Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 12

የገቢዎች የመረጃ ቋት

(Revenue Data Warehouse)


መሰረታዊ የአጠቃቀም አጭር
መግለጫ (ማጣቀሻ)
ማውጫ
ክፍል አንድ .............................................................................................................................................. 1
መግቢያ................................................................................................................................................... 1
1.1. የገቢዎች የመረጃ ቋት ምንድን ነው? ......................................................................................... 1
1.2. የገቢዎች የመረጃ ቋት ለምን ይጠቅማል? ................................................................................. 2
1.3. የመረጃ ቋቱ መነሻ ገፅ ላይ ምን ይገኛል? .................................................................................. 2
1.4. ወደ መረጃ ቋቱ እንዴት ይገባል?............................................................................................... 3
1.5. የመረጃ ቋቱ ተጠቃሚዎች እነማን ናቸው?................................................................................ 3
ክፍል ሁለት ............................................................................................................................................. 4
2. የሪፖርቶች መሰረታዊ ይዘት ............................................................................................................. 4
2.1. የአገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብን የተመለከቱ ሪፖርቶች...................................................................... 4
2.2. የጉምሩክ ገቢ አሰባሰብን የተመለከቱ ሪፖርቶች ............................................................................ 6
ክፍል ሶስት .............................................................................................................................................. 7
3. ሪፖርት ማስተካከያ መንገዶች .......................................................................................................... 7
3.1. መረጃ ማጣራት (Data Filtering) ........................................................................................... 7
3.2. በአንድ ገጽ የሚኖረውን የመስመር ብዛት መወሰን (Rows per Page Limit) .......................... 7
3.3. የሪፖርቱን አምድ ማስተካከል (Column Editing) ................................................................... 7
3.4. ቅደም ተከተል ማስያዝ (Sorting) ............................................................................................ 8
3.5. ቻርት ማዘጋጀትና ኮፒ ማድረግ (Charting & Snipping) ....................................................... 8
3.6. አዲስ አምድ መጨመር [Compute] ........................................................................................ 9
3.7. ማቅለም [Highlight] .............................................................................................................. 9
3.8. ሪፖርት ማውረድ (Downloading) ........................................................................................ 10
ክፍል አንድ
1. መግቢያ
ይህ የማጣቀሻ ጽሁፍ የገቢዎች ሚኒሰቴር የመረጃ ቋትን የሚጠቀሙ አካላት ስለ መረጃ ቋቱ አጠቃቀም መሰረታዊ
መረጃ የሚሰጥ እና በተለይ ለዚሁ ሲባል ከተዘጋጁት ቪዲዮዎች ጋር ጥቅም ላይ እንዲውል ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ይህ
ማጣቀሻ የመረጃ ቋቱን ምንነት፤ አገልግሎቱንና አጠቃቀሙን የተመለከቱ ጉዳዮችን ይዳስሳል።

1.1. የገቢዎች የመረጃ ቋት ምንድን ነው?


የገቢዎች ሚኒስቴር ለአገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብ እና ለጉሙሩክ ስራ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ የመረጃ አስተዳደር
ስርዓቶችን በስራ ላይ ማዋሉ ይታወቃል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

 ለአገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብ


 SIGTAS  E-payment
 ETAX  TASS
 Cash Register  Others
 ለጉሙሩክ
 ASYCUDA  Ethiopian Customs Valuation
 Ethiopia Customs Management System (ECVS)
System (ECMS)  Value Declaration Detail (VDD)
 Traders Risk Profiling system (TRDP)
እነዚህ በርካታ ሲሰተሞች እርስ በእርስ የተናበቡና የተወራረሱ ባለመሆናቸው ከሲስተሞቹ ሊገኝ የሚገባውን እና
ለተለያዩ ውሳኔወች ጠቃሚ የሆኑ ሪፖረቶችን በቀላሉ ማግኘት አልተቻለም። ይህን ችግር ለመፍታትና በርካታ
ሪፖርቶችን ለማግኘት ይረዳ ዘንድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የገቢ መረጃ ቋት በስራ ላይ አውሏል፡፡ ይህ የመረጃ ቋት
ከሁሉም ሲሰተሞች አስፈላጊውን መረጃ ዘወትር ማታ ማታ በመሰብሰብ የሚይዝ ሲሆን ሰራተኞች የተፈቀደላቸውን
ያህል የተለያዩ ሪፖርቶችን እንዲያገኙ ያስችላል፡፡

የመረጃ ቋቱ ሞዴል ከታች የተመላከተውን ይመስላል፡፡

መግለጫ 1: የመረጃ ቋቱ ሞዴል

1
ከላይ በስዕሉ እንደተመላከተው የገቢዎች የመረጃ ቋት በተለያዩ የመረጃ ምንጮች [ሲስተሞች] ያሉትን መረጃዎች
በመውሰድ በአንድ ቋት በማቀናጀት የተናበበ እና የተወራረሰ መረጃ በማጠናቀር በርካታ ሪፖርቶችን በቀላሉ
ያዘጋጃል፡፡ እነዚህ ሪፖርቶች እጅግ በርካታ ቢሆኑም በአጠቃላይ የታክስ ከፋይ መረጃዎችን የተመለከቱ፣ የተለያዩ
የታክስ አሰባሰብን የተመለከቱ፣ የታክስ ተገዥነትን የተመለከቱ፣ዕቅድ እና አፈፃፀምን የተመለከቱ፣ የጉምሩክ ነክ እና
የመሳሰሉትን የተመለከቱ ሪፖርቶችን ያካትታል፡፡

1.2. የገቢዎች የመረጃ ቋት ለምን ይጠቅማል?


