Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 17

አራቱ የአምልኮተ እግዚአብሔር መሠረቶች

1) የአምልኮት ስግደት
የመጀመሪያውና ቀዳሚው በአምልኮተ እግዚአብሔር ሕይወት ውስጥ የሚጠቀሰው መንፈሳዊው መሠረት
የአምልኮት ስግደት ነው፡፡
የአምልኮት ስግደት ከስሙ ብቻ ተነሥተን እንደምንረዳው፤ እግዚአብሔርን ስለማምለክ፣ መለኮታዊ ኃይሉን
ስለመያዝ፣ ሰማያዊ እውነትንና ምሪትን ከኑሮ ጋር ለማገናኘት፣ ጸጋና ሞገስን ለመቀበል፣ ከማይሰግዱት የክፉ መናፍስት
ነገድ ለመለየት፣ ሌሎች መንፈሳዊ ምግባራትን ኃይል ለማልበስ የምንሰግደው እንደ እስትንፋስ መለየት የሌለበት
ታላቅ ስግደት ነው፡፡
የአምልኮት ስግደት፤ መስለው በሚኖሩ እና ሆነው በሚኖሩ አማኞች መካከል የተሰመረ መንፈሳዊ ድንበር
ነው፡፡
ልዑል እግዚአብሔር በባሕሪይው አምላክ ስለመሆኑ ተለይቶ በሰዎች ሕይወት ውስጥ የሚገለጥበት ስግደት
ይሄ የፍጥረታት ሁሉ ስግደት ነው፡፡ ቅዱሳኑ ሁሉ በሰማይ መቅደስ ለእግዚአብሔር መገዛታቸውን የሚገልጹበት
ስግደት ነው፡፡ ይህን ስግደት በፈቃዳቸው የማይሰግዱት ብቸኛ ፍጡራን የዲያብሎስ መናፍስት ብቻ ናቸው፡፡ አንድ
ማንኛውም ከፀሐይ በታች ያለ ጤናማና ባለ አቅም አማኝ የሆነ ግለሰብ የአምልኮትን ስግደት ባልሰገደባቸው የሕይወት
ምዕራፎቹ ሁሉ ላይ ከክፉ መናፍስት ምድራዊ ፈቃድ ጋር ተስማምቶ የመኖር ምርጫው ተከብሮለት፤ አንዴ እንደ
ሰው፥ አንዴ እንደ መንፈስ ኑሮው እየተለዋወጠ ዘመኑን ይገፋል፡፡
የአምልኮት ስግደት በጭራሽ ሰግዳችሁ ለማታውቁ ሰዎች ከዚህ ስግደት ተነሡ፡፡ ጸሎት ቦታ በሚገባ
አዘጋጅታችሁ ቢያንስ ቢያንስ በቀን ሁለቴ መስገድ ጀምሩ፡፡
መነሻ የአምልኮት ስግደት
ለአብ እሰግዳለሁ
ለወልድ እሰግዳለሁ
ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ
ምስጋና ይሁን ለአብ
ምስጋና ይሁን ለወልድ
ምስጋና ይሁን ለመንፈስ ቅዱስ
ሃሌሉያ ለአብ
ሃሌሉያ ለወልድ
ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ
በረከቱን ለሰጠን
ኃይሉን ላበዛልን
በዚህ ሰዓት ላቆመን
በቸርነቱ መንገድ ለመራን
በዚህ ሰዓት በጸጋው ለጠበቀን
በብርሃኑ መንገድ ለመራን
ቅዱስ እግዚአብሔር
ቅዱስ ኃያል
ቅዱስ ሕያው
ቅዱስ ኤልሻዳይ
ቅዱስ አዶናይ
ቅዱስ ያሕዌ
ቅዱስ ጸባዖት
ቅዱስ ኢየሱስ
ቅዱስ ክርስቶስ
ቅዱስ አማኑኤል
የድንግል ማርያም ልጅ
ክብር ምስጋና ይግባው
ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
ከጀማሪ አለፍ ላላችሁ፥ መስገድ መንበርከክ የጀመራችሁ ከበታች ያለውን የአምልኮት ስግደት ከ7ቱ ጸሎተ
ሰዓታት ውስጥ ችላችሁ ጸሎት በገባችሁበት ሰዓት ሁሉ ስገዱ፡፡
41 የአምልኮት ስግደት
እሰግድ ለአብ ቅዱስ ያሕዌ
እሰግድ ለወልድ ቅዱስ ጸባኦት
እሰግድ ለመንፈስ ቅዱስ ቅዱስ እብኖዲ
እሰግድ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ (3X) ቅዱስ ታዖስ
ስብሐት ለአብ ቅዱስ ኢየሱስ
ስብሐት ለወልድ ቅዱስ ክርስቶስ
ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ቅዱስ አማኑኤል
ምስጋና ለአብ እስከዚች ጊዜ ላደረሠን
ምስጋና ለወልድ በመለኮቱ ኃይል ለጠበቀን
ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ ፍጹም ፍቅሩን ለሰጠን
ሃሌሉያ ለአብ ቸርነቱን ላበዛልን
ሃሌሉያ ለወልድ በብርሃኑ መንገድ ለመራን
ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ኃጢአታችንን ለታገሠልን
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ (3X) በሥጋወ ደሙን ለባረከን
ቅዱሰ እግዚአብሔር ለድንግል ማርያም ልጅ
ቅዱስ ኃያል ለልዑል እግዚአብሔር
ቅዱስ ሕያው አምልኮም ምስጋናም ክብርም ይግባው
ቅዱስ አዶናይ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን፡፡
ቅዱስ ኤልሻዳይ
ኃይል ሲያጥራችሁ፤ ነፍሳችሁ የዛለች እንደሆነ ሲታወቃችሁ፤ መንፈሳዊ ጉልበት ሲደክምባችሁ በአምልኮት
ስግደት በኩል እንደገና መታደስ ትችላላችሁ፡፡
የመንፈስ ቅዱስን ኃይል መሳቢያ የአምልኮት ስግደት
ለአብ እሰግዳለው ለንስረ ትንቢት ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው
ለወልድ እሰግዳለው ለሃይማኖት መሪ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው
ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለው ለእምነት መምህር ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው
እግዚአብሔር አብ ምስጉን ነው ለቅዱሳን ጌጥ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው
እግዚአብሔር ወልድ ምስጉን ነው ለጻድቃን አክሊል ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ምስጉን ነው ለሰማዕታት መመኪያ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው
መንፈስ ቅዱስ ሆይ ወደኔ ና 3X ለሕይወት መብረቅ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው
ጵራቅላጦስ ሆይ ወደኔ ና 3X ነብያትን ላናገረ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው
መለኮተ እሳት ሆይ ወደኔ ና 3X ሐዋሪያትን ለመራ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው
ለንጽሕና መንፈስ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው ድንግል ማርያምን ለከደነ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው
ለቅድስና መንፈስ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው መልአክትን ላሰለጠነ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው
ለእውነት መንፈስ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው መናፍስትን ለሚያሳድድ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው
ለስጦታ ምንጭ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው መንፈስ ቅዱስ ሆይ ኃይልን አብዛልኝ
ለእውቀት ፋና ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው መንፈስ ቅዱስ ሆይ ጉልበትን ስጠኝ
ለቸርነት ብርሃን ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው መንፈስ ቅዱስ ሆይ ጽናትን አካፍለኝ
ለእሳት ጎርፍ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው መንፈስ ቅዱስ ሆይ ብርታትን ላክልኝ
ለመለኮታዊ እርግብ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው መንፈስ ቅዱስ ሆይ ጸጋን ስደድልኝ፡፡
ለወርቅ ልብስ ጵራቅሊጦስ እሰግዳለው
በየዕለቱ በተለያየ የውጊያ አቅጣጫ እየመጡ የሚፈትኑትን የዲያቢሎስ መናፍስት በቅዱሳን ስም ግንባር ላይ
እንዲታሰሩ ትእዛዝ ሰጥቶ አብራችሁ ስገዱ በማለት በአምልኮት ስግደት ማድከምና መወጋት ይገባል፡፡
መናፍስትን የሚቀጠቅጥ የአምልኮት ስግደት
እሰግድ ለአብ ለሚያንቀጠቅጥ መለኮታዊ ግርማ እሰግዳለሁ
እሰግድ ለወልድ ለሚንቦገቦግ መለኮታዊ ነበልባል እሰግዳለሁ
እሰግድ ለመንፈስ ቅዱስ ላማረ መለኮታዊ ጋሻ እሰግዳለሁ
እሰግድ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ 3X ለስኩረ ኃይል መለኮታዊ ጦር እሰግዳለሁ
ቅዱሰ እግዚአብሔር ኃይል ሁነኝ ለሚያቃጥል መለኮታዊ ግለት እሰግዳለሁ
ቅዱስ ኃያል ሥልጣን ሁነኝ ለአሸናፊ መለኮታዊ እዘዝ እሰግዳለሁ
ቅዱስ ሕያው ብርታት ሁነኝ ለረቀቀ መለኮታዊ ሥልጣን እሰግዳለሁ
ቅዱስ አዶናይ ጉልበት ሆነኝ ለብርሃናዊ መለኮታዊ ጸዳል እሰግዳለሁ
ቅዱስ ኤልሻዳይ ግርማ ሁነኝ ለተሳለ መለኮታዊ ሰይፍ እሰግዳለሁ
ቅዱስ ያሕዌ ጽናት ሁነኝ ለሚያስፈራ መለኮታዊ ቃል እሰግዳለሁ
ቅዱስ ጸባዖት ምርኩዝ ሁነኝ ለአስደናቂ መለኮታዊ ነበልባል እሰግዳለሁ
ቅዱስ ማስያስ በረከት ሁነኝ ለሚቆራርጥ መለኮታዊ ገጀሞ እሰግዳለሁ
ቅዱስ ትስቡጣ ጸጋና ሞገስ ሁነኝ ለንጹሕ መለኮታዊ ባሕርይ እሰግዳለሁ
ቅዱስ ኢየሱስ ለጽኑ መለኮታዊ ምሣር እሰግዳለሁ
ቅዱስ ክርስቶስ ለምጡቅ መለኮታዊ ተራራ እሰግዳለሁ
ቅዱስ አማኑኤል አሜን፡፡ ለተነጣጠረ መለኮታዊ ቀስት እሰግዳለሁ
ለሚያስደነግጥ መለኮታዊ መብረቅ እሰግዳለሁ ለትኩስ መለኮታዊ ሙቀት እሰግዳለሁ
ለተንቦገቦገ መለኮታዊ ፍሕም እሰግዳለሁ ነበልባሉን ላስረዘመ መለኮታዊ እሳት እሰግዳለሁ
ለተወርዋሪ መለኮታዊ ቀስት እሰግዳለሁ ለአሸናፊ መለኮታዊ ኃይል እሰግዳለሁ
ለሚያቃጥል መለኮታዊ እሳት እሰግዳለሁ ገዥነት ላለው መለኮታዊ ገናንነት እሰግዳለሁ
ለሚያበራ መለኮታዊ ፋና እሰግዳለሁ የአድማስ ስፋት ላለው መለኮታዊ ብርሃን እሰግዳለሁ
ለአንጸባራቂ መለኮታዊ ፀሐይ እሰግዳለሁ በእሳት ለተከበበ መለኮታዊ ዙፋን እሰግዳለሁ
ክቡድ ለሆነ ዕብነ መለኮት እሰግዳለሁ እውነት በእውነት ለዘላለሙ አሜን፡፡
በተመሳሳይ ከጸጋ ስግደት ጋር በማጣመር ክፉ መናፍስትን በእንዲህ መልክ መዋጋት ይቻላል፡፡
መናፍስትን የሚቀጠቅጥ የአምልኮትና የጸጋ ስግደት
እሰግዳለሁ ለአብ 3X ንግሥት ሆይ አሰልጥኚኝ የክፋትን መንፈስ
አሸንፈው ዘንድ
እሰግዳለሁ ለወልድ 3X
ንግሥት ሆይ አሰልጥኚኝ የእባቡን ራስ እቀጠቅጠው
እሰግዳለሁ ለመንፈስ ቅዱስ 3X
ዘንድ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ 3X
ንግሥት ሆይ አሰልጥኚኝ በልጅሽ መስቀለ ፍላጻ
ምስጋና ለአብ እነድፈው ዘንድ
ምስጋና ለወልድ ንግሥት ሆይ አሰልጥኚኝ በመለኮት ሰይፍ እቆርጠው
ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ ዘንድ

