Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 12

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ

የቴክኖሎጂ ምርምር ኢኖቬሽንና ሽግግር ዳይሬክቶሬት

በ 2014 በጀት ዓመት የተሰሩ(የተቀዱ) ቴክኖሎጂዎች ቶም ታዳሽ ቴክኖሎጂ ወደ


ትግበራ እንዲገቡ ለማድረግ የተዘጋጀ ረቂቅ ሰነድ

ሰኔ 2014 ዓ.ም

የዕቅዱ ይዘት

1. መግቢያ

2. የሰነዱ ዓላማ
3. የተካተቱ ተግባራት
o በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ

o በተግባር ምዕራፍ

Page 1
o በማጠቃለያ ምዕራፍ

1. መግቢያ

በሃገራችን እየተመዘገበያለውን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ይበልጥ በማሻሻልና በማስቀጠል ልማታዊ አስተሳሰብ
ጎልብቶ በህብረተሰቡ ውስጥ አምራች ዜጋን በመፍጠር የምርት/ማምረቻ እና የሃገር በቀል አገልግሎት/አሰራር
ቴክኖሎጂዎች አቅርቦትን ማሳደግ አስፈላጊ ነው፡፡

ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ማምጣት የሚቻለው የልማት ፕሮግራሞች መሪ መስሪያ ቤቶችን
ውጤታማነት እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ሲረጋገጥ በመሆኑ የበለፀጉ ሀገራት ሰፊ ጥናትና ምርምር
በማካሄድ ያፈለቁትን ቴክኖሎጂዎች በተለያየ መንገድ ወደ ሀገራችን አስገብቶ በመጠቀም የውጭ ምርትን
(Import substitution) መተካት የሚያስችል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ለዘርፉ የተሰጠውን ተልዕኮ ከመወጣት አንጻር ከእሴት ሰንሰለት
ትንተና በመነሳት አዋጭና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይች በማሸጋገር
ኢንተርፕራይቹ ሀብት አፍርተው ወደ ቀጣይ የእድገት ደረጃ አንዲሸጋገሩ እገዛ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ይህንኑ
ድጋፍ አጠናክሮ ለማስቀጠል ማሰልጠኛ ተቋማት የሰሯቸውን ቴክኖሎጂዎችን በየዓመቱ ለኢንተር ፕራይዞች
የማሸጋገር ስራ ሲሰራ ቆይተል። በመሆኑም በየአመቱ የሚሰሩ ቴክኖሎጂዎችን ለማሸጋገር አንዳንድ ማነቅ
የሆኑ ችግሮች መኖራቸው አይቀሬ ነው። እነዚህን ክፍተቶች ለመሙላት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን
ለመስራት ቢሮው እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

Page 2
2. በፍተሻ የተረጋገጠውን ቴክኖሎጂ የማሸጋገር ሂደት፡-

አንድ ቴክኖሎጂ ተለይቶ ንድፍ ተዘጋጅቶለት ከተሰራ በኋላ እንዲሁም የተሠራው ቴክኖሎጂ የፍተሻ ስራ
ተካሄዶበት ፍተሻውን ካለፈ በኋላ ወደ ማሸጋገር ስራ ይገባል፡፡ ከናሙናነት አንስቶ አባዝቶ ወደ ገበያ ለማሸጋገር
በመጀመሪያ አብዢዎችን የመለየትና እነሱን የማብቃት ስራ ሊሠራና ከዛም አልፎ ቴክኖሎጂውን ከገበያ ጋር
ማስተሳሰር ይገባል፡፡

