Walle

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 8

በኢፌዴሪ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

በፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከክልሎች ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ጋር ለሚያደርገው ግንኙነት የአሰራር ሥርዓት

ለመዘርጋት የተዘጋጀ (Guide Line)

ታህሳስ 2014 ዓ.ም


አዲስ አበባ

መግቢያ

የአንድ አገር መንግስት የሚነድፋቸውን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በማስፈጸም ረገድ ሲቪል ሰርቪሱ ቁልፍ መሳሪያ
ነው፡፡ ፖሊሲዎቹና ስትራቴጂዎቹ ተተግብረው በዜጎች ዘንድ እርካታን የማረጋገጣቸው ጉዳይ በዋነኛነት በሲቪል ሰርቪሱ
ወይም በመንግስት መዋቅሩ የመፈጸም/ማስፈጸም አቅም ላይ የሚወሰን ይሆናል፡፡ መንግስት አገርንና ህዝብን የሚመራ

0
ከመሆኑ አንጻር የነደፈውን ሀገራዊ ዕቅድ በብቃት ለማሳካትና የህዝቡን ጥያቄዎችንም በአግባቡ ለመመለስ እንዲችል
የመንግስት የመፈጸም/የማስፈጸም አቅም ቢቻል የዜጎች የፍላጎት ደረጃ ከሚጠይቀው ቀደም ያለ አለበዚያም ደግሞ
በእኩል የሚራመድ እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡

ከዚህ አንጻር ባለፉት አስራአምስት ዓመታት ሲቪል ሰርቪሱን በማጠናከር የመንግስትን የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት
እንዲቻል የተለያዩ የማሻሻያ ፕሮግራሞች ተነድፈው ሲተገበሩ ቆይተዋል፡፡በተለይ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 89 (4) በእድገት ወደ ኋላ ለቀሩ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች፣ ህዝቦች መንግስት ልዩ ድጋፍ
ያደርጋል በሚለው ድንጋጌ በተሰጠው ሀላፊነት መሰረት በነዚህ ክልሎች የመደገፍ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡
ሀገራችን የጀመረችውን ለውጥ በተሟላ ሁኔታ ለማሳካት በልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ተገቢውን እገዛ በወሳኝ
መስኮች በማድረግ በክልሎች መካከል ተመጣጣኝ የኢኮኖሚ፣ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ እድገት በማምጣት
ድኅነትንና ኋላቀርነትን በመቀነስ በየደረጀው ያለውን ኅብረተሰብ የለውጥና የልማቱ ተጠቃሚ ማድረግ
ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን አምኖ ለዚህ ዓላማ ስኬት ከፌደራል እስከ ክልሎች ባሉት
የተለያዩ የስልጣን እርከኖች የማስፈፀምና የመፈፀም አቅም ግንባታ ስራ በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ ተናቦ
መተግበሩ ለለውጡ ውጤታማነትና ቀጣይነትና ወሳኝ ነው፡፡
በመሆኑም ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎችን ዳይሬክቶሬቱ በለውጥ ስራ አመራር በሰው ሀብት ልማት ስራ እና
በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚደረገውን ክትትልና ድጋፍ አጠናክሮ በመቀጠል የአመራሩንና የሰራተኛውን
አቅም በመገንባት የህብረተሰቡን (የዜጋውን) ተሳትፎ በማረጋገጥ የለውጥ ስራ አመራሩን በተገቢው
በመተግበር የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ በልዩ ድጋፍ ክልል ድጋፍ ሰጪ
ባለሙያዎችንና ተፈላጊውን ግብዓት በማሟላት ህገ-መንግስታዊ ግዴታውን በመወጣት በክልሎቹ አንጻራዊ
ለውጥ ለማምጣት እየሰራ ይገኛል ።በመሆኑም ይህንን ለውጥ ያመጣ ዘንድ

