Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 2

የሥራ ባህላችን

የሰው ልጆች የአኗኗር ዘዬ በየጊዜው እየተቀየረ ነው፡፡ በሁሉም ዘርፍ ዕድገት ለማስመዝገብ ከተፈለገ
ብዙ መድከምና መሥራት የግድ እየሆነ መምጣቱን ዓለም እያሳየች ነው፡፡

ለመኖር መልፋት፣ በተለይ በአገልግሎትና ንግድ ዘርፍ ያለው ውድድር አገራዊ ብቻ አይደለም፡፡
ውድድሩ ዓለም አቀፋዊ ሆኗል፡፡ ተወዳድሮ ለማሸነፍ ደግሞ ብዙ ሊለወጡ የማይችሉ የአሠራር
ዘዬዎች ያሻል፡፡ ከብዙዎቹ አንዱ የሥራ ባህል ነው፡፡

ዕድገት ከታሰበ የሥራ ባህል መቀየር ይኖርበታል፡፡ ያደጉት አገሮች ልምድም ይህንን ይነግረናል፡፡
መሻሻል አለበት ከምንለው የሥራ ባህላችን ውስጥ ለሥራ የምንሰጠው ቦታና ጊዜ አንዱ ነው ሲሉ
ብዙዎች ያነሳሉ፡፡ ከዚህ አንፃር የአገራችንን የሥራ ባህል በጥልቀት እንቃኝ ካልን እጅግ ኋላቀር
ስለመሆኑ በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡ ኋላቀር ብቻ ሳይሆን በዕቅድ የተመራ አሠራርም ብዙም
የለም፡፡ በአቋራጭ የመበልፀግ ፍላጐት ይንፀባረቅበታል፡፡ የሥራ ባህላችን ደካማነት በዚህ ብቻ
የሚገለጽ ሳይሆን፣ በሕግና በሥነ ምግባር የታነፀ አለመሆኑም ትልቅ ችግር ነው፡፡

ብዙዎች ወደ ቢዝነስ ሲገቡ በጥልቀት አስበውበት ፕላን አድርገው የዛሬንና የነገን ገበያ አልመው
ነው ብሎ ለመናገርም ያስቸግራል፡፡ ሌሎች አተረፉበት፣ አደጉበት የተባለ ቢዝነስ ከተሰማ ሌላውም
ያለጥናት ዘው ብሎ ሲገባ ይታያል፡፡ ሌሎችን ብቻ በማየትና የሥራውን የትርፍ ህዳግ ምን ያህል
እንደሆነ ሳይገነዘቡ የሚገቡት ጥቂቶች አይደሉም፡፡በዚህም ምክንያት አዲስ የስራ ዕድልም
መፍጠርንም ሆነ አዳዲስ ግኝቶች ለይ ለመፍጠርም ለመስራትም ሲፈልጉ አይታይም፡፡

ለዚህም ቢዝነሶቻቸውን በሒሳብ መዝገብ ይዘው ትርፍና ኪሳራቸውን ማወቅ ሀጥያት የሚመስላቸው፣
በየዕለቱ ወጪና ገቢያቸውን በትክክል የሚሠሩ የንግድ ሰዎቻችን ጥቂት መሆን ሊያሳስብ ይገባል፡፡
በተለይ በተለይ ከንግድ ሥራዎች ጋር በተያያዘ የደንበኞችን ፍላጐት አርክቶ እነሱም ተጠቃሚ
የሆኑበትን መንገድ ከማሰብ ይልቅ፣ በተቃራኒው ለመጓዝ መሞከር ትልቅ ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡

በሕግና በሥርዓት ጥሩ ተወዳዳሪ መሆን የምችልባቸው ብዙ ሥልቶችና የቢዝነስ ጥበቦች ቢኖርም፣


በዚህ መንገድ ከመጓዝ ይልቅ ተወዳዳሪን ጠልፎ አሸናፊ የመሆን ክፉ ምኞት ሲንፀባረቅም ይታያል፡፡
አገልግሎት እየሰጡ ተጠቃሚ ለመሆንና የደንበኞችንም ፍላጐት ለማርካት መደረግ ይገባቸዋል
ከሚባሉ እጅግ የበዙ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ፣ ደንበኞች በፈለጉበት ሰዓትና ጊዜ አገልግሎት ለማግኘት
ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ነው፡፡

