Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

ወልቃይት ጠገዴ ስሜን ጃናሞራ ፣

ሰውም ጎንደሬ ነው፣ መሬቱም የአማራ (ሻምበል በላይነህ)።


ይድረስ ለሳኦላዊያን‼‼‼

( "እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ!")

* ቀደምት እስራኤላውያን እንደሌላ ህዝቦች ንጉሥ አልነበራቸውም ነበር። ህዝቡ ንጉሥ ካልሾምህልን ብሎ
በእግዚአብሔር ላይ ማጉረምረሙ ሲበዛ፥ ከመካከላቸው ሳኦልን ንጉሥ አድርጎ ቀባላቸውና በምድራዊው ሥርዓት
መተዳደር ጀመሩ። ጥንት እስራኤላዊያኑ አባቶቻቸው ከግብፅ ባርነት ነፃ ወጥተው ወደ ተስፋዪቱ ምድር ሲጓዙ ብዙ
ግፍና መከራ አይተዋል። ዘግናኝ ጭፍጨፋና ግፍ ከፈፀሙባቸው ህዝቦች መካከልም አማሌቃውያን የቀዳሚነቱን ሥፍራ
ይይዛሉ።

እግዚአብሔርም አማሌቃዊያን በግፍ ስላፈሰሱት ነፍስ ሊበቀል ተነሳ። በነብዩ ሳሙኤል በኩልም እንዲህ ሲል መልዕክት
ላከበት፦ "እስራኤል ከግብፅ ሲወጣ፥ አማሌቅ በመንገድ እየተቃወመ ያደረገበትን ሁሉ እበቀላለሁ። ወደ አማሌቅ ምድር
ውጣ፣ በዚያም ያገኘኸውን ታናሹንና ታላቁን፣ ንጉሱንና ባለሟሉን እንስሳውንም አጥፋ" የሚል ትዕዛዝ ተሰጠው።
ሳኦልም ወደ አማሌቅ ወረደ፣ እንደታዘዘውም ታላላቅና ታናናሹን አጠፋ፤ ነገር ግን ከእንስሳው መካከል ለሰቡ ፍሪዳዎችና
ጠቦቶች ዐይኑ ጎመጀ፣ የአማሌቅ ንጉስ የነበረውን አጋግንም በህይወት ማርኮ አመጣው።

እግዚአብሔርም በሳኦል አለመታዘዝ ተቆጣ፤ ሳሙኤልንም በድጋሚ ወደ ሳኦል ላከው። ሳሙኤልም ወደ ሳኦል በቀረበ
ጊዜ "ይህ የምሰማው የኮርማዎችና የጠቦቶች ጩኸት ምንድነው?" ሲል ጠየቀው። የራሱን የቁስ ሰቀቀንና የሆዳምነት
ችግሩን ለመደበቅ ሲል ሳኦል ለእግዚአብሔር የተቆረቆረ በመምሰል፦ "ፍሪዳዎቹንና ጠቦቶቹን ለእግዚአብሔር መስዋዕት
አቀርባቸው ዘንድ አመጣኋቸው" አለ። ሳሙኤልም አስደንጋጩን መርዶ እንዲህ ሲል አረዳው፦ "መታዘዝ ከመስዋዕት
ማቅረብ አይበልጥምን? እነሆ ዛሬ እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ!" አለው።

ከዚያች ቅፅበት ጀምሮ ከልጁ ዮናታን ጋር በጦርሜዳ እስከሞተበት ቀን ድረስ ለ 20 ዓመታት ሠላምና ድል የራቀው
ተቅበዝባዥ ሆኖ ኖረ።

በአማራ ስም የሚነግዱ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ታዋቂ ሰዎች፣.....ወዘተ በሙሉ፥ በግብራቸው የሳኦል ወራሾች
ሳኦላዊያን መሆናቸውን በተግባር በተደጋጋሚ አሳይተውናል።