ሃሌሉያ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ንግሥት ሆይ አሰልጥኚኝ በልጅሽ የጸናች ክንድ
እጥለው ዘንድ
ሃሌሉያ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
ንግሥት ሆይ እሰልጥኚኝ በአርያም እሳት አቃጥለው
ሃሌሉያ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ዘንድ
ስብሐት ለእግዚአብሔር አብ ድንግል ሆይ የጠላቴን የልቡን አሳብ ዘርዝሪ
ስብሐት ለእግዚአብሔር ወልድ ድንግል ሆይ የጠላቴን እጅ እግር እሰሪ
ስብሐት ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ድንግል ሆይ የጠላቴን ኃይሉን አድክሚ
ድንግል ማርያም ሆይ ወደኔ ነይ 3X ድንግል ሆይ የጠላቴን ክንፍ ስበሪ
ማኅደረ መለኮት ሆይ ወደኔ ነይ 3X ድንግል ሆይ የጠላቴን አንደበቱን ለጉሚ
ወላዲተ አምላክ ሆይ ወደኔ ነይ 3X ድንግል ሆይ የጠላቴን ምክር ከሕሊናው ሰውሪ
የአዶናይ እግዚአብሔር እናት ምስጋና ላንቺ አሜን።
የኤልሻዳይ እግዚአብሔር እናት ምስጋና ላንቺ ቅዱስ እግዚአብሔር ኃይልህን አካፍለኝ
የጸባኦት እግዚአብሔር እናት ምስጋና ላንቺ ቅዱስ ኃያል ሞገስህን አልብሰኝ
የመለኮት ዙፋን ሆይ እታመንሻለው ቅዱስ ሕያው ጥበቃህ አይለየኝ
የአርያም እህት ሆይ እታመንሻለው ቅዱስ አዶናይ በረከትን ስጠኝ
መንፈሳዊት መርከብ ሆይ እታመንሻለው ቅዱስ ኤልሻዳይ ድካሜን አስችለኝ
መቅረዝ የብርሃን እናት ቅዱስ ያሕዌ ጥበብን ለግሰኝ
ንጽሕት ጥጃ የነጭ በሬ እናት ቅዱስ ጸባኦት ሠራዊትህን ላክልኝ
ልዕልት በአርያም የሚኖር የልዑል እናት ቅዱስ ኢየሱስ መድሃኒት ሁነኝ
ውድስት የምስጉን እናት ቅዱስ ክርስቶስ ኑሮዬን ቀድስልኝ
ቤተመንግሥት የመሲሕ እናት ቅዱስ አማኑኤል ከኛ ጋር ይሁን
መቅደስ የሊቀ ካህናት እናት ለዘላለሙ አሜን፡፡
ምንም አይነት መንፈሳዊ ክንውን አድርጉ ስግደት (በተለይ የአምልኮት) ከሌለው ጎዶሎ ነው፡፡ ጸሎት ያለ
ስግደት ኃይሉ አያድግም፡፡ ጾሞ ያለ ስግደት በረከቱ አይጨምርም፡፡ ቅዱስ ቁርባን ያለ ስግደት ጸጋን አይገልጥም፡፡
እየሰገዳችሁ መንፈሳዊ ምግባራትን ስታደርጉ ለነዚያ ተግባራት ሰማያዊ ኃይል ሰጣችሁ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ስ-ገ-
ዱ!! እዚህም እያመሰገናችሁ ስገዱ፡፡
የምስጋና የአምልኮት ስግደት
ለአብ እግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ለወልድ እግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ለመንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የአካል ሦስትነቱ ለማይጎድል ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የመለኮቱ አንድነት ለማይከፋፈል ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የአማልክቶች አምላክ ለሚሆን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የጌቶች ጌታ ለሚሆን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የነገሥታት ንጉሥ ለሚሆን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የገዥዎች ገዢ ለሚሆን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የግሩማን ግሩም ለሚሆን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የልዑላኖች ልዑል ለሚሆን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ከከበሩ ይልቅ ለሚከብር ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
እንደርሱ ያለ ንጉሥ ለማይኖር ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ለዘላለም ሕያው ሆኖ ለሚኖር ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ልዕልናው ሊነገር ለማይቻል ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
አዳራሹ ጽርሐ አርያም ለሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
መገኛው በአጸደ ትጉሃን ለሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
መቅደሱ በተራራ ላይ ለሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ድንኳኑ የጽድቅ ብርሃን ለሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ማደሪያው በኢዮር ሰማይ ለሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
መቀመጫው የእሳት አትሮንስ ለሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ሠረገላው የነፋስ ባሕርይ ለሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ፍለጋው ንጹሕ ለሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ፍርዱ ለማይለወጥ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ቃሉ ለማይታበል ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
እውነቱ ለማይዛባ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
አድልዎ ለሌለበት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
በምክሩ ለሚጠበብ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
