Rule of Law-1

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 20

የኢትዮጵያ መርከበኞች የሰራተኞች መሰረታዊ ማህበር መተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ 1

የማህበሩ ስም

ይህ ማህበር የኢትዮጵያ መርከበኞች የሰራተኞች መሰረታዊ ማህበር ተብሎ ይጠራል፡፡

አንቀጽ 2 የማህበሩ አድራሻ

የማህበሩ አድራሻ 14 ቀበሌ----- የቤት ቁጥር------ሲሆን ስ. ቁ-------------------የፓ.ሳ.ቁ---------ከተማ


አዲስ አበባ ነው፡፡

አንቀጽ 3

ትርጓሜ

በዚህ መተዳደሪያ ደንብ አፈፃፀም ፡-

3.1 ማህበር ማለት የኢትዮጵያ መርከበኞች የሰራተኞች መሰረታዊ ማህበር ማት ነው፡፡

3.2 ድርጅት ማለት አሰሪ ድርጅት ማለት ነው፡፡

3.3 ጠቅላላ ስብሰባ ማለት የአባል መርከበኞችስብስብ ማለት ነው፡፡

3.4 ምክር ቤት በማህበሩ ጠቅላላ ስብሰባ የተመረጠ እና የማህበሩን ስራ አስፈፃዎች እንቅስቃሴ የሚቆ ጣጠር
የማህበሩ መዋቅር አካ ነው፡፡

አንቀጽ 4

የማህበሩ ዓላማ

4.1 ማህበሩ የአባለቱን መብት ፣ ጥቅም፣ ደህንነትና የስራ ዋስተናቸው አስተማማኝ እንዲሆን በማስከበር
የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፍላጎታቸው እነዲሟለላቸው የሚያስችል የስራ ባህል እንዲፈጠር ማስቻል ነው፡፡

4.2 ሰራተኛው የስራ ግዴታውን እንዲወጣና የስራ ተሳትፎን ከፍ እነዲያድረግ ከአሰሪው ጋር ጤና ግኑኙነት
እንዲፈጥ ጥረት ማድረግ ነው፡፡

4.3 በአገረፍ አቀፍ ደረጃ በመደራጀት ኢዱስትሪያዊትግሉን ለማጎልበት፡፡

አንቀጽ 5

ማህበሩ የተመሰረተበት ቀን

ይህ ማህበር በአዋጅ 377/96 መሰረት መስከረም 18 ቀን 2012 ዓ.ም ተመሰረተ፡፡

አንቀጽ 6
የማህበሩ አርማ

6.1 የማህበሩ አርማ

አንቀጽ 7

የማህበሩ ተግባርና ኃላፊነት

7.1 ሠራተኞች በማህበር እንዲሰበሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ፣

7.2 አባላቱን በማንኛውም ደረጃ መወከል፣

7.3 የአባላቱን መብትና ጥቅም ማስከበር፣

7.4 የሥራ አካባቢ ደህንነትና የሠራተኛው ጤንነት እንዲጠበቅና በዚህ ረገድ የወጡ ሕጎች፣ ደንቦችና
መመሪያዎች ሠራተኛው ዘንድ እንዲታወቅ ማድረግ፣

7.5 የድርጅቱ የእቅድና የአስተዳደር ፖሊሲዎች ሲነደፉ የሠራተኛው ተሳትፎ እንዲኖር ማድረግ፣

7.6 በዕድገት፣ በደሞዝ ጭማሪ፣ በዝውውር፣ በቅጥርና ምደባ፣ በሥራ ክርክር አፈጻጸም ሠራተኞች
ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ፣

7.7 በአዋጅ በተሰጠው መብት መሠረት የድርጅቱን ሠራተኛ በመወከል ከድርጅቱ ጋር የሕብረት
ስምምነቶች መደራደር መፈረምና ማስፈጸም፣

7.8 በሥራ ክርክር ሰሚ አካላት ዘንድ አባላትን መወከልና ለሥራ የሚያስፈልገውን የገንዘብ ወጪ
በአቅሙ ድጋፍ ማድረግ ፣

7.9 ሠራተኞች በሥራ አካባቢያቸው ማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲሟሉላቸው ሁኔታዎችን ማመቻቸት ፣

7.10 በተቋሙ ውስጥ የኢንዱስትሪ ሠላም እንዲሰፍን ማድረግ፣

7.11 የሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና የብድር ሕብረት ሥራ ማህበራት አገልግሎት እንዲቋቋሙ ፣


እንዲጠናከሩና ለሠራተኛው የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ፣

7.12 የሰራተኛው ትምህርትና ስልጠና የሚጎለብትበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣

7.13 ሠራተኛው በተለያዩ የስፖርት ውድድሮች እየተሳተፈ ጤንነቱን እንዲጠብቅና የአካል ብቃት
እንዲዳብር እገዛ ማድረግ፣

7.14 የአባላትን መዋጮ በአግባቡ መሰብሰቡን ማረጋገጥ፣ የበላይ ማህበራትን ድርሻ በወቅቱ ማስተላለፍ፣
7.15 የአባላትን ወቅታዊ መረጃ በተደራጀ ሁኔታ መያዝ፣

7.16 ለአባላት ጥቅም ማስከበሪያና ለተሻለ የጥቅማ ጥቅም ዕድል ለመፍጠርና የማህበሩን የገቢ ምንጭ
ለማጎልበት እንዲረዳ በማህበሩ ስም አክሲዮን መግዛት መሸጥ እና ማስተላለፍ፣

7.17 ሌሎች ተጨማሪ ለሠራተኛ ጠቃሚ የሚሆኑ ተግባሮችን መሥራት፣

አንቀጽ 8

የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር የአመራር አካላት፣

8.1 የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ፣

8.2 የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር የምክር ቤት፣

8.4 የመሠረታዊ ማህበሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣

8.5 የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበሩ ኦዲት ኮሚቴ፣

አንቀጽ 9

የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ጠቅላላ ስብሰባ

9.1 የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ አባላት የሚሳተፉበት የመሠረታዊ ማህበሩ የበላይ
አካል ነው፡፡

9.2 ከድርጅቱ አደረጃጀትና የሥራ ፀባይ የተነሳ ጠቅላላ የማህበሩ አባላት በሙሉ በስብሰባ ላይ መገኘት
የማይችሉ ከሆነ የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ ባሉት የመገናኛ ዘዴዎች ወይንም በድርጅቱ ዋና ዋና
የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከስብሰባው ቀን አስር ቀን በፊት ከተለጠፈ በኋላ ምልዓተ ጉባኤ
የሚሆነው ከአባል ሠራተኞች 50+1 በስብሰባው ላይ ሲገኙ ይሆናል፡፡ በመጀመሪያ ስብሰባ ከላይ
የተጠቀሰው የአባላት ብዛት ካልተገኘና ስብሰባው ለሌላ ጊዜ ከተላለፈ ለሁለተኛ ጊዜ የሚደረገው
ስብሰባ በተገኙት አባላት ይወሰናል፡፡

9.3 የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በዓመት አንድ ጊዜ ይደረጋል ሆኖም ምክር ቤቱ ወይም ሥራ አስፈጻሚ
ኮሚቴው ወይም አባል ሠራተኞች ከግማሽ በላይ ከጠየቁ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡

9.4 ጉባኤውን የሚመራው የማኅበሩ ሊቀመንበር ይሆናል፡፡ እርሱ በሌለበት ጊዜ ምክትል ሊቀመንበሩ ይሆናል፡፡ ሁለቱም
በሌሉበት ጊዜ በፀሐፊው ይሆናል፡፡ ሦስቱም በሌሉበት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚወክለው የስራ አስፈጻሚ
አባልስብሰባውን ይመራል ፡፡

9.5 የጉባኤው የመሰብሰቢያ ቀን፣ ቦታ ሰዓት የሚወሰነው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ይሆናል፡፡
9.6 የጉባኤው ስብሰባ ከመድረሱ ከአንድ ወር በፊት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ማኅበርተኞች በጉባኤው

