Professional Documents
Culture Documents
WPS Office
WPS Office
WPS Office
ንጉሥ፦
ለመሆኑ ቄሳርን ከድቶ ከካሃዲዎችና ውዳቂዎች ጎን መቆም ክፍያው ምን እንደሆነ ታውቃለህ ?
ንገሪኝ እስኪ በታላቋ ሮምና በአማልክታችን ላይ ክህደት እንድትፈጽም ያደረገህ ነገር ምንድነው??
ዝምታ............
የጦር መሪ፦(ማርሴለስን)
ንጉሥ ሆይ! አንተ እንዳልከው ክህደትና ቅጥፈት አይደለም የአባቴን የምላኬን ፍቅር በወንድሞቼ
ማንነት ውስጥ አግኝቼ ነው የተሸነፍኩት። በትዕዛዝህ መሠረት ሳሳድዳቸው ሳስጨንቃቸው የኖርኩ
ቢሆንም እነርሱ ግን እንደ ከበረ እንግዳ ተቀብለው ክፋቴን በፍቅር ነበረ ያካፈሉኝ።ታዲያ እነርሱ ሰው
ሆነው ከበቀል ይልቅ ፍቅርን ካሳዩኝ አምላካው ምን ያክል መሃሪ እና አፍቃሪ ይሆን። ይሄ ሲገባኝ
ተሸነፍኩለት።
ንጉሥ፦
ግድ የለም ከንጉሥ ሃሳብ ጋር መቃረን ክፍያው ምን እንደሆነ አሁን አሳይሃለሁ። ክደሀኛል አዎ ክደሀኛል
በአንተ መካድ ለእኔ ወረደት ለንግስናዬ ስድብና ንቀት ነው! ሆኖም ግን አንተ በአንድ ወቅት መልካም
የጦሬ መሪ ነበርክ።የላኩህን ጦርነቶች በሙሉ በድል ተወጥተሃቸዋል የግዛቴን የሮምን ክብር
የመንግቴንም ሃያልነት አስጠብቀሃል ስለዚህም ምንም እንኳን ከፍርዴ ባታመልጥ ሞትህ ባይቀርም
ስለሰራሃው መልካም ስራ ግን ከሞተህ በፊት እንድትዝናና አደርግሃለሁ።ከደናግሎቼ የተመረጡትን
አቅርቡለት ከንጉሱም ወይን በዋንጫ ቅዱለት የደም ጥማት በአል እስኪደር እስኪገደል ድረስ ነፍሱን
ያስደስታት።
ንጉሥ፦
እኔ ንጉስ ቄሳር ከ ጥቁር ባህር እስከ አፍሪካ በረሃዎች፣ከአባይ ወንዝ አስከ አረብ በረሃዎች ከኤፍራጥስ
እስከ አትላንቲክ በላው ግዛቴ ማንም ሰው አዎ የትኛውም ገዥ ቃሌን አጥፎ ትዕዛዜን አልፈጽምም
ብሎ አያውቅም ምክንያቱም እኔ ንጉስ ቄሳር ነኝን።አንዴ ከተናገርኩ ቃሌን አልመልስም ይሁን ካልኩ
አደርገዋለሁ።ታደርገዋለህ ከደናግል ጋር ትተኛለህ በንጉሱ ወይንም ትሰክራለህ።ውሰዱና የተናገርኩትን
እንዲያደርግ አስገድዱት።የሮም መንግስት የማንም ባለዕዳ አትሆንም።
የጦር መሪ፦ (ማርሴለስን)
ንጉሥ፦
አሃሃ.....ሚስቱን ልጁን ሃምጡልኝ ያኔ ጀግንነቱን እናያለን።
እባክህ ንጉሥ ንጉስ ሆይ ቤተሰቦቼን አትጉዳቸው መቅጣት የፈለክ እንደሆነ እኔን እንዳሻህ ቅጣኝ።
ንጉሥ፦
ልጅ፦
ንጉሥ፦
አንግዲህ ወስን ከደናግል ጋር ነፍስህን አስደስት ከወይኑም ጠጣ ካልሆነ በልጅህ ህይወት ላይ ፍረድ።
ልጁን(የጦር መሪውን) ውሰዷት እና አንገቷን ቆርጣችሁ ጭንቅላቷን በሰሃን አምጡለት።
ልጅ፦
ሮጣ አባቷ እቅፍ ስር ገብታ እያለቀሰች አባዬ! አባዬ! እንዳይገሉኝ አባዬ አድነኝ አባዬ!!
ሚስት፦
አረ ባክህ የሚሉህን አድርግላቸው እግዚአብሔር እኮ የምህረት አምላክ ነው። ይቅር ይልሃል በአድ
ልጅህ በኤርማዳ አትፍረድባት።እጇን ዘርግታ አረ እኔን ውሰዱኝ ልጄን ተውአት በማለት በእንባ
ትማፀናለች።
የጦር መሪ፦
ልጅ፦
እያለቀሰች እየተማፀነች ቀስ በቀስ ድምጿ እየራቀ ይሄዳል......
ሚስት፦
ንጉስ፦
ጠባቂ፦
ንጉስ ሆይ ሽ አመት ንገስ! ከእጁ ለማስጣል ያላደረግነው ነገር የለም ግን ሞቴን አለ።
ንጉስ፦
ይጥላል በርግጥም ይጥላል! በእጅህ የያዝከውን ጣልና አድርግ ያልኩህን አድርግ ቢያንስ ሚስትህ
በህይወት ትኖራለች።
ንጉስ፦
የፌዝ ሳቅ እየሳቀ .... የታላቁ ቴርሜይ ምንጭ ወይስ የባላኒያ መጣቢያ ምንጭ ሃሃሃ....በሉ ከእጁ ላይ
ተቀበሉት
ጠባቂዎች ለመቀበል ይታገሉታል ይከለክላል....
ንጉስ፦
በእጅህ የያዝከውን ጣል አለዚያ ሚስትህን በኮሎሲየም አደባባይ ደም ጠምቶት ለሚጠብቀው ህዝቤ
የመስዋዕት ትሪት ነው የማደርጋት።ውሰዷት በኮሎሲየም ህዝብ በተሰበሰበበት አንገቷ በካራ ቁረጡት።
ሚስት፦
በለቅሶ አረ በአምላክህ ልለምንህ የሚሉህን እሺ በላቸው በእኔም ጨከንክ?
ንጉስ፦
በቁጣ....አልጥልም ነው ያልከው! እንደውም ልንገርህ አምላክህ እኔ ነኝ ተሰግደልኛለህ በእጂህ
የያዝከውን ትጥላለህ ወይኑንም ትጠጣለህ! እኔ ቄሳር ይህን ባላደርግብህ አማልክቶቼ ነፍሴን ከስጋዬ
ይነጥሏት። አሰግዱልኝ!!
ንጉሥ፦
በብስጭት ውሰዱት የስቃይ ጥግ አሳዩት ከጥፍሩ ጀምሮ ቀስበቀስ እያቃያችሁ ቆራርጡት መጨረሻ
ላይ በእሳት አቃጥላችሁ ግደሉት።
ንጉስ ሆይ በመጨረሻም አንድ ነገር ልንገርህ ጌታ ኢየሱስ ይወድሃል።አንተም በእርሱ አምነህ ነፍስህ
አትርፍ
እንግዳ ነኝ እኔ ስኖር በዚህ አለም
ቤቴ በሰማይ ነው..... መዝሙር የጦር መሪው(ማርሴለስን )እየዘመረ ይወጣል