Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

: ጤና ይስጥልኝ መምህር

: ጤና ይስጥልኝ

: በቅድሚያ ጥሪያችንን አክብረህ ስለተገኘህ እናመሰግናለን

: እኔም አክብራችሁ ስለጠራችሁኝ አመሰግናለሁ

: ለአንባቢያን ራስህን ብታስተዋዉቅልን

: ስሜ መምህር ሰለሞን አስፋው ይባላል የ 1 እና 2 ደረጃ አስተማሪ ነኝ

: እሺ ጥሩ ወደ ዋናው ጥያቄ ስንገባ የ 2013 አ.ም የመማር ማስተማር ሂደት በተመለከተ ትንሽ ነጥቦችን ብታነሳልን

: የ 2013 አ.ም የመማር ማስተማር ሂደት ከሌሎች አመታት ተለይቷል ይህም የሆነው በ አለም አቀፉ የ ኮሮና ወረርሽኝ
ምክንያት ነው። እንደ ከዚህ ቀደመው ለተማሪዎች ኖቶችን ማፃፍ እና ተደጋጋሚ የቤትስራዎችን ማሰራት ካለው ጊዜ
አኳያ ለመስጠት አይመችም ምክንያቱም ተማሪዎች ትምህርታቸዉ በፈረቃ በሳምንት 3 ቀን ስለሚማሩ በ 3 ቀን
ውስጥ ኖቶችን መፃፍ የማይታሰብ ነው። እንኳን ኖቶችን አፃፈን ሙሉ 45 ደቂቃ ክፍለጊዜዉን አስረድተን እንኳን
መፅሀፉን ለመጨረስ የማይቻልበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው። በዚህም ምክንያት የ 2013 አ.ም የመማር ማስተማር ሂደት
ከባድ ሆኗል።
: ወደ ሁለተኛው ጥያቄያችን ስናልፍ የትምህርት ስርዓት ከ ኮሮና በፊት እና በኋላ ምን መልክ ይዟል ?
: የትምህርት ስርዓት ከኮሮና በፊት እንደሚታወቀው ተማሪዎች በሳምንት 5 ቀናትን በመማር ያሳልፋሉ እንዲሁም
መምህራንም የማስተማሪያ ፕሮግራማቸውን በሳምንት እቅድ ከፍለው በደንብ በተደራጀ እና ለተማሪዎች በሚመች
መንገድ ነበር ትምህርት የሚሰጡት ከኮሮና በኋላ ግን ነገሮች በጣም ተዘበራርቀዋል መንግስት ለመምህራን በዛ ያሉ
ምዕራፎችን በአጭር ጊዜ እንዲያስተምሩ ጫና ዉስጥ ይከቷቸዋል መምህራንም የግድ መጨረስ ስላለባቸው በፍጥነት
ለማስተማር ሲሉ አብዛኛውን ሀላፊነት በተማሪዎች ላይ ያሳርፋሉ ለምሳሌ ብንጠቅስ በ 1 ምዕራፍ ውስጥ 30 ገፅ ቢኖር
ቢያንስ ከ 10-15 የሚሆነውን ገፅ ተማሪዎች በራሳቸው እንዲያነቡ ይደረጋል በዚህ መሀከል ብዙ ተማሪዎች ሳይገባቸው
ያልፋል የ
ያህም የተማሪዎችን ዉጤት ይጎዳል።
: በጣም ጥሩ ማብራሪያ ነበር የሰጠኸኝ አመሰግናለሁ ቀጣዩ ጥያቄያችን የሚሆነው በሳምንት 6 ቀን ማስተማር ምን
ይመስላል?
: በሳምንት 6 ቀን ማስተማር እዉነቱን ለመነጋገር አድካሚ ነው በቀደመው ጊዜ ቅዳሜን ለመጪው ሳምንት ትምህርት
ዝግጅት የምናደርግበት ነበር አሁን ግን እሁድን እንኳን ማረፍ አንችልም። ከዚህም በተጨማሪ 3 ወይም 4 የተለያዩ
ክፍሎች አስተምሮ በቀጣዩ ቀንም ለተረኛ ፈረቃ እራሱን መድገም መሰላቸትም ይፈጥራል እንዲሁም የግድ
ለተማሪዎችና ለራሳችን ጤንነት ለመጠበቅ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛችንን ሳናወልቅ ለ 45 ደቂቃ ሙሉ ማስተማር
ከፍተኛ ድካም አለው።
: የተማሪዎች የትምህርት ተነሳሽነት እና ፍላጎት ምን ይመስላል?
: ይህ ወረርሽኝ ሀገራችን ከገባ ቀን አንስቶ ካልተሳሳትኩ ለ 8 ወራት ተማሪዎች ያለስራ በቤታቸው ነዉ ተቀምጠው
ያሳለፉት ይህም በተማሪዎች ስነ ልቦና ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳደረ ይመስለኛል። በአሁኑ ወቅት በተማሪዎች ላይ ብዙ
የትምህርት ፍላጎት አይታይም ይሄም እስከሚስተካከል ጊዜ የሚወስድ ጉዳይ ነው። አብዛኛው ተማሪ መፃሀፍቶችን
ከማንበብ ይልቅ ሶሻል ሚድያ ላይ ብዙ ትኩረትን አድርጓል አብዛኛውንም ጊዜውን የተለያዩ ኦንላይን ጨዋታዎችን
በመጫወት ያሳልፋል። ነገሮች በዚሁ ከቀጠሉ አንባቢ ተማሪዎችን እንዳናጣ የተማሪዎችን የንባብ ባህል እንዴት ማዳበር
እንዳለብን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ዉይይት ተደርጎ አንድ ነገር ላይ መደረስ ያለበት ይመስለኛል።
: የመጨረሻው ጥያቄያችን የሚሆነው ያለፈው የትምህርት አመት ላይ ያላለቁት ምዕራፎች ለመጨረስ ምን እየተካሄደ
እንዳለ ብትነግረን?
: እኔ እንደማስበው አብዛኛው መምህር ያለፈውን የትምህርት ዘመን ያላለቁትን ምዕራፎች ሙሉ በሙሉ ባይሆንም
ተነካክተዋል የቀረውን ተማሪዎች በደንብ አንብበው እንዲረዱት የሚያስችል ነጥቦችን በማጋራት ታልፈዋል። ካለን ጊዜ
አንፃር ሙሉ በሙሉ መምህራን ሊጨርሱት የሚችሉት ነገር አይደለም።
: በጣም እናመሰግናለን መምህር ሰለሞን በመጨረሻም ማስተላለፍ የምትፈልገው ነገር ካለ?
: በርግጥ ብዙ የምለው ነገር የለም ነገርግን ተማሪዎች ያላቸውን ጊዜ በአግባቡ ትምህርታቸው ላይ ማዋል አለባቸው ብዬ
አምናለሁ እና በርቱ ጠንክሩ ለማለት እወዳለሁ እናንተንም እንግዳ አድርጋችሁ ስላቀረባችሁኝ ላቅ ያለ ምስጋናዬን
ማቅረብ እፈልጋለሁ አመሰግናለሁ ስለነበረን ጊዜ።

You might also like