የመረጃ ቋቱ ከሚሰጠን ፈርጀ ብዙ ጥቅሞች መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ።
1. በቀላሉና በፍጥነት የተለያዩ ሪፖርቶችን ለማግኘት ፣
2. የተደራጀ መረጃ በማቅረብ የታክስ ፖሊሲ ውሳኔዎችን ለመደገፍ ፣
3. በተለያየ መንገድ የተሰበሰቡ መረጃዎችን ለመተንተን፣
4. የተደራጁ የታክስ መረጃዎችን ከአንድ ቋት ለማግኘት ፣
5. የተቋሙን የመረጃ ኔትወርክ መጨናነቅ ለመቀነስ ፣
6. የተሻለ አሰራር ለመዘርጋትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

1.3. የመረጃ ቋቱ መነሻ ገፅ ላይ ምን ይገኛል?


ወደ መረጃ ቋቱ መነሻ ገፅ ለመግባት እንደሚከተለው ያድርጉ።
1. በመጀመርያ የበይነመረብ ማሰሻውን [internet browser] ይከፍታሉ
2. በመቀጠል አድራሻ መጻፍያው ላይ ወደ መረጃ ቋቱ የሚወስድዎትን ቁጥር ያስገባሉ። ቁጥሩን
(አድራሻውን) የቅርብ አለቃዎን በመጠየቅ (ወይም እንደአግባብነቱ በኮምፒውተር ባለሙያነት የሚሰሩ
ሰራተኞችን ወይም ሃላፊወችን በማናገር) ማግኘት ይችላሉ፡፡
3. ከዚያም የተሰጠዎትን ቁጥር በበይነመረብ ማሰሻው [internet browser] አድራሻ መጻፊያ ላይ አስገብተው
ኪይቦርድዎ ላይ ኢንተር የሚለውን ሲጫኑ ወደ መረጃ ቋቱ መነሻ ገፅ ይወስድዎታል።

የመረጃ ቋቱ መነሻ ገፅ ይዘት ለመገንዘብ ከታች የሚታየውን መግለጫ ይመልከቱ።

መግለጫ 2

2
በዚህ የመጀመሪያው ገፅ (Home Page) ፊት ለፊት ያለውን ሰፊ ቦታ የያዘው የገቢዎች ሚኒስቴርን አጠቃላይ
እንቅስቃሴ የሚያሳይ ዳሽቦርድ (Dashboard) ሲሆን የያዘው መረጃ በተለይ ለበላይ አመራሮች ፈጠን ያለ ምልከታ
የሚሰጥ ነው፡፡

በመረጃ ቋቱ በግራ በኩል የሪፖርቶች ዝርዝር በቡድን በቡድን ሆነው ተቀምጠዋል። ከጽሁፎቹ አጠገብ ያሉትን
የቀስት ምልክቶች በመንካት በስራቸው የያዙትን የሪፖርት አይነት ማየት ይቻላል።

1.4. ወደ መረጃ ቋቱ እንዴት ይገባል?


የትኛውንም ሪፖርት ለማየትና ከመነሻው ገፅ ወደ የትኛውም ሌላ ገፅ ለመሄድ የመግቢያ ስም (user name) እና
የይለፍ ቃል (Password) አንዲያሰገቡ ይጠየቃሉ፡፡ የመግቢያ ስም እና የይለፍ ቃል የሚሰጣቸው ከሰራተኛው የስራ
ድርሻ አንጻር የመረጃ ቋቱን መጠቀም የሚያስፈልጋቸው ሰራተኞች ናቸው። አሁን ባለው አሰራር ለሰራተኞች
የመግቢያ ስም እና የይለፍ ቃል የሚሰጠው በዋናነት በቅርብ ሃላፊዎች በጽሁፍ ሲቀርብ እና ለዋናው መስሪያ ቤት
ሲቀርብ ነው።

1.5. የመረጃ ቋቱ ተጠቃሚዎች እነማን ናቸው?


