ይነበብ

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 3

ሙሉዉን ሳታነቡ አስተያየት እንዳትሰጡ አደራ!!

Guys ታስታዉሱ እንደሆነ a year before (ከአመት በፊት) የወልቃይት እጣ ፈንታ በርከት ባሉ ነገሮች ሊደመደም
ይችላል ብለን ነበር፣ we said that, The Issue Of Wolkait is serous!!

አንደኛ፦ ወያኔን ደቁሰን አሸንፈን ወልቃይትን ያለማንም ሌላ አካል አዛዥነት የጎንደር አካል አድርጎ እንደ አንድ ዞን
ማቋቋም የሚል ነበር፣ እሄ የሚሆነዉ ግን ሙሉ ለሙሉ ወያኔን መደምሰስና ማስወገድ ከቻልን ብቻ ነዉ ብለን ነበር።
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የእስካሁኑ ቆይታዉና አደረጃጀቱ በዚህ መልኩ የተመሰረተ ነዉ። ምክንያቱም
ወያኔን ወልቃይት ላይ ደቁሰን አበጥረን አሸንፈነዋልና።

ሁለተኛ፦ -----
ሶስተኛ፦ -----
አራተኛ ፦ ወያኔ ተሸነፈም አልተሸነፈ የወልቃይት ጉዳይ ህጋዊና ፖለቲካዊ በሆነ መንገድ ይፈታ ሊባል ይችላል። ይህም
" ወልቃይት ወደ አማራ ወይስ ወደ ትግሬ? " የሚል ሪፈረንደም ተካሂዶ የወልቃይት እጣ ፈንታ በሪፈረንደም
ሊደመደም ይችላል የሚል ግምት አስቀምጨ ነበር።

ወያኔን ሙሉ በሙሉ ማሸነፍ ከቻልን እጣ ፈንታችን በተራ ቁጥር አንድ የተቀመጠው እንደሆነ ካላሸነፍነው ደግሞ
በተራ ቁጥር አራት (ሪፈረንደም) የሚቀመጥ ድምዳሜ እንደሚኖረው እንድንገምት የሚያደርገን የአገሪቱ ፖለቲካና
ጦርነቱ ሽክፍ ያለ ባለመሆኑ፣ የአማራ ፖለቲካ ደግሞ ዘልዛላና እንቅልፋም መሆኑን በመገንዘብ ነበር።

ከላይ የጠቀስኳቸዉ ሁሉም ለአመት በቆየዉ የአገራችን ሁኔታና የህዝባችንን ሁኔታ ግምት ዉስጥ አስገብተን
የገመትናቸዉ ነበሩ። አሁን ሁሉም ተጠቅልሎ ተራ ቁጥር 4 ላይ እንደሚወድቅ ያሳያል። ለምን የግሌን እይታ
ተመልከቱ።

አሁን ወያኔን እንደ ሀገር ማሸነፍ ስላልቻልን የመጨረሻዉ ይሆናል ያልነዉ ግምት ወደ መጀመሪያ በመምጣት
የወልቃይት ጉዳይ በሪፈረንደም ሊወሰን እንደሚችል 90% እርግጠኛ መሆን ይቻላል።

ለምን?

አንደኛ፦ ጦርነቱን ማሸነፍ ስላልቻልን


ሁለተኛ፦ አገራዊ እርቅ መፈፀም የግድ ሆኖ በመገኘቱ የወልቃይትም ሆነ የራያ ጉዳይ፣ እንዲሁም እንደ አገር የተፈጠሩ
አልመግባባቶችን ለመፍታት እንቅስቃሴ በመኖሩ ነዉ።
ሶስተኛ፡- የአለም አቀፍ ጫናዎች መብዛት
በእነዚህ ምክንያቶች የወልቃይት ጉዳይ የሚፈታዉ በሪፈረንደም ነዉ ወደ ሚለዉ የሚያመራን ሆኖ ይገኛል። ያዉ
ታስታውሱ እንደሆነ ቀደም ሲል በነበረኝ ፅሁፌ " ጦርነቱን ማሸነፍ ካልቻልክ ወደድክም ጠላህም ትደራደራለህ "
ያልኩት ማለት ነዉ።