ጠዋት 2፡30 ሰዓት ሥራ ገብቶ እስከ አሥራ አንድ ሰዓት ብቻ የሚሠሩ በርካታ የአገልግሎት ሰጪ
ተቋማት ከዚህ ያፈጀና ያረጀ አመለካከት አለመውጣታቸው፣ የአገራችን የስራ ባህል ወደኋላ ካስቀሩ
ምክንያቶች አንዱም ነው፡፡ እስካሁን ከሚሠራበት የአሠራር ሒደት ወጣ ብሎ ደንበኞችን ማስተናገድ
አንዱ የመወዳደሪያ መስፈርት መሆኑ እየታወቀ እንኳን፣ ይህንን ለማድረግ ሰበብ የሚያበዙ
መሆናቸው ሊጠቀስ ይችላል፡፡

ለምሳሌ ከዚህ ቀደም እንደ ባንክ ያሉ ተቋማት እንደሌሎች የመንግሥትና የግል መሥሪያ ቤቶች
አሥራ አንድ ሰዓት ላይ በራፋቸውን ጥርቅም ማድረጋቸው ከሥራ ወጥቶ ባንክ ለመጠቀም አላስቻለም
ነበር፡፡ በጊዜ በራፋቸውን መጠርቀማቸው ደግሞ ሥራ ላይ ያለ የባንክ ተገልጋይ ከሥራ ወጥቶ ወደ
ባንክ ቢሄድ አገልግሎት ስለማያገኝ፣ የግድ ሥራውን አቆይቶ ወደ ባንክ ቤት እንዲሮጥ ያስገድደው
ነበር፡፡ ይህ ትልቅ በደል ነው፡፡ አሁን ግን በተወሰነ ደረጃ በተለያዩ አማራጮች ይህ ችግር
ተስተካክሏል፡፡

በዚህ የስራ ባህላችን እና አዲስ ፈጣራ ለይ ያለን አመለካከት በፍጥነት መለወጥ ይኖርብናል፡፡ የስራ
ባህላችንን የሚያሳድጉ መጠነ ሰፊ የሆኑ ጥናቶችን በማካሄድ እና ፖሊሲዎችን በመንደፍ እና በቀመር
በጊዚዬ ወደ ተግባር በመግባት ኢትዮጵያም ከገባችበት ጦርነት በፍጥነት ተላቃ ፊቷን ወደ ልማት
ማዞር ማስቻል አለብን፡፡

ወርቅና ለም አፈር ላይ ተቀምጦ መራብና መለመን ስለሚያሳፍር፣ በተፈጥሮ የተለገሱ ፀጋዎችን


በመጠቀም ከጠኔ መላቀቅ ወደ ስራ መግባት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ በሥራ ባህል እና አዲስ
ፈጠራዎችን በማምጣት መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት መዘጋጀት ተገቢ ነው፡፡

በቀን ስምንት ሰዓት ብቻ በሥራ ላይ የማዋል ልማድን በመቀየር እጥፍ ለመሥራት ራስን ማሳመን
ይገባል፡፡ ለዕረፍትና ለመዝናናት የሚባክን ጊዜ እንዳይኖር የሚያደርግ የሥራ ባህል ለመፍጠር
የሚቻለው፣ ሰፊ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊፈጥር የሚችል በዕውቀት የሚደገፍ ጥናት ሲደረግ ነው፡፡
ንቅናቄው በተለመደው መፈክርና የአንድ ሰሞን ሁካታ ተጠልፎ እንዳይወድቅ፣

በሥራ ዓለም ያሉ ዜጎች በሙሉ የባህሪ ለውጥ የሚያደርጉባቸው መድረኮች ሊኖሩ ይገባል፡፡ ለጦርነት
በአንድ መንፈስ እንደሚሰማራ ሠራዊት ለአንድ የጋራ ዓላማ መሠለፍ የግድ መሆን አለበት፡፡

የኢትዮጵያ ወጣት ልጆቿንና የተፈጥሮ በረከቶችን ይዛ በረሃብ መቆራመድ የለባትም፡፡ ምዕራባውያን


በማዕቀብ ሊያሽመደምዷት ሲያሴሩ፣ ልጆቿ ሸብረክ እንዳይሉ ከፍተኛ የሆነ ብሔራዊ መነቃቃት
መፈጠር አለበት፡፡ ይህ ብሔራዊ መነቃቃት በአግባቡ ከተመራ ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና ወደ
መልካም አጋጣሚ መለወጥ አያቅታትም!

You might also like