Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 69

Kedemena

belay
Writer Biruk molla

Eden film production

[] ከደመና በላይ

ማስታወሻ የሚሰጠው ድጋሚ ለማታገኘው ሰው ሲሆን ብቻ ነው

0940198826

ሲን ምንታጅ
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

1. መስኮቱ ተከፍቷል ብርሀን ወደ ውስጥ እየገባ ነው የጥዋት ብርሃን መሆኑን እንረዳን፡፡ አልጋ ላይ ዳንኤል
/27/ ተኝቷል፡፡ ከትራስጌው አጠገብ ጠረጴዛ እናያለን፡፡ ጠረጴዛው ላይ ቀይ ጽጌሬዳ አበባ እናያለን፡፡ ዳንኤል
ከእንቅልፍ ሲባንን ከጠረጴዛው ላይ ቀይ አበባውን ሲያይና በፈገግታ አንስቶ ከመኝታ ቤቱ ሲወጣ እናያለን፡፡
ሳሉን ቀይ ጽጌሬዳ አበባውን ይዞ ሲገባ ጁስና ቁርስ ምግቦችን ጠረጴዛው ላይ ተቀምጦ ያያል፡፡ ሔዩ
መመገብ ይጀምራል…. ስልክ አንስቶ ሲደውል እናያለን፡
v/o
ዳንኤል
ሰው የሚኖረው የራሱን ሒወት ሊመራ በራሱ መንገድ ላይ ተራምዶ ልሎችን ሊርሳ
ከሆነ የኖረበትን አለም ትርጉም አላወቀውም ማልት ነው

2 አካባቢው የጠዋት ግርግር ያለበት አካባቢ ሲሆን በብዙ ሰዎች መሀል ….ሔለን ብዙ መጽሐፎችን ይዛ
ስልክ እያወራች ስትሄድ እናያለን፡፡ፊቷ ላይ ፈገግታ ይታያል፡፡

v/o
ዳንኤል
ትላለች ....በእሷ አእምሮ ውስጥ እኔ አለው ድስተኛ ንኝ

3 ዳንኤል ፎቶ ካሜራውን ይዞ የተለያዩ ነገሮችን ሲያነሳ እናያለን

4 ሔለን በጣም የሚያምር አለባበስ ለብሳ ወደ በሩ እያየች እናያለን፡፡ ወደ በሩ የምታየው በፈገግታ ነው፡፡ ቤቱ
ውስጥ ብትን ያሉ አበባዎች ተበትነዋል፡፡ የሻማ ብርሃን በየቦታው ሆኖ በሚያምር አደራደር ተደርድረው
እናያለን፡፡ በሩ ተከፈተ ዳንኤል ገባ፡፡ በጣም ደስ አለው አቀፋት በተከፈተው

ሙዚቃ መደነስ ጀመሩ

ሲን 2 ውስጥ መኝታ ቤቱ ውስጥ/ጠዋት/

መኝታ ቤት ውስጥ በውጪ የሚገባ የጸሀይ ብርሃን እናያለን፡፡አልጋው ላይ ብርድ ልብስተሸፋፍነው ዳንኤል እና
ሄለንን እናያቸዋለን ፡፡ ሁለቱም ብርድ ልብስ ውስጥ ሁነው እናያቸዋለን፡፡ ሄለን በፍቅር ደስ በሚል ስሜት አይኑን
እያየችው ነው ዳንኤል በጣም በስስት አይን አይኗን እያያት ነው፡፡

ዳንኤል

/በስስት እያያት/

ሔለን …. ሁሌም ደስተኛ ነኝ፡፡

ሔለን

/በፍቅር ስሜት/

እውነት አንድ ነገር ልንገርህ እኔ በዚህ አለም ላይ ካሉት ሰዎች ጋር ከማሳለፍ ደስታ

በላይ ካንተ ጋር ሁኜ ሁሌም አይንክን ማየቴ ያስደስተኛል…..

ዳንኤል

እኔም ….. የኔ ፍቅር ….. አንድ ቀን እንደምታገቢኝ ተስፋ አደርጋለሁ

ሔለን

አዎ …. በእውነት . አገባሀላው ግን ያስብኩት በስደተኞች ላይ የምጽፈውን

ጥናታዊ መጽሐፌን ስጨርስ ነው የማገባህ

ዳንኤል

እሺ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ….

1
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

/ሔለን ….. በአዎንታ እራሷን ወዘወዘች …. ዳንኤል ፈዞ አያት/

ዳንኤል

አይንሽ ለሰኮንዶች ተጨፍኖ እስኪገለጥ የማሳይሽ ስጦታ ትቀበያለሽ

ሔለን

/በደስታ እያየችው/

የአንተን ስጦታ ለመቀበል ለሰኮንዶች አይደለም እድሜ ልኬንም ቢሆን እጨፍናለው፡፡

ዳንኤል

እሺ ….. አሁን …. አይንሽን ጨፍነሽ እስክትገልጭው ስጦታ አለኝ፡፡

ሔለን

እሺ

በዝምታ ተያዩ …. ሔለን ካየችው በኃላ አይኗን ጨፈነችው ወዲያውኑ ገለጠችው ዳንኤል የቃል ኪዳን
ቀለበት በጣቱ ይዟል ደነገጠች ፈገግ አለ …. በጣም ደስ አላት፡፡

ዳንኤል

/ቀለበቱን ወደ ጣቱ አስጠግቶ/

ቃል እንድትቢልኝ እፈልጋለው

ሔለን የተሰማትን ስሜት በደስታ መቆጣጠር አቅቷት ጣቷን ዘርጋችለት፡፡ ቀለበቱን አደረገላት ደስ አላት
ከብርድ ልብሱ በላይ ሁነን እነሱ ውስጥ ሲተቃቀፍ እናያለን፡፡

ሲን 3

ውስጥ የሄለን እናት /አበበች/ ቤት ቀን፧፧

ከቤቱ ሁኔታ በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ሰው መሆናቸውን እንረዳለን፡፡ ቤቱ ውስጥ የሄለን እና የአበበች
ፎቶዎች እናያለን ወ/ሮ አበበች ከፊት ካለው መቀመጫ ላይ ቁጭ ብለዋል፡፡ ከእነሱ ትይዩ ዳኤልና ሔለን ቁጭ
ብለዋል፡፡ ከውስጥ ወደ ውጪ የበግ ግልገል ድምጽ እና የእናት በግ ድምጽ እንሰማለን ፡፡

ሄለን

በግሽ ወለደች

እናት

አዎ

ሄለን

እኔኮ እማ ግራ ነው እምትገባኝ . . . አዲስ አበባን እምታክል ከተማ ላይ


በግ ማሳደግ አይከብድም . ..
እናት

ሰው ጋር ሁነው ይቅርና ጎዳና ጫት እየበሉ ይኖሩ የለ … ግን እኒ በጎች ካለ እረኛ እንዲኖሩ አልፈልግም . . . እና


ደሞ የድሮው እረኝነቴ ይናፍቀኛል . . .

2
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ዳንኤል

/ በመገረም /
ለዛ ነው እሚያሳድጉት

እናት

አዎ እኔ ደስታዬ ሁሉም ሰው ለራሱ ሰው እረኛ ነው… ከእንግዲ አንተ ነህ ልጄን እምጠብቀው . . . ደሞ


አባቴ መድሃኒያለም ያግዝሃል እኔም ልጄን ድሬ ሁላችንን ወደሚጠብቀን እረኛ መሄድ ቤቱ ሁኜ ላመሰግነው
እፈልጋለው ፡፡

ሔለን

/በስስት እያየቻቸው/
እማ እወድሻለው

ወ/ሮ አበበች እናት

እኔም ሰ

ተቃቀፉ ….. ዳንኤል ደስ በሚል ስሜት ውስጥ ሁኖ ያያቸዋል፡፡ ከውጪ የግልገሏ ድምጽ እና የእናቷ
ድምጽ ይሰማል ፡፡

ሲን 4

ውስጥ የዳንኤል ፎቶ ስቱዲዮ ቀን

ቢሮው ሰፊ ቢሮ ሲሆን የተለያዩ የሚያማም ፎቶዎች እናያለን ስምንት ሴትና ወንድ ሰራተኞች ኮምፒተር
ላይ ሁነው ስራ እየሰሩ እናያለን፡፡ በመስታወት የተከለለች ቢሮ እናያለን ያሬድ የቢሮ ሰራተኛ ስልክ እያወራ
እናያለን ድምጽ አንሰማም የቢሮ በር ተከፈተ ዳንኤል ወደ ውስጥ ገባ፡፡

ያሬድ

/ስልክ እያወራ/

እሺ ሁለተኛው ፎቶ ለመግዛት ፕሮፓዛል ማስገባት ትችላለኸ

ወንድ o/s

እሺ ….. አመሰግናለው

ያሬድ

/ዳንኤልን እየተመለከተው/

ደና ዋሉ

ስልኩን ዘጋው …. ዳንኤልን እየተከተለ ሲሄድ እናያለን፡፡

ያሬድ

አለቃዬ ዛሬ የኪንያ እና የሳውዝ አፍሪካ ደንበኞች በሚሰሩት ፋሽን

ሾው ላይ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

3
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ዳንኤል

ቀኑ መቼ ነው ?