በሥራው ለተደነቀ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ርኩሳንን ለሚቀድስ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የተዳደፉትን ለሚያነፃ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የተረገሙትን ለሚባርክ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ድውያንን ለሚፈውስ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ችግረኞችን ለሚረዳ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የድኩማን ኃይል ለሚሆን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የሐንካሳን ምርኩዝ ለሚሆን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ያዘኑትን ለሚያጽናና ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የተከዙትን ለሚያስደስት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ብቸኞችን ለሚያረጋጋ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የወደቁትን ለሚያነሣ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የጠፉትን ለሚፈልግ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የተራቡትን ለሚያበላ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የተጠሙትን ለሚያጠጣ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የሰጠሙትን ለሚያመጥቅ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የታረዙትን ለሚያለብስ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የተኙትን ለሚያነቃ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የተጣሉትን ለሚያስታርቅ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ትሑታንን ለሚያከብር ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ትዕቢተኞችን ለሚያዋርድ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ክፉዎችን ለሚያራራ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ቂመኞችን የዋህ ለሚያደርግ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ሰነፎችን ለሚያበረታታ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የክፋትን መርዝ ለሚያፈርስ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የሴራን ምክር ለሚያከሽፍ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ስህተትን ለሚያርም ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
የአረጋዊያንን ዕድሜ ለሚያረዝም ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ጎልማሶችን ለሚያገርም ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
መዓቱን በይቅርታ ለሚሰውር ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
መቅሠፍቱን በምሕረት ለሚሸፍን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
ፍቅሩ ለማይደርቅ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል
በሰማይና በምድር በባሕርና በቀላያት ሁሉ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል፡፡
ከዚህ በታች ያሉትም እንዲሁ የአምልኮት ስግደቶች ናቸው፡፡ በደንብ የበረታችሁና የአምልኮት ስግደት ኃይል
የገባችሁ ሁሉ ልትሰግዷቸው የሚገባ ስግደቶች ናቸው፡፡ በተለያየ ጊዜና የጸሎት ሰዓት እያቀያየራችሁ በመስገድ
በርቱ፡፡
የአምልኮት ስግደት
ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወደኔ ና 3X መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ብርሃን ነው 3X
አማኑኤል ሆይ ወደኔ ና 3X አንዱ አብ ቅዱስ ነው 3X
መድኅኒተዓለም ሆይ ወደኔ ና 3X አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው 3X
ለአብ እሰግዳለሁ 3X አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው 3X
ለወልድ እሰግዳለሁ 3X ምስጋና ይሁን ለአብ 3X
ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ 3X ምስጋና ይሁን ለወልድ 3X
አብ ቅዱስ ነው 3X ምስጋና ይሁን ለመንፈስ ቅዱስ 3X
ወልድ ቅዱስ ነው 3X ሃሌሉያ ለአብ 3X
መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው 3X ሃሌሉያ ለወልድ 3X
አብ ፀሐይ ነው 3X ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ 3X
ወልድ ፀሐይ ነው 3X በረከቱን ለሰጠን
መንፈስ ቅዱስ ፀሐይ ነው 3X ኃይሉን ላበዛልን
አብ ፍቅር ነው 3X በዚህ ሰዓት ላቆመን
ወልድ ፍቅር ነው 3X በቸርነቱ መንገድ ለመራን
መንፈስ ቅዱስ ፍቅር ነው 3X በዚህ ሰዓት በጸጋ ለጠበቀን
አብ እሳት ነው 3X በብርሃኑ ኃይል ለመራን
ወልድ እሳት ነው 3X ክብር ምስጋና ይግባው
መንፈስ ቅዱስ እሳት ነው 3X ቅዱስ እግዚአብሔር
አብ ጉንድ ወይን ነው 3X ቅዱስ ኃያል
ወልድ ጉንድ ወይን ነው 3X ቅዱስ ሕያው
መንፈስ ቅዱስ ጉንድ ወይን ነው 3X ቅዱስ ኤልሻዳይ
አብ የሃይማኖት መሠረት ነው 3X ቅዱስ አዶናይ
ወልድ የሃይማኖት መሠረት ነው 3X ቅዱስ ያሕዌ
መንፈስ ቅዱስ የሃይማኖት መሠረት ነው 3X ቅዱስ ጸባኦት
አብ መለኮታዊ ቀስት ነው 3X ቅዱስ ኢየሱስ
ወልድ መለኮታዊ ቀስት ነው 3X ቅዱስ ክርስቶስ
መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ቀስት ነው 3X ቅዱስ አማኑኤል
አብ መለኮታዊ ብርሃን ነው 3X የድንግል ማርያም ልጅ
ወልድ መለኮታዊ ብርሃን ነው 3X አምልኮም ክብርም ምስጋናም ይግባው፡፡
የአምልኮት ስግደት
በአብ ሰም አመልካለሁ 3X ወልድ መለኮታዊ ወርቅ ነው 3X
በወልድ ስም እታመናለሁ 3X መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ወርቅ ነው 3X
በመንፈስ ቅዱስ ስም እባረካለሁ 3X አብ መለኮታዊ ጦር ነው 3X
ለአብ እሰግዳለሁ 3X ወልድ መለኮታዊ ጦር ነው 3X