በተዋረድ የአመራር ግንኙነት ስርዓት የሚመራበት ራሱን የቻለ የግንኙነት ስርዓት ማውጣትና ገቢራዊ
ማድረግ በማስፈለጉ ይህ የግንኙነት ስርዓት ተዘጋጅቷል ፡፡በልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች አቅም በማጎልበት
በሌሎች ክልሎች የተመጣጠነ እድገት ደረጃ ላይ ለማድረስ የሰው ኃይልና ሎጀስቲክ ድጋፍ አጠናክሮ
በማስቀጠል ክልሎች በአጭር ጊዜ ራሳቸውን የሚችሉበትን አቅም ለመፍጠር የሚያስችል አሠራር መዘርጋት
በማስፈለጉ በእስካሁኑ በነበረው የድጋፍ አሠጣጥ ወቅት ይታዩ የነበሩ የአሠራር ጉድለቶችን በትክክል በመለየት
ችግሮችን ሊቀርፍ የሚችል አሰራርሥርዓት በመዘርጋት (Guide Line) መልክ ተዘጋጅቶ እንደሚከተለው
ቀርቧል፡፡

የግንኙነት ስርዓት አላማ (Guide Line)

 የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና በክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ መካከል ግልጽ


አሳታፊነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት የስራ አተገባበር እንዲኖር /ሁሉም ሃላፊነቱን
ድርሻውን እንዲወጣ ማስቻል

1
 የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከክልል ሲቪል ሰርቪስ አመራሮች ለተሰጣቸው ተልኮ የሚመጥን
ብቃት ያለው አመራር ተከታታይና ቀጣይነት ያለው ስምሪት እንዲካሄድ ማስቻል ፡፡

 በክልሎች መካከል የልምድ ልውውጦችን በማካሄድ በመካከላቸው የሚታየውን የአፈጻም ወጣ-


ገባነት፡ የጥራት ልዩነቶችን ማጥበብና ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖር ማድረግ፡፡

 ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች እና ከፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተገቢውን ክትትል እና


ድጋፍ በተናበበ መልኩ ተደራሽ እንዲደረግላቸው

 ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች በተደረገላቸው በተቀናጀ አግባብ ክትትል እና ድጋፍ አገልግሎት


አሰጣጣቸው ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ የተገልጋይ ቅሬታ እና አቤቱታን ለማስወገድ

 ተቋማትን ቅንጅታዊ የጋራ አቅሞችን በማጣመር ማለትም በሰው ሃብት; በአቅም


ግንባታ ዘርፍ በትስስር ወደ ተዋጣለት አፈፃፀም ደረጃ ለማሳደግ

የግንኙነት ስርዓት አስፈላጊነት

የዚህ የግንኙነት ስርዓት ፌዴራል በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንና በክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ጋር የክልሎች
የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ማሳደግና በጋራ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ የግንኙነት አግባብ ተፈጥሮ የጋር
ግቦች ለማሳካት የተዘጋጀ የግኙነት ስርዓት (Guide Line) ነው፡፡

የአመራር ግንኙነት መድረኮች የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና የክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የሚከተሉት
ናቸው፡-

 የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

 የክልልሎች ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ፣

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ግንኙነት መድረክ ተሳታፊ

 የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር

 የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ም/ ኮሚሽነር

 የስትራቴጅክ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት

2
 የሰው ኃብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት

 ልዩ ድጋፍ ይሬክቶሬት

 እቅድ ዳይሬክቶሬት

 ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
የክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ግንኙነት መድረክ ተሳታፊ

 የክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ

 የክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ም/ኃላፊ

 ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የእቅድ ዳይሬክቶሬት

የግኙኝነት አግባብ

 የግንኙነት መድረክ በየ ሩብ ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን


የመጀመሪያ የ 3 ወር የግንኙነት መድረክ በማዘጋጀት ከክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር
ሲሆን የውይይት ቦታውም አመች በሆነ ከባቢ ተግባራዊ ይሆናል

 ቀጣይ የግንኙነት መድረክ ፈቃደኛ በሆነ ክልል አዘጋጅ ሲሆን ፈቀደኝነት ከለለ ግን
በመድረክ የተሰጠው ክልል እንዲያዘጋጅ ይደረጋል የውይይት ቦታውም አዘጋጁ
በሚወስነው ቦታ ይሆናል፡፡

የግኙኝነት መድረኩ ተግባርና ኃላፊነት

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ግንኙነት ስርዓት መሰረት የሚከተሉት ዝርዝር ተግባርና ሀላፊነቶች
ይኖሩታል

