Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 11

1.

በትራንስፖርት ዘርፍ መረጃ የሚተላለፍላቸው ሌሎች መሰል ድርጅቶች ይኖራሉ፡፡


ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
2. በተሽከርካሪ ላይ የሚጫንን እቃ ከመጫኑ በፊት ባለቤቱ አስቀድሞ በአግባቡ መታሸጉን ማረጋገጥ አለበት
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
3. አካል ጉዳተኞች በማንኛውም የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት እንዲገለገሉ አይፈቀድላቸውም፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
4. የየአካባቢውን እሴት ማወቅ የድርጅት አገልግሎት መስጫ መርህ ተብሎ ይጠራል፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
5. በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ውስጥ ለተሳፋሪዎች አክብሮትና እኩል ፍቅር የመስጠት ግዴታ የ ነዉ
ሀ) የአሽከርካሪው ሐ) የባለንብረቱ
ለ) የረዳቱ መ) የሱፐርቫይዘሩ
6. በተሽከርካሪ ላይ ተሰባሪ እቃዎችን መጫን አይፈቀድም፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
7. በመኪና ላይ የተጫነ እቃ ቢጣፋ የሚጠየቀዉ ረዳቱ ነዉ
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
8. ስለ ጉዞ መረጃ አስቀድሞ መሰብሰብ ከአላስፈላጊ ወጪ ያድናል፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
9. በተሽከርካሪ ላይ የሚጫን እቃ እንዴት መጫንና መውረድ እንዳለበት የሚወስነው ነው፡፡
ሀ) ባለንብረቱ ሐ) አሽከርካሪው
ለ) እረዳቱ መ) ሱፐርቫይዘሩ
10. በትራንስፖርት ዘርፍ ውስጥ ያሉት የተለያዩ የቁጥጥር ደረጃዎች የሥራ ሀላፊነቶችን ለመወጣት ጠቃሚ ናቸው፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
11. በትራንስፖርት ዘርፍ ከሚዋቀሩ የቁጥጥር ደረጃዎች ውስጥ አሽከርካሪዎች አይካተቱም፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
12. ረዳቶች የመንገደኞችን ደህንነት ይጠብቃሉ
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
13. የተሽከርካሪው ባለንብረት ተሳፍሪዎች ሲሳፈሩና ሲወርዱ የመቆጣጠር ሀላፊነት አለበት፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
14. በጉዞ ወቅት አደጋ ቢያጋጥም መረጃ ሊተላለፍላቸው ከሚገቡ አካላት አንዱ የአሽከርካሪው ቤተሰቦች ናቸው፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
15. አንድ አሽከርካሪ በሚጓዝበት ጊዜ የፖሊስን ስልክ ቁጥር /አድራሻ/ መያዝ አይጠበቅበትም፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
16. በአብዛኛው ሱፐርቫይዘር እየተባለ የሚጠራው የቱ ነው?
ሀ) አሽከርካሪው ሐ) ባለንብረቱ
ተሳ ፋሪዎች Page 1
ለ) እረዳቱ መ) መልሱ አልተሰጠም
17. በትራንስፖርት ዘርፍ ጥሩ መግባባት እንዳይኖር የሚከለክሉ ነገሮችን ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
18. የመንገደኛ እቃዎች ሲጫኑ መደረግ ያለበት ተግባር የቱ ነው?
ሀ. እቃዎችን በሚገባ ማሸግና ማሰር
ለ. በአንድ ላይ መጫን የሌለባቸውን እቃዎች መለየት
ሐ. እቃው በሚጫንበት ጊዜ የእቃውን አያያዝና አቀማመጥ መወሰን
መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
19. የመንገደኞችን እቃዎች በአግባቡ መቆጣጠርና ማድረስ ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች ውስጥ የማይካተተው?
ሀ. በጉዞ ወቅት ጊዜን ይቆጥባል
ለ. የአሽከርካሪውን ታማኝነት ይጨምራል
ሐ. ከኪሳራ ያድናል
መ. መልሱ አልተሰጠም
20. ለአካል ጉዳተኛ ተጓዦች የተለየ ትኩረትና እንክብካቤ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