የመረጃ ቋቱ ተጠቃሚዎች በአምስት ቡድን ይከፈላሉ። እነሱም Regular User፣ System Administrator፣
Confidential User፣ Super User፣ እና Planning ናቸው። አንድ ተጠቃሚ ከቋቱ የሚያገኘው ሪፖርት እንደ
ተሰጠው የተጠቃሚነት መደብ ይወሰናል። ይህም እንደሚከተለው ቀርቧል

1. Regular User- የRegular User ተጠቃሚ የሚያያቸው ሪፖርቶች የ“User Management” እና


“Confidential” ፍቃድ ከሚፈልጉ ውጭ ያሉ ሪፖርቶች ሆነው የሚሰራበትን የታክስ ቅርንጫፍ መስሪያ
ቤት የተመለከቱትን ብቻ ነው።
2. System Administrator- የSystem Administrator ተጠቃሚ እንደ ሲስተም አስተዳዳሪነቱ
የተጠቃሚዎችን ሪፖርት የማየት ፍቃድ ለማስተዳደር ሁሉንም ሪፖርቶች ማየት ይችላል።
3. Confidential- የConfidential ተጠቃሚ ምስጢራዊ ተብለው የተለዩ ሁሉንም ሪፖርቶች ማየት ይችላል።
4. Super User- የSuper User ተጠቃሚ ምስጢራዊ ከሆኑ ሪፖርቶች ውጭ የሚሰራበትን የታክስ
ባለስልጣን እንዲሁም በስሩ ያሉ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶችን የተመለከቱ ሁሉንም ሪፖርቶች ማየት ይችላል
5. Planning- የPlanning ተጠቃሚ የሆነ ሰው እቅዶችን ወደ ቋቱ የማስገባት ፍቃድ አለው።

3
ክፍል ሁለት
2. የሪፖርቶች መሰረታዊ ይዘት
2.1. የአገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብን የተመለከቱ ሪፖርቶች
• የመረጃ ቋቱ በርከት ያሉ ሪፖርቶችን በክፍል በክፍል በማድረግ በዝርዝርና በጥቅል መልክ አደራጅቶ
አስቀምጧል። አንድ ሪፖርት የያዘውን መረጃ ለማግኘት የሪፖርቱን ገጽ ከከፈትን በኋላ “Selection
Criteria” በሚለው ስር የተጠየቀውን መረጃ በማስገባት “Search” የሚለውን ስንጫን ሪፖርቱን ተዘርዝሮ
እናገኘዋለን።
• በSelection Criteria ክፍል ውስጥ ሪፖርቱ እንዲያካትት የምንፈልገውን መረጃ እንደሪፖርቱ አይነት
በDrop Down፣ በ“Date Picker”፣ በ“Radio Button ” እንዲሁም በ“Text Field” መልክ ከቀረቡት
ውስጥ መምረጥ ይኖርብናል።
• በSelection Criteria ስር የኮከብ ምልክት ያለበት ቦታ በግዴታ መመረጥ ወይም መሞላት ይኖርበታል፡፡
ሌሎች ግን ከተፈለገ እንጅ የግድ አይደሉም፡፡
• አንድን ሪፖርት ካገኘን (ከከፈትን) በኋላ በሪፖርቱ በስተቀኝ ጫፍ ላይ ያለውን የተመሳቀለ የቀስት ምልክት
በመጫን ሪፖርቱን ሙሉ ስክሪን ሆኖ ማየትና መልሶ በመንካት እንደነበረው ማድረግ ይቻላል።
• Reset የሚለውን በመጫን ደግሞ ከዚህ በፊት ያደረግነውን ማጣራት በማጥፋት አዲስ ፍለጋ ማድረግ
እንችላለን፡፡
• በዚህ ክፍል ከመረጃ ቋቱ የሚገኙ የተወሰኑ ሪፖርቶችን ጥቅምና ለመክፈት የምናስገባውን የመረጃ አይነት
እናያለን።

1. Taxpayer Profile
• ይህ ሪፖርት የአንድ ግብር ከፋይን ዝርዝር መረጃ አስራ ሁለት ቦታ በመክፈል ያሳየናል።
• የሪፖርቱን ገጽ ለማግኘት እነዚህን በቅደም ተከተል ይጫኑ Home->Taxpayer Profile
• የሪፖርቱን ገጽ ከከፈቱ በኋላ ይዘቱን ለማግኘት የግብር ከፋዮን መለያ ቁጥር ማስገባት አለብዎት። እንደ
አስፈላጊነቱ “Find Taxpayer by Name” የሚለውን በመጫን በሚያገኙት አዲስ ገጽ ላይ የግብር ከፋዩን
ስም አስገብተው “Search” የሚለውን ሲጫኑ ዝርዝር ሪፖርቱን ያገኛሉ፡፡

2. List of Taxpayer by Tax Type


• ይህ ሪፖርት በእያንዳንዱ የግብር አይነት ግብር የመክፈል ግዴታ ያለባቸውን የታክስ ከፋዮች ዝርዝር የያዘ
ሪፖርት ነው።
• የሪፖርቱን ገጽ ለማግኘት እነዚህን በቅደም ተከተል ይጫኑ Home -> Detail/List Reports ->
Taxpayer Registration -> List of Taxpayer by Tax Type
• የሪፖርቱን ገጽ ከከፈቱ በኋላ ይዘቱን ለማግኘት የግብሩን አይነት አስገብተው “Search” የሚለውን ሲጫኑ
ዝርዝር ሪፖርቱን ያገኛሉ፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ በዚህ ሪፖርት ገጽ ግርጌ የሚገኙትን የሬድዮ በተኖች
በመጫን ሪፖርቱ ግብር ከፋዮ እንቅስቃሴውን ያቆመ፣ ያላቆመ፣ ወይም ለጊዜው ያቋረጠውን ብቻ ለይቶ
እንዲሰጠን ማድረግ ይቻላል።

