Edited - Final ADANE

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 17

አባድር ታህፊዝ

ማዕከል
የመተዳደሪያ
ደንብ
እና
ማቋቋሚያ ሰነድ

0
መግቢያ..................................................................................................................................................1
ክፍል አንድ.............................................................................................................................................4
የነባራዊ ሁኔታ ትንተና............................................................................................................................4
1.1 የቁርዓን ማስተማሪያ ማዕከል ጥንካሬ..............................................................................................4
1.2 ያጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮች...............................................................................................................5
1.3 ችግሮችን ለመፍታት ያሉ መልካም አጋጣሚዎች................................................................................6
1.4 ፕሮግራሙ ውድቀትን ሊያስከትል የሚችል ስጋት (ተግዳሮት).............................................................6
ክፍል ሁለት............................................................................................................................................7
አደረጃጀት እና አሰራር............................................................................................................................7
2.1 ማቋቋም..............................................................................................................................................7
2.2.ስያሜ.................................................................................................................................................7
2.3 የቢሮ አድራሻ.................................................................................................................................7
2.4 ዓላማ..................................................................................................................................................7
2.4 የአባድር ታህፊዝ ት /ቤት አወቃቀር.................................................................................................7
2.5 ጊዜያዊ የሽግግር ኮሚቴ አባላት መሰየም........................................................................................8
2.6 የስብሰባ ስነ ስርዓት........................................................................................................................8
2.7 ጊዜያዊ የሽግግር ኮሚቴ ስልጣን እና ሃላፊነት..................................................................................9
2.8 የሰብሳቢው ኃላፊነት............................................................................................................................9
2.10 የፋይናንስ ኃላፊ ኃላፊነት..............................................................................................................10
2.11 አል ኢምራን የታህፊዝ ማአከል ስልጣን እና ሃላፊነት......................................................................10
2.13 የታህፍዝ ማእከል ሙዲር ሃላፊነት.................................................................................................11
2.14 የተማሪዎች ጉዳይ ክትትል እና የቁጥጥር አስተባባሪ......................................................................12
2.15 የጋራ የምክክር መድረክ................................................................................................................13
2.16 ስነዱን ማፅደቅ............................................................................................................................14

1
መግቢያ

በአላህ ፍቃድ የአባድር ቁርኣን ማእከል ከተመሰረተ 2010 ጀምሮ ጥሩ ጅምርዎችን ማሳየት
ችሏል። የዚህ የቁርኣን ማእከል ትልቅ የስኬት ምክንያት የበርካታ ባለድርሻ አካላት
በእውቀታቸው እና በገንዘባቸው ድጋፍ በማድረጋቸው ምክንያት ነው። ለዚህ የቁርኣን
ማእከል ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ያደረጉትን ሁሉ አላህ ምንዳቸውን
ይክፈላቸው።ይህንን የቁርዓን ማዕከል ተማሪዎች የመቀበል አቅም ሲጀምር 26 ተማሪዎች
የነበረ ቢሆንም በሁለተኛው ዙር ግን የቁርዓን ታህፊዝ ተማሪዎች የመቀበል አቅም ወደ 40
ተማሪዎች ማሳደግ ተችሏል። ይህንን የቁርኣን ማእከል የማስተዳደር ሂደት ሁሉም
የአስተዳደር እና የአስተማሪዎች ጥሩ ልምድ የቀሰሙበት የትምህርት ሂደት ነበር ማለት
ይቻላል። በማገልገል ሂደት ላይ ሆን ተብሎ ወይም በቸልተኝነት ለደርሰ ጥፋት እና
ስህተቶችን የአላህን ምህረትን እንለምናለን።
ለአንድ ተማሪ ዓመታዊ በጀት ፍላጎት በዋጋ ግሽበት ምክንያት እየጨመረ በመምጣቱ
ለአላህ ምስጋና ይድረሰውና ለጋሾች ችግሩን ተገንዝበው ዋጋ ግሽበትን ለማካካስ ለአንድ
ተማሪ ይመድቡት የነበረውን በጀት ከ 10,000 ወደ 25,000 ብር አሳድገዋል። ተማሪዎች
በአማካኝ ቁርአን ለመጨረስ የሚስያስፈልጋችው ጊዜም በልምድ ታውቆአል ። የቁአራን
ትምህርት ቤቱ የመቀበያ መስፍርት ላይም መሻሻል ይታያል ። በቁርናን ታህፊዝ ያጠናቀቁ
ተማሪዎች በየመስጊዱ ታራዊህ ሰላት በብቃት ማሰገድ መቻላችው ከፍተኛ ደስታን
ይሚያጎናፅፍ ከመሆኑም በተጨማሪ በማህበርሰቡ ውስጥ ቁርአንን የመማር ፍላጎት
አንዲጨምር አድርጎታል ።
ብዙ ስኬት ቢመዘገብም ይህ የቁርዓን ማስተማሪያ ማዕከል ገና በመነሻ ደረጃ ላይ የሚገኝ
እና በሁለት እግሩ ለመቆም ወደ ሚችልበት ደረጃ በመሄድ ላይ ይገኛል ። የመስራች
ኮሚቴው አባላት በኩል የአመራር ክፍተቶች እንዳሉ ተረድተዋል።
ማእከሉ በምን አይነት ሁኔታ መቀጠል አለበት የሚለውን ነጥብ ለመመለስ መስራች
ኮሚቴው ከአንዳንድ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ካደረገ በኋላ አሁን ባለው ሁኔታ በዚህ
ደረጃ ለአዲስ ኮሚቴ ርክክብ አድርጎ መተዉ የታለመውን ግብ ከማድረስ በፊት የውድቀት
ስጋት ሊመጣ ይችላል ወደ ሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል።.
ስለዚህም የመስራች ኮሚቴው አባላት ከሁለት የወቅቱ የመስጂድ ኮሚቴ አባላት እና አንድ
የበጎ ፍቃድ አባል ጋር በመሆን በሽግግር ጊዜያዊ ኮሚቴ የመሪነት ሚና ስራውን መቀጠል
ያለበት መሆኑን አስምረውበታል። ሆኖም የመስጊዱ የናዝር ኮሚቴ አባላት ይሁንታ