አጀንዳ ላይእንዲሰፍርላቸው የሚፈልጉአቸውን ጉዳዮች እንዲያቀርቡ በማስታወቂያ ይጠይቃል፡፡

9.7 ጉባዔው ከመድረሱ ከአስር ቀን በፊት የጉባኤው መሰብሰቢያ ቦታ ፣ ቀንና ሰዓት ማኅበርተኞች

በማስታወቂያ ወይም በሌሎች አማራጮች እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡

9.8 በጣም አስቸኳይ በሆኑ ደንቦች ወይም በልዩ ልዩ ምክንያት ወይም ከማኅበርተኞቹ 50%

+1 ሰዎች ሲጠይቁ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወይም ም/ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ ሊጠራ ይችላል፡፡

9.9 የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በታዛቢነት የሚጋብዘው ሰው በማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤ

አንቀጽ 10

የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ተግባርና ኃላፊነት

10.1 የመሠረታዊ ማህበሩን ደንብ ያጸድቃል ፣ ያሻሽላል ፣ ይለውጣል፡፡

10.2 የመሠረታዊ ማህበሩን ምክር ቤት ፣ ሥራ አስፈፃሚ ፣ የዘርፍ ማህበራት ኮሚቴዎችንና ፣ የኦዲት


ኮሚቴንና አባላትን ቁጥር ይወስናል፡፡

10.3 የመሠረታዊ ማህበሩን ም/ቤት ፣ የኦዲት ኮሚቴ አባላትን ይመርጣል፡፡

10.4 ከምክር ቤቱና ከኦዲት ኮሚቴ የሚቀርቡለትን ሪፖርቶች ይመረምራል ያጸድቃል፡፡

10.5 ማህበሩን በሚመለከቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፡፡

10.6 አስፈላጊ ሲሆን ለማህበሩ ምክር ቤት ወይም ለምክር ቤትና ለክፍል ተጠሪዎች የጋራ ስብሰባ እንደ
ሁኔታው ውክልና ሊሰጥ ይችላል፡፡

10.7 በሠራተኛ አዋጅ 377/96 መሠረት ማህበሩ በሚፈርስበት ጊዜ ተፈጻሚ እንዲሆን በማህበሩ ንብረትና
ገንዘብ ላይ ይወስናል፡፡
አንቀጽ 11

የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ምክር ቤት

11.1 የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ምክር ቤት ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ስብሰባ ሆኖ በስብሰባዎች መካከል
የመሠረታዊ ማህበሩን የሚመራ አካል ነው፡፡

11.2 የመሠረታዊ ማህበሩ ም/ቤት የስራ አስፈጻሚውን ጨምሮ 15 (አስራ አምስት) አባላት ይኖሩታል፡፡
ከዚህ ውስጥ 5 (አምስት) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ፣ 3 (ሶስት) ኦዲት ኮሚሽን አባላት ሲሆኑ
ቀሪዎቹ 7 (ሰባት) የም/ቤት አባላት ደግሞ ለስራ አስፈጻሚ ተለዋጭ አባልት ናቸው፡፡

11.3 የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ምክር ቤት በ 3 ወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል፡፡ ሆኖም
የማህበሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ካመነበት ወይም ከምክር ቤቱ አባላት ሁለት ሦስተኛው (2/3 ኛው)
ከጠየቁ አስቸኳይ ስብሰባ ሊደረግ ይችላል፡፡

11.4 ተጠባባቂ የምክርቤት አባላት የስራ አስፈፃሚው አባል በፈቃዱ ስራውን ሲለቅ ወይም ወደ ስራ ከአገር
ቤት ሲወጣ ስራውን በለቀቀው ስራ አስፈፃሚ ቦታ ተለዋጭ ስራ አስፈፃሚ አባል እንዲሆኑ ከስራ
አስፈፀሚው አቅራቢነት በተጓደለው ስራ አስፈፃሚ አባል ቦታ ይሾማል፡፡

አንቀጽ 12

የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ምክር ቤት ተግባርና ኃላፊነት፣

12.1 የማህበሩን ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎችና መመሪያዎች ተግባራዊ ማድረግ፣

12.2 የመሠረታዊ ማህበሩን የበጀትና የዕቅድ አፈጻጸም በቅርብ መከታተል፣

12.3 የመሠረታዊ ማህበሩን ምክር ቤት አባላት ላይ በማህበሩ የዲስፕሊን ደንብ መሠረት ውሳኔ
ያስተላልፋል ፡፡

12.4 በማኅበሩ የአመራር መመዘኛ (መስፈርት) መርህ መሠረት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ምርጫ
የሥራ ድልድል ያከናውናል ፡፡

12.5 ከመሠረታዊ ማህበሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚቀርቡለትን ሪፖርቶች ይመረምራል ፣ አስፈላጊውን
መመሪያና ውሳኔ ይሰጣል፡፡

12.6 ምክር ቤቱ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አቅራቢነት ለሠራተኛው ጥቅም ማስከበሪያና ከዚሁ ጋር
ለሚያያዙ ተጨባጭ የሥራ ክንውኖች የሚውል እስከ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የመፍቀድ
ስልጣንና ኃላፊነት ይኖረዋል ፡፡ ነገር ግን የማህበሩ አብይ ሥራዎችን ለማከናወን ኢንቨስት ለማድረግና
አክሲዮን ለመግዛት የገንዘቡ መጠን ከተጠቀሰው ገንዘብ በላይ ሊጨምር ይችላል ፡፡

12.7 የማህበሩ ቁጥጥር ኮሚቴ (ኦዲት ኮሚቴ) በሚጠየቁበት ወቅት የማህበሩን የወጪንና የገቢውን ሁኔታ
ይመረምራል፡፡ ውጤቱንም ለጠቅላላ ጉባኤ ያቀርባል ፡፡
12.8 የማኅበሩ አመራር አካላት መካከል በተለያዩ ምክንያቶች የተመረጡበትን ሥራ ማከናወን ባይችሉ ፣
ምክር ቤቱ በምትካቸው በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የሚቀርቡትን የምክርቤቱ አባለት መካከል
ተመራጭ በጥልቀት በማየት ከም/ቤት አባላት ውስጥ ባላቸው ብቃትና የስራ ቁርጠኝነት መርጦ
ለአመራርነት የቀረቡትን ገምግሞ ያጸድቃል ፡፡

12.9 የማህበሩን የተለያዩ ሥራዎች ለማከናወን በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚቋቋሙትን ልዩ ልዩ ንዑሳን
ኮሚቴዎች የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል ፣ ውሳኔ ያስተላልፋል ፡፡

12.10 የማህበሩ አመራር አባላት ለማህበሩ የሥራ ጉዳይ ከሚኖርበት አካባቢ ውጭ ሲመደቡ የውሎ አበል
እንደ አስፈላጊነቱ ይወሰናል ፡፡ የአመራር አባላቱ የተመደቡበት የማህበሩ ሥራ ከአገር ውጭ ከሆነና
ወጪው በሌላ አካል የማይሽፈን ከሆነ በድርጅቱ የውሎ አበል አከፋፈል መሠረት ወጭአቸውን ወስኖ
ይከፍላል ፡፡ በሌላ አካል የሚሸፈን ወጪ ከድርጅቱ የአበል አከፋፈል ደንብ የሚያንስ ከሆነ ልዩነቱን
በቅድሚያ ይከፍላል ፡፡

12.11 ማህበሩ አባል ለሆነበት ፌዴሬሽን ተወካዮች ይመርጣል ፡፡

12.12 ከጠቅላላ ጉባኤ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል ፡፡

12.13 በሁኔታዎች አስገዳጅነት ካልተስተጓጎለ በስተቀር የማኅበሩ የአመራር አባላት ምርጫ በአራት ዓመት
አንድ ጊዜ

ይደረጋል (ይከናወናል) ፡፡

አንቀጽ 13

ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

13.1 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤ እና ለምክር ቤት ሆኖ፣ የማህበሩን የዕለት
ተዕለት ሥራ የሚመራ አካል ነው፡፡