2.1 የአብዢዎችን አቅም ክፍተት መለየት


አንድ ቴክኖሎጂ የፍተሻ ስራ ከተሠራበትና ፍተሻውን ካለፈ በኋላ የማብዛት ስራ ይሰራል፡፡ ቴክኖሎጂውን
ለማባዛት መጀመሪያ አብዢን መለየት ያስፈልጋል፡፡ አብዢዎችን ስንለይ ልንመለከታቸው ከሚገቡን ነጎሮች
መካከል ዋንኛው የአብዢዎቹን አቅም ማወቅ ነው፡፡ የአብዢዎችን አቅም ስንል የሰው ሀይል ብዛት እንዲሁም
እውቀትና ክህሎት፣ የማምረቻ ቴክኖሎጂ፣ የገንዘብ አቅምን ከግምት ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡ በኢትዮጵያ
ቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደት ውስጥ የማብዛቱን ስራ ሊሠሩ የሚችሉት የጥቃቅንና አነስተኛ እና በማኑፋክቸሪንግ
ዘርፍ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራዞች ናቸው፡፡ ከኢንተርፕራይዞቹ መካከል የተፈተሸውን ቴክኖሎጂ
ለማብዛት አቅሙ ያላቸውን መርጦ የማባዛት ስራውን እንዲሰሩ ማድረግ ነው፡፡

2.2 አብዢዎችን ማብቃት


የቴክኖሎጂው አብዢዎችን ከተለዩ በኋላ ያለባቸውን የክህሎት ክፍተት በመለየትና ክፍተቱን የሚሞላ ስልጠና
አዘጋጅቶ በመስጠት ማብቃት አስፈላጊ ነው፡፡ አብዢዎችን የማብቃት ስራ ሊሠራ የሚችለው በቴክኒክና ሙያ
ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ሲሆን እነዚህን አብዢዎች በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተደራጁ ነባርና አዲስ
ኢንተተርፕራይዞችን በማብቃት እንዲያባዙ ይደረጋል፡፡ የሚሸጋገረውን ቴክኖሎጂ በሚፈለገው ጊዜ ውስጥ
ጥራቱንና ብዛቱን ጠብቆ ለማምረት እንዲያስችል የሚያስፈልገውን እውቀትና ክህሎት የያዘ የሙያ ስብጥር
ያላቸው አንቀሳቃሾችን መምረጥና ማብቃት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መልኩ ቴክኖለሎጂው ከተሸጋገረ በኋላ
በአራቱ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት የድጋፍ ማዕቀፎች መሰረት ድጋፉን በመስጠት ቀጣይነት ባለው
መልኩ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን በመስራት ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ይሄም
ኢንተርፕራይዙን በስራ ፈጠራ ክህሎት በማብቃት ምርቱን በተለያየ መንገድ በማስተዋወቅ ቀጣይነት ባለው
መልኩ አምርተው እንዲጠቀሙና ቋሚ ደንበኞች እንዲኖራቸው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

2.3 ፋይዳ ዳሰሳ (Impact Assessment)


ፋይዳ ዳሰሳ በቴክኖሎጂው ሽግግር የመጣን ለውጥና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጡን የምናከናውንበት
ስልት ነው፡፡ይኽውም አንድ ታቀቦ የተሸጋገረን ቴክኖሎጂ በማህበረሰቡ ኑሮና ዕድገት ላይም ሆነ በተሸጋገረበት
ኢንዱስትሪ ምርት ጥራት፣ ብዛት፣ ምርታማነትና ገበያ ላይ ያመጣውን ለውጥ በዳሰሳ ጥናት ማረጋገጥ

Page 3
ካልተቻለ በስራው ወደፊት ለመቀጠል አዳጋች ነው፡፡ በየማሰልጠኛ ተቋማቱ ያሉ አሰልጣኞችም ሆኑ
የሠልጣኞች ሕይወት፣ የሥራ ባህሪና እንዲሁም በተቋማትና አብረዋቸው በሚሰሩት ጥቃቅንና አነስተኛ
የንግድ ተቋማት ላይ የፈጠረውም አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ተጽዕኖ በትክክል ተቀምሮ ሊቀመጥ ይገባል፡፡
ይህም ለወደፊት የአሠራር ሂደት ማስተካከያም ሆነ ማሻሻያ በሚደረግበት ጊዜ በተጨባጭ እንደ ማስረጃነት
ይጠቅማል፡፡