21. አሽከርካሪዎች ለአካል ጉዳተኞች የቅድሚያ ትኬት እንዲያገኙ ማድረግ አለባቸው፡፡


ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
22. አካል ጉዳተኞች መኪና ውስጥ በሚሳፈሩበት ጊዜ መቀመጥ ያለባቸው ከሹፌሩ አጠገብ ነው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
23. አንድ አሽከርካሪ የቀጣሪ ድርጅቱን መርሆችና ሥርዓቶችን ጠንቅቆ መረዳት አለበት፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
24. በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማራ አንድ አሽከርካሪ ሊያውቀው የሚገባ ጉዳይ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የአካባቢውን እሴት ማወቅ ሐ. የህብረተሰቡን ባህል ማወቅ
ለ. የአካባቢውን ሀይማኖት መረዳት መ. ሁሉም መልስ ነው
25. በመኪና ላይ የሚጫን የመንገደኞች እቃ ቢጠፋ /ቢሰረቅ/ ተጠያቂው የተሽከርካሪው ባለቤት ነው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
26. በመኪና ላይ ለሚጫን እቃ የአሽከርካሪው ሀላፊነት እቃውን መጫንና ማውረድን ያካትታል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
27. የጉዞ መረጃዎች የሚባሉት ?
ሀ. የጉዞ መስመር ካርታ ሐ. የእርዳታ መስጫ አድራሻዎችን ማወቅ
ለ. የማህበረሰቡን ባህልና ወግ ማወቅ መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
28. በትራንስፖርት ዘርፍ የተሽከርካሪው ባለቤት የሥራ ድርሻ ከሆኑት ውስጥ ብቃት ያለው አሽከርካሪ ማቅረብን
ያካትታል፡፡

ተሳ ፋሪዎች Page 2
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
29. በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ ከቁጥጥር ደረጃዎች ውስጥ የሚካተተው የቱ ነው?
ሀ. ባለንብረቶች ሐ. እረዳቶች
ለ. አሽከርካሪዎች መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
30. የተሳፋሪውን ብዛት መቁጠር የአሽከርካሪው ሀላፊነት ነው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
31. ለተሳፋሪዎች መረጃ የመስጠት ሀላፊነት የረዳቱ ነው?
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
32. በጉዞ ወቅት አደጋ በሚያጋጥምበት ጊዜ መረጃ የሚተላለፍለት አካል የቱ ነው?
ሀ. ፖሊስ ሐ. ህክምና መስጫ
ለ. ቀይ መስቀል መ. ሁሉም መልስ ናቸው
33. በጉዞ ወቅት የባለንብረቱ የሥራ ኃላፊነት ለተሳፋሪዎች የሻይ ቡና ሰዓትን ማሳወቅና ማክበር ነው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
34. የተሽከርካሪን ፍጥነት መቆጣጠር የሥራ ላይ ሁኔታ ተብሎ ይገለጻል፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
35. ተሳፋሪን ከታሪፍ ውጪ ማስከፈል ህገ ወጥ ነው ፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
36. የተሳፍሪ እቃ ሲጫን የእቃው ታግ ለተሳፋሪው መሰጠት ይገባዋል፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
37. ተሳፋሪዎች ሻንጣዎቻቸውን የፈለጉበት ቦታ ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
38. እቃዎች በተሽከርካሪ ላይ ሲጫኑ የት ቦታ ላይ መቀመጥ እንዳለባቸው የሚወስነው ባለንብረቱ ነው፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
39. በጉዞ ላይ መንገደኞች የራሳቸውን እቃ የመጠበቅ ሀላፊነት አለባቸው፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
40. በተሳፋሪ ሻንጣ ላይ የተለጠፈን ታግ እቃው ከወረደና ባለቤቱ ከተረከበ በኋላ ተገንጥሎ መሰብሰብ አለበት፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
41. በተሳፋሪ ሻንጣ ውስጥ ምን ምን እንዳለ የመፈተሸ ተግባር የረዳት ኃላፊነት ነው፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
42. የጐማውን ንፍስ መጠን መቆጣጠር የግንኙነት መርህ ተብሎ ይጠራል፡፡
ሀ) እውነት ለ) ሀሰት

