇ በሮም ግዚት ሥር ያሇ አንዴ ባሇሥሌጣን


ነበር ይህም በወንጌለ መግቢያ ሊይ ተገሌጧሌ 1፥1 ቴዎፍልስ ማሇት መፍቀሬ እግዙአብሓር
ማሇት ነው:: ለቃስ በስብከቱ አስተምሮ ያሳመነው ባሇሥሌጣን አንዯኾነ በወንጌለ መጀመሪያ
ሊይ ካለት የመግቢያ ቃሊት እንገነ዗ባሇን፡፡

አንዲንድች ግን « ቴዎፍልስ» የሚሇው ይህ ስም የሚያመሇከተው አንዴን የታወቀ ሰውን


ሳይሆን መጽሏፉን እንዱያነቡ የተጻፈሊቸውን የእግዙአብሓር ወዲጆች ሁለ ነው በማሇት
ይናገራለ። ነገር ግን አንዴ የታወቀ ሰው መሆኑን የሚከተለት ማስረጃዎች ይገሌጣለ፡፡

1. « ቴዎፍልስ » የሚሇው ስም በዙያ ዗መን በግሪኮችና በአይሁዲውያን ዗ንዴ


የግሇሰቦች መጠሪያ ስም /የተጸውኦ ስም/ ሆኖ የተሇመዯ ስም ነበር፡፡ ስሇዙህ «
ቴዎፍልስ» የአንዴ ሰው የተጸውኦ ስም መሆኑን እንረዲሇን፡፡

2. ለቃስ ይህን ሰው ሲጠራው « ኡ አዙዜ ታአፊሊ- የከበርህ ቴዎፍልስ ሆይ / Most


excellent / Most noble / ብል ይጠራዋሌ ከዙያም አያይዝ የሚናገራቸው ቃሊት ሁሇተኛ
መዯብ ነጠሊ ቁጥር የሆኑ ቃሊት ስሇሆኑ ቴዎፍልስ በሮም ግዚት ውስጥ አንዴ የታወቀ
ባሇሥሌጣን የነበረ ሰው መሆኑን እንገነ዗ባሇን /1፥1-4

3. የለቃስ ወንጌሌ ትርጓሜ / አንዴምታ/ በመግቢያው ሊይ ቴዎፍልስ / ታኦፊሊ


በመቄድንያ አጠገብ ያሇችው የእስክንዴርያ መኯንን /ሀገረ-ገዥ/ እንዯ ነበረና በለቃስ
ስብከት ክርስትናን የተቀበሇ ሰው እንዯሆነ ገሌጦ ይናገራሌ፡፡

የተጻፈበት ዓሊማ

ለቃስ ወንጌሌ የተጻፈበት ዓሊማ በወንጌለ መግቢያ ሊይ በግሌጽ ተቀምጧሌ፡፡ እርሱም« . .


ስሇተማርከው ቃሌ እርግጡን እንዴታውቅ በጥንቃቄ ሁለን ከመጀመሪያው ተከትዬ በተራው
ሌጽፍሌህ መሌካም ሆኖ ታየኝ፡፡ » ይሊሌ፡፡ /1፥1-4/ ስሇዙህ የወንጌለ ዓሊማ ቴዎፍልስ በቃሌ

34
የተማረውን የክርስቶስን ነገር እርግጡን / በጥሌቀት፣በሚገባ/ እንዱያውቅ ሇማዴረግ ነው፡፡
ዚሬም መጽሏፉን የሚያነቡ ሁለ ስሇክርስቶስ ታሪክና ሥራ በስፋትና በጥሌቀት እንዱያውቁ
ያዯርጋሌ፡፡

ከዙህ በመነሳት ለቃስ ከጽንሰቱ እስከ እርገቱ የመ዗ገበው የጌታ ታሪክ ሲጠና ያተኮረባቸው
ነገሮች የሚከተለት ናቸው፡፡

1. ከዴንግሌ ማርያም የተወሇዯው የሰው ሌጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ የእግዙአብሓር ሌጅ


መሆኑና ጌታ መሆኑን የተሇያዩ ማስረጃዎችን ምስክሮችን በማቅረብ ሇቴዎፍልስ
ያስረዲሌ:: [1፥35፡43፡47፤ 2:49፣3፥22፡38፤ 4፥3፡41፣10፥22፣ 23፥42/

2. ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሲሆን በዴህነት እንዯተገሇጠ፣ በማስተማር ዗መኑም ዴሆችን


ይጉበኝና ይቀበሌ እንዯነበር በመግሇጥ ቴዎፍልስም ክብሩን ሇጌታ ሰመተው ከበታቹ
ያለትን ዴሆችንና ግፉዏን ሰዎች እንዱቀበሌ ያስተምረዋሌ፡፡ /2፥6፡7፡24፤3፥10፤4፥19፤
5፥30፤7፥34 50፤ 8፥2:3፤ 10፥29-37፤ 12፥13-21 ፤ 14፥12-14፤ 16፥19-31 ፤19፥1-
10፡፡/

3. ስሇ መዜሙርና ስሇጸልት የተሇያዩ ማስረጃዎች በማቅረብ የስተምረዋሌ፡፡ 11፥46-


55:67 79፤ 2፥14:29-34፤3፥21፣5፥16፤ 6፥12፤11፥1-13፤ 18፥1-14፤ 22፥39/

የወንጌለ ጥናት ይዝታው

እንዯላልቹ ወንጌሊት ሁለ የለቃስ ወንጌሌ ይዝታው የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን


ታሪክ፣ታምራትና ትምህርት መግሇጥ ነው፡፡ በዙህ ክፍሌ የምናጠናው በለቃስ ወንጌሌ ብቻ
የተመ዗ገቡትን ይሆናሌ፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ

በለቃስ ወንጌሌ ብቻ የተመ዗ገቡት የጌታ ታሪኮች 20 ናቸው፡፡ እነርሱም፡-

1. መጥምቁ ዮሏንስ በተፀነሠ በ6ኛው ወር ጌታ እንዯተፀነሰ /1፥1-56/

2. የመጥምቁ ዮሏንስ ሌዯትና እዴገት /1፥57-80/

35
3. ጌታ በበረት ሲወሇዴ እረኞች ስሇ እርሱ የሰሙትንና ያዩትን እንዯመሰከሩ /2፥1-20

4. በተወሇዯ በ8ኛው ቀን ሲገረዜ ስሙ ኢየሱስ እንዯተባሇ /2፥21/

5. በ4ዏ ቀን ወዯ ቤተ መቅዯስ እንዯተወሰዯና ስምዖንና ሏና እንዯመሰከሩሇት /2፥22-39/

6. በ12 ዓመቱ ሇፋሲካ በዓሌ ወዯ ኢየሩሳላም እንዯሄዯ/2፥40-52/

7. ከዮሴፍ እስከ ኣዲም ወዯኋሊ የተቆጠረ የጌታ ሏረገ-ትውሌዴ /3፥23-38/

8. ስምዖን ጴጥሮስና የ዗ብዳዎስ ሌጆች መጠራት /5፥1-11/

9. ጌታ በፈሪሳዊው ቤት ከማዕዴ ተቀምጦ ሳሇ ወዯ እርሱ የመጣቸውን ኃጢአተኛ


ኃጢአቷን እንዲስተስረየሊት /7፥36-50/

10. በገን዗ባቸው ያገሇግለት የነበሩት ሴቶች /8፥1-3/

11. ሰባ አርዴእትን ሾሞ ሁሇት ሁሇት አዴርጏ እንዯሊካቸው /10፥1-20/

12. ማርታ ሰቤትዋ እንዯተቀበሇችው/10፥38-42/

13. በኢያሪኮ በ዗ኬዎስ ቤት እንዯዋሇ /19፥1-10/

14. ወዯ ኢየሩሳላም ተጉዝ ሉዯርስ ሲቀርብ ከተማይቱን አይቶ እንዲሇቀሰሊት /19፥41-64

15. በተያ዗ ጊዛ በገሉሊው ገዥ በሄሮዴስ ፊት እንዯተጠየቀ /23፥6-12/

16. ሉሰቅለት ሲወስደት ሙሾ የሚያወጡ ሴቶችና ብዘ ሔዜብ እንዯተከተለት ነ23፥27-31/

17. በትንሳኤው ወዯ ኤማሁስ ይሄደ ሇነበሩት ሁሇት ዯቀመዚሙርት ተገሌጦ


ብዘ እንዲነጋገራቸው 124፥13-35/

18. ሇ11ደና አብረዋቸው ሇነበሩት ሲገሇጥ መንፈስ እንዯመሰሊቸውና እንዳት


እንዲሳመናቸው [24 ፥ 13-35/

19. ከሊይ ኃይሌን እስኪሇብሱ ዴረስ በኢየሩሳላም እንዱቆዩ እንዲ዗ዚቸው /24፥44-49/

36
20. ወዯ ሰማይ ሲያርግ እየባረካቸው እንዲረገና እነርሱም ተመሌሰው እግዙአብሓርን
እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅዯስ እንዯኖሩ /24፥50-53/

የኢየሱስ ክርስቶስ ታምራት

በለቃስ ወንጌሌ ውስጥ ጌታ ብዘ ታምራትን አዴርጏ እንዯነበር በየሥፍራው ተመዜግቧሌ


/4፥40:41፤ 6፥17-19፡፡ /ነገር ግን በዙህ ወንጌሌ ሙለ ታሪካቸው የተመ዗ገበሊቸው ታምራት 19
ናቸው፡፡ ከእነዙህም ውስጥ በለቃስ ወንጌሌ ብቻ የሚገኙት 4 ናቸው:: እነርሱም፡

1. ናይን በሚባሌ ከተማ የአንዱት መበሇትን ሌጅ ከሞት እንዯ አስነሳ 17፥11-17/

2. በሰንበት በአንዴ ምኩራብ ሲያስተምር የ18 ዓመት ጏባጣ አቀና /13፥1ዏ-17

3. በሰንበት ቀን ከፈሪሳውያን አሇቆች በአንደ ቤት የተዯረገውን ፈውስ /14፥1-6/

4. ወዯ ኢየሩሳላም በመሄዴ ባንዱት መንዯር 10 ሇምጻሞችን አነጻ /17፥11-19ላልቹን 15


ታምራት በማርቆስ ወንጌሌ ጥናት ተመሌከት::

የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች

ከሲኖፕቴክ ወንጌሊት ውስጥ የለቃስ ወንጌሌ እንዯማቴዎስ ወንጌሌ ሁለ የጌታ የኢየሱስ


ክርስቶስ ትምህርቶች በስፋት መዜግቦ የሚገኝ ወንጌሌ ነው፡፡ ጌታ በቀጥታ
ካስተማራቸውና በጥያቄዎች መነሻነት ካስተማራቸው ትምህርቶች ውስጥ ብዘ ትምህርቶች
በለቃስ ወንጌሌ ይገኛለ፡፡ ከእነዙህም ውስጥ በለቃስ ወንጌሌ ብቻ የሚገኙት 12 ናቸው።
እነርሱም፡

ሀ. እርሱ ራሱ በቀጥታ ካስተማራቸው ትምህርቶች

1. ባዯገበት በናዜሬት ምኩራብ በአንዴ አገር ያዯረገውን አንዴ ዴርጊት የግዴ በላሊ
አገር ማዴረግ እንዯላሇበት በዕሇተ ሰንበት ያስተማረው ትምህርት /4፥16-30/

2. በሰንበት ቀን ከፈሪሳውያን አሇቆች ባንደ ቤት እንጀራ ሉበሊ ገብቶ ሳሇ በግብዣ


የተጠራ ሰው በከበሬታ ወንበር መቀመጥ እንዯላሇበት፣ ብዴራት የማይመሌሱትን
ዴሆች በግብዣ መጥራት እንዯሚገባ ያስተማረው ትምህርት /14፥1-24/

37
3. ከእርሱ ጋር ሇሚሄዯው ሔዜብ ዗ወር ብል የእርሱ ዯቀመዜሙር ሇመሆን ሁለን
ትቶ መከተሌ እንዯሚያስፈሌግ የሰጠው ትምህርት /14፥25-35