 በፌደራሉ በሲቪል ስርቪስ ኮሚሽን ፖሊሲዎች፣ ሕጎችና ስትራቴጂዎች ፣ደንብና


መመሪያ ላይ ተቀራራቢ የአፈፃፀም ደረጃ እንዲኖር የጋራ መግባባት ይፈጥራል፤

 በሁሉም የለውጥ መሳሪያዎች አተገባበር ላይ በቂ ግንዛቤ በመያዝ የለውጥ መሳሪያዎችን


አስተሳስሮ በመተግበር የጋራ መግባባት ይፈጥራል ፡፡

3
 በጋራ የተከናወኑ ተግባራትን አፈጻጸም በመገምገም ጥንካሬና ክፍተቶችን ይለያል
ለቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ፡፡

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የበላይ አመራር ሥልጣንና ኃላፊነት

 የአመራር ግኝኙነት ኮሚቴ ጋር ግልፅ ውይይት በማድረግ በሂደቱም ሆነ በውጤቱ ላይ


የጋራ ግንዛቤ እንዲያዝ ያደርጋል፡፡

 የአመራር ግኝኙነት መድረክ ኮሚቴ አቅም በላይ የሆኑ ጉዳዮች ሲቀርቡለት አፋጣኝ
ምላሽ ይሰጣል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡

 የአመራር ግኝኙነት መድረክ በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ መሠረት እንዲፈጸምና


እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ክትትል ያደርጋል፤

 የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንና በክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮዎች መካከል ምርጥ
ተሞክሮዎችና የልምድ ልውውጥ በማስፋት የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል ያደርጋል

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የግንኙነት መድረክ አጀንዳዎች

 የክልሎች የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል

 በአገልግሎት አሰጣጥ ጥንካሬና ድክመት ይገመግማል

 ለልዩ ድጋፍ ቦርድ የሚቀርቡ የ 6 ወር እና የአመታዊ ሪፖርቶችን ያዘጋጃል

 የቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጠል


ከፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሚጠበቅ ተግባራት

 ደረጃውን የጠበቀ የመስክ ተሸከርካሪ መኪና ከሁለት ስኮርት ጎማ ከበቂ ነዳጅና ቅባት
ጋር እንዲሁም የተቋሙን ተልዕኮ ለመወጣት ብቁና ዝግጁ የሆነ በስነ-ምግባሩም
ለክልሎች አርኣያ መሆን የሚችል ባለሙያና አሽከርካሪ መመደብ፤
 የክልል ከፍተኛ አመራርን በማስፈጸም አቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ ትኩረት እንዲሰጡ
የስልጠና፣ ድጋፍና ክትትል ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል፤ በጋራ የዓመቱን ድርጊት
መርሃ-ግብር አውጥቶ ተግባራዊ ማድረግ
 በልዩ ደጋፍ ቦርድ በሚደረገው ድጋፍና የሚያጋጥሙ ችግሮችን በማንሳት እልባት
እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ መስራት፤
 ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልል ከአጎራባች ክልሎች ጋር በተቀናጀ መልኩ ድጋፍ እንዲሰጡ
የማድረግ ሥራ መስራት፤ መከታተል፣ በምክክር መድረክ ላይ አፈፃፀሙን መገምገም፤
 ክልሎች በየወሩ በሪፎርም ላይ የሚሰጠው ድጋፍ ሂደት የሚያሳይ ሪፖርት እንዲልኩ
በማድረግ ክፍተትን መሠረት ያደረገ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፤
 በየዓመቱ የፍላጎት የዳሠሣ ጥናት እንዲካሄድ ማድረግ
4
 በየ 3 ወሩ የክልል የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አመራሮች የጋራ ምክክር መድረክ መፍጠር፤
 ሁሉም ክልል የፌዴራል መስሪያ ቤቱ የሚያደርገውን የአመራር ስልጠና፣ሱፐርቪዥን
እና ሌሎችንም አውቆ በዝግጅት ምዕራፍ በዕቅድ እንዲያካትት የዓመት ድርጊት መርሃ-
ግብሩን ቀድሞ ማሣወቅ፤
 በልዩ ድጋፍ ክልሎች የሚሰጠው ድጋፍ በውጤት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ማድረግ፤
 የባለሙያዎች አቅም ክፍተት በማየት ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ፤
 የኮሚሽኑ የሥራ ባህሪ ከፍተኛ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ተግባር እንዲያከናውኑ ለተላኩት
ባለሙያዎች ከ 2 ዓመት በላይ ላገለገሉት በልዩ ማበረታቻ መልክ የትምህርት እድል
ማመቻቸት፤
 እንደ አስፈላጊነቱ ባለሙያዎችን በልዩ ድጋፍ ክልሎች እያዘዋወሩ ማሰራት