የፋይዳ ዳሰሳው በአሰልጣኝ፣ በተቋም፣ በክልልነሰ በፌዴራል ደረጃ የሚከናወን ሲሆን እንደ አጠቃላይ በዚህ
ዳሰሳ ጥናት የሚገኘው ውጤት በቀጣይ ቴክኖሎጂው ላይ ለሚደረገው ለውጥና ለእሴት ሰንሰለት ክለሳ እንደ
ግብዓት ያገለግላል፡፡

3. የሰነዱ አላማ፡-
3.1. ዋና አላማ፡-

በ 2014 በጀት አመት የተሰሩ (የተቀዱ) የማምረቻ፣የምርት እና የሀገር በቀል ቴከኖሎጂዎችን


ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለአብዢ ኢንተርፕራይዞች በማሸጋገር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን የተሻለ ውጤት
እንዲመጣ ለማድረግና እንዲሁም ቶም ታዳሽ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የአከባቢ የአየር ብክለት በመቀነስ
ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከፍ ማድረግ፣

3.2. ዝርዝር ዓላማዎች


በአጠቃላይ ለልማት ፕሮግራሞቻችን ተስማሚ የሆኑትን ቴክኖሎጂ መቅዳት እና የማሸጋገር ዓላማዎች፡-
 በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰመማሩ የአነስተኛ፣ መካከለኛ እና የኤክስፖርት ስታንዳርድ ማምረት ስራ
የደረሱ ኢንተርፕራይዞች ጋር በመሆን ምርትና ምርታማነት ለማሻሻል ሌሎች ያፈለቁትን
ቴክኖሎጂዎች ፈጥኖ በመኮረጅ ሀብት አፍርቶ አቅም ለመገንባት፣

 የሚሸጋገረው ቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዙ ሀብት እንዲያፈራ ከማስቻሉም በላይ ከውጭ የሚገቡ


ቴክኖሎጂዎችን በመተካት ለውጭ ምንዛሪ የሚወጣውን ገንዘብ ለማስቀረት እና ተወዳዳሪ ምርት
ለተጠቃሚ ማቅረብ፣

 የቀዳውን ቴክኖሎጂ በማላመድ በሂደት በማሻሻል ተጨማሪ ሀብት የመፍጠር አቅም በማጎልበት
ለቀጣዩ ስራ ከዘርፉ ተመራማሪዎችና ቴክኖሎጅስቶችን ማፍራት።

Page 4
 በተሸጋገሩላቸው ቴክኖሎጆዎች ኢንተርፕራይዞች ሃብት እንዲያፈሩ ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ
የበኩሉን ድርሻ መወጣት፣

 ከውጭ የሚገቡ ማሽኖች እና ምርቶችን ለማስቀረት የኢንተርፕራይዞችን አቅም ለማሳደግ ድጋፍ እና


ክትትል በማድረግ ማብቃት፣

 ህብረተሰቡ እና ኢንተርፕራይዞች ስለ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማብዛት ያላቸውን ግንዛቤ ማሳደግ፣

 በተገነባ አቅምና በፈራ ሀብት የተቀዳውን ቴክኖሎጂ በማላመድ በሂደት በማሻሻል ተጨማሪ ሀብት
ለመፍጠር፣

 ሌሎች ባለድረሻ አካላትን በማሳተፍ ስራዎችን በመገምገም፣በማረም እና ማስተካከያ በመስጠት


ውጤታማ ማድረግ፣

 እንደ መነሻ የተጀመረው ቴክኖሎጂ ቀጣይነት ባለው መልኩ መሰራት ይኖርበታል፣

4. የሰነዱ ወሰን፡-
ሰነዱ ተፈፃሚ የሚሆነው፡-

 በስራና ክህሎት ሚንስቴር (የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ሚንስቴር ዴታ) ፣


