Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 11

የተሻለ አስተራረስ

ለተሻለ መጻኢ ጊዜ

የUTZ መመሪያ ሰነድ


የመህበሩ አባላት ስልጠና (ነሐሴ 2016 እትም 1።0)
በUTZ የተመሰከረ ወሳኝ የአሰራር ደንብ ለማህበር እና ለፈርጀ ብዙ ማህበራት (ዕትም 1.1) ብቃት ማረጋገጫ
ውስጥ እንደሚጠይቀው የስልጠና ፕሮግራም አዘገጃጀት መመሪያ፡፡

ይህ መመሪያ ሰነድ በUTZ ወሳኝ የአሰራር ደንብ ዝርዝር ርዕሶች አፈፃፀምን ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀው የሰነዶች
ስብስብ አንዱ አካል ነው፡፡ ይህ ሰነድ ታቅዶ የተሰራው ለአርሶ አደሩ ማህበራት እና ለሰርተፍኬት ሂደቱ ሙያዊ እገዛ
ለሚሰጡ ባለሞያዎች ነው

ስልጠና ለበለጠ በስልጠና እና


ዘላቂ አመራረት በግንዛቤ
እና ንግድ ማስደጊያ
የሴቶችን የስልጠና
አስተዳደር ፕሮግራማ
ይመራል ተሳትፎ መዝገብ
ማመቻቸት መያዝ

የአርሶ አደሩ
ፍላጎት በተሳካ
ሁኔታ ማሟላት
ሰልጠና
በUTZ ፕሮግራም ውስጥ ስልጠና ወሳኝ ነው፡፡ የአርሶአደሮች
ስልጠና ለተሻለ ግብርና እና ቢዝነስ አስተዳደር፣ ምቹ የስራ ሁኔታ
እና ለተሻለ የተፈጥሮ ጥበቃ ይመራል በተጨማሪም ግብርናውን
በይበልጥ በቁጠባ፣ ማህበራዊ እና ተፈጥሯዊ ዘላቂነት ያበቃል፡፡

የUTZ አሰራር ደንብ በሚጠይቀው መሰረት በሁሉም


የUTZ የአሰራር ደንብ በያዙ ሀሳቦች ላይ ማህበራት
ሳጥን 1 አባላቶቻቸውን ማሰልጠን(ጂ.ኤ.19)፡፡ ለማህበር አባላት እና ለማህበር አባል
ሰራተኞች እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው ስለ ጥሩ የስራ ሁኔታ ማህበራት ግንዛቤ
መጨመር አለባቸው(ጂ.ኤ.20)
ስልጠና ፍቱን ሊሆን የሚችለው በሰልጣኝ ማህበራቱ አባላት ፍላጎት ብቻ
ማወቅ ጥሩ ሲተገበር ነው፡፡ የስልጠናው ውጤት በአፈፃፀም ላይ ለውጥ ማምጣት ከቻለ
ይህ ስልጠና የተመራው ብቃት ባለው አሰልጣኝ ብሎም ስልጠና የተካሄደው
ስልጠና ምንድነው ? በተገቢው የማህበሩ አባላት የኑሮ ሁኔታ በሚስማማበት ሰአት ላይ ነው፡፡
ስልጠና የሚለው ቃል
የሚያሳየው እውቀትን የዚህ ሰነድ አላማ በአርሶ ሰደሩ ስልጠና ላይ የUTZ የተደነገገ ደንብ
ማስተላለፍ እና ችሎታን ለማብራራት ነው፡፡ አላማው፡-
ማሻሻል፡፡ አላማው አፈፃፀምን  የማህበሩ አባላት ስልጠና እንዴት እንደሚካሄድ ማብራራት
ማሻሻል ነው፡፡  በUTZ አሰራር ደንብ መሰረት ለማህበራት እንዴት መጀመር፣ መተግበር
እና ውጤታማ ስልጠናዎችን በሰነድ መያዝ እንዳለባቸው መመሪያ
ግንዛቤ ማስያዝ ምንድነው? ማቅረብ፡፡
ግንዛቤ ማስያዢያ ትኩረት
የሚያደርገው በውይይቱ
መጨረሻ ላይ በዛ ርዕስ ላይ
ያለውን አስተሳሰብ መቀየር ሳጥን 2፡፡ የማህበሩ አባላት ስልጠና፣ የአሰራር ደንቡ ምንድ ነው
ነው፡፡ የአርሶ አደሩን ሚለው?
አስተሳሰብ ለመቀየር
የመጀመሪያው እርምጃ በUTZ አሰራር ደንብ መሰረት (ጂ.ኤ.19)
ይሆናል፡፡  ስልጠናው መሰጠት ያለበት ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች መሆን
ያስፈልጋል
 የማህበሩ አባላት እንዲገነዘቡ ስልጠናው ግልፅ እና ቀላል መሆን
ያስፈልጋል
 የስልጠናው ርዕሶች ግንዛቤ መፍጠራቸውን ለማረጋገጥ ማጣራት
ያስፈልጋል፡፡
 የማህበሩ አባላት የተሻለ ምርት እንዲያመርቱ ስልጠናው መዘጋጀት
ያለበት ከምርታማነት ጋር በተያያዘ ሀሳብ መሆን ያስፈልጋል፡፡
 ስልጠናው በቁጥር በቂ መሆን ያስፈልገዋል እና ለማህበሩ አባላት
በእውቀት፣ ችሎታ እና ልዕልና ከUTZ አሰራር ደንብ መሰረት ለመሄድ
ቀጣይነት ባለው መላኩ መቅረብ ያስፈልጋል፡፡
 በUTZ አሰራር ደንብ ውስጥ ከተዘረዘሩት ቢያንስ ሁለቱ ርዕሶች
(ጂ.ኤ.20) በየአመቱ ሊሸፈኑ ያስፈልጋል እናም ሁሉም ርዕሶች
በአራት አመት ጊዜ ውስጥ መሸፈን ያስፈልጋል፡፡
 በስልጠናው ለሚነሱ ስራዎች የሚመለከታቸው ወይም ላፊነት ያለባቸው
ግልሰቦች ናቸው በስልጠናው ላይ መሳተፍ ያለባቸው፡፡ እነዚህም
የማህበሩ አባላት፣ ቤተሰቦች፣ ጭሰኛ እና ሰራተኞች
 በስልጠና እና ግንዛቤ ፈጠራ ላይ ሴቶች እኩል የሆነ እድል
እንደተሰጣቸው ለማረጋገጥ ምዘና ማድረግ ያስፈልጋል (ጂ.ኤ.21)፡፡

