Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 83

የኪነ ጥበባት አደረጃጀት፣ ድጋፍ አሰጣጥና

ክትትል መመሪያ ቁጥር 3/2008 ዓ.ም.


መግቢያ

የክልሉን የኪነ ጥበብ ኢንዱስትሪ በየደረጃው ወጥና ሕጋዊ በሆነ አደረጃጀት


የሚመራ እንዲሆን ማድረግና ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጣሪነቱ ደረጃ በደረጃ
እየጎለበተና እየተስፋፋ የሚሄድበትን አቅጣጫ ማስያዝ በማስፈለጉ፣

የኪነ ጥበብ ዝንባሌና ተሰጥኦ ያላቸውን ተተኪ ከያኒያን በማፍራት በክልሉ የኪነ
ጥበብ ሙያና ሙያተኛነት እንዲስፋፋ ለማድረግ የሚያስችል ዘላቂነትና አግባብነት
ያለውን የክትትልና ድጋፍ ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፣

የክልሉ ከያኒያን ድምፅ በተለያዩ መድረኮች ላይ በአጥጋቢ ሁኔታ መቅረብና


መሰማት የሚችልበትን ሁኔታ ማመቻቸትና ከያኒያኑ በተሰማሩበት የኪነ ጥበብ
ዘርፍ ለራሳቸው፣ ለክልላቸውና ለሃገራቸው እድገት ሊያስገኙ የሚችሉ ኪነ
ጥበባዊ ፈጠራዎችን መፍጠር የሚያስል ሁኔታ ማመቻቸትና የበለጠ ማጎልበት
በማስፈለጉ፣

ለክልሉ የኪነ ጥበብ እንቅስቃሴ መጎልበትና መስፋፋት በየደረጃው ድጋፍና


ክትትል የሚያደርጉ አስፈፃሚ አካላትን ኃላፊነት መለየትና ማመልከት
በማስፈለጉ፣

በክልሉ በየደረጃው የሚገኝ የኪነ ጥበብ እንቅስቃሴ መረጃን በአግባቡ ለመያዝ፣


ለማደራጀትና ለግብአት ለማዋል የሚያስችል ምቹ ሁኔታን መፍጠር አስፈላጊ
ሆኖ በመገኘቱ፣

1
የቢሮውን በሥራ ላይ ያለውን የአማተር ኪነ ጥበባት ክበባትና ማህበራት
አደረጃጀት መመሪያ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

የአማራ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ በክልሉ መንግሥት ምክር ቤት የአስፈፃሚ


አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር --------/-----
-- ዓ.ም. በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

ክፍል አንድ

ጠቅላላ

1. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ የኪነ ጥበባት አደረጃጀት፣ ድጋፍ አሰጣጥና ክትትል መመሪያ


ቁጥር --/2008 ዓ.ም ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2. ትርጓሜ

በዚህ መመሪያ ውስጥ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ


በስተቀር ፡-

1. “ቢሮ” ማለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ


ነው፡፡
2. “አስፈፃሚ መሥሪያ ቤት” ማለት በየደረጃው የሚገኙ የባህልና ቱሪዝም
ቢሮ አስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች ወይም በክልሉ አሥር ዞኖችና ሶስት ከተማ

2
አስተዳደሮች የሚገኝ የባህልና ቱሪዝም መምሪያና በወረዳ የሚገኝ የባህልና
ቱሪዝም ጽ/ቤት ማለት ነው፡፡
3. “የኪነ ጥበብ ክበብ ” ማለት በአስፈፃሚው መ/ቤት የሚደራጁና ክትትል
ድጋፍ የሚደረግላቸው፣ ወጣት ተተኪ ከያኒያን የኪነ ጥበብ ተሰጥኦ፣
ፍላጎትና ዝንባሌያቸውን የሚፈትሹባቸው፣ መሠረታዊ ዕውቀት
እንዲጨብጡና በቀጣይ ሙያውን አጠናክረው እንዲቀጥሉበት የማስቻል
ተልኮ ያላቸው የክልሉ መሠረታዊ የኪነ ጥበብ አደረጃጀት ናቸው፡፡
4. “የባህል ሙዚቃ ቡድኖች” ማለት በክልሉ ውስጥ በወረዳ፣ በዞንና በከተማ
አስተዳደር ደረጃ በአስፈፃሚው መ/ቤትና በአካባቢው የመንግሥት
አስተዳደር አካላት የሚደራጁና ክትትል ድጋፍ የሚደረግላቸው፤
የአካባቢውን ሕብረተሰብ ትውፊታዊ የሙዚቃና ቴአትር እሴቶች
የሚያስተዋውቁ፣ የሚያስፋፉና እንዲጠበቅ የሚያደርጉ፤ በኪነ ጥበብ
ለአካባቢው ልማት አስተዋፆ የማበርከት ተልዕኮ የተሰጣቸው አደረጃጀት
ናቸው፡፡
5. “የኪነ ጥበብ ኢንተርፕራይዝ” ማለት በተለያዩ የኪነ ጥበብ የሙያ ዘርፎች
ኪነ ጥበባዊ የፈጠራ ውጤቶችን በማምረት፣ በማከፋፈል፣ በመሸጥ፣
በማከራየት፣ በማስተዋወቅ፣ አገልግሎቱን በመስጠት ወይም በመሳሰሉት
ሥራዎች በየደረጃው ከሚገኝ የባህልና ቱሪዝም አስፈፃሚ መ/ቤት የሙያ
መስፈርት ብቃት ማረጋገጫ አግኝቶ በክልሉ በሚመለከተው አካል ሕጋዊ
የንግድ ፍቃድ በማውጣት በሥራው የተሠማራ ወይም የሚሠማራ የንግድ
ተቋም ማለት ነው፣
6. “የኪነ ጥበብ የሙያ ማህበር” ማለት በአንድ ዓይነት የኪነ ጥበብ ዘርፍ
ሙያ በተሰማሩ ባለሙያዎች በፈቃደኝነት ትርፍ ለማግኘትና ለመከፋፈል
ሳይሆን በሙያቸው የሚገባቸውን ሕጋዊ መብት ለመጠበቅ፣ ሙያቸውን
በጋራ ለማስፋፋትና ለማሳደግ ዓላማ በክልሉ ከሚመለከተው አካል ሕጋዊ
ፍቃድ በማግኘት የተደራጀና የሚመሠረት የሙያ ማህበር ነው፡፡
3
7. “የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት” ማለት በአስፈፃሚ
መሥሪያ ቤት አደራጅነት በዚህ መመሪያ መሠረት ለሚደራጁ የኪነ ጥበብ
ክበባት ወይም የባህል ቡድን በአሥፈፃሚ መሥሪያ ቤት የሚሰጥ የሕጋዊ
ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማለት ነው፡፡
8. “የሙያ መስፈርት ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት” ማለት በባህል
ኢንዱስትሪ የሙያ ዘርፎች ገቢ ማስገኛ የንግድ ስራዎች ለመሰማራት
ለሚጠይቅ ሰው ወይም ድርጅት የንግድ ፍቃዱን ለማውጣት
የሚያስችለው፣ ፍቃዱን ከማግኘቱ አስቀድሞ የግዴታ በመስኩ ለመስራት
የሚያስችለውን ባህላዊ መስፈርቶች ማሟላቱ ተረጋግጦ በየደረጃው
በአስፈፃሚው መ/ቤት የሚሰጥ የሙያ ብቃት ማረጋጫ የምስክር ወረቀት
ነው፡፡
9. “ የበጀት ዓመት” ማለት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከሐምሌ 1 እስከ ሰኔ 3ዐ
ወይም በግሪጎሪያን አቆጣጠር ከጀንዋሪ 1 እስከ ዲሴምበር 31 ያለው ጊዜ
ነው፡፡

3. የተፈፃሚነት ወሰን

ይህ መመሪያ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ክልል ውስጥ በተደራጁና


በሚደራጁ ማናቸውም የኪነ ጥበባት ዘርፍ ክበባት፣ የባህል ቡድኖች፣ የኪነ
ጥበብ ሙያ ዘርፎች አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች እና የኪነ ጥበባት
ሙያ ማሕበራት ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡

4
ክፍል ሁለት

የኪነ ጥበባት ክበባት ዓላማ፣ አደረጃጀት፣ ድጋፍ አሰጣጥና


ክትትል

4. ዓላማ

የኪነ ጥበብ ክበባት ዓላማ የሚከተሉት ናቸው ፡-

1. አባላት ያላቸውን የኪነ ጥበብ ተሰጥኦ፣ ፍላጎትና ዝንባሌ የሚፈትሹበትንና


የሚያጠናከሩበትን መድረክ መፍጠር፣ ማመቻቸት፣
2. አባላት ፍቅርና ዝንባሌ ያሳደረባቸውን የኪነ ጥበብ ዘርፍ መሠረታዊ
ዕውቀት እንዲጨብጡና በቀጣይ ሙያውን አጠናክረው እንዲቀጥሉበት
ማስቻል፣
3. አባላት ያካበቱትን ዕውቀትና ልምድ አስመልክቶ መረጃዎችን
የሚለዋወጡበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
4. አባላት በመረጡትና ዝንባሌ ባሳደሩበት የኪነ ጥበብ ዘርፍ በትርፍ ላይ
የልተመሠረተ እንቅስቃሴዎች ውስጥ እንዲሳተፉ ማድረግ ፣

5
5. አባላት ትርፍ ጊዜያቸውን በአልባሌ ቦታ እንዳያሳልፉ፣ በኪነ ጥበብ
እየተዝናኑ ለወደፊት ሕይወታቸው ጠቃሚ እውቀት በመገብየት
የሚያሳልፉበትን አማራጭ መፍጠር፣
6. ለአስፈፃሚው መ/ቤት ተተኪ ከያኒያንን ለማፍራት የሚያስችል የክትትል፣
የድጋፍ አሠጣጥ፣ የመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ምቹ ሁኔታን መፍጠር፣

5 የኪነ ጥበብ ክበብ ዓይነቶች

1. የኪነ ጥበብ ክበብ በአንድ ዓይነት የኪነ ጥበብ ዘርፍ ወይም ከአንድ በላይ

በሆኑ ተዛማጅ የኪነ ጥበብ ዘርፎች ጥምረት መደራጀት ይችላሉ፣


2. በአንድ ዓይነት የኪነ ጥበብ ዘርፍ የሚደራጁ የክበብ ዓይነቶች የሚከተሉት

ናቸው ፡-

ሀ. የሙዚቃ ክበብ

ለ. የቴአትር ክበብ

ሐ. የስነ ጽሁፍ ክበብ

መ. የሥዕልና ቅርፃ ቅርፅ ክበብ

3. ተዛማጅ በሆኑ የኪነ ጥበብ ዘርፎች ጥምረት የሚደራጁት የክበብ ዓይነቶች

የሚከተሉት ናቸው፡-

ሀ/ የሥነ ጽሁፍና የቴአትር ክበብ

ለ/ የሙዚቃና የቴአትር ክበብ

ሐ/ የሥነ ጽሁፍና የሥዕል ክበብ

6
4. ከላይ በንዑሥ አንቀፅ 2 እና 3 ላይ ከተዘረዘሩት ውጪ የሆነ የክበብ

ዓይነት ለማደራጀት ካስፈለገ ሐሳቡ ለቢሮው መቅረብ አለበት፣


አስፈላጊነቱና አግባብነቱ ታይቶ ቢሮው በሚሰጥ ውሳኔ ተፈፃሚ ይሆናል፣

6. የኪነ ጥበብ ክበባት አደረጃጀት

1. የኪነ ጥበብ ክበባት በከተማ አስተዳደሮች በክፍለ ከተማና በቀበሌዎች፣

በወረዳ ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች ደረጃ ይደራጃሉ፣


2. ማንኛውንም ዓይነት የኪነ ጥበብ ክበብ የሚያደራጀው በደረጃው የሚገኘው

አስፈፃሚ መ/ቤት ብቻ ነው፣


3. አስፈፃሚው መ/ቤት ማንኛውንም ዓይነት የኪነ ጥበብ ክበብ ሲያደራጅ
ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የአደረጃጀት ሒደት ድንጋጌዎች በቅደም ተከተላቸው
አግባብ የማከናወንና የማደራጀት ግዴታና ኃላፊነት አለበት ፡-

ሀ/ በአካባቢው ት/ቤቶች፣ ተቋማት፣ ቀበሌዎች ወዘተ…. የዘርፉ


ባለሙያን በማሰማራት ዝንባሌና ፍላጎት ስላላቸው የሕብረተሰብ
ክፍሎች መረጃ ማሰባሰብና ጥናት ማካሄድ፣

ለ/ በዘርፉ ዝንባሌና ፍላጎት ያላቸውን ለማሠልተን የስልጠና መስጫ


TOR የስልጠናውን ይዘትና ሂደት ፣ አመቺ በሆነ ሁኔታ
የሚሰጥበትን ጊዜ፣ ቦታና ግብአት ባካተተ አግባብ ማዘጋጀት፤

ሐ/ በሥልጠናው በዘርፉ የተፈጥሮ ዝንባሌና ፍላጎት ያላቸው ሁሉ


እንዲሳፉ በማስታወቂያና በተለያየ መንገድ ጥሪ ማድረግ፣
መመዝገብና ቁጥራቸው ከ20 ላልበለጡት ሥልጠና መስጠት፣
የሥልጠና ተመዝጋቢዎቹ ቁጥር ከ30 በላይ ከሆነ ቀሪዎቹ
በቀጣይ ዙር እንዲሰለጥኑ ማመቻቸት፣

7
መ/ በሥልጠናው ማጠናቀቂያ ሠልጣኞች አጫጭር የተሰጥኦ
መፈተሻ ሥራዎችን በተናጥል ወይም በቡድን ሠርተው
እንዲያሳዩ በማድረግ መገምገምና ከፍተኛ ተሰጥኦ
የሚታይባቸውን በክበብ ለማደራጀት መመልመል ውጤታማ
የማይሆኑትን መክሮ ማሰናበት፣

ሠ/ የተመለመሉት ሰልጣኞችን በክበብ ስለመደራጀት ጠቀሜታና


አስፈላጊነት ግንዛቤ እንዲጨብጡ የሚያስችሉ መድረኮችን
ማካሄድና የክበብ መመሥረቻ ስብሰባ እንዲየካሂዱ ማስተባበርና
ማመቻቸት፣

ረ/ በክበብ መመሥረቻ ጉባኤው በዚህ መመሪያ አባሪ በሆኑት የክበብ


መተዳደሪያ ደንብና የአባላት የሥነ ምግባር መመሪያ ላይ
እንዲወያዩና ግንዛቤ ጨብጠው በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት
የክበቡን የሥራ አስፈፃሚ አባላት ምርጫና በዚህ መመሪያ አንቀፅ
7 መሠረት የክበቡን መጠሪያ ስያሜ እንዲሰይሙ ማድረግ፣

ረ/ በሁለት ቅጂ በተዘጋጀ የክበቡ መተዳደሪያ ደንብ፣ የአባላት የሥነ


ምግባር መመሪያና የክበብ መመሥረቻ ቃለ ጉባኤ ላይ ሁሉም
መሥራች አባላት እንዲፈርሙበትና የአስፈፃሚው መ/ቤት
ማህተም እንዲርፍበት በማድረግ ክበቡን ማደራጀት፣

4. በክበብ የሚታቀፉት አባላት እድሜ ከ15 ዓመት በላይ መሆን አለባቸው፣

የግዴታ በእኩል ቁጥርም ባይሆን ፆታዊ ስብጥር የሚገኝባቸው እንዲሆኑ


አስፈፃሚው መ/ቤት ጥረት ያደርጋል፤
5. በክበብ የሚታቀፉት አባላት ብዛት በሙዚቃ ከ10 ያላነሰ ከ30 ያልበለጠ ፣

በቴአትር ከ8 ያላነሰ ከ15 ያልበለጠ፣ በሥነ ጽሁፍ ከ10 ያላነሰ ከ20


ያልበለጠ፣ በሥዕልና ቅርፃ ቅርፅ ከ5 ያላነሰና ከ12 ያልበለጠ እንዲሁም

8
ተዛማጅ በሆኑ የኪነ ጥበባት ጥምረት የሚደራጁት እስከ አሁን
ለእያንዳንዱ የተጠቀሰውን በማጣመር ያልበለጠ መሆን አለበት፤
6. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 3፣ 4 እና 5 ሥር የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ

ክበባትን በት/ቤቶች፣ መንግሥታዊና መንግስታዊ ባልሆነ ተቋሞች ሥር


የተቋማቱን ፍላጎት፣ ይሁንታና የመከታተልና የመደገፍ ፍቃደኛነትን
በአረጋገጠ አግባብ በአስፈፃሚው መ/ቤት እንዲደራጁ ማድረግ ይቻላል፣
7. የማንኛውም ክበብ ተጠሪነት ለአስፈፃሚው መ/ቤት ነው፤ ነገር ግን ከላይ

በንዑስ አንቀፅ 6 በተጠቀሰው አግባብ በተቋማት ሥር የተደራጁ ክበባት


የቅርብ ተጠሪነታቸው ለተቋማቱ ሆኖ አስፈፃሚው መ/ቤት የበላይ
ተጠሪያቸው ይሆናል፣ ይሄንኑ ተቋማቱ እንዲውቁት ያደርጋል፣
8. በሁሉም የክበብ ዓይነቶች የሚደራጁ የክበብ አባላት በሚደራጁበት የኪነ

ጥበብ ዘርፍ ወደ ሥራ ለመግባት የሚያስችላቸው የመሥሪያ ቁሳቁስ


ቢያንስ በውስን ደረጃም ቢሆን እንዲኖራቸው በአስፈፃሚው መ/ቤትና
በአባላቱ የተለያዩ ጥረቶች መደረግ አለባቸው ፣
9. ይህ መመሪያ በሥራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ማንኛውም የኪነ ጥበብ

ክበብ ተደራጅቶ መንቀሳቀስ የሚችለው በመመሪያው መሠረት ብቻ ነው፣


ከመመሪያው ውጪ የሚደራጅ በአስፈፃሚው መ/ቤት እንዲፈርስና ቀጣይ
እርምጃዎችም እንዲወሰዱበት ይደረጋል፣

7. የክበብ መጠሪያ ስያሜና አጠቃቀም


1. የክበብ መጠሪያ ስያሜ በአባላት የጋራ ስምምነት የሚሰየም ሆኖ አሰያየሙ

ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ሁኔታዎች በአንዱ ላይ ተመሥርቶ መሆን ይኖርበታል


፡-

9
ሀ/ በአካባቢው በሚገኝ ታዋቂ ተፈጥሯዊ የመልክአ ምድር መስህብ
ገፅታን ማለትም ተራራ፣ ኮረብታ፣ ጅረት ሐይቅ ፏፏቴ ወዘተ..
የመሳሰለውን ስያሜ በመጠቀም፣

ለ/ በሐገራችን ወይም በክልላችን ወይም በአካባቢው የሚገኙ ብርቅዬ


የዱር አራዊቶችንና የእፅዋቶች መጠሪያን በመጠቀም፣

ሐ/ በሐገራችን ወይም በክልላችን ወይም በአካባቢው የተከሰተ


ታሪካዊ ክስተት ወይም ሁነት መጠሪያን በመጠቀም፣

መ/ በአካባቢው የሚገኝ ልዩ የሆነ የታሪካዊ ቅርስ ወይም ብርቅዬ


የቱሪዝም መስህብ ፀጋ መጠሪያን በመጠቀም፣

ሠ/ በሐገራችን ወይም በክልላችን ወይም በአካባቢው ለኪነ ጥበቡ


ዘርፍ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፆ ባበረከቱ ወንድ ወይም ሴት፣
በሕይወት ያሉ ወይም የሌሉ አንጋፋ አርቲስቶች ስምን
በመታሰቢያነት በመጠቀም ፣

ረ/ የሐገራችንን የታዋቂ ነገሥታትን፣ አርበኛና ጀግኖችናና ሌሎች


ለወገንና ለሐገር ጠቃሚ ታሪካዊ ገድል የፈፀሙ ሰዎችን ስም
በመጠቀም፣

ሰ/ በአካባቢው የሚገኝ ቀደምት ትምህርት ቤት ወይም ሌላ ተቋም


መጠሪያን በመጠቀም፣

2. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 1 ከተገለፀው አግባብ ውጪ ለክበባት ስያሜ


መስጠትና በተለይም ክበባትን በባእዳን ቋንቋ ወይም በውጭ ሐገራት ቋንቋ
መሰየም ፈፅሞ የተከለከለ ነው፣
3. ለአንድ ክበብ የተሰጠን ስያሜ መጠቀም የሚቻለው ስያሜውን ከፊት
አድርጎ የክበቡን ዓይነት በማስከተል ብቻ ነው፣ ለምሳሌ ራስ ዳሸን የቴአትር
ክበብ፣

10
4. ለክበብ የተሰጠ ስያሜን ብቻ ነጥሎ በመጥራት ወይም ክበብ የሚለውን

ቃል ቡድን፣ ግሩፕ፣ ክለብ፣ ማህበር፣ ድርጅት ወዘተ … በሚሉ ቃላቶች


ለውጦ መጥራት ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡

8. ምዝገባና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ፣

1. አስፈፃሚው መ/ቤት በዚህ መመሪያ መሠረት የተደራጀን ማንኛውም


ዓይነት የኪነ ጥበብ ክበብ የመመሪያውን መሥፈርቶች ሙሉ በሙሉ
ማሟላቱን አረጋግጦ ክበባትን ይመዘግባል፤ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ
የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣
2. አስፈፃሚው መ/ቤት የክበብ ምዝገባውን የሚያከናውነው በዚህ መመሪያ

በአባሪ በተያያዘው የክበባት የምዝገባ ቅፅ የሚጠይቀውን መረጃ ዝርዝር


አባላት በጥንቃቄ እንዲሞሉና እንዲፈርሙ በማድረግ ነው፣
3. አስፈፃሚው መ/ቤት ከላይ በንዑስ አንቀፅ 2 መሠረት ምዝገባውን አከናውኖ

የክበቡን የምዝገባ የግል ፋይል ይከፍታል፣ በፋይሉም የሚከተሉት


ሠነዶች እንዲካትቱ ያደርጋል ፡-

ሀ/ በምስረታው ወቅት አባላት የፈረሙበት የክበብ መተዳደሪያ


ደንብ፣ የሥነ ምግባር መመሪያና የመመሥረቻ ቃለ ጉባኤን አንድ
ቅጂ፣

ለ/ የክበባት ምዝገባ ቅፅና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር


ወረቀት ቀሪ ቅጂን ፣

ሐ/ በቀጣይ ክበቡን የሚመለከቱ ማናቸውንም የፅሁፍ ሪከርዶች፣

4. በአስፈፃሚው መ/ቤት የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት


የተሰጠው ክበብ የራሱ አርማና ማሕተም፣ የባንክ አካውንት ሊኖረው

11
ይችላል፣ ነገር ግን አርማና ማሕተሙ ከክበቡ ስያሜና ዓይነት ጋር
የተጣጣመ መሆን አለበት፣ የተጠቀሱትን እንዲያወጣ አስፈፃሚው መ/ቤት
የድጋፍ ደብዳቤ ይሰጣል፣
5. የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለሶስተኛ ወገኖች ተላልፎ