13.2 የሕብረት ስምምነት ድርድር ከመጀመሩ በፊት ለህብረት ስምምነት ዝግጅት ግብዓት የሚሆኑ
ሃሳቦችን ከአባላት ይሰበስባል ከአሰሪው ድርጅት ጋር የሚደራደሩ አባላትን በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
አቅራቢነት ከሥራ አስፈጻሚው ወይንም ከምክር ቤት አባላት እንዲሁም ልዩ ሙያ (አስረጂነት)
ሲያስፈልግ እንደ አሰፈላጊነቱ ልዩ ሙያ ካስፈለገበት የስራ ክፍል ከአባላት እንዲመረጡ ያደርጋል
ውጤቱንም በየጊዜው ይገልፃል፡፡

13.3 የአባላትን መዋጮ ያሰባስባል ፡፡

13.4 የማህበሩን ንብረት ገንዘብና ጽ/ቤት ያስተዳድራል ፡፡

13.5 የመሠረታዊ ማህበሩን ምክር ቤት ስብሰባዎች አጀንዳና ሪፖርት ያዘጋጃል ፡፡


13.6 የድርጅቱን የሥራ ደንብ ፣ የመንግስት አዋጆችና መመሪያዎች በሠራተኛው ተሳትፎ እንዲወጡና
ሠራተኛው በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረግ የሠራተኛውንም መብትና ጥቅም በዚህ መሠረት
ማስጠበቅ ፣

13.7 ስለ ሥራው አፈጻጸም ለምክር ቤቱናለጠቅላላ ጉባኤ ሪፖርት ያቀርባል ፡፡

13.8 ከምክር ቤቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ፡፡

13.9 ማህበሩ 5 (አምስት) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ይኖሩታል ፡፡

13.10 ኮሚቴው የሚሰጠው ውሳኔ ተፈጻሚነት የሚኖረው በድምጽ ብልጫ ሲደገፍ ሲሆን የኮሚቴው
ስብሰባ የተሟላ የሚሆነው የአባሎቹ ሃምሳ በመቶ ሲደመር አንድ (50+1) ሲገኝ ብቻ ነው ፡፡

13.11 የኮሚቴው አባሎች ወይም ሌሎች አባሎች ሥራቸውን በደንቡ መሠረት የሚያካሂዱ ከሆነ ወይም
በልዩ ልዩ ምክንያት ሥራቸውን በደንቡ መሠረት መቀጠል ካልቻሉ ኮሚቴው ጉዳዩን ለምክር ቤት
አቅርቦ በምትካቸው ሌላ ሰው እንዲመረጥ ያደርጋል ፡፡ በአመራር መካከልም አስፈላጊ ሲሆን
ሽግሽግ ይካሂዳል ፡፡

13.12 የኮሚቴው አባል የሆነ ሰው ሥራውን በፈቃዱ ለመልቀቅ ከፈለገ በስራ አሰፈጻሚው አቅራቢነት
የሥራ መልቀቂያውን ደብዳቤ ለምክር ቤቱ በማቅረብ ሲጸድቅ ሥራውን አስረክቦ ከአመራርነት
ሊሰናበት ይችላል ፡፡

13.13 ኮሚቴው በዓመት አንድ ጊዜ ለጠቅላላ ጉባኤ አጠቃላይ የሥራ ሪፖርት ያቀርባል ፡፡ በተጨማሪም
እንደ አስፈላጊነቱ በየጊዜው መግለጫዎችን ለማኅበሩ አባላት ይሰጣል ፡፡

13.14 የማህበሩን ገንዘብ በወቅቱ ለማይከፍሉ አባሎች ማስጠንቀቂያ ይሰጣል ፡፡ ከሦስት ማስጠንቀቂያ
በኋላ ጉዳዩን ለም/ቤትአቅርቦ ከአባልነት ይሰርዛቸዋል ፡፡

13.15 በማህበሩ አባሎችም ሆነ መሪዎች መካከል አለመግባባት ሲፈጠር ጉዳዩን መመርመርና በተጨባጭ
ማስረጃ በሚደገፍ በግልጽ ሂስና ግለሂስ በማድረግ ያለመግባባትን ለማስወገድ አስፈላጊውን ጥረት
ያደርጋል፡፡ በውይይት ሊፈጸም ካልቻለ ግን ለውሳኔው ወደ ምክር ቤት ያሳልፋል፡፡ ሆኖም በውሳኔው
ቅር የተሰኘ ወገን በምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ይግባኙ በአጀንዳ ተይዞለት እንዲታይ ማድረግ
ይችላል ፡፡

13.16 ማናቸውም የማህበር መሪ ወይም አባል በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ከተገለጸው ውጭ የማህበሩን
ንብረት በይዞታው ወይም በቁጥጥር ሥራ ያደረገ ወይም የማህበሩን ገንዘብ ያጠፋ መሆኑ
ሲረጋገጥበት ከአባልነት ታግዶ ጉዳዩን አባል ማህበርተኞች እንዲያውቁ አድርጎ ስልጣን ባለው ፍርድ
ቤት ክስ ለመመስረት ይችላል፡፡
13.17 በዚህ አብይ ኮሚቴ ስር ለጊዜው በማህበሩ መዋቅር ላይ ያልታዩ አዳዲስ ንዑሳ ኮሚቴዎች እንደ
አስፈላጊነታቸው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስራውን እንደጀመረ አቋቁሞ ለምክር ቤት ያጸድቃል፡፡

13.18 በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ስልጣናቸውና ተግባራቸው ላልተገለጸ ለማንኛውም ንዑሳን ኮሚቴዎችም
ሆነ ለሌሎች ጊዜያዊ ኮሚቴዎች የሥራ መመሪያና ደንብ እያወጣ ይቆጣጠራል፡፡

13.19 የሊቀመንበሩን ፣ የዋና ፀሐፊውን ፣ የሂሳብ ሹሙን ፣ የም/ሊቀ መንበሩን


የም/ፀሐፊውንና የገንዘብ ያዥን ፊርማ የማህበሩ ሂሳብ ለሚገኝበት ባንክ ይሰጣል፡፡ ይህም የማኅበሩ
ተቀዳሚ ፈራሚ አመራሮች በሌሉበት ጊዜ በውክልና ሊሰሩ እንዲያገለግል ይሆናል ሆኖም በውክልና
ለሚሰሩበት ጊዜ ለባንክ ፣ ለወጪ ትዕዛዞች እንዲሁም ፊርማ የሚፈልጉ ወሳኝ ጉዳዮችን
ለማከናወንየውክልና ደብዳቤ ከወካዩ ሊኖራቸው ይገባል ፡፡

13.20 የማህበሩ ቅጥር ሠራተኞች እየመለመለ በግልጽ ማስታወቂያ አወዳድሮ ቅጥር ይፈፅማል ፤ በሥራ
ቦታቸው ምደባ ይሰጣል ፣ ይቆጣጠራል፡፡

13.21 ለማህበሩ ሥራ ማስኬጃ ተብሎ በማህበሩ ጽ/ቤት ከሚቀመጠው ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
ውስጥ የሚደረጉ ወጪዎችንና የማህበሩን ቋሚ ወጪዎች የመፍቀድ ስልጣን አለው ፡፡ በተጨማሪም
ለተጨባጭ የማህበሩ ሥራ እንደ ሁኔታው አስገዳጅነት በቃለ ጉባኤ ተይዞ እስከ ብር 50,000.00 (ሃምሳ
ሺህ ብር) ወጪ ማድረግ ይችላል ፡፡

13.22 ለምክር ቤቱ የሚቀርብ የውሳኔ መጠየቂያ አጀንዳዎች አስቸኳይ ካልሆኑ በስተቀር ከስብሰባው ቀን
አስራ አምስት ቀን ቀደም ብሎ ለምክር ቤቱ እንዲደርሱ ያደርጋል ፡፡