2 © UTZ Version 1.0, August 2016


በቦታው ምን ያስፈልጋል?
ለማህበሩ አባላት ስልጠና ማዘጋጀት

1 አመት 2 አመት 3 አመት 4 አመት


የስልጠና አመራር
ማድረግ (ጂ.ኤ.8)
ይህ ግለሰብ (ኮሚቴ) አንዱ የውስጣዊ ስራ አመራር ሲስተም (IMS) አካል ሲሆን ለማህበሩ ሰራተኞች እና
ለማህበሩ አባላት ለሚቀርቡ ስልጠና ላፊነት አለበት (ጂ.ኤ.8)፡፡ የስልጠናው አመራር የIMS አመራር የሆነው
ሰው መሆን ይችላል ወይም ከIMS አመራር ጋር በቅርበት የሚሰራ እና ለዛ ቦታ የሚመጥን ሰው መሆን ይችላል፡፡

ጥሩ የስልጠና አማራር የሚያሰኘው ምንድነው?


የስልጠናው አመራር የሚከተሉት ላምዶች ሊኖሩት ይገባል
 ስልጠናው የሚያስፈልገውን አምራቾች መለየት
 ስልጠናዎችን ማዘጋጀት፣ ማስፈፀም እና መከታተል
 የአሰልጣኞችን ስብስብ ማስተባበር
ምን አይነት ስልጠና
እንደሚያስፈልግ
መገመት (ጂ.ኤ.19)
እየተካሄዱ ያሉ ስልጠናዎችን መገምገም ያስፈልጋል (ለበለጠ መረጃ ስልጠናን መገምገም ያስፈልጋል በሚለው ምዕራፍ
ላይ ይዩ) (ጂ.ኤ.19) (ያማፅናል)
ለማህበሩ አባላት ስልጠናን
ለማካሄድ የአሰልጣኞችን
ስብስብ ማሰልጠን እና መለየት
የወደፊት ሰልጣኞች ትክክለኛ ብቃት ማረጋገጫ እንዳላቸው እንዴት እርግጠኛ መሆን ይቻላል?
ስልጠናው መካሄድ ያለበት ብቁ በሆነ ሰው ነው(ጂ.ኤ.19) ማለትም ይፋ የሆነ በቂ የሚያረገው ነገር ያለው
ወይም ስልጠናው ላይ ከሚያስተላልፋቸው ሳቦች ጋር የተያያዘ ልምድ ያለው መሆን አለበት፡፡ ብቃት ማረጋገጫ
ከትምህርት ቤት ዲፕሎማ፣ ቴክኒክ እና ሙያ ተቋም፣ ዩንቨርስቲ፤መንግስት የተቀበለው ወይም ስልጠናላይ ስለመሳተፉ
መስረጃ(ለምሳሌ ለመስክ አርሶአደሮች ትምህርት ቤት ማመቻቸት ስልጠና) ወይም በተመሳሳይ ስራ ዘርፍ የተረጋገጠ
ልምድ
የስልጠና መርሀ
ግብር ማዳበር

መርሀ ግብሩ የእያንዳንዱን ስልጠና ቀን፣ ቦታ እና ርዕስ ማሳየት ይኖርበታል፡፡ የስልጠናውን አላማ እና ተሳታፊ
አካላትን መጥቀስ ይኖርበታል፣ በውጤቱ መሰረት ስልጠናው ግምገማ ያስፈልገዋል፡፡
በስልጠናው ላይ የተደረጉ
እንቅስቃሴዎችን መዝግቦ
ማስቀመጥ
ማህበራት በስልጠናው ላይ የተደረጉ እንቅስቃሴዎችን እና በስልጠናው ላይ የተሳተፉትን ተሳታፊዎች መዝግቦ
የማስቀመጥ ሂደቶችን ማዘጋጀት ያስፈልገዋል፡፡
የስልጠና መርሀ
ግብርን ማሻሻል
መርሀ ግብሩ የማህበሩ የዕቅዱ ክፍል መሆን አለበት እና ያለፈው አመት
የስጋት ግምገማ ውጤት፣ ውስጣዊ ምርመራ እና ኦዲት እና የስልጠና
ቁጥጥሮችን ዋጋ መስጠት፡፡

Guidance to the Core Code of Conduct for group and multi-group certification version 1.1 3
በተግባር፡- ጥሩ የስልጠና ፕሮግራሞች
መፍጠር
የአሰልጣኞች ስብስብን መፍጠር
ሳጥን 3 ብቁ የሆኑ አሰልጣኞችን ለመለየት ከብሄራዊ የግብርና ማስፋፊያ አገልግሎት፣
NGO እና ማህበረሰብ ተኮር ድርጅት ጋር መቀናጀት፡፡
ከአማካሪዎች፣ በኩባንያ ውስጥ የሚሰሩ አሰልጣኞች ወይም በአካካቢያችን
ከሚገኙ መሪ ከሆኑ አርሶ አደሮች ጋር አብሮ መሰራት፡፡
ያስታውሱ የUTZ ደንብ እንደሚፈልገው በተለያዩ ርዕሶች ላይ ስልጠና መውሰድ (ከግብርና
የማህበሩ ሰራተኞችም (ለምሳሌ፡ ስራ እስከ አካባቢ እና ማህበራዊ ጉዳይ ለቢዝነስ አመራር)፣ ይህን ርዕሶች
- IMS ሰራተኞች) ደግሞ ሁሉ ለመሸፈን ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር መቀናጀት ያስፈልጋል ለምሳሌ፡- የጤና
መሰልጠን ተቋም፣ ሠራተኞች ማህበር እና ልዩ የሆነ የመንግስት ወኪል ድርጅት፡፡
አለባቸው(ጂ.ኤ.18)፡፡ ይህም
የሚሸፈነው በተለያዩ መመሪያ
ሰነዶች፡- IMS መመሪያ ሰነድ፡፡