አይሰጥም ወይም አይተላለፍም፣


6. የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በሰጠው አስፈፃሚ መ/ቤት

በየዓመቱ መታደስ አለበት፣ የሚታደሰው ዓመቱ ከሞላ በኋላ ባሉት አሥር


ቀናቶች ውስጥ ብቻ ነው፡፡

9. በኪነ ጥበብ ክበባት የሚከናወኑ ተግባራት

የኪነ ጥበባት ክበባት ዓላማቸውን ለማሳካት የሚከተሉትን ተግባራት


ያከናውናሉ፡-

1. በሙዚቃ ክበብ

ሀ/ በአባላት በተናጥልና በቡድን የዜማ ግጥምና የዜማ ድርሰት


መፍጠር፣

ለ/ የግጥምና የዜማ ድርሰቶችን በሙዚቃ መሣሪያ ማቀነባበር፣


ከውዝዋዜ ስልት ጋር ማዋሀድ መለማመድና ማዘጋጀት፣
ሐ/ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ዙሪያ ሕብረ ዝማሬዎችን፣ የሙዚቃ
ትርኢቶችንና አጫጭር ሙዚቃዊ ጭውውት ድራማዎች
ማዘጋጀት ፣
መ/ የሰውነት ማፍታቻ እንቅሰቃሴዎችንና መሰረታዊ የውዝዋዜ
ሰልቶችን፣ የድምጽ አወጣጥና አዘፋፈን እና የዜማ ቅኝቶችና

12
መሣርያ አጨዋወት ስልቶችን ልምምድ በቋሚ ፕሮግራም
ማካሄድ፣
ሠ/ የአካባቢውን ሕብረተሰብ ትውፊታዊ የሙዚቃ ባህልንና
አጨዋወትን፣ የውዝዋዜና ዳንኪራ ስልቶችን ትክክለኛ
መረጃዎችን ከምንጫቸው በማሰባሰብ በግብአት መጠቀም፣
ረ/ በአስፈፃሚው በመ/ቤት ባለሙያ ብቃታቸው የተረጋገጠ የሙዚቃ
ዝግቶችን፣ ሕብረ ዝማሬዎችንና አጫጭር ሙዚቃዊ ድራማዎች
በተለያዩ ህዝባዊና መንግሥታዊ በዓላት ቋሚ ፕሮግራም
በመዘርጋት ለተመልካች ማቅረብ፣

ሰ/ የክበቡ አባላት ክህሎታቸውን ለማሻሻል የሚረዱዋቸውን የተለያዩ


የሙዚቃ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ የተለያዩ ስልቶችን በመቀየስ
ተግባራዊ ማድረግ፣

ሸ/ በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ የባህል ቡድኖችና ታዋቂ የሙዚቃ


ሰዎችን በመጋበዝ አባላት የተሞክሮ ልውውጥና ልምድ
እንዲቀስሙ ማድረግ፣

ቀ/ በቋሚ ፕሮግራም ቀደም ሲል በተሠሩና በወቅታዊ የሙዚቃ


ስራዎች ዙሪያ እና በክበቡ እንቅስቃሴ አባላት የነቃ ተሳትፎ
የሚያደርጉባቸውን የውይይትና የሒስ መድረኮችን ማዘጋጀትና
ማካሄድ፣

2. በቴአትር ጥበብ ክበብ

13
ሀ/ በአባላት በተናጥልና በቡድን አጫጭር የመድረክ፣ የቴሌቪዥንና
የሬድዮ ተውኔቶችን፣ የማይም ድራማና የኮሜዲ ዝግጅቶችን
መፍጠር በአስፈፃሚው መ/ቤት ባለሙያ ማስገምገም በሚሰጥ
አስተያየት ማሻሻልና በማዘጋጀት ለተመልካች ማቅረብ፣
ለ/ በልማታዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ፣ በማህበራዊ ጠንቆችና በጎጂ
ልማዳዊ ድርጊቶች ዙሪያ ሕብረተሰቡን እያዝናኑ በማስተማር
መልዕት የሚያስተላልፉ አጫጭር ጭውውት ድራማዎችን፣
ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ
ተቋማት የፋይናንስ ድጋፍ በማፈላለግ አዘጋጅቶ ማሳየት፣
ሐ/ የተዘጋጁና ብቃታቸው የተረጋገጠ የቴአትር ዝግጅቶችን በተለያዩ
ህዝባዊና መንግሥታዊ በዓላት፣ በቋሚ ፕሮግራም፣ በአዳራሽ፣
በአደባባዮች፣ በገበያ ላይ ወዘተ… ለተመልካች ማቅረብ ፣
መ/ የትወና ብቃትና ክህሎትን የሚያሳድጉ የሰውነት ማፍታቻ
እስፖርታዊ እንቅሰቃሴዎችንና የድምጽ አወጣጥ ልምምዶችን፣
አጫጭር የመነባንብና የድንገቴ ፈጠራ ሥራዎችን በቋሚ
ፕሮግራም ልምምድ ማድረግ፣
ሠ/ የአካባቢውን ሕብረተሰብ ትውፊታዊ ድራማ ክዋኔዎችን
በሚቀርቡቧቸው ማሕበረሰባዊ የክዋኔ መድረኮች ላይ በመገኘት
ማጥናት፣ ትክክለኛ መረጃቸውን ከምንጩ በማሰባሰብ ለዝግጅት
በግብአት መጠቀም፣
ረ/ ብቃታቸው የተረጋገጠ የክበቡን አጫጭር ጭውውትና የቪዲዮ
ድራማ ሥራዎችን በማሳተም ለሕዝብ ማቅረብ፣
ሰ/ አባላት ክህሎታቸውን ለማሻሻል የሚረዱዋቸውን የቴአትር
አፃፃፍ፣ የትወናና የቴአትር አዘገጃጀት ስልጠናዎችን እንዲያገኙ
የተለያዩ ስልቶችን በመቀየስ ተግባራዊ ማድረግ፣

14
ሸ/ በአካባቢው ጠንካራ እንቅስቃሴ ያላቸውን የቴአትር ቡድኖችን፣
ታዋቂና ዝናን ያተረፉ ፀሐፌ ተውኔቶችን፣ ተዋናዮችንና የቴአትር
ጥበብ ምሁራንን በመጋበዝ ልምዳቸውን እንዲያካፍሉና አባላት
የተሞክሮ ልውውጥና ልምድ እንዲቀስሙ ማድረግ፣

ቀ/ በተውኔት አፃፃፍ፣ በትወናና በቴአትር አዘገጃጀት በተዘጋጁ


ማኑዋሎችና የትምህርት መርጃ መጽሐፎች እና በክበቡ
እንቅስቃሴ ዙሪያ አባላት የነቃ ተሳትፎ የሚያደርጉባቸውን
የውይይትና የሒስ መድረኮችን በቋሚ ፕሮግራም ማዘጋጀትና
ማካሄድ፣

3. በሥነ ጽሁፍ ክበብ

ሀ/ ግጥሞችን፣ ወጐች፣ መነባንቦችን፣ መጣጥፎች፣ ግለታሪኮችን ፣


አጫጭር ልብ ወለዶችን፣ ተውኔቶችንና ሌሎች የሥነ ጽሁፍ
የፈጠራ ድርሰቶችን በአባላት በተናጥል ወይም በቡድን መፍጠር
፣ በባለሙያ አስገምግሞ በሚሰጥ አስተያየት ማስተካከል፣
ማሻሻልና ማቅረብ፣
ለ/ የአካባቢውን የሕዝብ ትውፊታ የሥነ ቃል ሀብቶች ማለትም
የስራ፣ የሰርግና የበዓል ዘፈን፣ የለቅሶ፣ የጀግንነት፣ የልመና ፣
የልጆች ጫወታ ፣ የአምልኮ ፣ የስድብና ሙገሳ ፣ የፍቅር ፣
የተቃዉሞ ፣ የእሹሩሩ ወዘተ … ግጥሞችን ፤ ተረቶች፤
አፈታሪክ፤ እንቆቅልሽ፣ ምሳሌያዊ ንግግሮች ፣ እንካስላንትያዎች
፣ ተግባራዊ ቀልዶች ፣ እሰጥ አገባዎች ፣ መሀላዎች ፣
እርግማኖች ፣ ግዝቶች፣ ምርቃቶች ወዘተ… መሰብሰብ፣

15
ሐ/ የአባላት የፈጠራ ድርሰቶች፣ ከታዋቂ ደራሲያን የተመረጡ
ሥራዎች፣ ሥነ ቃሎችና ሌሎች አዝናኝ የሥነ ጽሁፍ ዝግጅቶች
የሚቀርቡባቸውን የሥነ ጽሁፍ ምሽቶችን በወርሐዊነት ወይም
በተለያየ ቋሚ ፕሮግራም በመዘርጋት ማካሄድ፣
መ/ የሥነ ጽሁፍ ምሽቶች ሳቢና ማራኪ፣ ቁጥሩ እየጨመረ የሚሄድ
ቋሚ ታዳሚ ያላቸው እንዲሆኑ፣ የድራማ፣ የሙዚቃ፣ የቅኔ
ዘረፋ ወዘተ… አድማቂ ሥራዎችን ማካተት፣ ለዚህም ከተለያዩ
ክበባት፣ ከቅኔ ት/ቤቶች ወዘተ.. ጋር በቅንጅት መሥራትና
ስፖንሰሮችን በማፈላለግ ማሳተፍ፣
ሠ/ በተለያዩ መንግስታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት
በማስታወቂያና በሚዲያ በሚወጡ የሥነ ጽሁፍ ውድድሮች ላይ
መሳተፍ፣
ረ/ በተለያዩ መንግስታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት በሚዘጋጁ
መድረኮች በመገኘት ለመድረኩ ተሳታፊዎችን እያዝናኑ ጠቃሚ
መልእክቶችን የሚያስተላልፉ ሥነ ጽሁፋዊ የፈጠራና የሥነ ቃል
ሥራዎችን ማቅረብ፣
ሰ/ ብቃታቸው በአስፈፃሚው መ/ቤት የተረጋገጠ፣ የተለያዩ የሥነ
ጽሁፍ ፈጠራ ሥራዎችን፣ የተሰበሰቡ ሥነ ቃሎችን በአባላት
በተናጥል ወይም በቡድን ወይም እንደ ክበብ በማደራጀት፣ ጉዳዩ
ከሚመለከታቸውን ስፖንሰሮችን በማፈላለግ ማሳተምና
ለአንባቢያን ማቅረብ፣
ሸ/ አባላት ክህሎታቸውን ለማሻሻል የሚረዱዋቸውን የሥነ ጽሁፍ
ኪነ ጥበባት ስልጠናዎችን እንዲያገኙ የተለያዩ ስልቶችን በመቀየስ
ተግባራዊ ማድረግ፣
ቀ/ ጠንካራ እንቅስቃሴ ያላቸውን አቻ ክበባትን፣ ታዋቂና ዝናን
ያተረፉ የሥነ ጽሁፍ ሰዎችን፣ የኪነ ጥበብ ምሁራንን በመጋበዝ
16
ልምዳቸውን እንዲያካፍሉና አባላት የተሞክሮ ልውውጥና ልምድ
እንዲቀስሙ ማድረግ፣

በ/ በቋሚ ፕሮግራም በታዋቂ ደራሲያን ሥራዎች፣ በፈጠራ ሥነ


ጽሁፍ አፃፃፍ በተዘጋጁ የትምህርት መርጃ መጽሐፎች ፊልሞች፣
የተቀረፁ ድምፆች እና በክበቡ እንቅስቃሴ ዙሪያ አባላት የነቃ
ተሳትፎ የሚያደርጉባቸውን የውይይትና የሒስ መድረኮችን
ማዘጋጀትና ማካሄድ፣

4. በሥዕልና ቅርፃ ቅርፅ ክበብ

ሀ/ በአካባቢው የሚገኙ ቁሳቁሶችን በመጠቀም በአባላት በተናጥል


ወይም በቡድን በልዩ ልዩ ርዕሠ ጉዳዮች ሥዕሎችንና ቅርፃ
ቅርፆችን መሥራት፣
ለ/ የአባላት የፈጠራ ውጤት የሆኑ የሥዕልና ቅርፃቅርፅ ዝግጅቶች
የሚቀርቡባቸውን የሥዕልና ቅርፃ ቅርጽ ኤግዚቢሽኖችን፣ በተለያየ
ዝግጅት መድረኮች ላይ እና በቋሚ ፕሮግራም በመዘርጋት
ማካሄድ፣ የተመልካቾችን አስተያየት መሰብሰብ፣
ሐ/ የሚዘጋጁ የሥዕልና ቅርፃ ቅርጽ ኤግዚቢሽኖች በርካታ
ተመልካችና ጎብኚዎች ያላቸው እንዲሆኑ የተለያዩ ዘዴዎችን
መቀየስ፣ መተግበር፣ ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት መሥራትና
ስፖንሰሮችን በማፈላለግ ማሳተፍ፣
መ/ በተለያዩ መንግስታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት
በማስታወቂያና በሚዲያ በሚወጡ የሥዕልና ቅርፃ ቅርጽ
ውድድሮች መሳተፍ፣

17
ሠ/ በተለያዩ መንግስታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት
ተዘጋጅተው በሚካሄዱ መድረኮች በመገኘት ለመድረኩ
ተሳታፊዎች የአባላትን የሥዕልና ቅርፃ ቅርጽ የፈጠራ ሥራዎችን
ለተሳታፊዎች ማቅረብና አስተያየት መሰብሰብ፣
ረ/ በአባላት በተናጥልና በቡድን የተሠሩ የክበቡን ምርጥ የሥዕልና
ቅርፃ ቅርፅ የፈጠራ ውጤቶች ስፖንሰሮችን በማፈላለግ
በመጽሔት ማሳተምና ማቅረብ፣
ሰ/ አባላት ክህሎታቸውን ለማሻሻል የሚረዱዋቸውን የሥዕልና ቅርፃ
ቅርፅ ኪነ ጥበባት ስልጠናዎችን እንዲያገኙ የተለያዩ ስልቶችን
በመቀየስ ተግባራዊ ማድረግ፣
ሸ/ ጠንካራ እንቅስቃሴ ያላቸውን አቻ ክበባትን፣ ታዋቂና ዝናን
ያተረፉ ሠዓሊያንና ቀራፂያንን፣ የዘርፉ ምሁራንን በመጋበዝ
ልምዳቸውን እንዲያካፍሉና አባላት የተሞክሮ ልውውጥና ልምድ
እንዲቀስሙ ማድረግ፣

ቀ/ በታዋቂ ሰዓሊያንና ቀራፂያን ሥራዎች፣ የሥዕልና ቅርፃ ቅርፅ


ኪነ ጥበባት ዙሪያ በተዘጋጁ የትምህርት መርጃ መጽሐፎች
ፊልሞች፣ የተቀረፁ ድምፆች እና በክበቡ እንቅስቃሴ ዙሪያ አባላት
የነቃ ተሳትፎ የሚያደርጉባቸውን የርስ በርስ መማማሪያ
የውይይትና የሒስ መድረኮችን በቋሚ ፕሮግራም ማዘጋጀትና
ማካሄድ፣

5. ተዛማጅ በሆኑ የኪነ ጥበብ ዘርፎች ጥምረት በሚደራጁ ክበባት የሚከናወኑ

ተግባራትን በሚመለከት እንደሚከተለው ይሆናል ፡-

18
ሀ/ የሥነ ጽሁፍና የቴአትር ክበብ በዚህ አንቀጽ ንዑሥ አንቀፅ 2
ላይ ከተራ ቁጥር ሀ እስከ ቀ እና በንዑሥ አንቀጽ 3 ከተራ
ቁጥር ሀ እስከ በ የተጠቀሱትን በማጣመር፣

ለ/ የሙዚቃና የቴአትር ክበብ በዚህ አንቀጽ ንዑሥ አንቀፅ 1 ላይ


ከተራ ቁጥር ሀ እስከ ተ እና በንዑሥ አንቀጽ 2 ከተራ ቁጥር
ሀ እስከ ቀ የተጠቀሱትን በማጣመር፣

ሐ/ የሥነ ጽሁፍና የሥዕል ክበብ በዚህ አንቀጽ ንዑሥ አንቀፅ 3


ላይ ከተራ ቁጥር ሀ እስከ በ እና በንዑሥ አንቀጽ 4 ከተራ
ቁጥር ሀ እስከ በ የተጠቀሱትን በማጣመር፣ ያከናውናሉ፣

10. የኪነ ጥበብ ክበባት ኃላፊነትና ግዴታዎች

1. በዚህ መመሪያ የሠፈሩ ድንጋጌዎችን ፣ የክበቡን መተዳደሪያ ደንብና የስነ


ምግባር መመሪ እና በቀጣይ አስፈፃሚው መ/ቤት የሚያወጣቸውን ደንቦችና
መመሪያዎች፣ የሚያስተላልፋቸውን ውሳኔዎች ለአባላት ማሳወቅ፣ በጥብቅ
ዲሲፕሊን ማክበርና መተግበር፣
2. በክበቡ የሚሠሩ ማናቸውንም የኪነ ጥበብ ፈጠራ ድርሰቶችና ዝግጅቶችን
ለተመልካች ከማቅረቡ በፊት በአስፈፃሚው መ/ቤት ባለሙያ ብቃቱን
የማስገምገም፣ በሚሰጥ አስተያየት ደጋግሞ የማስተካከልና የማሻሻል፣
3. በአስፈፃሚው መ/ቤት ብቃቱ ተረጋግጦና ለለሕዝብ እንዲቀርብ በደብዳቤ
ፍቃድ ያልተሰጠውን ማንኛውንም ዓይነት የኪነ ጥበብ ዝግጅት
በማንኛውም ሁኔታ ያለማሳተምና ለተመልካች ወይም ለተደራሲ
ያለማቅረብ፣

19
4. በማንኛውም ጊዜ በአስፈፃሚው መ/ቤት ማናቸውም ዓይነት መረጃ ሲጠየቅ
የመስጠትና የማቅረብ፣ በሚሰጠው ቅጽ መሠረት መረጃ የመያዝና
ሲጠየቅም የማቅረብ እንዲሁም በማንኛውም ጊዜ ጥሪ ሲያደርግለት
የመቅብና የመሳተፍ፣
5. የአስፈፃሚውን መሥሪያ ቤት በክትትልና ግምገማው የደረሰባቸውን
በእንቅስቃሴው ላይ የሚታዩ ጉድለቶችን እንዲያስተካክል በቃል ወይም
በጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ወይም ማስተካከያ ሲደርሰው በተገለፀው የጊዜ ገደብ
ውስጥ ጉድለቱን የማስተካከል፣
6. ከክበባት ዓላማ ውጪ በሆኑ በገቢ ወይም በትርፍ ማግኛ ተግባራት ወይም
በዚህ መመሪያ አንቀፅ 9 ከተዘረዘሩትና እንዲከናውን ከተፈቀዱለት
ተግባራት ውጪ ከኢንተርፕራይዞች ጋር በጨረታ የመሳተፍና የመሳሰሉ
ተግባራትን አለመፈፀም፣
7. ብቃታቸው የተረጋገጡ ሥራዎችን ለሕዝብ እንዲያቀርብ በአስፈፃሚው
መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ካልተሰጠው በስተቀር ከተቋቋመበት አካባቢ ውጪ
ያለመንቀሳቀስ፣
8. የክበቡን ስያሜ ከለወጠ ለውጡን ወይም ማሻሻያውን ለአስፈፃሚው መ/ቤት
አቅርቦ የማስመዝገብና የማሳወቅ ፣
9. የክበቡን ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባዎች በክበቡ መተዳደሪያ ደንብ በተደነገገው
መሠረት ማካሄድና ስብሰባውን ከማካሄዱ ከሶስት የሥራ ቀናት አስቀድሞ
የስብሰባውን ጊዜና ቦታ ለአስፈፃሚው መቤት በጽሁፍ የማሳወቅ የመ/ቤቱ
ተወካይ በስብሰባው በታዛቢነት እንዲሳተፍ የማድረግ፣
10.የክልሉን ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህሎች፣ ቅርሶች፣ ቋንቋዎች፣
ታሪኮች እና ሕጎች የሚፃረር ድርጊት ያለመፈጸም፣ በሌሎች ሲፈፀምም
በወቅቱ ለአስፈፃሚው መ/ቤት ሪፖርት የማድረግ፣

20
11.በዕቅድ የመመምራት፣ አባላትን ባሳተፈ አግባብ ዓመታዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና
ማፅደቅ፣ የፀደቀውን የክበብ ዓመታዊ ዕቅድ ለአስፈፃሚው መ/ቤት አንድ
ቅጂ የማቅረብ፣
12.የክበቡን ዓመታዊ የሥራ ዕቅድ ክንውን አፈፃፀም ሪፖርትን፤ ታቅደው
የተከናወኑ ተግባራትን፣ በአባላት መዋጮ፣ በስጦታ፣ ከተሰጠ አገልግሎት፣
ወዘተ… የተገኘ ፋይናንስ ገቢና የወጪ አጠቃቀምን፤ ያጋጠሙ ችግሮችና
የተወሰዱ መፍትሔዎችን ባካተተ አግባብ በየ6 ወሩ በማዘጋጀት 6ኛው
ወር በገባ በ 15 ቀናት ውስጥ ለአስፈፃሚው መ/ቤት የማቅረብ፣
13.የአባላትን መረጃዎችን፣ በክበቡ ወይም በአባላት የተሠሩ ማናቸውም
አይነት ኪነ ጥበባዊ ሥራዎችንን፣ ዓመታዊ ዕቅድና ሪፖርት ፋይሎችን፣
የቋሚ ንብረቶች፣ የገቢና ወጪ ሰነዶችን እና ሌሎች ስለ ክበቡ እንቅስቃሴ
የተመለከቱ የጽሁፍ፣ የምስል፣ የድምፅ ወዘተ… መረጃዎችንና ሠነዶችን
በአግባቡ አደራጅቶ የመሠነድና የመያዝ፣
14.የባንክ አካውንት በመክፈት የክበቡን የፋይናንስ እንቅስቃሴ በመተዳደሪያ
ደንቡ በተደነገገው መሠረት የማንቀሳቀስ፣
15.የፋይናንስና የማቴሪያል ድጋፎችን ወይም ልገሳዎችን ስሙ ካልተገለፀ ሰው
ወይም ተቋም አለመቀበል ፣ በክበቡ የተገዙ ወይም በድጋፍ፣ በልገሳ ወይም
በሌላ ማናቸውም አግባብ የተገኙ ቋሚ ቁሳቁሶችን ወይም ንብረቶችን
ለአስፈፃሚው መ/ቤት በፅሁፍ ዘርዝሮ የማሳወቅ፣
16.ክበቡ ሲፈርስ ማናቸውንም ዓይነት የክበቡን ቋሚ ንብረቶችና የሠነድ
ማስረጃዎች ለአስፈፃሚው መሥሪያ ቤት የማስረከብ ኃላፊነትና ግዴታ
አለባቸው፡፡