13.23 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የማህበሩን ደንብ ለማዘጋጀት ፣ ለመተርጎም ፣ መሻሻል የሚያስፈልጋቸውን
አንቀጽ ለማሻሻል ደንቡን የማይቃረኑ ንዑሳን ደንቦች ለማውጣት እንዲሁም የሥራ አመራር ሥነ
ሥርዓት (ፕሮሲጀርስ) ለአሰራር እንዲያመች አድርጎ መመሪያ ይሰጣል ፣ የሚዘጋጁትንም ደንቦች
ለም/ቤት አቅርቦ በአብላጫ ድምጽ ተቀባይነት ሲያገኝ ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ በማጸደቅ በስራ ላይ
ያውላል፡፡

13.24 ከማኅበሩ አመራር አባላት እና ም/ቤት አባሎች መካከል በተለያዩ ምክንያቶች የተመረጡበትን ሥራ
ማከናወን ባይችሉ ፣ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በምትካቸው ከም/ቤት አባላት ውስጥ ለስራ
አስፈጻሚ ኮሚቴነት ሊሰሩ የሚችሉ ሰዎችን መርጦ ለም/ቤት በማቅረብ አጸድቆ ያስመድባል፡፡

13.25 ከም/ቤቱና ከጠቅላላ ጉባኤ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል ፡፡

አንቀጽ 14

ኦዲት ኮሚቴ

የማህበሩ የኦዲት ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለጠቅላላጉባኤ ሆኖ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል ፡፡

14.1 የማህበሩ ምርጫ በሚካሄድበት ጊዜ 3 (ሦስት) ዋና እና 2(ሁለት) ተጠባባቂ የውስጥ ኦዲተሮች በጠቅላላ
ጉባኤ ይመረጣሉ፡፡
14.2 የአባላት መዋጮ በወቅቱ መሰብሰቡንና በተገቢው ቦታ መቀመጡን ይቆጣጠራል፡፡

14.3 የማህበሩ ገንዘብና ንብረት በትክክል መመዝገቡን እና ለተገቢው አገልግሎት መዋሉን ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፡፡

14.4 በማህበሩ ስር የሚተዳደሩ የአገልግሎት መስጫና የገቢ ማስገኛ ተቋማት ሥራ በትክክል መካሄዱንና
የገንዘብና የንብረት አስተዳደራቸው የማህበሩን ደንብ የተከተለ መሆኑን ይቆጣጠራል፡፡

14.5 የማህበሩ ዕቃ ግዥና ልዩ ልዩ ወጪዎች በደንቡ መሠረት መካሄዳቸውን ይቆጣጠራል፡፡

14.6 በየ 3 ወሩ ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በየ 6 ወሩ ለምክር ቤት እንዲሁም በዓመት አንዴ ለጠቅላላ ስብሰባ
ስለ ማህበሩ ገቢና ወጪ፣ ንብረትና ሀብት በጠቅላላው ስለ ሂሳብ ይዘት ሪፖርት ያቀርባል፡፡

14.7 ኦዲተሮች በማንኛውም ጊዜ የሂሳብ መዝገቦችንና ሌሎች ሂሳብ ነክ የሆኑ ሰነዶችን ሊመረምሩ
ይችላሉ፡፡ የማህበሩ ደንብ በማህበሩ ተመራጮች በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን ይቆጣጠራል ፡፡

14.8 የማህበሩን የገንዘብ አያያዝ ለመመርመር በሚጠይቁበት ጊዜ ተመርማሪው አካል ወይም የማኅበሩ
አመራር ዛሬ ነገ በማለት ኦዲተሮችን ለማወክ ከሞከረ ወይም የተሳሳተ ማስረጃ ካቀረበላቸው
የተሳሳተ ሰነድ የሚገኝበትን ቦታ እንደአስፈላጊነቱ አሽጎ ሊመረምር ይችላል ፡፡

አንቀጽ 15

የማህበሩ ሊቀመንበር

15.1 ሊቀመንበሩ ጠቅላላ ጉባኤ፣ የምክር ቤትና የስራ አስፈፀሚ ኮሚቴ ስብሰባ ይመራል ፣ ምክር ቤቱና
ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚሰጠውን መመሪያ በመከተል የማህበሩን ሥራ ይመራል፡፡

15.2 የማህበሩን ሥራ በበላይነት ይቆጣጠራል ፣ በማህበሩም ስም ደብዳቤዎችን ይፈርማል፡፡ እንዲሁም


በማናቸውም ማህበሩን በሚመለከቱ ጉዳዮች ማህበሩን የመወከል ስልጣን አለው፡፡

15.3 የማህበሩን ጠቅላላ ስብሰባ ፣ የምክር ቤት ስብሰባ ፣ ምክር ቤትና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
ስብሰባዎችን በሊቀመንበርነት ይመራል፡፡

15.4 የማኅበሩ ጽ/ቤት ሥራን ይቆጣጠራል፡፡

15.5 የማህበሩን የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች በስርዓት እንዲጠበቁ ያደርጋል፡፡

15.6 የማህበሩ ገንዘብ ወጪና ገቢ በሚሆንበት ጊዜ ደንቡ ከሚፈቅድላቸው የማህበሩ መሪዎች ማለትም
ከዋና ፀሓፊው ወይም ከሂሳብ ሹሙ ጋር በመሆን ይፈርማል፡፡

15.7 አስፈላጊ በሆነ ሠዓት ለማኅበሩ ስራ ውክልና የመስጠት ስልጣን አለው ፡፡


15.8 ማኅበሩን ወክሎ ይከሳል ይከሰሳል

15.9 ሌሎች የማኅበሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ም/ቤት የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል ፡፡

አንቀጽ 16

ምክትል ሊቀመንበር

16.1 ምክትል ሊቀመንበሩ ሊቀመንበሩን በማንኛውም ሥራ ይረዳል፡፡ ሊቀመንበሩ በሌላ ጊዜ በርሱ ምትክ
ሥራውን በሙሉ ይሰራል፡፡

16.2 በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና በም/ቤት የሚሰጠውን ሥራ ያከናውናል፡፡

አንቀጽ 17

ዋና ፀሐፊ

17.1 ዋና ፀሐፊ የማህበሩን ስብሰባዎች ሁሉ ቃለ ጉባኤ ይቀበላል ፣ በማንኛውም ስብሰባ ላይ


በቀደምትነት ያለፈውን ስብሰባ ቃለ ጉባኤውን አዘጋጅቶ እንዲጸድቅ ያቀርባል፡፡

17.2 ማናቸውም ውሳኔዎች ከተፈረመባቸው በኋላ በእርሱ ክትትል በፋይል ተደራጅተው እንዲቀመጡ
ያደርጋል ፡፡

17.3 ማናቸውም የማህበሩን መዝገብ፣ አርማ፣ ማህተምና ሰነድ ይይዛል፡፡

17.4 የጽሕፈት ቤቱን የጽሕፈት ሥራ ያከናውናል፡፡

17.5 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የሚያዘውን ሥራ ሁሉ ያከናውናል፡፡

17.6 የማህበሩን ገንዘብ ገቢና ወጪ በሚሆንበት ጊዜ ደንቡ ከሚፈቅድላችው የማህበር መሪዎች ማለትም
ከሊቀ መንበሩና ሂሳብ ሹሙ ጋር ይፈርማል፡፡

17.7 የማህበሩን ጽ/ቤት ሠራተኞች ይቆጣጠራል፡፡

17.8 የማህበሩን አመታዊ የሥራ ክንውን ሪፖርት ያዘጋጃል፡፡

17.9 የማኅበሩ ሊ/መንበርና ምክትል በሌሉበት ጊዜ እነሱን ውክሎ ይሰራል ፡፡

17.10 የማኅበሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሆነ ማንኛውም አባል በተለያዩ ምክንያቶች የተሰጣቸውን ሃላፊነት
መወጣት ባይችሉ በጽ/ቤት ሃላፊው አቅራቢነት በዚሁ ኮሚቴ ተገምግሞ ተገቢው ውሳኔ ይሰጣል ፡፡