ያሬድ

በነሱ ኦክቶበር 1 የኬኒያው …. የሳውዝ አፍሪካው ሴብቴምበር 25 ነው፡፡

ዳንኤል

እንደዛ አልችልም ….. እዚሁ ሀገር ውስጥ የሀገረሰብ እሴቶችን ለበሐልና ቱሪዝ

የተስማማውት የረጅም ጊዜ ስራ አለብኝ

ዳንኤል የመስታወት ክፍሉን ቢሮ ከፍቶ ገባ፡፡ ቁጭ አለ

ያሬድ

ስለዚህ ለመልስ ?

ዳንኤል

/አናቱን እየነቀነቀ/

አዎ

ያሬድ በአክብሮት አመሰግኖ ወጣ፡፡ ዳንኤል ቀለበቱን በጣቱ እየነካካ እናያለን፡፡

ሲን 5

ውስጥ ከፌ ቀን

ካፌ ውስጥ ሰዎች ብቻ ነው የምናየው፡፡ ሄለን እና ደላላው ሳምሶን /40/ እያወሩ እናያለን ትኩስመጠጦች
እየጠጡ እናያለን፡፡ ሳምሶን ሱሰኛ እና የሚስፈራ ፊት ያለው ሰው ነው፡፡

ሄለን

እሺ ስለ ጉዞው ሂደት ንገረኝ

ሳምሶን

እየውልሽ …. መጀመሪያ እስከ ኬንያ በህጋዊ መልኩ ነው የምትሄጅው

ከኬኒያ በህገወጥ መንገድ በመኪና ከሄድሽ በኃላ ዩጋንዳ ትደርሺያለሽ ከዩጋንዳ

በእግር ሰሜን አፍሪክ ከደረስሽ በኃላ በመርከብ ወደ ጣሊያን ትገቢያለሽ፡፡

ሄለን

ምን ያህል ጊዜ ይፈጅብኛል ?

ሳምሶን

2 ወር …. እና በየ ሀገራቱ ለሚጥሙሽ ደላሎች የምትከፊውን ዶላር

መዘርዘርሽን እንዳትረሺ፡

፡ ወደ ካፌው ዳነኤል ሲገባ እናያለን፡፡ አጠገባቸው ደርሶ ሰላም ሲባባሉ እናያለን፡፡

ሔለን

4
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ፍቅረኛዬ ነው

ደላላውና ዳንኤል ሰላም ተባባሉ፡፡

ሲን 6

ውጪ የእነ ሄለን ግቢ ማታ

ግቢው ውስጥ ካለ ግሪን ኤሪያ ቦታ ላይ ጨርቅ ተነጥፎ እናያለን፡፡ ሔለን እና ዳንኤል ጨርቁ ላይ በጀርባቸው
ተኝተው ወደ ሰማይ እያዩ ነው፡፡ ሰማዩ ደመና ለብሷል፡፡ ደመና ውስጥ ጨረቃ ተደብቃለች፡፡ የጨረቃዋ ብርሃን
ደመናው ውጦት እናያለን፡፡ ሁለቱም ደስ በሚል ስሜት ሰማዩን እያዩት እናያለን፡፡

ሄለን

/በጣም ዝም ባለ ስሜት/

ድሮ በልጅነቴ በብዙ ህይወት ውስጥ ተደብቄ ነበር …. ልክ በደመና

ውስጥ እንዳለችው ጨረቃ እኒም ….. መፈተን እወዳለው … ሰው ስኬቱን ይበልጥ የሚወደው
ባለፈ ታሪኩ ሲፈተን ነው እኔም ያለፈው

ታሪኬ እንደዚች ጨረቃ ደመና ውስጥ ነበር …..

ዳንኤል በአትኩሮት እያያት እያዳመጣት ነው ፡፡ ሔለን በተመስጦ እያወራች ነው፡፡

ሄለን

አባቴን አላውቀውም …. እናቴ ስለ አባቴ የነገረችን

እንደሞተ ብቻ ነው፡፡ በጣም ድሆች ስለነበርን ዝቅተኛ ስራ እየሰራች

እናቴ ታስተምረኝ ነበር ….. እኔ ሂወቴን ሙሉ በጨለማ ውስጥ

ያሳለፍኩበት ጊዜን ከልቤ እወደዋለው ለዚህ ነው ጨረቃ በደመና

ስትፈተን ማየት ደስ የሚለኝ ….ብርሃን ….

እኔም ለሀገሬ አንድ ቀን የምሰጣት ነገር አለኝ

ትርምስምስ ባለ ደመና ውስጥ ደመናውን አሸንፋ ጨረቃ ስትወጣና ነጸብራቃዊ ስታበራ የዳንኤልና የሄለን
ሲት የብርሃን ምስራቅ ፊታቸው ላይ ብርሃን ሲሰጥ እናያለን፡፡

ሄለን

/በስሱ ፈገግ እያለች/

የጸሀይ እና የጨረቃ ብርሃን ወደ ምድር

ለመድረስ ሰኮንድ እንኳን አይፈጅባቸውም በቃ …. የእኔም ህይወት

እንደዚህ እንዲሆን እፈልጋለው …. ካሳለፍኩት ህይወት በኃላ

በሰኮንድ ውስጥ ሁሉም የሚያየኝ ብርሀን መሆን እፈልጋለው

…. ብዙ መጽሐፎችን ህዝቡን እያስተማርኩ ከአንተ ጋር በፍቅር

ልጅ ወልጄ መኖር እመኛለው፡፡

5
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ዳንኤል በዝምታ ካዳመጣት በኃላ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡ሄለን በዝምታ ሰማዩን እያየች ነው፡፡
ዳንኤል

ተስፋ አለኝ …. በምትጽፊያቸው መጽሀፎችሽ ብዙዎችን

ማስተማር እንደምትችይ በዚህ አለም ላይ ጸሐይና ጨረቃ

ሁለት ሁለት አይደሉም ግን … አንቺ ሁለተኛዋ

ጸሐይን ሁለተኛዋ ጨረቃን ትሆኛለሽ፡፡

ሁለቱም ዞሩ ተያዩ በጣም ተጠጋግተው ደስ በሚል ስሜት ነው የሚተያዩት

ሲን 7

ውስጥ እነዳንኤል ቤት/ሣሎን/ማታ

ሳሎን ውስጥ ቡና እየተፈላ እናያለን…. ሰላም /25/ በአለባሷ ሰራተኛ መሆኗን ያስታውቃል፡፡ ቡና እያፈላች
እናያለን የሳሎን በር ይከፈታል፡፡ ሄለን እና ዳንኤል ወደ ውስጥ ገቡ፡፡ ወንበር ላይ ተቀመጡ፡፡ ሰራተኛዋ ሁለት ሲኒ
ቡና አቀረበች ሁለቱም ቡና መጠጣት ጀመሩ፡፡

ዳንኤል

ሔለን ….