IMS ወይም  ለስልጣኝ የማህበሩ አባላት የስልጠናውን ጊዜ የሰልጣኞች አመራር ያስኬዳል፡፡


የስልጠና  በማሰልጠን ችሎታው ብቃት ያለው አሰልጣኝ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
አመራር UTZ በUTZ ፕሮግራም "የአሰልጣኞች ስልጠና" ይሰጣል፣ ለበለጠ መረጃ፡
www.utzacademyonline.com
ስልጠና
Trains
እና ዝግጁ and • መሪ የሆኑ አርሶ አደሮች ወይም ብቁ አርሶ አደሮች
ብቃት ያላቸው
sets
መሆን up
ያሰልጣኞች • አማካሪ፣ የአርሶ አደር አሰልጣኞች
ስብስብ • የማስፋፋት አገልግሎት

Trains
ስልጠና • የማሀበሩ አባላት
የማህበሩ • ቤተሰቦቻቸው
አባላት
• ሰራተኞች

ርዕስ መምረጥ
በአሰራር ደንብ ውስጥ ከተዝዘሩት የስልጠና ርዕሶች ውስጥ ርዕስ
ይወሰወዳል(ጂ.ኤ.19)፡፡ ስልጠናው የተዘጋጀው የማህበሩ አባላት በሚፈልጉት
እውቀት እና ችሎታ መሠረት መሆኑን ለማረጋገጥ IMS ከሚያከናውናቸው
የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ላይ ሊወስዱ ይችላሉ( ለምሳሌ ስልጠና ግምገማ
ይፈልጋል፣ የበፊቱን ስልጠና መቆጣጠር፣ ውስጣዊ ምርመራ፣ ውስጣዊ ኦዲት፣
ስጋት ግምገማ)፡፡ ስልጠና ከአሰራር ደንብ ውስጥ ቢያንስ ሁለቱን ርዕሶች
በየአመቱ መሸፈን ይኖርበታል በዚህ የተነሳ ከአራት አመት በኋላ ሁሉም ርዕስ
ይሸፈናል፡፡ ከታች ባለው ሰንተረዥ የርዕሶችን ዝርዝር ያሳያል፡፡

4 © UTZ Version 1.0, August 2016


ለማህበሩ አባላት ስልጠና ግንዛቤ ማዳበር
(ጂ.ኤ.19) (ጂ.ኤ.20)
 የምርቱ ምንጭ የሚገኝበት ዘዴ
 ጥሩ የእርሻ አያያዝ እና
ምርታማነት
 የተቀናጀ የተባይ መከላከል አመራር
 የሰብል ማሰባጠር
 የተፈቀዱ የፀረ-ተባይ አስተማማኝ
አያያዝ እና አጠቃቀም፣ በቅድመ
ሰብል ስብሰባ ጊዜ እና በዳግም
መግቢያ ጊዜያት ጭምር
 የሰብል መሰብሰብ እና የድህረ
ሰብል ስብሰባ ተግባራት
 የምርት ጥራት እና የምግብ
ደህንነት
 የመዝገብ አያያዝ ክህሎቶች
 የስራ ላይ ጤና እና ደህንነት  የሰራተኞች መብት
 የህፃናት ጉልበት፣ አደገኛ ስራን
እና የሰዎች ዝውውርን ጨምሮ
 የትምህርት ጠቃሚነት ሳጥን 4
 ለሴቶች የሚሰጥ እኩል መብት
እና እድሎች
 የወሲብ ጥቃት፣ ብዝሃነት እና ይህን ያስታውሱ
መድልኦ ሁልም የማህበሩ አባላት ፍላጎት
 የቤተሰብ የጤንነት ሁኔታ እና በስልጠና ዉስጥ ላይዳሰስ
የተመጣጠነ ምግብ ይችላል፡፡
 ሌሎች ቸግባብነት ያላቸው የስልጠና አቅርቦት እና
ርዕሰ ጉዳዮች
ምቹሁኔታዎች ሊታወስ ይገባል፡-
 የውሀ አካላት ሀብትን አጠባበቅ የግብርና ግብአት ወይም ፋይናንስ
 የእንስሳት እና እፅዋት አጠባበቅ ተደራሽነት
 የአየር ንብረት ለውጥ ጥራት፣ ዋጋ፣ ወዘተ ላይ መረጃ
 የቆሻሻ (ዝቃጭ) አወጋገድ ማትጊያ ለምሳሌ የተሻለ ጥራት
ላለው ምርት ብልጫ ያለው ዋጋ
ከፍተኛ ሙያ ለማከናወን ብቃት
ያለው ባለሞያን ለመቅጠር
ስልጠና ለመስጠት የስልጠና ፍላጎቶችን መለየት የሚያስችል ሁኔታ መኖር፡፡
የስልጠና ፕሮግራሞችን ከመዘጋጀት እና ስልጠና ለማካሄድ ከመጀመር በፊት
ይህ ድጋፍ ዘወትር መቅረብ
የስልጠና ፍላጎቶችን መለየት ይመከራል፡፡ በዚህ መለያ ማን መሰልጠን ያለበት ከስልጠና ጋር ተያይዞ
እንደሚፈልግ፣ ምን ማወቅ እንደሚፈልጉ እና በስልጠናው መጨረሻ በተለየ ሁኔታ ይሆናል፡፡
ማድረግ የሚፈልጉትን መለየት ይቻላል፡፡ ከስልጠናው ፍላጎት በመነሳት
የስልጠናውን አሰራር እንዴት እንደሆነ ያውቃሉ፡፡ ይህም ለማህበሩ አባላት
እንደሚፈልጉት መጠን ስልጠናው መስጠት እንዲቻል እና ባላቸው ቁሳት ባግባቡ
መሰረት መጠቀም የሚያስችል፡፡ ውጤታማ ስልጠናን ለመስጠት ሁሉም የማህበሩ
አባላት ተመሳሳይ ፍላጎት ሊኖራቸው ስለማይችል ፈላጎቶችን ለማሟላት በአነስተኛ
የስልጠና ቡድን ከፋፍሎ እንዲሰጥ ይመከራል፡፡ ካሎት ልምድ ወይም ከስጋት
ግምገማ ውጤቶች በመነሳት የተወሰኑ የስልጠና ፋላጎቶችን ሊለዩ ይችላሉ፡፡ ሁልጊዜ
የስልጠና አመራሩ የስልጠና ፋላጎቶችን የመለየት ሀላፊነት አለበት ቢሆንም እንኳን
IMS ሌላ ሰው ስራውን እንዲሰራ ወይም የስልጠና አመራሩን እንዲያግዝ ሊመደብ
ይችላል፡፡