43. ተሳፋሪዎች እንደ አወራረዳቸው ቅደም ተከተል መሠረት መቀመጥ አለባቸው፡፡


ሀ) እውነት ለ) ሀሰት

ተሳ ፋሪዎች Page 3
44. ተሳፋሪዎች በጉዞ ላይ እስከ ስንት ኪሎ ግራም ድረስ እቃ በነጻ ተሽከርካሪ ላይ ማስጫን ይችላሉ?
ሀ) 25 ሐ) 40
መ) 30 መ) 55
45. በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ውስጥ የመንገድ ህግጋትን የማክበርና የመፈፀም ሀላፊነት የማን ነው?
ሀ) የአሽከርካሪው ሐ) የባለንብረቱ
ለ) የረዳቱ መ) የሁሉም
46. ጥራቱን የጠበቀ ተሸከርካሪ አቅርቦ አገልግሎቱን ቀልጣፋና አስተማማኝ ማድረግ የትራንስፖርት ባለስልጣን የሥራ
ድርሻ ነው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
47. በተሳፋሪ ሻንጣ ውስጥ ምን ምን እንዳለ የመፈተሸ ተግባር የተሽከርካሪው ባለንብረት ነው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
48. በህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ውስጥ የሚለጠፍ ማስታወቂያ ሊይዝ የሚገባው መረጃ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የተሳፋሪ ብዛት
ለ. የተሳፋሪ መብትና ግዴታ
ሐ. የባለንብረት አድራሻና ስልክ
መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
49. በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ተሸከርካሪው ተበላሽቶ ከቆመና ለጥገና ረጅም ጊዜ የሚወስድ ከሆነ አሽከርካሪው
/ባለንብረቱ/ ለተሳፋሪዎቹ የአገልግሎት ክፍያውን መመለስ አለበት፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
50. ስለ ከተማ አውቶቡስ ትክክል የሆነው የቱ ነው ?
ሀ. ትኬቱ ለተሳፋሪው መስጠት ያለበት ጉዞ ከመጀመሩ በፊትና ነው
ለ. ትኬቱ ለማንኛውም ጉዞ ያገለግላል
ሐ. አንድ ሰው ትኬቱን ከተጠቀመበት በኋላ ወደ ሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችላል
መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
51. አንድ የሕዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪ በሰጠው አገልግሎት መጠን ልክ የአገልግሎት ክፍያ የማስከፈል መብት አለው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
52. በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት የአገልግሎት ክፍያ እንደ ስምምነቱ መሰረት በኮንትራት ለአንድ ጊዜ ጉዞ ያገለግላል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
53. አንድ አሽከርካሪ የተሳፋሪዎችን እቃ በሚገባ ማሸግና ማሰር አለበት፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
54. ቱሪስቶችን የሚያጓጉዝ አሽከርካሪ በቅድሚያ ማዘጋጀት ያለበት የቱን ነው?
ሀ. በቂ ገንዘብና ነዳጅ
ለ. ድንኳንና ልብሶችን
ሐ. የመጀመሪያ የህክምና መስጫ መሣሪያ
መ. ሁሉም መልስ ናቸው
ተሳ ፋሪዎች Page 4
55. ተማሪ የሚያጓጉዝ አሽከርካሪ ሞተር ሳይጠፋ ወርዶ ተማሪዎቹ በሙሉ ወደ ተሸከርካሪው መግባታቸውን ማረጋገጥ
አለበት፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
56. ከሚከተሉት አንዱ ከጉዞ ዓይነቶች ውስጥ አይመደብም፡፡
ሀ. መካከለኛ ጉዞ ሐ. የከተማ ውስጥ ጉዞ
ለ. እረጅም ጉዞ መ. መልሱ አልተሰጠም
57. ተሸከርካሪው ሙሉ ለሙሉ በመቆሚያ ቦታ ቆሞ በር ከመከፈቱ በፊት መንገደኞች ከመቀመጫቸው መነሳት
እንደሌለባቸው የማሳሰብ ኃላፊነት የማን ነው?
ሀ. የረዳቱ ሐ. የሱፐርቫይዘሩ
ለ. የአሽከርካሪው መ. የሁሉም
58. አንድ የሕዝብ ትራንስፖርት የሚያሽከረክር አሽከርካሪ የተሳፋሪዎችንና የሻንጣዎቻቸዉን ደሕንነት ጠብቆ በተፈለገው
ቀንና ሰአት የማድረስ ሀላፊነት አለበት
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
59. አንድ የሕዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪ የተሳፋሪዎችን ዕቃ ፖርቶ መጋሊያ ላይ ወጥቶ የመጫን ግዴታ አለበት
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
60. አንድ የሕዝብ ትራንስፖርት የሚያሽከረክር አሽከርካሪ አካል ጉዳተኞችን የጫነና መንገዱ የተበላሸ ቢሆን ምን
ማድረግ አለበት?
ሀ/ በከፍተኛ ፍጥነት ማሽከርከር
ለ/ ከተሸከርካሪው ወርደው በእግር እንዲሄዱ ማድረግ
ሐ/ በዝቅተኛ ፍጥነት ምቾታቸውን ጠብቆ ማሽከርከር
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው

61. አንድ የሕዝብ ትራንስፖርት የሚያሽከረክር አሽከርካሪ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት


ሀ/ ዕቅድ እና የጉዞ መስመር ካርታ ማወቅ አለበት
ለ/ የመንገዱን ባሕሪያትና የአካባቢውን ደሕንነት ማወቅ አለበት
ሐ/ አደጋ በሚያጋጥም ጊዜ መረጃ የሚያስተላልፍለትን አካል ማወቅ አለበት
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው

62. አንድ የሕዝብ ትራንስፖርት የሚያሽከረክር አሽከርካሪ የሚጓዝበትን አካባቢ ባሕል እና ሐይማኖት ማወቅ
አያስፈልገውም
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
63. በሚመለከተው መ/ቤት ለጉዞ የተመደበውን የትራንስፖርት ታሪፍ የማስከፈል ግዴታ የ ነው፡፡
ሀ. አሽከርካሪው ሐ. የረዳቱ
ለ. የተሳፋሪው መ. የባለንብረቱ

ተሳ ፋሪዎች Page 5
64. ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውልን ደረሰኝ የማሳተም መብት የማን ነው
ሀ. የአሽከርካሪው ሐ. የረዳቱ
ለ. የተሣፋሪው መ. የባለንብረቱ
65. በሕዝብ ማመላሻ ትራንስፖርት ውስጥ ተሣፋሪዎች በመቀመጫ ወንበሮች ላይ መቀመጥ ያለባቸው በአወራረዳቸው
ቅድም ተከተል መሠረት መሆን አለበት፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
66. አንድ ተሣፋሪ ዕቃውን ሲረከብ ዕቃው ላይ የተለጠፈውን ታግ ገንጥሎ መጣል አለበት፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
67. በአንድ ላይ መጫን የሌለባቸውን እቃዎች አስቀድሞ መለየት እቃዎቹ እንዳይበላሹ ለመከላከል ይጠቅማል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
68. እቃዎች በተሸከርከሪ ላይ ሲጫኑ በተገኘው ቦታ ላይ መሆን አለበት፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
69. መልካሙንና መጥፎውን መለየት የሚያስችል ዘርፍ ሙያ ይባላል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
70. በአሁን ወቅት በሀገራችን ለአካል ጉዳተኛ ተጓዦች በቂና የተሟላ አገልግሎት በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
71. እያንዳንዱ በተሸከርካሪ ላይ የሚጫን እቃ የራሱ የሆነ የአጫጫንና አያያዝ ደንብና ስርአት አለዉ
ሀ/እውነት ለ/ ሀሰት
72. ተሳፋሪዎች የራሳቸዉን እቃ እራሳቸዉ መጫንና ማውረድ አለባቸዉ
ሀ/እውነት ለ/ ሀሰት
73. አሽከርካሪዎች ለተሳፋሪዎች ተገቢዉን አክብሮትና ክብር መስጠት አለባቸዉ
ሀ/እውነት ለ/ ሀሰት
74. አብዛኛዉን ጊዜ ሱፐርቫይዘሩ እቃ የሚጭንና የሚያወርድ ሰዉ ነዉ
ሀ/እዉነት ለ/ሀሰት
75. እያንዳንዱ በተሸከርካሪ ላይ የሚጫን እቃ የራሱ የሆነ የአጫጫንና አያያዝ ስርዓት አለዉ
ሀ/እውነት ለ/ ሀሰት
76. ተሳፋሪዎች የራሳቸዉን እቃ እራሳቸዉ መጫንና ማውረድ የለባቸውም
ሀ/እውነት ለ/ ሀሰት
77. አሽከርካሪዎች ለተሳፋሪዎች ተገቢዉን አክብሮትና ክብር መስጠት ያለባቸው እንደ አለባበስና ቁመናቸው መሆን
ይኖርበታል
ሀ/እውነት ለ/ ሀሰት
78. በአብዛኛዉን ጊዜ ሱፐርቫይዘር የጉዞ ሥምሪት የሚፈቅድ ሠራተኛ ነው
ሀ/እውነት ለ/ ሀሰት