11. የድጋፍ አሰጣጥና ክትትል

21
አስፈፃሚው መ/ቤት ለማንኛውም ክበብ የሚከተሉትን ድጋፍና ክትትል
ማድረግ አለበት ፡-

1. የኪነ ጥበብ ዝንባሌ ያላቸውን በዚህ መመሪያ መሠረት በክበብ


የማደራጀት፣
2. የክበብ አባላት በተናጥል፣ በቡድንና እንደ ክበብ ያሉባቸውን ሙያዊ
የአቅም ክፍተቶች ቀጣይነት ባለው አግባብ በመከታተል፣ መለየት ሙያዊ
አቅማቸውን የመገንባት፣
3. ኪነ ጥበባዊ የፈጠራ ድርሰቶቻቸውና ዝግጅቶቻቸው ለተደራሲ ወይም
ለሕዝብ በስፋት የሚቀርቡባቸውን መድረኮች የማመቻቸት፣
4. ውስጣዊ የአደረጃጀትና የአሠራር እንቅስቃሴያቸውን በየጊዜው በመፈተሽ
ማጠናከርና ማጎልበት፣ ጠንካራ የአሠራር ሥርዓት እንዲዘረጉ
መከታተልና መደገፍ፣
5. ከክበባትና ከሌሎች ባለ ድርሻና አጋር አካላት ጋር ሰላማዊና ጠንካራ የርስ
በርስ ግንኙነትን እንዲመሠርቱ፣ በመተባበር ዓላማ ላይ የተመሠረተ
ቅንጃታዊ አሠራርን እንዲፈጥሩና እንዲያጎለብቱ መደገፍና ሁኔታዎችን
ማመቻቸት፣
6. ለሥራ እንቅስቃሴ አስፈላጊ በሆኑ መሣሪያዎችና በፋይናንስ አቅማቸው
እየተጠናከረ እንዲሄድ ማድረግ፣ ድጋፍ መስጠትና ድጋፍ እንዲያገኙ
ማመቻቸት፣
7. ቋሚነት ባለው መንገድ የተለያዩ ኪነ ጥበባት ውድድሮችን፣
ፌስቲቫሎችን፣ ኤግዚቢሽንና አውደ ርዕዮችን ማዘጋጀትና ማካሄድ፣
እውቅናና ማበረታቻ የሚሰጥበትን ስርዓት መዘርጋት፣ሁሉንም ክበባት
በእኩልነት ማሳተፍ፣ ማበረታት፣
8. በክበብ ሲንቀሳቀሱ ቆይተው እድሚያቸው 26 የሞላቸውና በክብር
የሚሰናበቱ አባላት በቀጣይ በሙያው ኢንተርፕራይዝ በማቋቋም

22
እንዲንቀሳቀሱ ወይም ከፍተኛ ትምህርት እንዲቀጥሉ መደገፍ፣
ማበረታታት፣ አስፈላጊ ሁኔታዎችን የማመቻቸት፣
9. በዚህ አንቀፅ ከላይ ከንዑሥ አንቀፅ 1 እስከ 6 የተዘረዘሩት ድጋፎች፣
ያሉትን ክበባት በሙሉ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ በሚያስተናግድ፣ ቀጣይነት
ባለው ሁኔታ የተዘጋጀ ቋሚ ፕሮግራም ወጥቶለት፣ በቼክ ሊስት ተደገፈና
ግብረመልስ በመቀበል መሰጠት አለበት፣
10. ማንኛውም ክበብ ሕጋዊ ፍቃድ ማውጣቱን፣ ፍቃዱ በወቅቱ
መታደሱን፣ በተፈቀደለት የሙያ ዘርፍ እየተሠራ መሆን ፣ ዕድሜያቸው
26 የሞላቸው አባላቱን በክብር ማሰናበቱንና ሌሎች አግባብነት ያላቸው
ጉዳዮችን በሚመለከት በየጊዜው ክትትልና ቁጥጥር በማካሄድ ፍተሻ
ያደርጋል፣
11. በሕግ አግባብ ፍቃድ ሳያወጡና በዚህ መመሪያ
መሠረት የማይሰሩ አካላት በመቆጣጠርና ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ
ያደርጋል፣

12. የክበባት መዋሐድ

1. በተመሳሳይ የክበብ ዓይነት የሚንቀሳቀሱ ሁለት ክበባት መዋሐድ ይችላሉ፣


ነገር ግን ከሁለት በላይ ከሆኑ ወይም ሁለትም ቢሆኑ በተለያየ የተለያየ
የክበብ ዓይነት ከሆኑ መዋሐድ አይችሉም፣
2. ሁለት ተመሳሳይ የክበብ ዓይነቶች ለመዋሀድ ሲወስኑ የሚከተሉትን ቅድመ
ሁኔታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል ፡-

23
ሀ/ ውህደቱን የሚፈፅሙት ሁለት ክበባት ጠቅላላ ጉባዔ አባላት
የተገኙበት የውህደት ስምምነት መፈፀሚያ ጉባኤ ወይም የጋራ
ስብሰባ ማካሄድ፣

ለ/ በጋራ ስብሰባው ላይ የውህደቱን ዓላማ፣ ምክንያትና አስፈላጊነት፣


ጠቀሜታውንና የተዋሐደውን ክበብ መጠሪያ ስያሜ፣ የሀብትና
ንብረት ውህደቱን በሚዘረዝር ቃለ ጉባዔ ላይ ሁሉም የጉባዔው
አባላት በመፈራረም ማፅደቅ፣

ሐ/ የውህደት ስምምነቱን ያፀደቁበትን ቃለ ጉባኤ ሁለቱም ክበባት


ከተቋቋሙበት የቀድሞ መተዳደሪያ ደንብና የሕጋዊ ሰውነት
ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቶች ጋር በማያያዝ ለአስፈፃሚው
መ/ቤት ማቅረብ፣

3. አስፈፃሚው መ/ቤት በዚህ አንቀፅ ከላይ በንኡስ አንቀፅ 2 በተዘረዘረው


መሠረት ሲቀርብለት የተዋሃደው አዲስ ክበብ በዚህ መመሪያ መሠረት
አዲስ የመተዳደሪ ደንብ እንዲፈራረሙ በማድረግና በመመዝገብ ሕጋዊ
ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በመስጠት ውህደቱን ያፀድቃል፣
4. በውህደት የሚመሠረተው ክበብ በአዲስ ስም ወይም ከሚዋሃዱት ክበባት
በአንዱ ክበብ ስም ሊጠራ ይችላል፣ እንዲሁም ውህደቱ ሲፈጸም የቀድሞ
ክበባት ማንኛውም ሠነድ ቋሚና አላቂ ንብረት ወደ ተዋሃደው ክበብ
ይተላለፋል፡፡

13. የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እድሳት፣


1. ለማንኛውም ክበብ የተሰጠ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት
በየዓመቱ በሰጠው አስፈፃሚው መሥሪያቤት በተቀመጠው የማደሻ ጊዜ
ውስጥ መታደስ አለበት፣

24
2. የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሚታደሰው ክበቡ በዚህ
መመሪያ መሠረት መንቀሳቀሱ፣ በዓመቱ ውስጥ አጥጋቢ እንቅስቃሴ
ማድረጉና በእንቅስቃሴው መቀጠል ያለበት መሆኑ በአስፈፃሚው መሥሪያ
ቤት ሲታመንበት ብቻ ነው፡፡

14. የክበባት መፍረስ

ማንኛውም ክበብ በሚከተሉት ምክንያቶች በአስፈፃሚው መሥሪያ ቤት


እንዲፈርስ ይደረጋል ፡-

1. የተሰጠውን የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ዓመቱ በተጠናቀቀ በ10 ቀናት ጊዜ


ውስጥ ለሰጠው አስፈፃሚ መሥሪያ ቤት አቅርቦ ካላሳደሰ፣
2. ለአንድ ዓመት ያህል ክበቡ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ሳያደርግ ከቆየ፣
3. ከአባላቱ 3/4 ኛ የሚሆኑት እንፈርስ ሲጠይቁና በአስፈፃሚው መሥሪያቤት
መፍረሱ ታምኖበት ሲፈቀድ፣
4. በዚህ መመሪያ መሠረት ተደራጅቶ ከአስፈፃሚው መሥሪያ ቤት ፍቃድና
እውቅና ማረጋገጫ ሳያወጣ ሲንቀሳቀስ ከተገኘ፣
5. ከተፈቀደለት ተግባር ውጪ ሲያከናውን ከተገኘ ወይም ከመመሪያው
አፈንግጦ ከተገኘ፣
6. በማታለል ወይም በማጭበርበር ወይም ከተቋቋመበት አላማ ውጪ በሆነ
ተግባር ወይም በአርአያነት የሚጠቀስና በተጨባጭ ማስረጃ የተረጋገጠ
የሥነ ምግባር ግድፈት ፈፅሞ ከተገኘ፣
7. በዚህ መመሪያ ውስጥ የተደነገጉትን ግዴታወች በመጣስ ከህግ ውጭ
ሲሰራ ከተገኘ፣
8. አስፈፃሚው መሥሪያ ቤት ለሚያወጣው መመሪያ ደንብ ወይም ውሳኔ
ተገዢ ካልሆነ፡፡

25
ክፍል ሶስት
የባህል ቡድን አስፈላጊነት፤ የአመሠራረት መርህ ፤
ተልዕኮና ዓላማ፤ ተግባርና ኃላፊነት፤ አደረጃጀት እና አስተዳደር

15. የባህል ቡድን አስፈላጊነት


የባህል ቡድን የማቋቋም አስፈላጊነት የሚከተሉት ናቸው ፡-

1. የአካባቢውን ሕብረተሰብ ያልተበረዙና ያልተከለሱ እምቅ የሙዚቃ ሀብቶችን


ለመድረክ ለማብቃት፣

2. ባህሉን ከመጤ የባህል ወረራ ለመታደግና በዘላቂነት በመጠበቅ ለመጭው


ትውልድ ለማስተላለፍ፣

3. የአካባቢዋን ብሎም የክልሉን የባህል ገጽታ ተቋማዊና ኘሮግራማዊ በሆነና


ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማስቀዋወቅ የሚያስችል ምቹ ሁኔታን
ለመፍጠር፣

4. የአካባቢውን ማራኪ ባህላዊ ክንዋኔዎችና ዜማዎችን በተደራጀ መልኩ


በማስተዋወቅ ወደ ቱሪዝም ገበያው በማስገባት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ
ለማሣደግ፣

5. የአካባቢውን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፈርጀ ብዙ


እንቅስቃሴዎችን መረጃዎችና መልእክቶችን ለማስተላለፍ፣ በኪነ ጥበብ
እያዝናኑ በማስተማር በሕብረተሰቡ የተሸለ ግንዛቤ እንዲፈጠር ማድረግ፣

6. በተለያየ ደረጃ በሚካሄዱ የተለያዩ የባህል ፌስቲቫልና ሁነቶች አካባቢውን


በብቃት መወከል በሚችል ሥራ ለመሳተፍና ደረጃ ሊመጥን የሚችል
ዝግጅት ለማቅረብ ፣ ገፅታን ለመገንባት፣
26
7. በአካባቢው የሙዚቃና ኪነ ጥበባት እንቅስቃሴን ለማስፋፋትና ለማጠናከር፣
ተተኪ ከያኒያንን ለማፍራት ፣

8. ህብረተሰቡ ባህልና ወጉ መጠበቁን በመከታተልና ማህበራዊ ሂስ በመስጠት


ለባህሉ መጠበቅና ለሙያው እድገት የበኩሉን ተሳትፎና አስተዋጽኦ
የሚያበረክትበትን መድረክ ለመፍጠር፣

16. የባህል ቡድን ተልዕኮና ዓላማዎች


የባህል ቡድን ተልዕኮና ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው ፡-
1. ተልዕኮ

ኪነ ጥበብ ለሁለንተናዊ ዕድገት ያለውን አስተዋፆ እውን ማድረግና


ልማታዊ እንቅስቃሴንና ቱሪዝምን በማጎልበት ገፅታን መገንባት፤
መጤ የባህል ወረራን፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና ፀረ ልማት
አስተሳሰብና አመለካከቶችን መመከትና የባህል እሴቶች በመጠበቅ
በማስተዋወቅ ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፉ ማስቻልና ለአካባቢው
ሕብረተሰብ ደረጃውን የጠበቀ የባህላዊ የኪነ ጥበብ መዝናኛ መድረክ
መፍጠር ነው፡፡

2. ዓላማዎች
ሀ/ የካባቢውን ሕዝብ ያልተበረዘና ያልተከለሠ ባህላዊ የሙዚቃ
ትውፊቶች ማስተዋወቅ ፣

ለ/ መጤ የባህል ወረራንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመመከትና


የባህል እሴቶች ሳይበረዙና ሳይከለሱ ለመጪው ትውልድ
እንዲቆዩ ማስቻል፣

ሐ/ የአካባቢውን ሕብረተሰብ የልማት እንቅስቃሴን በኪነ ጥበብ


መደገፍና ውጤታማ ማድረግ ፣ ኪነ ጥበብ ለሁለንተናዊ ዕድገት
ያለውን አስተዋፆ እውን የማድረግ፣

27
መ/ ለአካባቢው ሕብረተሰብና ቱሪስቶች ደረጃውን የጠበቀ የኪነ ጥበብ
መዝናኛ መድረክ መፍጠር፤

ሠ/ የህብረተሠቡን ንቃተ ህሊና ለማዳበርና ሁሉን አቀፍ የሆነ


የልማት እንቅስቃሴ ላይ የመነቃቃት መንፈስ በመፍጠር
የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ማፋጠን፣

ረ/ የአካባቢውን የተለያዩ የባህል ትርኢቶች እና ፊስቲቫሎችና


ለማዘጋጀት፣ ለማካሄድና ሕብረተሰብ የባህሉ ተሳታፊ እንዲሆን
ማስቻል ነው፡

17. የባህል ቡድን ተግባርና ኃላፊነቶች

የባህል ቡድን የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡-

1. የአካባቢው ሕዝቦች ያልተበረዙና ያልተከለሱ የባህል ሙዚቃ ኪነ ጥበባት


መረጃ ምንጮችን በመለየት ፣ ግንኙነት በመፍጠር ቱባ መረጃዎችን
ከምንጩ መሰብሰብና ማደራጀት፣
2. የአካባቢው ሕዝቦች የማንነት ማገለጫ የሆኑና ትክክለኛ ባህለዊ ገፅታን
የሚያንፀባርቁ የባህል ሙዚቃ ኪነ ጥበባት ባህላዊ እሴታቸው ተጠብቆና
ኪነ-ጥበባዊ ውበት ይዘው በመድረክ በሚዲያና በተለያዩ መንገዶች
እንዲቀርቡ እንዲታወቁ ማድረግ፣
3. የአካባቢው ሕዝቦች በመወከልና የባህል አምባሳደር በመሆን በክልል፣ በአገር
አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሔዱ መድረኮች ደረጃውን የጠበቀ የባህል
ኪነ-ጥበብ ዝግጅት ማዘጋጀትና ማቅረብ መሳተፍ፤
4. የከተማዋ ነዋሪዎች በባህላዊ ፤ ማህበራዊ ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ
መስኮች ያላቸውን የርስ በርስ ግንኙነት የሚያጠናክሩና ትስስሩን
የሚያሳድጉ፣ ለሰላም ፤ ለዲሞክራሲና ለልማት የሚያነሳሱ ኪነ-ጥበባዊ

28
ብቃት ያላቸው ሙዚቃዎችን ፤ መዝሙሮችን፣ አጫጭር ጭውውት
ድራማዎችን፣ ሙዚቃዊ ተውኔቶችንና ክሊፖችን በማዘጋጀት ማቅረብ ፤
5. መጤ የባህል ወረራን፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና አሠራሮችንና ፀረ ልማት
አስተሳሰብና አመለካከቶችን እያዝናኑ በማስተማር የሚያስወግዱና
ሁለንተናዊ ልማት ለማፋጠን የሚረዱ፣ የገፅታዋን የሚገነቡ ዝግጅቶችን
ማዘጋጀትና ማቅረብ፤
6. ለከተማዋ የውጪና የሐገር ውስጥ ቱሪስቶቿ ደረጃውን የጠበቀ፣ የክልሉን
ሕዝቦች ባህል በተሟላ አግባብ የሚያስተዋውቅ የኪነ ጥበብ መዝናኛ
መድረክ ማቅረብና የቱሪዝም እንቅስቃሴዋን ማጎልበት፣
7. በከተማዋ ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ አማተር የኪነ-ጥበባት ቡድኖች
ሥራዎቻቸው መድረክ የሚየገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ፤ ሥልጠና፣
የሙያ እገዛ በማድረግ ማበረታታትና መደገፍ፤ በከተማዋ የኪነ-ጥበብ
የፈጠራ እንቅስቃሴ እንዲጎለብት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣
8. በከተማዋ የኪነ ጥበብ ፍላጎትና ተሰጥኦ ላላቸውና ስልጠና ለሚፈልጉ
በባህል ሙዚቃ ፤ በውዝዋዜና በተለያዩ የመድረክ ኪነ ጥበባት ሙያ
ሥልጠና መስጠት ፤ ለዚህም ተገቢውን የአገልግሎት ዋጋ ማስከፈል፤
9. መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ቅንጅታዊ አሰራር
በማጠናከርና ወጪን የሚሸፍኑ ስፖንሰሮችን በማፈላለግ ትርኢቶችን
ማቅረብ፡
10. የተዘጋጁ ትርኢቶችን በአውዶቪዥዋል በማሳተምና በማሰራጨት ሰፊ
ተደራሲ እንዲያገኙ የገቢ ምንጭ ማስቻል በፌስቲቫሎች ማቅረብ
11. የአገልግሎት ገቢ ምንጭና አሰባሰብን ማሳደግ የስፖንሰር
የማስታወቂያ ፕሮሞሽንና ሌሎች የገቢ ምንጮችን ማስፋት” ፕሮጀክት
ፕሮፖዛሎችን በማዘጋጀት ሀብት ማፈላለግ ለተልዕኮ ማዋል፣

29
18. የባህል ቡድን አደረጃጀት

1. በክልሉ ውስጥ የባህል ሙዚቃ ቡድን የሚደራጀው ወይም የሚቋቋመው


በወረዳ፣ በዞን እና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ብቻ ነው፤
2. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 1 ላይ በተጠቀሰው ደረጃ በአሁኑ ወቅት ተደራጅተው
በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ የባህል ሙዚቃ ቡድኖች ተጠሪነት በየደረጃው
ለሚገኘው አስፈፃሚ መ/ቤት ነው፣
3. የወረዳና የዞን የባህል ሙዚቃ ቡድንን የሚያቋቁሙት በዋነኛነት የወረዳው
አስፈፃሚ መ/ቤት ከወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት፣ የዞኑ አስፈፃሚ መ/ቤት
ከዞኑ አስተዳደር መምሪያ ጋር በመቀናጀት እና ሌሎች በየደረጃው የሚገኙ
አጋር አካላትን በማስተባበር ነው፣
4. በከተማ አስተዳደር ደረጃ የሚቋቋመውን የባህል ሙዚቃ ቡድን
የሚያቋቁመው የከተማ አስተዳደሩ አስፈፃሚ መ/ቤት ከከተማው አስተዳደር
ጋር በመቀናጀትና ሌሎች አጋር አካላትን በማስተባበር ነው፣
5. በዞን፣ በወረዳና በከተማ አስተዳደር ደረጃ የተቋቋሙና አዲስ የሚቋቋሙ
የባህል ሙዚቃ ቡድኖች ድርጅታዊ አወቃቀር የሚከተለው ይሆናል፡
ሀ/ የበላይ ጠባቂ ቦርድ

ለ/ የባህል ቡድን ባለቤት/አስፈፃሚ መ/ቤት

ሐ/ የባህል ቡድን ኃላፊ

መ/ የባህል ቡድን ባለሙያዎች

19. የባህል ቡድን የበላይ ጠባቂ ቦርድ


30
የበላይ ጠባቂ ቦርድ የባህል ሙዚቃ ቡድን የበላይ አካል ሲሆን በተለያየ ደረጃ
ወይም በወረዳ፣ በዞንና በከተማ አስተዳደር ደረጃ እንደሚከተለው ይደራጃል፡-

1. የወረዳ የባህል ቡድን የበላይ ጠባቂ ቦርድ የሚከተሉትን 7 አባላት በማቀፍ


የሚደራጅ ይሆናል፡-
ሀ/ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ሰብሳቢ

ለ/ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ ም/ሰብሳቢ

ሐ/ የወረዳው የአስፈፃሚ መሥሪያ ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ ፀሐፊ

መ/ የወረዳው ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ


አባል

ሰ/ የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የጽ/ቤት ኃላፊ አባል

ረ/ የወረዳው የባህል ተቆርቋሪና ታዋቂ የሆኑ ሁለት የሐገር


ሽማግሌዎች አባል

2. በክልሉ የብሔረሰብ ዞኖች የባህል ቡድን የበላይ ጠባቂ ቦርድ የሚከተሉትን


7 አባላት በማቀፍ የሚደራጅ ይሆናል፡-
ሀ/ የዞኑ ዋና አስተዳዳዳሪ ሰብሳቢ

ለ/ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ ም/ሰብሳቢ

ሐ/ የዞኑ አስፈፃሚ መ/ቤት መምሪያ ኃላፊ ፀሐፊ

መ/ የብሔረሰብ ዞኑ ም/ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ


አባል

ሰ/ የዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ የመምሪያ ኃላፊ አባል


አባል

31
ረ/ በዞኑ የባህል ተቆርቋሪና ታዋቂ የሆኑ ሁለት የሐገር ሽማግሌዎች
አባል

3. በሌሎች የክልሉ ዞኖች የባህል ቡድን የበላይ ጠባቂ ቦርድ የሚከተሉትን 7


አባላት በማቀፍ የሚደራጅ ይሆናል፡-
ሀ/ የዞኑ ዋና አስተዳዳዳሪ ሰብሳቢ

ለ/ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ ም/ሰብሳቢ

ሐ/ የዞኑ አስፈፃሚ መ/ቤት መምሪያ ኃላፊ ፀሐፊ

መ/ የብሔረሰብ ዞኑ ም/ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ


አባል

ሰ/ የዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ የመምሪያ ኃላፊ አባል


አባል

ረ/ በዞኑ የባህል ተቆርቋሪና ታዋቂ የሆኑ ሁለት የሐገር ሽማግሌዎች


አባል

4. በከተማ አስተዳደሮች የባህል ቡድን የበላይ ጠባቂ ቦርድ የሚከተሉትን 7


አባላት በማቀፍ የሚደራጅ ይሆናል፡-
ሀ/ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ሰብሳቢ

ለ/ የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ ም/ሰብሳቢ

ሐ/ የከተማ አስተዳደሩ አስፈፃሚ መ/ቤት መምሪያ ኃላፊ ፀሐፊ

መ/ የከተማ አስተዳደሩ ም/ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ


ሰብሳቢ አባል

32
ሰ/ የከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ የመምሪያ
ኃላፊ አባል

ረ/ በከተማው ተመረጡ የባህል ተቆርቋሪና ታዋቂ የሆኑ ሁለት


የሐገር ሽማግሌዎች አባል

5. ከላይ በንኡስ አንቀፅ 1 እስከ 4 የተዘረዘሩት የባህል ቡድን የበላይ ጠባቂ


ቦርድ አባላት በየደረጃው ባሉት አስፈፃሚ መ/ቤቶች አቅራቢነት በሰብሳቢው
ይሰየማሉ፣

6. በየደረጃው የሚሰየሙት የበላይ ጠባቂ ቦርዶች አመራር አካላት የቦርዱ


ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና ፀሐፊ ሲሆኑ ስልጣንና ተግባራቸውም
የሚከተለው ይሆናል፡-