Guidance to the Core Code of Conduct for group and multi-group certification version 1.1 5
የስልጠና ፍላጎቶችን ለመለየት የሚቀጥለውን ጥያቄ መመለስ ይኖርበታል፡-
 የታለመለት ቡድን ምንድነው? ማን በምን ላይ መሰልጠን ይፈልጋል?
ስልጠናው በቀጥታ የሚመለከታቸው ብቻ እንጂ ሁሉም የማህበሩ አባላት
ሳጥን 5 በሁሉም የስልጠናው ክፍለ ጊዜ ላይ መካፈል አያስፈልጋቸውም፡፡ ለምሳሌ፡
- በባለ መሬት እና በገባር ስርአት ባለበት የመሬት ስሪት ሁኔታ
የማህበሩን አባል ሆኖ የተመዘገበው ባለመሬቱ ቢሆንም ነገር ግን
ይህን ያስተውሉ ትክክለኛውን የግብርና ስራ አፈፃፀም የሚያከናውነው ገባሩ ስለሆነ
ሰልጠና ፍላጎቶችን መለየት ካልተቻለ ስልጠናውን መሳተፍ የሚገባው እሱ ነው፡፡
የሚቀጥለውን ሁኔታዎች ሊያስከትል  ያለንበት ጊዜ የዕውቀት ደረጃ እና ልምምድ ምንድነው?
ይችላል፡- የስልጠናው ደረጃ የሚጠይቀውን ለመወሰን እና በኋላም የስልጠናውን
 የስልጠናዎ ፕሮግራም ባልተፈለገ መርሀ ግብር ውጤታማነት ለመቆጣጠር ይህ መረጃ ያስፈልጋል፡፡
ቡድን ላይ ትኩረት ሊሰጥ  ስልጠናው የትኛውን አርእስት ይሸፍናል?
ይችላል UTZ የርዕስ ዝርዝሮችን ሰጥቷል የትኛው ለዚኛው አመት እና
 የሰልጠና ፕሮግራሙ በተሳሳተ ለሚቀጥለው አመት እነደሚሆን መቅደም ያለበት(ቅደም ተከተሉን)
ማስቀመጥ፡፡
አርዕስት ላይ ትኩረት ሊሰጥ
 ሰልጠናው ምን ያህል በጥኝቃቄ ጠደረገ እነደሆን እና ምንያህል ጊዜ
ይችላል ይህም ተሳታፊዎች ሊወስድ ይችላል? የአንድ ክፍለ ጊዜ ስልጠና ይበቃል ወይስ ሰፋ ያለ
በሚያውቁት ወይንም ማወቅ ክፍለ ጊዜ ያስፈልጋል ?
በማይገባቸው ጉዳዮች ላይ ብዙ
UTZ የስልጠና ፍላጎቶችን ለመለየት አሳታፊ አቀራረብ እንዲወስድ ይመክራል፡፡
ጊዜ ሊባክን ያችላል፡፡ ይህ ምንአልባት የተወሰኑትን የሚከተለውን ያጠቃልላል፡፡
 የምትጠቀማቸው ዘዴዎች የቡድኑ  ከማህበሩ አባላት እና ከታለመላቸው ማህበራት ጋር የቃል ጥያቄ እና
አባላትን የማያነሳሳ፣የማያሳትፍ እና የቡድን ውይይት
አዳዲስ ዕውቀት እና ክህሎትን  የማህበሩ አባላት ትክክለኛው ተግባራት፣ የውስጥ ምርመራ እና ያለፈው
ለመጠቀም የማያስችል ሊሆን አመት የኦዲት ሪፖርት ምልከታ
ይችላል፡፡  ከIMS ቡድን ጋር ውይይት
 የመነሻ ሁኔታን ማወቅ ካልቻልክ  ከባለሞያ ጋር ምክክር(ለምሳል፡- የግብርና ዘዴ ማስፋፋት አገልግሎት፣
የስልጠናህን ተፅኖ መቆጣጠር በፀረ ተባይ ባለሞያ፣ በህፃናት ጉልበት እና በተመጣጠነ ምግብ ላይ
አትችልም፡፡ የሚሰራ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት)
 በምርት ቅብብሎሽ ሰንሰለት ውስጥ ላሉ ገዚዎች እና ሌሎች ተዋናዮች
ጋር በመመካከር በጥራት ደረጃ መስፈርቶች፣ በገበያ ፍላጎቶች፣
አለማቀፍ ደንቦችን ወዘተ ለማብራራት፡፡

6 © UTZ Version 1.0, August 2016


የስልጠና መርሀ ግብር ማዘጋጀት
የስልጠና መርሀ ግብር የእያንዳንዱን ስልጠና ጊዜ በዝርዝር መያዝ አለበት፡፡
የስልጠና መርሀ ግብር ምሳሌ ይህን ይመስላል፡-