2
ማግኘት ያለበት በመሆኑ ሰነዱ ቀርቦ አስፈላጊ ማሻሻያ በማከል ወደ ሕጋዊ መስመር
መግባት ይኖርበታል ።
ኮሚቴው በአጠቃላይ አስተዳደራዊ ሂደት ላይ ዝርዝር ግምገማ በማድረግ ስራውን
ጀምሯል።ለዚህም የችግሮቹን ጥልቀት ለመረዳት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በዋናነት
አስተዳዳሪው እና ሙዲር እንዲሁም ከጉዳዩ ጋር በቀጥታ የተገናኙ አል ኢምራን የታህፊዝ
ማአከል ኃላፊዎች እና ሌሎች ሰራተኞች ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸዋል። በተጨማሪም
ኮሚቴው ያሉትን ችግሮች እና ስኬቶች ለመረዳት ይህንን የቁርዓን ማእከል በአካል ጉብኝት
በማድረግ ችግሮችን በጥልቀት አስተውሎአል። በኮሚቴው በተደረገው ምልከታ በዋነኛነት
ስኬቶችን እንደ ጥንካሬ በማየት ችግሮች እና ድክመቶች በዝርዝር በመለየት በቀጣይ
ችግሮቹን ለማሻሻል የሚያስችሉ ዕድሎችና እንዲሁም በመጨረሻም እንቅፋት ሊሆኑ
የሚችሉ ተግዳሮቶች በግልጽ ተቀምጧል።
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ቀዳሚው ተግባር ግልጽ የሆነ የስራ ክፍፍል መኖሩን ማረጋገጥ
ያስፈልጋል በማለት ኮሚቴው ተስማምቷል። ግልጽ የሆነ ድርጅታዊ መዋቅር እያንዳንዱ
አካል በመዋቅሩ ውስጥ የሚጠበበቅበትን ስራ በግልፅ አውቆ ኃላፊነቱን በትክክል
እንዲወጣ ግዘዋል የሚል አሳቤ በዋነት ተውስዶአል ።
ይህንን ሰነድ በማዘጋጀት ሂደት የፋይናንስ እና የሂሳብ አያያዝ ለማሻሻል አንደዚሁም
ዘመናዊ የአስተዳደር ስርዓት ለመዘርጋት የኮሚቴው አባላት ለአስተዳዳሪው ሙሉ ድጋፍ
ለመስጠት ተስማምተዋል ። በተጨማሪም ሥራው የግንባታና የጥገና ሥራ በሚፈልግበት
ጊዜ የኮሚቴ አባላት ማዕከሉን ለማገልገል ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል ።
በመጨረሻም ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ተጨማሪ ውይይት በኋላ በመስጂዱ የናዚር
ኮሚቴ ሲፅድቅ ይህ ሰነድ ለሁሉም የቁርኣን ማእከል አባላት እና ሰራተኞች እንደ እለት ተለት
የሚጠቀሙበት ሰነድ ሆኖ ያገለግላል።