3. List of Filers
• ይህ ሪፖርት ግብር ማስታወቂያ ያቀረቡ የታክስ ከፋዮችን ዝርዝር የሚያሳይ ነው።
• የሪፖርቱን ገጽ ለማግኘት እነዚህን በቅደም ተከተል ይጫኑ Home -> Detail/List Reports -> Filing
and Compliance -> List of Filers

4
• የሪፖርቱን ገጽ ከከፈቱ በኋላ ይዘቱን ለማግኘት የግብር ማስታወቂያ ሊቀርብለት የሚገባውን የግብር
አይነት፣መነሻ የግብር ጊዜ እና መድረሻ የግብር ጊዜ አስገብተው “Search” የሚለውን ሲጫኑ ዝርዝር
ሪፖርቱን ያገኛሉ፡፡
• እንደ አስፈላጊነቱ በዚህ ሪፖርት ገጽ ግርጌ የሚገኙትን የሬድዮ በተኖች በመጫን ሪፖርቱ በወቅቱ
ያስታወቁትን ወይም ዘግይተው ያስታወቁትን ብቻ እንዲያካትት ማድረግ ይቻላል። በተጨማሪም ሪፖርቱ
በኢ-ፋይሊንግ ወይም በማንዋል ያስታወቁትን ብቻ እንዲያካትት ማድረግ ይቻላል።

4. List of Non-Filers
• ይህ ሪፖርት ግብር ማስታወቂያ ያላቀረቡ የታክስ ከፋዮችን ዝርዝር የሚያሳይ ነው።
• የሪፖርቱን ገጽ ለማግኘት እነዚህን በቅደም ተከተል ይጫኑ Home -> Detail/List Reports -> Filing
and Compliance -> List of Non-Filers
• የሪፖርቱን ገጽ ከከፈቱ በኋላ ይዘቱን ለማግኘት የግብር ማስታወቂያ ሊቀርብበት የሚገባውን የግብር
አይነት፣መነሻ የግብር ጊዜ እና መድረሻ የግብር ጊዜ አስገብተው “Search” የሚለውን ሲጫኑ ዝርዝር
ሪፖርቱን ያገኛሉ፡፡

5. Taxpayer Financial Statements


• ይህ ሪፖርት የግብር ከፋዮችን የሂሳብ መግለጫ የሚያሳይ ነው። የዚህን ሪፖርት ገጽ ለማግኘት እነዚህን
በቅደም ተከተል ይጫኑ Home -> Detail/List Reports -> Filing and Compliance -> Taxpayers
Financial Statements
• የሪፖርቱን ገጽ ከከፈቱ በኋላ ይዘቱን ለማግኘት የግብር ከፋዮን መለያ ቁጥር፣ የመነሻ የግብር ጊዜን
እንዲሁም የመድረሻ የግብር ጊዜ አስገብተው “Search” የሚለውን ሲጫኑ ዝርዝር ሪፖርቱን ያገኛሉ፡፡
6. List of Taxpayers using Cash Register Machine
• ይህ ሪፖርት የሽያጭ መመዝገቢያ መሳርያ የሚጠቀሙ የግብር ከፋዮችን ዝርዝር የሚያሳይ ነው።
• የሪፖርቱን ገጽ ለማግኘት እነዚህን በቅደም ተከተል ይጫኑ Home -> ECX, Cost Sharing, -> List of
Taxpayers using Cash Register Machine
• የሪፖርቱን ገጽ ሲከፍቱ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳርያ የሚጠቀሙ የግብር ከፋዮችን ዝርዝር የሚያሳይ
ሪፖርት በቀጥታ ያገኛሉ። ይህን ሪፖርት ከሌሎች ሪፖርቶች የተለየ የሚያደርገው “Search” የሚል በተን
የሌለው መሆኑ ነው።
7. Daily Collection Summary
• ይህ ሪፖርት የተሰበሰበን ግብር በዋናነት በአይነት እና በቀን ለይቶ የሚያሳይ ነው።
• የሪፖርቱን ገጽ ለማግኘት እነዚህን በቅደም ተከተል ይጫኑ Home -> Detail/List Reports -> Tax
Collection Reports -> Daily Collection Summary
• የሪፖርቱን ገጽ ከከፈቱ በኋላ የግብሩን አይነት፣ የመነሻ ቀኑንና የመድረሻ ቀኑን አስገብተው “Search”
የሚለውን ሲጫኑ ሪፖርቱን ተዘርዝሮ ያገኙታል።
• በስተግራ ያለው ሪፖርት በየቀኑ የተሰበሰበውን ሁሉንም የግብር አይነት በጥቅሉ በድምር የሚያሳይ ሲሆን
በስተቀኝ ያለው ሪፖርት ደግሞ ከላይ የመረጡትን የአንዱን ግብር አይነት የየቀኑን የተሰበሰበ ገንዘብ
የሚያሳይ ነው።
8. Tax Collection by Tax Center
• ይህ ሪፖርት በተወሰነ ጊዜ የተሰበሰበን የአንድ ግብር አይነት በታክስ ቅርንጫፍ ለይቶ የሚያሳይ ነው።
• የሪፖርቱን ገጽ ለማግኘት እነዚህን በቅደም ተከተል ይጫኑ Home -> Summary and Dashboard ->
Collection Summary -> Tax Collection by Tax Center