# የስልጠናው ማጠቃለያ የሚመለከተው አሰልጣኝ/ ለስልጠና ማጣሪያ ጊዜ፣ሰአት፣ የስልጠና


ርዕስ/ ቡድን ሀላፊነት ያለበት ው መንገዶች/ የሚፈጀው ስፍራ
የሚሸፍነው አካል የተጠቀም ምርመራን ጊዜ
አርዕስት ናቸው ማስተዋል
ቁሳቁሶች
1 ጥሩ የእርሻ ጥቅሙን በማርቲን ገመቹ መሪ ለአርሶ ተግባራዊ ማሳያ ግንቦት የማርቲን
አያያዝ(እንክብ መወያየት እና ቡድን ውስጥ አርሶ አደር አደሩ 2( 2 ማሳ እና
ካቤ)፣ ገረዛ እነዴት ያሉ አርሶ የመስክ ሰአት) በአካባቢ
እደሚገረዝ አደሮች(10) ማስተማሪ ው
መማር ያ መምሪያ የማህበሩ
አባት
ማሳ

2 መዝገብ አያያዝ የትኛውን መዝገብ ደን መንደር በቀለ የቢዝነ የመዝገብ ጥያቄ መስከረም በደን
ለምስክር ወረቀቱ አርሶ አደሮች አሰልጣኝ መያዣ 7( 3 መንደር
መያዝ እንዳለብን እና የቤተሰቡ ትንሽ ሰአት) የኋብረተሰ
መረዳት እና አባላት መፅሀፍ ቡ
መዝገብ አያያዝን መዝገብ አዳራሽ
እንዴት መጠቀም የመያዝ
እንዳለብን መማር ሀላፊነት
አለበት
3 የመሳሰሉት

የስልጠና መርሀ ግብርን በሚያዘጋጁበት ጊዜ ይህን እርግጠኛ ይሁኑ፡-


 የስልጠና ጊዜ እና ሰአት የማህበሩ አባላት ስራ፣ ባህል እና ማህበራዊ ክስተትን
በግምት ውስጥ ያስገባል እና ሌሎች የሚፈፅሟቸውን ሀላፊነቶችንም (ወላጅ
መሆን፣ የማህበረሰቡ ሹም፣ ወዘተ)
 ቴክኒካል ወይም የግብርና ርዕሶችን ከእውነተኛው አለም እንቅስቃሴ ጋር
አቀናጅቶ ማሰልጠን አዳዲስ እውቀቶችን በፍጥነት ለመተግበር ይረዳል

ሳጥን 6፡፡ ለሴቶች ስልጠና


የአሰራር ደንቡ እንደሚጠይቀው በስልጠና ላይ የሴቶችን
ተሳታፊነት ማህበራት ያመቻቻል(ጂ.ኤ.21)፡፡ ሴት
አርሶ አደሮችን እና ሰራተኞችን በስልጠና ለመድረስ
በይበልጥ ይፈትናል ምክንያቱም የተመዘገበ የማህበራቱ
አባል ላይሆኑ ይችላሉ፣ ሁል ጊዜም ቤተሰብን እና ህፃናት
መንከባከብ ወደ ስልጠና ከመሄድ እና ከመሳተፍ
ሊያግዳቸው ይችላል እናም ይህ ዝቅተኛ መሠረታዊ
ትምህርት እንዲኖራቸው ያረጋል፡፡ ስልጠና ለመስጠት
ፍላጎቶችን በሚለዩበት ጊዜ እራሶን ይጠይቁ፡- ሴቶች
ስልጠና ላይ እንዲሳተፉ እንዴት ማበረታታት እዳለቦት?
ተሳትፎአቸውን ለማበረታታት ምን አይነት እርምጃ
መውሰድ ያስፈልጋል? ለአንዳንድ ምሳሌዎች እና ምክሮች
በፆታ ላይ ያሉ መመሪያ ሰነዶች ጋር መማከር፡፡

Guidance to the Core Code of Conduct for group and multi-group certification version 1.1 7
ሳጥን 7
የስልጠናዎን ክፍለ ጊዜ መንደፍ (ማቀድ)
የስልጠናዎን ክፍለ ጊዜ ሲነድፉ ለርዕሶ እና ለማህበሩ አባላት በተሻለ ሁኔታ
የሚስማማ የስልጠና ዘዴዎችን መምረጥ ይገባል፡፡ የማህበሮ አባላት የዕውቀት
ሀባት ይዘው እንደመጡ እና የተማሩትን ትምህርት በፍጥነት ችግሮቻቸውን
ማወቅ ጥሩ ለመቅረፍ መጠቀም እንደሚፈልጉ ልብ ይበሉ፡፡
ጎልማሶች እነዴት እንደሚማሩ
ለማወቅ አሜሪካዊው የትምህርት ብዙ አይነት የተለያዩ ዘዴዎች ይንራሉ እናም እርሶ ለስልጠናው ተሳታፊዎች
ንድፈ ሀሳብ ቀማሪ የዳቪድ ኮልብን ሥልጠናውን በሚረዱት እና ማራኪ በሆነ መልኩ የሚደርግ ዘዴን ይምረጡ፡፡
ኤክስፕራንሻል ለርኒንግ ሳይክል
ፅንሰ ሀሳብ እና የማልኮም ኖውለስ ከታች ያለው ሰንጠረዝ በብዛት የምንጠቀማቸውን ዘዴዎች ይዘረዝራል
የጎልማሶች ትምህረት ባህሪያትን በተግባር የተለያዩ አማራጭ የአሰለጣጠን ዘዴዎችን መጠቀም የሰልጣኞችን በነቃ
ቀጥሎባሉት ድህረ ገፅ ማየት ሁኔታ እዲሳተፉበት ያረጋል
ይቻላል፡
http://tribehr.com/blog/workpl
ace-training-education-how-
adults-learn