3
ክፍል አንድ

የነባራዊ ሁኔታ ትንታኔ

1.1 የቁርዓን ማስተማሪያ ማዕከል ጥንካሬ

ይህ የቁርዓን ታህፍዝ ማእከል የተቋቋመበት ከ ጥቅምት 2010 ጀምሮ የተለያዩ ፍሬያማ


ውጤቶችን ማሳየት ችሏል ።

1. ማዕከሉ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ 28 ተማሪዎች የቁርዓን ታህፍዝ ትምህርት


በማጠናቀቅ በአንደኛው ዙር ተመርቀዋል።

2. በአሁኑ ጊዜ 40 ተማሪዎች ወደ ማዕከሉ ገብተው የቁርዓን ሂፍዝ ፕሮግራም በመከታተል


ላይ ይገኛሉ።

3 ከተመረቁት ተማሪዎች ውስጥ 8 ተመራቂዎች የከፍተኛ ሃይማኖት ጥናት መርሃ ግብር


ተቀላቅለዋል። ይህ ማለት በሀገር ውስጥ በሲኤምሲ የሃይማኖት ጥናት ማዕከል 7
ተመራቂዎች የገቡ ሲሆን በዓለም አቀፍ የሃይማኖት ጥናት ማከል ማለትም በተሪም
የመን 2 ተማሪዎች የሃይማኖታዊ ትምህርት ቀጥለዋል ።

4 ተመራቂዎች በርካታ ሰዎችን የቁርዓን የማስትማር ሥራ መጀማራችው የተገለፅ


ቢሆንም የማስትማር ሥራ ያለበት ደረጃ ሁኔታ ተገምግሞ መታወቅ ይኖርበታል ።

5. ቁጥራቸው 13 የሚደርሱ ተመራቂዎች ተራዊህ ሰላት በተለያዩ መስጂዶች ኢማም


በመሆን አሰግደዋል።

6. ከተመራቂዎች መካከል 3 ቱ በአሁኑ ወቅት ወደ የመን ተሪም ኢስላሚክ ማስተማሪያ


ማዕከል ለመቀላቀል ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

4
7 ተማሪዎቹ በአባድር መስጂድ ኢማም እና ሙአዚን ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ

8.ተማሪዎች ዳዋ እና ሰለዋት ፕሮግራም እየተሳተፉ ነው ።

9 ባለፉት አራት አመታት ከ አራት ሚሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ ለፕሮግራሙ ወጪ


ተደርጓል።

1.2 ያጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮች

1.አስተዳደሩና መምህራኑ ግልጽ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የላቸውም።

2 ከሙሉ ኃላፊነት ጋር የሚመራ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አለመኖሩ ።

3. የጋራ ራዕይ እጥረት ።

4. ሁሉንም ፕሮግራሞች ለመቆጣጠር እና መከታተል የሚያስችል ግልጽ እቅድ አለመኖር ።

5. የክትትል እና የሪፖርት አቀራረብ ስርዓት እጥረት ።

6.ግልፅ የተማሪዎች ምልመላ ምዝገባ ስርዓት አለመኖር ።

7.የተማሪዎች የዲሲፕሊን እርምጃ አወሳስድ ስርዓት አልመዘርጋት ።

8 .የሂሳብ ወጭ ሪፖርት በትክክል ያለመቅረብ ችግር ።

9.. ኩሽና ውስጥ የንፁህና እጥረት ።

10. የአስቶር እና ፍሪጅሬተር ችግር ተስተውላል ።

11. በርካታ ቁጥር ያላችው አይጦች በሮሮዎች መኖር ።

12. መጸዳጃ ቤት ከጽዳት ጋር የተያያዘ ችግር አለበት ።

13. ተማሪዎች ተገቢ የልብስ ማጠቢያ ቦታ የላቸውም ።

14.ተማሪዎች የአልጋ ልብስ የሳቡና እጥረት አለባቸው ።

5
15. አንዳንድ ተማሪዎች የልብስ ማስቀመጫ ሳጥን የላችውም ።

16. ቆሻሻ ልብስ ክፍሎቻቸው ውስጥ መቀመጡ ከክፍሎቻቸው ጥበት ጋር ተዳምሮ


የክፍሉን የመታፈን ችግር ያስከትላል ።

17 .ተማሪዎች ክፍላቸውን አያፀዱም።

18. ዶርም ውስጥ መመገብ አይጥን እና ባክቴሪያዎችን ይስባል ።

19. አንዳንድ ክፍሎች በጣም ጠባብ ናቸው እና በቂ የአየር ዝውውር እጥረት አለ ።

1.3 ችግሮችን ለመፍታት ያሉ መልካም አጋጣሚዎች

1. በቲም ችግሩን ለመፍታት ቁርጠኝነት ታይቷል።

2 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ተጨማሪ በጎ ፈቃደኞችን እንደ ሲቪል መሐንዲሶች