5
• የሪፖርቱን ገጽ ከከፈቱ በኋላ የግብሩን አይነት፣ የመነሻ ቀኑንና የመድረሻ ቀኑን አስገብተው “Search”
የሚለውን ሲጫኑ ሪፖርቱን ተዘርዝሮ ያገኙታል። በስተግራ ያለው ሪፖርት በጊዜው የተሰበሰበውን ሁሉንም
የግብር አይነት በጥቅሉ በድምር በታክስ ቅርንጫፍ ለይቶ የሚያሳይ ሲሆን በስተቀኝ ያለው ሪፖርት ደግሞ
ከላይ በታክስ ቅርንጫፉ በጊዜው የተሰበሰበውን የመረጡትን የአንዱን ግብር አይነት ገንዘብ የሚያሳይ
ነው።

2.2. የጉምሩክ ገቢ አሰባሰብን የተመለከቱ ሪፖርቶች


የጉምሩክ አስተዳደር በባህሪው ከሀገር ውስጥ የግብር አስተዳደር የተለየ እንደመሆኑ መጠን የመረጃ ቋቱ ጉምሩክ
ነክ የሆኑ ሪፖርቶችን ለብቻቸው በመግቢያ ገጹ ላይ “Customs Commission” በሚል ርዕስ ስር በመሰብሰብ
ዘርዝሮ አስቀምጧቸዋል። እነዚህ ሪፖርቶችን ከቋቱ ለማግኘት የምናስገባውን የመረጃ አይነት እና የሚይዙትን
የመረጃ ይዘት ለማየት ያህል ከዚህ ቀጥሎ የተወሰኑት ተዘርዝረው ቀርበዋል፡፡

1. eCMS Payment Details

ይህ ሪፖርት እያንዳንዱን ከገቢና ከወጪ ንግድ ጋር በተያያዘ የተከፈሉ ጉምሩክ ነክ ክፍያዎችን በዝርዝር
ያሳየናል። ክፍያዎችን በዝርዝር ለማግኘት በሪፖርቱ ገፅ ላይ የሚገኙትን መረጃወች መሙላት ወይም መምረጥ
ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም የጉምሩክ ጣቢያውን ስም እንመርጣለን፣ ክፍያው የሚመለከተውን ጉዳይ
እንመርጣለን፣ ክፍያ የተፈጸመበትን የመነሻ እና የመድረሻ ቀን ከመረጥን በኃላ “Search” የሚለውን ስንጫን
ሪፖርቱን ተዘርዝሮ እናገኘዋለን።

2. eCMS List of Declarations

ይህ ሪፖርት እያንዳንዱን የእቃ ዲክላራሲዮን በዝርዝር ያሳየናል። እያንዳንዱን የእቃ ዲክላራሲዮን በዝርዝር
ለማግኘት በሪፖርቱ ገፅ ላይ የሚገኙትን መረጃወች መሙላት ወይም መምረጥ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም
የጉምሩክ ጣቢያውን ስም ይህን “Dropdown” ምልክት በመንካት እንመርጣለን፣ የዲክላራሲዮኑን የመነሻ እና
መድረሻው ቀን እንመርጣለን፣ የገቢና የወጪ እቃ ሞድ እንመርጣለን፣ ሳዱ (SAD) ያለበትን ሁኔታ በመምረጥ
“Search” የሚለውን ስንጫን ሪፖርቱን ተዘርዝሮ እናገኘዋለን።

3. ECMS List of Importers/Exporters


ይህ ሪፖርት በገቢና በወጪ ንግድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን መሰረታዊ መረጃ በዝርዝር የሚያሳይ ነው።
የዚህን ሪፖርት ይዘት ለማግኘት በመጀመርያ ድርጅቱ የተሰማራበትን የንግድ ዘርፍ ከተዘረዘሩት መካከል
እንመርጣለን፣ በመቀጠል የምንፈልገው ድርጅት እንቅስቃሴውን ያቆመ ወይም ያላቆመ መሆኑን መርጠን
“Search” የሚለውን ስንጫን ሪፖርቱን ተዘርዝሮ እናገኘዋለን።

4. ECMS List of Transitors/Declarants


ይህ ሪፖርት የጉምሩክ አስተላላፊዎችን መሰረታዊ መረጃ በዝርዝር የሚያሳይ ነው። የዚህን ሪፖርት ይዘት
ለማግኘት በመጀመርያ የጉምሩክ አስተላላፊው እንቅስቃሴውን ያቆመ ወይም ያላቆመ መሆኑን
እንመርጣለን፣ የመነሻ እና የመድረሻ ቀን መርጠን “Search” የሚለውን ስንጫን ሪፖርቱን ተዘርዝሮ
እናገኘዋለን።