=> ይህን ከተረዳን የእኛ ስራ ምን ይሁን የሚለዉ ዋናዉ ነጥብ መሆን አለበት። በእኔ እይታ ወያኔን ማሸነፍ
እንዳልቻልን ማወቅ ተገቢ ነዉ እላለሁ። ኢትዮጵያም አላሸነፈችም። ስለዚህ ባላሸነፍንበት እንዴት ተጠቃሚ
እንሆናለን ብሎ Critically ማሰብ ተገቢ ነዉ። በእኔ እምነት እንደ አማራ ህዝብ በተለይም ደግሞ እንደ ጎንደርና
ወሎ ህዝብ ሁለት ወሳኝ ጉዳዮችን መፈፀም ይገባናል እላለሁ። የጎንደሩን እንደሚከተለዉ አቀርበዋለሁ፣

ወልቃይት የኖህ መርከብ


አንደኛ፦ ወያኔ አሁን ያለዉን ነባራዊ ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ተጨማሪ ቦታዎችን ሊቆጣጠር
ይችላል። በተለይ ጎንደርን ለመቆጣጠር አስቦ ሊሰራ ይችላል።እየሰራም ነዉ። ስለዚህ በምንም ተዓምር ተጨማሪ
ቦታዎች እንዳይያዙ ከፍተኛ የመከላከል ስራ መስራት የክልሉን መንግስት ማንቃት እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይ ከጎንደር
እሄን መፈፀም የግድ ይጠበቃል። በመሰረቱ ወያኔ ተጨማሪ ቦታ ይይዛል ብቻ ሳይሆን ጎንደርን ለማዉደም አልሞ
የሚሰራ መሆኑ ታዉቆ ያደረ ነዉ። ስላልተሳካለት እንጂ ለማዉደም ተደጋጋሚ ሞክሯል። አንድ ነገር ግልፅ ልንሆን
የሚገባዉ ወያኔ ለእርቅ ዝግጁ ከመሆኑ በፊት ጎንደርን ማዉደም ትልቁ እቅድ አድርጎ እየሰራ እንደሆነ ነዉ መረዳት
ያለብን። ጎንደርን ሳያወድም ድርድርም ይሁን እርቅ ሞቱ አድርጎ የወሰነ ነዉ። "ለድርድር እንቀመጣለን ወይ" የሚለዉን
ጥያቄ አሁን እርሱት ምላሹ እታች ታገኙታላችሁ። ወያኔ የሚረካዉ ጎንደርን በፈለገዉ ልክ ሲጎዳ ነዉ። እስካሁን
በፈለገዉ ልክ ባለመዉደሟ እንደሞት ቆጥሮታል። እሄ ጉዳት እንዳይደርስ በተፋለመዉ ህዝባችን እንኮራለን። ሌላዉ
ከዚህ በፊት በያዙትና አሁንም እንይዛለን ብለዉ በሚመኙት ቦታ ወልቃይትን መደራደሪያ እናደርጋለን ብለዉ
የሚያስቡ ናቸዉ። የአዲርቃይና የጠለምት አካባቢዎችም እንዳለ ሆኖ ማለት ነዉ።

ስለዚህ የጎንደር ህዝብ ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ መደራጀት፣ መታጠቅና መፋለም እንዲችል በጋራ ያለምንም ልዩነት
መስራት ያስፈልጋል። ወያኔ ተጨማሪ ቦታዎችን እንዳይቆጣጠር በመታገሉ ረገድ ከጎንደር የዞን አመራሮች ጋር ቀርቦና
አብሮ የመከላከሉን ስራ መስራት ይገባናል። እዚህ ላይ በግላጭ ከሚሰራ ነገር ይልቅ ዉስጥን አፍኖ መስራት ይበልጥ
ተጠቃሚ ያደርገናል። የአርማጭሆ ሰዉ " ልብ ያለዉ ሸብ ነዉ" ይላል ሙያ በልብ ነዉ እንደማለት ነዉ።