ሳንታሪ መሐንዲሶች እና የሂሳብ ባለሙያዎች ማሳተፍ ይቻላል።

3. ችግሮቹን ለመፍታት በቂ ሀብት ማሰባሰብ ይቻላል።

4. የግንኙነት ክፍተቶችን ለማስወገድ ተደጋጋሚ መደበኛ ስብሰባ ለማድረግ ፈቃደኛነት


አለ።

5. አካባቢው ያሉትን ችግሮች ለማስተናገድ የሚያስችል በቂ ቦታ አለ።

1.4 ፕሮግራሙ ውድቀትን ሊያስከትል የሚችል ስጋት (ተግዳሮት)


1. ለፕሮግራሙ ትኩረት አለመስጠት ችግሩን ሊያባብሰው ይችላል ።

2. አለመግባባት እና የተሳሳተ እና የተጋነኑ መረጃዎች ወደ ግጭት እና በመጨረሻም


ውድቀት ሊያስከትሉ ይችላሉ።

3. አድሎአዊ ወገንተኝነት ዓላማዎችን ከግብ ለማድረስ አስችጋሪ ሊያደርጉ ይችላሉ ።

4. ከሥራው ይልቅ የሰው ማንነት ስብዕና ላይ ማተኮር የስራ ተነሳሽነትን እና


ቁርጠኝነትን ሊቀንስ ይችላል።

6
5. መደበኛ የቡድን አባላት ለምሳሌ እንደ የሂሳብ ችሎታ እና የምህንድስና ክህሎት በቂ
ችሎታ ያለው ሰው ማሰራት አለመቻል ።

7
ክፍል ሁለት

አደረጃጀት እና አሰራር

2.1 ማቋቋም
ያሉትን እድሎች በመጠቀም እና ድክመቶችን በማሻሻል እና ሊያጋጥሙ የሚችሉ
ፈተናዎችን በመቋቋም ጥንካሬን ለማስቀጠል እና የበለጠ ወደ ውጤታማ እና ቀልጣፋ
የቁርዓን የመማሪያ ማእከል ለመለወጥ ግልጽነት ተጠያቂነትን እና ሃላፊነትን ለማረጋገጥ
የአባድሪ ቁርዓን ማስተማሪያ ማዕከል የአባድር መስጊድ ናዚር ኮሚቴ በኩል
እንደሚከተለው ተቋቁሟል ።

2.2.ስያሜ
የተቋሙ ስም አባድር ታህፊዘ ማዕከል ነው።

2.3 የቢሮ አድራሻ


በሳርር ቤቴ አካባቢ የሚገኘው አባድር መስጊድ ውስጥ ነው።

2.4 ዓላማ
አጠቃላይ አላማው የቁርዓን መንፈሳዊ ትምህርት እና ኢስላማዊ ግብረገብ ትምህርት
አባድር መስጊድ ግቢ ውስጥ ማስተማር ነው።

2.4 የአባድር ታህፊዝ ት /ቤት አወቃቀር


አባድር ታህፍዝ ማእከል በሚከተለው መዋቅር ተቋቁሟል ።
1 ጊዜያዊ የሽግግር ኮሚቴ

2 አል ኢምራን ታህፍዝ ማእከል ( ሲ ኤ ም ሲ )


3 አስተዳደር
4 የታህፍዝ ማእከል ሙዲር
5 የተማሪዎች ጉዳይ ክትትል እና የቁጥጥር አስተባባሪ

8
2.5 ጊዜያዊ የሽግግር ኮሚቴ አባላት መሰየም

የሚከተሉት አባላቶቹ ጊዜያዊ የሽግግር ኮሚቴ ሆነው እንዲያገለግሉ በአባድር መስጂድ


ናዚር ኮሚቴ ተመርጠዋል።

አባላት የአባልነት ደረጃ


1. ኤልያስ አብዱልመሊክ ሰብሳቢ
2. ሪያድ ዩሱፍ ምክትል ሰብሳቢ እና ፀሃፊ
3. በድሪ አብዱራህማን የፋይናንስ ኃላፊ
4. ፉአድ ማዊ አባል
5. መሀመድ ሳሊህ አባል
6. ሙኒብ መሀመድ አባል
7. አህመድ ኢዘዲን አባል