ሔለን

ወዬ የኔ ማር

ዳንኤል

ምንም ቢሆን እራስሽን ጠብቂ አስፈሪ ጉዞ ነው ጥንቃቄ ማድረግ አለብሽ

ሔለን

እሺ …. ደሞ … በየሳምንቱ እደውልልሃለው

በእሺታ እራሱን ወዘወዘ …. ቡናውን መጠጣት ጀመሩ፡፡

ሲን 8 ውስጥ የሄለን እናት ቤት /አበበች/ቀን

ቤቱ ውስጥ የተወሰነ ግርግር እናያለን …. የተለያዩ የባልትና ውጤቶች እናያለን ወ/ሮ አበበች ባልትናዎቹን
እያዘጋጁ እናያለን፡፡ ከተወሰኑ ሰኮንዶች በኃላ ሔለን የቤቱን በር ከፍታ ስትገባ እናያለን፡፡ ሔለን ትንሽ
ደነገጠች፡፡ሙሉ ሲኑ ላይ የበጎቹ ድምጽ ይሰማል

ሔለን

/በመገረም እናቷን እያየች/


እማዬ….. ይሄ ሁሉ ነገር እኮ አያስፈልገኝም

እኔ ምንም መያዝ አልፈለግም

ወ/ሮ አበበች

ምን እያልሽ ነው አይደለም ንጹዋ ልጄ ቅሪና

ሽፍታ እንኳን ከቤቱ ሲወጣ የእናቱን ስንቅ ይዞ ነው፡፡

6
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሔለን ከእናቷ አጠገብ ሄዳ ተቀመጠች፡፡ ጉንጫቸውን ሳመቻቸው፡፡


ሄለን

/በስስት እናቷን እያየች/


እማዬ….. ለኔ ስትይ ያሳለፍሽው ሂወት

በዋጋ አይመነዘርም …. ምንም ባረግልሽ

አልረካም ነገር ግን …. ስመለስ አንቺ ያሰብሽው

እንዲሳካና ቆርበሽ እግዚሀብሔርን እያመሰግነሽ

እንድትኖሪ እፈልጋለሁ …. የኔ ምኞት አንቺን ደስተኛ አድርጌ መጦር ነው፡፡

ወ/ሮ አበበች

አውቃለሁ …. ሁሉንም እረዳለው ….ልጄ እኔ ደስትኛ ሁኜ አላውቅም ...ብዙ እሚያሥክፋኝ ታሪክ አለ …

/እናት አለቀሰች/
ሄለን

/ደንግጣ /
ምን ሆንሽ እማ

ወ/ሮ አበበች

/እያለቀሰች/
የኔ ደስታ ሁልም እንደምልሽ የአንቺን ደስታ ማየት ብቻ አይደለም ... ብዙ የሚያሰቃየኝ ታሪክ አለ ... ግን
ብነግርሽ አንቺን ቢያሳምምሽ እንጂ እኔን አያክመኝም ...

ሄለን

/እየተጨነቀች/
ከኔ የደበቅሽኝ ነግር አለ ?

አበበች

/በመከፋት እያለቀሰች/
አዎ ሁሊም ባዶነቲን እሚነግረኝ ... የማልመልሰው የማልደርስበት የስቃይ ተሪክአለ

ሔለን

/እንባ እየተናነቃት/
እማ ለኔ ስትዪ አይክፋሽ ... እኔን ካለ አባት ያሳደግሽበት ጥንካሬሽ ነው ጠንካራ ያረገኝ ..

7
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

አበበች ዝም ብላ ሄለንን አየቻት ... ሔለን በዝምታ ካየቻት በኃላ አቀፈቻት …. ተቃቀፉ፡፡

ሲን 9

ውስጥ የነ ዳንኤል ቤት መኝታ ክፍል /ማታ/

ቤቱ ውስጥ ዳንኤል ብቻውን ነው የሚታየው …. ክፍሉ ውስጥ እራስጌ መብራ በርቶ ይታያ. የጨረቃ
ብርሀን ወደ ውስጥ እየገባ እናያለን፡፡ ዳንኤል የሄለንን ልብሶች እያጠፈ ሻንጣ ውስጥ ሲያስገባው እናያለን፡፡ ፊቱ
ላይ ትንሽ የመከፋት ስሜት እናያለን፡፡ ከቆይታ በኃላ ሔለን ወደ

ቤቱ ስትገባ እናያለን፡፡ ሐየለን ዳንኤል ልብስ እያጠፈ ባለበት ሁኔታ ከኃላው መታ አቀፈችው ሳመችው፡፡
እራስጌው አጠገብ ፎቶ ማንሻ ካሜራ አለ፡፡

ሔለን

/ያጠፈላትን ልብሶች እያየጭ /

የሚስፈልግሽን አጥፊልሻለው ….

ሔለን

እሺ አሁን እንተኛ

የለሌት ልብሷን መቀየር ጀመረች …. ዳንኤል ከኪሱ የወርቅ ሀብል ማስቀመጫ አወጣ … ሔለን ልብሷ
ቀይራ ዞር ስትል በእጁ የያዘውን የወርቅ ሀብል ማስቀመጫ አየጭው የዳንኤል አንገት ላይ የብር ሀብል እናያለን፡፡

ሔለን

/ወደ ዳንኤል አንዴ ወደ እቃው እያየች/

ምንድ ነው ደም ?

ዳንኤል

/ወደ ሔለን እየተጠጋ ከእቃው ወርቁን እያወጣ/

አይ ማስታወሻ ነው

ሔለን

/ በስሱ አንዴ ወርቁን አንዴ ዳንኤልን ካየችው በኃላ /

ዳንዬ …. እንደኔ እምነት ማስታወሻ የሚሰጠው

ድጋሚ ለምታገኘው ሰው ነው ….

ዳንኤል

/ትንሽ ቅር እያለው/

እና አትቀበይኝም ?

ሔለን

እሺ እቀበልሃለው …. ግን ደሞ የወርቅ ሀብል አልወድም …

8
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

. የምወደው የብር ነው፡፡

ዳንኤል

/አንዴ ሔለንን አንዴ አንገቱ ላይ ያለውን ሀብል አየ/

ሔለን

የኔ ማር አትጨነቅ …. ስመለስ ትገዛልኛለህ …

ዳንኤል አንገቱ ላይ ያለውን የብር ሀብል አውልቆ አንገቷ ላይ አሰረላት፡፡ ደስ አላት ጉንጩ ንሳመችው

ዳንኤል

የእናቴን ማስታወሻ ነው የሰጠሁሽ

ሔለን

እሺ … ዳንዬ … አሁን እስክመለስ ካንተ ጋር

መተኛት ስሚናፍቀኝ አቅፌህ በደንብ መተኛት እፈልጋለው፡፡

ዳንኤል ወደ ብርድ ልብስ ውስጥ ገባ፡፡ ተከታትለው ገቡ የትራስጌ አጠገብ ያለውን ካሜራ አነሳ
እናተሸፋፍነው ተኙዳንኤል ብርድ ልብስ ውስጥ ሆኖ ፎቶ ሲያነሳት ፍላሽ ብልጭ ሲል እናየለን

ሔለን

ፎቶ መነሳት እንደማልወድ እያወክ ታነሳኛለህ አይደል ?

ዳንኤል

አይ …. አንቺን የማስታውበት ፎቶ ፈልጌ ነው፡፡

ሔለን

አንተ ….ልጅ ማስታወሻ አትበል ….

ዳንኤል

እሺ

ከብርድ ልብስ ውስጥ ሁነው ሊያወሩ እንሰማለን የምናያቸው በብርድ ልብስ ውስጥ ሁነው ነው፡፡

ሔለን

እኔ ማስታወሻ…. ሲሰጥ ድጋሚ የማላገኘውን ሰው ነው

እኔና አንተ ገና ብዙ ያልኖርናቸው ብዙ ነገሮች አለን …

አብረን የሚያረጅ ትዝታ እንጂ እንዳንረሳሳ የሚያደርግ

ማስታወሻ አያስፈልገንም …… ሁሌም ከጎንህ ያለው ሰው ነኝ

ዳንኤል

/ልስልስ ባለ ድምጽ/

አውቃለሁ …. ሁሌም አብረሽኝ እንደምትሆኚ ግን

ለሶስት ወር መራራቅ ለኔ የመለየት ያህል ከባድ ነው፡፡

9
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሔለን

ቃል እንደገባሁልህ …. እስክመለስ ሁሌም አስብሀለው

ተመልሼ አግኝቼህ እስክኖር እናፍቃለው … ዳኒዬ

አፈቅርሀለው እሺ

ዳንኤል

እኔም …. እኔም አፈቅርሻለው …..