አሊ ቢራ የሚባል አዝማሪ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አርጅቶና ጃጅቶ ነው። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፥ ይህ ግለሰብ
በ 1980 ዎቹ ውስጥ የሙሉ አልበም ሽያጩን ለኦነግ የጥፋት ፖለቲካ በማዋል በያኔው ወለጋ ክፍለሀገር አሶሳ ከተማ
በአማራዊያን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ድርጊት የደገፈ ሰው ነው። በሌሎች ፖለቲካዊ ዘፈኖቹም አማራን በብሔራዊ
ጨቋኝነት ፈርጆ ሲቀሰቅስ የኖረና በቅርቡም የሐጫሉን ሞት ተከትሎ የጃዋር መሐመድ ሚዲያ ላይቭ በቀሰቀሰው
በአማራ ህዝብ ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጄኖሳይድ ደግፎ በሚዲያ የተናገረ ሰው ነው።

ሳኦላዊያኑ በአማራ ጭምብል የሚነግዱ ልሂቃን ታዲያ፥ "ነፍስ ይማር ማለት ባህላችን ነው" በሚል ሳኦላዊ የቅጥፈት
ሽፋን ተደብቀው፥ አጉል እወደድ ባይነትና ዘመኑን መስሎ ለማደር ካላቸው ተንበርካኪነት በመነሳት ዋነኛ ሙሾ አውራጅ
ሆነው ተከስተዋል።
የራሱ ልሂቃን በገዛ ወገኑ ደም ላይ በዚህ መጠንና ልክ እየተረማመደበት፥ እግዚአብሔርስ እንዴት ስራውን ይስራ⁉
ፍርዱንስ በየት በኩል ይከውን⁉

እግዚአብሔር ነብዩ ዳዊትን "እንደልቤ" ሲል የጠራው፥ አንድም ዳዊት ቆምጫጫና አንገቱን የሚሰብር ተንበርካኪ
ስላልነበር ነው።

ከአማራ ልሂቅ ውስጥ በጠላቶቹ ላይ ቂሙን ሳይረሳ በአቋሙ የዘለቀ ሰው ማግኘት እጅግ ከባድ እየሆነ ከመጣ
ሰነባብቷል። ለፈጣሪ ፍርድ እንቅፋት የሚሆን፣ ለሰውም እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ሳኦላዊ ጠባይ የተጣባው ልሂቅ በሞላበት
ሁኔታ፥ ስለ ነፃነትና ፍትሕ ማሰብ እጅግ ከባድና አድካሚ ነው።

አይቆጣም፣ አያጉረመርምም፣ አያኮርፍም፣ እርም በወገኖቼ ደም ላይ ብረማመድ ብሎ ቃልኪዳን አይገባም። ከመጣ


ከሄደው ጋር ይዳራል፣ የወገኖቹን አራጅ አስደስቶ አጉል ተወዳጅነትን ባተርፍ ብሎ ያሰላል።

የእኛ ልሂቅ ክንዱ የሚበረታው እርስበርስ ለመበላላትና ወንድም ወንድሙን ጠልፎ ለመጣል ብቻ ነው።

አሊ ቢራ በዕሜው መጃጀት ምክንያት በመሞቱ የሚፀፅተኝ አንድና ብቸኛ ጉዳይ ቢኖረኝ፥ ፍትህ ሳይበየንበት እንዲሁ
በማምለጡ ብቻ ነው‼‼‼

የወገኖቹ ቁስል የሚያመው ቆንጆው የአማራ ትውልድ እስኪፈጠር ድረስ፥ የሚነጥፍ ብዕር አይኖረንም‼‼‼

ኃፍረት በቁማቸው ለሞቱ ሳኦላዊያን‼‼‼

ዴቭ ዳዊት።

Amharawiw Man

2ቀ ·

#አምሓራ/አማራ/ ሦስት ዋነኛ ጥንተ መሠረቶች ያሉት ነው። ልጅ ተድላ መላኩ!