ልዩ ድጋፍ ከሚሽ ክልሎች ሲቪል ሰርቪስ ቢሮዎች የሚጠበቅ ተግባራት


 የተመቻቸ የሥራ ካባቢን መፍጠር፤
 የተላከውን አቅም በአግባቡ የመጠቀም፤
 ለክልሎች የሚሰጥ ስልጠና በቅድሚያ በተያዘው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት በክልሉ
ተዘጋጅቶ በሚላከው ፕሮፖዛል ላይ በመመስረት ይሆናል፤
 ክልሉን አቅም በማሳደግ የተመጣጠነ እድገት ላይ ለመድረስ የሚያስችል ተነሳሽነት
በአመራሩም ሆነ በሠራተኛው መካከል መፍጠር፤
 ክልሉን በአጭር ጊዜ ከድጋፍ እንዲወጣ የጋራ ስትራቴጂ ነድፎ መንቀሳቀስ፤
 ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ዋና ዋና ክፍተቶቻቸውን የመለየት፤
 ለእውቀት ሽግግር ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፤
 የሚላኩ ግብዓቶችን (የስልጠና ገንዘብ) አጠቃቀም ላይ የመንግስትን የፋይናንስ ህግና
ደንብ የተከተለ ሆኖ በአግባቡ እንዲፈፀም አቅም መፍጠር፤
 የተሰጠው ድጋፍ የተገኘውን ውጤት በዳሠሣ ጥናት በማረጋገጥ የተዘጋጀውን ሠነድ
ለሚመለከታቸው አካላት በወቅቱ በመሸኛ መላክ
 ምርጥ ተሞክሮዎችን በባለሙያዎች በመደገፍ ቀምሮ የማስፋት፤
ከአጎራባች ክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የሚጠበቅ ተግባራት
 በሪፎርም በሰው ሀብትና በአገልግሎት አሰጣጥ ያላቸው ተሞክሮ ለክልሎቹ ማስፋት፤
 ከፌዴ.ሲ.ሰ.ኮ. ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች ጋር በጋራ ሊሰራ የሚችሉ ባለሙያዎችን
መድበው በቡድን አግባብ ተደራጅተው በጋራ ከማቀድ ጀምሮ እስከ አፈፃፀም ተገቢውን
ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤
 የልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች ወደ ተመጣጠነ እድገት ደረጃ ላይ መምጣት ለክልሎቻቸው
እድገት ያለው አስተዋጽዖ ከፍተኛ መሆኑንና እድገታቸው በቀጨጨ መጠን ለክልላቸው
እድገት ቀጥተኛ ተጽዕኖ እንዳለው ጽኑ እምነት ኖሮ በቁርጠኝነት ድጋፉን ማስቀጠል፤

ከድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች የሚጠበቅ ተግባራት

የልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች ከደረሱበት ተመጣጣኝ የእድገት ደረጃ ላይ ለማድረስ ራዕይ ሰንቆ የዜግነት
ግዴታዉን ለመወጣት በቁርጠኝነት መነሳት፤

5
 የድጋፍ አቅሙን በየጊዜው በማጎልበት በክልሉ ለሚሰጠው ድጋፍ ተሰሚነት ያለው
ባለሙያ መሆን፤
 በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ተቋማትን ለመገንባት ቁርጠኛ አመለካከት የያዘና በማስፈጸም
አቅም ግንባታ ተግባራትን ለማከናወን ዋነኛ መሣሪያ መሆኑን በማመን ድጋፍ
ለመስጠት በተቀናጀ አግባብ እራሱን ከቴክኒክ ቡድኑና ለድጋፍ ከወጡት ባለሙያዎች
ጋር አደራጅቶ ለሌሎች አርኣያ ለመሆን ዝግጁ መሆን፤
 የሚሰጠው ድጋፍ ውጤት ላይ ያተኮረ እንዲሆን ማድረግ፤

6
7

You might also like