ሁለተኛ፦ አሁን ወደየትም ልንወረዉረዉ የማንችል ትኩስ ድንቹ እጃችን ላይ ይወድቃል በእኔ ግምገማ ወድቋል።
የትም ልንወረዉረዉ አንችልም። ትኩስ ድንች ያዉ ትኩስ ነዉ በጥበብ እጃችን ላይ እያገላበጥን ማብረድና መጠቀም
የእኛ ፋንታ ነዉ። የወልቃይት ጉዳይ እንደዛ ነዉ። የወልቃይት ጉዳይ በሪፈረንደም የሚከወን እጃችን ላይ የሚወድቅ
ወይም የወደቀ ትኩስ ድንች ስለሆነ በጥበብ አብርደን ለመጠቀም የሚያስችል ብልሃት ከእኛ በእጅጉ ያስፈልጋል።

በእኔ እምነት ከዚህ በፊት ወያኔ ያፈናቀለዉ ከ300,000 በላይ የወልቃይትን ህዝብ የሚተካ ህዝብ ከሶስቱም የጎንደር
ዞኖች አሰባስበን ማሟላት ይኖርብናል፣ በወያኔ ጥቃት ተሰደው በተለያዩ ሀገራት በስደት የሚኖረዉ ወልቃይቴ፣
ወልቃይትን ለቆ በአገር ዉስጥ ከሌሎች አካባቢ ህዝቦች ጋር ትዳር መስርቶ የሚኖሩ የወልቃይት ልጆች ከእነ
ቤተሰባቸዉ፣ ሌላዉ ቀርቶ የዉሸት ጋብቻ እንዲፈፅሙ እያደረግን በልዩ መልኩ ወደ ቦታዉ መመለስና እዛ እንዲከትሙ
ማድረግ አለብን። ወደ ወልቃይት የሚሄደዉ ህዝብ ኑሮዉ በቋሚ ወይም ጊዚያዊም ሊሆን ይችላል። ወጣቱንና
ተቆርቋሪዉ ሰዉ እየሄደ በከተሞችና በልዩ ልዩ ቀበሌዎች፣ ቤት እየሰራ እንዲቀመጥ ማድረግ ያስፈልጋል። በእኔ
እምነት ወልቃይት የኖህ መርከብ ነች። ኖህ ፍጡሮች ከጥፋት ለመዳን በመርከቡ ወንድና ሴት እያደረገ እንዳቆየዉ
ሁሉ ህዝባችንን ወንድና ሴት እያደረግን ወደ ወልቃይት ማስገባትና ማቆየት ወልቃይትን የመታደግ፣ የአማራን ህዝብ
በህይዎት የማቆየት ሀላፊነት አድርገን መውሰድ አለብን። እሄ የህልዉና ጉዳይ ነዉ። ኖህ እኮ ህልዉናን ለማትረፍ ነዉ
እንደዛ ያደረገዉ። ጉዳዩን እንደቀላል ካላየነዉና ሌላ እንዲፈፅመዉ ካልፈለግን በቀር ባልና ሚስት እያደረግን ብዙ ሰዉ
ማስቀመጥ አለብን። ትክክለኛ ጋብቻ የሚፈጥረዉ እንደተጠበቀ ሆኖ የውሸት ጋብቻ ሁሉ እንዲፈፀም ማድረግ
ከቻልን ያኔ ነው ምን ያክል ስለሁኔታው የገባን መሆኑን መረዳት ችለናል የምንለነዉ። ዘመዳሞች የዉሸት ባልና ሚስት
አድርገን እያጋባን ቦታዉን በሚገባ መቆጣጠር ይኖርብናል። ይህ የህልዉና ጉዳይ ነዉ። የክብር ጉዳይ ነዉ። እሄን
ስናደርግ ጥቅሙ ሁለት ነው ወልቃይትን በእጃችን እናስቀራለን እንዲሁም ህዝባችን በቋሚነት በቦታው መኖር ሲጀምር
እዛው ሆኖ ከወያኔ የሚመጣውን ጥቃት በፅናት እንዲከላከል ያደርጋል

