Revised Checklist For Lease Financung

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ለማግኘት መሟላት ያለባቸው


መስፈርቶች ዝርዝር

ክፍል አንድ ፡- አስገዳጅ መስፈርቶች (Mandatory Requirements)

1.1 ማመልከቻ፡-
1.1.1 የሊዝ ማመልከቻ

የባንኩ የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት የሚፈልጉ አመልከቾች ጥያቄያቸውን የሊዝ መጠኑንና ሊገለገሉበት
ያቀዱትን የካፒታል ዕቃ ዓይነት በመጥቀስ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
1.1.2 በባንኩ የተዘጋጀውን የሊዝ ማመልከቻ ቅጽ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡

1.2 ፈቃድ ( በስራ ላይ ያለ ድርጅት ከሆነ)


1.2.1 የንግድ ሥራ ፈቃድ
1.2.2 የዋና ምዝገባ የምስክር ወረቀት
1.2.3 የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር

1.3 መሬት/የማምረቻ ቦታ/

የማምርቻ ቦታ፡-

 የክልል መንግስት ሼድ
 የግል የዞታ

1.3.1 የግል ይዞታ ከሆነ


 ከዕዳና ዕገዳ ነፃ የሆነ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ኮፒ፣
 ይዞታውን በመዋጮ ለማቅረብና በመያዣ ለማስመዝገብ ፈቃደኛ የሆነበት ማረጋገጫ ደብዳቤ
በጽሁፍ ማቅረብ አለባቸው፡፡

1.3.2 ከክልል መንግስት በኪራይ የተገኘ ከሆነ


 የማምረቻ ቦታው የኪራይ ዘመን ከካፒታል ዕቃው የኪራይ ዘመን ጋር የተጣጣመና
በሚመለከተው አካል የተመዘገበ መሆን ይኖርበታል፤
 አከራዩ የመንግስት አካል ተከራዩ የማምረቻ ማሽኑን በቦታው መትከል እንደሚችል መፍቀድና
መስማማት ይገባዋል፡፡ ይህም በኪራይ ውሉ መካተት ይኖርበታል፡፡
 ተከራዩ ግዴታውን ባለመወጣቱ የማምረቻ ቦታው ለሶስተኛ ወገን መተላለፍ የሚችል መሆን
አለበት፡፡ ይህም በኪራይ ውሉ መካተት ይኖርበታል፡፡
ማሳሰብያ፡- የክልል ቢሮዎች እና የዲስትሪክት ጽ/ቤቶች የማምረቻ ቦታን በተመለከተ በቅንጅት
የማመቻቸት ኃላፊነት አለባቸው፡፡

1.4 ዋጋ ማሳወቂያ ሰነድ /Pro-forma Invoice/

ለሊዝ አገልግሎት ለሚቀርብ ጥያቄ ከሶስት አስመጪ ወይንም አቅራቢ ድርጅቶች የተሟላ የዋጋ
ማሳወቂያ ሰነድ መቅረብ ያለበት ሲሆን ለሊዝ አገልግሎት ለሚቀርብ ጥያቄ የአዋጭነት ጥናት
ለማከናወን አመልካቹ አንድ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ካቀረቡ በቂ ይሆናል፡፡

1.5 የተሳትፎ የምስክር ወረቀት፡- በባንኩ የተዘጋጀ ስልጠና የወሰደ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተሳትፎ
የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡

1.6 የንግድ ዕቅድ ወይም የአዋጭነት ጥናት ማቅረብ አለበት፡፡

1.7 የድርጅቱ/የግለሰቡ መዋጮ፡


1.7.1 ለስራ ማስኬጃ ወጪ መሸፈኛ የሚውል የ 20% መዋጮ በጥሬ ገንዘብ የሊዝ ዕቃ ጥያቄ
እንደተፈቀደ በባንኩ በሚከፈት ዝግ ሂሳብ ገቢ ለማድረግ ሰለመስማማታቸው በጽሁፍ
ማረጋገጥ፡፡
1.7.2 የመዋጮ ገንዘብ አጠቃቀምን በተመለከተ ባንኩ በሚያስቀምጠው ዕቅድ መሠረት ስራ ላይ
ለማዋል መስማማታቸው የጽሁፍ ማረጋገጫ፡፡

ክፍል ሁለት፡- እንደአስፈላጊነቱ/እንደሁኔታው (Optional Requirements) ተያይዘው የሚቀርቡ


ተጨማሪ ሰነዶች፡-

2.1 ውክልና (ስልጣን)

በሶስተኛ ወገን የሚቀርብ የሊዝ ፋይናንስ ጥያቄ/ማመልከቻ ከሆነ አግባብ ካለው አካል የተረጋገጠ የውክልና
ማስረጃ ባላቸው ወኪሎች መቅረብ ይኖርበታል፡፡

2.2 የቅድመ ሥራ ታሪክ መዝገብ (Track Record)


2.2.1 ሊዝ ጥያቄ አቅራቢው
በስራ ላይ የሚገኝ
አዲስ ስራ ጀማሪ

አመልካች በስራ ላይ ከሆነ ፡-

 የግብር ግዴታ ማስረጃ


 የሂሳብ መግለጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2.2.2 የሂሳብ መግለጫ፡- ከሶስት ዓመት ያልበለጠ ጊዜያዊ/ያልተረጋገጠ የሂሳብ መግለጫ (Provisional
Financial Statements) ወይም በተፈቀደላቸው የሂሳብ መርማሪዎች የታየ (የተጣራ) የሂሳብ
መግለጫዎች (Audited Financial Statements) ማቅረብ አለበት፡፡ ነገር ግን አዲስ ሆኖ የንግድ ስራ ላይ
ካልሆነ ግን የግብር ግዴታና የሂሳብ መግለጫ ማቅረብ አይመለከተውም፡፡

2.3 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ፡

- የማምረቻ ቦታ፡-
መንግስት ሼድ
በግል ይዞታ

አመልካች በግል ይዞታ ላይ የሚሰራ ከሆነ እንደ ኘሬጀክቱ ዓይነት እና ሁኔታ ከሚመለከተው አካል
የማረጋገጫ ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡፡

ነገርግን የሚሰራው በመንግስት ማምረቻ ቦታ ላይ ከሆነ ተከራዩ ይህ የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ማስረጃ
ማቅረብ አይገደድም ሆኖም የማምረቻ ቦታውን የገነባው የክልሉ መንግስት ተገቢውን የአካባቢ ተጽእኖ
ግምገማ ስራን ያከናውናል፡፡

You might also like