ብርድ ልብስ ውስጥ ሁነው ሲተቃቀፉ እናያለን፡፡

ሲን 10

ውጪ አበበች ቤት በረንዳ

በረንዳው ላይ የተለያዩ የአትክልት ቦታዎች እናያለን፡፡ የግልገሏ እናት በግ በጣም ትጨዋለች ፡፡ወይዘሮ
አበበች በመጨነቅ በጓን እያያባበሏት ነው

እናት

/ በመጨነቅ /
እሺ የት ብዬ ልፈልጋት . . . ህርሚን ብፈታብሽ ከልጅሽ አለያየሁሽ ወይ እናቴ
/ ውጪ ሊላ አተያይ /
አንድ ሴት ወንድ የሰፈር ህጻናት አፍናእጃቸውን እየነካኩ ድምጽ እያወጡ አውሮፕላኑን አንጋጠው እያዩ
ሲከተሉ እናያለን፡፡

እጅና እጃቸው እየነካኩ (ድምጽ)

/ ሃሃሃ …. አሃሃሃ … አሃሃሃ


/ ሊላ አተያይ /
ወ/ሮ አበበች በጓን እያዩ ጭወቱዋ አስጨንቋቸው እያዩዋት ከቆዩ በዋላ የአውሮፕላኑን ድምጽ ሰምተው
አንጋጠው ወደ ሰማይ እየተመለከቱ ነው የአውሮፕላን ሲሄድ እናያለን፡፡ አውሮፕላኑ እየሄደ በጉዋ በጣም
በሚያስጨንቅ ሁኔታ ስትጨው እንሰማለን ፡፡ አውሮፕላኑ እየራቀ ሲሄድ እናያለን ወ /ሮ አበበች አውሮፕላኑ
ከአይቸው እስኪርቅ በአይናቸው ሲሸኙት እናያለን፡፡ ፊታቸው ላይ በትንሹ የመከፋት ስሜት ይነበብባቸዋል፡፡

ሲን 11

ውስጥ ካፌ ቀን

ካፌ ውስጥ የተወሰኑ ሰዎች እየተዝናኑ እየጠጡ እናያለን ዳንኤልና …. መስፍን /40/ቁጭ ብለው

እናያለን ሁለቱም ማኪያቶ እየጠጡ እናያለን፡፡

መሳፍንት

/ማክያቶቸውን እየጠጣ እናያለን /

10
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ስማ ሔለን በቃ ዝም ብላሽ ሔደች አይደል ?

ዳንኤል

ባክህ አልቻለችም እንጂ እያሰበችህ ነበር

መሳፍንት

አይ ተዋት ስትመለስ ትቀጣለች፡፡

ዳንኤል

/የውሸት ኮስተር ብሎ እያየው/

እኔ እያለው አንተ ማነህ የምትቀጣው

መሳፍንት

/በሹፈት እያየው/

ያው ሚዜ ነኝ ባል ያላረገውን ሚዜ ያረጋል

ሁለቱም ሳቁ

መሳፍንት

ይልቅ …. ለምን የሻይ ቅጠሉን እርሻ በዛ አጋጣሚ

ሄደህ ለማስታወቂያ የሚሆን ፎቶ አታነሳም

ዳንኤል

አይ እዚህ በጣም ብዙ ስራ አለብኝ

መሳፍንት ተናዶ ያየዋል ….. ዳንኤል ሳቅ

ሲን 12

ውስት እነ ዳንኤል ምኝታ ቤት ማታ

ቤቱ ዝግ ነበር ዳንኤል ከፍቶት ገባ ስልክ እያወራ ነው

ዳንኤል

አሁንስ የት ገባችው

ሄለን

ኬንያ ገብተናል ምን አልባት ከዚ በዋላ ሰልክ ለማግኘት ስለምቸገር

ባልደውል እነኩዋን አትጨነቅ

ዳነኤል አለጋው ጫፍ ሂዶ ኩጭ አለ

ሄለን

በጣም ከተጨነክ ደላላው ጋር ደውልለት

ዳነኤል

ብቻ ላለመቆየት ሞክሪ እሺ

11
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሄለን

እሺ ግን እስካሁን ሁሉም ሰላም ነው አትጨነቁ

ዳነኤል

እሺ እወድሻለው

ሄለን

እኔም እወድሃለው ደና እደር

ዳንኤል

ደና እደሪ

ዳነኤል ስልኩን ዘጋው ከዘጋው በዋላ በረጅሙ ተነፈሰ

ሲን 13

ውስጥ የአበበች ቤት ጠዋት

አበበች ከጸሎት ቦታው ላይ ጸልየው ሲነሱ እናያለን ከተነሱ በዋላ ልክ ሊወጡሲሉ ዳነኤል ገባ ደነገጠች

አበበች

ምነው ቆየሁብህ እንዲ

ዳነአል

(እየተቀመጠ)

አረ ዛሬ እኔ ልምጣ ብዬ ነው

አበበች

እሺ ከዚ በዋላ ግን እኔ እመጣለው እንጂ አነተ እዚ ድረስ እንዳትለፋ

ዳነኤል

እሺ

ወድያውን ተነስታ ማብሰል ጀመረች

( የተለያዩ ሰዎች ግርግር ይታያል ጸሃይ ስጠልቅ ይታያል የጥዋት ግርግር እናያለን ዳንኤል
ፎቶ ሲያነሳ እናያለን ጨረቃ በደመና ውስት ሁና ስትርመሰመስ እናያለን )
ሲን 14

ውስጥ የመሳፍት ቤት ማታ

መሳፍንት እና ዳንኤል ጠረቤዛ ዙሪያ ተቀምጠው እራት እየበሉ ነው ዳነኤል ቲንሽ የመጨነቅ ስሜት
ይነበብበታል

መሳፍንት

ቆይ ሁልት ሳምንት ሙሉ አልደወለችም ?

ዳንኤል

12
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

( በጭንቀት )

አዎ ብዛ ላይ የደላላው ሲልክ እራሱ ዝግ ነው ቢያንስ የሱ ክፍት ሊሆን ይገባ ነበር

መሳፍንት

ለማንኛውም ተረጋጋ ያን ያህል የክፋ ነገር አይፈጠርም ትደውልልህ ይሆናል

ዳንኤል ሲያየው ከቆየ በዋላ በእሺታ እራሱን ወዘወዘ ሁለቱም መመገብ ጀመሩ

ሲን 15 ሲን 14 ቢ
ውጪ መንገድ ላይ ለሊት
ሄለን እና ዳንኤል አልጋ ውስጥ ተኝተዋል ፡፡ አንሶላው በጣም ሰፊ እና ነጭ ነው ፡፡ አልጋው ውስጥ
ናቸው የለሊት ቀንድ አውጣ እና ሊሎች ድምጾች ይሰማሉ ፡፡ ድምጾቹ ብዞም ባልተጋነነ ሁኔታ ነው
እሚሰሙት፡፡ ሄለን እና ዳንኤል አልጋው ውስጥ ሁነው እያወሩ ነው ፡፡ ምንጩ ኬት እንደሆነ
የማይታወቅ ብርሀን ወደ ውስጥ እየገባ ነው፡፡ሄለን እና ዳንኤል በስስት እየተያዩ ነው፡፡
ዳንኤል

/በስስት አኗን አያያት/


በቃ በጣም ነው የናፈቅሽኝ ... አላቅም ብቻ ቶሎ እንድትመጪ እፈልጋለው
ሄለን

/በስስት እያየችው/
እኔም በጣም ናፍቀከኛል ... ስመጣ ምን ታረግልኛለህ ?
ዳንኤል

አገባሻላው ... እምናፍቀው እሱን ነው...

ሌላ አለም የለኝም እሱ ነው ህልሜ ... ግን መቼ ነው እምትመጪው?