ለዚህ ሀሳቤ ደጋፊ የሚሆን አንድ ጥሩ ምሳሌ ልንገራችሁ። ምዕራብ አርማጭሆ በ1994ዓም እና 1995 ዓም ወያኔ
መሬታችንን ለሱዳን ሲሰጥ አንዱ የተጠቀመበት ስልት የሱዳንም ሆነ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች በያዙበት ቦታ እየታየ
ይከለል የሚል ነበር። በሱዳን አርሶ አደሮች እስከተያዘዉ ድረስ ወደ ሱዳን፣ በኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እስከተያዘዉ
ድረስ ወደ ኢትዮጵያ ይከለል የሚል ነበር። ክለላዉ በአርሶ አደሮች ይዞታ ይሁን የሚል ነበር። እንደምታዉቁት የእኛ
ህዝብ ስናር፣ ጎደቤ ፣ አብጥዩር፣ ወዲቁራ፣ኮረደም በሚባሉ የእርሻ ቦታዎች መሬት አለኝ እያለ ጎንደር ነበር ቁጭ
የሚለዉ። የረባ ካምፕ እንኳን አይሰራም ነበር። ሱዳኖች ግን ጓንግን ተሻግረዉ ካምፕ ሰርተዉ እርሻ ባያርሱ እንኳ
መሬቱን የእኛ ነዉ ለማለት ብቻ ካምፕ ሰርተዉ እንሰሳት ይዘዉ ይቀመጡ ነበር። በዚህ ምክንያት ብዙ መሬት
በሱዳኖች እጅ ዉስጥ ነበር። ብዙ መሬት ወደ ሱዳን ሊገባ መሆኑን የተረዱ ዉስን ሰዎች የድንበር ኮሚሽን የትኛዉ
መሬት በሱዳን አርሶ አደሮች እጅ ዉስጥ አለ? የትኛዉ መሬት በኢትዮጵያዉያን አርሶ አደሮች ይዞታ ይገኛል ?
የሚለዉን ለማረጋገጥ ወደ አካባቢዉ ከመምጣቱ በፊት የሱዳኑን ገበሬ ከያዘዉ መሬትና ከሚኖርበት ካምፕ በጥይት
እያባረሩ፣ በሱዳኑ ካምፕ ዉስጥ የእኛን አርሶ አደሮች በግ፣ ፍየልና ዶሮ እየያዙ ባባረሩት የሱዳን ካምፕ ዉስጥ
እንዲቀመጡ አደረጉ። እነሱ አባረሩን እያሉ ቢጮሁ ዉሸት ነዉ እያሉ ጭጭ አሉ። ከዛ የድንበር ኮሚሽን መሬት ላይ
ያለዉን ሊያጣራ ሲመጣ ሱዳኖች በነበሩበት ካምፑ ዉስጥ የሚገኙት የእኛ አርሶ አደሮች በመሆናቸዉ እጅግ ከፍተኛ
መሬት በእኛ (ወደ ኢትዮጵያ) እጅ እንዲቆይ ለማድረግ ተችሎ ነበር። ባንዳንድ አካባቢዎች እስከ 70000 ሄክታር
መሬት ነዉ በእኛ የቆየዉ፣ እሄ አካባቢ 99.99% ዘይት ያለዉ የዓለማችን ምርጡ የሰሊጥ ዓይነት ( White Sesame)
የሚመረትበት ስፍራ ነዉ። ያዉ ከ21 ዓመታት በኋላ በዚህ ጦርነት ፡የተወሰነዉን መልሰዉ ቢወሩንም ቅሉ። በወቅቱ
የሰራነዉ ስራ ሁሉንም ባንታደግም ብዙ ማትረፍ ችለን ነበር። እሄን ያነሳሁላችሁ ድንበሩን አናስከልልም የሚለዉን
ማስቆም ካልቻልን ሌላኛዉን የተሻለ ነገር መከተል የግድ ስለነበር የወሰድነዉ እርምጃ ነበር ። ከአቅም በላይ የሆነ
ችግር ሲያጋጥምህ ሙሉ ለሙሉም ባይሆን የምታተርፍበትን ሌላ መንገድ መቀየስ ትልቅ ብልጠት ነዉ።

