Professional Documents
Culture Documents
Wudase in : Homepage
Wudase in : Homepage
ስንክሳር
የአብይ ጾም ሳምንታት
ኒቆዲሞስ
wudase in ኒቆዲሞስ
ኒቆዲሞስ የሚለው ስም በዮሐንስ ወንጌል ብቻ ከተጻፉ ስሞች መካከል አንዱ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ የዚህን ሰው
ስም ባነሣበት ሥፍራ ሁሉ ‹አስቀድሞ በሌሊት የመጣው› የምትል ቅጽል ያስቀድማል፡፡ ይህ ሰው የአይሁድ አለቃ ነው፡፡
በሀብቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያለ ባለጸጋ ፣ በሹመቱ የአይሁድ ሸንጎ /synagogue/ አባል ፣ በትምህርቱ ደግሞ ጌታችን ራሱ
እንደመሰከረለት ‹የእስራኤል መምህር› የሆነና አዋቂ ነው፡፡ የአይሁድ አለቃ ፣ የእስራኤል መምህር ኒቆዲሞስ ጌታችን
ራሱ ለብቻቸው በቃል ምልልስ እያናገረ ጥያቄያቸውን እየመለሰ ካስተማራቸው ጥቂት ዕድለኛ ሰዎች አንዱም ነው፡፡
ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅነት ያገኘንበትን ምሥጢረ ጥምቀት በጥልቀት እና በዝርዝር የተማረው የመጀመሪያው
ሰውም ኒቆዲሞስ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ጌታችን ጥምቀትን በተግባር ሲመሠርት የዓይን ምስክር እንደነበረ ሁሉ
ጥምቀት በትምህርት ስትመሠረት ደግሞ የዓይን ምስክሩ ኒቆዲሞስ ነው፡፡
በትምህርቱ መካከልም ባቀረበው ጥያቄ ‹ከውኃና ከመንፈስ ዳግመኛ ስለ መወለድ› ጌታችን በምሳሌ አድርጎ ያስተማረው
ሲሆን አላምን ብሎ ‹እንዴት ሊሆን ይችላል?› ብሎ ሲከራከር ደግሞ ገሥጾታል፡፡ ዛሬም ድረስ ኒቆዲሞስ መልስ
ከተሠጣቸው በኋላ የሚነታረኩ ተከራካሪዎች ምሳሌ ሆኖ በሊቃውንት ይጠቀሳል፡፡ እመቤታችን ድንግል ማርያምን
የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት በሙሉ ልብ በመቀበሏ በምናመሰግናት ጊዜም ‹እንደ ዘካርያስ ሳትጠራጠሪ እንደ ኒቆዲሞስ
ሳትከራከሪ ቃሉን የተቀበልሽ› እያልን መሆኑ ይህን እውነታ ያጎላዋል፡፡
ኒቆዲሞስ ወደ ክርስትና ከመጣበት መንገድ ጀምረን በዮሐንስ ወንጌል ስንከተለው ቀስ በቀስ እያደገ የመጣ የመንፈሳዊነት
ደረጃን እናገኛለን፡፡ የኒቆዲሞስ ክርስትና እንደ ወጣኒ (ጀማሪ) እንደ ማዕከላዊና እንደ ፍጹም በሦስት ደረጃዎች ላይ
የሚታይ ሕይወት ሆኖ በዮሐንስ ወንጌል ላይ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ እንደሚከተለው እንመልከተው፡፡
ማዕከላዊው ኒቆዲሞስ
ፈሪሳዊያንና የካህናት አለቆች ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዘውት እንዲመጡ ሎሌዎች ላኩአቸው፡፡ እነዚህ
ሎሌዎች ጌታችንን ይዘው እንዲመጡ ቢላኩም በጌታችን ጣዕመ ትምህርት ተደንቀው ተመስጠው ሲማሩ ውለው ባዶ
እጃቸውን ተመለሱ፡፡ አይሁድ ‹ያላመጣችሁት ስለ ምንድን ነው?›› ብለው ቢጠይቋቸው ‹‹እንደዚህ ሰው ከቶ ማንም
ተናግሮ አያውቅም›› ብለው መለሱ፡፡ ይህን ጊዜ አይሁድ ተቆጥተው ሎሌዎቹን ‹‹እናንተ ደግሞ ሳታችሁ? ከአለቆች
ወይም ከፈሪሳውያን መካከል በእርሱ ያመነ ሰው የለም፡፡ ሕዝቡም ያመነበት ሕግ የማያውቅ ርጉም ስለሆነ ነው›› ብለው
ገሠጹአቸው፡፡ እናንተ ያመናችሁት ባለማወቃችሁ ነው ፤ ከእኛ ከአዋቂዎቹ ማን በእሱ አመነ? ብለው ሊያሸማቅቋቸው
ሞከሩ፡፡ ይህን ሁሉ ሲሆን የማታው ተማሪ የአይሁድ መምህር ኒቆዲሞስ እዚያ ቆሞ ነበር፡፡ ከአለቆች መካከል በጌታ
ያመነ የለም ሲባል እየሰማ ነው፡፡ አሁን ክርስትናው ልትፈተን ነው፡፡ ደፍሮ እኔ አምኜአለሁ ብሎ መናገር ባይችልም ፈራ
ተባ እያለ እንዲህ አለ ‹‹ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን? አላቸው።››
እነሱ በተናገሩት ብቻ ለምን ትፈርዳላችሁ? እሱን ሳትሰሙ መፍረድ ተገቢ ነው ወይ? ማለቱ ነበር፡፡ አይሁድ እንደ
ሎሌዎቹ ሁሉ ኒቆዲሞስን ማቃለል እንዳይችሉ የተከበረ መምህር ሆነባቸው፡፡ ስለዚህ ‹‹አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን?