 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ፣
 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ እድል ፈጠራና እና ስምሪት ቢሮ ፣
 ቴክኖሎጂ የተሰራበት ኮሌጆች የክፍለ ከተማና የወረዳ ስራ እድል ፈጠራ ና ስምሪት ጽ/ቤት የክፍለ
ከተማ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልመት ጽ/ቤት ፣
 ቶም ታዳሽ ተቋም እና የቴክኖሎጂ አብዢ ኢንተርፕራይዞችን የሚያጠቃልል ይሆናል፡፡

Page 5
 የተግባሩ ሽፋን ደግሞ የቴክኖሎጂ ትግበራና ወደ ኢኮኖሚ መቀየር ስራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ
የሚተገበርና የሚከናወን ይሆናል፡፡

5. በበጀት አመቱ የተቀዱ፣የተሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎች በአይነት

5.1. የማምረቻ ቴክኖሎጂ


ተ. የቴክኖሎጂው ስም የቴክኖሎጂው ምስል ከውጪ ስገባ ሲቀዳ የዋጋ ንፅፅር
ቁ ዋጋው የወጣበት ዋጋ
1 የሳሙና ማምረቻ ማሽን
286,000 162,662.4 123,337.6

2 ዘመናዊ የቡና መቁያ 216,010 150,000


ማሽን

66,010.0
3 ብሪኬት ማሽን 123,410 67,210.52 56,199.5

የዘይት መጭመቂያና
4 ማሸጊያ ማሽን 163,280 101,763.69

61,516.3

5 የእምነ በረድ ማጠቢያ 201,410 167,898.6


ማሽን

33,511.4

5.2. የምርት ቴክኖሎጂ

Page 6
ተ. የቴክኖሎጂው ስም የቴክኖሎጂው ምስል ከውጪ ስገባ ሲቀዳ የዋጋ ንፅፅር
ቁ ዋጋው የወጣበት ዋጋ

1 ቬንዲንግ ማሽን 95,000 48,930

46,070

72,420 36,109.4
2 መልቲ ፐርፐዝ አልጋ

36,311

3 አውቶማቲክ ዊል ቸር
21,375 12,087.3

9,288

5.3. ሀገር-በቀል ቴክኖሎጂ


ተ. የቴክኖሎጂው ስም የቴክኖሎጂው ምስል ከውጪ ስገባ ሲቀዳ የዋጋ ንፅፅር
ቁ ዋጋው የወጣበት ዋጋ

አውቶማቲክ የሽመና
1 ማሽን 113,685 72,818.46

40,866.54

Page 7
አውቶማቲክ የክር
2 ማጠንጠኛ ማሽን 56,790 33,446.16

23,343.84

3 ሸክላ መስሪያ ማሽን 56,865 39,575.25

17,289.75

6. የባለ ድርሻ አካላት ተግባርና ሃላፊነት፣


6.1. የስራና ክሎት ሚንስቴር፡-
 አዳዲስና የተሻለ ሀሳቦች በማምታት እንደ ሀገር የተጀመረው የቴክኖሎጂ ሽግግር መደገፍ፣
 የተሰራው ሰነድ መነሻ በማድረግ ሰነዱን ማዳበር ፣
 ኢንተርፕራየዞች የተሻለ አቅም እንዲኖራቸው መንግስትና መግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ጋር
በማገናኘት አቅም እንዲፈጥሩ ማድረግ፣
 የስራና ክህሎት ሚንስቴር ይኸንን የመጀመሪያ ዙር የሚተገበረው በኮሌጆች የተሰሩ ቴክኖሎጂዎች
ውጤታማ እንዲሆን ማድረግ፣
 አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለህብረተሰቡ ለማስተላለፍ በቂ በጀት እንዲመደብ ማድረግ፣

6.2. የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ሚና፡-


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኖሎጂ ምርምር
ኢኖቬሽንና ሽግግር ዳይሬክቶሬት የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡-