2.6 የስብሰባ ስነ ስርዓት

1. ኮሚቴው በየሁለት ሳምንቱ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል።


2. የመደበኛ ስብሰባ የሚደረግበትን ቅንና ቦታ በቅድሚያ በኮሚቴው ይወሰናል።
3. ሆኖም የመደበኛ የስብሰባው ቀን እና ቦታ ከተቀየረ በቅድሚያ ይገለፃል ።
4. እንደ ጉዳዩ አስቸኳይነት በማንኛውም አመቺ ጊዜ በሰብሳቢው እና በምክትል
ሰብሳቢው አማካኝነት ስብስባ ሊጠራ ይችላል።
5. ስብሰባ አንዲጠራ በማንኛውም የኮምቴ አባል በኩል ጥያቄ ሊቀርብ ይችላል ።
6. ስብሰባውን ለማካሄድ ከአባላቱ ውስጥ ሁለት ሦስተኛ አባላት ከተገኙ ስብሰባውን
ለማካሄድ የቻላል።
7. ስብሰባው በአብላጫ ድምፅ የሚወሰን ይሆናል ።

9
8. በግማሽ በላይ የሆኑ የኮሚቴ አባላት ጥያቄ መሰረት ውሳኔ የተሰጠበት ጉዳይ
እንደገና ሊታይ ይችላል።

2.7 ጊዜያዊ የሽግግር ኮሚቴ ስልጣን እና ሃላፊነት

1 ማንኛውም ተገቢ ስትራቴጂ ጉዳዮች ላይ መወሰን እና ከቁርኣን የማስተማሪያ


ማእከል ጋር የተያያዘ ጉዳዮች ላይ መመሪያ ይሰጣል ።
2 በአስተዳዳሪ እና በቁርዓን ማእከል ሙዲር የሚዘጋጀውን ዓመታዊ እና ወርሃዊ እቅድ
ያፀድቃል ።
3 የቁርዓን ማእከል አጠቃላይ የስራ አፈጻጸሞችን መከታተል እና መገምገም ተገቢ
መመሪያ ይስጣል ።
4 ለቁርዓን የመማሪያ ማእከል አስፈላጊውን ገንዘብ ያሰባስባል ።
5 የቁርአን ማእከል አጠቃላይ አፈፃፀም ይቆጣጠራል ።
6 የፋይናንስ አፈጻጸም ይገመግማል ።
7 አስተዳዳሪ ይመድባል ሙዲር እና መምህራን በ ሲ ኤ ም ሲ የትምህርት ማካል
አስተያየት ሲቀርቡ በቅጥር ሁኔታ ደሞዝ ጥቅማ ጥቅም ይውስናል ።
8 በዲሲፕሊን ችግር ምክንያት በሚሰናበቱ ተማሪዎች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል

9 የቁርኣን ማእከል ድርጅታዊ መዋቅርን እና ደሞዝ ይፅድቃል ።
10 ግቢውን እና የመማር ማስተማር ሂደቱን ድንገተኛ ጉብኝት በማድረግ የሥራ
አፈፃፀሙን ይገመግማል።
11 ቅሬታዎችን ያስተናግዳል እና ግጭቶችን ይፈታል ።
12 አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አስተዳድሪውን ሙድሩን ወይም መምህራን ከኃላፊነታቸው
ያነሳል ።

2.8 የሰብሳቢው ኃላፊነት


1. አጀንዳውን በሰብሰባው ሥርአት መስረት መዘጋጀቱን ያረጋግጣል ።
2.ስብሰባዎችን በአግባቡ ይመራል።
3.በስብሰባው ላይ ሥርዓትን ያስጠብቃል ።
4.የስብሰባው ውሳኔዎች መከበራቸውን ያረጋግጣል ።
5. በስብሰባው ላይ ፍትሃዊነትን እና እኩልነትን ተሳትፎ መኖሩን ያረጋግጣል ።

10
2.9 የምክትል ሰብሳቢ እና የጸሐፊ ኃላፊነት
1. ሊቀመንበሩ በሌለበት ጊዜ የሊቀመንበሩ ሥራ ተተኪ ሆኖ ይሠራል።
2. የስብሰባው ቃለ ጉባኤ ይመዘግባል ።
3. ከፋይናንስ ኃላፊው ጋር በመሆን የባንክ አካውንት ይከፍታል
ያስተርዳድራል ።
4. በባንክ ቡክ እና ቼክ ላይ ይፈርማል ።