ሄለን

/ ደንግጣ ወዲያውኑ አየችው/


እ ... እኒኮ .... ምንም አላውቅም...
ዳንኤል

/በሁኒታዋ ደንግጦ/
ማለት ... ቆይ ምን ሁነሻል?
ዝም ብላ አየችው ፡፡ ግራ በመጋባት ሁኔታ አያት፡፡ ከአንሶላው ውስጥ ደመና እሚመስል ጪስ መግት
ጀመረ፡፡

/ሊላ አተያይ/

13
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

የተኙበት አልጋ መሃል አስፓልት ላይ ተቀምጧል፡፡ የተረጋጋ እና አስፓልቱ ላይ የተንሳፈፈ ደመና


አልጋውን ውጦታል ፡፡ እጅግ በጣም ይጨንቃል ፡፡ የተለያዩ የለሊት ድምጾች በደንብ ይሰማሉ ፡፡
ከኣካባቢው ሁኔታ ጭር ያለ መሆኑን እንረዳለን፡፡

/ሊላ አተያይ አልጋ ውስጥ/


አንሶላው ውስጥ የሚገባው ደመና በጣም ጨምሯል ፡፡ ውስጡ በደመና እየተሞላ ነው፡፡ ዳንኤል በጣም
ጨነቀው ፡፡ ሄለን በፍጹም ዝምታ አይን አይኑን እያየችው ነው፡፡
ዳንኤል በጣም በተጨነቀ ሁኔታ ደመናውን አይቶት መልሶ ወደ ሄለን ዞር ሲል አጠገቡ የለችም ፡፡
ደነገጠ ወዲያውኑ አንሶላውን ለመግፈፍ ሞከረ እምቢ አለው፡፡ እየተወራጨ አንሶላውን ለመግፈፍ
እየታገለ ነው ፡፡ ድመናው ወደ አልጋው ውስጥ በጣም ገባ ዳንኤል ፡፡ ተጨነቀበውጥረት ውስጥ ሁኖ
ዕየተወራጨ ነው፡፡

/ሌላ አተያይ ከውጪ/


ደመናው በንፋስ ትርምስምስ እያለ እናያልን ፡፡ የመብረቅ ድምጽ ይሰማል ፡፡ ዳንኤል አንሶላው ውስጥ
ሁኖ ከአንሶላው ውስጥ ለመውጣት ሲታገል እናያለን፡፡ በመጨነቅ ስሜት ውስጥ ሁኖ አንሶላውን ገፎ
ብድግ ብሎ አልጋው ላይ ቁጭ አለ ፡፡ አካባቢውን ብውጥረት ስሚት ውስጥ ሁኖ አየው፡፡ ወደሱ ፊት
ላይ የተወሰነ ብርሃን አረፈ፡፡ ብርሃኑ ዕየቀረበ እና ፊቱ ላይ እየሰፋ ነው፡፡ ብርሃኑ ወደመጣበት ዐካባቢ
ዞረ ሲል፡፡ሄለን ጀርባዋን ሰታው እየሄደች ነው ፡፡ በእጇ የተለኮሰ መቅርዝ ይዛለች ፡፡ የመቅረዙ ብርሃን
በሃይለኛ ንፋስ እየተርገበገበ ነው፡፡ ሄለን ያረገችው እረጅም ቀሚስ በንፋስ እየተርገበገበ ነው፡፡ ወደሷ
በረጅሙ ያበራ ከባደ መኪና እየመጣ ነው፡፡ በረጅሙ የማይቋረጥ ክላክስ እያሰማ ነው፡፡ዳንኤል በረጅሙ
በመጮህ እጁን ሲዘረጋ አንሶላው እየተቦጫጨቀ በንፋስ ሲሄድ እናያለን

ሲን 14 ሲ

ውስጥ ዳንኤል መኝታ ቤት ለሊት

ዳንኤል አንሶላ ውስጥ ሁኖ እኛ ከላይ እናይዋለን፡፡ ሲኑ እንደጀመረ ዳነኤል ሁለት እጆቹን አውጥቶ
ፊቱ ላይ የነበረውን አንሶላ ገፈፈው ፡፡ ፊቱ ላይ ሙልት ያለ ላብ እና ጭንቀት ይታያል ፡፡ ቶሎ ቶሎ
በሃይል እየተነፈሰ ነው፡፡ በጭንቀት ውስጥ ሁኖ ቤቱን አየው፡፡

ሲን 15

ውስጥ ዳንኤል ቤት ማታ

ቤቱ ውስጥ ቴሌቭዥን ተከፍቱዋል ዜና እየታየ ነው የራቀ የሻወር ቤት ድምጽ እንስማለን


ድምጹብዙም ሳይቆይ ቆመ ዳንኤል ከሻወር ቤቱ የሻወር ቤት ልብስ አርጎ ወጣ ዜና እየታየ
ነው

ዜና

ሰበር ዜና ዛሬ ቀን የኢትዮፒያና የተወሰኑ የአፍሪካ ሃገር ስደተኞች በሰሜን አፍሪካ


ሽፍቶች ተገለው መገኘታቸውን የውጪ ሚዲያዎች ዘግበዋል

ዳነኤል ደንግጦ ማየት ጀመረ

ዜና

ስደተኞችን በማመላለስ የሚታወቁት ሰዎችም በሽፍቶቹ የተገደሉ

14
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሲሆን ከነሱ መሃል የተረፈው አንድ ደላላ ሶስት ሴቶችን አፍነው

እነደወሰዱዋቸው ቢናገርም እሱም በደረሰበት ጉዳተ መሞቱ ተነግሩዋል

የተቀሩት አስክሬኖች አካላቸው ተወስዶ ሙተው ተገኝተዋል

ዳንኤል በፍጹም ድነጋጤ ውስጥ ሁኖ ዜናውን እያየ ንው ፊቱ ላይ የመረበሽ ስሜት ይነበባል

ዜና

መንግስተ በዜጎቻችን ላይ በደረሰው አደጋ የተስማውን

ሀዘን ገልጾ በነገው በሰሞኑን ሃገር ውስጥ የሚገቡትን አስክሬኖች

መተው እነዲረከቡ ሲል በክፍተኛ ሃዘን ይገልጻል

ዳንኤል ደንግጦ ፈዞ እያዬ በነበረበት ስሜት እንባ አይኑ ላይ ሙልት አለ የቤቱ ስልክ
እየጮከ ነው ዳንኤል በፍጹም ድነጋጤ ዝም ብሏል

ሲን 16

ውስጥ ሚኒልክ ሆስፒታል ቀን

አበበች እያለቀሰች ነው በሰዎች እየተጎተተች ወጣች ክፍሉ ውስጥ አንደ እሬሳ ክፍል እና
ዳነኤለ አሉ በሶስት ቦታ ላይ ሶስት አስክሬኖች ፊታቸው ተሸፍኖ እናያለን ዳንኤል ዝም ብሎ
ሶስቱንም አስክሬኖች አያቸው

እሬሳ ክፍሉ

ካየሃቸው አስክሬኖች ውጪ ሴቶች እነዚ ብቻ ናቸው ማየት ትችላልህ

ዳንኤል በዝግታ ወደ አስክሬኖቹ ዝቅ ብሎ እጁን ወደ አንዲት አስክሬን ላክው ቀስ ብሎ


ፊቱዋ ላይ ያለውን ጨርቅ አነሳው እሱዋ አይደለችም ደነገጠ ሸፈናት ሁለተኛዋነ በጣም
በተረበሸ ስሜት ገለጣት አሱዋ እይደለችም ወደ ሶስተኛዋ ጠጋ አለ ሳይከፍተው ዝም አለ
ፍጹም የሃዘን ስሜት ውስጥ ነው በዝግታ እጁን ወደ ጨርቁ ላከው ፊቱ ላይ እጅግ በጣም
መረበሽ ይታያል ሶስትኛዋን ፊቱዋን ሳናይ ሲኑ በዳንኤል ፍጹም ጭንቀት ያልቃል

ሲን 17

ውስጥ ሆሰፒታል ኮሊድር ቀን

የተለያ ሰዎች ዳር ዳር ይዘው እያለቀሱ ነው የሄለን እናት እያለቀሱ ነው ዳንኤል


የአሰክሬኑን ቤት ከፍቶ ወጣ በዝምታ ውሰጥ ሁኖ እያለቀሰ ነው የወጣው አንገቱን ደፍቶ
እያለቀሰ ሲሄድ አበበች አየችው ከሁኔታው በተረዳችው ስሜት እየጮህች አለቀሰች
ሔለን