• የተሰሩ ቴክኖሎጂን ከሚንስቴር መ/ቤት ጋር በመሆን ማሸጋገርና ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍና ክትትል
ማድረግ፣
• የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን ለሚንስቴር መ/ቤት ሪፖርት ያቀርባል፤
• በኮሌጆች ተቀድተው ለሚሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎች ወጥ በሆነ የቴክኖሎጂ ቅጂ በመለኪያ መስፈርቶች
መሰረት በማሸጋገር ሂደቱ ላይ የሚፈጠሩ ቅሬታዎችን ይፈታል፡፡

Page 8
በአጠቃላይ ለዘርፉ የተሰጠውን ተልዕኮ ከመወጣት አንጻር በስሩ ለሚገኙ ኮሌጆች ከላይ የወረደውን አቅጣጫ
ለኮሌጆች ካስኬድ በማድረግ ቴክኖሎጂ የመቅዳት እና የማሸጋገር ተልዕኮ ለማስፈፀም ኮሌጆች ከእሴት
ሰንሰለት ትንተና በመነሳት አዋጭና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይች
ለመቅዳት እና ለማሸጋገር ብሎም ኢንተርፕራይቹ ሀብት አፍርተው ወደ ቀጣይ የእድገት ደረጃ አንዲሸጋገሩ
ለማድረግ እና ተፈፃሚነቱን ለማረጋገጥ በየግዜው ለኮሌጆች ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ።

6.3. የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሚና፡-


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስር የሚገኙ ኮሌጆች
የሚከተሉት በቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደት ላይ የሚከተሉት ተግባራት ያከናውናል፡-
• በተቋም ደረጃ ቴክኖሎጂን በመቅዳትና በማሸጋገር ኢንተርፕራይዞች ሃብት እንዲያፈሩ ላደረጉት
አሰልጣኞች እውቅና ይሰጣል፣
• የተሸጋገሩት ቴክኖሎጂዎች በተጠቃሚዎቸና በህብረተሰቡ ላይ ያመጡትን ለውጦች ከሌሎች አካላት
ጋር በመሆን የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት ያደርጋል፣
• የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን ለቴክኒክና ሙያ ቢሮ ሪፖርት ያቀርባል፤ በአህዝቦት ስራ ለህብረተሰቡ
ግንዛቤ ይፈጥራል፣
በአጠቃላይ ኮሌጆች ለዘርፉ የተሰጠውን ተልዕኮ ከመወጣት አንጻር ከእሴት ሰንሰለት ትንተና
በመነሳት አዋጭና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይች በማሸጋገር
ኢንተርፕራይቹ ሀብት አፍርተው ወደ ቀጣይ የእድገት ደረጃ አንዲሸጋገሩ ሙያዊ ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ፡፡
ይህንኑ ድጋፍ አጠናክሮ ለማስቀጠል ማሰልጠኛ ኮሌጆች የሰሯቸውን ቴክኖሎጂዎችን በየዓመቱ ለኢንተር
ፕራይዞች የማሸጋገር ስራ ሚና እንዲወጡ ማስቻል።

6.4. የአሰልጣኞች ተግባርና ኃላፊነት

የቴ/ሙ/ት/ስ/ተቋማት አሰልጣኞች የማሰልጠን ስራዎቻቸው እንደተጠበቁ ሆነው ቴክኖሎጂ መቶ


ፐርሰንት በመቅዳትና በማሸጋገር ሂደት ላይ በጉልህ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ እስካሁን ድረስ ሶስቱም
የአሰልጣኝ ደረጃዎች (ኤ፣ቢና ሲ) ቴክኖሎጂን ለየብቻቸው (ኤ 3 ቴክኖሎጂ፣ ቢ አንድ ቴክኖሎጂና 5 ሲ
አሰልጣኞች በጋራ አንድ ቴክኖሎጂ) እያሸጋገሩ ይገኛሉ፡፡ ይህ አካሄድ ከቴክኖሎጀው ውጤታማነትና
ከአቅም መገነባባት አንጻር ክፍተት እየተስተዋለበት ይገኛል፡፡ ስለዚህ ሶስቱም ደረጃ ላይ የሚገኙ