አንቀጽ 18
የማህበሩ ሂሳብ ሹም

18.1 ማንኛውም የማህበሩን የገቢና የወጪ ሰነድ ይይዛል፡፡

18.2 የማህበሩን የገቢና የወጪ ዝርዝር መግለጫ ያዘጋጃል፡፡

18.3 ማህበርተኞች መዋጮን በትክክል ለመክፈላቸው ይቆጣጠራል፡፡ ክፍያ ያላሟሉትን ማህበርተኞች


እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሪፖርት ያቀርባል፡፡

18.4 የማህበሩ ገንዘብ ወጭ በሚሆንበት ጊዜ ደንቡ ከሚፈቅድላቸው የማህበሩ መሪዎች ማለትም ከሊቀ
መንበሩና ከዋና ፀሐፊው ጋር ይፈርማል፡፡

18.5 ከማኅበሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል ፡፡

አንቀጽ 19

የማህበሩ ገንዘብ ያዥ

19.1 ማንኛውም የማህበሩ ገቢ ሲደርሰው በ 24 ሰዓት ውስጥ የማህበሩ ሂሳብ በሚገኝበት ባንክ በማህበሩ
ስም ገቢ ያደርጋል፡፡

19.2 ለመጠባበቂያ የተመደበውን ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በስሙ ቼክ ተሰርቶ ይይዛል ገንዘቡ
ወጪ ሲደረግ በተደራጀ ሰነድ በየወሩ ያወራርዳል፡፡

አንቀጽ 20

የማህበሩ የገቢ ምንጮች

20.1 የማህበሩ ዋና የገቢ ምንጭ ከማህበርተኞች የሚዋጣው የማህበርተኝነት መመዝገቢያና ወርሃዊ


መዋጮ ይሆናል፡፡

20.2 ማህበሩ በሚያዘገጋጃቸው ልዩ ልዩ የመዝናኛ ዝግጅቶች የሚገኘው ገቢ የማህበሩ የገቢ ምንጭ


ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

20.4 ማህበሩ ከኢንቨስትመንት፣ ከገንዘብና ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት አክሲዮን በመግዛት
እንዲሁም ከልዩ ልዩ ሼር ከሚሸጡ ድርጅቶች ሼር በመግዛት በሚያገኘው ትርፍ ወይም ወለድ
የገቢ ምንጭ ይሆናል፡፡

20.5 ጠቅላላ ጉባኤ ከወሰነ አባሎች ተጨማሪ መዋጮ እንዲያዋጡ ሊደረግ ይችላል፡፡

አንቀጽ 21
የአባላት መዋጮ

21.1 እያንዳንዱ አባል ለመመዝገብ 100 (አንድ መቶ) ብር እጩ መኮንን ወይም ከአንድ አመት በላይ ስራ
ላይ ኦፊሰር ያልሄደ ተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ 50 (ሃምሳ) ብር እንሁም በየጊዜው ወደ ስራ የሚሄድ
ኦፊሰር 100 (አንድ መቶ) ብር በየወሩ የማህበርተኝነት መዋጮ ይከፍላል፡፡

21.2 ማንኛውም የማህበሩ አባል የሆነ ሠራተኛ አንድ ጊዜ የ 6 ወር መክፈል የይችላል ከፈለበትን ደረሰኝም
ይቀበላል፡፡ በባንክ የከፈላ አባል የባንክ ደረሰኙን አሳይቶ ደረስኝ ይሰራለታል፡፡

21.3 በማንኛውም ምክንያት ከማህበሩ የወጣ ሰው የከፈለው ገንዘብ አይመለስለትም፡፡


21.4 ጠቅላላ ጉባዔው ከወሰነ የመዋጮውን ገንዘብ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
21.5 አንድ ማህበርተኛ ከማህበሩ በገዛ ፈቃዱ የወጣና እንደገና ማህበርተኛ የሚሆን ሠራተኛ ከማህበሩ የወጣበትን
ምክንያት በጽሁፍ ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አቅርቦ ከተፈቀደለት ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) እንደገና
ከፍሎ አባል መሆን ይችላል ፡፡

21.6 ማንኛውም የማህበሩ አባል ከማህበሩ ጽ/ቤት አባልነት ጊዜያዊ እገዳ ቢደረግበት ወይም ከማህበሩ አባልነት
እስካልወጣ ድረስ የማህበርተኝነት መዋጮ ገንዘብ አይቋረጥም ፡፡

አንቀጽ 22

የማህበሩ አባል ስለመሆን

22.1 ማንኛውም በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ሕግና የሚዳኝና መርከበኛ የሆነ ሠራተኛ የማህበር አባል ለመሆን
ፈቃደኛ ከሆነ በአባልነት ይመዘገባል፡፡

22.2 አባል ለመሆን የሚፈልግ ሠራተኛ በማህበሩ የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ በመሙላት ማህበርተኛ
ለመሆን ፈቃደኛነቱንና የማህበሩንም ግዴታ የሚያከብር መሆኑን በፊርማ ያረጋግጣል፡፡

22.3 በዚህ ንዑስ አንቀጽ 24.2 መሠረት የተሞላው ማመልከቻ ቅጽ መሟላት በማህበሩ ስራ አስፈጻሚ
ኮሚቴ ሲረጋገጥ ሠራተኛው በአባልነት ይመዘገባል፡፡

22.4 በአባልነት የተመዘገበ ማህበርተኛ የአባልነት መታወቂያ ካርድ ይሰጠዋል፡፡

22.5 የራሱ ጥፋት ባልሆነ ምክንያት እስር ቤት የቆየ አባል ሠራተኛ በነፃ ተለቆ ድርጅቱ ወደ ሥራው
ከመለሰውና እንደገና የማህበር አባል ለመሆን ካመለከተ ጉዳዩን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አጥንቶ
ከሥራ ውጭ ለሆነበት ጊዜ መክፈል የነበረበትን መዋጮ ዝቅተኛውን የአባልነት በየወሩ 50 (ሃምሳ) ብር
ከፍሎ በአባልነት ሊቀበለው ይችላል፡፡

አንቀጽ 23

የማህበሩ አባላት መብት

ማንኛውም የማህበሩ አባል የሚከተሉት መብቶች ይኖሩታል፡፡


23.1 የመምረጥና የመመረጥ

23.2 በሕግ ፤ በሕብረት ስምምነት፣ በሥራ ደንብ፣ ሊያገኝ የሚገባቸውን መብቶች ጥበቃ የማግኘት፣

23.3 በሥራ ክርክር ወቅት ከማህበሩ ተገቢውን ድጋፍ ማግኘት፣

23.4 ማህበሩ ለአባላቱ የሚያደራጀው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎቶች የመገልገል ወይም የመጠቀም፣

23.5 በስብሰባው ወቅት ሃሳብ የማቅረብ፣የመጠየቅ፣ የመቃወም፣

23.6 ማንኛውም አባል የማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሚሰጠው መመሪያ ላይ ሃሳብና አስተያየት
በጽሑፍ ማቅረብ ይችላል፡፡

23.7 ማንኛውም አባል የማኅበሩን መረጃ በየጊዜው ጠይቆ የማወቅና የመረዳት መብት አለው፡፡

23.8 ማንኛውም አባል ከድርጅቱ ከሥራ ቢባረርና ጉዳዩ በክርክር ላይ ከሆነ ከማኅበርተኝነት አይሰረዝም፡፡

23.9 ማንኛውም የማኅበሩ አባል በሥራ ላይ እያለ የሥራ ክርክር ሲያነሳበሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ
መሠረት
ለልዩ ልዩ ወጪዎች አስፈላጊው ወጪ በማኅበሩ ሊሸፍን ይችላል ፡፡