6
ክፍል ሶስት
3. ሪፖርት ማስተካከያ መንገዶች
በዚህ ክፍል ከመረጃ ቋቱ የሚገኙ ሪፖርቶችን መፈለግ እንዲሁም “Search Bar” እና “Actions” ሜኑን በመጠቀም

እንደምንፈልገው ኤዲት (edit) ማድረግ ከሚያስችሉን መንገዶች የተወሰኑትን እናያለን ።

3.1. መረጃ ማጣራት (Data Filtering)


• የመረጃ ቋቱ አንድን ርፖርት ካገኘን በኋላ በሁለት መንገድ እንድናጣራ ያስችለናል።

• የመጀመርያው ከታች የሚታየውን “Search Bar” በመጠቀም ነው።

• በዚህ “Search Bar” ላይ በስተግራ ያለውን የቀስት ምልክት በመንካት ከተዘረዘሩት የሪፖርቱ የአምድ
[column] ስሞች መካከል የምንፈልገውን አምድ በመምረጥና አምዱ እንዲይዝልን የምንፈልገውን
ቀጥሎ ባለው ባዶ ቦታ ላይ በመጻፍ Go የሚለውን ስንጫን ሪፖርቱ እንደሚፈለገው ሆኖ እናገኘዋለን ።
በማንኛውም ወቅት በዚህ መልኩ የተጣራ ሪፖርት ሁሉንም ወይም ሌላ መረጃ እንዲያሳይ ከተፈለገ
ከ“Search Bar” ስር ያለውን የx ምልክት መጫን ይኖርብናል፡፡ ይህ ካልሆነ በሁሉም ወቅት የምናየው
ሪፖርት ከላይ የተጠቀምነውን የሪፖርት ማጣሪያ ብቻ የሚከተል ይሆናል፡፡

• ሁለተኛው መንገድ Actions Menuን በመጫን “Filter” የሚለውን ስንመርጥ አንድ ሳጥን ያመጣልናል።

• እሱን በመጠቀም በመጀመሪያ “Column” የሚለውን ራዲዮ በተን እንመርጣለን

• ከዚያም “Column” ከሚለው ስር ማጣራት የምንፈልገውን “Column” እንመርጣለን። በመቀጠል


“Operator” ከሚለው ስር የምንፈልገውን “Operator” በመምረጥና Expression ከሚለው ስር
የምንፈልገውን ነገር በመጻፍ “Apply” የሚለውን ስንነካ ሪፖርቱ እንደምንፈልገው ተስተካክሎ ያሳየናል።

3.2. በአንድ ገጽ የሚኖረውን የመስመር ብዛት መወሰን (Rows per Page Limit)
• የመረጃ ቋቱ ሪፖርቶች ሲሰሩ በ 1 ገጽ 50 Rows እንዲያሳዩ ሆነው የተዘገጁ ናቸው። ነገር ግን የመረጃ ቋቱ
በአንድ ገጽ እንዲኖር የምንፈልገውን የሪፖርቱን ዝርዝር የመስመር (row) ብዛት ከ50 በላይም በታችም
ማድረግ ያስችለናል።

• ይህን ለማድረግ ሪፖርቱን ካገኘን በኋላ “Actions” ውስጥ “Format” ቀጥሎም Rows per Page
የሚለውን በመንካት በአንድ ገጽ ሊኖር የሚችለውን የመስመር (row) ብዛት መወሰን እንችላለን።

• ሪፖርቱ ከአንድ ገጽ በላይ የያዘ በሚሆንበት ጊዜ ከሪፖርቱ ግርጌ በስተቀኝ በኩል ከቁጥሮቹ ጎን ያለውን
“Next” እና “Previous” የሚለውን ቀስት በመጫን ወደፊት እና ወደኋላ መሄድ ይቻላል።

• በአንዳንድ ሪፖርቶች ላይ በአንድ ገጽ ላይ ሊኖር የሚገባውን የዝርዝር መጠን ለመወሰን የሚያስችለንን


ፊልድ ፊትለፊት ልናገኝ እንችላለን። ለምሳሌ “List of Filers” የሚለውን ሪፖርት ብናይ በአንድ ገጽ ላይ
ሊኖር የሚገባውን የዝርዝር መጠን “Search Bar” ላይ እንድንወስን ያስችለናል።

3.3. የሪፖርቱን አምድ ማስተካከል (Column Editing)


• የመረጃ ቋቱ አንድ ሪፖርት ከያዛቸው አምዶች መካከል የተወሰኑትን ለመቀነስ ወይም ለመጨመር
እንዲሁም አደራደራቸውን ለማስተካከል ያስችላል።

7
• ይህን ለማድረግ Actions የሚለውን በመጫን Columns የሚለውን በመምረጥ አምዶቹን
የምናስተካክልበትን ሳጥን ይሰጠናል።