እሄን ሀሳብ ያነሳሁት የእኛ ወጣትና ህዝብ ወልቃይት ላይ ሄዶ እንዲከትም ማድረግ የሚኖረዉን ተፅኖ ግምት ዉስጥ
እንድታስገቡት ለማሳሰብ ነዉ። እንደቀላል እንዳታዩት። በቃ እስከመጨረሻዉ እንፋለማለን የሚለዉ ብቻ አዋጭ
አይደለም። በተለይ የአማራ ህዝብ እድሜ ልኩን አንድ ሆኖ የማይናገር ህዝብ በመሆኑ አሸናፊ እንሆናለን ብሎ ማሰብ
ብቻ አስተማማኝ ስልት አይደለም፣ ሁሉ አቀፍ ፍልሚያ መጠቀም ያስፈልጋል። በፍልሚያ ዉስጥ ብዙ ጉዳት
የማያደርስ የተሻለ ስልት መጠቀም ይገባል። በፍልሚያ ወልቃይትን አሳልፈን አንሰጥም ማለት 100% ዋስትና
አይሰጠንም። ተፋልሞ መሸነፍም ይኖራል። እያየነዉም ስለሆነ ። እሄን ሀሳብ (የማስፈሩን ስራ) 100% ብንፈፅም
"ወልቃይት ወደ አማራ ወይስ ወደ ትግሬ" የሚለዉ ሪፈረንደም ቢመጣ በእርግጠኝነት "ወልቃይት ወደ አማራ "
በሚለዉ አሸናፊነት እንዲደመደም ያደርጋል።

• የወልቃይት ልጆች ከሌላዉ አካባቢ ህዝብ ጋር ተጋብተዉ የሚኖሩ ሚስቶቻቸዉን ወይም ባሎቻቸዉን እየያዙ ወደ
ስፍራዉ መሄድ አለባቸዉ፣

• እዚህ ላይ አንድ ተጨማሪ ሀሳብ ላንሳ የወልቃይት ህዝብ ለሪፈረንደሙ ወሳኝ ሚና ለመጫዎት የሚሄደዉን ህዝብ
በቀና መቀበል ይኖርበታል። በነገራችን ላይ በቋሚነት የማይቆይ ሚሽኑን ከፈፀመ በኋላ የሚመለስ ህዝብ ሊሆን
ይችላል። ለሶስትና አራት አመት እዛ ብናቆየዉ ሪፈረንደም ከተካሄደ ድል እናደርግበታለን። በዚህ አጋጣሚ ወልቃይት
ላይ የሚወለድ ህፃን ይበዛል። ማንም የተወለደበትን ቦታ የማይረሳ በመሆኑ የወልቃይት ጉዳይ ዝንተ አለም በእኛ ህዝብ
ይኖራል፣ ሁሌም በወልቃይት ጉዳይ አሸናፊ እንድንሆን ያደርጋል የሚለዉን በሚገባ መገንዘብ ይገባል።

ለዚህም አንድ ምሳሌ ላንሳ 200 ኪሎ የሚመዝን ድንጋይ አንድ ሰዉ ብቻዉን ካለበት ቦታ ሊገለብጠዉ አይችልም።
ልዩ ስልት (ፈልክረም ወይም ድጋፍ በመጠቀም) በመጠቀም ግን በቀላሉ ሊገለብጠዉ ይችላል ።

ሌላዉ ሁላችንም ልብ ልንለዉ የሚገባ መስራት ላይ እንጂ ማልቀስ አናተኩር፣ መታገልና ማልቀስ ይለያያሉ፣ ማልቀስ
አያዋጣም የሚለዉን በሚገባ ማስመር አለብን። ሪትም ቀይሮ መጫዎት መልመድ አለብን። ሰዉ ሲያለቅስ አይተን
ማልቀስ የለብንም።

You might also like