አንቀጽ 24

የማህበሩ አባላት ግዴታ

ማንኛውም የማኅበሩ አባል የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩበታል፡፡

24.1 ወርሃዊ የአባላት መዋጮ በወቅቱ መክፈል፣

24.2 በማህበሩ ጠቅላላ ስብሰባ የተላለፈውን ውሳኔ የማክበር፣ በማህበር ስብሰባዎች ላይ የመገኘት፣

24.3 ለማህበሩ ንብረት ተገቢውን ጥበቃና ጥንቃቄ የማድረግ፣

24.4 ከማህበሩ የሚሰጠውን ውሳኔዎችና መመሪያዎች የማከናወንና የመፈጸም፣

24.5 ማህበሩ ተከራክሮለት ደሞወዙም ሆነ ሌሎች ወጪዎች ከተመለሱለት የማህበሩን ወጪ ለመመለስ


መተማመኛ መፈረምና በመተማመኛውም መሠረት የመፈጸም፣

አንቀጽ 25

የማህበሩ ግዴታ

25.1 ማንኛውም የማህበር አባል የኅብረት ስምምነቱን ሳይጥስና ጥፋተኛነቱ ሳይረጋገጥበት ለሚቋረጥበት
ደሞዝና ጥቅማጥቅም ማህበሩ ወጪውን የከፈለው ሠራተኛ ከሥራ ለወጣበት ጊዜ ደመወዙ በፍርድ
ቤት ትዕዛዝ እንዲከፈለው ከተደረገ አስቀድሞ ለጽ/ቤቱ በፈረመው መተማመኛ መሠረት ማህበሩ
ያወጣውን ወጪ ያስመልሳል፡፡
25.2 ከሥራ ወጥቶ ማህበሩ ተከራክሮለት የተመለሰ አባል ማህበሩ በገባው ግዴታ ከከፈለው ሌላ ያወጣውን
ልዩ ወጪና ኪሣራ ከድርጅቱ ጋር በመነጋገር ወይም በፍርድ ቤት ከሶ ወጪውን ያስመልሳል፡፡

25.3 የማህበሩን የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም ገንዘብ ሲያባክንና ለግል ጥቅሙ ሲያውል
የተገኘ ማህበርተኛ የማህበሩ አመራር ከሶ ንብረቱን ያስመልሳል፡፡

25.4 በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ለአባሉ የተቀመጡ መብቶችና ጥቅማጥቅሞችን የማስከበር ግዴታ አሉበት ፡፡

25.6 የማኅበርተኝነቱን /የአባልነቱን/ ግዴታ ያሟላ ማንኛውም የማኅበሩ አባል ለማኅበሩ መሪነት ወይም
ለማንኛቸውም የማኅበሩ ኮሚቴ አባልነት እጩ ሆኖ መቅረብ ይችላል፡፡

25.7 በዚህ ደንብ መሠረት አባል ሠራተኛ ከማህበሩ ጋር ያለው ግንኙነት በማንኛውም መልኩ ቢሆን ከተቋረጠ
ማኅበሩ ከሚያስገኘው ጥቅም ተካፋይ አይሆንም፡፡

25.8 ማንኛውም የማኅበሩ አባል በማንኛውም ምክንያት ከማኅበሩ ቢወጣ የከፈለው ገንዘብ አይመለስለትም፡፡

አንቀጽ 26

የማኅበሩ የሂሣብ አያያዝና ገንዘብ አቀማመጥ

26.1 የማኅበሩ የሂሣብና ገንዘብ በዘመናዊ ሂሣብ አያያዝና አጠባበቅ ዘዴ ይከናወናል፡፡

26.2 ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሚወስነው መሠረት ለጥቃቅንና አስቸኳይ ጉዳዮች በገንዘብ ያዥ በቼክ ተዘጋጅቶ ብር
10,000.00 / አስር ሺህ ብር / እንዲያዝ ይደረጋል ሌላው የማኅበሩ ገንዘብ በሙሉ በአቅራቢያው በሚገኘው
ባንክ ይቀመጣል፡፡

26.3 የማኅበሩ ገንዘብ ከባንክ ወጪ በሚሆንበት ጊዜ ሊቀመንበሩ ፣ ወይም ም/ሊቀመንበሩና ሂሳብ


ሹም በማኅበሩ ስም ይፈርማሉ፡፡
አንቀጽ 27

የማኅበሩ ንብረት

27.1 የማኅበሩ የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ሁሉ በማኅበሩ ስም ተመዝግበው በጥንቃቄ


አገልግሎት ላይ ይውላሉ ፡፡
27.2 የማኅበሩ ንብረትናሰነዶች በዘመናዊንብረት አጠባበቅ ዘዴ ይይዛል፡፡
27.3 በማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ ከተገለፀው ውጭ የማኅበሩን ንብረት ያለአግባብ መጠቀም ወይም
ሌሎች እንዲጠቀሙ ማድረግ አይቻልም፡፡

አንቀጽ 28
የማህበሩ አባላትና አመራር አካላት ልዩ ልዩ ጥቅማቅሞች

የማህበሩ አባላትና አመራር አካላት በማኅበሩ የሚከተሉት ልዩ ልዩ ጥቅማቅሞች ይኖሩታል ፡

28.1 የማኅበሩ አባል ወይንም አመራር አባላት ለማኅበሩ ሥራ ጉዳይ ከመኖሪያ አካባቢ ውጭ ተመድበው
ሲንቀሳቀሱ በኅብረት ስምምነቱ በተቀመጠው የድርጅቱ ውሎ አበል አፈጻጸም መሠረት ውሎ አበል
ይከፈላቸዋል ፡፡ ሆኖም አባሉ በሚሄድበት ቦታ ሌላ አካል (ድርጅት) የሚከፍለው ከሆነ ማኅበሩ
በድጋሚ አይከፍልም ፡፡
28.2 በአዲስ አበባ ውስጥ ለሴሚናር ፣ ለዎርክሾፕ ፣ ስብሰባዎችና ለተለያዩ ጥሪዎች የሚካፈሉ የሥራ
አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ወይም የማኅበር አባል በሴሚናሩ ፣ በወርክሾፑ ወይም በስብሰባ ለሚቆዩበት
ጊዜ በሚሳተፉበት ቦታ አበል የማይከፈላቸው ከሆነ ለእያንዳንዳቸው በቀን ብር 100.00 (አንድ መቶ
ብር) ይከፈላቸዋል ፡፡
28.3 ከስራ ሰዓት ውጭ ለማህበሩ ሥራ ለተለያዩ ስራዎች በማኅበሩ ጽ/ቤት ታዘው ለሚንቀሳቀሱ በስራ
የሚቆዩበትን ሰዓት ታሳቢ ያደረገ በሰዓት ብር 20.00 (ሃያ ብር) ይከፈላቸዋል ፡፡
28.4 ከኢትዮጵያ ውጭ የሥልጠና ዕድል ወይም ዎርክሾፕ ወይም ተመሳሳይ ዕድል አግኝተው የሆቴል
የትራንስፖርት ወጪውን ሥልጠና ሰጭው ድርጅት የሚሸፍን ከሆነ ለኪስ ገንዘብ የሚሆን ለአንድ
ጊዜ እስከ አምስት ቀን ድረስ 300 (ሦስት መቶ) የአሜሪካን ዶላር ከአምስት ቀን በላይ ሲሆን 600
(ስድስት መቶ) የአሜሪካን ዶላር ይሰጠዋል፡፡
28.5 አንድ የማኅበሩ አባል ውጭ ሀገር ሄዶ እንዲታከም በመንግስት የህክምና ቦርድ የተፈቀደለትን
የህክምና ማስረጃ ለማኅበሩ ጽ/በት ሲያቀርብ የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ትክክለኛና አሳማኝ
መሆኑን ሲያረጋግጥ ለአንድ ጊዜ ብቻ ለህክምናው ጉዞ ማስፈጸሚያ የሚሆን ብር 25,000 (ሃያ
አምስት ሺህ ብር) ማኅበሩ ለአባሉ ይሰጠዋል ፡፡