ቀዳሚው ጥንተ መሠረቱ ከከለዳውያን ከጥንተ መስጴጦሚያ የሚመዘዘው የአግዓዚያን (ቀደምት ሳባውያን እና
ሕምያራውያን) ማንነት ነው። ነገደ ዮቅጣን የሚባለው ይኽ ነው። በተጨማሪ ደግሞ የጥንተ እሥራኤላውያን ዘር ያለው
ነው። ይኽ ደግሞ ከንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ጀምሮ የተዋሐደ ሲኾን የአምሓራ ነገሥታት ሐረግ የሚመዘዘው ከዚኽ ነው።
ሕዝቡም ራሱ የጥንተ እሥራኤላውያን ደም ያለው ሲኾን በእምነትና በባሕልም ከዚያ ከመጀመሪያው ምኵራብ ዘመን
የሚቀዳ ማንነት አለው። እነዚኽ ሴማውያን ናቸው። ሌላው ደግሞ የቀደምት አገው ማንነት ነው። ቀደምት አገው
የሚባለው ጥንት የነበረና አኹን በጥንተ ውሕደት ወደ አምሓራ ማንነትና ዘመናዊ አገው ማንነት ያደገ ነው።

ይሁዳ የሚባለው ነገድ እንጅ ሃይማኖት አይደለም። መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ከእናቱ ከድንግል ማርያም
በሥጋ ከይሁዳ ነገድ የተገኘ ነው። ዮቅጣንና አብርሃም ከኤቦር የሚወለዱ እንደመኾናቸው ኹለቱም ካንድ ግንድ ናቸው።
ነገር ግን አምሓራ ከኹለቱም፣ ከዮቅጣንም፣ ከአብርሃምም የተገኘ እንደመኾኑ የዮቅጣን ዘር ብቻ አይደለም። መታወቅ
ያለበት ነገር እሥራኤል ሲባል የዛሬዎቹን ከአውሮጳና ከመላው ዐለም የተሰባሰቡን አይሁዶች ማለት ሳይኾን የነርሱ
ዅሉ ጥንተ አያቶች የነበሩን የንጉሥ ሰሎሞን፣ የንጉሥ ዳዊት ዘመን እሥራኤላውያንን ነው። የዛሬዎቹ አሽከናዝ እና
ሴፋርዲ አይሁዶች ከነጭ አውሮፓውያን ጋር የተዳቀሉ ናቸው። ከነርሱም በላይ በእኛ ዘንድ የጥንተ እሥራኤላውያን
ባሕል፣ እምነትና ሥነ ልቡና አለ። ለምሳሌ ከእኛ በቀር በመላው ዐለም የታቦተ እሥራኤል የአምልኮ ባሕልና ትርክት
ያለው የለም። ነጠላችን ላይ ያለው ጥለትና ቁጭት ሳይቀር የጥንተ እሥራኤላውያን የዕብራውያን ያምልኮ ባሕል ነው።
ያጼ ፋሲል ቤተመንግሥት ውስጥ ገብተኽ ማየት እንደምትችለው የማንነት ምልክት ተደርጎ በውስጥ ከግንቡ ላይ ያለው
የዳዊት ኮከብ ነው። ዘርና ማንነቱን ከጥንተ እሥራኤላውያን ነገሥታት የሚቆጥር በዐለም ብቸኛው ሰሎሞናዊ ሥርወ
መንግሥት ከእኛው ሕዝብና ማንነት የሚፈልቅ ነው።

መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የዳዊት ሥር (ዘር) ተብሎ ነው በዮሓንስ ራዕይ የሚጠራው። የእኛ ነገሥታት፣ የእነ አፄ
ዘርዓ ያዕቆብን ሥራዎች ከተመለከትኽ የእሥራኤላውያን ወራሾች እኛ ነን ብለው ነው የሚያምኑት። በተጨማሪም
ከመጽሐፍ ቅዱስ ቀጥሎ ታላቁ የማንነታችን፣ የምንጭና መሠረታችን መጽሐፍ ክብረ ነገሥት የሚባለው ነው። ክብረ
ነገሥቱም የሚለን፣ ነገሥታትና ሕዝባችንም የሚያምኑት እኛው የጥንተ እሥራኤላውያን ወራሾች መኾናችንን ነው።
ዛሬ ደግሞ ይኽ ያባቶቻችን የማንነት ትርክት ሳይንሳዊ የዘረመል ድጋፍ ያለው ኾኖ ተገኝቶአል። አኹን በተለይ አዳዲስ
ትርክቶችን በመፍጠር ይኽን ማንነታችንን ለማጥፋት ብዙ ተሠርቶአል

You might also like