ሰብሳቢ፣
ሀ. በአስፈፃሚው መሥሪያ ቤት አቅረቢነት የቦርዱን አባላት
ይሰይማል፣
ለ. ከፀሀፊው ጋር በመሆን አጀንዳዎችን ያዘጋጃል፣ የቦርዱን
ስብሰባዎች ይጠራል፤ ስብሰባውን በሊቀመንበርነት ይመራል፣

ሐ. ቦርዱ የሚያወጣችውን ደንቦችና የሚሰጣቸውን ውሣኔዎች


በትክክል ስራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፣

መ. ቦርዱ ያጸደቃቸው ዓመታዊ የሥራ ክንውን፤ የሥራና የኦዲት


ሪፖርቶችና የሂሳብ መግለጫ ለሚመለከታቸው መንግሥታዊ
አካላት እና እንደአስፈላጊነቱ ለተጠቃሚዎችና ለለጋሾች
እንዲደርሱ ያደርጋል፣

ሠ. ለቦርዱ የሚቀርቡ ጉዳዮችን ቅደም ተከተል በማውጣት


ለውይይት እንዲቀርቡ ለፀሐፊው በአጀንዳነት ያስይዛል፣

33
ምክትል ሰብሳቢ
ሀ. ሰብሳቢው በማይኖርበት ጊዜ ተክቶ ይሠራል፣
ለ. በሰብሳቢው ወይም በቦርዱ የሚሰጡ ሌሎች ስራዎች ያከናውናል፣
ፀሐፊ
ሀ. ከሰብሳቢው ጋር በመሆን ለቦርዱ ስብሰባ አጀንዳዎችን ያዘጋጃል፣
ለ. የቦርዱን የስብሰባ ቃለ ጉብኤ ይይዛል፣
ሐ. በሰብሳቢው ወይም በቦርዱ የሚሰጡ ሌሎች ስራዎች
ያከናውናል፣
7. በየደረጃው የሚደራጀው የባህል ቡድን የበላይ ጠባቂ ቦርድ የሚከተሉት
ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

ሀ/ ለባህል ቡድን ለደሞዝና ለሥራ ማስኬጃ ከመንግሥት የሚመደብ


ዓመታዊ በጀት ምንጭና መጠንን ይወስናል፣ ያፀድቃል፣

ለ/ የባህል ቡድኑን የሰው ኃይል አስተዳደር፣ የውስት የአሠራር


መተዳደሪያ ደንብ፣ የዲሲፒሊን አፈፃፀም መመሪያንና ሌሎች
አስፈላጊ መመሪያዎችን መርምሮ ያፀድቃል፣ ያሻሽላል፣

ሐ/ የባህል ቡድኑን ኃላፊና ሌሎች ባለሙያዎች ቅጥር አፈፃፀምን


መርምሮ ያፀድቃል፣ ይወስናል፣

መ/ በአስፈፃሚው መ/ቤት በሚቀርብለት መነሻ የባህል ቡድኑን


ኃላፊና ሌሎች ባለሙያዎች ወርሐዊ የደሞዝ መጠን ከአካባቢው
ነባራዊ ሁኔታ አግባብ መርምሮ ያፀድቃል፣ ይወስናል፣

ሠ/ ለባህል ቡድኑ ማጠናከሪያ የሚሆን የፋይናንስ ማስገኛ ስልቶችን፣


ሕዝባዊ መዋጮዎችን ይቀይሳል፣ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
አፈፃፀሙን ይከታተላል፣

ረ/ ለባህል ቡድኑ ቋሚ የሆኑ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶችን ይቀይሳል፣


በአስፈፃሚው መ/ቤት በኩል ተጠንተው የሚቀርቡት ፕሮጀክቶችን

34
መርምሮ ያፀድቃል፣ እንዲተገበሩ ያመቻቻል፣ አፈፃፀማቸውን
ይከታተላል፣

ሰ/ የባህል ቡድኑን ዓመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርት፣ የኦዲት


ሪፖርትና የሂሳብ መግለጫ የኦዲት ሪፖርትና ይገመግማል፣
ያፀድቃል፣

ሸ/ የባህል ቡድኑን ከሌሎች ጋር ህብረት የመፍጠር፣ የመዋሃድ


ወይም የመከፈል፣ የመለወጥ ወይም የመበተን ጉዳይ ላይ
የመጨረሻ ውሳኔ ይሠጣል፣

ቀ/ ለባህል ቡድኑ ዘለቄታዊ እንቅስቃሴ አስፈላጊ በሆኑ በአስፈፃሚው


መ/ቤት ተጠንተው በሚቀርቡ የፖሊሲና የስትራቴጂ ጉዳዮችን
መርምሮ ያፀድቃል፣ ይወስናል፣

በ/ የሥነ ምግባር ግድፈት የፈፀሙና ግዴታቸውን ያልተወቱ ኃላፊና


ፈፃሚዎችን ጉዳይ መርምሮ የቅጣት ውሳኔ ይሰጣል፣
እንዲሰናበቱ ይወስናል፣

ተ/ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የቦርዱን የስብሰባ ሥነ-ስርዓትና ሌሎች


ደንቦች ያወጣል፣ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣

ቸ/ በሌሎች አካላት ስልጣንና ተግባራት ስር በማይወድቁ የባህል


ቡድኑን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ይወስናል፣
ከ/ ቦርዱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በዚህ ንዑስ አንቀጽ መሰረት
የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት ለአስፈፃሚ መ/ቤት ወይም
ለሚያቋቁመው ቋሚ ወይም ጊዚያዊ ኮሚቴ በውክልና ማስተላለፍ
ይችላል፣

8. የበላይ ጠባቂ ቦርድ የስብሰባ፣ የድምፅ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት


በሚከተለው አግባብ ይፈፀማል ፡-

35
ሀ. በበጀት ዓመቱ ውስጥ ቦርዱ አራት መደበኛ ስብሰባ ያካሂዳል፣
መደበኛ ስብሰባው በሰብሳቢው ጠሪነት የበጀት ዓመቱ ሩብ ዓመት
ከተዘጋ በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ መካሄድ ይኖርበታል፣

ለ. አስቸኳይ ስብሰባ የሚያስፈልግበት ምክንያት ሲኖር በማናቸውም


ጊዜ ልዩ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል፣ አስቸኳይ ስብሰባው
በሰብሳቢው ወይም በፀሐፊው ወይም ከቦርዱ 2 እና ከሁለት በላይ
የሚሆኑት አባላት በሚጠይቁበት ጊዜ ሊካሄድ ይችላል፤
ሐ. ከአባላቱ ውስጥ ከግማሽ በላይ ከተገኙ የስብሰባው ምልዓተ
ጉባኤው እንደተሟላ ይቆጠራል፣ ምልዓተ ጉባኤው ካልተሟላ
ድጋሜ ለስብሰባ ጥሪ ይደረጋል፡፡ በድጋሜ በተደረገው ጥሪ
ምልዓተ ጉባኤው ካልተሟላ በተገኙ አባላት ስብሰባ ሊካሄድ
ይችላል፣

መ. ለመደበኛ ስብሰባ ሶስት የስራ ቀናት ለአስቸኳይ ስብሰባ ደግሞ


አንድ የስራ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ በፊት አባላት የስብሰባውን
ዝርዝር ጉዳይ፣ ቦታውን፣ ቀኑን፤ ጊዜውን እንዲያውቁት
ይደረጋል፣

ሠ. ቦርዱ በግልጽ ካልፈቀደ በስተቀር ማንኛውም አባል በስብሰባ ላይ


እራሱ ተገኝቶ ድምጽ መስጠት ይኖርበታል፣

ረ. ማንኛውም የቦርድ አባላት እኩል ድምጽ አላቸው፣ የድምጽ


አሰጣጡ ሥነ-ሥርዓት ፍትሀዊ ነፃና ግልጽ በሆነ መንገድ
ተፈፃሚ ይሆናል፣ የተለየ ሃሣብ ያለው የቦርድ አባል የልዩነት
ሀሣቡን በቃለ ጉባኤው ላይ ለይቶ ማስፈር ይችላል፣

ሰ. የቦርዱ ውሳኔዎች በድምፅ ብልጫ ይተላለፋሉ፤ ድምፅ እኩል


በሚከፈልበት ጊዜ ሰብሳቢው የደገፈው ሀሳብ ይፀናል፤
36
ሸ. የቦርድ አባላት ያለደመወዝ ያገለግላሉ፤ ሆኖም ለባህል ሙዚቃ
ቡድኑ ስራ ለሚያወጡት ወጭዎች ማካካሻ ይከፈላል፡፡

20. የባህል ቡድን ባለቤት ወይም አስፈፃሚ መ/ቤት


1. በየደረጃው የሚገኝ ምክር ቤቶችና የመንግሥት የአስተዳደርና አስፈፃሚ
አካላት፣ በአካባቢው የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ በሕዝባዊ ማህበራትና
ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት የባህል ቡድንን አስፈላጊነት ተልዕኮና ዓላማ ዙሪያ
በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ ያደርጋል፣
2. ቀደም ሲል የተቋቋሙና በቀጣይ የሚቋቋሙ የባህል ቡድኖች አደረጃጀት
በዚህ መመሪያ መሠረት እንዲፈፀም አስፈላጊው ሁሉ ያከናውናል፣ በበላይ
ጠባቂ ቦርድ ውስጥ በኃላፊነት ይንቀሳቀሳል፣
3. በመመሪያው አንቀፅ 22 እና 23 በተደነገገው መሠረት ለባህል ቡድኑ
እንቅስቃሴ አስፈላጊ የሆኑና የግዴታ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች ደረጃ
በደረጃ እንዲሟሉ ያደርጋል፣
4. የባህል ቡድን ተልዕኮና ዓላማውን እንዲወጣ እና በመመሪያው አንቀፅ 17
የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች በብቃት ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል
የሙያ ክትትልና ድጋፍ ዘላቂነት ባለው አግባብ ያደርጋል፣
5. ለባህል ቡድን እንቅስቃሴ በየዓመቱ ከመንግሥት የሚሰጥ የበጀት ድጎማ
ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ቡድኑ ከሚሰጠው አገልግሎት የሚሰበሰብ ገቢ
እንዲስፋፋ አስፈላጊ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣
6. በመመሪያው መሠረት የባህል ቡድን ቋሚ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶን
ይቀርፃል፣ ሲፈቀድ ተግባራዊ ያደርጋል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
7. የባህል ቡድኑን የፋይናን፣የግዢና የንብረት አስተዳደር እንቅስቃሴን በዚህ
መመሪያ በተደነገገው መሠረት እንዲተገበር ድጋፍ ይሰጣል፣ ክትትልና
ቁጥጥር በማድረግ ተፈፃሚ እንዲሆን ያደርጋል፣

37
8. የባህል ቡድኑን የሰው ኃይል አደረጃጀትና አስተዳደር በዚህ መመሪያ
በተደነገገው መሠረት እንዲተገበር ያደርጋል፣ ድጋፍ ይሰጣል፣ ክትትልና
ቁጥጥር በማድረግ ተፈፃሚ እንዲሆን ያደርጋል፣
9. በየጊዜው የባህል ቡድን መንግሥስታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች
ከግለሰቦች የማተሪያልና የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኝ ስልቶችን ይቀይሳል፣
ይተገብራል፣ አስፈላጊ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣
10. በቦርዱ የሚሰጡትን እና ከባህል ሙዚቃ ቡድኑ ጋር ግንኙነት ያላቸውን
ሌሎች ሕጋዊያን ተግባራት ያከናውናል፡፡

21. የባህል ቡድን ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት

1. የባህል ቡድን ኃላፊ የባህል ሙዚቃ ቡድኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በመሆን


የቡድኑን ሥራዎች ያቅዳል፤ ያደራጃል፤ ይመራል፤ ይቆጣጠራል፡፡
2. ከላይ የተጠቀሰው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ የባህል ቡድን
ኃላፊ፡-

ሀ. በዚህ መመሪያ አንቀፅ 17 የተመለከቱትንና ለባህል ሙዚቃ ቡድን


የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች በሥራ ላይ ያውለል፤

ለ. የቡድኑን የሥራ ፕሮግራምና በጀት እቅድ አዘጋጅቶ ለአስፈፃሚው


መ/ቤትና ለቦርዱ ያቀርባል፤ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል፤

ሐ. ለቡድኑ በተፈቀደው በጀት መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል፤


በበላይነት ያስተዳድራል፤ ይቆጣጠራል፤

መ. የቡድኑን ገንዘብና ንብረት በሚገባ መጠበቁንና በተፈቀደለት ዓላማ


መዋሉን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል ፤

38
ሠ. ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች የባህል ሙዚቃ ቡድኑን
ይወክላል፤

ረ. የባህል ቡድኑን የሥራ አፈፃፀምና የሂሳብ ሪፖርት አዘጋጅቶ


ለአስፈፃሚው መ/ቤትና ለቦርዱ ያቀርባል፤

ሰ. በቦርዱና በአስፈፃሚው መ/ቤት የሚሰጡትን እና ከባህል ሙዚቃ


ቡድኑ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሌሎች ሕጋዊያን ተግባራት
ያከናውናል፡፡

3. የባህል ቡድን ኃላፊ ተግባሩን በሥሩ ለሚገኙ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች


የሥራ ኃላፊነት ውክልና ሊሰጥ ይችላል፣ ሆኖም ከአንድ ወር ጊዜ በላይ
መብለጥ የለበትም፡፡

22. በየደረጃው ለሚደራጁ የባህል ቡድኖች መሟላት ያለባቸው


የሰው ኃይልና የማቴሪያል አደረጃጀት ሁኔታዎች
1. በወረዳ ደረጃ ለተቋቋሙና ለሚቋቋሙ የባህል ሙዚቃ ቡድኖች ፡-
ሀ/ ቢያንስ አራት መሣሪያ ተጫዋቾች፣ አራት ድምፃውያ፣ ሦስት
ወንድ ሦስት ሴት በድምሩ ስድስት ተወዛዋዦች፣ አንድ መድረክ
መሪ ወይም አስተዋዋቂ እና አንድ የድምፅ የኤልክትሪክ
ቴክኒሻን፣ የሒሳብ ሠራተኛ፣ ገንዘብያዥና ገቢ ሰብሳቢ፣ አንድ
የቡድን ኃላፊ በጠቅላላ ድምር 19 የሰው ኃይል ሊኖረው ይገባል፣

ለ/ በዘመናዊ መልክ የተሰራ ሙሉ ሴት የባህል ከበሮ፣ ሊድና ቤዝ


ክራር ከነፒካፑ፣ መሰንቆ ከነፒካፑ፣ የሊድና የቤዝ ክራር
መለስተኛ አምፕሊፋየሮች፣ አንድ ኪቦርድ፣ አንድ 400 ዋት በላይ
የሆነ ሜክሰር ሦስት ማይኮች ከነስታንዳቸው፣ የአካባቢው

39
ሕብረተሰብ ባህላዊ አልባሳቶች፣ ጌጣጌጦች፣ የወግ ዕቃዎችና
ቁሳቁሶች ፣

2. በዞንና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ለተቋቋሙና ለሚቋቋሙ የባህል ሙዚቃ


ቡድኖች፡-
ሀ/ ሪትሚካል ሜሎዲካል እንዲሁም የተለያዩ የሙዚቃ ባህርያትን
ተግባብቶ ሊያሰራ የሚችል ዕውቀት ያላቸው እና ለዚህም
የትምህርት የስልጠና ወይም የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ
አምሰት መሣሪያ ተጫዋቾችና አምስት ድምፃውያን፣ አራት ወንድ
እና አራት ሴት በድምሩ ስምንት ተወዛዋዦች፣ አንድ መድረክ
መሪ ወይም አስተዋዋቂ እና አንድ የድምፅ የኤልክትሪክ
ቴክኒሻን፣ የሒሳብ ሠራተኛ፣ ገንዘብያዥና ገቢ ሰብሳቢ፣ አንድ
የቡድን ኃላፊ በጠቅላላ ድምር 23 የሰው ኃይል ሊኖረው
ሊሟሉለት ይገባል፣
ለ/ አንድ ሴት (Set) የባህል ከበሮ፣ ሊድና ቤዝ ክራር ከነፒካፓቸውና
አምፕሊፋየራቸው፣ የተሟላ መሰንቆ ከነፒካፑ፣ የተለያዩ ቅኝቶች
ያላቸው የተለያዩ ዋሽንቶች የተሟሉ ሴት (Set) ፣ አንድ
ኪቦርድ፣ አንድ ከ800 ዋት በላይ ሴት (Set) ሚክሰር ከ16-22
በላይ ቻናል ከአምስት ማይኮች ከነስታንዳቸው ፣የክልሉ ብሔር
ብሔረሰብና ሕዝቦች መገለጫ የሆኑ የተሟሉ ባህላዊ አልባሳቶች፣
ጌጣጌጦች፣ የወግ ዕቃዎችና ቁሳቁሶች ፣ ቢቻል የትራንስፖርት
መገልገያ አነስተኛ ተሸከርካሪ፣

23. የባህል ቡድን የመሥሪያ ቦታ

40
1. በሁሉም ደረጃ ለሚቋቋሙ የባህል ቡድኖች በየዕለቱ ኪነ ጥበባዊ ስራቸውን
የሚያከናውንበት፣ የሚያቀርብበትና የተለያዩ የገቢ ምንጭ ማስገኛ
ተግባራትን የሚፈፅሙበት አዳራሽና ተጓዳኝ ክፍሎችን ያካተተ በአማካኝ
ሥፍራ ላይ የሚገኝ የመሥሪያ ቦታ እንዲኖራቸው መደረግ አለበት፣
2. በዚህ አንቀፅ ከላይ በንዑስ አንቀፅ 1 የተገለፀው አጠቃላይ ድንጋጌ
እንደተጠበቀ ሆኖ ፡-
ሀ/ በወረዳ ደረጃ ለተቋቋሙና ለሚቋቋሙ የባህል ቡድኖች በወረዳው
ርዕሠ ከተማ የሚገኝና በሌላ መመሪያ ወደ መሥሪያ ቤቱ
እንዲዛወር የተደረገ የሕዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ለቡድኑ
የመሥሪያ ቦታ እንዲሆን መደረግ አለበት፣
ለ/ በዞን ደረጃ ለተቋቋሙና ለሚቋቋሙ የባህል ቡድኖች በሚመለከት
በከተማው አማካይ ስፍራ የመሥሪያ ቦታ የሚያገኙበት ሁኔታ
በበላይ ጠባቂ ቦርድ እንዲወሰን አስፈፃሚው መ/ቤት ያመቻቻል፣
ተግባራዊ ያደርጋል፣
ሐ/ በከተማ አስተዳደር ደረጃ ለሚቋቋሙ የባህል ቡድኖች በከተማ
አስተዳደሩ በሚገኝ የሲኒማ አዳራሽን ከሲኒማው አስተዳደር ጋር
በመቀናጀት የሚጠቀሙበትን ሁኔታ አስፈፃሚው መ/ቤት አጥንቶ
ለቦርዱ በማቅረብ ተፈፃሚ እንዲሆና ያደርጋል፣

24. የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት

1. በወረዳ ለተደራጁ የባህል ቡድኖች ወረዳው የሚገኝበት የዞን አስፈፃሚ


መ/ቤት የመመሪያውን መሥፈርቶች ሙሉ በሙሉ ማሟላቱን አረጋግጦ
የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣
2. በዞንና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ለተደራጁና ለሚደራጁ የባህል ቡድኖች

የክልሉ አስፈፃሚ መ/ቤት ወይም ቢሮው የመመሪያውን መሥፈርቶች

41
ሙሉ በሙሉ ማሟላቱን አረጋግጦ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር
ወረቀት ይሰጣል፣
3. በየደረጃው በአስፈፃሚው መ/ቤት የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር
ወረቀት የተሰጠው የባህል ቡድን የራሱ አርማና ማሕተም፣ የባንክ
አካውንት ሊኖረውና በመመሪያው መሠረት መንቀሳቀስ ይችላል፣

25. የገቢ ምንጭ


የባህል ቡድን ገቢ ከሚከተሉት የሚመነጭ ይሆናል ፡-

ሀ. ለባህል ቡድን በመንግስት የሚመደብ ዓመታዊ በጀት ፤


ለ.ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚሰበሰብ ገቢ፤
ሐ. ከቋሚ የገቢ ማስገኛ አገልግሎቶች የሚሰበሰብ ገቢ፣
መ. የአይነትም ሆነ በጥሬ ገንዘብ ከሚገኝ ስጦታ ወይም እርዳታ፤
ሠ. ሌሎች ፡፡

26. የገቢ ማስገኛ ሥራዎች

1. በየደረጃው የሚቋቋም የባህል ቡድን የፋይናንስ አቅሙን ለማጠናከር


ከተቋቋመበት ተልዕኮና ዓላማ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሕጋዊ የሆኑ
የተለያዩ የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን ማከናወን ይችላል፣ ማከናወንም አለበት፣
2. ከሚሰጣቸው የኪነ ጥበብ አገልግሎት የሚሰበስበውን ገቢ ቀጥሎ
በተዘረዘሩት አግባቦችና ሌሎች ተመሳሳይ ስልቶችን በመቀየስ በየጊዜው
በማስፋፋትና በማጠናከር መንቀሳቀስ ይጠበቅበታል፣
ሀ/ በተለያዩ በዓላት ቋሚ ፕሮግራም በመዘርጋት ዝግቶችን በገቢ
ለተመልካች በማቅረብ፣