ተሳ ፋሪዎች Page 6
79. አንድ አሽከርካሪ ተሳፋሪ ሙሉ ለሙሉ ወርዶ ከጨረሰና በር ከተዘጋ በኋላ ተሸከርካሪዉን ማንቀሳቀስ
ይኖርበታል፡፡
ሀ/እውነት ለ/ ሀሰት
80. የተሳፋሪዎችን ሻንጣ ተቆጣጥሮ ሚዛን ማስመዘንና በታሪፍ መሰረት ማስከፈል የማን ሀላፊነት ነዉ?
ሀ. የረዳቱ ለ. የአሽከርካሪዉ
ሐ. የባለንብረቱ መ. ሁሉም መልስ ነዉ
81. አንድ አሽከርካሪ ለመንገደኛ እቃዎች ማድረግ ያለበት
ሀ. በታሪፍ መሰረት ማስከፈል
ለ. እቃዉ ላይ ታግ መለጠፍ
ሐ. እንደመንገዶኛች የአወራረድ ቅደም ተከተል እቃዎችን መጫን
መ. ሁሉም መልስ ናቸዉ
82. የመንገደኛ እቃዎች በሚጫኑበት ጊዜ መደረግ ከሚገባዉ ጥንቃቄ ዉስጥ የማይከተተዉ የቱ ነዉ?
ሀ. እቃዎችን በሚገባ ማሸግና ማሰር
ለ. በአንድ ላይ መጫን የሌለባቸዉን ዕቃዎች መለየት
ሐ. በሚጫንበት ጊዜ የእቃዉን አያያዝና አቀማማጥ መወሰን
መ. እቃዎችን በአንድ ላይ ቀላቅሎ ማስቀመጥ
83. የተሳፋሪዎች እቃ በሚጫንበት ጊዜ እንደ አቀማመጣቸዉ ቅደም ተከተል መሆን ይኖርበታል፡፡
ሀ. እዉነት ለ. ሀሰት
84. በተሽከርካሪ ላይ የተጫኑት እቃዎች በሚወርዱበት ጊዜ
ሀ. እንደተጫኑበት ዘዴና ጥንቃቄ መሠረት መሆን ይኖርበታል
ለ. የእቃዉን ደረሰኝ በመቀበል እቃዉን ለባለቤቱ ማስረከብ ይገባል
ሐ. ሀ እና ለ መልስ ይሆናሉ
መ. መልሱ አልተሰጠም