የስልጠና ዘዴ መግለጫ
ትምህርተ ትምህርት የሚሰጠው በተወሰኑ ርዕሶች ላይ በአሰልጣኙ፣ ተጋባዥ ባለሞያ ወይም በአንድ የማህበሩ አባል
መስጠት(ሌክቸር ይሆናል፡፡ ትምህርቱ የሚሰጠው በአፍ ብቻ፣ ስላይዶች በመጠቀም፣ ባጭር የፊልም ክሊፖች፣ በስዕል፣
እና ፕረሰንቴሽን) በፖስተር ወይም በሚታደል ፅሁፍ ይሆናል፡፡ የትምህርት አሰጣጡ አላማ ዕውቀትን ማስተላለፍ ሲሆን
በስልጠናው ላይ በሚነሱ ጥያቄ እና መልስ፣ ውይይት እና መልመጃ ጥያቄ... ወዘተ ጊዜ የጠለቀ
እውቀት ያገኛሉ፡፡
ጥያቄ እና መልስ ባብዛኛው ከትምህረቱ በኋላ ጥያቄ እና መልስ ይኖራል በዚህም ጊዜ የማህበሩ አባላት ከተማሩት
ትምህርት በመነሳት ጥያቄ መጠየቅ ይችላሉ ጥያቄውም በትምህርት ሰጪው አካል፣ በአሰልጣኙ ወይም
በማህበሩ አባላት መልስ ይሰጥበታል፡፡
ውይይት በውይይት ጊዜ የማህበሩ አባላት ያላቸውን ልምድ እና ሀሳብ እንዲያካፍሉ ወይም ችግሮችን እዲቀርፉ
ይፈቅዳል፡፡ ውይይቱ በትንንሽ ቡድኖች ወይም ከአጠቃላይ ቡድኑ ጋር ሊካሄድ ይችላል፡፡
ሀሳብ ማሰባሰብ በሀሳብ ማሰባሰቢያ ክፍለ ጊዜ ብዙ ሀሳቦችን በአጭር ጊዜ መሰብሰብ እንጂ እያንዳንዱን ሀሳብ በዝርዝር
መወያየት አያስፈልግም፡፡ በግልም ሁነ በቡድን ሊካሄድ የሚችል የተለያየ አይነት የሀሳብ ማሰባሰቢያ አለ፡

ሰርቶ ማሳያ ሰርቶ ማሳያ አንድ ነገር እንዴት እንደሚሰራ የሚያሳይ የትምህርት መስጫ ዘዴ ነው ለምሳሌ የመርጫ
መሳሪያዎችን እንዴት መጠቀም እንዳለብን፡፡ ሰርቶ ማሳያን በስልጠና አካባቢ ወይም በመስክ ላይ ማሳየት
ይቻላል፡፡
ተውኔታዊ በተውኔታዊ አቀራረብ ውስጥ ሁለት ወይም ከዛ በላይ ተሳታፊዎች በተውኔቱ ክፍል ላይ ይተውናሉ፡፡
ተሳታፊዎች ስለጉዳዩ በተለያየ አቅጣጫ እንዲያስቡ ያበረተታል እናም አስተሳሰባቸውን እንዲቀይሩ
ይረዳል፡፡ ከተውኔቱ በሆላ ምንአይነት ልምድ እንዳገኙ እና ምን እንደተገነዘቡ ከቡድኑ አባላት ጋር
ያንፀባርቃሉ፡፡
ኬስ በገቢራዊ ሁኔታ ውስጥ የሚታዩ ክንዋኔዎችን ለማህበሩ አባላት በማቅረብ ትንተና እንዲሰጥበት እና
ስተዲ(ጥናታዊ ለችግሮች አማራጭ መፍትሄዎችን እንዲለዩ ማድረግ ይህም የጋራ ችግሮችን በገቢራዊ ኡነታ ውስጥ
ዳሰሳ መፍትሄ መሻት የሚያስችልበትን ውይይት እንዲያካሂዱ ያስችላል
የመስክ ጉብኝት የመስክ ጉብኝት የማህበሩ አባላት የሚሹትን ልምድ በተግባር ለማየት እንዲችሉ ለማስቻል ይዘጋጃል፡፡ የመስክ
ጉብኝቱ በሞዴል አርሶ አደር ማሳ፣ በማቀናጃ ስፍራ ወይም በችግኝ ማፍያ ቦታ ይዘጋጃል፡፡
መልመጃ ጥያቄ የመልመጃ ጥያቄ ለግል ወይም ለአነስተኛ ቡድን እንዲለማመዱበት እና ከስልጠናው ምን እንደተማሩ
እንዲያንፀባርቁ ይሰጣቸዋል
የአፈፃፀም ዕቅድ የማህበሩ አባላት በስልጠናው ላይ የተማሩትን በራሳቸው የኑሮ ሁኔታ ላይ እርዳታ እና መመሪያ
ማዘጋጀት ለመቀበል ከሚያስችላቸው እድሎች ጋር እንዲጠቀሙበት መፍቀድ
አጫጭር ጥያቄ በአስቂኝ መንገድ የተሳታፊዎችን ግንዛቤ በጥያቄ መገምገም እና እርስ በእርሳቸው ወይም በቡድን
እንዲወዳደሩ በማድረግ ተሳታፊዎችን ማነቃቃት
ፈተና በደንቡ መሰረት ፈትና በስልጠናው መጨረሻ ላይ የማህበሩ አባላት የስልጠናውን ይዘት መረዳታቸውን
እና ተግባር ላይ እንደሚያውሉት ለመገምገም ይሰጣል
ማነቃቂያ/ ዝምታ ዝምታ ሰባሪ/ ማነቃቂያ አጭር አስቂኝ የሆነ ጨዋታ ሲሆን ተሳታፊዎች እርስ በእርሳቸው እንዲተዋወቁ
ሰባሪ እና የእንኳን ደህና መጣችሁ ክፍት ሁኔታ መፍጠር ይህም ህዝቡን በጥሩ ሁኔታ እንዲማር ይረዳዋል፡፡
በተጨማሪም ከምግብ እና ከከባድ የስራ ጊዜ በኋላ አዲስ መነቃቂያ ለመፍጠር መጠቀም ይቻላል፡፡
ይህን ጨዋታ በስልጠናው ክፍለ ገዜ በሙሉ መጠቀም ይቻላል፡፡

8 © UTZ Version 1.0, August 2016


እያንዳንዱን የስልጠና ጊዜ ማቀድ
ለእያንዳንዱ የስልጠና ጊዜ የእቅዱን ዝርዝር በማዘጋጀት ለሰልጣኞች በጽሁፍ
መስጠት እና የሚሰጠው ስልጠና እና የሚወሰደው ዘዴ ፈሩን እንዳይስት
ይረዳል፡፡
ምሳሌው ከታች ይታያል፡፡