Page 9
አሰልጣኞች ቴክኖሎጂዎች ላይ በጋራ እየተጋገዙ በመስራት ተፈላጊውን የቴክኖሎጂ ጥራት ማምጣት
እንዲሁም እውቀትና ክህሎትን በመለዋወጥ አቅማቸውን መገንባት ይኖርባቸዋል፡፡

 በሥራው ላይ ከሚሳተፉ አካሎች ጋር በመሆን የዕሴት ሰንሰለት ትንተና ለተዘጋጀላቸው


ምርቶች/አገልግሎት ችግሮቻቸውንና ክፍተታቸውን መለየት፣
 የተቋሙ ወርክሾፕ ቴክኖሎጂውን መቶ ፐርሰንት ለመቅዳት ደረጃውን የጠበቀና በቂ ግብዓቶች ያሟላ
መሆኑንና የሌሉትን ሚመለከተውን እነዲሟላ ይጠይቃል
 ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ ለመቅዳትና ለማሸጋገር በክህሎት፣ በእውቀትና በአመለካከት ራሱን
ማዘጋጀት እና እንዲሁም ከስራ ክፍሉ ባልደረቦች ጋር በቡድን ለማከናወን ራሱን ማዘጋጀት፤
 ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ ለመቅዳት በወጣው የአሰራር ማኑዋል፣ የአፈጻጸም መመሪያና ሌሎች
አስፈላጊ ሰነዶች ላይ ተገቢውን ግንዛቤ መያዝ፣
 ለቴክኖሎጂ መቶ ፐርሰንት መቅዳት ስራ ውጤታማነት ትኩረት በመስጠት ኤ ለቢ እና ቢ ለሲ ድጋፍና
ክትትል ማድረግ፤
 ክፍተቶቻቸው ለተለየላቸው የምርቶች/አገልግሎቶች አስፈላጊውን የቴክኖሎጂ አማራጮችን
ማፈላለግና መለየት፣ ከተለዩትም ውስጥ የአዋጭነት ትንተና በማከናወን ምርጡን ቴክኖሎጂ
መምረጥ፣
 ለተመረጠው ቴክኖሎጂ ንድፍ (የቴክኖሎጂ ልኬትና ምስል፣ የአመራረት ሂደት፣ የአሰራር ማኑዋልና
የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎችን ዝርዝር) የያዘ ሰነድ ማዘጋጀት፣
 ቴክኖሎጂውን መቶ ፐርሰንት ለመቅዳት የሚያስፈልጉ ወጭዎች አዘጋጅቶ ማቅረብ፤
 በተዘጋጀው ንድፍ መሠረት ደረጃውን የጠበቀ ናሙና ማዘጋጀትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር
በተከታታይ ፍተሻ ማካሄድ፣
 ተፈትሸው ባለፉ ናሙናዎች ላይ ወደፊት አምርተው ለሚያስተላልፉ አብዢ ኢንተርፕራይዞችን
ስለአሠራሩ/ስለአመራረቱ ስልጠና በመስጠት ማብቃት፣
 መቶ ፐርሰንት ተቀድቶ ለተሸጋገረው ቴክኖሎጂ ውጤታማነት ትኩረት ሰጥቶ ለጥ/አ እና
በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በአ/መ ለተሰማሩት ኢንተርፕራይዞች ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤

Page 10
7. ቴክኖሎጆዎችን በመቅዳት እና በማሸጋገር ሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ መልካም አጋጣሚዎች፣ስጋቶች፣ጥንካሬዎች እና