42
ለ/ ፕሮፖዛል ቀርፆ የፋይናንስና የማቴሪያል ድጋፍ ከመንግስታዊና
መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት በማፈላለግ እያዝናኑ መልዕት
የሚያስተላልፉ ትርኢቶችን አዘጋጅቶ በማሳየት፣
ሐ/ በተለያዩ ተቋማት በሚዘጋጁ የስብሰባና መሰል መድረኮች፣
በሠርግ ሥነ ሥርዓትና መሠል ማህበራዊ ሁነቶች በተመጣጣኝ
ክፍያ ትርኢቶችን በማቅረብ፣
መ/ የአካባቢውን ትውፊታዊ የሙዚቃ ባህልንና አጨዋወትን፣
አጫጭር ሙዚቃዊ ድራማ ጭውውት ሥራዎችን በሲዲና
በካሴት በማሳተምና ለሽያጭ በማቅረብ፣
3. ከሚሰጠው አገልግሎት ከሚሰበሰብ ገቢ በተጨማሪ የገቢ ማስገኛ
አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በማቋቋም ገቢ መሰብሰብ አለበት፣ ለዚህም
አስፈፃሚው መ/ቤት ከቡድኑ ጋር በመቀናጀት የአካባቢውን ተጨባጭ
ምቹ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያተገናዘበ የቢዝነስ እቅድ አዘጋጅቶ ለቦርዱ
አቅርቦ የማፀደቅና መነሻ ካፒታል የማስፈቀድ ተግባር ያከናውናል፣
4. ከላይ በንዑሥ አንቀፅ 3 በተገለፀው አግባብ ሊከናወኑ ከሚችሉ የገቢ
ማስገኛ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ዓይነቶችን በሚመለከት፡-
ሀ/ የተለያዩ ባህላዊ ምግብና መጠጦች አቅርቦቶችን ያካተተ የባህል
ምሽት ቤት መዝናኛ አገልግሎት፣
ለ/ የዲኤስ ቲቪ የእግር ኳስ ፊልምና ሌሎች ፊልሞችን ከፊልም
ሠሪዎች ጋር በመዋዋል በቋሚ ፕሮግራም ማሳየት፣
ሐ/ የባህል ውዝዋዜ እና የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች /ክራርና
መሰንቆ/ ማሰልጠኛ አገልግሎት፣
መ/ የአካባቢው የባህል ወግ ዕቃዎች፣ ባህላዊ ጌጣጌጦችና አልባሳት
መሸጫ ሱቅ፣
ሠ/ ፑል፣ ካራምቦላ፣ ጆቶኒና የመሳሰሉ የቤት ውስጥ የስፖርት
መዝናኛ አገልግሎት፣
43
ረ/ ለስብሰባና መሰል ዝግጅቶች የአዳራሽ ኪራይ አገልግሎት
መስጠት፣
ሰ/ እና ሌሎች በአካባቢው አዋጪ የሆኑ ተመሳሳይ አገልግሎቶች
ሊሆኑ ይችላሉ፣
5. በዚህ አንቀፅ ከላይ በንዑሥ አንቀፅ 3 እና 4 ላይ ለተደነገጉት ተፈፃሚነት

በዚህ አንቀፅ ሥር ቀጥሎ የተዘረዘሩት ተግባራዊ መሆን አለባቸው ፡-


ሀ/ የሚሰማራበት የንግድ ዘርፍ የታወቀ መነሻ ካፒታል ያለው
እንዲሆን ማድረግና በሥራው ለመሰማራት የሚያስችል የንግድ
ስራ ፈቃድን ከተገቢው አካል ማውጣት፣
ለ/ በንግድና ኢንቨስትመንት ወይም ትርፍ ለማግኘት በተቋቋሙ
ሌሎች ድርጅቶች ላይ ተፈፃሚነት ያላቸው የምዝገባ፣ የፈቃድ፣
የግብር እና ሌሎች ግዴታዎችን መፈፀም፣
ሐ/ ለገቢ ማስገኛ አገልግሎቱን የዕለት ተዕለት ስራዎችን
የሚያከናውኑ የራሱ የተቀጠሩ ሠራተኞች እንዲኖሩት ማድረግ፣
አስፈፃሚው መ/ቤትና ቡድኑ ስራውን በበላይነት መቆጣጠር ፣
መ/ ማናቸውም ገቢ የሚያስገኙ ስራዎችን በተመለከተ ከቡድኑ ሂሳብ
የተለየ የባንክ አካውንት የሂሳብ መዛግብት የመያዝ ፣ የሚያዘው
የሂሳብ መዝገብ በንግድ እና በግብር ህጐች ውስጥ የተዘረዘሩትን
የሂሳብ አያያዝ መስፈርቶች ያሟላ እንዲሆን ማድረግ፣
ሠ/ የቡድኑን አስተዳደርና አስተዳደራዊ ወጪዎች ከገቢ ማስገኛ
ስራው አስተዳደርና አስተዳደራዊ ወጪዎች መለየት ፣
ረ/ የገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴው ወጪና ኪሳራ አግባብ ባላቸው የንግድ
ህጉ ድንጋጌዎች መሠረት ከተሰላ በኋላ የሚገኘው የተጣራ ትርፍ
በገቢ ማስገኛ ተቋሙ የሂሳብ ሠራተኛ አማካኝነት ወደ ዋናው
የቡድኑ የባንክ አካውንት ሂሳብ እንዲገባ ማድረግ፣

44
ሰ/ ከቡድኑ መደበኛ ሪፖርት በተለየ የገቢ ማስገኛ ስራውን የገንዘብ
እንቅስቃሴ ሊያሳይ የሚችል አመታዊ የኦዲት ሪፖርት ማዘጋጀት
ለቦርዱ ማቅረብ፣
6. ከዚህ በፊት የንግድ ፈቃድ አውጥተው የንግድ ስራ በማከናወን ላይ ያሉ

የባህል ቡድኖች ካሉ ይህ መመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ወር


ጊዜ ዉስጥ ሥራው ከመመሪያው ጋር በተጣጣመ አግባብ እንዲፈፀም
ማድረግ አለባቸው፣

27. የፋይናንስ፣ የግዢና ንብረት አስተዳደር ሁኔታ

1. በየደረጃው የሚደራጅ ማንኛውም የባህል ቡድን በዚህ መመሪያ አንቀፅ 26


መሠረት የሚያሰባስበውን የገቢና ወጪ የፋይናንስ እንቅስቃሴውን
በሚከተለው አግባብ ያስተዳድራል፣

ሀ/ የቡድኑ የገቢና ወጪ ሒሳቡን የሚያንቀሳቅስበት የባንክ አካውን


ይከፍታል፣

ለ/ የቡድኑን የገቢ መሰብሰቢያ ሕጋዊ ደረሰኝ ያሳትማል፣


ማንኛውንም ገቢ በደረሰኙ ይሰበስባል፣

ሐ/ የገቢና ወጪ የገንዘብ እንቅስቃሴዎች የሚያብራራ እና


በማናቸውም ጊዜ ሊያሣይ የሚችል የሂሳብ መዝገብ ይይዛል፣

መ/ የቡድኑ የሂሣብ ሰነዶች የተሰበሰበ ጠቅላላ ገቢ ገንዘብና


ያወጣውን ወጪ፣ የወጪውን ምክንያት፣ ሀብትና ዕዳ ያካተቱ
መሆን አለባቸው፣
ሠ/ የቡድኑ ሂሳብ የሚንቀሳቀሰው በታወቀ የሂሳብ አሠራር ደንብ
መሠረት ይሆናል፣

45
ረ/ የቡድኑ የባንክ አካውንቶችና የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኞች በቦርዱ
ውሳኔ የሚከናወኑና በቦርዱ በግልፅ የሚታወቁ መሆን አለባቸው፣

2. በቡድኑ ሥም በተከፈቱ የባንክ ሂሳብ ሣጥኖች ቼክና የወጪ ሰነዶች ላይ


የአስፈፃሚው መ/ቤት ኃላፊና የባህል ቡድን ኃላፊ በጣምራ በመፈረም
ሒሳቡን ያንቀሳቅሳሉ፣ ለቡድኑ የደሞዝና ሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን
ይፈቅዳሉ፣ ገቢና ወጪ ሒሳቡን በበላይነት ይቆጣጠራሉ፣

3. የባህል ቡድን የሒሳብ ሠራተኛ የቡድኑን ገቢና ወጪ ሂሳብ ሠነዶች


ያዘጋጃል፣ አሠራሩ በታወቀ የሂሳብ አሠራር ደንብ መሠረት መሆኑን
ያረጋግጣል፣ የሂሳብ መዛግብትና ሠነዶችን በጥንቃቄ ይይዛል፣ የሂሳብ
መዝገብ፣ ገቢና ወጭ፣ ኃብትና እዳን ያካተተ የሒሳብ መግለጫ ሰነድ
ያዘጋጃል፣ ቡድኑ ገቢ በሚያስገኙ ሥራዎች ላይ በሚሰማራበት ጊዜ ለዚሁ
ሥራ የሚውሉ የተለያዩ የሂሳብ መዛግብት እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣
4. የባህል ቡድን ገንዘብ ያዥ ማንኛውንም የቡድኑን ገቢዎች በህጋዊ ደረሰኝ
ይሰበስባል፣ባንክ ገቢ ያደርጋል፣ ገቢ ያደረገበትን ደረሰኝ በጥንቃቄ
ያስቀምጣል፣ ቼክ ይይዛል፣ ከሒሳብ ሹሙ ጋር የወጪና የገቢ ሒሳብ
በየወሩ ያመሳክራል፣ በአስፈፃሚው መ/ቤት ኃላፊና በባህል ቡድን ኃላፊ
ጣምራ ፊርማ በወጪ ሰነድ ሲታዘዝ ወጪ ያደርጋል፣ ማንኛውንም ግዢ
ይፈፅማል፣
5. ማንኛውም ለባህል ቡድኑ የሚከናወን የቋሚና አላቂ ንብረቶች ግዢና
የአገልግሎት ክፍያ እና የደመወዝ ወጪና ገቢ ምዝገባና አያያዝ
የመንግሥት መመሪያና አሠራር ሒደትን በተከተለ አግባብ መፈፀም
አለበት፣
6. የማንኛውም የባህል ቡድን ሂሣብ በየዓመቱ በተመሰከረለት ኦዲተር ወይም
የውስጥ ኦዲተር ወይም ቦርዱ በሚመድበው ኦዲተር መመርመር አለበት፣

46
7. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6 ቢኖርም ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ
መሰረት ማንኛውም ዓይነት የቡድኑ የሂሳብ ምርመራ በማንኛውም ጊዜ
በውጭ ወይም በውስጥ በቦርዱ በሚሰየም ኦዲተር ሊመረመር ይችላል፣
8. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6 እና 7 መሠረት በቦርዱ የተሰየመ ኦዲተር
ለሚገኝ ማናቸውም ስህተቶች ጥፋተኛና ተጠያቂዎቹ ሒሳቡን
የሚያንቀሳቅሱት የሥራ መሪዎቹና ሠራተኞች ይሆናሉ፣
9. የሥራ መሪዎቹ የበጀት ዓመት የፋይናን ክንዋኔዎች ሪፖርትና አስፈላጊ
መረጃ በማዘጋጀት ለቦርዱ ማቅረብ አለባቸው፣ የተመለከተው ሪፖርት
የሂሣብ ዓመቱ ባለቀ ጊዜ ውስጥ እንዲሁም ቦርዱ በማናቸውም ልዩ
ምክንያት በሚጠይቅበት ጊዜ ውስጥ ማቅረብ አለባቸው፣
10. በዚህ አንቀፅ ከላይ በንዑስ አንቀፅ 3 እና 4 የተጠቀሱትን ድጋፍ
ሰጪ ሠራተኞችን ቡድኑ እስኪያሟላ ድረስ የሚያከናውኑት ተግባር
ለቦርዱ በማስወሰን የአስፈፃሚውን መ/ቤት በጀት በሚያንቀሳቅሱ የፋይናንስ
ድጋፍ ሰጪ ሠራተኖች ይከናወናል፣

28. የሥራ መደቦች፣ ደመወዝና የአበል ክፍያ

1. በየደረጃው የሚቋቋሙ የባህል ቡድን ቀጥሎ የተዘረዘሩት የሰው ኃይል

የሥራ መደቦች ደረጃ ይኖራቸዋል፡-

ሀ/ ደረጃ አራት የባህል ቡድን ኃላፊ፣

ለ/ ደረጃ ሶስት የተለያዩ የሙዚቃ መሣሪያ ተጨዋቾች፣ የድምፅና


ኤሌክትሪክ ቴክኒሻን፣

ሐ/ ደረጃ ሁለት ድምፃዊያን፣ የመድረክ መሪና አስተዋዋቂ፣

47
መ/ ደረጃ አንድ ወንድና ሴት ተወዛዋዦች፣ ገንዘብ ያዥ፣ የሒሳብ
ሠራተኛ፣

2. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 1 በደረጃ አንድ፣ ሁለትና ሶስት ውስጥ የተካተቱት

የሥራ መደቦች እኩል ዋጋ ያላቸው ሥራዎች ናቸው ተብሎ ስለሚታመን


እኩል መነሻ ደመወዝ ይኖራቸዋል፣
3. በወረዳ፣ በዞንና በከተማ አስተዳደር ደረጃ የሥራ መደቦቹ የደመወዝ
መጠንና የሚጠይቁት የትምህርት ዝግጅት፣ ተፈላጊ ችሎታና የሥራ
ልምድ ዝርዝር መነሻ በዚህ መመሪያ በአባሪ የተያያዘው ይሆናል፣ ነገር
ግን የቀረበውን መነሻ አስፈፃሚው መ/ቤት የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ
ባገናዘበና በተጠና አግባብ ማሻሻል ይችላል፣
4. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 3 የተገለፀው ተግባራዊ የሚሆነው ለበላይ ጠባቂ ቦርድ

ቀርቦ ቦርዱ ሲያፀድቀው ብቻ ነው፣ እንዲሁም ወደፊት የሚደረግ የደሞዝ


ጭማሪ ወይም የክፍያ ማሻሻያ ቢኖር በአስፈፃሚው መ/ቤት መጠናትና
ለቦርዱ ቀርቦ በቦርዱ መፅደቅ አለበት፣
5. የባህል ቡድን በየወሩ መጨረሻ ለሠራተኞቹ ወይም ለሕጋዊ ወኪሎቻቸው

የደመወዝ ክፍያ የሚፈፅ ሲሆን የማንኛውም ሠራተኛ ደመወዝ በፍርድ


ቤት ትዕዛዝ ወይም በበላይ ጠባቂ ቦርድ ውሳኔ ካልሆነ በስተቀር ሊያዝ
ወይም ሊቆረጥ አይችል፣
6. ለማንኛውም የባህል ቡድን ሠራተኛ ለሥራ መስክ ሲወጣ የመስክ አበልና

በማንኛውም መድረክ ቡድኑ ዝግጅት ሲያቀርብ የመድረክ የጽዳትና


የመዋቢያ አበል ይከፈላል፣ የሁለቱም አበል ኣይነቶች መጠን በእስፈፃሚው
መ/ቤት አቅራቢነት የበላይ ጠባቂ ቦርድ በሚወሰነው መሠረት ይሆናል፣

29. የባለሙያ ምልመላ፣ መረጣና ቅጠር አፈፃፀም

48
1. በማንኛውም የባህል ቡድን የሥራ መደብ ላይ የሚፈፀም የሰው ኃይል
የቅጥር ዓይነት ዘላቂነት የሌለው ወይም የኮንትራት ቅጥር ሆኖ የሚፈፀም
ነው፣
2. የማንኛውም የባህል ቡድን የሰው ኃይል ምልመላ፣ መረጣና ቅጥር
የሚካሄደው ባለቤቱ በሆነው አስፈፃሚ መ/ቤት ሲሆን ቅጥሩ ተግባራዊ
የሚሆነው ለበላይ ጠባቂ ቦርድ ቀርቦ በቦርዱ ውሳኔ ሲፀድቅ ብቻ ይሆናል፣
3. አስፈፃሚው መ/ቤት ክፍት የሥራ መደቦችን በሠራተኛ ማስያዝ የሚችለው
በቅጥር ወይም በዝውውር ወይም በደረጃ ዕድገት ሲሆን ማስታወቂያ
ማውጣት አመልካቾችን መጋበዝ በፈተና ማወዳደርና የሥራ መደቡ
የሚጠይቀውን ተፈላጊ ችሎታ አሟልቶ በውድድሩ ብልጫ ያገኘውን
በመምረጥ ብቻ ነው፣
4. የክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ አወጣጥ፣ አመልካቾች አመዘጋገብ፣
የፈተና አዘገጀጀት፣ የፈተና አሰጣጥና ውጤት አገላለጽ የመንግሥት
ሠራተኞች የቅጥር አፈፃፀም መመሪያን በተከተለ አግባብ የሚፈፀም
እንዲሆን በአስፈፃሚው መ/ቤት መደረግ አለበት፣
5. በክፍት የሥራ መደብ ለመቀጠር የማያስችሉ ሁኔታዎች ዕድሜ ከ18
ዓመት በታች መሆን፣ ወንጀል ፈፅሞ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት
የተፈረደበት መሆንና ከሌላ የባህል ቡድን በዲሲኘሊን ጉድለት ከሥራ
ተሰናብቶ ከተሰናበተ ሁለት ዓመት ያልሞላው ሆኖ መገኘት ብቻ ሲሆኑ
በሌላ በማንውም ሁኔታ በሥራ ፈላጊ ተወዳዳሪዎች መካከል ልዩነት
ማድረግ ክልክል ነው፣
6. ለክፍት የሥራ መደቡ በውድድር ብልጫ የተመረጠው ተወዳዳሪ የሥራ
ልምድ፣ የትምህርት፣ ከወንጀሎች ነፃ መሆኑን የሚያረጋግጥ የፖሊስ
ማስረጃና ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን የማቅረብ ግዴታ አለበት፣ በሃሰተኛ
ማስረጃ ቅጥር መፈፀም ወይም እንዲፈፀም ማድረግ ክልክል ነው፣

49
7. የክፍት የስራ መደቡ ምደባ በቦርዱ ከፀደቀ ለተመረጠው እጩ የሥራ
መደቡን መጠሪያ፣ የኮንትራት ቅጥር መሆኑን፣ የተመደበበትን ደረጃ፣
ደመወዙንና ሥራውን የሚጀምርበትን ቀን የሚገልፅ በባህል ቡድኑ ኃላፊ
የተፈረመ የቅጥር ደብዳቤ ከሚያከናውነው የሥራ ዝርዝር መግለጫ ጋር
መሰጠት አለበት፣
8. በአንድ የባህል ቡድን ውስጥ ተፈላጊ ችሎታውን እስካሟሉ ድረስ ከዝቅተኛ
የሥራ ወደ ከፍተኛ የሥራ መደብ ሰራተኞችን በደረጃ ዕድገት አወዳድሮ
መመደብ ይቻላል፣ ነገር ግን ምደባው ማስታወቂያ ወጥቶ ተወዳዳሪዎችን
በመጋበዝ፣ በማወዳደርና ብልጫ ያላቸውን በመምረጥ የሚፈፀም ነው፣
9. አስፈፃው መሥሪያ ቤት ለሥራው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ከሌላ የባህል
ቡድን ባለሙያን በተመሳሳይ የሥራ መደብ ላይ በዝውውር ተቀብሎ
በመመደብ ማሠራት ይችላል፣ ነገር ግን በዝውውሩ ላኪው የባህል ቡድን
እንዲሁም ሠራተኛው ስምምነታቸውን በጽሁፍ መግለፅና ማሳወቅ
አለባቸው፣

30. መደበኛ የሥራ ሰዓት

1. የባህል ቡድን ሠራተኞች መደበኛ የሥራ ሰዓት፣ የሥራ መግቢያና


መውጫ እንደ ሥራው ሁኔታና የሥራ አመቺነት በባህል ቡድኑና
በአስፈፃሚው መ/ቤት የሚወሰን ሆኖ ነገር ግን በሣምንት ሠራተኞቹ
የሚሰሩበት ሠዓት ከ39 ሰዓት መብለጥ የለበትም፣
2. በኪነ ጥበብ የሙያ ባህሪ አስገዳጅነት በሕዝብ በዓላት፣ በሣምንት የእረፍት

ቀናት ወይም በመንግሥት ውሣኔ መሥሪያ ቤቶች ዝግ ሆነው


በሚውሉበት ቀን፡ ቡድኑ ለሕዝብ ትርኢት የሚያቀርብ ከሆነና ማንኛውም
ሠራተኛ እንዲሠራ ከታዘዘ የመሥራት ግዴታ አለበት፣ አለመስራት
እርምጃ የሚያስወስድ ይሆናል፣
50
3. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 2 በተደነገገው አግባብ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለሠራ

ማንኛውም ሠራተኛ በሠራተኛው ምርጫ መሠረት የማካካሻ እረፍት ሰዓት


ይሰጣል፣ ቢሆንም የማካካሻ እረፍት ስለሚሰጥበት ሁኔታ ቡድኑ ዝርዝር
መመሪያ ማውጣት ይችላል፣

31. የዓመት ዕረፍት ፈቃድና ልዩ ልዩ ፈቃዶች

1. ማንኛውም የባህል ቡድን ሠራተኛ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ያገኛል፣


የዓመት ዕረፍት ፈቃድ የሚሰጠው ሠራተኛው ለተወሰነ ጊዜ በማረፍ
አገልግሎቱን በታደሰ መንፈስ እንዲቀጥል ለማስቻል ሲሆን የዓመት
ዕረፍት ፈቃድ በገንዘብ አይለወጥም፣
2. በአንድ የበጀት ዓመት ውስጥ ለማንኛውም የባህል ቡድን ባለሙያ የሚሰጥ
የዓመት ዕረፍት ፈቃድ የ25 የሥራ ቀናት እረፍት ሲሆን የዓመት ዕረፍት
ፈቃዱ የሚሰጠው ለሁሉም የባህል ቡድኑ ባለሙያዎች በአንድ ወቅት
ወይም በተመሳሳይ ጊዜ ወይም በአንድ ላይ መሆን አለበት፣
3. የቡድን ኃላፊ በበጀት ዓመቱ ባለሙያዎች የዓመት ዕረፍት ፈቃድ
የሚወጡበትን ጊዜ የባህል ቡድኑን ዓመታዊ የስራ ዕቅድና የባለሙያዎቹን
ፍላጎት ባመዛዘነ አግባብ በፕሮግራም እንዲያዝ የማድረግና ፕሮግራሙን
ሁሉም ባለሙያዎች በግልፅ እንዲያውቁት የማድረግ ኃላፊነት አለበት፣
4. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 3 መሠረት በተያዘው ፕሮግራም በቡድኑ የሥራ
አስገዳጅነት ምክንያት ባለሙያዎቹ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ካልተሰጣቸው
ለሌላ አመቺ ጊዜ ተዛውሮ መሰጠት አለበት፣
5. ሠራተኛው የኣመት ዕረፍት ፈቃዱን በሚወስድበት ጊዜ በዕረፍት ላይ
የሚቆይበትን ወር ደመወዙን በቅድሚያ ሊወስድ ይችላል፣ ይሁን እንጂ
ፈቃድ ወስዶ ሥራውን በገዛ ፈቃዱ ያቋረጠ ሠራተኛ አገልግሎት