85. የመንገዶኞችን እቃዎች በአግባቡ ተቆጣጥሮና ጠብቆ አለማድረስ


ሀ. በጉዞ ወቅት ጊዜን ይቆጥባል ሐ. የአሽከርካሪዉ ታማኛነት ይጨምራል
ለ. ለኪሳራ ይዳርጋል መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
86. አካል ጉዳተኛ መንገደኞች በትራንስፖርት ዘርፍ ዉስጥ እኩል ከሌሎች መንገዶች ጋር መስተናገድ ይኖርባቸዋል፡፡
ሀ. ሀሰት ለ. እዉነት
87. አሽከርካሪዎች ለአካል ጉዳተች ማድረግ ከሚገባቸዉ ተግባራት ውስጥ የማይካተተዉ የቱ ነዉ?
ሀ. የቅድሚያ ትኬት እንዲያገኙ ማድረግ
ለ. ወንበር አስለቅቆ ማስቀመጥ
ሐ. |ላ ወንበር ላይ ረዳቱ አጠገብ እንዲቀመጡ ማድረግ
መ. መልሱ አልተሰጠም
88. በአገራችን ለአካል ጉዳተች እንዲያመች ተብሎ የሚሰጥ የትራንስፖርት አገልግሎት የለም፡፡
ተሳ ፋሪዎች Page 7
ሀ. እዉነት ለ. ሀሰት
89. አካል ጉዳተች ከመኪና ሲወርዱም ሆነ ሲወጡ አቅፎና ደግፎ መንከባከብ ተገቢ ነዉ፡፡
ሀ. እዉነት ለ. ሀሰት
90. አካል ጉዳተኛ መንገዶች መኪና ዉስጥ በሚሳፈሩበት ጊዜ መቀመጥ ያለባቸዉ የት ነዉ
ሀ. መሀል ላይ ሐ. ከሹፊሩ አጠገብ
ሐ. ከፊት መ. ከ|ላ ከረዳቱ አጠገብ
91. አንድ አሽከርካሪ በአገልግሎት ወቅት ለአካል ጉዳተች ግዴታ የሌለበት ተግባር 
ሀ. ከታሪፍ በታች እንዲከፍሉ ማድረግ
ለ. እንዳይንገላቱ እረጋ ብሎ ማሽከርከር
ሐ. የቅድሚያ ትኬት እንዲያገኙ ማድረግ
መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
92. በሰለጠኑት ዓላማት ለአካል ጉዳተች ተብለዉ የሚዘጋጁ የትራንስፖርት ዘርፎች ይገኛሉ፡፡
ሀ. እዉነት ለ. ሀሰት
93. አንድ አገልግሎት ሰጪ አካል ስለ አገልግሎት አሰጣጥ መርሆችና ሥርዓቶች ጠንቅቆ የመረዳት ግዴታ የለበትም፡፡
ሀ. ሀሰት ለ. እዉነት
94. በመ/ ቤት ወይንም በድርጅት መርሆችና ሥርዓቶች ውስጥ መካተት ከሚገባቸው ነገሮች የማይመደበዉ የቱ ነው?
ሀ. የሠራቶችን የቅጥር ሁኔታ ሐ. ስለ ዲሲሊን እርምጃ አወሳሰድ
ለ. የሠራተችን የደሞዝ ሁኔታ መ. መልሱ አልተሰጠም
95. የድርጅት የአገልግሎት መስጫ መርሆችና ሥርዓቶች ከድርጅት ድርጅት ሊለያዩ ይችላሉ፡፡
ሀ. እዉነት ለ. ሀሰት
96. በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች የሚሠጡትን አገልግሎት ለመንገዶኞች በግል ማብራራትና
በጉልህ እንዲታይም መለጠፍ ግዴታቸዉ ነዉ፡፡
ሀ. እዉነት ለ. ሀሰት
97. የድርጅቶችን የአገልግሎት መርሆችና ሥርዓቶችን ማወቅና ጠንቅቆ መረዳት የአገልግሎት ሰጪዉ አካል ብቻ ነዉ፡፡
ሀ. ሀሰት ለ. እዉነት
98. የትራንስፖርት አገልግሎት ከሌሎች ዘርፎች በበለጠና በተለየ የህዝቦችን የእርስ በርስ ግንኙነት ለማጠናከር ያለዉ
ፋይዳ እጅግ የላቀ ነዉ፡፡
ሀ. እዉነት ለ. ሀሰት
99. በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማራ አንድ አሽከርካሪ ሊያውቃቸዉና ሊተገብራቸዉ ከሚገቡ አቢይ ጉዳዩች ዉስጥ
የማይካተተው የቱ ነው
ሀ. የአከባቢዉን እሴት ማወቅ ሐ. የአከባቢዉን ሀይማኖት መረዳት
ለ. የህብረተሰቡን ባህል ማወቅ መ. መልሱ አልተሰጠም
100. አሽከርካሪዎች ከቦታ ወደ ቦታ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ለሁሉም ህብረተሰብ ክፍል ማድረግ ያለባቸው፡፡
ሀ. አክብሮት መስጠት ሐ. ለሁሉም እኩል ፍቅር መለገስ
ተሳ ፋሪዎች Page 8
ለ. ታማኝነታቸዉን ማረጋገጥ መ. ሁሉም መልስ ናቸዉ
101. አንድ አሽከርካሪ የመንገዶኞች እቃ በሚጫንበት ጊዜ ማወቅ ያለበት አቢይ ነጥብ
ሀ. እቃዉ በደንብ የታሰረና የታሸገ መሆኑን ማረጋገጥ
ለ. እቃዉ ተሰባሪ መሆንና አለመሆኑን መለየት
ሐ. እቃዉ በቀላሉ ሊበላሽ የሚችል መሆኑን መወቅ
መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
102. በመኪና ላይ የሚጫን የመንገዶኞች እቃ ቢጠፋ / ቢሰረቅ / ተጠያቂው ማን ነው
ሀ. አሽከርካዉ ሐ. ባለቤቱ
ለ. ረዳቱ መ. አሠሪዉ ድርጅት
103. ከሚከተሉት ዉስጥ አንዱ በመኪና ላይ ለሚጫን እቃ የአሽከርካዉ ሀላፊነት አይደለም፡፡
ሀ. የእቃዉ አጫጫን ሁኔታ ለ. የእቃዉ አወራረድ ሁኔታ
ሐ. እቃዉን መጫንና ማዉረድ መ. እቃዉን ከስርቆት መጠበቅ
104. አንድ አሽከርካሪ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ስለ ጉዞዉ ጠቃሚ መረጃዎችን መሰብሰብና መዘጋጀት ተገቢ ነዉ፡፡
ሀ. አዉነት ለ. ሀሰት
105. የጉዞ መረጃዎችን መሰብሰብ ለምን ያስፈልጋል?
ሀ. ከአላስፈላጊ እንግልት ያድናል ሐ. ከጊዜ ብክነት ያድናል
ለ. ከአላስፈላጊ ወጪ ያድናል መ. ሁሉም መልስ ይሆናል
106. ከሚከተለት አንዱ ከጉዞ መረጃዎች ዉስጥ አይካተትም
ሀ. የጉዞመስመር ካርታ
ለ. የተሳፋሪዎችን የጤና ሁኔታ
ሐ. የማህረሰቡን ባህልና ወግ ማወቅ
መ. መልሱ አልተሰጠ
107. ጉዞ ከመጀመሩ በፊት እያንዳንዱ አሽከርካሪ ስለሚ¹ዝበት የመንገድ ባህሪና የÐጥታ ሁኔታ ማጣራት ይኖርበታል፡፡
ሀ. እዉነት ለ. ሀሰት
108. በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ዉስጥ የተለያዩ የቁጥጥር ደረጃዎች ማዋቀር የአሽከርካሪዉ ሀላፊነት ነዉ፡፡
ሀ. ሀሰት ለ. እዉነት
109. በአንድ የትራንስፖርት አገልግሎት የተሰማራ ድርጅት በዉስጡ ከሚያቅፋቸው የተለያዩ የቁጥጥር አካላት ዉስጥ
የማይካተተው የቱ ነው
ሀ. ባለንብረቶች ሐ. ረዳቶች
ለ. አሽከርካሪዎች መ. ሁሉም መልስ ናቸዉ
110. የአሽከርካሪዉ የሥራ ሀላፊነት ከሆኑት ዉስጥ የማይመደበዉ የቱ ነው
ሀ. ከጉዞ በፊትና በ|ላ ፍተሻ ማድረግ
ለ. የተሳፋሪዉን ብዛት መቆጣጠር
ሐ. የመንገደችን እቃ መጠበቅ