2.10 የፋይናንስ ኃላፊ ኃላፊነት


1. ከምክትል ሊቀመንበሩ ጋር የባንክ አካውንት ይከፍታል።
2. የባንክ ቼክ ፈራሚ አንዱ ይሆናል።
3. ሁሉም የሂሳብ አያያዝ ሂደቶች እና ደንቦች መከበራቸውን ያረጋግጣል ።
4. ከአስተዳዳሪው ጋር በመሆን የገቢ እና የወጪ ሪፖርት ያዘጋጃል ።

2.11 አል ኢምራን የታህፊዝ ማአከል ስልጣን እና ሃላፊነት

1 የቁርዓን ማዕከል ሥርዓተ ትምህርት አዘጋጅቶ ያጸድቃል ይህም የቁርኣን ማስተማር


ሥራ እንደ መሰረታዊ የአሠራር መመሪያ ሆኖ ያገለግላል።
2 ብቃት ያለው መምህር ለመቅጠር መስፈርት ያዘጋጃል።
3 የቁርዓን ማእከል እንዲቀጠር ብቃት ያለው ሙዲር እና አስተማሪን ያቀርባል።
4 የሙዲር እና የቁርዓን መምህራንን ተግባር ይገመግማል ።
5 በቅድመ-መመዘኛዎች መሰረት አዳዲስ ተማሪዎችን ይመለምላል ።
6 የተማሪዎችን የቁርዓን ሂፍዝ ስኬት ያፀድቃል ።
7 አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ውጤታማ ያልሆኑ የቁርዓን መምህራንን ከስራ
ለማሰናበት ለጊዜያዊ ሽግግር ኮሚቴው ያሳውቃል ።

11
2.12 አስተዳዳሪ ሃላፊነት

\የመስጂዱ አስተዳዳሪ ተጠሪነቱ ለአስፈፅሚ ኮሚቴ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት


ይኖረዋል ።

1 ለጊዜያዊ አስፈፃሚ ኮሚቴው አስፈላጊውን እቅድ እና በጀት አዘጋጅቶ ያቀርባል።


2 በኮሚቴው በኩል የጸደቀውን በጀት ተግባራዊ ያደርጋል ።
3 ከመዲር ጋር በመተባበር በአል ኢምራን ይሂፍዝ ማእከል የተቀመጠውን የሥነ
ምግባር ኮድ ተግብራዊ ያደርጋል ።
4 ወጭውን እና የስራ አፈፃፅም የሚያሳይ ወርሃዊ እና አመታዊ የስራ አፈጻጸም
ሪፖርት ያቀርባል ።
5 የቁርኣን ማእከል ንብረትን በአግባቡ መያዙን ያረጋግጣል ።
6 ሁሉንም አስፈላጊ የሰራተኞች አስተዳደር ሥራ ያከናውናል። ሆኖም በሲኤምሲ
ታህፊዝ ማእከል የሚወጡት ህጎች እና መመሪያዎች ለአስተማሪዎች ላይ ተፈጻሚ
ይሆናሉ ።
7 በድርጅታዊ መዋቅር የደሞዝ አስኬል ጥቅማጥቅም ላይ አስፈላጊውን ለውጥ
አዘጋጅቶ ለኮሚቴ ያቀርባል እና ኮሚቴው ተቀባይነት ሲያገኝ ተግባራዊ ያደርጋል ።
8 የምግብ አቅርቦት ግዢ ያካሄዳል በሁሉም የምግብ ዝግጅት ሂደት ጥራትን
ያረጋግጣል።
9 የተማሪዎች መኝታ ክፈሎች ኩሽና እና ከመታጠቢያ ቤቶች ከማጽዳት ጋር የተያያዙ
ሁሉንም ችግሮች የመፍታት እና እለት ተእለት ሰራዎች መሰራታችውን ያረጋግጣል
10 ለተማሪዎች አስፈላጊ የሆነውን የምግብ ሜኑ ያዘጋጃል እና ተማሪዎቹ በአግባቡ
መመገባቸውን ያረጋግጣል።
11 ለቁርዓን ማእከል የምያስፈልጉ ሰራተኞች በኮሚቴ በፀደቀው መዋቅር መሰረት
ተግባራዊ ያደርጋል ሆኖም የሙድር እና የመምህራን ቅጥር በሲ ኤ ሚ ሲ እና
በኮሚቴው መፅደቅ ይኖርበታል ።