ነቢይ ከገሊላ እንዳይነሣ መርምርና እይ አሉት። እያንዳንዱም ወደ ቤቱ ሄደ።›› ጌታችን ከገሊላ ናዝሬት መምጣቱን
በመጥቀስ መሲህ ከገሊላ አይነሣም ብለው ሊያስተባብሉ ሞከሩ፡፡ ይህ ግራ መጋባት በሐዋርያው ናትናኤልም የታየ ነበር
እርሱ ‹‹ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልን?›› ብሎ የጠየቀው መሲሁ ከይሁዳ ቤተ ልሔም እንደሚነሣ የተነገረውን
ትንቢት በማየት ነበር፡፡ ጌታችን የተወለደው ከቤተ ልሔም ነው ያደገው ግን በገሊላ ናዝሬት በመሆኑ ነው ይኼ ሁሉ
ውዥንብር፡፡ ኒቆዲሞስ ክርስትናውን በሌሊት ፈርቶ ጀመረ፡፡ አሁን ሙሉ በሙሉ ክርስቲያን ነኝ ብሎ መመስከርና
መግለጥ ባይችልም ቢያንስ አይሁድ ከአለቆች ማን በእርሱ አመነ? ብለው ሲዘብቱ ቢያንስ ድምፁን ለማሰማት ሞከረ፡፡
በጥያቄ አስጨንቆም በዚያች ዕለት ስብሰባውን በተነው፡፡
ፍጻሚው ኒቆዲሞስ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል መከራ ዓለምን የማዳን ሥራውን ፈጸመ፡፡ በዚህ የመከራ ወቅት
በዋለበት የዋሉ ባደረበት ያደሩ ደቀ መዛሙርቱ ከዮሐንስ በቀር በፍርሃት ተበተኑ፡፡ ነፍሱን ከሥጋው ተለይቶ ከመስቀሉ
ሲወርድም አንድም ሐዋርያ አብሮት አልነበረም፡፡ በዚህ ወቅት ኒቆዲሞስ እንደ ቀድሞው ሌሊት እስኪሆን አልጠበቀም፡፡
መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ ከአርማትያው ዮሴፍ ጋር ሆነው የጌታችንን ሥጋ ወሰዱ፡፡ እንደ
አይሁድ የአገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት፡፡ ሲገንዙት እያለቀሱ ነበር ‹‹ሞትከኑ መንሥኤሆሙ
ለሙታን ፤ ደከምከኑ መጽንኤሆሙ ለድኩማን›› ‹‹ሙታንን የምታስነሣ ሆይ ሞትክን? ደካሞችን የምታጸናቸው ሆይ
ደከምክን?›› እያሉ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ጌታችን በመለኮቱ ሕያው እንደመሆኑ አነጋገራቸው፡፡ በነገራቸው መሠረት
‹‹ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት…›› የሚለውን በኪዳን ወቅት የምናደርሰውን ዓለም
አቀፋዊ ጸሎት እያደረሱ ገነዙት፡፡ ኒቆዲሞስ ሲፈራ ፣ ቀስ እያለ ሲናገር የነበረውን ክርስትናውን በአደባባይ ገለጠ፡፡ ‹‹ልቡ
ለጻድቀ ውኩል ከመ አንበሳ›› ‹‹ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ሳይፈራ ይኖራል ›› እንዲል ጠቢቡ በጌታ የደረሰ መከራ
ቢደርስብኝ ሳይል ሥጋውን ተሸክሞ ገነዘ፡፡ ከምኩራብ ያስወጡኛል ብሎ የፈራው ኒቆዲሞስ ቤተ ክርስቲያን እንዳለች
ስለተረዳ በድፍረት ክርስትናውን መሰከረ፡፡ ከሦስቱ የኒቆዲሞስ ክርስትና ደረጃዎች እኛ በየትኛው ላይ ነን? ስለ
ሃይማኖታችንስ በየትኛው ደረጃ እንመሰክራለን፡፡ በጨለማ ነው? ፈራ እያልን ነው ? ወይንስ ያለ ፍርሃት?
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