ለወልድ እሰግዳለሁ 3X መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ጦር ነው 3X
ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ 3X ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ይገባል 3X
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ 3X ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል 3X
አብ አልፋና ኦሜጋ ነው 3X ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ መገዛት ይገባል 3X
ወልድ አልፋና ኦሜጋ ነው 3X ለጌታዬ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል 3X
መንፈስ ቅዱስ አልፋና ኦሜጋ ነው 3X ለንጉሤ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል 3X
አብ የባሕርይ አምላክ ነው 3X ለአምላኬ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል 3X
ወልድ የባሕርይ አምላክ ነው 3X ለአለቃዬ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል 3X
መንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክ ነው 3X በረከቱን ላካፈለን
አብ ነድ ነው 3X ኃይሉን ላበዛልን
ወልድ ነድ ነው 3X በዚህ ሰዓት ላዳረሰን
መንፈስ ቅዱስ ነድ ነው 3X በዚህ ቦታ ላይ ላቆመን
አብ ፍሕም ነው 3X በቸርነቱ መንገድ ለመራን
ወልድ ፍሕም ነው 3X ሥጋወ ደሙን ለኛ ለሰጠን
መንፈስ ቅዱስ ፍሕም ነው 3X ክብር ምስጋና አምልኮት ይድረሰው
አብ ነበልባል ነው 3X ቅዱስ እግዚአብሔር
ወልድ ነበልባል ነው 3X ቅዱስ ኃያል
መንፈስ ቅዱስ ነበልባል ነው 3X ቅዱስ ሕያው
የተመሰገነ አብ ልዑል ነው 3X ቅዱስ ኤልሻዳይ
የተመሰገነ ወልድ ልዑል ነው 3X ቅዱስ አዶናይ
የተመሰገነ መንፈስ ቅዱስ ልዑል ነው 3X ቅዱስ ያሕዌ
የተመሰገነ አብ ታላቅ ነው 3X ቅዱስ ጸባኦት
የተመሰገነ ወልድ ታላቅ ነው 3X ቅዱስ ኢየሱስ
የተመሰገነ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ ነው 3X ቅዱስ ክርስቶስ
የተመሰገነ አብ ክቡር ነው 3X ቅዱስ አማኑኤል
የተመሰገነ ወልድ ክቡር ነው 3X ለወላዲተ አምላክ ልጅ
የተመሰገነ መንፈስ ቅዱስ ክቡር ነው 3X መገዛት መስገድ ይገባል
አብ መለኮታዊ ወርቅ ነው 3X ለዘላለሙ አሜን፡፡
የአምልኮት ስግደት
ጸባኦት ሆይ ወደኔ ና 3X መንፈስ ቅዱስ የትሩፋት አበጋዝ ነው 3X
እብኖዲ ሆይ ወደኔ ና 3X አንድ እግዚአብሔር የባሕሪይ ባለጸጋ ነው 3X
ማስያስ ሆይ ወደኔ ና 3X ምስጋና ይገባል ለአብ 3X
ለአብ እሰግዳለሁ 3X ምስጋና ይገባል ለወልድ 3X
ለወልድም እሰግዳለሁ 3X ምስጋና ይገባል ለመንፈስ ቅዱስ 3X
ለመንፈስ ቅዱስም እሰግዳለሁ 3X ሃሌሉያ ለአብ 3X
አብ የብርሃን አዕማድ ነው 3X ሃሌሉያ ለወልድ 3X
ወልድ የብርሃን አዕማድ ነው 3X ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ 3X
መንፈስ ቅዱስ የብርሃን አዕማድ ነው 3X ስብሐት ለአብ 3X
አንድ እግዚአብሔር ጽኑ ፍሕም ነው 3X ስብሐት ለወልድ 3X
አብ የመባርቅት ብልጭታ ነው 3X ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ 3X
ወልድ የመባርቅት ብልጭታ ነው 3X እውነትንና ኃይልን በቸርነቱ የሚሰጠን
መንፈስ ቅዱስ የመባርቀት ብልጭታ ነው 3X ፍቅርና ጸጋን በየጊዜው ያካፈለን
አንድ እግዚአብሔር ባለ ግርማ ነው 3X አምላክ ሲሆን አባት የሆነን ጌታ
አብ የእሳት ባሕሪይ ነው 3X በጤናና በበረከት ኃይል ያቆየን
ወልድ የእሳት ባሕሪይ ነው 3X ለገሩ ንጉሥ መድኃኒዓለም
መንፈስ ቅዱስ የእሳት ባሕሪይ ነው 3X ለጌትነቱ ፍጹም ምስጋና ይግባው
አንድ እግዚአብሔር የመለኮት ነበልባል ነው 3X ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ኃያል ነው 3X
አብ እውነተኛ ፀሐይ ነው 3X ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ ኃያል ነው 3X
ወልድ እውነተኛ ፀሐይ ነው 3X ቅዱስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ኃያል ነው 3X
መንፈስ ቅዱስ እውነተኛ ፀሐይ ነው 3X ቅዱስ እግዚአብሔር
አንድ እግዚአብሔር የዓለም ብርሃን ነው 3X ቅዱስ ኃያል
አብ የመለኮት ጦር ነው 3X ቅዱስ ሕያው
ወልድ የመለኮት ጦር ነው 3X ቅዱስ ጸባኦት
መንፈስ ቅዱስም የመለኮት ጦር ነው 3X ቅዱስ አዶናይ
አንድ እግዚአብሔር የእምነት ጋሻ ነው 3X ቅዱስ ኤልሻዳይ
አብ ሰማያዊ መርከብ ነው 3X ቅዱስ ያሕዌ
ወልድ ሰማያዊ መርከብ ነው 3X ቅዱስ ኢየሱሰ
መንፈስ ቅዱስ ሰማያዊ መርከብ ነው 3X ቅዱስ ክርስቶስ
አንድ እግዚአብሔር የጽድቅ መልሕቅ ነው 3X ቅዱስ አማኑኤል
አብ የትሩፋት አበጋዝ ነው 3X ምስጋና አምልኮትና ውዳሴ ይግባው
ወልድ የትሩፋት አበጋዝ ነው 3X ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን፡፡
2) ጸሎት
ሁለተኛው የአምልኮተ እግዚአብሔር የመሠረት ክፍል ጸሎት ነው፡፡ ጸሎት እግዚአብሔርን [እና ቅዱሳኑን]
የማነጋገሪያ መንፈሳዊ ቋንቋ ነው፡፡ ጸሎት እግዚአብሔርና የእግዚአብሔር እስትንፋስ(ነፍስ) የሚገናኙበት መለኮታዊ
ድልድይ ነው፡፡ ጸሎት ከሰማይ በላይ ያሉ ቅዱሳንን መግባቢያ ልዩ ቃል ነው፡፡
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ሰማያዊም ምድራዊም ፍጡር እስከሆነ ድረስ ሁለቱንም የማንነቱን ክፍል አስማምቶ
ሊኖር ያስፈልገዋል፡፡ ሰማያዊ ብቻ ልሁን እንዳይል በመሬታዊነቱ በኩል ራሱን የቻለ ሥጋዊ ግብሮችና ፍላጎቶች
የግድ ይኖሩበታል፡፡ ምድራዊ ብቻ ልሁን ካለ ደግሞ ሰማያዊነትን የተገፈፉት የዲያቢሎስ መናፍስትን አሊያም ሰማያዊ
መሆን የማይችሉትን እንስሳት ሆነ ማለት ነው፡፡
ጸሎት ቤት ስዕለ አድኖ አቀማመጥ
➢ በመቆም ልክ ከግንባር ትይዩ የሥላሴ ፥ ከግራ የመድኃኒዓለም ፥ ከቀኝ የስቅለቱ
➢ በመንበርከክ ልክ ከግንባር ትይዩ የእመቤታችን ፥ ከግራ የቅዱስ ሚካኤል ፥ ከቀኝ የቅዱስ ገብርኤል
➢ ከበታች የሌሎች ቅዱሳንን ስዕለ አድኖ
ሰባቱ የጸሎት ሰዓታት