ድክመቶች (SWOT Analysis) ፡-

በጥንካሬ ድክመቶች
 ቴክኖሎጂዎች የኮሌጆችን አቅም ባገናዘበ መልኩ ተቆጥሮ  የሚሰሩ ቴክኖሎጂዎች ጥራት በሚፈለገው መልኩ
የተሰጣቸው መሆን፣ ያለመምጣት፣
 ቴክኖሎጂዎች ከፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በመነሳት መሰራት  ኤልከትሮ መካኒካል ክፍሉ በሚፈለገው መልኩ ያለመስራት፣
መቻላቸው፣  ቴክኖሎጂ 100% ኮፒ የማድረግ አቅም ውስንነት
 ሁሉም የሚሰሩ ቴክኖሎጂዎች የእሴት ሰንሰለት  በሚሸጋገሩ ቴክኖሎጆዎች በሚጠበቀው መሊኩ ኢምፖርት
የተሰራላቸው መሆን፣ ሰብስቲቱዩሽን ውጤት ያለማምጣት፣ በበቂ ሁኔታ ድጋፍ እና
 ቴክኖሎጂዎች በዘርፍ ተለይተው መቅረባቸው ክትትል ያለማድረግ፣
 የቴክኖሎጂ ስራው ከአብዢ ኢንተርፕራይዙ ጋር በጋራ  አሰልጣኞች ቴክኖሎጂ ሲሰሩ ለደረጃ እድገት በሚል እሳቤ ብቻ
መሰራት መቻሉ፣
መስራታቸው
 የተሰሩ እና የተሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎች ሙሉ በሙሉ በሰነድ
መቀመጣቸው፣
SWOT
መልካም አጋጣሚዎች ስጋቶች
 በመንግስት ፖሊሲ እና እስትራቴጂ የሚደገፍ በመሆኑ፣  በበቂ ሁኔታ የላቁ (advanced) የሆኑ ማሽነሪዎች ያለመኖር፣
 የኢንተርፕራይዞች የቦታ ዉስን መሆን፣
 ከግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ እና ተሳትፎ መኖሩ  ኢንተርፕራይዞች በተለያየ ምክንያት ስራ ማቆም፣
 ለአብዢነት የተመረጡ ኢንተርፕራይዞች ቴክኖሎጆዎችን
 ከሌላው ግዜ በተሻለ መልኩ ለሚሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎች
አባዝቶ ወደገበያ ለማስገባት የፈይናንስ መኖር፣
ትኩረት በመስጠት እንቅስቃሴ እየተደረገ በመሆኑ፣
 ተጠቃሚ እንተርፕራይዞች የሀገር ውስጥ ምርት የመጠቀም
ባህልን ያለማዳበር፣

Page 11
8. ማጠቃለያ
በአጠቃላይ በ 2014 ዓ.ም የተሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎች

• ከዚህ በፊት ከነበረው በተሻለ መልኩ ቴክኖሎጂዎችን ማሸጋገር መቻሉ፣


• አብዛኛዎቹ የተሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎች በ 2013 ዓ.ም እና ከዚያ በፊት ያልተሸጋገሩና አዳዲስ ስራዎች
መሆናቸው፣
• ይሁን እንጂ ቴክኖሎጂ ማሸጋገር እና በቂ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ ላይ አሁንም ክፈተቶች
ተስተውሏል፣
• አንዳንድ ኮሌጆች ካላቸው አቅምና አደረጃጀት አንፃር ውጤታማ የሆነ ቴክኖሎጂን የማሸጋገር ስራ
አነስተኛ መሆን፣
• ስለሆነም የተቋም አመራሮች፣ አሰልጣኞችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች እነዚህን ችግሮች
በጋራ በመቅረፍ በቀጣይ የተሻለ ስራ እንዲሰራ የድርሻቸውን ኃላፊነትና ተግባር ለመወጣት
ተከታታይነት ያለው ክትትልና ድጋፍ ማድረግና የማስተካከያ ዕርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል።
ስለሆነም የተቋም አመራሮች፣ አሰልጣኞችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች እነዚህን ችግሮች በጋራ
በመቅረፍ በቀጣይ የተሻለ ስራ እንዲሰራ የድርሻቸውን ኃላፊነትና ተግባር ለመወጣት ተከታታይነት ያለው
ክትትልና ድጋፍ ማድረግና የማስተካከያ ዕርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል።

Page 12

You might also like