12
12 ከስንብት ውጭ ያሉ ማናቸውንም የተማሪዎች የስነምግባር ደንቦችን መጣስ
እርምጃ ይውስዳል ሆኖም ጉዳዩ ስንበት የሚያስከትል ከሆነ በቅድምያ ላስፈፃሚ
ኮሚቴ መጽደቅ ይኖርበታል ።
13 የተማሪዎች ትምህርታዊ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ጨምሮ ሁሉም አስፈላጊ
የተማሪዎችን መረጃ እና ሰነዶች በአግባቡ ተደራጅቶ መያዛቸውን ያረጋግጣል።
14 የፋይናንስ ሪፖርት ያደራጃል በማንኛውም ጊዜ ባለድርሻ አካላት ሲጠየቅ ያሳያል ።
15 በለጋሾች ሲጠየቅ ለሚደረጉት የገንዘብና የአይነት ስጦታዎች ደረሰኝ ወይም
የምስጋና ደብዳቤ ይሰጣል።
16 ሁሉንም አስፈላጊ መረጃዎች አደራጅቶ በማስቀመጥ ባለድርሻ አካላትን ሲጠየቅ
ያሳያል ።
17 የሙዲር እና የቁርዓን መምህራንን በሥራ ሰዓት እና ቦታ መገኘታችውን ይከታተላል
በዚህም መሠረት ወርሃዊ ደሞዛቸውን ይፈፅማል ።
18 በኮሚቴው የተመደበውን ማንኛውንም ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል።

2.13 የታህፍዝ ማእከል ሙዲር ሃላፊነት


የቁራን ማከሉ ሙዲር በዋናነት ተማሪዎችን የቁርአን ትምህርት የማስተማር ስነምግባር
የማነፅ የቁርኣን መምህራንን የስራ መመደብ ተማሪዎችና መምህራንን መቆጣጠር እና
መገምገም ኃላፊነት ያለበት ሲሆን ዋና ስራውንና ተግባሩን በተመለከተ ተጠሪነቱ በቀጥታ
ለ አል ኢምራን ታህፍዝ ማእከል ሲሆን አለት ተለት በሥራ ገበታ ላይ መገኝትን ስራውን
እየፈፅመ መሁኑን ማየት በተመለከት ተጠሪነቱ ለመስኪዱ አስተዳድር ሆኖ የሚከተሉትን
ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል ።

1. በዋነኛነት ተማሪዎቹ በአል ኢምራን ሂፍዝ ሴንተር የተዘጋጀውን የ 24 ሰአት


ፕሮግራም ተግባራዊ እያደረጉ መሆናቸውን ያረጋግጣል።
2. መምህራን በመደበኛ የስራ ጊዜና ቦታ በመገኘት የማስተማር ሰራችውን
በተቀመጠላችው አቅጣጫ እና አቅድ መሰረት መፈጽማችውን ያረጋግጣል ።
3. ተማሪዎች በቂ የስነምግባር ትምህርት መቅሰማችውን ያረጋግጣል።

13
4. ተማሪዎች የግል ንጽህና የመኖሪያ ከፍላችውን ንፅሕና አና የመስጊዱ ንጽሕና
አንዲጠብቁ መመሪያ ይሰጣል ።
5. በመስጊዱ ውስጥ በሚደርጉ የተማሪዎች አገልገሎት አዛን ማድረግ ማሰገድ የሰለዋት
ፕሮግራም አንደዚሁም የዳአዋ ፕሮግራም ላይ ተገቢውን ፕሮግራም አዘጋጅቶ
ተግባርዊነቱ ይሰራል ።
6. ከባድ ወይም ተደጋጋሚ የስነመግባር ችግር ያለባችው ተማሪዎች አርምጃ
እንድውሰድባችው ላስተዳዳሪው ያቀርባል ። አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የዲሲፕሊን
እርምጃውን በጋራ ይወስዳሉ ።
7. የተማሪዎች የትምህርት የጥናት የምግብ የእረፍት እቅድ ወዘተ በማዘጋጀት
ለመስጊዱ አስተዳደር ያቀርባል ።
8. አስተዳድሩ ጋር በመተባበር ተማሪዎች ከትምህርት በተጨማሪ ለምሰሯችው
ስራዎች አስፈላጊ የጊዜ ሰሌዳ መካተቱን እንደዚሁም በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ
መሰረት አስፈላጊውን ተግባራት አንድፈፅሙ መቹ ሁኔታ ይፈጥራል ።
9. በተለያዩ ምክንያት በትምህርታችውን በተቀመጠላችው የጊዜ ሰሌዳ መስረት
መፈፀም ያቃታችውን የተማሪዎች ሁኔታ ውሳኔ አንድሰጥበት ላስተዳዳሪው
ያቀርባል።