51
ያልተሰጠበትን በፈቃድ ላይ እያለ የተከፈለውን ደመወዝ እንዲመልስ
ይደረጋል፣
6. ለማንኛዋም ነፍሰጡር የሆነች የባህል ቡድን ባለሙያ እወልዳለሁ ብላ
ከገመተችበት ቀን በፊት 3ዐ ተከታታይ ቀናት የቅድመ ወሊድና
ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 30 ተከታታይ ቀናት የድህረ ወሊድ በድምሩ 60
ቀናት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣታል፣ እንዲሁም የተወሰነውን
የወሊድ ፈቃድ ከጨረሰች በኋላ ብትታመምና ተጨማሪ ፈቃድ
የሚያስፈልጋት መሆኑ በሐኪም ከተረጋገጠ የሕመም ፈቃድ መውሰድ
ትችላለች፣
7. ማንኛውም የባህል ቡድን ባለሙያ በሕመም ምክንያት ሥራ መሥራት
ያልቻለ እንደሆነና መታመሙን ለኃላፊው ካሳወቀ የሕመም ፈቃድ
ይሰጠዋል፣ ይሁን እንጂ ከስድስት ቀን በላይ በሕመሙ ምክንያት ከሥራ
የቀረ እንደሆነ ለመታመሙ የሕክምና ማስረጃ ማቅረብ አለበት፣
8. ከላይ በንዑስ አንቀጽ 7 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ ባለሙያው ህመሙ
ጠንቶበት በሐኪም ትእዛዝ ከወር በላይ በህክምና ላይ ከቆየ ለመጀመሪያው
አንድ ወር ከሙሉ ደመወዝ ጋር፣ ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት ከግማሽ
ደመወዝ ጋር እና ለመጨረሻው አንድ ወር ያለ ደመወዝ የሕመም ፈቃድ
ይሰጠዋል፣
9. ማንኛውም የባህል ቡድን ባለሙያ ለሐዘን፣ ለጋብቻ፣ ለፈተና እና
ለመሳሰሉት በአንድ የበጀት ዓመት ውስጥ የአምስት ቀን ፈቃድ እንዲሁም
ከፍርድ ቤት መጥሪያ ሲደርሰው የተጠራበት ጉዳይ ለሚጠይቀው ጊዜ
ደመወዝ ሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጠዋል፣

32. የባህል ቡድን ባለሙያ ሥነ-ምግባር ግዴታዎች

52
1. ማንኛውም የባህል ቡድን ባለሙያ የሚከተሉትን ..የሙያ ሥነግባሮች
የመተበቅ ኃላፊነትና ተግባራዊ የማድረግ ግዴታዎች አሉበት፡-
ሀ/ ለባህል ቡድኑ ታማኝ የመሆን፣ መላ ጉልበቱንና ኪነ ጥበባዊ
የፈጠራ ችሎታውን ለቡድኑ አገልግሎት ማዋል፣
ለ/ በሥራ ዝርዝሩ መሠረት የሚሰጡትን የሥራ እቅዶች እና ሌሎች
ከሥራው ጋር አግባብ ያላቸው የሚሰጡትን ትዕዛዞች መፈፀም፣
ሐ/ ከባህል ቡድን ባልደረቦቹ ጋር ተግባብቶ የመሥራትና
በማንኛውም የቡድን ተግባር ላይ የነቃ ተሳትፎ የማድረግ፣
መ/ የአካባቢውን ሕብረተሰብ፣ የክልሉን ብሄር፣ ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች ባህሎች፣ ቅርሶች፣ ቋንቋዎች፣ ታሪኮች እና ሕጎች
የሚፃረር ድርጊት ያለመፈጸም፣
ሠ/ የቡድኑን ሥራ የሚመለከቱ በበላይ ጠባቂ ቦርድና በአስፈፃሚው
መ/ቤት የሚወሰኑና የሚተላለፉ ውሳኔዎችን፣ ደንቦችና
መመሪያዎችን ማክበር፣ በብቃት መፈፀም አለበት፡
ረ/ ማንኛውንም የቡድኑን የጋራ ንብረት ደህንነት የመንከባከብ
የመጠበቅ፣ ለሥራው ማከናወኛ የተሰጡትን የግል መሣሪያዎችና
መገልገያዎች በአግባቡ የመጠበቅና የመጠቀም ኃላፊነት አለበት፣
ሰ/ በማንኛውም የቡድኑ ንብረትና ለሥራው ማከናወኛ በተሰጡት
መሣሪያዎችና መገልገያዎች ላይ በቸልተኝነት ወይም ሆን ተብሎ
በሚፈፀመው ጉዳት ወይም ጥፋት በዕዳ ተጠያቂ የመሆንና
የመተካት ግዴታ አለበት፣
2. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 1 ላይ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አስፈፃሚው
መሥሪ ቤት ከባህል ቡድን ኃላፊ ጋር በመሆን ባለሙያዎች
የሚተዳደሩበትን፣ ከአካባቢውና ከሙያው ሁኔታጋር በተገናዘበ አግባብ
ዝርዝር የሥነ-ሥግባር ደንብ በማውጣት በበላይ ጠባቂ ቦርድ አፀድቆ
ተግባራዊ ማድረግ ይችላል፣
53
33. የዲሲኘሊን ጥፋት እርምጃዎችና የቅሬታ አቀራረብ

1. የዲሲኘሊን ቅጣት ዓላማ የባህል ቡድን ባለሙያው በፈፀመው የዲሲኘሊን

ጉድለት ተፀፅቶ እንዲታረምና ብቁ ሠራተኛ እንዲሆን ለማስቻል ወይም


የማይታረም ሆኖ ሲገኝ ከቡድኑ ለማሰናበት ነው፣
2. በባህል ቡድን ውስጥ ማንኛውም ባለሙያ የሚከተሉት ጥፋቶች ከፈፀመና

መፈፀሙ በማስረጃ ከተረጋገጠ የቀላል ወይም የከባድ የዲሲኘሊን ቅጣት


እርምጃ የሚያስወስኑበት ይሆናሉ፡-

ሀ/ የሥራ ትዕዛዝ ባለማክበር፣ በቸልተኝነት፣ በመለገም ወይም ሆን


ብሎ ከሥራ ከትርኢት ማቅረቢያ መድረክ መቅረት፣በትርኢት
ማቅረቢያ ሥራ ቦታ ለሕዝብ ሞራል ተቃራኒ የሆነ ድርጊት
መፈፀም ፣
ለ/ ባልተጨበጠ አሉባልታ ባለሙያን ከባለሙያ፣ ባለሙያን ከኃላፊና
ከአስፈፃሚ መ/ቤት ማጋጨት፣
ሐ/ የቡድኑን የአሠራር ሥነ-ሥርዓትን ወይም የወጡ ደንብ
መመሪያና የተላለፉ የበላይ ውሳኔዎችን ባለመከተል በሥራ ላይ
በደል ማድረስ፣
መ/ የተሰጠ ሥራን ሆን ብሎ ማዘግየት ወይም በቡድንና በጋራ
ሥራ ላይ ሌሎችን ማጉላላት ፣
ሠ/ ባለሙያዎችን በቡድን መከፋፈል፣ ሥራ እንዳይሰራ ሆን ብሎ
ማወክ ወይም ከሚያውኩት ጋር መተባበር፣
ረ/ በቀላል የዲሲኘሊን ቅጣት እርምጃዎች ባለመታረም ያለበቂ
ምክንያት በተደጋጋሚ ከሥራ መቅረብ ወይም የሥራ ሰዓት
አለማክበር፣

54
ሰ/ በሥራ ቦታ በጠብ አጫሪነት መደባደብ፣ በልማዳዊ ስካር ወይም
በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ በመመረዝ ሥራን መበደል፣
ሸ/ ጉቦ መቀበል ወይም እንዲሰጠው መጠየቅ ፣ የማታለል ወይም
የማጭበርበር ድርጊት መፈፀም ፣በቡድኑ ውስጥ ወይም በሌላ
የሌብነት ወይም የእምነት ማጉደል ድርጊት መፈፀም ፣
ቀ/ በቡድኑ የጋራ ንብረት ላይ ወይም ለግል መገልገያ በተሰጠ
ንብረት ላይ ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ጉዳት ማድረግ ፣
በ/ ኃላፊነትን ወይም የሥራ ድርሻን አለአግባብ መጠቀም በሴቶች
ወይም በሌላ ባልደረባ ተፅኖ መፍጠር፣
ተ/ የሴሰኝነት ወይም በሥራ ቦታና ባልደረቦች ላይ ፆታዊ ጥቃት
መፈፀም ፣
ቸ/ በዚህ አንቀፅ ከተዘረዘሩት ጋር ተመሳሳይ ክብደት ያለው ሌላ
የዲሲኘሊን ጉድለት መፈፀም፡፡
3. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 2 የተዘረዘሩንና መሰል የዲሲኘሊን ጉድለቶችን የፈፀመ
ማንኛውም የባህል ቡድን ባለሙያ እንደጥፋቱ ክብደት ተመዝኖ
ከሚከተሉት ቅጣቶች አንዱ ሊወሰንበት ይችላል ፣

ሀ/ ለቀላል የዲሲፕሊን ጥፋቶች የቃል ማስጠንቀቂያና የጽሑፍ


ማስጠንቀቂያ ፣

ለ/ ለከባድ የዲሲፕሊን ጥፋቶች የገንዘብ መቀጮ ወይም የአንድ ወር


ደመወዝ መቀጮና ከሥራ ማሰናበት፣

3. ማንኛውም የባህል ቡድን ባለሙያ በዲሲኘሊን ከተቀጣ በኋላ ቅጣቱ


በሪኮርድገት ሊቆይና ሊጠቀስበት የሚችለው ፣
ሀ/ ቀላል የዲሲኘሊን ቅጣት ከሆነ ቅጣቱ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ
ለአንድ ዓመት ፣

55
ለ/ ከባድ የዲሲኘሊን ቅጣት ከሆነ ቅጣቱ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ
ለሁለት ዓመት፣ ይሆናል፡፡

4. የቡድን ኃላፊ ከላይ በንዑስ አንቀፅ 2 የተዘረዘሩትን ወይም ተመሳሳይ


የሆኑ ጥፋቶችን የፈፀመ ባለሙያን ጉዳይ ጥፋቱ ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ
ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ በተጨባጭ ማስረጃ አስደግፎ ለአስፈፃሚው
መ/ቤት የማቅረብ ኃላፊነትና ግዴታ አለበት፣ ካልሆነ ተጠያቂነት
የሚያስከትልበት ሊሆን ይችላል፣
5. አስፈፃሚው መ/ቤት ከላይ በንዑስ አንቀፅ መሠረት በቡድን ኃላፊ
የሚቀርብለትን የዲሲፕሊን ጉዳይ በቀረበለት በአምስት ቀናት ባልበለጠ ጊዜ
ውስጥ መርምሮ ቀላል የዲሲፕሊን ጥፋት ነው ብሎ ካመነ የቀላል
ዲሲፕሊን እርምጃ በቡድን ኃላፊው እንዲወሰድ የመወሰን እና ከባድ
የዲሲፕሊን ጥፋት ነው ብሎ ካመነ ለቦርዱ በማቅረብ እንዲወሰንበት
የማድረግ ኃላፊነት አለበት፣
6. የበላይ ጠባቂ ቦርድ ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት ተብሎ በአስፈፃሚው መ/ቤት
ለቀረበለት ጉዳይ በቀረበለት ቀን ጀምሮ ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ
ውሳኔ ይሰጣል፣ የቦርዱን ውሳኔ አስፈፃሚው መ/ቤትና የቡድን ኃላፊው
ውሳኔው ከተላለፈበት በአምስት ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ
እንዲሆን የማድረግ ግዴታ አለባቸው፣
7. ማንኛውም የባህል ቡድን ባለሙያ በተከሰሰበት የዲሲፕሊን ጥፋት
በሚወሰንበት ቀላልም ሆነ ከባድ ቅጣት ላይ ቅሬታ ለአስፈፃሚው መ/ቤት
ወይም ለቦርዱ የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
8. አስፈፃሚው መ/ቤት ወይም ቦርዱ ቅሬታው በማስረጃ የተደገፈና አግባብነት
ያለው ሆኖ ካገኘው ያስተላለፈውን ውሳኔ የመሻር ወይም የማሻሻል እርምጃ
ሊወስድ ይችላል፤

56
34. የሥራ አፈፃፀም ምዘናና የሥልጠና ሁኔታ

1. በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የባህል ቡድን በየዓመቱ የሠራተኞቹን የሥራ


አፈፃፀም ምዘና ማካሔድ ያለበት ሲሆን የሥራ አፈፃፀም ምዘና ዓላማ
የሚከተለው መሆን አለበት፡-
ሀ/ ሠራተኞች ሥራቸውን በሚጠበቀው መጠን፣ የጥራት ደረጃ፣ ጊዜ
እና ውጪ በተሟላ ሁኔታ እንዲያከናውኑ ለማድረግ ፣
ለ/ የሠራተኞችን ጠንካራና ደካማ ጐኖች በመለየት ቀጣዩ የሥራ
አፈፃፀማቸው እንዲሻሻል በማድረግ ውጤታማ እንዲሆኑ
ለማብቃት ፣
ሐ/ የሠራተኞችን የስልጠናና የመሻሻል ፍላጐት በትክክል ለይቶ
ለማወቅ ፣
መ/ በውጤት ላይ የተመሠረተ ማትጊያ ለመስጠት ፣
ሠ/ በተጨባጭ መረጃ ላይ ተመስርቶ አስተዳደራዊ ሣኔዎች
እንዲሰጥ ለማስቻል ነው፣
2. የቡድኑ ባለሙያዎች የሥራ አፈፃፀም ምዘና በቡድን ኃላፊው ግልፅ የሆነ
ሥርዓትን በመከተል በየወሩ መፈፀም ያለበት ሲሆን አስፈፃሚው መ/ቤት
የሥራ አፈፃፀም ምዘና መመሪያ ያወጣል፣
3. ማንኛውም የባህል ቡድን ባለሙያ የሥራ ችሎታውን አሻሽሎ በተመደበበት
ሥራ ላይ የተሻለ ውጤት ለማስገኘት እንዲችል ወይም በሙያው ለበለጠ
አገልግሎት ዝግጅት እንዲኖረው ሥልጠና እንዲያገኝ ይደረጋል፣
4. የቡድን ኃላፊና አስፈፃሚው መ/ቤት ቡድኑ ወይም እያንዳንዱ ባለሙያ
የሚያስፈልገውን ሥልጠና በየጊዜው በክትትል በመለየትና በማጥናት
ሥልጠናው የሚሰጥበትን ሁኔታ ጭምር ለቦርዱ አቅርቦ አስፈላጊውን
በጀት በማስፈቀድ ቡድኑ ወይም ባለሙያው ሥልጠና እንዲያገኝ የማድረግ
ኃላፊነት አለባቸው፣

57
35. የሥራ ውል መቋረጥ ወይም ከሥራ መሰናበት

1. ማንኛውም የባህል ቡድን ባለሙያ በማንኛውም ጊዜ በገዛ ራሱ ፍቃድ


ሥራውን መልቀቅ ይችላል፣ ይሁን እንጂ አፈፃፀሙ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን
ድንጋጌዎች በተከተለ አግባብ መሆን አለበት፡-

ሀ/ ሥራውን በገዛ ፈቃዱ የሚለቅ መሆኑን በጽሁፍ ለኃላፊው


ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ ከአንድ ወር በኋላ ሊለቅ ይችላል፣

ለ/ በዚህ ንዑስ አንቀፅ ከላይ በፊደል ተራ ቁጥር ሀ የተገለፀው


ቢኖርም የቡድን ኃላፊውና አስፈፃሚው መ/ቤት ባለሙያው
ለሥራው እጅግ አስፈላጊና በቀላሉ ለመተካት የማይቻል መሆኑን
ካመኑበት የመልቀቂያውን ጥያቄ ባለሙያው ካመለከተበት ቀን
ጀምሮ ከሦስት ወር ለማይበልጥ ጊዜ ሊያራዝሙት ይችላሉ፣

ሐ/ ከላይ በፊደል ተራ ቁጥር ሀ እና ለ ከተገለፀው ውጪ ሥራውን


የለቀቀ ማንኛውም የባህል ቡድን ባለሙያ ግዴታውን ባለመወጣቱ
ለሚደርሰው ጉዳት እንደ ተገቢነቱ በፍትሐብሔር እና በወንጀል
ሕግ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፣

2. በህመም ምክንያት የሚፈጠር ስራ ማቋረጥን በሚመለከት በዚህ መመሪያ


አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 8 በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ለመመለስ
ካልቻለ በሕመም ምክንያት አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ይደረጋል፣
3. በችሎታ ማነስ ምክንያት ባለሙያ ሥራውን እንዲያቋርጥ ይደረጋል፣ ነገር
ግን ተግባራዊ የሚሆነው ባለሙያው በተመደበበት ሥራ ላይ ውጤታማ
ሳይሆን ሲቀርና ይህም የሥራ አፈፃፀም ውጤቱ በተከታታይ ሶስት ወራት

58
ከአጥጋቢ በታች መሆኑ ሲረጋገጥ እና ስልጠና እንዲወስድ ተደርጎ በድጋሜ
ውጤታማ መሆን ከተሳነውና ቀርቦ በቦርዱ ሲወሰን ብቻ ነው፣

4. ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በሥራ ገበታው ላይ የሚቀር ወይም


ሥራውን የሚያቋርጥ ባለሙያ ማሰናበትን በሚመለከት በሚከተለው
አግባብ ተፈፃሚ ይደረጋል፡-
ሀ/ ባልታወቀ ምክንያት ባለሙያው ለተከታታይ አሥር ቀናት
ከመደበኛ የሥራ ቦታው ላይ ከተለየ በተከታታይ አስር ቀናት
ልዩነት ለሁለት ጊዜ በማስታወቂያ ጥሪ ይደረጋል፣
ለ/ በመጀመሪያው ወይም በሁለተኛው የጥሪ ማስታወቂያ ቀርቦ
ሪፖርት ካደረገና ለቀረበት ምክንያት የሚያቀርበው ማስረጃ
በኃላፊውና በአስፈፃሚው መ/ቤት ከታመነበት ሥራውን
እንዲቀጥል ይደረጋል፣ ነገር ግን የሚያቀርበው ማስረጃ አሳማኝ
ካልሆነ ይሰናበታል፣
ሐ/ በሁለቱም የጥሪ ማስታወቂያ ተጠርቶ ለቡድኑ ሪፖርት ካላደረገና
ከአንድ ወር በላይ በሥራ ገበታው ላይ ካልተገኘ ያለተጨማሪ
ሥነ-ሥርዓት ከሥራ እንዲሰናበት ይደረጋል፣
5. በዲሲፕሊን ቅጣት ውሳኔ ማንኛውም ባለሙያ ከሥራው እንዲሰናበት
ሊደረግ ይችላል፣ ነገር ግን የሚሰናበተው በዚህ መመሪያ አንቀፅ ንዑስ
አንቀፅ መሠረት የተላለፈበት የዲሲኘሊን ቅጣት ከስራ መሰናበት ከሆነና
በቦርዱ ከፀደቀ እንዲሁም ባለሙያው ለቦርዱ ቅሬታ ወይም ይግባኝ ጠይቆ
ቅጣቱ ያልተሸሻለለት ወይም ያልተሠረዘለት እንደሆነ ብቻ ነው፣
6. በሞት ምክንያት የባለሙያ መነጠል ሲያጋጥም ባለሙያው ከሞተበት ቀን
ጀምሮ አገልግሎቱ ይቋረጣል፣ ቢሆንም አገልግሎቱ በሞት ምክንያት
የተቋረጠበት ባለሙያ የሞተበት ወር ሙሉ ደመወዙ ለትዳር ጓደኛው
ወይም ለህጋዊ ወራሾቹ ይከፈላል፣
59
7. ማንኛውም ባለሙያ በሥራ ላይ እያለ ወይም በማናቸውም ምክንያት
ከስራው ሲሰናበት የሥራ ልምድ ማስረጃ ከጠየቀ ሲሠራ የነበረውን የሥራ
ዓይነት፣ የአገልግሎት ዘመኑና ሲከፈለው የነበረውን ደመወዝ የሚገልፅ
የአገልግሎት የምስክር ወረቀት በቡድን ኃላፊው ይሰጠዋል፣

36. የሥራ ዕቅድና ሪፖርት አቀራረብና የመረጃ አያያዝ

1. የባህል ቡድን ኃላፊ ከአስፈፃሚው መ/ቤት ጋር በመሆን የበጀት ዓመቱን


የባህል ቡድኑን የሥራ ዕቅድ የማውጣትና ተግባራትን በቅዱ መሠረት
እንዲከናወን ማድረግ አለበት፣
2. የባህል ቡድኑን ወርሐዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የ6 ወርና ዓመታዊ የዕቅድ
አፈፃፀም ሪፖርት በቡድን ኃላፊ ተዘጋጅቶ ለአስፈፃሚው መ/ቤት
ይቀርባል፣
3. አስፈፃሚው መሥሪያ ቤት የባህል ቡድን የሩብ ዓመት ዋና ዋና የዕድ
ክንውን አፈፃፀም ሪፖርት ለቦርዱ ያቀርባል፣
4. ማንኛውም የሥራ ክንውን ሪፖርት ሲቀርብ የፋይናንስ እንቅስቃሴን
የሒሳብ መግለጫ ባካተተ አግባብ ተዘጋጅቶ መሆን ይኖርበታል፣
5. የባህል ቡድን ኃላፊአስፈፃሚው መ/ቤትና የባህል ቡድን ኃላፊ ለእያንዳንዱ
የባህል ቡድን ሠራተኛ አግባብነት ያላቸውን መረጃዎች የሚይዝ የግል
ማህደር እንዲኖር ያደርጋሉ፣
6. ማንኛውም የባህል ቡድን ሠራተኛ በግል ማህደሩ ውስጥ የሚገኙትን
ማስረጃዎች የመመልከት ወይም ቅጂውን የመውሰድ መብት አለው፣
7. የቡድን ኃላፊ እያንዳንዱን የባህል ቡድን ሠራተኛ የሚመለከቱ
ስታትስቲካዊ መረጃዎች አደራጅቶ የመያዝና በማንኛውም ወቅት
በአስፈፃሚው መ/ቤትና በቦርዱ ሲጠየቅ የማቅረብ ኃላፊነት አለበት፣

60
ክፍል አራት

የኪነ ጥበባት ሙያ ዘርፎች ጥቃቅንና አነስተኛ


ኢንተርፕራይዞች

አደረጃጀት፣ ድጋፍ አስጣጥና ክትትል

37. የኪነ ጥበባት የሙያ ዘርፎች ጥቃቅንና አነስተኛ


ኢንተርፕራይዝ ዓይነቶች

1. በኪነ ጥበብ የሙያ ዘርፍ ተቋቁመው የሚንቀሳቀሱ ኢንተርፕራይዞች


ዓይነቶች በኢትዮጵ የንግድ ሥራ ፈቃድ መሥጫ መመሪያ መሠረት
የፈቃድ መሥጫ መደብ ቁጥር የተሰጣቸውንና በአስፈፃሚው መ/ቤት
የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የሚሰጣቸውን የኪነ ጥበብ የሙያ ዓይነቶች
በሙሉ ይመለከታል፣
2. ከላይ በንዑስ ንዑሥ አንቀፅ 1 የተገለፀው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ

ሆኖ በአሁኑ ወቅት በክልላችን ካለው ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር

61
በየደረጃው በመቋቋም የሚንቀሳቀሱና ተቋቁመው ሊንቀሳቀሱ የሚችሉት
የኪነ ጥበብ የሙያ ዘርፎች ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ዓይነቶች
ቀጥሎ የተዘረዘሩት ይሆናሉ ፡-
1) የሙዚቃ /የፊልም፣ የትያትር እና ሌሎች የኪነጥበብ/መሣሪያዎች
መፈብረክ /ማምረት/ 39220
2) የሙዚቃ /የፊልም የቲያትር እና ሌሎች ኪነጥበብ/መሳሪያዎች
የጅምላ ንግድ 61332
3) የተቀዱ /ኦሪጅናል/ ካሴቶችና ሲዲዎች ቪሲዲ እና ዲቪዲዎች
የጅምላ ንግድ 61335
4) የሙዚቃ /የፊልም የቲያትር እና ሌሎች ኪነጥበብ/መሳሪያዎች
የችርቻሮ ንግድ 62396
5) የተቀዱ /ኦሪጂናል/ ካሴቶች ሲደወችና ቪሲዲዎች እና ተዛማጅ
ምርቶች የችርቻሮ ንግድ 61335
6) የሙዚቃ መሣሪያዎች አስመጭ /የሙዚቃና የፊልም የትያትር
እና ሌሎች የኪነጥበብ/ 65332
7) የተቀዱ /ኦሪጂናል/ ካሴቶች ሲደዎችና ቪሲዲዎች እና ተዛማጅ
ምርቶች አስመጭ 65333
8) የሙዚቃና መሣሪያዎች ላኪ /የሙዚቃና የፊልም የትያትር እና
ሌሎች የኪነጥበብ/ 66232
9) የተቀዱ /ኦሪጂናል/ ካሴቶች ሲዲወች ቪሲዲና ዲቪዲዎች ላኪ
10) የባህል እና የኪነጥበብ ኮንሰልታንሲ/ የማማከር አገልግሎት
8815
11) የባህልና ኪነጥበብ ትምህርት ትያትር፣ ሙዚቃ፣ፊልም፣
ሞዴሌንግ፣ ዳንስ/ውዝዋዜ፣ የቪዲየና ፎቶግራፍ፣ የስዕልና ደዛይን
ወዘተ ሠርከስ ት/ቤት 9222

62
12) ተንቀሳቃሽ የቴአትርና የቪዲዮ ፊልም ሥራና ማከፋፈል
96111
13) ተዛማጅ ሥራዎች የፊልምና የካሴት ክር ለሌሎች
ኢንዱስትሪዎች ማከራየት፣ ፕሮግራም ማስያዝ መስጠትና
ማከማቸት 96112
14) የፊልም ሥራ ዝግጅት፣ የፊልም ፕሮዳክሽን ፣ ሲኒማ ቤት
፣ የፊልም ስቱዲዮ፣ የፊልም ቀረጻ 96113
15) የትያትር ሥራ ፣ ትያትር ቤት፣ የትያትር ፕሮዳክሽን 96114
16) ሌሎች ሌላ ቦታ ያልተጠቀሱ የተንቀሳቃሽ ፊልም ፊልም
የቪዲዮ ቀረፃና ማከፋፈል፣ የድምጽና የምስል ፕሮዳክሽን ስርጭት
/የሬድዮና ቴሌቪዥን ተዛማጅ የኪነጥበብ ስራዎች/96119
17) የፊልምና ቴአትር /ሲኒማ በአዳራሽ ማሳየት ስራዎች 96121
18) በግቢ ውስጥ የሲኒማ የማሳየት ስራ በመኪና በሌላ መንገድ
96122
19) የድራማ የሙዚቃና እና ሌሎች ተዛማጅ የኪነጥበብ ሥራዎች
የፕሮሞሽን አገልግሎቶች /የትያትር፣ ስነጽሁፍ፣ የሙዚቃ፣
ፊልም፣ የስዕልና ቅርፃቅርጽ ወዘተ/96140
20) የሙዚቃ ባንድ ፣ ሚኒ ባሕላዊ ባንድ ፣ መለስተኛ ባሕላዊ
ባንድ፣ ሁለገብ ባሕላዊ ባንድ 96141
21) ሙዚቃ መሣሪያ ኪራይ /የሙዚቃ፣ የፊልም የትያትር ሌሎች
የኪነጥበብ መሣሪያዎችን ማከራየት፣ ፕሮግራም ማስያዝ፣
መስጠትና ማከማቸት ስራ 96142
22) የሙዚቃ መሣሪያ አጫዋች /ዲ²/96143
23) ቀረጻ ስቱዲዮ የሙዚቃ 96144
24) የስዕልና ቅርፃ ቅርጽ ጋለሪ 96145
25) የስዕልና ቅርፃ ቅርጽ ስቱደዮ 96146
63
26) ሌሎች የማዝናናት ስራዎች ልዩ ዝግጅት ማስተባበር
(Eventorganizer)ፌስቲቫሎች ኤግዚቪሽን ኮንፍረንሶች 96190
27) የባህል ማዕከል 96323
28) የፋሽንና የቁንጅና ትርኢት ስራዎች 99028

38. የኢንተርፕራይዞች አመሠራረት

1. በኪነ ጥበባት የሙያ ዘርፎች ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች


አስፈላጊውን የሕግ መስፈርት ካሟሉ በወረዳ፣ በከተማ አስተዳደር፣ በዞን
ወይም በክልል ደረጃ መቋቋምና መንቀሳቀስ ይችላሉ፤
2. የኪነ ጥበብ የሙያ ዘርፎች ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ዓይነቶች

በግል የሚቋቋም እና በንግድ ሕግ መሠረት የሚቋቋም የንግድ ማህበር


ወይም በህብረት ሽርክና ማህበር፣ በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና
በአክስዮን ማህበር ዓይነት ሆነው ሊቋቋሙ ይችላሉ፣
3. ለመቋቋምና ለመንቀሳቀስ የሚችሉት በቅድሚያ በየደረጃው ከሚገኙ
የአስፈፃሚው መ/ቤት " የአገልግሎት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ መስፈርት
የምስክር ወረቀት" ተሰጥቷቸው በየደረጃው ከሚገኙ የንግድና ትራንስፖርት
አስፈፃሚ አካላት የንግድ ምዝገባና የንግድ ሥራ ፈቃድ ሲያወጡ ብቻ
ነው፣
4. እንቅስቃሴያቸው በክልል ደረጃ በመሆን ለሚመሠረቱ ኢንተርፕራይዞች
የአገልግሎት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ መስፈርት የምሥክር ወረቀት
የሚሰጠውና የሚታደሰው በክልሉ አስፈፃሚ መ/ቤት ወይም በባህልና
ቱሪዝም ቢሮ ሲሆን የክልሉ ንግድና ትራንስፖርት ቢሮ የምስክር ወረቀቱ
በቢሮው መሰጠቱን ወይም መታደሱን አረጋግጦ የንግድ ምዝገባና የንግድ
ሥራ ፈቃድ ይሠጣል ወይም ያድሳል፣

64
5. እንቅስቃሴያቸው በዞን፣ በወረዳ እና በከተማ አስተዳደር ደረጃ በመሆን

ለሚመሠረቱ ኢንተርፕራይዞች የአገልግሎት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ


መስፈርት የምሥክር ወረቀት የሚሰጠውና የሚታደሰው በየደረጃው
በሚገኙት የአስፈፃሚው መ/ቤቶች ሲሆን በየደረጃው ያሉት የንግድና
ትራንስፖርት አስፈፃሚዎችም የምስክር ወረቀቱ መሰጠቱን ወይም
መታደሱን አረጋግጠው የንግድ ምዝገባና የንግድ ሥራ ፈቃድ ይሠጣሉ
ወይም ያድሳሉ፣
6. አስፈፃሚው መ/ቤት " የአገልግሎት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ መስፈርት

የምስክር ወረቀት" የሚሰጠው በባህል የሙያ ዘርፎች ለሚሰጡ የንግድ


ፈቃዶች ሊሟሉ የሚገባቸው የሙያ ብቃት መስፈርቶችን ለመወሰን
በወጣው መመሪያ ላይ የተደነገጉትን የጋራና የተናጥል መስፈርቶች ሲሟሉ
ነው፣
7. በዚህ አንቀፅ ከላይ በንዑስ አንቀፅ 4 ፣5 እና 6 በተጠቀሰው አግባብ ፍቃድ

ሲሰጥ በተጠቀሱት አስፈፃሚ አካላት ፍቃድ የሚያወጣው ኢንተርፕራዝ


ስምና አርማ ቀደም ሲል ፈቃድ ባወጡት ኢንተርፕራይዞች ያልተያዘ
መሆኑን የማረጋገጥና ተይዞ ከሆነ የመቀየር ግዴታ አለባቸው፣
8. የኪነ ጥበባት የሙያ ዘርፎች ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለዜጎች

የሥራ ዕድል በመፍጠርና ለኪነ ጥበባት እንቅስቃሴ መስፋፋትና መጎልበት


ካላቸው የማይተካ ሚናና የሙያ መስኩን ከማልማት አንፃር በአስፈፃሚው
መ/ቤት በኢንተርፕራይዞች ምሥረታ ለማስፋፋት የሚከተሉት ተግባሮች
ይፈፅማል፣
ሀ/ ከአካባቢው ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታዎች አግባብ
ለኢንተርፕራይዝ አዋጪ የሆኑ በተለያዩ የኪነ ጥበብ የሙያ
ዘርፎች የመለየት የመተንተንና መረጃውን በአግባቡ የማደራጀት፣

65
ለ/ ባላቸው እውቀት የተፈጥሮ ክህሎትና ሙያዊ ተሞክሮ
ኢንተርፕራይዝ መሥርተው ቢንቀሳቀሱ ውጤታማ የሚሆኑ
አካላትንና ሊሠማሩ ሚችሉባቸውን የሙያ ዘርፎች በመለየት
የዘርፉን የገበያ አዋጭነትና የገበያ አማራጮችን አስመልክቶ በቂ
ዕውቀት እንዲያገኙ የግንዛቤ ማስጨበጫ የጋራና የተናጥል
መድረኮችን በማመቻቸት ግንዛቤ ማስጨበጥ፡

ሐ/ ለኢንተርፕራይዝ መመሥረቻ የሚሆን መነሻ ካፒታል ከቦታ


አሰጣጥና ከብድር አቅርቦት አንፃር ከሚመለከታቸው ተቋማት
ድጋፍ ሊያገኙ የሚችሉበት መንገድ ማመቻቸት፣
መ/ ስለ ኢንተርፕራይዝ አመሠራረት ሒደቶች ማለትም ስለ "
የአገልግሎት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ መስፈርት የምስክር
ወረቀት" እና ስለ የንግድ ምዝገባና የንግድ ሥራ ፈቃድ አወጣጥ
ሒደቶች በቂ ማብራሪያና መረጃ እንዲጨብጡ ማድረግ፣

39. የኪነ ጥበባት የሙያ ዘርፎች ጥቃቅንና አነስተኛ


ኢንተርፕራይዝ መብትና ግዴታዎች

1. በዚህ መመሪያ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት የተመሠረተ


ማንኛውም ኢንተርፕራይዝ ሕጋዊ በሆነ አግባብ የመሥራት፣ በተለያዩ
ጨረታዎች የመሳተፍና አገልግሎት የመስጠት መብት አለው፣
2. በተመሠረተበት ደረጃ ከሚገኝ አስፈፃሚ መ/ቤት በማንኛውም ጊዜ የሙያ
ምክርና መረጃ የማግኘትና በዚህ መመሪያ በተደነገገው አግባብ ድጋፍና
ማበረታቻ የማግኘት መብት አለው፣
3. የአገልግሎት ፈቃድ ያገኙበትን ዘርፍ የመቀየር፣ አስፈላጊዎቹን
መስፈርቶች በማሟላትና የአገልግሎት ፈቃድ በመውሰድ በተጨማሪ

66
ዘርፎች ላይ የመሰማራት ወይም የወሰደውን የሙያ ፈቃድ የመመለስ
መብት፣
4. የክልሉን የንግድ ምዝገባና የንግድ ሥራ ፈቃድ ህጎችን፣ በአስፈፃሚው
መ/ቤት በኪነ ጥበባት ዙሪያ የወጡና የሚወጡ መመሪያዎችን በአግባቡ
አውቆ ማክበርና ለማስከበር በመንቀሳቀስ መሥራት፣
5. የሙያ ፈቃድ በተሰጠው የስራ ዘርፍና እንዲሠራ በተፈቀደለት ቦታ ወይም
ክልል ውስጥ ብቻ መስራትና በየአመቱ የአገልግሎት ሙያ ብቃት
ማረጋገጫ መስፈርት የምስክር ወረቀቱን እና የንግድ ምዝገባና የንግድ
ሥራ ፈቃዱን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የማሳደስ ግዴታ አለበት፣
6. የአድራሻ ለውጥ ወይም በሚሰራው ስራ ላይ ማንኛውንም ለውጥ ካደረገ
ለውጡን ካተደረገበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 ቀናት ውስጥ ፍቃዱን ለሰጠው
አስፈፃሚ መ/ቤት ማስታወቅ አለበት፣
7. የተሰጠውን የአገልግሎት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ መስፈርት የምስክር
ወረቀትና የንግድ ምዝገባና የንግድ ሥራ ፈቃዱን በሥራ ቦታው
ለማንኛውም አካል በግልፅ ሊታይ በሚችል ሁኔታ መስቀል ወይም
ማስቀመጥ ይኖርበታል፣
8. የሕብረተሰቡን ባህል፣ ታሪክና ሕጎች የሚፃረር ድርጊት ያለመፈጸም፣
በሕገ-ወጥ ሥራ ከተሰማሩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ጋር ያለመስራት፣
ያለማበር፣ ያለባለቤቱ ፈቃድ የሌላውን ሰው የፈጠራ ስራ ያለመጠቀም፣
ስራውን ያለማባዛት፣ ያለማሰራጨት፣ ድርጊቱ በሌሎች ሲፈፀምም በወቅቱ
ለአስፈፃሚው መቤትና ለሚመለከተው አካል ሪፖርት የማድረግ ግዴታ
አለበት፣
9. በአስፈፃሚው መሥሪያ ቤት በማንኛውም ጊዜ ስለ ኢንተርፕራይዙ
እንቅስቃሴ መረጃ ሲጠየቅ በአግባቡ የመስጠት፣ መ/ቤቱ በሚያስተላልፈው
ቅጽ መሠረት መረጃ የመያዝና ሲጠየቅም የማቅረብ፣. የአስፈፃሚውን

67
መሥሪያ ቤት ጥሪ የመቀበልና በቀጠሮው ቀን ቀርቦ የመሳተፍ ግዴታ
አለበት፣
10. የአስፈፃሚውን መሥሪያ ቤት በሚያደርገው ክትትል የደረሰበትን
ጉድለቶችን እንዲያስተካክል የጽሁፍ ማስታወቂያ ሲደርሰው
በማስታወቂያው በተገለፀው የጊዜ ገደብ ውስጥ ጉድለቱን የማስተካከል፣
11. የፊልም ቀረፃ ለማካሄድ የቀረጻ ፈቃድ መያዝ አለበት፣ ያለ
አስፈፃሚው መሥሪያ ቤት እውቅና እና ፈቃድ ማናቸውም የኪነ-ጥበብ
ሥራዎችን በመድረክ፣ በሲኒማ፣ በDVD፣ በቪዲዮ፣ በሲዲ፣
ያለማሰራጨት፣

40. የኢንተርፕራይዞች ድጋፍ አሠጣጥና ክትትል

በአስፈፃሚው መ/ቤት ቀጥሎ የተዘረዘረው ድጋፍና ክትትል ይደረጋል ፡-

1. በተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ የበለጠ ትርፋማና ውጤታማ ሊሆኑ


የሚያስችላቸውን ሁኔታ የማማከርና መረጃ የመሥጠት አገልግሎት በቼክ
ሊስት በተደገፈና ቀጣይነት ባለው አግባብ ይሰጣል፣
2. በየጊዜው ያለባቸውን የአቅም ክፍተት በማጥናት ስልጠና በመስጠትና
ስልጠና እንዲያገኙ በማመቻቸት ክፍተቱ እንዲሞላ ያደረጋል፣
3. መልካም ተሞክሮ ያላቸው ኢንተርፕራይዞችን በመጋበዝ የልምድ ልውውጥ

የሚያደርጉባቸውን መድረኮች እንዲዘጋጁ ያደረጋል፣ በፌዴራልና በክልል


ደረጃ በሚዘጋጁ ተመሳሳይ መድረኮች የመሳተፍ ዕድል እንዲያገኙና
የክህሎት የዕውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ ያደርጋል፣
4. በሚንቀሳቀሱበት ደረጃ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማትና

ግለሰቦች ጋር የስራ ስምምነቶችና የገበያ ትስስር የሚያገኙባቸውን


ሁኔታዎች ያመቻቻል፣ ትብብርና ድጋፍ ደብዳቤ ይሰጣል፣

68
5. ከባለድርሻና አጋር አካላትን በማስተባበር የተለያዩ ፌስቲቫሎችን ኤግዚቢሽና

አውደርዕዮችን በማዘጋጀት በማሳተፍ የገበያ ዕድሎች እንዲፈጠሩላቸው


ይሠራል፣
6. የፈጠራ ስራ ውድድር በማካሄድ አካባቢዊና አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ኪነ

ጥበባዊ የፈጠራ ስራዎች ለሚያቀርቡና በተሠማሩበት ዘርፍ የላቀ ጠንካራ


እንቅስቃሴ ላሳዩ ኢንተርፕራይዞች እውቅናና ማበረታቻ የሚሰጥበትን
ስርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣
7. የኢንተርፕራይዞቹ የፈጠራ መብት በህግ አግባብ እንዲጠበቅ ይደረጋል፣

በህገወጥ መንገድ የፈጠራ ስራዎችን በሚያባዙና ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት


በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ተገቢ ቁጥጥር ይደረጋል፣
8. በግልም ሆነ በማህበር ተደራጅተው ብድር የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች

ይደረጋል፣ የተዘዋዋሪ ፈንድ ድጋፍ እንዲያገኙ፣ የዘርፉን እድገት የሚጫኑ


የግብር ስርዓቶች እየተጠኑ እንዲስተካከሉ ይሰራል፣
9. የዘርፉን እንቅስቃሴ ወይም በዘርፉ በመንቀሳቀስ ላይ በሚገኝ ማንኛውም

አካል ላይ ሕጋዊ ፍቃድ መያዝና አለመያዙን፣ ፍቃዱ መታደስና


አለመታደሱን፣ በተሰጠ የሙያ ዘርፍ እየተሠራ መሆን አለመሆኑን፣
ፈቃድ ሲያወጣ ወይም ሲያሳድስ በሰጣቸው መረጃዎች ላይ ለውጥ ካደረገ
ለውጡን ማሳወቁና አለማሳወቁንና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ጉዳዮችን
በሚመለከት በየጊዜው ክትትልና ቁጥጥር በማካሄድ ፍተሻ ያደርጋል፣
10. በሕግ አግባብ ፍቃድ ሳያወጡና በዚህ መመሪያ መሠረት የማይሰሩ አካላት

በመቆጣጠርና ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣

41. የአገልግሎት ሙያ ብቃት ማረጋገጫና የንግድ ፈቃድ


እድሣት

69
1. የአገልግሎት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ መስፈርት የምሥክር ወረቀትና
የንግድ ሥራ ፈቃድ ከተሰጠበት ወይም የታደሰበት የበጀት ዓመት ካበቃ
በኋላ ባሉት 3 ወራት ጊዜ ውስጥ ከሀምሌ 1 እስከ መስከረም 3ዐ መታደስ
አለበት፣
2. አስፈፃሚው መ/ቤት በዚህ መመሪያ እና በአገልግሎት የሙያ ብቃት
መመሪያ የተቀመጡት መሥፈርቶች መሟላታቸውን ከገመገመ በኋላ
ጥያቄው የተሟላ ሆኖ ሲያገኘው በአንድ የሥራ ቀን ውስጥ የምሥክር
ወረቀቱን ያድሳል፣
3. ማንኛውም የኪነ ጥበብ ሙያ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በዚህ
አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ 1 በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ፈቃዱን ካላሳደሰ ፈቃዱ
ይሰረዛል፣
4. በንግድና ትራንስፖርት ቢሮ እና በየደረጃው ባሉት አስፈፃሚ አካላቶቹ
ማንኛውም በኪነ ጥበባት የሙያ ዘርፎች በጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዝ የንግድ ሥራ ፈቃድ እድሳት ሲጠይቅ በቅድሚያ የምስክር
ወረቀቱ በሰጠው አስፈፃሚው አካል መታደሱን ወይም ማሳደሱን
ሲያረጋግጥ ብቻ የንግድ ሥራ ፍቃድ እድሳት ይፈፅማል፣

42. የፈቃድ ዕገዳና ስረዛ

1. የአገልግሎት ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀትና የንግድ ስራ ፈቃድ


በሚከተሉት ምክንያቶች ላልተወሰነ ጊዜ ሊታገድ ይችላል፣

ሀ/ በዚህ መመሪያ በአንቀጽ 18 መሠረት በጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ


በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ፈቃዱን ካላሳደሰ፣
ለ/ አስፈፃሚው መ/ቤት ጉድለቶች እንዲያስተካክል በሚወስነው የጊዜ
ገደብ ውስጥ ካላስተካከለ፣

70
ሐ/ የአገልግሎት ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለመውሰድ ወይም ለማደስ
የተሳሳተ መረጃ ከሰጠ፣
መ/ በዚህ መመሪያ ውስጥ የተደነገጉትን ግዴታዎች በመጣስ ከህግ
ውጭ ሲሰራ ከተገኘ ይታገዳል፣
2. የማንኛውም ኢንተርፕራይዝ የአገልግሎት ብቃት ማረጋገጫ የምስክር
ወረቀትና የንግድ ስራ ፈቃድ በሚከተሉት ምክንያቶች ይሰዘራል፣

ሀ/ ኢንተርፕራይዙ የሚያከናውነውን ስራውን ማቆሙን በጽሁፍ


ሲያስታውቅ፣
ለ/ ፍቃድ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ባለው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ
ከአቅም በላይ ባልሆነ ምክንያት ስራውን ማከናወን ካልቻለ፣
ሐ/ በዚህን መመሪያና በአገልግሎት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ
መስፈርት መመሪያ አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 8.2.3. እና በአንቀፅ
10 ንዑስ አንቀፅ 10.3. ላይ የተደነገጉትን ግዴታዎች ተላልፎ
ከተገኘ፣
ሠ/ የንግድ ምዝገባና የንግድ ሥራ ፈቃድ መስጫ አዋጅና ልዩ ልዩ
ድንጋጌዎቹን በመጣስ የወንጀል ድርጊት ከፈጸመ፤

ክፍል አምስት

የኪነ ጥበባት ዘርፍ የሙያ ማኅበራት

ዓላማ ፣ አመሠራረት፣ ድጋፍ አስጣጥና ክትትል

71
43. የኪነ ጥበባት ዘርፍ የሙያ ማህበራት ዓላማና ተግባራት

የኪነ ጥበብ ዘርፍ የሙያ ማኅበራት የሚከተሉት አላማዎች ይኖራቸዋል፡-

1. የባለሙያውን መብት ማስከበር፣ ባለሙያው ስለመብቶቹ በቂ ግንዛቤ


እንዲኖረው በማድረግ የራሱን መብቶች ማስከበር እንዲችል መርዳትና
ግዴታዎቹንም ማሣወቅ፣
2. ባለሙያዎቹ የተሠማሩበት ኪነ ጥበብ ዘርፍ እየተስፋፋና እየጎለበተ
እንዲሄድ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣ ማመቻቸት፣
3. የማህበሩ አባላት የሙያቸውን ክህሎት የሚያሳድጉባቸውን ሁኔታዎች
መፍጠርና ተግባራዊ ማድረግ፣
4. አባላት በየዘርፋቸው ያካበቱትን ዕውቀትና ልምድ አስመልክቶ መረጃዎችን