ተሳ ፋሪዎች Page 9
መ. የተሳፋሪዎችን ደህንነት መጠብቅ
111. በጉዞ ወቅት የረዳት የሥራ ድርሻ የሆነዉ የቱ ነዉ?
ሀ. ለተሳፋሪዎች መረጃ መስጠት
ለ. የመንገዶችን እቃ መጠበቅ
ሐ. ከጉዞ በፊትና ከጉዞ በ|ላ የተሸከርካሪዉን ጤንነት መጠበቅ
መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
112. ተሳፋሪዎች ሲወርዱና ሲሳፈሩ በአግባቡ መሆኑን የማወቅና የመቆጣጠር ሀላፊነት የ ነዉ
ሀ. የአሽከርካሪዉ ሐ. ረዳቱ
ለ. የባለንብረቱ መ. ሁሉም መልስ ናቸው
113. የባለንብረቱ / የሱፐርàይዘሩ / የሥራ ሀላፊነት የሆነው የቱ ነዉ?
ሀ. የተሳፋሪዉን ድህንነት መጠበቅ
ለ. አስተማማኝ ብቃት ያለዉ አሽከርካሪማቅረብ
ሐ. ተሸከርካሪዉ ሲቆም ጤንነቱ መፈተሸ
መ. ተሳፋሪዎችንና ንብረታቸዉ ከጥፋት መጠበቅ
114. አደጋ በሚያጋጥምበት ጊዜ መረጃ ከሚተላለፍላቸዉ አካላት ዉስጥ የማይመደበዉ ነዉ
ሀ. ቀይ መስቀል ሐ. ባለንብረት
ለ. ፖሊስ መ. መልሱ አልተሰጠም
115. የባለንብረቶች የሥራ ድርሻ የሆነዉ የቱ ነዉ?
ሀ. ለጉዞ አስፈላጊ ግብዓቶችን ማቅረብ ሐ. ብቃት ያለዉ አሽከርካሪ መቅጠር
ለ. ስለ ጉዞዉ እቅድ ማዘጋጀት መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
116. በትራንስፖርት ዘርፍ ከቁጥጥር ደረጃዎች ዉስጥ የማይካተተዉ የቱ ነው
ሀ. ጫኝና አዉራጅ ሐ. ባለንብረቱ / ሱፐርቫይዘር/
ለ. አሽከርካሪዉ መ. ረዳቱ
117. በጉዞ ወቅት ለተሳፋሪዎች የምሳና ሻይ ቦታና ሰዓት የማሳወቅና የማክበር የሥራ ድርሻ ____ ነዉ፡፡
ሀ. የረዳቱ ሐ. የአሽከርካሪዉ
ለ. የባለንብረቱ መ. የሱፐርቫይዘሩ
118. በድርጅት የሚዘጋጁ የመረጃ መያዥ/ቅች/ ከሚይዛቸዉ መረጃዎች ዉስጥ የማይካተተዉ የቱ ነዉ?
ሀ. መነሻና መድረሻ ቦታ ሐ. የተጠቀመዉ የነዳጅ መጠን
ለ. የድርጅቱ ሥም መ. መልሱ አልተሰጠም
119. ስራ አካባቢ ግጭቶች እንዳይነሱ ከሚረዱ ሥልቶች ዉስጥ የማይመደበው የትኛዉ ነዉ?
ሀ. ፍፁማዊነት ለ. መደራደር
ሐ. ቸር መሆን . መልሱ አልተሰጠም

ተሳ ፋሪዎች Page 10
120. ሰላማዊ የሆነ የትራንስፖርት አሰጣጥ እንዲኖር ተሳፋሪዎችም የራሳቸው ድርሻ አላቸው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

ተሳ ፋሪዎች Page 11

You might also like