ሲን 18

ውስጥ የእናት ቤት ቀን

15
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ቤቱ ውስጥ ውስን የሀዘን ነጠላ እና ጋቢ የለበሱ ሰዎች እናያለን፡፡ ከሰኮንዶች በኋ ዳንኤል በሩን ከፍቶ ገባ
ሁሉም እሱን እያዩት ነው፡፡ በንዴት እና በቁጣ አፍጦ አያቸው አሁንም እያዩት ነው በጣም በተበሳጨ
ስሜት ወደ ጎዳ ገባ

ሲን 19

ውስጥ ጎዳ ቀን

የሂለን እናት በጣም ባዘነ ስሜት ፊታቸው ተቧጭሮ አይናቸው ቀልቶ ጉንጫቸው ላይ የደረቀ እንባ
እየታየ በጣም በሚያሳዝን የሀዘን ስሜት ውስጥ ሁነው ቁጭ ብለዋል፡፡ ሴት የሄለን እናትን ፀጉር እየላጨች
እናያታለን፡፡ ዳንኤል ገባ እናትን አያት አዘን በዝግታ ብሄደ በኋን ከአጠገቧ ቁጭ ብል ሁሉም ዝም ብለው
ስትንጭ የሚሰማው የመንጨት ድምፅ ብቻ ነው የሚታየው ዝምታው እናት የእናት ሀዘን ያስፈራል

ዳንኤል
/ከዝምታ በኋላ/
ሔለንን ቀብረሻታል
ዳንኤል
/ቀና ብሎ እናትን እያያት/
ቀብረሻታል ወይ?
ፀጉር የምትላጭዋ ሴት

ይቅርታ ወንድሜ … እሷ ከዛ ሁሉ ሰው ተለይታ አተርፍም ይልቅ ቶሎ ሀዘኑ

እንዲረሳ ማዘንም ካለባችው አሁን ነው

ዳንኤል
/ከተቀመጠበት በቁጣ እየተነሳ/
ተነሽ!!! ውጪ እዚ ….ምንም አይነት ሀዘን የለም… አልሞተችም፡፡
በንዴት እየተናገረ እንባው ወረደ … ፀጉር የምትንጭዋ ሴት በድንጋጤ ወጣች

ዳንኤል
/በጭሆት እየተከተላት/
አልሞተችም… አልሞተችም
ሲን 20 a ውስጥ የእናት ቤት ሳሎን ቀን

ፀጉር የምትላጭዋ ሴት በድንጋጤ እየሮጠች ወጣች፡፡ ሳሎን የነበሩት በድንጋጤ እያዩት ነው ዳንኤል በእልህ
እያለቀሰ ወደ ሳሎን ገባ

ዳንኤል
/ሁሉንም እያየ እየጮኸና እያለቀሰ/
እዜ ቤት ሀዘን የለም… ሄዱ ከዚ
ሁሉም በድንጋጤ ከተቀመጡበት በተራ በተራ ተነሱ … ሁሉም ወጡ ዳንኤል እያለቀሰ ወንበር ላይ ቁጭ አለ፡፡
ቀና ብሎ ሲያይ በእሱ እይታ የሂለንን ፎቶ በሀዘን መግለቻ ተሰርቶ በፍሬም ተደርጎ እንያዋለን ስቅ ስቅ ብሎ
አለቀሰ… ተስፋ በመቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ እናየዋለን

ሲን 21

ውስጥ የዳንኤል መኝታ ቤት ማታ

መኝታ ቤቱ ውስጥ ከውጪ የሚገባው የጨረታ ብርሀን እና የራስጌ መብራት ብቻ ነው የሚታየው ዳንኤል ብርድ
ልብስ ውስጥ ሆኖ እናያለን፡፡ ፊቱን ሳይሆን ከላይ ተሸፋፍኖ ነው የምናየው በጣም የሀዘን ለቅሶ እና ሲቃ እንሰማለን ሲቃው እረጅም
ሰኮንዶች ይቆያል

ሲን 22 ውጪ መንገድ ላይ ቀን

16
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ዳንኤል ተስፋ በቆረጠ ስሜት መንገዱ አሻገር መኪኖቹ እስኪያልፉ እየጠበቀ ነው፡፡ ብዙ መኪኖች እያለፉ እናያለን፡፡ ከመንገዱ
ማዶ ብዙ ሰዎች እየተገፋፉ እናያለን ሔለንን የላካት ደላላ ካፓርት ለብሶ ኮፍያ አድርጎ ሲያልፍ እናያለን፡፡ ቀና ሲል ዳንኤል
ደላላውን አየው ደነገጠ በፍጥነት መኪኖቹ ተሻግረው ሳያልቁ መንገዱን ማቋረጥ ጀመረ ውስን መኪኖች ፍሬን ያዘ በዳንኤል ሁኔታ
በተወሰኑ ሰዎች ግራ ተጋብተው ዞር ዞር ብለው አዩት ….. ደላላው ዞር ብሎ እየሄደ ሲመለከት ዳንኤል ወደ እሱ እየመጣ ነው፡፡
በፍጥነት ወደ ፊት መሮጥ ጀመረ ዳንኤል ተከተለው ሁለቱም በሰዎች መሀል በሃይል ሲሮጡ ይታያሉ

ዳንኤል

/እየሮጠ በጭሆት/

ቁም … ቁም
ደላላው በጣም እየሮጠ ነው የተወሰነ መንገድ ከሮጡ በኋላ ከደላላው ፊት የሆነች ታርጋ የሊላት መኪና በፍጥነት ተነድታ ቆመች…
በሩ ተከፈተ … ደላላው በፍጥነት ገባ፡፡ መኪናዋ ተነዳች ዳንኤል መኪናዋን ተከተላት… መኪናዋ እርቃ ሄደች ተስፋ በመቁረት አይነት
ስሜት ቆመ ተናደደ

ሲን 22 ውስጥ ሬስቶራንት ማታ

ሬስቶራንቱ ውስጥ የተወሰኑ ሰዎች እየተመገቡ እናያለን ዳንኤል እና የዳንኤል ጎደኛው ቁጭ ብለዋል፡፡ የዳንኤል ፊት ላይ እና
የጎደኛው ፊት ላይ ምግብ እናያለን፡፡ ዳንኤል ዝም ብሎ እያሰበ እናያለን ጎደኛው ሊበላ ያለውን ምግብ አቁሞ ሶፋ ላይ ከደረሰ በኋላ
መለሰው በረጅሙ ተነፈሰ

ጎደኛ

/ዳንኤልን እያየው/

እባክህ … ቢያንስ እራስህ


አታስጨንቅ ያለውን ነገር ለመርሳት ሞክር
ዳንኤል

/በዝግታ ቀና ብሎ ካየው በኋላ/

እንዴት እረሳዋለው …ትኑር ትሙት አላውቅም

‹ ዳንኤል በጣም የመከፋት ስሜት ይታይበታል›

ዳንኤል

/በጣም በተከፋ ስሜት/

በጣም አፈቅራታለው … በጣም


ጎደኛ

/በተረበሸ ስሜት/

አውቃለው ለእሷ ያለህን ፍቅር … ግን ብጠፋም ፈልገህ አታገኛትም … ብትሞትም


አትመልሳትም
ዳንኤል
/እንባ አያኑ ላይ እየቀረረ/
አዎ… ትክክል ነህ …. ግን እጠብቃታለው ካለ እሷ መኖር አልችልም … አይደለም
እረስቻት ደስተኛ ልሆን ቀርቶ… ልተኛ እንኳን አልችልም…
ጎደኛ

እሺ …. ስለ እሷ መጨረሻዋን እስክናውቅ … ቢያንስ ቢያንስ ምግብ በደንብ

ብላ እራስህን ተንከባከብ

17
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ዳንኤል

/እያለቀሰ እያየው/

እንዴት ብዬ… በሄወት ካለች እኮ ትብላ ይራባት ምንም አላውቅም … እኔ ስበላ እሷ


እዛ እየራባት ቢሆንስ … እንዴት ብዬ ልብላ? ንገረኝ…

ጎደኛ

እሺ አንድ ስራ እንስራ የደላላው ቁጥር እስከ መጨረሻው ድረስ ዝግ ቢሆነ ቴሌ ጎደኛ አለኝ ሲም ካርዱ ያወጣበትን
አድራሻ ይነግረናል ያኔ ቤቱ ድረስ ሄደን ያሉትን ነገሮች እናጣራለን … እስከዛ ራስህን አረጋጋ