4. በገን዗ብ ዴሆችን መርዲት ያሇውን መሌካም ውጤትና አሇመርዲቱ ዯግሞ ያሇውን


መጥፎ ውጤት /ጉዲት/ በተመሇከተ በ2 ምሳላዎች የሰጠው ትምህርት 16፥1-31/

5. ስሇጸልት በሁሇት ምሳላዎች የሰጠው ትምህርት /18፥1-14/

ሇ. በጥያቄዎች መነሻነት ካስተማራቸው ትምህርቶች

1. ሔግ አዋቂው ስሇ዗ሊሇም ሔይወትና፣ባሌንጀራው ማን እንዯሆነ ጠይቆት በዯጉ


ሳምራዊ ምሳላነት የሰጠው ትምህርት /10፥25-37

2. ከዯቀመዚሙርቱ አንደ ስሇጸልት እንዱያስተምራቸው ጠይቆት አቡነ዗በሰማያትንና


ላሊም ጸልትን የሚመሇከት ምሳላ በመስጠት ያስተማረው ትምህርት 11፥1-13/

3. አንዴ ሰው ከወንዴሙ ጋር ርስት እንዱካፈሇው በጠየቀው ጥያቄ ተነሥቶ የሰው


ሔይወት በሀብቱ ብዚት እንዲሌኾነ በተሇያዩ ምሳላዎች ያስተማረው ትምህርት
/12፥13-59/

4. ጲሊጦስ ስሇገዯሊቸው የገሉሊ ሰዎች ከተነገረው ተነሥቶ ንስሏ ያሌገባ ሁለ


እንዱሁ እንዯሚጠፋ በምሳላ የሰጠው ትምህርት /13፥1-9/

5. ፈሪሳውያንና ጻፎች ኃጢአተኞችን እያቀረበ ሲያስተምር አይተው ስማንጏራጕራቸው


በኃጢአት የጠፋውን ሰው በንስሏ መቀበሌ እንዯሚገባ በ3 ምሳላዎች የሰጠው
ትምህርት /15፥1-32/

6. ሏዋርያት እምነት ጨምርሌን ባለት ጊዛ ስሇእምነትና ስሇትሔትና የሰጣቸው


ትምህርት 17፥5-11/

7. ፈሪሳዉያን የእግዙአብሓር መንግሥት የምትመጣው መቼ እንዯኾነ ጠይቀውት


በመጠባበቅ እንዯማትመጣ የሰጠው ትምህርት /17፥20:21/

38
አከፋፈለ

1. መግቢያ ሇማን? ሇምን? እንዳት እንዯጻፈው ይገሌጣሌ/1፥1-4/

2. የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ የሔፃንነቱ ታሪክ | 1፥5-2፥52/

 መሌአኩ ገብርኤሌ ወዯ ዗ካርያስ በተሊከ በ6ኛው ወር ወዯ ዴንግሌ ማርያም ተሌኮ


ጌታን እንዯምትወሌዴ ማብሰሩ /1፥5-38/

 ዴንግሌ ማርያም በኤሌሳቤጥ ቤት /1፥39-56/

 የመጥምቁ ዮሏንስ መወሇዴ መገረዜና ማዯግ /1፥57-80/

 ጌታ ሲወሇዴ እረኞች በቤተሌሓም በግርግም እንዯተወሇዯ /2፥1-20/

 ሉገርዘት 8 ቀን ሲሞሊ ጊዛ ስሙ ኢየሱስ ተብል እንዯተጠራ /2፥21

 መሥዋዕት ሉያቀርቡ ወዯ ኢየሩሳላም እንዯወሰደት 12፥22-39/


 በ12 ዓመቱ ሇፋሲካ በዓሌ ወዯ ኢየሩሳላም እንዯወጣ /1፥40-51/

 በጥበብና በሞገስ ማዯጉ /2፥52/

3. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ሲ዗ጋጅ የተዯረጉ ነገሮች 3፥1-4፥13/

 የመጥምቁ ዮሏንስ ጥመቀትና ስብከት /3፥1-20/

 የጌታ መጠመቅ /3፥21:22/

 እሰከ አዲም የተቆጠረው የጌታ ሏረገ- ትውሌዴ /3፥23-283

 በምዴረ በዲ 40 ቀን ከዱያብልስ እንዯተፈተነ/4፥1-13/

4. ጌታ በገሉሊና ባጠገቧ ባለ አገሮች ያዯረገውና ያስተማረው ነገር /4፥14-9፥50/

 በናዜሬት ምኩርብ ያስተማረው ትምህርት 14፥14-30

 በቅፍርናሆም ያዯረጋቸው ተአምራት /4፥31-48/

 በጌንሳሬጥ ባሔር ዲር ስምዖንና የ዗ብዳዎስን ሌጆች መጥራቱ /5፥1-11/


 በቅፍርናሆም ውስጥ በቤት፣ በምኩራብና፣ በከተማዋ ዘሪያ ያዯረጋቸው ነገሮች/5፥12-
6፥16/
 በተካከሇ ሥፍራ የሰጠው ሰፊ ትምህርት /6፥17-49/