የስልጠናው ርዕስ፡- አሰልጣኝ፡- አቶ ጊዜ፣ ሰአት ወይም የሚፈጀው ጊዜ ቦታ፡- ሰርቶ ማሳያ በትላልቅ
ተባዮች እና መሀመድ ፡- ሚያዚያ 1 ጠዋት (2.5 መንደር
ማጥፊያ መንገድ ሰአት)
ተሳታፊዎች፡- 15 አርሶ አደሮች ከትልቁ መንደር
አላማ፡- አርሶ አደሩ እንዴት ተባዮችን መለየት እና ማጥፋት እናዳለበት ማወቁን እርግጠኛ መሆን
የአጀንዳ ነጥቦች፡- የሚሸፈነው ርዕስ፡- የሚጠቀመው ቁሳቁስ እና ዘዴ፡- የሚያስፈልገው ሰአት፡-
መግቢያ  አሰልጣኞችን  ንግግር 30 ደቂቃ
ማስተዋወቅ  ጨዋታ/ዝምታ መስበሪያ
 ተሳታፊዎች  በፖስተር የታገዘ ትምህርት
እራሳቸውን መስጠት
ማስተዋወቅ
 የስልጠናውን ክፍለ
ጊዜ አጠቃላይ ዳሰሳ
የተለመዱ ተባዮች  የተለመዱ ተባዮች  ስለ ተባዮች በፖስተር የታገዘ 30 ደቂቃ
 ተባዮችን እንዴት ትምህርት መስጠት
መለየት ይቻላል
ተባዮችን መከላከያ የተቀናጀ የተባይ ግብርና ስነ-ምህዳር የሰርቶ 60 ደቂቃ
እና ማጥፊያ መከላከል አመራር ማሳያዎች ትንተና ላይ ጉብኝት
 የመልመጃ ጥያቄ፡- ተሳታፊዎች
ተባዮችን በእርሻ ላይ እንዲለዩ
ፈተና/ማረጋገጫ አርሶ አደሩ ተባዮችን እያንዳንዱ አርሶ አደር የተባዮች 30 ደቂቃ
እንዴት መለየት እና ስዕል የያዘ ካርድ ይሰጠው እና
ማጥፋት እንዳለበት የትኛው የተባይ አይነት እንደሆነ
ማወቁን ሰርቶ ማሳያ እነዲለይ ይጠየቃል ከዚያም
በእርሻው ላይ ቢያገኘው እንዴት
መቆጣጠር እንደሚችል ለስራ
ባልደረባው እንዲያስረዳ ይጠበቃል

ከአካባቢው እና ለእህል ተስማሚ የሆነ በአካባቢ የሚገኝ የስልጠና ቁሳቁስ


እንዲመለከቱ ይመክራል፡፡ ከመጀመሪያ በራሶ ሁሉንም ነገር ለማዳበር ከመሞከር
ይልቅ በመንግስት፣ መንግስታዊ ካልሆነ ወይም ዘላቂነት ያለው የግብርና እንቅስቃሴ
በሚያደርግ የግል ድርጅት ውስጥ የተመረተ(የዳበረ) ቁሳቁስ መጠቀም ሁልጊዜ
በይበልጥ ውጤታማ ነው፡፡

የስልጠናውን ተጽእኖ መቆጣጠር


በስልጠናው ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ተሳታፊዎች የተማሩትን ነገር መረዳታቸውን
ማረጋገጥ፡፡ የቃል ጥያቄ፣ የተማሩትን ተግባር በጥያቄ ወይም ተግባራዊ ሰርቶ
ማሳያ ማሳየት ለምሳሌ፡- ዛፍ መከርከም ወይም ከዛፍ ላይ ተባዮችን መለየት፡፡
በመቀጠል ተሳታፊዎች የተማሩትን በትክክል ተግባር ላይ እንዳዋሉት ማረጋገጥ
ያስፈልጋል ለምሳሌ፡- የእርሻ ቦታዎችን በመጓብኘት፡፡ ተሳታፊዎች የስልጠናውን
ሀሳብ እንዳልተረዱት ከተገነዘቡ(ካወቁ) እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡-
የስልተናውን ሀሳብ ለመድገም ተጨማሪ እርዳታ ማዘጋጀት( ለምሳሌ፡- ምክር፣
የክትትል ስልጠና) እና ተሳታፊዎች እንዲረዱት በሚቀጥለው ጊዜ በርዕሱ ላይ
ስልጠና ማዘጋጀት ስለሆነም የስልጠና ቁሳቁሶችን ማበጃጀት፡፡

በተከታታይ እንቅስቃሴዎን ለማሻሻል በቁጥጥር ጊዜ ያገኙትን ውጤት በቀጣይ


በሚያዘጋጁት ስልጠና ላይ እንዲያካትቱት እርግጠኛ ይሁኑ፣ ሰልጠናው የማህበሩን
አባላት ፍላጎት እንዳገኘ እና አሰራራቸው እንደተሻሻለ እርግጠኛ ይሁኑ፡፡

Guidance to the Core Code of Conduct for group and multi-group certification version 1.1 9
ሰልጠናዎን በሰነድ መያዝ እና ግንዛቤን
የመጨመር እንቅስቃሴ
የUTZ አሰራር ደንብ የስልጠናውን እንቅስቃሴ በመዝገብ እንዲያዝ
ይጠይቃል ስለሆነም የሰርትፊኬሽን አካላት ታዛዣነቶን
ያረጋግጣሉ፡፡ ይህ መዝገብ የተሰጡ ስልጠናዎችን እና የተደረጉትን
ለውጦች ለመቆጣጠር እና ለመዘገብ ይረዳል፡፡
ሰነዶቹ ይህን ማካተት ያስፈልጋቸዋል፡
 የስልጠናው ክፍለ ጊዜ መዝገብ(ጂ.ኤ.19)፣ የርዕሱን ይዘት፣ ተሳታፊዎች፣
አሰልጣኞች እና ቀን፣ ሰአት እና የስልጠናውን ቦታ የሚይዝ ማስታወሻ፡፡
ለምሳሌ፡- መሰረታዊ የስልጠና መዝገቦች ከታች ይታያል፡፡ የስልጠናውን
መርሀ ግብር ወይም የስልጠናውን ጊዜ ዕቅድ ለዚህ መጠቀም እንደሚቻል
ያስታውሱ፡፡