ይህም ተፈጻሚ የሚሆነው ለአንድ አባል በአምስት ዓመት ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው ሆኖም አባሉ ውጭ
ሀገር ሂዶ ከታከመ በኋላ የታከመበትን ማስረጃ ለማኅበሩ ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል ነገር ግን
የታከመበትን ማስረጃ ሳያቀርብ ቢቀር ማኅበሩ የወሰደውን ገንዘብ ተመላሽ እንዲያደርግ ያደርጋል ፡፡

28.6 አንድ የማኅበሩ አባል በስራ ላይ የአካል ጉዳት ቢደርስበት ማኅበሩ ብር 35,000 (ሠላሳ አምስት ሺህ
ብር) ይከፍላል ፡፡ ይህም ተፈጻሚ የሚሆነው በህክምና ቦርድ ተሰልቶ በሚቀርበው መሠረት ይሆናል
(ለአብነት ያህል ስሌቱም የጉዳቱ መጠን 20% (ሃያ በመቶ) መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ቢያቀርብ
ብር 7,000 /ሰባት ሺህ ብር/ ይከፈለዋል ማለት ነው ፡፡
28.7 የማኅበሩ አባል በህመም ወይም በአደጋ ቢሞት ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ይከፈላቸዋል ፡፡ ሆኖም
አባሉ ስለመሞቱ ከስራ ክፍሉ ወይም የሟች ህጋዊ ወራሾች ማስረጃ ካቀረቡ ለቀብር ማስፈጸሚያ
ከዚሁ ብር በቅድሚያ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ይሰጣል ፡፡ ቀሪው ብር 15,000 (አስራ አምስት
ሺህ ብር) ከአንድ ወር በኋላ የሟች ህጋዊ ወራሾች ማስረጃ ካቀረቡ ክፍያው ይፈጸማል ፡፡ ሆኖም ግን
የሟች ህጋዊ ወራሾች ነን ባዮች ከወር በኋላ የሚቀርቡ ከሆነ ክፍያው አይፈጸምም ፡፡
28.8 በአጋጣሚ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የማኅበሩ አባላት የሞት አደጋ ወይም ከስራ መፈናቀል
ቢያጋጥማቸው ወይም የጅምላ እስር ቢደርስባቸው ወይም ከነዚህ የተለየ ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ
አደጋ ቢያጋጥማቸው ማኅበሩ አባላትን ከአደጋው ለመታደግ አቅሙ ባይፈቅድ አስቸኳይ የጠቅላላ
ጉባኤ ጠርቶ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይችላል ውሳኔውም የመጨረሻ ይሆናል ፡፡
28.9 የማኅበሩ አባል የትዳር አጋር ወይም ልጅ ቢሞትበት (ቢሞትባት) ከድርጅቱ መረጃ ከቀረበ ለዕዝን
ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ማኅበሩ ይከፍላል ፡፡
28.10 የማኅበሩ አባል እናት ወይም አባት ቢሞትበት (ቢሞትባት) ከድርጅቱ መረጃ ከቀረበ ለዕዝን ብር
1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ማኅበሩ ይከፍላል ፡፡

28.11 ማንኛውም የማኅበሩ አመራር በመሪነቱ ወይም ለሌሎች አባላት ማህበሩን ወክሎ በሚያደርገው
ተሳትፎ ምክንያት አሰሪው መ/ቤት ከህብረት ስምምነቱ (ከህግ) ውጭ ከስራው ቢያሰናብተው
ድርጅቱ ካሰናበተበት ቀን አንስቶ ወደ ስራው እስኪመለስ ወይም ሌላ ስራ እስከሚያገኝ ድረስ
ማኅበሩ ጉዳዩን ወደ ፍ/ቤት በመውሰድ በማኅበሩ ጠበቃ አማካኝነት ይከራከርለታል ፡፡ እንዲሁም
በድርጅቱ ያገኝ የነበረውን የህክምና ጥቅማጥቅም ህጋዊ ደረሰኝ ሲያቀርብ ወጪው ይሸፈንለታል ፡፡
ሆኖም ማህበሩ የሚሸፍነው የህክምና ወጪ በዓመት ከብር 20,000.00 (ከሃያ ሺህ ብር)
መብለጥ የለበትም ፡፡
28.12 ማንኛውም የማህበር አባል ከኅብረት ስምምነቱ ውጭ ወይም ሌሎች የሀገሪቱን ህጎች
ሳይጥስና ጥፋተኛነቱ ሳይረጋገጥበት ድርጅቱ ከሥራ ቢያስወጣው ወይም ለጊዜው ቢያግደው
ጉዳዩ በዲሲፕሊን ኮሚቴ የሚታይ ከሆነ ማኅበሩን ወክለው በዲሲፕሊን ኮሚቴነት የተቀመጡ
የማኅበሩ ተወካይ/ተወካዮች ጉዳዩን አጣርተው ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባሉ ጥፋተኛ
እንዳልሆኑ ያቀረቡ ከሆነ ሠራተኛው ወደ ስራ ገበታው እንዲመለስ ማኅበሩ ጉዳዩን ወደ
ፍ/ቤት ወስዶ ይከራከርለታል ፡፡ ነገር ግን ጉዳዩ በዲሲፕሊን ኮሚቴ ያልታየ ከሆነ የማህበሩ
ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፣ የማኅበሩ የህግ ባለሙያዎችና ተበዳይ ሠራተኛው በሚያደርጉት
የጋራ ስብሰባ ስለ ሠራተኛው ጥፋተኛ አለመሆኑን ካጣሩ ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት ሄዶ ሙሉ
ወጪው ተሸፍኖ ማኅበሩ ይከራከርለታል ፡፡ በዚህም የተነሳ ሠራተኛው ከሥራ ከወጣበት ቀን
ጀምሮ የወር ደመወዙን ሃምሳ በመቶ 50% ለአስራ ስምንት ወራት ይከፈለዋል ነገር ግን በዚህ
ጊዜ ውስጥ የክስ ሂደቱ ውሳኔ ባያገኝ ክፍያው ተቋርጦ ማኅበሩ የክሱን ሂደት ውሳኔ
እስከሚያገኝ ድረስ ያስቀጥላል ፡፡ ሆኖም ክርክሩ ከማለቁ በፊት ሌላ ሥራ ቢያገኝ ማህበሩ
የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ወዲያውኑ ይቋረጣል፡፡
28.13 ማንኛውም የማኅበሩ አባል የስራ ክርክር ቢያጋጥመውና ክርክሩን በግል ጠበቃ ማከናወን
ቢፈልግ ወይም በግል ጠበቃ መከራከር የሚያስፈልግ አስገዳጅ ሁኔታ ቢያጋጥም ወጪውን
ማኅበሩ እንዲሸፍን አባሉ የሚፈልግ ከሆነ የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ
መክሮበት በሚወስነው መሠረት የሚፈጸም ይሆናል ፡፡
28.14 ማኅበሩን ወክሎ በድርጅቱ በተለያዩ ስራ ላይ በኮሚቴነት ለሚሳተፉ አባላት/አመራር የሰሩት
ስራና ያደረጉት አስተዋጽኦ በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እየተገመገመ (እየተመዘነ) ማበረታቻ
ሊሰጥ ይችላል ፡፡
28.15 እንደአስፈላጊነቱ በማኅበሩ ስራ አስፈጻሚ አቅራቢነት በም/ቤቱ ውሳኔ ሌሎች ጥቅማጥቅሞች
ለአመራሩ እና ለአባላት ሊያደርግ ይችላል ፡፡
አንቀጽ 29
የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት

29.1 ማህበሩ በአመት 1 ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ ያደርጋል፡፡ ሆኖም ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ወይም
ምክር ቤቱ ወይንም ከሚገኙት አባላት ከግማሽ በላይ በጽሑፍ ሲጠይቁ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ
ይችላል፡፡

29.2 የስብሰባው ምልዓተ ጉባዔ ከተገኙት አባላት 1/2 ኛ+1 ከተገኘ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

29.3 ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባላይ ከተገኙ አባላት በድምጽ ብልጫ ሲሆን ከግማሽ በላይ
ድምጽ ያገኘው ሐሳብ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡

አንቀጽ 30

30.1 የምርጫ አፈጻጸም ሥነ ሥርዓት

30.1.1 በሁኔታዎች አስገዳጅነት ካልተስተጓጎለ በስተቀር የማህበሩ መሪዎች ምርጫ በየአራት


አመት አንድ ጊዜ ይደረጋል ፡፡

30.1.2 ማንኛውም የማህበሩ ምርጫ የሚከናወነው ጠቅላላ ጉባኤው በሚመርጠው 5


የአስመራጭ ኮሚቴ አማካይነት ይሆናል ፡፡

30.1.3 የምርጫውም ሂደት በጠቅላ ጉባኤው ለተጠቃሚዎች በሚሰጠው ድምጽ ይሆናል ፡፡


ይህም የሚሆነው በአባላት ጥቆማ ነው፡፡

30.2 የአስመራጭ ኮሚቴ

30.2.1 በጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጡ 5 አባላት ይኖሩታል ፡፡


30.2.2 ምርጫው በአንቀጽ 30.1.2 በተገለጸው መሠረት ይሆናል ፡፡

30.2.3 የአስመራጭ ኮሚቴ ሊቀመንበርና ፀሐፊ ይኖረዋል ፡፡

30.2.4 የአስመራጭ ኮሚቴ አባል ለማህበር አመራር እጩነት አይቀርብም ፡፡

30.3 የአስመራጭ ኮሚቴ ስልጣንና ተግባር

30.3.1 የሠራተኛ ማህበሩን ሥራ አስፈጻሚነት፣ የኦዲት ኮሚቴ እና በጠቅላላ ስብሰባ እና


የማህበሩ ም/ቤት አባላት ከምክር ቤት ያስመርጣል፡፡

30.3.2 የምርጫውን ውጤት በአምስት ቀን ውስጥ ለማህበሩ አባላት በማስታወቂያ ሰሌዳዎች


ያሳውቃል፡፡ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላትና ለበላይ ለሚመለከተው የሠራተኛ
ፌዴሬሽንና ኮንፌዴሬሽን ማኅበራት በግልባጭ ያሳውቃል፡፡

30.3.3 የምርጫው ሥነ-ሥርዓት ተፈጽሞ በሚመለከተው የመንግስት አካል በተመዘገበ አስራ


አምስት ቀን ውስጥ በነባሩ ሥራ አስፈጻሚና በአዲስ የሥራ አስፈጻሚ መካከል
የንብረትና የሂሳብ ርክክብ ይደረጋል፡፡

30.4 የእጩ ተመራጮች መመዘኛ

ለማህበሩ አመራር አባል ሆኖ ለመመረጥ የሚችለው ፡-

30.4.1 በቂ እውቀትና የአመራር ችሎታ ያለው ፣

30.4.2 የሥነ-ምግባር ጉድለት የሌለበት ፣

30.4.3 በሠራተኛው የሚታመንና ሙሉ ወገናዊነትን የሚያሳይ ፣

30.4.4 በማህበር አባልነት ቢያንስ ሁለት ዓመት የቆየ መሆን አለበት ፡፡

30.4.5 የክፍል ተጠሪ ለመሆን ቢያንስ በአባልነት አንድ ዓመት የቆየ መሆን አለበት ፡፡

30.4.6 አስመራጭ ኮሚቴ የእጩ ተመራጭ የሚሆኑ አባላትን ሲያስመርጡ የስራ ክፍሎችን
ተዋጽኦ ታሳቢ ያደርጋሉ ፡፡

አንቀጽ 31

የሥነ-ሥርዓት እርምጃ

31.1 ማንኛውም ማህበርተኛ ወይም የማህበር መሪ ፣ የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ሳያከብር ወይም
የማህበሩን ስምሲያጎድፍ ፣ ሚስጥር ሲያባክን ፣ ወይም የማህበሩን አቋም ለማናጋት ሲሞክር ወይም
የሐሰት ወሬ በመንዛት አባሎቹን ሲያወናብድ ወይም ተመሳሳይ ጥፋቶች ሲፈጽም ቢገኝ እንደጥፋቱ
ክብደት ከአባልነቱ እስከ መወገድ ይደርሳል ፡፡

31.1.1 አጥፊው ተራ አባል ከሆነ ውሳኔውን የሚሰጠው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይሆናል፡፡ ቅጣቱ የተወሰነበት
አባል ለምክር ቤት ይግባኙን ማቅረብ ይችላል፡፡

31.1.2 አጥፊው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ወይም የምክር ቤት አባል ከሆነ ውሳኔውን የሚሰጠው ምክር ቤት
ይሆናል፡፡ ቅጣት የተወሰነበት መሪ ለምክር ቤት ስብሰባ ይግባኙን ማቅረብ ይችላል ፡፡

31.2 ከአባልነት የተወገደ ወወይም ከማህበሩ አመራርነት የተገለለ ሰው በጥፋቱ ተጸጽቶ ይቅርታ ከጠየቀ
ጥፋቱ በማህበሩላይ ያደረሰው ጉዳት ተመዝኖ በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔ አባል ሊሆን ይችላል ፡፡

31.3 በንዑስ አንቀጽ 31.1 ከተጠቀሱት ጥፋቶች አንዱን ወይም ሁሉን በተደጋጋሚ ለሦስት ጊዜ የፈጸመ
ሰው ከአባልነት እስከመጨረሻ ይሰረዛል ፡፡

31.4 ንዑስ አንቀጽ 31.1 ከተጠቀሰው ሁኔታ ውጭ አባልነቱን የተወ /ያቋረጠ/ ሰው የአባልነት መመዝገቢያ
ቅጽ ከሞላ በኋላ ጉዳዩን በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተጣርቶ በአብላጫ ድምጽ ሲደገፍ በድጋሚ 200
ብር በመክፈል በአባልነት ይመዘገባል ፡፡

አንቀጽ 32

ማህበሩ ስለሚፈርስበት ሁኔታ

ማህበሩ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሁኔታዎች በአንዱ ምክንያት ሊፈርስ ይችላል፡፡

32.1 የተቋቋመበት ድርጅት ሲፈርስ፣ ሲቀላቀል፣ ሲከፋፈል፣

32.2 የአባላቱ ቁጥር በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ከተወሰነው በታች ሆኖ ከአንድ አመት በላይ
ሲቆይ ወደፊትም ከተወሰነው ቁጥር መድረስ አጠራጣሪ ሆኖ ሲገኝ፣

32.3 በንዑስ አንቀጽ 32.1 እና 32.2 ማህበሩም ሊፈርስ የሚችለው ከአባላቱ 2/3 ኛ እና
ከዚያ በላይ ሲስማሙና ሲወስኑ ብቻ ነው፡፡

32.4 ማህበሩ ሲፈርስ ንብረቱ በጠቅላላ ጉባኤው በሚወስነው መሠረት ይፈጸማል፡፡

አንቀጽ 33

የማህበሩ ደንብ ስለሚሻሻልበት ሁኔታ

33.1 ይህን ደንብ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አቅራቢነት
ለማህበሩ ም/ቤት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ በጠቅላላ ጉባኤ ከተገኙት አባላት ½ ኛ
+1 ድምጽ ሲደገፍ ሊሻሻል ይችላል፡፡

አንቀጽ 41
ደንቡ ስለሚጸናበት ጊዜ

ይህ ደንብ በጠቅላላ ጉባኤ ከፀደቀ ከዛሬ 22 ጥር ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

You might also like