• የሳጥኑ የግራ ክፍል ሪፖርቱ የማይዛቸውን አምዶች የሚያሳይ ሲሆን የቀኝ ክፍል ደግሞ ሪፖርቱ
የሚይዛቸውን አምዶች የሚያሳይ ነው። በሁለቱ መካከል ያሉትን በጎን የተሰመሩ የቀስት ምልክቶችን
በመጠቀም አምዶቹን ከአንዱ ወደ ሌላው በመውሰድ እንደምንፈልገው ማድረግ ይቻላል። በተጨማሪ
የተዘረዘሩት አምዶች (columns) እንደምንፈልገው እንዲደረደሩ ለማድረግ በሳጥኑ በስተቀኝ መጨረሻ ላይ
ያሉትን ወደላይና ወደታች የሚያሳዩ የቀስት ምልክቶችን በመጠቀም የምንፈልገውን አምድ ወደ ላይና ወደ
ታች እንዲሄድ ማድረግ ይቻላል፡፡

• የምንፈልጋቸውን አምዶች በመምረጥና ቅደምተከተላቸውን ካስተካከልን በኋላ Apply የሚለውን በተን


ስንጫን ሪፖርቱ እንደምንፈልገው ተስተካክሎ ማየት እንችላለን፡፡

3.4. ቅደም ተከተል ማስያዝ (Sorting)


• የመረጃ ቋቱ አንድ የሪፖርት አምድ የያዘውን መረጃ ቅደም ተከተል በሁለት መንገድ ማስያዝ ያስችላል።

• የመጀመርያው ሪፖርቱን ካገኘን በኋላ የአምዱን ስም ስንነካ አራት ንኡስ ሜኑ የያዘ “Column Heading
Menu” ያሳየናል። ከተዘረዘሩት ውስጥ እንደምርጫችን “Sort Ascending” ወይም “Sort Descending”
የሚለውን በመምረጥ ማስተካከል ይቻላል።

• ሌላኛው መንገድ “Actions” የሚለውን በመጫን Data ከዚያም Sort የሚለውን ስንመርጥ ወደ ቅደም
ተከተል ማስተካከያ ገጽ ይወስደናል። ከዚያም “column” ከሚለው እንዲደረደር የምንፈለገውን አምድ
በመምረጥ፣ “Direction” ከሚለው እንደምርጫችን “Ascending” ወይም “Descending” የሚለውን
በመምረጥ፣ በመጨረሻ “Null Sorting” ከሚለው ስር አምዱ ውስጥ ያለ፣ ነገር ግን መረጃ የሌለው ሴል
ከላይ ወይም ከታች እንዲሆን በመወሰን Apply የሚለውን በተን በመጫን ሪፖርቱ እንደፈለግነው ተቀይሮ
እናገኘዋለን፡፡

3.5. ቻርት ማዘጋጀትና ኮፒ ማድረግ (Charting & Snipping)


• የመረጃ ቋቱ ሪፖርትን ወደ ምስል ወይም ቻርት መቀየር ያስችላል።

• ይህን ለማድረግ ሪፖርቱን ካገኘን በኋላ Actions የሚለውን በመንካት Chart የሚለውን እንጫናለን ፡፡
ከዚያም በሚመጣው የቻርት ማስተካከያ ገጽ ላይ የሚጠይቀንን እንደሚከተለው እናስገባለን፥

 Chart Type የሚለው ላይ የቻርት ዓይነት እንመርጣለን።


 Label የሚለው ላይ የምንፈልገውን Column እንመርጣለን

 Value የሚለው ላይ የምንፈልገውን ሌላ Column እንመርጣለን

 Axis Title for Label የሚለው ላይ የLabel ስም እንሰጣለን።

 Axis Title for Value የሚለው ላይ የValue ስም እንሰጣለን።

 Function የሚለው ላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ ቻርቱ እንዲያሳየን የምንፈልገውን እስታቲስቲክስ


እንመርጣለን፡

 Sort የሚለው ላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ የቻርቱን ባሮች ቅደም ተከተል እንደምንፈልገው


እንመርጣለን

8
• በመጨረሻ Apply የሚለውን በተን ስንጫን ቻርቱን እናያለን፡፡ ነገር ግን ይህን ቻርት ኮፒ ማድረግ አይቻልም
። ኮፒ ማድረግ ከፈለግን የኮምፒዩተሩን Snipping Tool መጠቀም ይኖርብናል። ይህን ለማድግ በመጀመርያ
ኪቦርዳችን ላይ “Window Logo”ን “Shift”ን እና “S”ን በጋራ እንጫናለን እሱ የSnipping Window
ያመጣልናል:: የ4 ማእዘን ምልክቱን በመምረጥ ቻርቱን ሴሌክት ካደረግን በኋላ ወደምንፈልገው ፋይል
ወስደን paste በማድረግ ቻርቱን ለምንፈልገው ሪፖርት መጠቀም ይቻላል።

• ቻርቱን መቀየር ብንፈልግ ከቻርቱ በላይ ያለውን “Edit” የሚለውን በመንካት ወደ ቻርት ማስተካከያው
ገጽ ይወስደናል እዚያ ላይ የምንፈልገውን ማስተካከያ በማድረግ ሌላ ሪፖርት ማግኘት እንችላለን።

• ከቻርቱ በላይ ያለውን የ x ምልክት በመንካት ቻርቱን ማጥፋትና ወደ ሪፖርቱ መመለስ እንችላለን።

3.6. አዲስ አምድ መጨመር [Compute]