2.14 የተማሪዎች ጉዳይ ክትትል እና የቁጥጥር አስተባባሪ

በቀጥታ ተጠሪነቱ ለመስጂዱ አስተዳዳሪ ነው ። በማነኛውም ጊዜ ከተማሪዎች በቁራን


ማስተማርያ ውስጥ ከተማሪዎች ጋር የመቆየት ግዴታ ያለበት ሲሆን በተለይም በዋናነት
መስጂድ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከተማሪዎች ጋር አብሮ የሚያድር ሆኖ የሚከተሉት
ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል።

1 ተማሪዎቹ የመስጂዱ አስተዳዳሪ እና በሙዲር የተቀመጠውን ደንብ እና መርሃ


ግብር በማክበር ላይ መሆናችውን ያረጋግጣል ።
2 ኃላፊነታችውን የማይውጡ የተማሪዎች ሁኔታ ለአስተዳድሩ አና ለቁርአን ማእከሉ
ሙዲር ሪፖርት ያደርጋል ።

14
3 ሁሉም ተማሪዎች ከንፅህና አጠባበቅ ጋር የተያያዙ ተግባራትን እየፈጸሙ እና
እየተከተሉ መሆናቸውን ያረጋግጣል።
4 ተማሪዎችን መኝታ ቤት መጸዳጃ ቤት ሁል ጊዜ ለተማሪዎች በተዘጋጀው ፕሮግራም
መሰረት ንጽህና ተግባራት እየፈፅሙ መሆኑን ያረጋግጣል።
5 ከንጽሕና ጋር የተያያዘ አስፈላጊ ሥልጠና ለተማሪዎች መሰጠቱን ያረጋግጣል
6 ከተማሪዎቹ ጋር የተያያዙ አስፈላጊ መረጃዎች በጥሩ ሁኔታ መመዝገባቸውን እና
መያዙን ያረጋግጣል።
7 ሌሎች ከቁርአኑ ማእከል ጋር የተያያዙ ስራዎች በመስኪዱ አስተዳዳሪ በሚሰጠው
መመሪያ መሰረት የፈስማል።

2.15 የጋራ የምክክር መድረክ


1. የሽግግር ኮሚቴ አባላት የሲኤምሲ የቁርዓን ማእከል ተወካዮች፣ አስተዳዳሪ
ሙዲር እና መምህራን የጋራ የምክክር መድረክ አባላት ናቸው።
2. የሽግግር ጊዜያዊ ኮሚቴው ሰብሳቢው የጋራ የምክክር መድረክ ሰብሳቢ
ይሆናል ።
3. የሽግግር ጊዜያዊ ኮሚቴው ጸሃፊም ለዚህ የጋራ ስብሰባ ጸሃፊ ሆኖ ያገለግላል።
4. ጉባኤው በየሶስት ወሩ አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል።
5. የስብሰባው አላማም የዚህን የቁርዓን ማእከል አጠቃላይ አፈፃፀሙን
ለመገምገም እና በቁርዓን ማስተማሪያ ማእከል የሚያጋጥሙ ዋና ዋና
መሰናክሎችንና ችግሮችን ለመፍታት እና የተሻለ ልምድ ለመለዋወጥ ነው።
6. የስብሰባው አጀንዳ በሊቀመንበሩ እና በጸሐፊው ቢገለጽም ሌሎች አባላት
አጀንዳዎችን ሊያቀርቡ ይችላሉ።
7. የሽግግር ኮሚቴው፣ የሲኤምሲ የቁርዓን ማእከል፣ አስተዳዳሪ እና MUDR
አፈጻጸማቸውን ሪፖርት እንዲያቀርቡ እድል ይሰጣቸዋል ወይም መረጃ
መለዋወጥ እና ማስተላለፍ ይችላሉ።

15
8. በጋራ ስብሰባው ላይ የተደረሰው አቅጣጫ የቁርኣን ኢንስቲትዩት አፈጻጸምን
ለማሻሻል እንደ መመሪያ ይወሰዳል።

2.16 ስነዱን ማፅደቅ

ይህ አባድር ታህፊዝ ማዕከል ጊዜያዊ የአሰራር መዋቅር ማቋቋሚያ ስነድ በአባዲር


መስጊድ የናዚር ኮሚቴ አባላት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት ከዚህ በታች ስም እና
ፊርማቸውን ባኖሩ አባላት ዛሬ ቅዳሜ ጁን 4 ቀን 2022 የፈርነጆች አቆጣጠር ተቀባይነት
አግኝቷል።

ተራ ቁ አባላት ስም ፊርማ
1
2
3
4
5
6
7
8
9

16

You might also like