ዳንኤል በዝምታ ከቆየ በኋላ እንባውን ጠርጎ ራሱን ወዘወዘ

ሲን 23

ውስጥ የእነ ዳንኤል ቤት ማታ


ቤቱን ደብዝዝ ባለ ብርሀን እናየዋለን የበሩት ኮርነር ላያቶች ብቻ
ናቸው… ጠረጴዛ ላይ ምግቦች ተደርድረዋል የሄለን እናት ጥቁር ልብስ ለብሳ በጣም በተከፋ ስሜት የእራት
ጠረጴዛው አጠገብ ካለ ወንበር ላይ ቁጭ ብላለች፡፡ ፀጉሩዋ የተላጨ ነው፡፡ እላዩ ላይ ስስ የሀዘን ጥቁር ሻሽ
አርጋለች፡፡ በጣም ዝም ባለ ስሜት ወደ በሩ እያየች እናያለን፡፡ የግድግዳ ሰዓቱ 5 ሰዓት ይላል፡፡ ከሰኮንዶች በኋላ ከውጪ
በክብር ስሜት የዳንኤል ድምፅ ይሰማል

ዳንኤል 0/5

/በጭሆት እና በስካር ስሜት/

ጠጣሁኝ እንዳትቀየሚኝ … ሰክሬ ስለመጣው እንዳትቀየሚኝ.. ሒንዬ… ሰከርኩኝ

እኮ እናት የሀዘን ስሜት ውስጥ ሁና ወደ በሩ እያየች ነው፡፡ በሩ ተከፈተ ዳንኤል ወደ ውስስ ገባ፡፡ በሩን ከፍቶ
ዝም ብሎ ቆመ፡፡ እናትን አያት …. ዝም አለ፡፡

እናት

/በጣም በተሰበረ ስሜት/

ቁጭ በል

(ዳንኤል እየተንገዳገደ ወደ መቀመጫው ሄዶ ተቀመጠ፡፡)

ዳንኤል

/በስካር ስሜት እያዘነ/

በላሁኝ … በደንብ አድርጌ በላሁኝ


እስክሰክር ጠጣሁኝ … በምግብና በመጠጥ እሷ ልትረሳ … ሆዴን ሞልቼ ከአምሮዬ ሔለንዬን
ላስወጣት ፈልጌ በላሁኝ እዚም እበላለው … በደንብ አድርጌ እበላለው

እናት ዝም ብላ በሀዘን ስሜት አየችው ዳንኤል ሰሀን ላይ ምግብ አድርጎ በስካር ስሜት መብላት ጀመረ.. እናት
አለቀሰች
ዳንኤል

/እየጎረሰ በስካር ስሜት/

እበላለው …. ከምወዳት ህይወቷን ሙሉ ልትስጠኝ ከተዘጋጀችው ሴት በላይ

18
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ይሄ ምግብ ይበልጥብኛል አያደለም እንዴ እማዬ


ቀና ብላ… እናት እያለቀሰች ነው… ዳንኤል እየብላ ቀናብሎ እያያት
ዳንኤል

/በስር ስሜት ውስጥ እንዳለ እያዘነ/

ለምን ታለቅሽያለሽ… አንተዋት … ዝም ብለን እንርሳት …. እናቴ መርሳት ታውቂያለሽ

እኔ ብዙ ሰዎችን እረስቺያለው …እሷንም እንርሳት…

አለቀሰ … እናት ዝም ብላ … ቁጭ እንዳለች እያለቀሰች ነው ዳንኤል ….ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ መኝታ ቤት


እየሄደ ነው

ዳንኤል

/ወደ መኝታ ቤት እየሄደ/

እንርሳት … እሚሻለን በሆዳችን እና በኑራችን ብንለውጣት ነው የሚሻለን …


እናት በተከፋ ስሜት ውስጥ ሆና እያለቀሰች እያየችው ነው ከተቀመጠችበት ተነሳች ወደ መኝታ ቤቱ ሄደች፡፡

ሲን 24 ውስጥ የዳንኤል መኝታ ቤቱ በር/ኮሌደሩ ጋር/ ማታ

እናት ወደ መኝታ ቤቱ በር ስትሄድ እናያታለን፡፡ ከዳንኤል መኝታ ቤቱ ውስጥ የለቅሶ ድምፅ እንሰማለን፡፡ በተሰበረ
ስሜት ቆመች

ዳንኤል 0/5

/በጣም በሚያሳዝን ስሜት/

እሺ ቆይ እንዴት ብዬ ልርሳሽ …. ናፍቀሽኛል እየጠበኩሽ እኮ ነው …

ሁሌም ወደ ቤት ስገባ የማገኝሽ ይመስለኛል፡፡


ስቅስቅ ብሎ ሲያለቅስ እንሰማለን … እናት በጣም በተረበሸ ስሜት ሀዘኗን መቆጣጠር ከብዷት ከቤቱ ስትወጣ
እናያለን

ሲን 25

ውጪ የደላላው ቤትግቢ ቀን
የደላላው ቤት ግቢ በር እየተንኳኳ ነው፡፡ በሩን ልትከፍት የደላላው ሚስት ስትሄድ እናያለን፡፡ በሩን ከፍተችው ግራ
በመጋባት አየች፡፡ ዳንኤል እና ጎደኛው ቁመዋል፡፡

ጎደኛው

/ብህትና/

ሰላም ነሽ?

ሚስት

ደህና … ማን ልበል?

ጎደኛ

የሳምሶን ቤት ነው?

19
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሚስት

/በሩን እየዘጋችው በጥርጣሪ/

አያደለም
ዳንኤል በሩን ይዞት ቀመ … በጣም ተናዷል … ሽጉጥ አወጣ
ዳንኤል

/በንዴት ሽጉጡን ደቅኖበት/

እየሁልሽ የሱ ቤትያሂ እንደሆነ አውቃለው እሱን ካላገናኘሽን እደፋሻለው አቀባበለው፡፡ ጎደኛው ደነገጠ፡፡
የደላላው ሚስት በፍርሀት ወደ ቤቱ በር ሄደች ዳንኤል በቀረቦት ተጠግቷት ሽጉጡን እንደደቀነበት ተከተላት

ሲን 26

ውስጥ የደላላው ቤት
ዳንኤል የደላላው ሚስት ላይ ሽጉጡን እንደደቀነ ሦስቱም ተከታትለውገቡ፡፡ ደላላው ከመኝታ ቤቱ ውስጥ
በድንጋጤ ወጣ፡፡ የዳንኤል ጎደኛ ግራ በመጋባት ውስጥ ነው፡፡ ቤቱ ውስጥ ያሉ ጠረጴዛ ዙሪያ የተደረደሩ ወንበሮች
እናያለን
ዳንኤል

/በጣም በንዴት ስሜት ደላላውን እያየው/

ሚስቴን የትም ጥለህ የምትሸሸግ መሰሎሀል


ደላላው

/በድንጋጤ እጁን ወደ ላይ እንዳደረገ/

በሁሉም ነገር አንተ እንደምታስበው ተጠያቂው እኔ አይደለሁም


ዳንኤል

/በጣም በሽቶ ሽጉጡን እንደደቀነ/

ሁለታችውም ወንበሩ ላይ ቁጭ በሉ
ደላላውና ሚስቱ በጣም በተደናገጠ ሁኔታ ክቡ ጠረጴዛ ዙሪያ ካሉ ሁለት ወንበሮች ዙሪያ ቁጭ አሉ፡፡
የዳንኤል ጉዋደኛ ግራ በመጋባት አይነት ስሜት ዳንኤል አየው

ጎደኛው

/ጨምቆት ዳንኤል እያየው/

እየውልህ ተረጋጋ እንደዚ እይደለም


ዳንኤል

/በጣም በሽቆ እያየው/

አያገባህም … ከዚ በኋላ የኔ ስራ ነው
ዳንኤል ሽጉጡን ወደ ደላላው ወስዶ በእጀታው ግንባሩን መታው ደላላው ደማ የደላላው ሚስት
ጮኸት፡፡

20
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ዳንኤል

/ከደላላው ጀርባ እንደላ ሽጉጡን ደቅኖበት/

ዝም በይ
የደላላው ሚስት እየተርበታች ዝም አለች ደላላው እየደማ ነው ደላላው ፊቱን አልቦታል…በጣም በጭንቀት
ውስጥ ነው ያለው

ዳንኤል

/መልስ ደላላው ላይ ሽጉጡን ደቅኖ/

እመነኝ ስለ ሚስቴ እውነቱን ካልነገርከኝ እገልሀለው … ሁሉንም ነገር በግልፅ ንገረኝ


ደላላው

/በጭንቀት ውስጥ ሆኖ/

እውነት ስለ ሄለን የማወቅ መረጃ የለኝም … እኔ ይሄንን ስራ ስሰራ እንደዚ


ሰዎች ሙተውብኝ አያቅም … ሆን ብዬ ያደረኩት
ዳንኤል

/ንግግሩን አቋርጦት በጭሆት እና በንዴት/

.. አያገባኝም እኔ የሚያገባኝ የሄለን መጨረሻ ነው እሱን ንገረኝ …

ካልነገርከኝ አንተንም ሚስትህንም ገድያችው ነው የሚሄደው…ንገረኝ … ንገረኝ


ሸጉጡን የደላላው ግንባር ላይ በደንብ አጥብቆ እየደቀነው ነው፡፡ ጎደኛው በጭንቀት እየተቁነጠነጠ ዳንኤልን አየው
ደላላው

/እየተርበተበተ በጭሆት/

እሺ ቆይ ምን ልንገርህ … ምንድን ነው አርግ የምትለኝ…


ዳንኤል

/ፊቱ በንዴት ውስጥ ሆኖ እየጮኸ/

ንገረኝ ….

ሽጉጡን ከደላላው አናት ላይ አንስቶ ትከሻው ላይ ተኮሰበት፡፡የደላላው ትከሻ በጥይት የተመታበት ቦታ


መድማት ጀመረ፡፡የደላላው ሚስት … በምሬት እያለቀሰች ነውከተቀመጠችበት ተነስታ ልትይዘው ስትል በጥፊ መቶ
ጣላት፡፡ወደቀች፡፡
ጎደኛው

/በንዴት ሄዶ ያዘው/

ምን እየሆንክ ነው!!! ሰው ልገል ነው እንዴ የመጣህው ወይ በሰርአቱ

ጠይቃቸው ወይ እንሂድ
ዝቅ ብሎ የወደቀችውን የደላላውን ሚስት አንስቷት ወንበሯ ላይ አስቀመጣት
ዳንኤል

/እያፈጠጠች በሽቆ/

21
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

በሔለን የመጣብኝን ሰው ከመግደል ወደኋላ አልልም … ስለዚ ዝም በል

ጎደኛው ዞር ብሎ በአጋጣሚ ሲሚለከት ከመኝታ ቤቱ አንድ ህፃን ልጅ ከእንቅልፉ እንደተነሳ የሚያስታውቅ ልጅ ቁሟል.. የዳንኤል
ጓደኛ በፍጥነት ወደ ህፃኑ ሄዶ መኝታ ቤቱ ውስጥ አስገባው … ካስገባው በኋላ አልወጣም

ዳንኤል

/ደላላውን እያየው/

ትዕግስቴ አልቋል እውነቱን ንገረኝ


ደላላው

/በተደከመ ስሜት/

አንድ ነገር ብቻ ተረዳኝ … ቤተሰቦቼን ተዋቸው አእኔ ግን እንደፈለክ


ብታረገኝ ይገባኛል … እውነቱን ብነግርህ እንደምታገለኝ አውቃለው …
ዳንኤል

/እንደ መረጋጋት ብሎ/

መስማት የምፈልገው እውነቱን ነው


ደላላው

/በተዳከመ ስሜት/

ሽፍቶቹ ሁሉም ጨካኞች እና ለአንድ ብር ሲሉ የሰው ነብስ የሚያጠፉ ናቸው …በዛ ላይ የስደተኞቹን
አካል በመሸኘም ይጠቀማሉ እመነኝ ደላሎቹ ሁሉ ሳይቀሩ ሙተዋል የተረፈ ሰው የለም

ዳንኤል

/በተረበሸ ስሜት ሽጉጡን እንደደቀነ/

ስለዚ ሄለን ሙታለች


ደላላው

/ከዝምታ በኋላ/

አስክሬኗ ስላልተገኘ እንጂ እንደ ማተረፍ እርግጠኛ ነኝ


ዳንኤል ዝም አለ፡፡ ሽጉጡን አሁንም እሱ ላይ እንደደቀነበት ነው ፊቱ እየተለዋወጠ እየበሸቀ … እየተናደደ እንባ እየተናነቀው
የሽጉጡን እጀታ አጥብቆ ያዘ

ዳንኤል

/በጣም በተረባበሸ ስሜት/

ሚስቴን አሳጣኸኝ አይደለ


ደላላው

/በጭንቀት ስሜት/

እባክህ ተረጋጋ …
ዳንኤል

/እየጮኸ ሽጉጡን ወደ ደላው ሚስት ደቀነ/

22
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

አልረጋጋም
ወደ ሚስቱ ደቅኖ ቃታውን ሳበው ጥይት ተተኮሰ … ድጋሚ ተኮሰ ደጋግሞ ተኩሶ … ደላላው
በድንጋጤ ቁጭ እንዳለ ነው የደላላው ፊት ላይ እንባ ሲቀር እናያለን፡፡ የዳንኤል ጎደኛ በድንጋጤ ከመኝታ ቤቱ እየሮጠ ሲወጣ
እናያለን … ከተተኮሰበት በኋላ የደላላውን ሚስት አናያትም … ዳንኤል በእልህ ፊቱ እየተለዋወጠ እናየዋለን … እንባ ካይኑ ወጣ፡፡
ሽጉጡን ዝቅ ካደረገው … ደላላው አለቀሰ … የዳንኤል ጎደኛው በድንጋጤ ዳንኤልን ደገፈው … ዳንኤል ተንገዳገደ፡፡ደላላው ሚስቱን
አንባ አያት እየፈሰሰ በድንጋጤ እያያት ነው፡፡ በእሱ እይታ ሚስቱን ስናያት ፍጹም ድንጋጤ በተሞላበት ሁኔታ ቁጭ ብላለች በጥይት
አልተመታችም የተቀመጠችበት ወንበር በአንድ በኩል ብትንትኑ ወቷል ዳንኤል እያለቀሰ እየተንገዳገደ ከቤቱ ወጣ … ጎደኛው
ተከትሎት ወጣ

ሲን 27

ውስጥ የሄለን እናት ቤት ቀን

የሄለን እናት በጣም በተሰበረ ፒስታል በእጇ ይዛለች … የሄለንን ፎቶ በግድግዳው ላይ እያየች አለቀሰች… ወደ ቤቱ
ውስጥ ዳንኤል ገባ፡፡ እናትን አያት ሄዶ እንባዋን ጠረገላት

ዳንኤል

/በፒስታል የያዘችውን ልብስ እያየ/

በፒስታል የያሽው ልብስ ምንድን ነው?

እናት

/በተሰበረ ስሜት/

የልጄን ሰርግ አለሟን አይቼ ወደ እግዚአብሔር ቤት የመግባትፍላጎት ነበረኝ…


አሁን ግን አጥቺያት ገዳም ልገባ ነው… በዚ አለም ላይ ብዙ ያጣሁት
ነገር አለ … ግን እሷን ያጣሁበት ቀን ለኔ ሞቴ ነው፡፡ ካለ እሷ የመኖር ፍላጎት የለኝም
በኔ አቅም እሚሆን ነገር ስለሌለ… ካለችም በሰላም እንዳትኖር… ከሞተችም ነብሷን
በገነት እንዲያኖርልኝ እፀልያለው…
ዳንