Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 18

ዜሮነት

ዜሮነት

እንደ እውነት ከሆነ የብዙ ነገር ችግር ሰውነትን ካለማወቅ ይጀምራል፡፡ሰውነትን ዓለማወቅ የአለም ትልቁ

ችግር ነው፡: ሰውነትን ዓለማወቅ በከፊል ማወቅና አለመረዳት በራሱ ችግር ቢሆንም ከዚህ አለማወቅና

አለመረዳት ተነስቶ ለሰውነት የተሰጠው ትርጉም ደግሞ በራሱ ሌላ ችግር ነው፡፡ሰውነትን ካለማወቅና

ካለመረዳት በመነጨ ትርጉም ላይ ተመስርቶ አለምን፣ አህጉርን፣ አገርን፣ ከተማን፣ መንደርን እንዲሁም

ሐይማኖት እና እምነትን ለመረዳት መሞከር አሁን ችግሩን በአላት ላይ መመስረት ነው፡፡

Human being, culture-bearing primate classified in the genus Homo,

especially the species H. sapiens. Human beings are anatomically

similar and related to the great apes but are distinguished by a more

highly developed brain and a resultant capacity for articulate

speech and abstract reasoning.

ከስህተት መረዳት በመነሳት አምላክንም እምነትንም ፣ፍልስፍናንም፣ሰውንም፣አገርንም፣ ወዘተ ማወቅ

አይችልም፡፡ ይህ በስህተትና ስህተት ላይ በመነሳት የሚሰጥን ትርጉም፣ ትምህርት፣ፍልስፍና ፣የሥነ

መለኮት፣የሳይንስ ወዘተ እያልን ብንጠራው የነገሩን ማንነት መረዳታችን አያርመውም፡፡ ለዚያም ነው

አለም የስህተት አስተሳሰቦች ውጤትና የልዩነት መድረክ የሆነችው፡፡ ለዚያም ነው አለም አንድ ነገር በነገሩ

ማንነት መረዳትና ማወቅ የተሳነው፡፡ ይሄ ልዩነት ነው ወደ አምባጓሮና ጦርነት የሚወስደው፡፡

ሰውነትን በልኩ መረዳት ሌላን ነገር በልኩ ከመረዳት ለሰው ይጠቅማል፡፡ ሰውነትን በልኩ የተረዳ ሰው

ሌላውን ለመረዳት መሰረት ማድረግ ይችላል፡፡ ሰውነትን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ያልተረዳ ሰው

ከሰውነት ውጭ ያለን ምንም ነገር ሊረዳና ሊያውቅ አይችልም፡፡

አዲስቱ አለም ሰውነት ካለመረዳት በመነጨ ማንነት ላይ እምነትን፣ሐይማኖትን፣ አስተሳሰብን፣አገርን

ወዘተ መስርታለች፡፡

ከዚህ ላይ በመነሳት አምላካን፣ሰውን፣ሰማይና ምድርን፣ ፍልስፍናን፣አገርን፣ቤተሰብን፣ መስርታለች፡፡

Human identity is a magical mixture of mindset, values, behavior,

skills, attitude and external appearance. All these are influenced by

childhoods, family and social backgrounds. Each

individual identity is unique, like a fingerprint.

በሙላት ታዘበዉ 1
ዜሮነት

ሰውን የስሜት ህዋስ አድርገነዋል፡፡ ሰውነት ቁስ ሆኗል፡፡ የሰውነት ማንነቱ አፈር ሆኗል፡፡ ከቲማቲምና

ካሮት እጥረት የሚከሳውና የሚሞተውን ሰው ብለነዋል፡፡ የወባ ትንኝን የማይገድለው በአይን የማይታይ

ተህዋስ የሚገድለውን ገላ ሰው ብለን ጠርተንዋል፡፡ ሰውን ከሁሉም ነገር አሳንሰን አካል አድርገነዋል፡፡

ሰው ዐይን፣አፍንጫ፣ጆሮ፣አይን ሆኗል፡፡ በጆሮ የሚሰማው፣በአይን የሚያየው፣ በአፍንጫ የሚያሸተውን፣

ሰው ረስተነዋል፡፡ ጆሮ የሰው አካል አይደለም፡፡ አይን የሰው አካል አይደለም፡፡ የሰው ቁሳቁስ ናቸው፡፡ ሰው

አካል (Body) አይደለም፡፡ የአካል ክፍል የሚኖረው አካል ካለ ነው፡፡ በአፉ የሚናገረው ሰው ኦሮሞ፣

አማራ፣ ትግሬ፣ ነጭ፣ ጥቁር፣ የተማረ፣ ያልተማረ፣ ወፍራም፣ ቀጭን አይባልም፡፡ ሰው ሀሳብ እንጂ አካል

አይደለም፡፡ የባራክ ኦባማ ሀሳብ ጥቁር አይደለም፡፡ የትራምፕ ሀሳብ ነጭ አይደለም፡፡ ሀሳብ የኦሮሞ

የአማራ ፣ የትግሬ የነጭ ፣ የጥቁር፣ የኬንያ፣ የሱዳን ወዘተ አይባልም፡፡ ማንነት የለውም፡፡ አካል ቁጭ ቢል

ሀሳብ አይቀመጥም፡፡ አካል ተኝቶ ሀሳብ አይተኛም፡፡አካል ተጋጭቶም ታርቆም፣ አንድ ሆኖና ተለያይቶም

አያውቅም፡፡የሚጋጨው የሚታረቀው ሀሳብ ነው፡፡ ሰው ሀሳብ ነው፡፡ የሚራመደው

የሚቀመጠው፣የሚቆመው ወዘተ ሀሳብ ነው እንጂ አካል አይደለም፡፡ አለም አካልን አግዝፎ

ሀሳብን/ሰውነትን/ አሳንሶታል፡፡ አካል ሳይሆን ሀሳብ ያለው ሀሳብ ነው አካል ያለው፡፡ ሀሳብ አንድ ነው፡፡

የሰው አንድነት ምንጩ የሰውን ማንነት ሀሳብ ከሆነ ነዉ፡፡

Family, a group of persons united by the ties of marriage, blood, or

adoption, constituting a single household and interacting with each

other in their respective social positions, usually those of spouses,

parents, children, and siblings.

አካል የመሰረተውን አባት፣ እናት እህት፣ ወንድም ፣ ሚስት ፣ ባል ፣ሴት ፣ ወንድ ፣ ትንሽ ፣ ትልቅ ፣የተማረ

፣ ያልተማረ ወዘተ አያውቅም፡፡ሀሳብ ቤተሰብ ሌላ የለውም ፡፡ ቤተሰቡ ሀሳብ ነው፡፡ ሀሳብ ብሔር የለውም፡፡

እድሜ ፣ቁመት፣ ቀለም፣ዘር ወዘተ የለውም፡፡ ሰው አካል የለውም፡፡ አይን፣ አፍንጫ፣ ጆሮ፣ እጅ ፣ እግር

፣ልብ ፣ኩላሊት ወዘተ ሀሳብ አይደሉም፡፡ ሰው አይደሉም፡፡ ቲማቲም፣ ገብስ፣ ስንዴ፣ ቃሪያ፣ ማንጎ፣ ጤፍ፣

ውሀ በአጠቃላይ አፈር ናቸው፡፡ሰውነት ከዚህ ይበልጣል፡፡ አንጻራዊነት የለውም፡፡ሰውነትን በአካልነት

ከወሰድነው ከእንስሳትና ከእጸዋት አይደለም፡፡ እነዚህ የሰው መገልገያ ቁሳቁስ ናቸው እንጂ ሰው አይደለም፡፡

ሰው ቋንቋ የለውም፡፡አገር የለውም፡፡ቤተሰብ የለውም፡፡መልክየለውም፡፡ቁመትየለውም፡፡እምነት የለውም፡፡

በሙላት ታዘበዉ 2
ዜሮነት

ሐይማኖት የለውም፡፡ ምንም የለውም፡፡ሰውነት ባዶነት ነው፡፡ ማንነት አልባነት ነው በአጠቃላይ ዜሮነት

ነው፡፡

ዜሮነት የአካልነት ተቃራኒ ነው፡፡የሰውነት የሀሳብ ዜሮነት እና አካል 1-2-3-4 ነት ነው አርማጌድዮን

የተባለውን ጦርነት የፈጠረዉ፡፡ አካል ቤተሰብ አለው ፡፡ አፈር ቤተሰቡ አፈር ነው ፡፡ ጥቁር አፈር ጥቁር

አፍርን ቤተሰብ ዘመድ ይለዋል፡፡ ነጭ አፈር ነጭ አፈርን ዘመድ ቤተሰብ ይለዋል፡ አካል ቋንቋ፣ሀይማኖት

፣እምነት ዘር ፣አገር፣ አህጉር፣ ቁመት ፣ ክብደት ፣ቤት አለው፡፡ሀሳብ የሆነዉ ሰው በመኪና ሄዶ አያውቅም፡፡

በምንም ሄዶም ቀርቶም አያውቅም፡፡ አሮጌው አዳም አካልነት ነው፡፡ ቁስነት ነው፡፡ አዲሱ አዳም ኢ-

አካልነት ነው፡፡ አካልን መስቀል ነው፡፡ አካል ላይ መፍረድ ነው፡፡ ለሰውነት ሲኦሉ አካልነት ነው፡፡ ለሰውነት

ጽድቁ/መንግስተ ሰማያዊነት/ሀሳባዊነቱ መንፈሳዊነቱ ነው፡፡ ንጽጽር ፣ ውድድር ፣ ልዩነት፣ ዝርዝር ፣ቁጥር

ወዘተ አካላዊነት ነው ፡፡ አካላዊነት ተፈጥሮአዊ አይደለም፡፡ አካላዊነት ሰውነት አይደለም፡፡አካላዊነት

መልካሙን እና ክፉን ማወቅ ነው፡፡

አካላዊነት ራቁትነትን ማወቅ ነው፡፡ መንፈሳዊነት ዜሮነት ነው፡፡ ይሄ ትምህርት እውቀት ፣እምነት

፣ሐይማኖት ፣መገለጥ መንፈሳዊነት አላማዊነት፣ ፍልስፍና አይደለም፡፡ እውነት መንገድ እና ህይወት ነው ፡፡

በዚህ እውነት ማንም ከማን አይበልጥም አያንስም፡፡ በዚህ መንገድ ሰው ዘላለማዊ ነው፡፡ መንፈሳዊ ነው ፡፡

ወደ አብ ነት የሚያደርሰው መንገድ ይህ ነው፡፡ በዚህ ህይወት ህያውነት ይቀጥላል፡፡

የኢየሱስ ማንነት ልጅነት ይህ ነበር፡፡ ዜሮነት ነበር፡፡ አባት የማንነት ምንጭ ነበር፡፡ የአብ ፈቃድ

ማለፊያነት ነበር ፡፡የአብ ፈቃድ ማለፊያነት ነበር፡፡ አካልነትን መግደል ነበር፡፡ አሁን ያለው ገሀነም ወይንም

ሲኦል አካልነት ነው፡፡ እሳት ፣ ውሀ፣ አፈርነትና ነፍስነት ነው፡፡ ከሰውነት ውጭ ነው፡፡

አሁን ያለው ገነት/መንግስተ ሰማያት/ አብነት ነው፡፡ ዜሮነት ነው፡፡ “ከራሴ አንዳች አላደርግም” ማለት

ነው፡፡ አለመቁጠር ነው፡፡ ምህረትም ርህራሄም ይሄ ነው፡፡ ከዜሮ በላይ ጸድቅ ራህራሄ፣ ምህረት ፣ የዋህነትና

በጎነት የለም፡፡ ሰውነት ቋንቋው ዜሮነት ነው፡፡ ማለፊያነት ነው፡፡ ፈቃድ አልባነት ነው፡፡ ከራሱ የሚጀምር

ምንም ነገር የለም፡፡ ሰውነት መጀመሪያና መጨረሻ የለውም፡፡ እልፍና ኦሜጋ ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሔር

መልክ ነው፡፡ ጥልቅ ነው ፡፡መንግስት (Kingdom) ነው፡፡ ዜሮነት ነው፡፡

ይሄ አሁን እየሰማነው ያለው ሰውነት ነው፡፡ ሀሳብ ነው፡፡ ኦሮሞ ፣አማራ አገው ፣ ጉራጌ ፣ ኬንያዊ ፣ጥቁር ፣

ነጭ አይደለም፡፡ እድሜ ልምድ እና እውቀት የለውም፡፡ አውሮፓዊ፣ አሜሪካዊ፣ ካናዳዊ ወይንም ካርታና

ፓስፖርት አይደለም፡፡

በሙላት ታዘበዉ 3
ዜሮነት

ፍልስፍና ወይንም ሳይንስ ወይንም ፖለቲካ ወይንም እምነት አይደለም፡፡ አለማዊነት ወይንም

መንፈሳዊነት አይደለም፡፡ እውነት ነው፡፡ ያለዚህ እውነት ሰውነት የለም፡፡ አብ የለም፤ ሰላም የለም፡፡

በዚህ የህይወት ስርዓት ነገሮች ይሆናሉ እንጂ ማድረግ አይችልም፡፡ ጆሮ የአብ ማዳመጫ ፣አይን የአብ

ማያ፤ አፍንጫ የአብ ማሽተቻ፤ አፍ የአብ መናገሪያ፤ ወዘተ ይሆናል እንጂ ሰው አይናገርም፡፡

የእግዚአብሔር መንግስት ይሄ ነው፡፡ ለዚህ ለአብ ሚደሪያነት ራስን መልቀቅና ማስገዛት ዜሮነት/ ልጅነት/

ነው፡፡ ኢየሱስነት ነው፡፡

መሪነት ይሄ ነው፡፡ እናቴ ፣አባቴ፣ ልጆቼ፣ አላማዊነት ነው፡፡ እንኳን ሌላውን ራስን የራስ አለማድረግ ነው፡፡

ዜሮነት ራስን መካድ ነው፡፡ ኢየሱስን መምሰል ነው፡፡ መሪነት የአብ ልጅነት ነው፡፡ማለፊያት ነው፡፡ ይህ ነው

የአዲስ ኪዳን አዲሱ ልሳን፡፡ሰው የማይገባዉ ቋንቋ ይህ ነው፡፡

አንተ አልሞትህም ፤የራስህ ህይወት አለህ፤ ስላልሞትህ ቤተሰብ አለህ፣ ራስህ፤ አገር፤አለህ ፣ቋንቋ አለህ፤

ወንድም አለህ፣ ድግሪ አለህ፤ ወዘተ ሁሉ አለህ፤ሁሉ ስላለህ ህይወት አያስፈልግህም፡፡ ለአካል/ ለዚህ አለም

ያልሞተ ህይወት አያስፈልገውም፡፡ ራስህን ካድ፡፡ አሮጌነትን በመስቀል ላይ ስቀለው፡፡ ሞትህ ትንሳኤ

አግኝ፡፡ ያኔ ሁሉም ይገባሃል፡፡ አገር ፣ቋንቋ ፣ መሪነት ጽድቅ፣ ኩነኔ፣ ታውቃለህ፡፡

ለዚህ አለም ህያው ሆነህ ለመንፈስ አለም ህያው መሆን አትችልም፡፡ ጨለማና ብርሃን ህብረት የለውም፡፡

ላንዱ መኖር ላንዱ መሞት ነው፡፡ ለዲያብሎስ ህያውነት ለእግዚአብሄር መሞት ነው፡፡ ሁለቱም መንግስት

ናቸው፡፡ አካል አይደሉም፡፡ ከውጭ አይደሉም፡፡ቁስ አይደሉም፡፡ስርዓት ናቸው፡፡ አካልነት ትንሽነት ነው፡፡

ሰውነት ዘላለማዊነት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ መብት ነው፡፡ ዋጋ የተከፈለበት ነው፡፡ ማንም ለማን የሚሰጠው

አይደለም፡፡ ሰላም ደስታ እና እረፍት ከዚህ ውጭ የለም፡፡

መጀመሪያ በዚህ ሰላም ደስታና እረፍት ስትሞላ ሌላው ሁሉ ይጨምርልሃል፡፡ ለሌላ መናገር፤ ለሌላ

መትርፍ፤ መምራት ፤ማዘዝ ትችላለህ፡፡ ያኔ መሪነት መብት ይሆናል፡፡ ሰው ከህግ በታች ሳይሆን ከህግ ሁሉ

የበላይ ነው፡፡

ዜሮነት ፍጹም ሙላትነት ነው፡፡ ዜሮነት አንድነት (Oneness) ነው፡፡ ከሆርሞን ነጻ መውጣት ነው፡፡

ዜሮነት አርነት ነው፡፡ ፍጹም ባዶነት ነው፡፡ አንድነት ቁጥር አይደለም፡፡አልፋና ኦሜጋነት ነው፡፡ አንድነት

የእግዚአብሔር መልክ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሰውነትና የሰው እግዚያብሔርነት ነው፡፡ ኢየሱስ የአዲሱ

ሰውነት ጅማሬ ነው፡፡ ትምህርት ነው፤ ኢየሱስነት የዜሮነት ሞዴል ነው፡ በአየር ላይ መንጠልጠል ነው፡፡

በሙላት ታዘበዉ 4
ዜሮነት

ኢ-አንጻራዊነት ነው፡፡ በሰውነት /ሀሳብ/ ንጽጽርና ቁጥር የለም፡፡ መጠን የለም፡፡ ቦታና ሁኔታ የለም፡፡ ጊዜ

የለም ፤ቁስ የለም፡፡ ሰው የለም ፤ዜሮነት ብቻ ነው፡፡ ገነት ላይ የተሰራው ስራ ሰውነትን ወደ አካልነት

ማውረድ (ወደ ሲኦል ማውረድ) ሲሆን መስቀል ላይ የተሰራው ስራ ደግሞ ወደ ቀደም ማንነቱ (ሰውነቱ)

በአካል ራሱን አላማወቁ መመለስ ነው፡፡ በአካል አለም/ በዚህ አለም/ ብዙ ክስተት የሚባል አለ፡፡ በሰውነት

አለም (አዲሱ አዳም) ያለ ጊዜ ሁኔታ እና ቦታ የተፈጸመ ክስተት አለ፡፡ ሞትና ህይወት ይባላል፡፡

ዲያቢሎስና እግዚአብሄርም ይባላል፡፡ ብርሃን እና ጨለማን ይባላል፡፡ ክፉና ጥሩም ይባላል፡፡ ወዘተ ሞት

የተባለው ገነት ላይ ሕይወት የሚባለው መስቀል ላይ ተፈጽመ ሌላ ሞትና ህይወት በሰውነት ላይ

ተፈጽሞ አያውቅም (አይፈጽምም)፡፡ሰውነት አሁን ተሰልቧል፤ ተሰርቋል፤ተሸንግሏል፡፡ ከውጭ

አድሯል፤የጎዳና ተዳዳሪ ሆኗል፡፡ ሰውነት ማደሪያ ጉድጓድ ካላት ቀበሮና መስፈሪያ ዛፍ ካላት ወፍ በታች

ሆኗል፡፡ የተሰረቀ ፣ የተሰለበ እና የተሸነገለ ደግሞ ሊሰረቅ፣ ሊሰልብ እና ሊሸነግል አይችልም፡፡ ስዉ ራሱን

ማዳን ነው ያለበት፡፡ሰውነት ቁመት ቀለምና ውፍረት ሆኗል፡፡ ሰውነት እና አፍነት ተቀራርበዋል፡፡ ሰውነት

መንፈሳዊነት ሲሆን ወደ ቁስነት ማስገባት ኩነኔ ነው፡፡

ሰውነትን በአካል አለማወቅ እሩጫን መጨረስ ነው፡፡ ያኔ መምራት ቀላል ይሆናል፡፡ ሙሴነት ይወድማል፡፡

ህግ ይወድማል፡፡ ጸጋነት ይለመልማል፤ የሰውነት ወርዱ ቁመቱ ስፋቱና ጥልቀቱ ኢየሱስነት ይሆናል፡፡ፊደል

ራሱ ይሞታል፤ ቃል ግን ስጋ ያጋኛል፡፡ ይሄ አሁን ነው፤ሰውነት ከሰውነት ውጭ ያለን ነገር ከመግደል

ይጀምራል፡፡ ሰውነት ራስን ከመካድ ይጀምራል፡፤ ሰውነት የአንድ ዘር ልጅነት ነው፡፡ ሰውነት ደረጃ አልባነት

ነው፡፡ ሰውነት እኔነትን ማጥፋት ነው፡፡ ሰውነት ከአንጻርዮሽ መውጣት ነው፡፡ ሰውነት መንፈሳዊነት ነው፡፡

በዚህ ጊዜ የሰው ክቡርነት መገለጥ ይጀምራል፡፡ ሰው ኪሩቤል ይሆናል፡፡ ሰው የእግዚአብሔር እስትንፋስ

እና ቤተ መቅደስ ይሆናል፡፡አንድ አባት ብቻ ይኖረዋል፡፡ ሌላው ወንድም ይሆናል፡፡ ሌላው እውቀት ይገረዛል፡፡

ገለባውን እሳት ይበላዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ሰውነት የምድር አፈርነቱ ያበቃና የእግዚአብሔር እስትንፋስ

ይሆናል፡፡ ለሰው የተሰቀለው አፈር ሰው ሳይሆን ሀሳቡ ሰው ይሆናል፡፡ ከኢየሱስ የሚያስፈልገን ቀዩ ደም

ሳይሆን ዜሮነቱን ይሆናል፡፡ አብነቱን ይሆናል፡፡ መሲህነቱን ይሆናል፡፡ መስቀል ምን እንደሆነ ይገባናል፡፡

መስቀል ፈቃድ አልባነት ሲሆን ራሱን ማቋሚያ፤ማሳረፊያ ማሳጣት ሲሆን፣ አየር ላይ መሆን ሲሆን ፤

መሞት ሲሆን ህይወት ይሆናል፡፡ ልጅነት ይሆናል፡፡ ልጅነት ደግሞ ሰውነት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ዘር ነው፡፡ ዘርን

ደግሞ አንማረውም፡፡ አንቀርጸውም፡፡ በዘራችንም ላይ ፈቃድ የለንም፡፡ ጸጥ እና እርጭ ብሎ መኖር ብቻ

ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ዘላለማዊ እረፍት ይሆናል፡፡ መንግስተ ሰማይ ይሆናል፡፡ ከዚያ ሰላም ደስታ እና እረፍት

በሙላት ታዘበዉ 5
ዜሮነት

ከውጭ የምናመጣው ሳይሆን ከኛ ውስጥ የሚፈልቅ ይሆናል፡፡ ለሌላው የምናስተምረው ሳይሆን

የምናከፍለው ይሆናል፡፡ ወደ አብ ማረግ ይሆናል፡፡

“ የስሜት ህዋስ (አይን አፍንጫ ፣ ጆሮ (አፍ ምላስ ቆዳ) በኢ-ቁሳዊው ሰው(ሀሳብ) እና በቁስ አለም

(Body) መካከል ያለ የጥል ግድግዳ እንጂ ሰውም ቁስም አይደለም፡፡ መካከለኛ ነው፡፡ ሰውነት ሀሳብ

ሲሆን አለም አንድ ይሆናል ፡፡ ሀሳብ አገር የለውም፤ ብሔር ፤ነገድ፣ ዘር የለውም ፡፡ የተማረ ያልተማረ

የለውም፤ እድሜ ጾታ የለውም፤ ሀይማኖት እና እምነት የለውም፤ ሚስትና ባል የለውም ፣ ልጅ ወንድም

እህት አክስትና አጎት የለውም፡፡ ምንም የለውም፡፡ ዜሮነት ይሆናል፡፡ ዜሮነት ራሱን ለሌላ ማስገዛት

ይሆናል፡፡ በዜሮነት አንድነት ይጀምራል፤ በአንድነት ዘላለማዊነትም ከቁጥርነት በላይ ይሆናል፡፡ አዲሱ

የህይወት ስርዓት አለምን ይገዛል፡፡ አዲስ ኪዳን መጽሀፍ ሳይሆን ይህ አዲስ የህይወት ስርዓት ነው፡፡፡ አዲሱ

የህይወት ስርዓት ለአሮጌው የህይወት ስርዓት መሞት ነው፡ አዲሱ ኪዳን ለብሉይ ኪዳን መሞት ነው፡፡

መልካምነት ትምህርትና ስልጠና አይቀይርም፡፡ መልካም ለተቃራኒው መሞት ነው፡፡ በአንዱ መሞት ነው

ሌላኛው ህያው የሚሆነው፡፡ መልካምነት ለመጠጥ፣ ለጫት ሲጋራ ለሐሽሽ መሞት አይደለም፡፡ ለክፋት

/ለዲያቢሎስ / ለዚህ አለም/ ራስን ማጥፋት /Suicide/ ነው፡፡ ዜሮነት በአማርኛ ሳድስ የሆኑ ፊደሎችን

አለመጠቀም ነው፡፡

በእንግሊዘኛ “I” ን መግደል ነው፡፡ “እኔ” እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ “ እኔነት” ምንጭ ነው፡፡ የሰውነት

ምንጭ /Source/ እንጂ ራሱ ሰውነት አይደለም፡፡ “ እኔነት” አባትነት ነው፡፡ በእኔነት ውስጥ አባትነት

(አብነት) እንጂ ልጅነት የለም፡፡ የሰው ሞት እንጂ ህይወት የለም፡፡

ስግደት አምልኮና ምስጋና ማለት ይሄ ነው፡፡ ከዜሮነት በላይ ስግደት የለም፤ ከዜሮነት በላይ ምስጋናና

አምልኮ የለም፡፡ ከዜሮነት ውጭ የሆነ ስግደት አምልኮ የዲያቢሎስ ነው፡፡ ይሄ መነጠቅ ነው፡፡ይሄ እውነት

ህይወትና መንገድ ነው፡ አብ መንፈስ ነው፡፡ ሰውነት መንፈሳዊነት ሐሳብነት ወደ አብ መነጠቅ ወይንም

ማረግ ነው፡፡ አካልን መግደል ነው፡፡ የሰላሞንን ቤተ መቅደስ አፍረሶ መስራት ነው፡፡

ሰውነት / ለዚህ አለም ክብር ወድቆ አለመስገድ ነዉ፡፡ አሁን በዚህ ብርሃን ነገሮችን ማየት እንችላለን፡፡
በድቅድቅ ጨለማ ማንም ማየት አይቻልም፡፡ ራስንም ማየት አይችልም፡፡ በዚህ እውነትና ብርሃን ነገሮችን
በአዲስ ቋንቋ /ልሳን/ መስማትና ማየት መረዳት እንችላለን፡፡ ይሄ ብርሃን ራሱ ከአንተ የጀመረ አይደለም፡፡

በሙላት ታዘበዉ 6
ዜሮነት

ከኔ የጀመረ አይደለም፤ ከኔ የጀመረ አይደለም፡፡ ከዜሮነት ከባድነት የጀመረ ነው፡፡ አብ ዋጋ የከፈለበት ነው፡፡
መብት ነው፡፡ ከሰውነት የሚጀመር ማንነት የለም፡፡ እውነት ራሱ ምንጩ አብ /Source/ ነው፡፡

አካላዊ ሰው ግን አብነት ከራሱ አስጀምሮ ፈጣሪ ነው ይላል፤ አምላክ ነው ይላል፤ እግ/ር ነው ይላል፤ ሰማይ

ነው ያለው ይላል፤ ይመጣል ይሄዳል ይላል፡፡ ይወልዳል ይወለዳል ይላል፡፡ አንድ ነው ሶስት ነው ይላል፡፡

አይወልድም አይወለድም ይላል፤ አብን የአሮን ጣኦት /ጥጃ አድርጎታል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ማንነት

የሚመነጭ እና የሚጀምር ሳይሆን እግዚአብሄር ከሰው እምነት ሀይማኖት ትምህርትና እውቀት የሚጀምር

የሚመነጭ ልጅ ሆኗል፡

የሚቆጣ ፣ የሚስቅ፣ የሚናደድ፣ ምህረት የሚያደርግ፣ የሚሰጥ፣ ሚነሳ የሚደሰት፣ የሚከፋ ጣኦት

ሰርተን እያመለክን ነው፡፡ ይሄ ነው አመንዝራነት፤ ይሄ ነው ማሰብና መመኘት፤ ይሄ ነው ግብረ ሰዶማዊነት

ሌላ የለም፡፡ ሰው ለምንም ነገር ምንጭ ሊሆን አይችልም፡፡ ከልጅነት እና አብን ከተመተረክ ውጭ ምርጫ

የለውም፡፡ ስለዚህ የዘሩን መኖር ሲጀምር መንፈስ ቅዱስ መስራት ይጀምራል፡፡ ያኔ ሰው በእግዚአብሔር

እግ/ር በሰው አንድነት/Once/ይጀምራል፡፡ የዘላለም ህይወትና የእግ/ር መንግስት ይሄ ነው፡፡ ቃል ስጋ

አግኝቷል፤ ቃል ስጋ ሆኗል፡፡

ሃጥያት ሰው ከእግዚአብሔር ክብር ሲጎድል ብሎም ሰውነት ከሰው ውጭ ሲሆን ነው፤ እግዚአብሔር

ከጎደለ ጉድለቱን በምን መሙላት ይችላል፤፤ ጉድለቱ እና የጥልቀቱ መጠን ራሱን የጎደለውን ሲያክል

ገሃነም /ሲኦል /ሞት ዲያቢሎስ ወዘተ ነው፡፡

ሰውነት ከውስጥ ሲሆንና የአብ ማለፊያ /መሳሪያ፤ መናገሪያ ቤተመቅደስ ስትሆን እኔነትህን ስትገድል

የሚመጣው ሰላም ደስታ እረፍት ገነት መንግስተ ሰማይ ወዘተ ይባላል፡፡

ስለዚህ ጽኑ መንግስት በዚህ ብርሃን ላይ የቆመ መሪ ይፈልጋል፡፡ በዚህ እውነት ላይ የቆመ መሪ ያስፈልጋል፡፡

በዚህ የብርሃን እውነት ላይ የቆመ መንግስት ትጸናለች፡፡ፍቅር እና ፍርሃት

መሬትን እና ሰማይን መሰረት አድርጎ የተመሠረተው ዓለም መሠረቱ ሃሳብ ነው፡፡ ሐሳብን ለመግለፅ

የተቀመጡ ምልክቶች እና ፊደሎች ካለሆኑ በቀር ግዐዝ የሚባል ነገር አይታየኝም፡፡ ወደ የትኛውም ግዐዝ

የሚባል ነገር ተመልከቱ ፣ በራሳቸው ማንነት የላቸውም፡፡ ማንነታቸው ሃሳብ ነው፡፡ የሐሳብ መገላጫዎች

ናቸው፡፡ ጦርና ጋሻ ወይንም ታንክ እና ጄት ብታዩ የፍርሃት ሃሳቦች ናቸው፡፡ የፈጠሩዋቸው ፣

የተቀበላቸው፣ የሚጠቀሙባቸው የፈሩ ናቸው፡፡ ቤትን፣ አውሮፕላንን፣ መኪናን ወዘተ ብንመለከት

የተለያዬ ሃሳቦች ናቸው፡፡

በሙላት ታዘበዉ 7
ዜሮነት

ቤት ራስን ከአደጋ ፣ ከበሽታ ፣ ከመሠረት ወዘተ ከመጣ ፍርሃት ለመከላከል የተገነባ የፍርሃት ሃሳብ ሊሆን

ይችላል፡፡ ብርድ ከመታኝ እታመማለሁ ንብረቴ ይሰረቃል፣ ሰውና አውሬ ይገድለኛል ከሚል ሊሆንም

ላይሆንም ሊደርስም ላይደርስም ከሚችል ፍርሃት የሚመነጭ ነው፡፡ አውሮፕላን እና መኪና የፍጥነት

ሃሳብ ነው፡፡ ቶሎ የመድረስ ወይንም እርቀትን ወይንም ግዜን የማሳጠር ሃሳብ ነው፡፡ ዘመናዊ መንገዶች

የምቾች፣ ያለመንገላታት፣ ቶሎ የመድረስ፣ ንብረት ላይ ጉዳት ያለማድረስ፣ ወዘተ ሃሳብ ነው፡፡ መብራት

ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ ትምህርት፣ ሐይማኖት፣ እምነት፣ ወዘተ የምንላቸው ነገሮች ሃሳባዊ ናቸው፡፡

መብራት የጨለማ ፍርሃት ምንጩ ነው፡፡ ጨለማን የመፍራት ሃሳብ መብራትን እንድንፈጥር ወይንም

እንድንጠቀም አድርጎን ሊሆን ይችላል፡፡ ትምህርትን እንድንማር ምንጩ የተሻለ ኑሮ ለመኖር ወይንም

ወድቆ ለመቅረት የሚል ሃሳብ ምንጩ ሊሆን ይችላል፡፡ ሐይማኖት ከሲኦል ለመዳን ወይንም መንግስት

ሰማያት ለመግባት የሚል ሃሳብ ነው፡፡ ምንም ያህል ብንዘርዝር ከሃሳብ ውጭ የራሱ ማንነት ያለው ግዐዝ

ነገር ወይም አስተምሮት ወይንም እውቀት ወይንም ባህል፣ ፍልስፍና፣ ወይንም ቴክኖሎጂ የለም፡፡ ምድር

እና ሰማይ ላይ ያለውን የትኛውንም ዓይነት ፍጥረታት ብናያቸው እና ብናስተውላቸው የሐሳብ

ውክልናዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ውጭ በፍፁም ግዐዝ ዓይደሉም፣ በመሠረታዊነት የሐሳብ ማንነት እና ምንጭ

አንድ ቢሆንም ለመረዳት ቀለል እንዲል ብቻ የሃሳብን ምንጭ ለሁለት ከፍለን እና የትኛውም ፍጥረት

(አካላዊው) አየነውም አላየነውም ምን ወይ ከሰው አለበለዚያ ከእግዚያብሄር ነው አለበለዚያ ደግሞ

ከተፈጥሮራዊ (እግዚያብራዊ) ነው፡፡ ከሰው ያልጀመረውን ማንነት በሙሉ የእግዚያብሄር ሃሳብ በሚል

ተክቼዋለሁ፡፡ ስለዚህ እግዚያብሄር ወይንም ሰው ለጋሃዱ ዓለም (አካል) ምንጭ ናቸው፡፡ እግዚያብሄር እና

ሰው ገሃዱን ዓለም ፈጥረዋል፡፡ ሰው የሚባለው አካላዊ ማንነት ጨምሮ የሰው ያልታከለበት የትኛውም

ዓይነት ፍጥረት ምንጩ የትኛውንም ዓይነት ስም ብንሰጠው ምንጩ የአስገንው መገለጫዋች (ዓለማዋች)

ችሎታዎች ናቸው፡፡ ቤት፣ መኪና፣ ልብስ፣ ትምህርት፣ ወዘተ የተባሉ ነገሮችን ብንዘርዝር ደግሞ ምንጩ

ሰው ነው፡፡ ከሰው ያልጀመረው የትኛውንም ቅርጽ፣ቀለም፣ ሁኔታ፣ መጠን፣ ወዘተ የእግዚያብሄር ሃሳብ

ብለን ብናስብ ለመድረሻዬ መንገድ ይሆነኛል፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሁለት ሃሳቦች ገሃዱን ዓለም ቅርፅ፣ቀለም፣

መጠን ሆኔታዎች እና ሰርዓቶች ወዘተ የሚባሉትን ሃሳቦች ገልፀውበታል፡፡ እግዚያብሄር የፈጠረው (ራሱን

የገለፀበትን) ነገሮች በሙሉ እና አንዱ ለአንዱ ወይንም አንዱ ካንዱ ያለውን ትስስር የእግዚብያሄር የሚባል

ሃሳብ ሙሉ ችሎታ ነው፡፡ ሰው የፈጠረው (ራሱን የገለፀበት) ነገሮች በሙሉ እና አንዱ ላንዱ ወይንም

አንዱ ከአንዱ ያለው ትስስር ደግሞ የሰው ሙሉ ችሎታ ነው፡፡ ሁለቱም በመበላለጥ እና በመመናናስ

ሃሳባቸው በሙልዓት ተገልፃባቸዋል፡፡ እግዚያብሄር የሚባለው ሃሳብ ሰው ከሚባለው ሃሳብ ራሱን በተሸለ

በሙላት ታዘበዉ 8
ዜሮነት

ገልል፡፡ እየገለፀም ነው፡፡ ይቀጥላልም፡፡ ሰው የሚባለው ሃሳብ እግዚያብሄር ከሚባለው ሃሳብ በመነሳት ራሱን

ገልል፡፡ ከምክንያቶቹ ውስጥ የመጀመሪያው እግዚያብሄርነት ያለ ውሰንነት ራሱን በማንነት መግለፅ መቻሉ

ሲሆን ሰውነት ግን በሐሳብነት ሙሉ ለሙሉ ራሱን መግለፅ አለመቻሉ እና በአካላዊ ማንነቱ ላይ ጥገኛ

በመሆኑ ነው፡፡ ሰው የተባለው ሃሳብ በአካል እና በአካልነት ላይ ወይም የሰሜት ህዋስ ላይ ጥገኝነት

በመመስረቱ ጉደለቶች ሰሜቶች፣ ልምዶች፣ ወዘተ ሸብበውታል፡፡ እግዚያብሃር ራሱን ከእነዚህ ውስንነቶች

ለመውጣት ሙሉ በሙሉ በንፅህና የተገለፀ ማንነትን አምጥቷል ሰው ግን ከእግዚያብሄራዊ (ሃሳባዊ)

ማንነት እና አዕምሮት የተደቀለ ግብር-ሰደማዊ ዓለም ፈጥራ፡፡ የተገነባው ግሃዳዊ ዓለም ምንጩ አንድ

ዓይደለም፡፡ ለእግዚያብሄር ሃሳብ የተገባው ዓለም ምንጩ አንድ ነው፡፡ የእግዚያብሄርን ሃሳብ ፍቅር ብለን

ልንገለፀው እንችላለን፡፡ ፍቅር ሲባል ግን የሰው ሃሳብ ከመሰረተው ፍቅር መለየት ተገቢ ነው፡፡ የእግዚያብሄር

ሃሳብ ማንነት የተገለፀባት ጋሃዳዊ ዓለም ፍቅራዊ ማንነት ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ በሰው እና በእፅዋት መካከል

ያለው ፍች የሌለው ጋብቻ የመሬት ሰቦት፣ የመሬትና የሰው ቁርኝት፣ የውሃና የሰው ወይንም አንዱ

ለአንዱ እና አንዱ ከአንዱ ጋር ያለው ቋጠሮው የማይለይ የአሰፈላጊነት ተፈጥራአዊ ትስስር ነው፡፡

በእግዚያብሄር ሃሳብ የተገለፀ ማንነቶች ትስስር በስው ሃሳብ ሊመረመር አይችልም፡፡ ጥልቅ ነው፡፡

የእግዚያብሄር ሃሳብ ምንጩ አንድ ነው፡፡ የሰው ሃብብ ምንጩ ሁለት ነው፡፡ የእግዚያብሄር ችሎታ ምንጩ

አንድ ነው፡፡ የሰው ችሎታ ምንጩ ሁለት ነው፡፡ የእግዚያብሄር ችሎታ ፍቅር ነው፡፡ የሰው ችሎታ

የተገለፀው በፍቅር እና በፍርሃት ነው፡፡ ፍቅር የሰው የውስጣዊ ማንነት ችሎታ ሲሆን ፍርሃት ደግሞ የሰው

የውጫዊ ችሎታ ነው፡፡ ሁለቱ ምንጮች ተቃራኒዎች ናቸው፡፡ ፍቅር ብቻውን ችሎታ ነው፡፡ ፍርሃት

ብቻውን ፍፀም ችሎታ ነው፡፡ በሰውነት ላይ ተቀላቅለዋል፡፡ ሁለቱ ተገናኝተው ዲቃላነት ተፈጥሮል፡፡

ፍቅር ተፈጥሮአዊ እውቀት ነው፡፡ ፍርሃት ግን የተገላቢጦሽ ነው፡፡ ፍርሃት ምንጩ ከአካላዊ ግሃዳዊ

ማንነት የሚመንጭ እና ከአለማወቅ የመጀመር ነው፡፡ ዓለማወቅ ጨለማነት ነው፡፡ በጨለማ ውስጥ

የሌለው ነገሮችን ዓለማየት ነው፡፡ በጨለማ ውስጥ የሌለው ነገር አለማወቅ ነው፡፡ ምክንያቱም በጨለማ

ውስጥ ብርሃን የለም ጨለማ የሚፈጥረው ፍርሃት በጨለማ ማየት ካለመቻል የጀመረ ነው፡፡ ማየት

ባለመቻል ደግሞ ገደል ይኑር አይኑር ማወቅ አይቻልም፡፡ አውሬ ይኑር አይኑር ማወቅ አይቻልም፡፡ ዘራፊ፣

ማጅራት መች፣ ወንበዴ ይኑር አይኑር ዓለማወቅ አለ ይህ አለማወቅ በሰው ውስጥ ያለውን የሞት ፍርሃት

ይቀሳቅሰዋል፡፡ ፍርሃት መብራት እንዲፈጠር ምንጭ ሆኗል፡፡ በጨለማ ላለመቀሳቀስ ምክንያት ሆኗል፡፡

በአለማወቅ ውስጥ ሁልግዜ ፍርሃት ዓለ፡፡ ነገር ባለማወቅ ውስጥ ነገር መፍራት ዓለ፡፡ የበሽታ ፍርሃት፣

የመችገር፣ ፍርሃት፣ የመጠቃት ፍርሃት፣ ወዘተ ምንጩ ዓለማወቅ ነው፡፡ ጨለማ ነው፡፡ፍርሃት ውጤትን

ካለማወቅ ይጀምራል፡፡ ሁሉም ዓይነት ፍርሃቶች መድረሻቸው ዋትን ከመፍራት ይጀምራሉ፡፡ የመቸገር

በሙላት ታዘበዉ 9
ዜሮነት

ፍርሃት በርሃብ መሞትን ከመፍራት ነው፡፡ የበሽታ ፍርሃት፣ ሞትን ከመፍራት ይጀምራል፡፡ሁሉም ፍርሃት

በሞት መኖር ላይ የሚጀምሩ ናቸው፡፡ መጨረሻቸው ሞትን መፍራት ነው፡፡

ችግር የሚባለው የፍርሃት ሃሳብ ባይኖርም ሰርቆት ፣ዝርፊያ፣ ግድያ ወዘት የሚባል ዋና ዋና ወንጀል

አይኖርም ነበር፡፡ ሞት የሚባለው ዋነኛው የፍርሃት ምንጭ ባይኖር ኖሮ ገሃዳዊው ዓለም አሁን ባለው

ሁኔታ በፍፁም አይኖርም፡፡ አሁን አለም የገነባው ስርዓት በፍፁም አይኖርም ነበር፡፡

ፍርሃትን የሚቀሰቅስው ከውጭ ወደ ውስጥ የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በሽታ፣ ጦርነት፣ ወረርሽኝ እርጅና፣ ርሃብ

አመፅ፣ ድህነት ወዘተ የሚባሉ እውቀቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ደግሞ በራሳቸው የቆሙ ሳይሆኑ መነሻቸው

ሞት ነው፡፡ በባህል፣ በትምህርት፣ በፓለቲካ በሐይማኖት በእድገት ወዘተ በተለያዬ ሰዎች እና ተቋማት

እየተሰጠው ስም ያለው ፍርሃት ነው፡፡ ፔንታጐን የፍርሃን ስም ነው፡፡ የሲአይ ኤ፣ የኤፍ ቢ አይ፣ መሠረት

ፍርሃት ነው፡፡ ኤርፎርስ ፍርሃት እንጅ የቴክኖሎጅ እድገት አይደለም፡፡ የአንድ አገር የመከላከያ ተቋም

የድህንነት ተቋም፣ የጤና ሚኒስትር ወዘተ የፍርሃት ውጤቶች ናቸው፡፡ አገር በራሱ የፍርሃት ውጤት ነው፡፡

ፍርሃት ባይኖር አሁን ያለው ሰው አይኖርም ነበር፡፡ የእግዚያብሄር ሃሳብ ወይንም እግዚያብሄር ብቻ ይኖር

ነበር፡፡ ሰውነት የተገነባው ከውጭና ከውስጥ ባሉ ሁለት ተፃራሪ የሃሳብ ምንጮች ነው፡፡ ከፍቅር እና

ከፍርሃት!!

ፍቅር ተፈጥሮዓዊ ነው፡፡ እውነተኛ ማንነት ነው፡፡ የፍቅር ምንጭ አዕምሮ አይደለም፡፡ ፍርሃት ምንጩ

አዕምሮ ነው፡፡ አዕምሮ ደግሞ ግብዓቱ የስሜት ህዋሳት ናቸው፡፡ እውቀት ነው፡፡ መልካሙን እና ክፉን

የመፍጠርና የመለየት ጉዳይ ነው፡፡

ለምሳሌ የአንድን ቤት ዲዛይን እና ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ብንመለከተው ከፊሉ ከፍርሃት ከፊሉ ከፍቅር

የመነጩ ነገሮችን ማስተዋል እንችላለን፡፡

የቤቱ አጥር ምንጩ ፍርሃት ነው፡፡ የተሠራበትን ቁሳቁስ በመምረጥ ረገድ ግን ፍቅር ወይንም ፍርሃት

አስተዋጽኦ አድርጎ ሊሆን ይችላል፡፡ ውብ የሆኑ ቅርፃ ቅርፃችን ወይንም እጽዋትን ብንጠቀም ለነሱ ላን

ፍቅር የጀመርን ሲሆን፣ አጥሩ የሚሰራበትን ቁሳቁስ ሰንመረጥ ግን ጠንካራ እና ጥይት የማይበሳቸው

በጣም ከፍ ከፍ ያሉ፣ እሸሃማ ወይንም የኤሌክትሪክ አጥር ከሆነ አጥሩም ፣ ዲዛይኑም፣ ሁሉም ፍርሃት

ነው፡፡ የመኝታ ክፍሎቻችን ቀለሞች በመምረጥ ረገድ፣ የመስኮቶች ብዛት እና መጠን፣ የተሠሩበት ቁሳቁስ

ወይንም የቁሳቁሱ ጥንካሬ ወዘተ ምንጩ ፍርሃት ወይንም ፍቅር ሲሆን የሚችል ሲሆን ተቀላቅሎ

የሚገኝበት አጋጣሚም ብዙ ነው፡፡ ተመሳሳይ ሁኔታዎች እና ድርጊቶች ነገር ግን የተለያዩ ምንጭ

በሙላት ታዘበዉ 10
ዜሮነት

ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ለምሳሌ ቤት አንዱ ፍርሃት ላንዱ ደግሞ ከፍቅር ሊመነጭ ይችላል፡፡ ጋብቻ ለአንዱ

ከፍቅር ላንዱ ደግሞ ከፍርሃት ሊመነጭ ይችላል፡፡ የአንዱ ጋብቻ የተመሰረተው የብቸኝነት ኑሮ

አስጠልቶት፣ ሆቴል መመገብ ስልችቶች፣ ልብስ ማጠብ እንገሽግሽት በዚሁ ከቀጠለ ሳያገባ ዘሩን ሳይተካ

ባክኖ የሚቀር መስሎት፣ የሚኖርበትን ማህበረሠብ ወግና ባህል መቋቋም አቅቶች፣ እርጅናን ሊቀድም

ሊሆን ይችላል፡፡ ለሌለኛው ደግሞ ከሚኖርበት ማህበረሰብ በማግባት የሚገኘውን ክር ለማግኘት እና

ባለማግባት (ቆሞ በመቅረት) የሚደግውን ሰውን መቅጣት ለማምለጥ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዱ አለማግባት

(ጋብቻ አለመመሰረት) ምንጩ ፍርሃት ለሌለኛው ፍቅር ሊሆን ይችላል፡፡ ግሮሠሪ ማምሽት ምንጩ ላንዱ

ከፍቅር ላንዱ ከፍርሃት ሊሆን ይችላል፡፡ አበባን መውዳድ ከፍቅር ነው፡፡ ህፃናትን መውደድ ከፍቅር ነው፡፡

ፍርሃት ተፈጥሮአዊ ዐይበለም፡፡ ከአለማወቅ የሚጀምር ነው፡፡ ሁሉን በማወቅ ውስጥ ፍርሃት በፍፁም

የለም፡፡ ለምሳሌ አንድ ወረርሽኝ ቢነሳ ወረርሽች ብዙ ሰው እንደገደለ መረጃ ቶሎ ቶሎ ቢነገረን

እንፈራለን፡፡ የምንፈራው ሌሎቹን እየገደለ ከሆነ እኔንም ሊገድልኝ ይችላል ከሚል ድምዳሜ ነው፡፡

እንደማይገድለው የሆነ ምክንያት ቢነገረው ግን ፍርሃቱ አይኖርም፡፡ አብዛኛው የፍርሃት ምንጭ ሊሆን

ይችላል፣ ሊደርስ ይችላል፣ አይታወቅም ወዘተ ከሚሉ አለማወቆች የሚጀምር ነው፡፡ አለማወቅ ወይንም

ጨለማ የፍርሃት ምንጭ ነው፡፡ የሚገርመው እና የሚያሳዝነው ነገር ግን ሁለቱን የሐሳብ ምንጮች

ሐይማኖት እግዚያብሄር እና ዲያቢሎስ እያለ ቢጠራቸውም በትክክል አለመረዳቱ ነው፡፡ እነዚህ ምንጮች

እግዚያብሄር እና ዲያቢሎስ ናቸው፡፡ ብርሃን እና ጨለማ ወይም ክር እና ጥሩ ወይንም ሞትና ህይወት

ወይንም ከውስጥና ከውጭ ወይም ህይወትና እውነት እያለን ልንጠራቸው እንችላልን፡፡ ፍርሃት ምንጩ

ውሸት ነው፡፡ ለምሳሌ ነገ ታመህ በሆስፒታል ብትገባ የሚያሳክምህ የለም፡፡ ኮሮና ቢይዝህ ትሞት

ትችላለህ፣ የሚያገበሽ የለም፡፡ ከስህተትህ የማትማር ሰው ነህ፣ ወዘተ የሚሉ ሃሳቦች ውሸት ናቸው፡፡

ከነዚህ ፍርሃት ይጀምራል፡፡ ጎረቤት ሃገሮች ሊያጠቁን ይችላሉ ብለን ከባድ የመከላከያ ሃይል እንገነባለን፡፡

ግን ላያጠቁንም ደግሞ ይችላሉ፡፡ ፍርሃት ምንጩ የወደፉቱን በአለማወቅ ውስጥ ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱ

የሰውን አካል ሲያንቀሳቅሱት ይውላሉ፡፡ የአንዱንዱ እንቅስቃሴ ምንጭ ፍርሃት ነው፡፡ የአንዳንዱ

እንቅስቃሴ ምንጭ (source) ፍቅር ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት በፍርሃት ስንቀሳቅስ ለዲያቢሎስ (ለጨለማ)

ለአለማወቅ/ለክፋት ወዘት እያገለገልን ሲሆን የአንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ምንጭ ፍቅር ሲሆን ደግሞ

ለፈጣሪ ለብርሃን/ለማወቅ/ ለእውነት ወዘተ እያገለገልን ነው፡፡ ይህ አካል የሁለቱ የሐሳብ ዓለሞች

መገልገያ ነው፡፡ የራሱ ምንም ፈቃድ የለውም፡፡ይሁን የምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ምንጩ ፍርሃት ወይም

ደግሞ ፍቅር ነው፡፡ አንዱ ከጠኛው ማንነት የሚመነጭ ሲሆን ሌላኛው ከውጨኛው ማንነት የሚመነጭ

በሙላት ታዘበዉ 11
ዜሮነት

ነው፡፡ የውጨኛው ሰንል የስሜት ህዋሳትን መሠረት አድርጎ ከውጭ ወደ ውስጣችን የገባ መረዳት፣

እውቀት፣ እምነት፣ ልምምድ ወዘተ ነው፡፡ ይቀያየራል፡ ቋሚ አይደለም፣ ተፈጥሮዓዊ ዓይደለም

ፍርሃትን ማስወገድ ይችላል፡፡ ፍቅርን ግን ማስወገድ አይችልም፡፡ ፍርሃትን ማስወገድ የሚችለው

መጀመሪያ ፍርሃትን ማንነቱ ለማወቅና ምንጩን በማድረቅ ነው፡፡ ፍርሃት ምንጩ ውሸት እና ዓለማወቅ

ነው፡፡ ስለዚህ ከምንጩ ለማድረቅ እውነቱን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

ይህ እውነት ምንድ ነው?

የመጀመሪያው እውነት ሰው አይሞትም፡፡

ሰው ሞቶ አያውቅም፡፡ ወደፊትም አይሞትም፡፡ ይሄ ለአንዳንዱ ትልቅ የምሰራች ሲሆን ለአንዳንዳችሁ

ደግሞ የዋዛ ፈዛዛ ቀልድ ሽንገላ ወይንም ሹፈት ነው፡፡ የምድርና ሰማይ የመጨረሻው እውነት፣ የሁሉም

ችግሮቻችሁ መፍትሄ፣ ይሄንን ማወቅ፣ በትክክል መረዳት፣ እና ማረፍ ነው፡፡ ይሄንን ለማወቅ ዛሬውኑ ገነት

ትገባለችሁ፡፡ ያለምንም ነቀፌታ እና ጉድለት ነገሩ ግልጽ እንዲሆንላችሁ ለመጀመሪያ ሰውነትን ማወቅ

ተገቢ ነው፡፡ ሰው ሲታወቅ ቀጥሎ የሰው ምንነትን እና ዘለለማዊነትን መረዳት ቀላል ነው፡፡

ለመጀመሪያ ሰውነት ምንድን ነው?

አንድ መኪና የሚያሽከርክርን ሰው ወደ ህሊናችን እናምጣ እና ለትቂት ደቂቃዎች ስለ እሱ እናስብ፡፡

መኪናው ወንበር ላይ ከመቀመጡ በፊት የነበረው ሙሉ ሃሳብ መኪናው ወንበር ላይ ሲቀመጥም አብሮት

ነው፡፡ ከሰራ ባልደረባው ጋር ከመጨቃጨቁ የተነሳ ወደ መኪና ማቆሚያው ሲሄድ ተናዶ ነበር፡፡ ያው

የተናደደው ማንነት ወደ መኪናው ገባ፡፡ ከመኪናው ውጭ የነበረው ንዴት መኪና ውስጥ በመግባቱ

አልተቀየረም፡፡ ቀጥሎ የመኪና ማስነሻውን ቁልፍ ፊት ለፊቱ ወደ ዓለው ቀዳደ ሰክቶ መኪናውን

አስነሳው፡፡ መኪናውን ካስነሳው በውኃላ ከጋቢና በመውረድ ዘይት፣ ውሃ፣ ጎማ ወዘተ ካረጋገጠ በውኃላ

በዚያው የንዴት ስሜት ወደ መኪናው ተመልሶ ገባ፡፡ ቀጥሎም የአገሪቱ የመንገድ ስነ ስርዓት ህግ ፈቅደው

መሰረት ማሽከርከር ጀመረ፡፡ ፍጥነቱ 30 ከ.ሜ/በስዓት ማሽከርከር ባለበት በዚያው ፍጥነት መሠረት

ያሽከረክራል፣ 60 ከ.ሜ በሰዓት ማሸከርከር ባለበት ግዜ በዚያው ፍጥነት ያሽከርክራል፡፡ ሀ- ታጥፎ መዞር

ባለበት ግዜ እንዲያው ያደርጋል፡፡ ጡሩንባ መንፋት ባለበት ግዜም ያንኑ ይፈጽማል፡፡ "ጡሩንባ መንፋት

ክልክል ነው" የሚል ምልክትም ሲያይ ዐይነፋም፡፡ መብራት ሲይዘው ይቆማል፡፡ አረንጓዴ ሲበራ ይሄዳል፡፡

እንዲህ እንዲህ እያለ ዋለና የመኪና ማጠቢያ ያለበት አካባቢ አፈላልጎ መኪናውን አጠበ፡፡ ከዚያም የመኪና

በሙላት ታዘበዉ 12
ዜሮነት

ማሳደሪያው በማስገባት ሞተር አጥፎቶ የዕለቱን ውሎውን አጠናቆ ወደ ቤቱ ገብቶ አረፈ፡፡ ነገር ግን ጥዋት

ወደ መኪናው ከመግባቱ በፊት በነበረው ጭቅጭቅ የተፈጠረው ንዴት ከቤቱ ገብቶ ካረፈ በውኃላ

እንደቀጠለ ነበር፡፡ይህ ምሳሌ ያነሳሁት ሰውነትን ለማስረዳት ነው፡፡ መኪናው ራሱን የቻለ አንድ ማንነት

ነው፡፡ አሽከርካሪው ደግሞ ራሱን የቻለ ሌላ ማንነት ነው፡፡ መኪናው ከአሽከርካሪው ጋር አንድ

የሚያደርጋቸው የጋራ ማንነት የላቸውም፡፡የመኪናው ጥቅም አሽከርካሪውን ወይንም ሌሎችን

ተሳፋሪዎች በሚፈለገው ፍጥነት ከቦታ ቦታ ማድረስ ነው፡፡ አሽከርካሪው ያሉበትን ውስንነት በመኪናው

ጎማዎች፣ መስታውቶች፣ ጡርንባ፣ መብራቶች፣ ወዘተ በመጠቀም ፍጥነቱን፣ ድምፅን፣ እይታውን፣

የመሸከም አቅሙን፣ ያለብታል፡፡ በየግዜው ያድሳዋል፣ ጎማ ሲያልቅ ይቀይራል፣ መስታውት ቢሰበር

ያሰጠግናል፣ መብራት ቢሰበር ይቀይራል፣ ሊቆሽሽ ይጥበዋል ወዘተ፡፡ በመጨረሻም ሲያረጅ ይጥለዋል፡፡

ከግዜ በውኋላ ሁሉም የመኪናው አካላት ወደ አፈርነት ይቀየራሉ፡፡ መኪናውን ይጠቀምበት የነበረው

አሽከርካሪም በራሱ ማንነት ይቀጥላል፡፡ መኪናው የራሱ ፈቃድ የለውም፡፡ በራሱ ሞተር አስነስቶ

አይሄድም፡፡ በራሱ አይፈጥንም፣ በራሱ መብራት አያበራም፣ በራሱ አይሄድም፣ በራሱ አይታደስም፣ በራሱ

አይታጠብም በራሱ ነዳጅ አይሞላም፣ በራሱ ምንም ማድረግ አይችልም፣ የመኪናው እጣ ፈንታ

በአሽከርካሪው ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ፍጥነቱ የተሸከርካሪው ሳይሆን የአሸከርካሪው ነው፡፡ የጥሩምባው

ድምጽ የአሽከርካሪው ድምጽና ፈቃድ ነው፡፡ መኪናው ሲጋጭ የአሽከርካሪው ግጭት እንጅ የተሸከርካሪው

የራሱ ዐይደለም፡፡ ለሚፈፀመው የትኛውም ዓይነት ህግ የሚቀጣው አሽከርካሪው እንጅ ተሸከርካሪው

ዐይደለም፡፡ የመኪናው የአገልግሎት ግዜ የሚወሰነው በአሽከርካሪው ነው፡፡ የአሽከርካሪው ማንነት

መኪናውን በሚጠቀምበትም ግዜ ይሁን መኪናው አገልግሎት ካቆመ በውኃላ ተመሳሳይ ነው፡፡ ከመኪናው

የሚጀምር ማንነት የለውም፡፡ መኪናው የአሸከርካሪው ማንነት መገለጫ ሆኖ ያገለግላል ይሄንን ሙሉ

ለሙሉም ይሁን በከፊል መረዳት ከቻልን ቀጥሎ ሰውነትን ለመረዳት ጥሩ ምሳሌ ይሆናል፡፡ ይሄ ሁላችንም

እያሸከርከር ነው ያለውን አካል እንደ መኪና እንውሰደው፡፡ ማንነቱ ተሸከርካሪ ነው፡፡ እግሮቻችን እንደ ጎማ

እንውሰዳቸው፡፡ አይችን እንደ ጥሩንባ እንውሳደው፡፡ አይናችን እንደ መስታውት፣ ጨጓራችን፣ አንጀታችን፣

ልባችን ኩላሊታችን፣ ጀሮዓችን፣ እጃችን፣ወዘት ልክ እንደተለያዩ የመኪና ክፍሎች እንቁጠራችው

በአካላችን ውስጥ ያሉ ሰርዓቶች (system) ልክ መኪናው ውስጥ እንዳሉ የተለያዬ ሰርዓቶች

እንቁጠራቸው፡፡ መታወቂያችን ልክ እንደ ታርጋ እና የተሸከርካሪ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ ዓለም አቀፍና አገር

አቀፍ ህጎችን በዚህ አካል ከወጡ ህጎች ጋር እናፃፅፍቻው፡፡ በአብዛኛው ተቀራራቢ ናቸው፡፡ ሰው

አሽከርካሪው እንጂ ተሸከርካሪው ዐይደለም፡፡ ሰው አካልን የሚነዳው እንጂ አካሉ ዓይደለም፡፡ ተሸከርካሪው

(አካሉ) የራሱ ማንነት አለው፡፡ አሽከርካሪው የራሱ ማንነት ዓለው፡፡ በፍፁም የጋራ ማንነት የላቸውም፡፡

በሙላት ታዘበዉ 13
ዜሮነት

የአካል ጥቅሙ ውሰጠኛውን ሰው (ማንነት) ወይም ሌሎችን ተሳፊሪዎች ከቦታ ቦታ ማድረስ ነው፡፡

የውሰጠኛው ሰውነት ያሉበትን ውሰንነት በአካሉ ላይ በተገጠሙ ዓይኖች፣ አፍንጫ፣ እግር፣ እጅ፣ ጀሮ፣

አፍ፣ ወዘተ በመጠቀም ይንቀሳቀሳል፣ ያያል፣ ይሰማል፣ ያወራል(ይጨሃል) ባጠቃላይ ራሱን ይገልፃል፡፡

አሽከርካሪው (የውሰጠኛው ሰውነት) ደግሞ አካል ሲታመም ያሳክመዋል፣ ጫማ ይቀያይርለታል፡፡ ከተለያዩ

አካልን፣ ከሚጎዱ ነገሮች ይጠበቀዋል፡፡ ይጠግነዋል፣ ሲቆሽሽ ያጥበዋል ወዘተ፡፡ በመጨረሻም ሲያረጅ

ይጥለዋል፡፡ ከግዜ በውኃላ ሁሉም አካላት ወደ አፈርነት ይቀየራሉ፡፡ አካሉን ይጠቀምበት የነበረው ማንነት

በራሱ ማንነት ለብቻው ይቀጥላል፡፡ አካሉ የራሱ ፈቃድ የለውም፡፡ በራሱ አይሄድም፣ በራሱ አይፈጥንም

በራሱ ዐያይም፣ በራሱ ዐያወራም፣ በራሱ ዐይታከመም፣ በራሱ ምግብ ዐይመገብም፣ በራሱ ዐይታጠብም፣

በራሱ ምንም ነገር ማድረግ ዐይችልም፡፡ የአካሉ እጣፈንታ በውሰጠኛው ሰውነት (inner man) ላይ

መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ፍጥነቱ የአካሉ የራሱ ዐይደለም፡፡ አፍ ሳይሆን የሚያወራው በአፍ የሚያወራው

አሽከርካሪው ነው፡፡ አካል በራሱ አይጋጭም፡፡ የሚያጋጨው ሰውየው ነው፡፡ የአካላችን የትኛውም ዐይነት

ጥፋት ኃላፊነት የሚወስደው የውሰጠኛው ሰውነት እንጅ አካል ዐይደለም፡፡ የውሰጠኛው ማንነት

(ሰውነት) አካል ውስጥ እያለም ሆነ ከአካል ሲወርድ ማንነቱ ዐይቀየርም፡፡ ከአካል (እግር፣ እጅ፣ ዐይን፣

ጅሮ፣አፍንጫ፣ ወዘተ) የሚጀምር ምንም ዐይነት ማንነት የለውም፡፡ አካል የሰውነት ማንነት መገለጫ ሆኖ

ያገለግላል እንጂ የራሱ ማንነት የለውም፡፡ ስለዚህ አሸከርካሪው ማንነቱ አይከፋፈልም፡፡ አካላችን

የሚደነዳው (የሚጋልበው) ማንነት አንድ ነው፡፡ ሃሳብ (የመንፈስ ልጅ ነው፡፡) ነብስ ወይንም መንፈስ

ዐይደለም፡፡ አይከፋፈልም፡፡ ሁሉም አካል ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ አሽከርካሪ ነው፡፡ ይህ ማንነት ሰውነት

(የእግዚያብሄር ልጅነት) ነው፡፡ በቃ ሌላ ምንም ሊባል ዐይችልም፡፡ ሰውነት አካል አይደለም፡፡ አካል

ወደተፈጠሩት ማንነት ይቀየራል፡፡ ሰውነትም ወደ ተገኘበት ማነነት ይቀየራል፡፡ አፈር የነበረው አሁንም

አፈር ሆኖ ያለው ቀጥሎም አፈርነቱን ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል፡፡

ኢየሱስ ከዮሴፍና ከማርያም አልተወለደም፡፡ሰውነት መሲህ እንጂ ከአካላዊው ሰው አይወለድም፡፡

ሁላችንም ማንነታን የእግዚያብሄር ልጅነት ብቻ ነው፡፡ ሌላ መሆን በፍፁም አይችልም፡፡

ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የተወለደው ከመንፈስ ነው፡፡ እኛም ተፀንሰን የተወለድነው ከመንፈስ ቅዱስ

ነው፡፡ የሰውነት የህይወት ታሪክ (ዕድሜ) በመጀመሪያ አዳም ህያው ነብሰ ነበር፡፡ ያህያው ነብስ ሲሞት

አካሉን ዲያቢሎስ ገባበት (ወለደው) እና የዲያቢሎስ ልጅ የሚባል ማንነት መጣ፡፡ ቀጥሎ ደግሞ

የዲያቢሎስ ልጅ በመሰቀል ሞተና የእግዚያብሄር ልጆች ህያው ሆነ፡፡

በሙላት ታዘበዉ 14
ዜሮነት

የሰው ችግር ሰውነትን አለማወቅ ብቻ አይደለም፡፡ ችግራችን አለማወቃችን በራሱ ሌላ ችግር ነው፡፡

ችግርን አለማወቅ ለችግሩ መፍትሄ እንዳንፈልግ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን በራሱ የሌሎች ችግሮች ምንጭ

መሆኑ ደግሞ አሳሳቢ ነው፡፡ ችግሩን ከምንጩ ዓለማወቅ የሌለን ችግር ጭምር ያለ ሊያስመስል እና የሌለን

ችግር ለመፍታት እንድንባዝን ሊያደርገን ይችላል፡፡

ለዚህ ማስረጃ የሚሆን አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡፡

ሁለት ወጣቶች አንዲት መኝታ እና አንዲት ሳሎን ያላት ቤት ተከራይተው በጋራ ይኖሩ ነበር፡፡ ከዕለታት

ባንዱ ቀን አንዱ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ በነበረበት ሰዓት ጓደኛው ከሽንት ቤት ትንሽ ሠገራ ጠንቁሎ

በማምጣት የጓደኛው አፍንጫ ስር ይቀበውና ይወጣል፡፡ በእንቅልፍ ምክንያት ምን እንደተደረገ ያለወቀ

ጓደኛው ሲነቃ የስጋራ ሽታ ይሸተዋል፡፡ የሽታው ምንጭ የት እንደሆነ ያላወቀው አልጋውን በሙሉ ከታች

ከላይ ቢፈልግ ምንም ነገር ማግኘት አልቻለም፡፡ መኝታ ቤቱን ሊያስስም ምንም ማግኘት አልቻለም፡፡

የሽታው ምንጭ የት እንደሆነ ማወቅ ያልቻለው ወጣት ወደ ሳሎን ወጥቶ ፍለጋውን ቢጧጥፈውም

ምንም ማግኘት አልቻለም፡፡ በዚህ ግራ ሲጋባ ከሳሎን ወጥቶ ግቢው ውስጥ ማሳስ ይጀምራል፡፡ የፈለገውን

ያህል ቢጥርም ሽታው አለ ነገር ግን የት እንደሆነ ሊያረጋግጥ ግን በፍፁም አልቻለም፡፡ በመጨረሻ ከግቢው

ቢወጣም ሽታው ዓለ፡፡ ከአከባቢው ራቅ ወደ አለ አካባቢ ርቆ ቢሄድም ሽታው ባለመጥፋቱ በአቅራቢው

ወደ ምትገኝ ትንሽ ከተማ ሄደ ለመዋል ይወስናል፡፡ እንደሃሳቡ ባቡር ተሳፍሮ ቢሄድም መፍትሄ ሊያገኝ

አልቻለም፡፡ በመጨረሻ " ዛሬ አለም ትገማለች" ብሎ ተመልሶ ቤቱ ገብቶ ተኛ፡፡

ይህ ምሳሌ የችግሩን ምንጭ አለማወቅ መፍትሄውን እንዳናገኝ ብቻ ሳይሆን ያልሆነና ያልተገባ

መደምደሚያ ላይ እንድንደርስ ሊያደርገን ይችላል፡፡ ብዙዎቻችን አጠጋባችን ላሉ ችግሮች ሐይማኖትን፣

እምነታችን ፣ ቤተሠባችን፣ አገራችን፣ዘራችን ቀለማችን፣ መንግስትን አህጉራችን ወዘተ ተጠያቂ ወደ

ማድረግ ከመሄዳችን በላይ የምንወሰደቸው የመፍትሄ ሃሳቦችን ጥረቶች ከንቱ ድካም ይሆናሉ፡፡ የሰውነት

ችግር ሰውነትን ካለማወቅ ስለሚጀምር ማንም የሰጠንን መፍትሄ ሳንወድ በግድ ለመቀበል እንገደዳለን፡፡

Don’t depenel on death to librate you from your imperfection.

You are exactly the same after death as you were before.

Nothing changes; you only give up the body.

በሙላት ታዘበዉ 15
ዜሮነት

ቀኑን ሙሉ በስራ ተጠምደህ ውለሃል ብለን ብናስብ ማታ ምን ያህል ለማረፍ ጓጉታህ ወደ መኝታህ

እንደምትሄድ መገመት አያቅትም፡፡ ድብን ባለ እንቅልፍ ውስጥ እያለህ እነዚህን እና ሌሎች ጥያቄዎችን

መመለስ ወይንም ማወቅ አትችልም፡፡

ስምህን ቢጠይቁህ አታውቅም፡፡ እድሜህን፣ ዜግነትህን፣ ትውልድ ቦታህን፣ ፆታህን፣ ስራህን፣

የቤተሠቦችህን ስም፣ የት/ት ደረጀህን፣ ቁመትህን፣ ክብደትህን፣ ቁኑን፣ የትኛህበትን ሰፈር፣ ቤት ወዘተ

ምንም አታውቅም፡፡ በማንቀላፋት ውስጥ ምንም ሞት እየተባለ የሚጠራው ይሄ እንቅልፍ ነው፡፡ ምንም

አለማወቅ ነው፡፡ ልዩነቱ በየቀኑ የሚፈፀመው እንቅልፍ ውስጥ ትንሳኤ በየቀኑ ዓለ፡፡ "ሞት" ተብሎ

በተለምዶ የሚታወቀው እንቅልፍ ውስጥ ግን በየቀኑ መንቃት /መነሳት የለም፡፡ "ሞት" እና እንቅልፍ

ልዩነታችው እና አንድነታቸው ይህ ነው፡፡ ቀጥሎ ያለውን ምሳሌ እንመልከት፡፡ በሞትኖርበት ምድራዊ

አከባቢ ታክሲ ማጭበርበር ነውር ነው፡፡ የሰውን ንብረት መውሰድ፣ የባለ ትዳር ሚስት ማማገጥ፣ መሳደብ፣

ነስከር፣ ማጨስ ወዘተ በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው ከመሆናችውም በላይ በህግ ያስጠይቃሉ

ብለን እናስብ፡፡ አንተም እነዚህን የማህበረሰብ እና የመንግስት ህጎች በመጣስ ራስህን ትወቅሳለህ፡፡ በህግም

ላለመጠየቅ ራስህን በመደበቅ፣ አለባበስህን በመቀየር፣ ወዘተ በመኖር ላይ ትገኛለህ፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን

እንደተለመደው በሳራ ተወጥረህ ውለህ ወደ ቤትህ ስትገባ ጐርቤቶችህ ፖሊስ በተደጋጋሚ እየተመላለስ

ሲፈልግህ እንደዋለ ይነግሩሃል፡፡ በዚህ ስጋት ውስጥ ሆነህ ወደ መኝታህ ሄድክ እና የተለመደው እንቅልፍ

ውስጥ ወደቅህ ብለን ብናስብ ህልምህ ምን ሊመሳል ይችላል? በአብዛኛው ቀን በነበረህ ሰላም፣ ደስታ፣

እርፍት፣ ስጋት፣ ፍርሃት፣ ጭንቀት ወዘተ ላይ መሠረት የሚደርግ ነው፡፡

እዚህ ላይ መሠረት አድርጎ ያንተን ህልም መገመት ብንችል ጎርቤቶችህ በነገሩህ መረጃ ላይ መሠረት

ያደረገ ነው፡፡ ፖሊስ ሲያባርርህ፣ አንተ ለማሞለና ሙከራ ስታደርግ፣ የሚያባርሩህን ፖሊሶች ለማምለጥ

ስትምሞከር ፊት ለፊትህ ያሉ ሰዎች ሲይዙህ እንደገና ለፖሊሶቹ ሊያስረክቡህ ሲሉ ከአነስቶ ስታመልጥ

ከነሱም አምልጣህ የተወሰነ እንደሮጥህ እንደገና ፊት ለፊት ሌሎች ፖሊሶች ሲያገኙህ፣ ከነሱ ለማምለጥ

ወደ መጣህበት ዘረህ ስትሮጥ ባርሩህ የነበሩ ፖሊሶች ድጋሚ ሊያገኙህ፣ በሁለቱ አቅጣጫ በፖሊስ ተከበህ

እያለ በጭንቀት ስትጮህ በጎን እና በጐን ጥልቅ ገደል በመሆኑ አማራጭ ሰታጣ፣ ከዚህ የመጨረሻ

አማራጭ ስታጣ መብረር እንደምትችል ሃሳብ ሲመጣልህ ከዚያም ወደ ገደሉ አቅጣጫ ለመብርር

ስትሞክር ከትንሽ መውደቅ መነሳት በውኃላ መብረር መቻልህ እና በማምለጥህ ደስ ብሎህ ልትነቃ

ትችላለህ፡፡

በሙላት ታዘበዉ 16
ዜሮነት

ይሄ ሁሉ ሲሆን አካልህ አልጋው ላይ ነበር፡፡ አይኖችህ ዝግ ነበሩ፡፡ አፍህ ዝግ ነበር ለአካልህ ምንም ዓይነት

እንቅስቃሴ አላድርግም፡፡ ታዲያ ከዚህ አካል ውጭ ስትሮጥበት የነበረው እግርህ ከየት መጣ? ስታወራበት

የነበረው አፍህ፣ ስታይበት የነበረው አይንህ ስታሽትበት የነበረው አፍንጫህ ስትጨነቅበት እና ስታስብብት

የነበረው አዕምሮህ እና እውቀቱ ከየት መጣ? ህይወት ከዚህ አካል ከወጣን የሚመስለው ይሄንን ነው፡፡

ይሄኛው እንቅልፍ ለሚቀጥለል እንቅልፍ ጥላ እና እውቀት ነው፡፡

በሙላት ታዘበዉ 17

You might also like