39
 በምዴረ በዲና በፈሪሳዊው ቤት ያዯረገውና ያስተማረው /7፥18-50/

 እየተ዗ዋወረ ሲያስተምር በምሳላዎች ያስተማረው ትምህርት /8፥1-21

 ከገሉሊ ወዯ ጌንሳሬጥ ተሻግሮ እንዱሁም ወዯ ገሉሊ ተመሌሶ ያዯረጋቸው ታምራት


/8፥22-56/
 በገሉሊ ውስጥ ሇመጨረሻ ጊዛ ሇሏዋርያት የተናገረውና ያሳያቸው ነገሮች /9፥1-50
5. ገሉሊ ወዯ ኢየሩሳላም በመጓዜ ሊይ ሳሇ ይሁዲ ውስጥ ሳይገባ ያዯረጋቸው ነገሮች /9፥51
1፥37/

 በስማርያ ሉያሌፍ ሲሌ ስሊሌተቀበለት ወዯ ላሊ መንዯር መሄደ /9፥51-56

 በትክክሇኛ ሏሳብ ሳይሆን በጉዝው ሉከተሇው የጠየቀውን እንዲሌተቀበሇው 9፥57-62/

 ሰባ አርዴእትን ሹሞ በፊቱ ወዲለ ከተሞች እንዯሊካቸው /10፥1-24

 በጉዝ ሊይ ሳሇ ሉፈትነው ሇጠየቀው ሔግ አዋቂ የሰጠው መሌስ /10፥2537/

6. ወዯ ኢየሩሳላም በመውጣት ሊይ ሳሇ በይሁዲ ውስጥ ያዯረጋቸው ነገሮች /10፥38-19፥27/

 በቢታንያ ማርታ በቤትዋ እንዯተቀበሇችው /10፡38-42/

 በጉዝው ሊይ በተሇያዩ ሥፍራዎች ሇሔዜብና ሇዯቀመዚሙርቱ ያስተማራቸው


የተሇያዩ ትምህርቶች /11፥1-18፥34
 በኢያሪኮ ውስጥ ያዯረጋቸውና የተናገራቸው ነገሮች /18፡35-19፥27/

7. ወዯ ኢየሩሳላም ከገባ በኋሊ /በመጨረሻው ሳምንት/ ያዯረጋቸውና ያስተማራቸው


ነገሮች 19፥28-22፥46

 ወዯ ኢየሩሳላም ሲገባ ሔዜቡ እየ዗መሩ እንዯተቀበለት /19፥28-46/

 በዙህ ሳምንት በመቅዯስ ዕሇት ዕሇት ያስተማረው ትምህርት /19፥47-21፥38/

 በፋሲካ ምሽት ያዯረጋቸውና የተናገራቸው ነገሮች /22፥1-46/

8. የጌታ የስቅሇቱ ታሪክ /22፥47-23፥56/

 ተይዝ በሉቀካህናቱ፣ በጲሊጣስና በሄሮዴስ እንዯተመረመረ (22፥47-23፥25/

 በብዘ መከራ አሠቃይተው በመስቀሌ እንዯሰቀለት !23፥26-49/

40
 ዮሴፍ ዗አርማትያስ ከዓሇት በተወቀረ አዱስ መቃብር እንዲኖረው /23፥50-56/

9. የጌታ ትንሣኤውና ዕርገቱ /24፥1-53/

 ከተነሣ በኋሊ ሇተከታዮቹ በተሇያዩ ቦታዎች መታየቱ /24፥1-43/

 ሇሏዋርያት የተናገራቸው የመጨረሻዎቹ ቃሇት /24፥44-49/

 በቢታንያ እየባረካቸው ወዯሰማይ ማረጉ /24፥50-53/

ወስብሏት ሇእግዙአብሓር

አ዗ጋጅ መ/ር ወ/ትንሣኤ በዚ

41

You might also like