ለሊት 11:00 ☞ ውዳሴ ማርያም፣ ሰይፈ መለኮት፣ ሰይፈ ሥላሴ የዘወትር

ጠዋት 3:00 ☞ መልክአ ገብርኤል፣ መዝሙረ ዳዊት፣ አርጋኖን

ቀትር 6:00 ☞ መልክአ ሚካኤል፣ መልክአ ሥላሴ

ቀን 9:00 ☞ መልክአ መድኃኒዓለም፣ መልክአ ዑራኤል

ከሰዓት 11:00 ☞ ውዳሴ ማርያም፣ ሰኔ ጎለጎለታ፣ የምሕላ ጸሎት፣ መልክአ ፋኑኤል

ማታ 3:00 ☞ አርጋኖን፣ መልክአ ሩፋኤል

እኩለ ለሊት 6:00 ☞ መልክአ ሥላሴ፣ መልክአ ሚካኤል፣ መዝሙረ ዳዊት

ለሊት 9:00 ☞ መልክአ ኢየሱስ፣ መልክአ ማርያም (አማራጭ)


የጸሎት አደራረግና የመናፍስት ውጊያ አካሄድ

1ኛ መጀመሪያ ጸሎት ቤታችሁ (ትንሽዬ ቤተመቅደሳችሁ) ከመግባታችሁ በፊት ፊታችሁንና እጅ እግራችሁን


ታጥባችሁና ንጹሕ ሆናችሁ ተዘጋጁ፡፡ ደመ ጽጌ (ለሴቶች) በሚሆንበት ወቅት ከተቻለ ሙሉ ሰውነት ታጥባችሁ
ቢሆን መልካም ነው፡፡
ምክንያቱም፦ ለእግዚአብሔር ንጹሕ መሥዋዕት ይሰጣልና፡፡ የጸሎት ቦታን የማክበር መግለጫ ነው፡፡

2ኛ ከተቻለ ነጭ አልባስ ብትለብሱ መልካም፡፡ ካልሆነ ግን ነጠላ አይጠፋም፡፡


ምክንያቱም፦ ክርስቶስ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ብሏልና ነጭ ብርሃንነቱን ወክለን በእኔ የሚመላለስ ብርሃን ይሆንለታል
እንጂ በጨለማ አይመላለስም ያለውን የተስፋውንና የቃልኪዳኑን ቃል እንይዛለንና፤ ብርሃንነቱን በነጭ ነጠላ
እንገልጻለን፡፡
3ኛ እንደ ገባን በመቆሞ ልክ ከሥላሴ ስዕል ትይዩ እንሆንና ሦስት ጊዜ እናማትባለን፡፡ ካማተብንም በኋላ በቅዱሳን
ስሞቹ ጸሎታችንና ስግደታችንን በመባረክ፤ በሰዓቱ እና በጊዜው ላደረሰን እና ላቆመን አምላክ ምስጋና ከማድረስ
መጀመር፡፡

4ኛ በመቀጠል መዝሙር 22'ን እንደ መግቢያ ጸሎት መጸለይ፡፡


[ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን
አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት
ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው። ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም
እኖራለሁ። ]

5ኛ አስከትለን በዛው "አባታችን ሆይ" እንላለን

6ኛ ቀጥለን ከቆምንበት የሥላሴ ትይዩ ስዕል ሆነን ጸሎታትችንን እንዲባርክልና እንዲያጸድቅልን ጠይቀን
የአምልኮት ስግደት መስገድ፡፡

7ኛ ስንጨርስ ተንበርክከን የሰዓቱን ጸሎት ማለትም ለምሳሌ ምሽት 3፡00 ከሆነ ጸሎተ አርጋኖን፤ ሌሊት 11፡00
ከሆነ ውዳሴ ማርያም ማድረስ፡፡

8ኛ በአባታችን ሆይ የሰዓቱን ጸሎት መዝጋት

9ኛ የግል ጸሎታችንን ማድረስ (ርዕስ ሰጥተን የምናደርሰው ወይንም የምንጠይቀው የግል ጸሎት)

10ኛ ጸሎቱን ካደረስንም በኋላ መቁጠሪያችንን አንስተን በመለኮተ ስሞቹ በመባረክ፤ በመቀጠል አሁንም በመለኮተ
ስሞቹና የቅዱሳንን ስሞች እየጠሩ ጠላትን መቀጥቀጥ፡፡ የመሸጉ ክፉ መናፍስትን ለመለየት ጀርባን፣ ሁለቱንም
ትከሻዎች፣ ጭንቅላትንና ሆድን በእምነት ስሞች ተቃጠል እያሉ መቀጥቀጥ፡፡

11ኛ በመቀጠል ሁለተኛ የአምልኮት ስግደት መስገድ፡፡ ያደፈጠውን መንፈስ ግንባር ላይ በሰማያዊ ስሞች
አስረነው፤ ግንባራችንን የእንጨት መስቀል ላይ አሊያ ቅዱሳን ስዕላት ላይ ወይንም ጸሎተ መጽሐፍ ላይ እያስነካን
ስንሰግድ፤ መንፈሱ በጣም ይቃጠላል፡፡ አስቀድሞ ከሰገድነው የአምልኮ ስግደት ይኸኛው የሚለየው ይሄ መንፈሱን
ካዳከምን በኋላ፤ የጠላት መንገድ ለመዝጋትና ለማዳከም 'አብረኸኝ ስገድ' ብለን ትእዛዝ ሰጥተን ስለምንሰግድ ነው፡፡

13ኛ መናፍስቶች ሠራዊት እንዳይስቡና ከሌሎች መንፈሶች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይፈጥሩ በቅዱሳን
ስም ማዘዝና ግንባር ላይ እንዲታሰሩ መንገር