• የመረጃ ቋቱ አንድ ሪፖርት የያዛቸውን አምዶች [Columns] በመመርኮዝ ሌላ አምድ ሪፖርቱ ላይ
መጨመር ያስችላል። ይህ በተለይ ቁጥር ነክ መረጃ ይዘው ለሚመጡ ሪፖርቶች የሚውል ነው፡፡

• ይህን ለማድረግ በመጀመርያ Actions የሚለውን በመጫን Data ከዚያም Compute የሚለውን
እንመርጣለን፡፡

• ከዚያም ስሌት የምንሰራበትን ሳጥን ይሰጠናል። እዚያ ላይ፥

 Computation Heading የሚለው ውስጥ የአዲሱን አምድ (Column) ስም እንጽፋለን


 Format Mask የሚለው ላይ የምንፈልገውን የቁጥር Format ከተዘረዘሩት አራት አይነት
አማራጮች መካከል እንመርጣለን።
 Computation Expression የሚለው ውስጥ ስሌቱ የሚመሰረትባቸውን አምዶች (Columns)
እና የስሌት መሳሪያዉን ከስሩ የተዘረዘሩትን columns, keypad እና Functions በመጫን
እናስገባለን።
 በመጨረሻ Apply የሚለውን በተን ስንጫን ከሪፖርቱ በቀኝ መጨረሻ ላይ አዲስ አምድ ተካቶ
እናያለን፡፡

3.7. ማቅለም [Highlight]


• የመረጃ ቋቱ ከሪፖርቱ ላይ የምንፈልገውን መረጃ በቀለም በማጉላት ማየት ያስችላል።

• ይህን ለማድረግ Actions የሚለውን በመጫን Format ከዚያም Hightlight የሚለውን በመምረጥ
ወደማስተካከያው ገፅ እንመጣለን።

• ከዚያም

 Name የሚለው ላይ የፈለግነውን ስም እንጽፋለን።

 Sequence የሚለው ላይ ቁጥር እንጽፋለን?

 Enabled የሚለው ላይ “yes” የሚለውን እንመርጣለን.

 Highlight Type የሚለው ላይ እንዲደምቅ የምንፈልገው ሙሉ ረድፍ (Row) ወይም ሴል መሆኑን


እንመርጣለን

 Background Color: የሚለው ላይ የBackground ቀለም እንመርጣለን

9
 Text Color : የሚለው ላይ የፊደሎችን ቀለም እንመርጣለን

 ከዚያም እዚህ Highlight Condition በሚለው ስር

 Column ከሚለው የምንፈልገውን አምድ (Column) እንመርጣለን


 Operator ከሚለው የምንፈልገውን እንመርጣለን
 Expression ከሚለው ከላይ የመረጥነው አምድ ከያዛቸው መካከል የምንፈልገውን መረጃ
እንመርጣለን

 ከዚያም Apply የሚለውን በመጫን ከሪፖርቱ ውስጥ በቀለም ጎልቶ እንዲወጣ የተፈለገውን
በማጉላት ማየት ይቻላል፡፡

3.8. ሪፖርት ማውረድ (Downloading)


• የመረጃ ቋቱ ሪፖርትን ማውረድ (Download ማድረግ) ያስችላል።

• ይህን ለማድረግ Actions የሚለውን በመጫን Download የሚለውን እንመርጣለን ፡፡

• ከዚያም 4 ምርጫዎችን እናገኛለን፡፡ እነሱም

 CSV፡ ሪፖርቱን በExcel ፋይል መልክ ለማውረድ ያስችላል።


 HTML፡ ሪፖርቱን በHTML ፋይል መልክ ለማውረድ ያስችላል።
 Email፡ ሪፖርቱን በኢሜይል ለመላክ ያስችላል።
 PDF፡ ሪፖርቱን በPDF ፋይል መልክ ለማውረድ ያስችላል።

ለምሳሌ CSV የሚለውን በመምረጥ ሪፖርቱን አውርደን ብንከፍት ሪፖርቱ የሚከፈተው Excel ፋይል መስሎ ነው።
ነገር ግን የፋይሉ አይነት CSV ስለሆነ ሴቭ ለማድረግ ስንሞክር ስለ ፋይሉ ፎርማት ማስታወሻ መልእክት እናገኛለን።
በመሆኑም እዚህ ፋይል ላይ የፈለግነውን ለመስራት ወደ Excel format መቀየርና መጠቀም ተመራጭ ነው። ይህን
ለማድረግ “Save As” ብለን የምንፈልገውን ፎልደር ከመረጥን በኋላ “Save as type” ላይ “Excel Workbook”
የሚለውን በመምረጥ “Save” ማድረግ አለብን። ይህ ሴቭ ያደረግነው ፋይል የExcel format የያዘ ነው። እሱን
እንደማንኛውም የExcel ፋይል መጠቀም እንችላለን ።

ተጨማሪ ማብራርያ ለማግኘት የገቢዎች የመረጃ ቋት አጠቃቀም የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ጠይቀው ይመልከቱ።

መልካም ስራ

10

You might also like