# ቀን ርዕስ ማጠቃለያ የቆይታ የተሳታፊዎች የአሰልጣኞች


ጊዜ # ስም
1 ግንቦት 2 ጥሩ የግብርና ጥቅሙን መወያየት እና 2 ሰአት 10 ማርቆስ፣
አጠባበቅ፡ እንዴት እንደሚከረከም የአርሶ አደሮች
ክርከማ መማር መሪ

2 መስከረም 7 መዝገብ አያያዝ ለሰርተፍኬሽን ምን 3 ሰአት 15 ዳንኤል፣


አይነት መዝገብ መያዝ የንግድ
እንዳለበት መረዳት እና አሰልጣኝ
እንዴት የመዝገብ አያያዝ
መፅሔትን መጠቀም
እንደሚቻል መማር

 የተሳታፊዎች ዝርዝር(ጂ.ኤ.19) ከመጀመሪያው አመት ጀምሮ የእያንዳንዱ


የስልጠና ጊዜ ማስቀመጠ ያስፈልጋል፡፡ ዝርዝሩ በትንሹ የእያንዳንዱን
ተሳታፊ ስም፣ ጾታ እና ፊርም ወይም የእጅ አሻራ ማካተት ይኖርበታል፡፡
የተለየ መለያ ባህሪም እነዲካተት እንመክራለን፤ ለምሳሌ የማህበሩ አባል
መታወቂያ ወይም የልደት ቀን፣ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር እና የስልጠና
ቦታ፡፡ ቀለል ያለ የአቴንዳነስ ዝርዘር ምሳል ከታች አለ፡፡ ምንአልበታ
የስልጠናው ተሳታፊ የማህበሩ አባል ካልሆነ(ለምሳል የማህበሩ አባል
ተከራይ ወይም ባለቤት)፤ የሚቀርበውን የማህበር አባል ስምና መታወቂያ
ቁጥር መያዝ ያስፈልጋል፡፡

የስልጠናው ርዕስ፡- ተባዮች እና መከላከያው ቀን፣ ሰአት ወይም አሰልጣኝ፡ አቶ


የቆይታው ጊዜ፡- መሀመድ
ሚያዚያ 1፣ 3-5
የተሳታፊዎች ስም የማህበሩ አባላት ወይም ተሳታፊዎቹ ጾታ፡- ወንድ/ሴት ፊርማ ወይም የእጅ
# የወከሉት የማህበሩ አባላት ስም አሻራ
1 ማርታ 001 ሴት ማርታ
2 ጴጥሮስ 002 ወንድ ጴጥሮስ

 በስልጣና እና ግንዛቤ ማሳደጊያ እንቅስቃሴ የሴቶች ተሳትፎን ለማመቻቸት


የተወሰዱትን እርምጃዎች መዝገብ ከሁለተኛው አመት ጀምሮ ማስቀመጥ
 የማህበሩ አባልተ የስልጠናውን ሀሳብ መረዳታቸውን የሚያሳይ ግምገማ
መዝገብ (ጂ.ኤ.19)፡፡
 የአሰልጣኞች ማሟያ(ጂ.ኤ.19) ስልጠናው መስፈርቱን በሚያሞሉ
አሰልጣኞች እነዲሰጥ ለማሻሻል ከ1 አመት ጀምሮ መመዝገብ አለበት፡፡
የስልጠና ሰርተፍኬት፣ ዲፕሎማ እና ከመንግስት ያገኙትን ኮፒ ማስቀመጥ
10 © UTZ Version 1.0, August 2016
ተጨማሪ ንባብ
የUTZ የሰልጠና ቁሳቁስ
የUTZ የብቃት ማረጋገጫ ሰነድ፡፡ የUTZ አሰራር ደንብ አፋፃፀም እና
አረዳድ መረጃ፡፡ የሚገኘው፡-https://www.utz.org/resource-library/

የUTZ በቀጥታ መስመር (Online) አካዳሚ፡፡ UTZ የቀጥታ መስመር የስልጠና


መድረክ ለፈፃሚዎች እና ለሰርተፍኬት ሰጪዎች፡፡ ከUTZ ፕሮግራም ጋር
ግንኙነት ያላቸውን ማቴሪያሎች፣ የስልጠና ዘዴዎች እና መረጃዎች በቀጥታ
ስርጭት እና በቀጥታ መስመር ያሉ የስልጠና መረጃዎች በነዚ መድረኮች ላይ
ሊገኙ ይችላሉ፡፡ እንዚን መድረኮችን ለመጠቀም በዚህ ድረ ገፅ ይመዝገቡ፡-
http://www.utzacademyonline.com/

የሌላ ድርጅት የስልጠና መሳሪያዎች


 ሶሊዳሪዳድ፣ ለገጠር አምራቾች የስልጠና ዘዴዎች- አጠቃላይ
ገፅታ(በእንግሊዘኛ እና በእስፓኒኛ)፡፡ ጠቃሚ እይታ በሰፋ ባለ
አጠቃቀም
 ሶሊዳሪዳድ፣ ለገጠር አምራቾች የሰልጠና መሳሪያ እና
ዘዴዎች(በእንግሊዘኛ እና በእስፓኒኛ)፡፡ እንዴት ማቀድ እና ለአነስተኛ
አርሰሶ አደሮች ማሰልጠን እንደሚቻል ተግባራዊ ምክር መስጠት
 ሲሲኢ የስልጠና መሳሪያዎች(በእንግሊዘኛ እና በእስፓኒኛ)፡፡ በምእራብ
አፍሪካ ያሉ የካካዎ ምርት አነስተኛ አርሶ አደሮች ስልጠና

እንዚህ ስልጠና መሳሪያዎች እና ሌሎች በርካታዎች ቀጥሎ ባለው ድህረ ገፅ


ይገኛሉ፡- https://www.utz.org/resource-library/

Guidance to the Core Code of Conduct for group and multi-group certification version 1.1 11

You might also like