14ኛ ጸሎታችንንና ስግደታችንንም ተቀበለን ብለን ከሁለተኛው ስግደት በኋላ መዝጊያ ጸሎት እንጸልይና
በአባታችን ሆይ እንጨርሳለን፡፡
3) መቁጠሪያ
በአምልኮተ እግዚአብሔር የእምነት ጎዳና ላይ፤ እግዚአብሔርን ማምለክ ለማስቆም እግዚአብሔርን
የማያመልኩት የጽልመት መናፍስት በምድር የሚመላለሱትን የሰው ልጆችን ሁሉ በዘመናቸው ላይ ይዋጉ ዘንድ
ግዴታ ነው፡፡ "ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ
ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።" (የዮሐንስ ራእይ 12፥9)
የሰው ልጆች ከተፈጠሩበት የመጀመሪያዋ ቀን አንስቶ፤ ተቃራኒ ባላንጣ በመሆን ከአምላክ ፈቃድና እቅፍ
ለይቶ ወደ ክህደትና የኃጢአት መንገድ ለማስገባት የዲያቢሎስ ነገድ ጠላትነትን ይዞ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ
ይዋጋል፡፡
ይሄን የሰው ልጆች ሁሉ ጠላት መዋጋት ምርጫችን አይደለም፡፡ ምክንያቱም በመረረ ጥላቻና ምቀኝነት
የሚያየን ክፉው ኃይል ብንዋጋውም ይዋጋናል፥ ባንዋጋውም ይዋጋናል፡፡ "አይ አልዋጋውም ከእኔ ጋር ምን
አደራረሰን?" ብለህ ስትቀመጥ፤ ብቸኛው ተጎጂ አንተና የአንተ የሆነው ሁሉ ይሆናል፡፡
መቁጠሪያ ለምን ከአምልኮተ እግዚአብሔር መሠረት እንደ አንዱ ሆነ ቢባል፤ ያለ መቁጠሪያ መንፈሳዊ
ልምምድን ስናከናውን ይዋጋን ዘንድ ያለው ያደፈጠ መንፈስ ይህን የቅድስና ተግባራት በርትተን እንዳናዘወትራቸው
በተለያየ ስልት ይፋለማል፡፡ በመሆኑም ሥራዎቹን የምታፈርስበት የውጊያ ኃይል ከሌለህ የሥጋ ድክመት አለብህና
በየቀኑ ሲታገልህ ሲታገልህ ያደክምሃል፡፡ ነገር ግን ስግደትንና ጸሎትን ከመቁጠሪያ ጋር አስተባብረህ ስታስኬደው፤
የእግዚአብሔርን ኃይል እየተቀበልክ ክፉውን በመዋጋት የቅድስና መስመርን በኑሮ ትጓዝበታለህ፡፡
በመቁጠሪያ ከመቀጥቀጣችን በፊት ምን እናድርግ?
ባሕሪያችንን ተመሳስለው ከሰውነታችን ውስጥ ያሉትን መናፍስት በቅድሚያ በሰማያዊ ስሞች እንዲታሰሩ
ማዘዝ ይኖርብናል፡፡ ከሰው የሚመጡት እንደ መተት፣ ዓይነጥላ፣ ቡዳና ሌሎችም አጥፊ መንፈሶች፤ ጸሎት ሲከብዳቸው
ለጊዜው ወጣ ብለው ይርቁና አምልኮት ስንጨርስ ተመልሰው ይገባሉ፡፡ ስለዚህ "ሁላችሁም ክፉ መንፈሶች በሰማያዊ
ስሞች ታስራችኋል!" እያልን ከሰውነታችን እንዳይወጡ አስሮ መቀጥቀጥ አስፈላጊ ነው፡፡
በመቁጠሪያ እንዴት እንቀጥቅጥ?
መቁጠሪያን ጸሎት በገባን ቁጥር መጠቀም ያደፈጡትን መንፈሶች ለማሰልቸትና ለማዳከም ትልቅ ዕድል
ይሰጠናል፡፡ መቁጠሪያ ስንቀጠቅጥ ታዲያ፤ የየዕለት ውሎአችንን እያየን ሊሆን ያስፈልጋል፡፡ ማለትም ለምሳሌ የማታው
የጸሎት ክፍለ ጊዜ ላይ የምንቀጠቅጥ ከሆነ፤ ቀን በትምህርታችን፣ በሥራችን እና በውሎአችን ላይ ያጋጠሙንን
አልከናወን ያሉ ችግሮች ለይተን ከነጠልን በኋላ፤ ባጋጠሙን ችግሮች መሠረት መናፍስቱን እንቀጠቅጣለን፡፡ "እዚህ
ቦታ ላይ ከሰው ያጣላኸኝ፣ ሕመም የፈጠርክብኝ፣ ጭንቀት የለቀክብኝ፣ ደብቶኝ እንድውል ያደረከኝ፣ ሰላምና
መረጋጋት የነሣኸኝ፣ ምናቤ ውስጥ የምትለፈልፍብኝ እና ወዘተ... የቀን ውሎ እከሎቼ እንዲፈጠሩ ያደረጋችሁ
ጠላቶቼ" እያልን እንቀጠቅጣለን፡፡ በጠዋት የጸሎት ክፍለ ጊዜ ከሆነ ደግሞ የምንዠልጣቸው "በመኝታ ሕልም
ያስፈራራኸኝ፣ ሕልመ ለሊት የመታኸኝ፣ ጭንቀትና ውጥረት ሆነህ ያሳደርከኝ፣ በእንቅልፍ ልብ እንድሄድ ያደረከኝ"
በማለት የአዳራችንን ችግሮች እያነሣንና በተጨማሪም በቀን ውሎአችንም የክፋት ሥራቸውን ከኛ ውስጥ እንዳይመሩ
"ቀኔን እንዳትነኩ!" እያልን እንቀጠቅጣቸዋለን፡
መናፍስትን ካሰርን በኋላ እያልን እንቀጠቅጣለን፦
➢ በሥላሴ ስም ተቃጠሉ
➢ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተቃጠሉ
➢ በወላዲተ አምላክ ስም ተቃጠሉ
➢ በቅዱስ ሚካኤል ስም ተቃጠሉ
➢ በቅዱስ ገብርኤል ስም ተቃጠሉ (ሌላም ወዘተ..)
➢ የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ጅራፍ ይሁንባችሁ
➢ የኢየሱስ ክርስቶስ አማኑኤል መለኮታዊ ኃይል ይቀጥቅጣችሁ
➢ የድንግል ማርያም የጸጋ ኃይል ያንድዳችሁ
➢ የቅዱስ ሚካኤል ሰይፍ ይቆራርጣችሁ
➢ የቅዱስ ገብርኤል የእሳት ሰንሰለት ይገረፋችሁ (ሌላም በምንቀጠቅጥ ሰዓት መንፈስ ቅዱስ ወደ አእምሮአችን
የሚያመጣውን የቅዱሳንን ስምና ኃይል መጥራት)
መናፍስቱን ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ስንቀጠቅጣቸው፦
1. ጀርባን መውረር ማሳከክ አሊያ የአንዳች ነገር መሯሯጥ
2. እንደ ድንጋይ መክበድና ምንም ስሜት አልባ መሆን
3. ልክ እንደ እሳት ማቃጠልና መብላት
4. አስቀድሞ ያልነበረ ሽፍታ፣ ብጉር፣ እብጠት፣ ቁስል መውጣት
5. ቦታው ላይ ልክ ጸጉር የወጣበት ይመስል መጥቆርና ጥላሸት መልበስ
6. በሌላ ቀን መቁጠሪያ ሲያዩ ፍርሃት ፍርሃት ማለት፣ መጨነቅ፣ መቁጠሪያ ላለመጠቀም ከውስጥ የራስ አሳብ
የሚመስል ድምፅ መወትወት እና ሌሎች ተመሳሳይ ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
4) ቅዱስ ቁርባን
ከላይ ያሉት ሦስቱ የየዕለት መንፈሳዊ ምግባራት በጸሎት ቤት የሚዘወተሩ የአምልኮተ እግዚአብሔር
መሠረቶች ናቸው፡፡ በነዚህ ልምምዶች በየቀኑ እየተመላለሰ በየጊዜው ደግሞ የክርስቶስን ሥጋና ደም የሚቀበል ሰው
ምድራዊ ሕይወቱን ወደ ሰማያዊ ልዕልና እያሳደገ እያሳደገ ይመጣል፡፡
ሃይማኖት መንግሥተ ሰማያትን የመውረስ መድረሻ ያለው ጉዞ አይደለም፡፡ ከክርስቶስ በስተቀኝ የተሰቀለው
ፊያታዊ ዘየማን በሃይማኖት ቆይቶ አይደለም መንግሥተ ሰማያትን የወረሰው፡፡ በተአምረ ማርያም የሚነገረው በላዒ
ሰብእም እንዲሁ የሃይማኖት ጉዞው አይደለም ለገነት ያበቃው፡፡
እንግዲያው ገነት ለመግባትና ሲዖልን ለመሸሽ ብቻ ስትሉ ሃይማኖተኛ አትሁኑ፡፡ ይልቅስ ሰው ሃይማኖትን
ኖረ የሚባለው በምድር ገነትን ኖሮ ሲዖልን የተቃወመ መንፈሳዊ ሕይወት ሲመራ ነው፡፡ የእምነት የመጨረሻው
ነጥብ መንግሥተ ሰማያት መግባት ሳይሆን ክርስቶስን በሕይወት ዘመን ሁሉ መምሰል ነው፡፡
ቅዱስ ቁርባን ገነትን በምድር እንድንኖር የሚያደርግ የሚስጢረ መለኮት ቃልኪዳን ነው፡፡ "ሥጋዬን የበላ
ደሜንም የጠጣ እኔ በእርሱ እኖራለሁ" በማለት ከገነት የበለጠው የመንግሥተ ሰማያት አስተዳዳሪ ንጉሥ ክርስቶስ
ስንቆርብ ከኛ ጋር በምድር እንደሚሆን በታመነ ቃሉ አስታውቆናል፡፡ እንኪያሳ፥ ከክርስቶስ ጋር ከመሆን በላይ ምን
ገነት አለን? ከክርስቶስ ጋር ከመኖር ባሻገር ምን መንግሥተ ሰማያት ይገኛል?
በተለይ ወጣቶች አትሸወዱ፡፡ ታላላቅ የእምነት ሥራዎችን በሃይማኖት ድጋፍ በኩል መሥራት የምትችሉት
ስትቆርቡ ነው፡፡ ክርስቶስን ወደ መምሰል የነፍስ ከፍታ ማደግ የምትችሉት ክርስቶስን ወደ ውስጥ ስትቀበሉት ነው፡፡
በክርስትና መንፈሳዊ ጉልበት ሆናችሁ የዓለምን ቅርጽ መለወጥ የምትችሉት መቀደስን ስታውቁበት ነው፡፡
አይምሰላችሁ ዓለም የራሷን ብቻ ነው የምትነግራችሁ፡፡ እንዴት እንደምትዋቡ፣ እንዴት ሐብታም እንደምትሆኑ፣
እንዴት ዝነኛ እንደምትሆኑ ታስተምራችሁ ታስተምራችሁና እንዳትደርሱበት ደግሞ አርቃ ትሰቅለዋለች፡፡ እነዚህን
ፍለጋ ስትኳትኑ ተስፋ እንዳትቆርጡ ደግሞ የራሷን ሰዎች አርአያ አድርጋ ታሳያችኋለች፡፡ ይሄ በክርስቶስ ላይ
የዓለም ገዢ ዲያቢሎስ ያመጣው ዓለምን የማሳየት ፈተና ነው፡፡ ግዴየላችሁም ከክርስቶስ ጋር ሁኑ፡፡ የሚያስፈልጋችሁን
መልካም ነገር ሁሉ የሚሰጥ ገር አባት ነውና እርሱ ይሻላችኋል፡፡

You might also like