የሚለዋወጡበትን መድረክ መፍጠር፣


5. የማህበሩን አባላት መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችሏቸውና ትምህርታዊ
ጽሁፎች እያዘጋጃ ማውጣት፣ ማህበራዊ ድረ ገፅና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያን
በመጠቀም ማሰራጨት ፡፡
6. ፌስቲቫሎች ወይም ኤግዚቢሽኖች እንዲዘጋጁና እንዲካሄዱ በማድረግ
ሙያው እውቅናን እንዲያገኝ ማድረግ፣
7. በአባላት የሚዘጋጁ የተመረጡ ብቃት ያላቸው ፕሮጀክቶች ተግባራዊ
እንዲሆኑ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ድጋፍ ማድረግ ፣
8. የሚሰሩ የኪነ ጥበብ ዉጤቶች የሚተዋወቁበትን ሁኔታ ማመቻቸት
ተግባራዊ ማድረግ፣
9. የማህበሩ አባላት የፈጠራ ሥራዎችና የፈጠራ ውጤቶች ገበያ ሊያገኙ
የሚችሉባቸውን መንገዶች በማመቻቸት ከዘርፉ ገቢ ተጠቃሚ እንዲሆኑ
ማድረግ፣

72
10. የሙያዉን የሥነ-ምግባር ደንቦች መመሪያዎች ማውጣት፣ በአባላትና
በሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ እንዲጨበጥባቸው ማስቻል፣
እንዲጠበቁ ማድረግ፣
11. በተለያዩ ምክንያቶች ከባድ ማህበራዊ ችግር የሚገጥማቸውን የማህበሩን

አባላት ችግራቸው በህብረት የሚቀርፍበትን መንገድ ማመቻቸትና ተግባራዊ


ማድረግን ፡፡
12. የክልሉ ኪነጥበብ የጥራት ደረጃ ከፍ እንዲል አስፈላጊውን ድጋፍ
መስጠት፣ የኪነጥበብ እንቅስቀሴዎችን መረጃዎችን ማጠናቀርና
ማሠራጨት፣
13. አባላትዕውቀታቸውን ሀብታቸውንና ጉልበታቸውን በማስተባበር
በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ እንዲሳተፉ ማበረታታት ፣
14. ከክልሉ፣ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጪ ጠቃሚ የሆኑ ልምዶችና
መረጃዎችን በማሰባሰብ መንግስት ለሚተገብራቸው ፖሊሲዎችና
እስትራቴጂዎች ጠቃሚ መረጃዎችን መስጠት ፣
15. የሙያ ማኅበራት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከመንግስት ጋር የጋራ ውይይት

የሚያደርጉበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣


16. ሌሎች ተመሳሳይ ዓላማዎችን ያከናውናሉ፡፡

44. የኪነ ጥበባት ዘርፍ የሙያ ማህበራት ዓይነቶች

1. በኪነ ጥበብ የሙያ ዘርፍ የሚመሠረቱ የሙያ ማህበራት ዓይነቶች


የሚከተሉት ይሆናሉ፣

ሀ/የፊልምና የቴአትር ባለሙያዎች ማኅበር

ለ/የሙዚቃ ባለሙያዎች ማኅበር

73
ሐ/የደራሲያን ማኅበር

መ/ የሥዕልና ቅርፃ ቅርፅ ባለሙያዎች ማኅበር

2. ከላይ በንዑስ ንዑሥ አንቀፅ 1 ከተዘረዘሩት በተጨማሪ የሚቋቋሙ የሙያ

ማህበራትን የተሠማሩበትን የኪነ ጥበብ የሙያ ዓይነትና የሙያ ማህበራቱ


እንዲኖራቸው ከሚፈልጉት አባላት ብዛት አንፃር አግባብነቱን በማገናዘብ
እንደአስፈላጊነቱ ቢሮው ሊወስን ይችላል፡፡

45. የኪነ ጥበባት ዘርፍ የሙያ ማህበራት አመሠራረት

1. ከተመሳሳይ የኪነ ጥበብ ሙያ የተውጣጡ ሰዎች ወይም ባለሙያዎች የኪነ


ጥበብ የሙያ ማህበር ሊመሠርቱ ይችላሉ፤
2. የሙያ ማህበራት የሚመሠረቱት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
የበጐ አድራጐት ድርጅቶችንና ማህበራትን መመዝገቢያና ማስተዳደሪያ
አዋጅ ቁጥር 194/2004 ዓ.ም “ እና ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም በወጡ
ደንቦች፣ መመሪያዎች መሠረት ነው፣
3. ከላይ በአንቀጽ 3 በተገለፁት የሕግ ድንጋጌዎች አግባብ ማህበራትን
የመመሥረት፣ የመመዝገብና ፍቃድ የመሥጠት ሥልጣን የተሰጠው
ለክልሉ የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮና በየደረጃው ለሚገኙት
አስፈፃሚዎቹ ሲሆን ቢሮው አስፈላጊ ሁኔታዎች ሲያሟሉና ሲፈጽሙ
አመልካቾችን በማህበርነት በመመዝገብ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር
ወረቀት ይሰጣል፡፡
4. የኪነ ጥበባት የሙያ ማህበራት ለኪነ ጥበባት እንቅስቃሴ መስፋፋትና
መጎልበት ካላቸው የማይተካ ሚና አንፃር አስፈፃሚው መ/ቤት
የሚከተሉትን ያከናውናል፡-

74
ሀ/ በሙ ማህበራት መደራጀት ስለሚያስገኘው ጠቀሜታ የተለያዩ
የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን ያዘጋጃል በቂ ግንዛቤ
ያስጨብጣል፣
ለ/ በየደረጃው በክልሉ የሚመሠረቱ የኪነ ጥበባት የሙ ማህበራትን
ይደግፋል፣ ያበረታታል፣
ሐ/ ስለ ኪነ ጥበባት ሙያ ማህበራት አመሠራረት ሒደቶች በቂ
ማብራሪያና መረጃ እንዲጨብጡ ያደርጋል፣
መ/ የሙያ ማህበራትን የመመሥረት፣ የመመዝገብና ፍቃድ
የመሥጠት ሥልጣን ለተሰጠው አካል ስለ መመስረታቸው
አግባብነትና የሙያው ባለቤት ስለመሆናቸው መረጃና መግለጫ
ይሠጣል፣ ድጋፍና ትብብር እንዲሰጣቸው ያደርጋል፣

46. በኪነ ጥበባት የሙያ ማህበራት የአስፈፃሚው መ/ቤት


የሥልጣንና ኃላፊነት ድርሻዎች

1. የአስፈፃሚው መ/ቤት በክልሉ የበጐ አድራጐት ድርጅቶችንና ማህበራትን


መመዝገቢያና ማስተዳደሪያ አዋጅ ቁጥር 194/2004 ዓ.ም አንቀፅ 61 እና
አንቀፅ 62 ላይ በተደነገገው መሠረት በክልሉ ውስጥ ለሚቋቋሙ የኪነ
ጥበባት ዘርፍ የሙያ ማህበራት የዘርፍ አስተዳዳሪ አስፈፃሚ አካል ነው፣
2. ከላይ በንዑሥ አንቀፅ 1 መሠረት አስፈፃሚው መ/ቤት በክልሉ
በተቋቋሙና በሚቋቋሙ የኪነ ጥበባት ዘርፍ የሙያ ማህበራት ላይ
የሚከተሉት ስልጣንና ኃላፊነቶች ድርሻ ይኖሩታል፡-

ሀ/ ሙያ ማህበር የመደራጀት ጉዳይ ሕገ መንግሳቲዊ መብት


ቢሆንም እንኳን በኪነ ጥበባት ዘርፍ ያሉ ሙያተኞች በማህበር
የመደራጀትን ጠቀሜታ ላይ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ያደርጋል፣
75
ለ/ አስፈፃሚው መ/ቤት ማህበራት በዚህ አዋጅና አዋጁን ለማስፈፀም
በሚወጡ ደንቦች የተቀመጡ መስፈርቶችን አሟልተው
እንዲመዘገቡና ሕጋዊ ሰውነት እንዲያገኙ ሲገኙ እንደተመሰረቱ
ይቆጠራል፡፡ የሙያ ማህበራት ምዝገባ ሂደት ለአስተዳደርና ፀጥታ
ጉዳዮች ቢሮ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፤

ሐ/ የሙያ ማህበራትን ኘሮግራሞችና ኘሮጀክቶች የሚገመግሙና


አስተያየት የሚሰጡ ባለሙያዎችን ይመድባል፤
መ/ የሙያ ማህበራትን የሥራ እንቅስቃሴ ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፤
ሠ/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (ሐ) መሰረት የወሰደውን እርምጃ
በሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ ለአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ
ያሳውቃል፤
ረ/ የሙያ ማህበራት ሥራዎች ህብረተሰቡ የላቀ ተጠቃሚ መሆኑን
ለማረጋገጥ የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ሊከተላቸው
የሚገቡ መስፈርቶችን ያወጣል፤
ሰ/ የአስፈፃሚ መ/ቤቱንና የሙያ ማህበራትን የጋራ ግቦች ለማሣካት
የሙያ ማህበራት ተቀናጅተው የሚሰሩበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡

47. የኪነ ጥበባት ዘርፍ የሙያ ማህበራት ኃላፊነትና


ግዴታዎች

1. በፍቃድ ሰጪው አካልና በአስፈፃሚው መ/ቤት የወጡና በየጊዜው


የሚያወጧቸውን አዋጆች ፣ ደንቦችና መመሪያዎች እንዲሁም
የተደራጀበትን መተዳደሪያ ደንብ በአግባቡ ተገንዝቦ በጥብቅ ዲሲፕሊን
በማክበር መንቀሳቀስና ለማስከበር በጋራም ሆነ በተናጠል መሥራት፣
76
2. የአባልነት መስፈርት የሚያሟሉ አዲስ አባላትን በመተዳደሪያ ደንቡ
መሰረት የመቀበልና የሚሰናበቱ አባላትንም በደንቡ መሠረት የማሰናበት፣
3. በማህበሩ ማናቸውንም ዓይነት ምልክት ለመጠቀም፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ለመክፈት፣ የማህበሩን ስያሜ፣ የሥራ ቦታው ከለወጠ ወይም መተዳደሪያ
ደንቡን ካሻሻለ ለውጡን ወይም ማሻሻያውን ለፍቃድ ሰጪው አካል አቅርቦ
ማስመዝገብና ለአስፈፃሚው መ/ቤት የማሳወቅ፣
4. የማህበሩን የሥራ እንቅስቃሴና የአባላቱን ዝርዝር ጉዳዮች መረጃ
በመመዝገብና አደራጅቶ በመያዝ በማንኛውም ወቅት በአስፈፃሚው ወይም
በፍቃድ ሰጪው አካል ሲጠየቅ የማቅረብ፣
5. አስፈፃሚው መሥሪያ ቤት በሚያስተላልፈው ቅጽ መሠረት መረጃ
የመያዝና ሲጠየቅም የማቅረብ፣. እንዲሁም የአስፈፃሚውን መሥሪያ ቤት
ጥሪ የመቀበልና በቀጠሮው ቀን ቀርቦ የመሳተፍ፣
6. ማንኛውም የሙያ ማህበር አባላት በጠየቁ ጊዜ ስለማህበሩ እንቅስቃሴ
የሚገልፁ ሰነዶችን የማሳየት የማሳወቅ ግዴታ፣
7. ስሙ ካልተገለፀ ሰው ልገሳ ወይም ስጦታ ያለመቀበል፣ በማናቸውም ጊዜ
የለጋሹን ማንነት በግልጽ የሚያመለክቱ መዝገቦችን የመያዝ ፣
8. የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባዎች በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ በተደነገገው
መሠረት ማካሄድና ማሕበር የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ከመካሄዱ ከሰባት
የሥራ ቀናት አስቀድሞ የስብሰባውን ጊዜና ቦታ ለፍቃድ ሰጪው አካልና
ለአስፈፃሚው መ/ቤት በጽሁፍ የማሳወቅ ፣
9. ማንኛውም ማህበር የምዝገባ የምስክር ወረቀቱን በዋናው መሥሪያ ቤትና
ግልባጩን በየቅርንጫፎቹ ለማናቸውም ጐብኝ ሊታይ በሚችል ቦታ
ማስቀመጥ ፣
10. ለማህበራቸዉ አባላት ያሉባቸውን የአቅም ክፍተት በየጊዜው
በመለየት የአቅም ግንባታ ተግባራትን ማከናወን፣

77
11. በዘርፋቸዉ ባሉት ላሉት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርኘራይዝ ዕድገት
ላይ በቀጥታ የመሳተፍ የማገዝና የመምራት ሚና የመጫወት፣
12. በማህበር የመደራጀትን ጠቀሜታና ለተደራሽነት ያለዉን ጉልህ
አስተዋጾ አዳዲስ በዘርፉ ለተሰማሩት ማስገንዘብ፣
13. በዘርፉ ከተደራጁ አቻ ማህበራትና ተቋማት ጋር ግንኙነትና የትብብር
ስምምነት በመፍጠር እንዲሁም ለሀገራዊ ትብብር በሚያግዙ በአጋርነት
በመሳተፍ ለዘርፉ ልማት የድርሻቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት፣
14. የአስፈፃሚውን መሥሪያ ቤት ጉድለቶችን እንዲያስተካክል የጽሁፍ
ማስታወቂያ ሲደርሰው በማስታወቂያው በተገለፀው የጊዜ ገደብ ውስጥ
ጉድለቱን የማስተካከል፣
15. በሕገ-ወጥ ሥራ ከተሰማሩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ጋር
ያለመስራት፣ ያለማበር
16. የክልሉን ሕዝብ ቅርስ፣ ባህል፣ ታሪክና ሕጎች የሚፃረር ድርጊት
ያለመፈጸም፣ በሌሎች ሲፈፀምም በወቅቱ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት
የማድረግ፣

48. ለኪነ ጥበባት ዘርፍ የሙያ ማህበራት ድጋፍ አሠጣጥና


ክትትል፣

ለማህበራት በአስፈፃሚው መ/ቤት ቀጥሎ የተዘረዘረው ድጋፍና ክትትል


ይደረጋል፣

1. የበለጠ ተሰሚነትና አቅም እንዲኖራቸውና ወደ ተደራጀ ኃይል ደረጃ


እንዲሸጋገሩ የሚስችሏቸውን ሁኔታዎች በየጊዜው በማጥናት የማማከርና
አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ የመስጠት፣

78
2. በሙያ ዘርፋቸው የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከመንግሥት ጋር የጋራ ውይይት
የሚያደርጉባቸውን መድረኮች ያመቻቻል.፣
3. ከክልሉ፣ ከሌሎች ክልሎች፣ ከፌደራልና ከውጭ ሐገራት አቻ የሙያ
ማህበራት፣ ባለድርሻና አጋር አካላት፣ ድርጅቶችና ተቋማት ጋር በጥምረት
ለመስራት የሚችሉባቸውን ሁኔታዎች የማመቻቸትና የመፈፀም፣
4. በየጊዜው በአባላቶቻቸው ያለውን የአቅም ክፍተት በማጥናት ተከታታይነት
ያላቸው የረጅምና የአጭር ጊዜ ስልጠና በየዘርፋቸው እንዲያገኙ ያደርጋል፣
5. በዘርፉ የዕውቀትና የክህሎት ክፍተት ላለባቸው አባላት የአጫጭር እና
የረጅም ጊዜ ስልጠና በመስጠት ክፍተቱ እንዲሞላ ያደረጋል፣አባላቱ
ስልጠና የሚያገኙባቸውና የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉባቸው መድረኮች
እንዲመቻቹ ይደረጋል፣

49. ስለ ፈቃድ እድሳት፣

1. ማህበራት በዚህ አዋጅ አንቀጽ 73 እና 75 መሠረት አመታዊ የሥራ


ክንውን ሪፖርትና የሂሳብ መግለጫዎችን ለቢሮው የማቅረብ ግዴታቸው
እንደተጠበቀ ሆኖ ፈቃዳቸውን በየሶስት ዓመቱ ማሳደስ አለባቸው፡፡
2. ፈቃድ የሚታደሰው በፈቃድና ምዝገባ ሰርተፊኬቱ ላይ የተገለፀው ጊዜ
የሚያገለግልበት የመጨረሻ ቀን ካለፈ በኋላ ባሉት ሁለት ወራት ውስጥ
ነው፡፡
3. /ለማሳደስ የእኛ ቢሮ ደብዳቤ ይስጥ/አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ፣ ሀ/
የማህበሩ የስራ አፈጻጸምና የኦዲት ሪፖርቶች የተሟሉና ትክክለኛ
መሆናቸውን፣ እና ለ/ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ የዚህን
አዋጅ ድንጋጌዎች ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት የወጡ ደንቦችንና
መመሪያዎችን ወይም አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ የተሰጡ ትዕዛዞችን
ወይም የራሱን መተዳደሪያ ደንብ ያልጣሰ መሆኑን ሲያረጋግጥና
አስፈላጊው የማሳደሻ ክፍያ ከተፈጸመ በኋላ ፈቃዱን ያድሳል፡፡
79
4. የማኅበሩ ዓመታዊ ክንውንና እውቅና ባለው የሂሳብ ባለሙያ የተረጋገጠ
የኦዲት ሪፖርት የተሟሉ መሆናቸውና የእድሳት ክፍያ መፈጸሙ
ሲረጋገጥ የእያንዳንዱ የሙያ ማኀበራቱ ፈቃድ በየሁለት ዓመቱ መታደስ
ይኖርበታል፣

50. ስለፈቃድ ዕገዳና ስረዛ

1. ማንኛውም የኪነ ትበባት የሙያ ማህበር፡-


ሀ/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 68 ንዑስ አንቀፅ (2) መሠረት የተላለፈውን
የቢሮውን ትዕዛዝ በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሳይፈጽም
ከቀረ፣

ለ/ ያቀረበው ሪፖርት ሀሰተኛ ከሆነ፣

ሐ/የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 (ሐ) እንደተጠበቀ ሆኖ የዚህን


አዋጅ ድንጋጌዎች ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት የወጡ ደንቦችንና
መመሪያዎችን ወይም በቢሮው የተሰጡ ትዕዛዞችን ወይም የራሱን
መተዳደሪያ ደንብ የጣሰ እንደሆነ፣

መ/ በዚህ አዋጅ መሠረት ለቢሮው ማቅረብ የሚገባቸውን


መረጃዎች በወቅቱ ያላቀረበ እንደሆነ፣ ጉድለቶቹን
እስከሚያስተካክል ድረስ ፈቃዱ በቢሮው ሊታገድ ይችላል፡፡

2. ማናቸውም የኪነ ትበባት የሙያ ማህበር፣


ሀ/የተመዘገበው በማታለል ወይም በማጭበርበር ከሆነ፣ ወይም

ለ/ሕገወጥ ለሆነ ዓላማ፣ ወይም የሕዝብን ሠላምና የክልሉን ደህንነት


ለሚጎዱ ዓላማዎች ውሎ ከሆነ፤

80
ሐ/በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ለዕግድ ምክንያት
የሆኑትን ጉድለቶች ቢሮው በሚወስነው የጊዜ ገደብ ውስጥ
ካላስተካከለ፣ ወይም

መ/በዚህ አዋጅ አንቀጽ 71 መሠረት ፈቃዱን ካላሳደሰ፣

ሠ/የወንጀል ሕጉን ወይም የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎች በመጣስ


የወንጀል ድርጊት ከፈጸመ፤ፈቃዱ ይሰረዛል፡፡

ማንኛውም የኪነ ጥበባት የሙያ ማህበር፣

3. በአንቀጽ 18 መሠረት ዓመታዊ የሥራ ክንውን እና የኦዲት ሪፖርቶችን


በጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ካላቀረበ ወይም ፈቃዱን
ካላሳደሰ ፈቃዱ ይታገዳል፣
4. የተመዘገበው በማታለል ወይም በማጭበርበር ከሆነ ወይም የተቋቋመበትን
አላማ ወይም የሚፈለግበትን አገልግሎት የማይሰጥ ሆኖ ከተገኘ ፈቃዱ
ይሠረዛል፡፡

ክፍል ስድስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

51. መመሪያውን የማሻሻል ወይም የመሻር ሥልጣን

አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ቢሮው ይህን መመሪያ በማንኛውም ጊዜ ማሻሻል


ወይም መሻር ይችላል፡፡

52. የተሻሩ መመሪያዎች


81
ቀደም ሲል በክልሉ የኪነ ጥበባት አደረጃጀትን ለመምራት፣ ለማስፈጸም
የወጡ መመሪያዎችና ዘልማዳዊ አሠራሮች በሙሉ በዚህ መመሪያ
ተሽረዋል፡፡

53. የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች

1. ከዚህ መመሪያ ጋር የሚጋጭ ሁኔታ ካልተነሳ በስተቀር ቀደም ሲል


በአስፈፃሚው መ/ቤት ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ የኪነ ጥበብ ክበባት፣
የባህል ሙዚቃ ቡድኖች፣ የኪነ ጥበብ ሙያ ዘርፎች አነስተኛና ጥቃቅን
ኢንተርፕራይዞችና የኪነ ጥበባት ሙያ ማሕበራት የህጋዊ ሰውነት
ማረጋገጫቸውን በማደስ ተግባራቸውን ሊቀጥሉ ይችላሉ፡፡
2. ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 በተገለጸው መሰረት ቀደም ሲል የተመዘገቡ የኪነ
ጥበብ ክበባት፣ የባህል ሙዚቃ ቡድኖች፣ የኪነ ጥበብ ሙያ ዘርፎች
አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችና የኪነ ጥበባት ሙያ ማሕበራት ይህ
መመሪያ ሥራ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ቀርበው
ፈቃዳቸውን ማሳደስ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንኑ የደረጃው የሚገኙ አስፈፃሚ
መ/ቤቶች ለሚመለከታቸው ሁሉ ያሳውቃሉ፡፡

54. ስለ ቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት

1. ማንኛውም የኪነ ጥበብ ክበባት፣ የባህል ሙዚቃ ቡድኖች፣ የኪነ ጥበብ


ሙያ ዘርፎች አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችና የኪነ ጥበባት ሙያ
ማሕበራት እገዳንና ስረዛን በተመለከተ ቅሬታ ካለው እገዳው ወይም ስረዛው
ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ባለው 2 ወር ጊዜ ውስጥ በተዋረድ ባለው
አስፈፃሚ መ/ቤት በፅሁፍ ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርበታል፣
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት አስፈፃሚው መ/ቤት ወይም
በተዋረድ ያሉ የክልል ወይም የዞን ወይም የከተማ አስተዳደር ወይም

82
የወረዳ መ/ቤቶች ቅሬታው ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ባለው አንድ ወር ጊዜ
ውስጥ ውሳኔውን በጽሁፍ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

55. መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ ከመጋቢት 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

ባሕር ዳር መጋቢት 30 ቀን 2008 ዓ.ም

አወቀ እንየው

የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ

83

You might also like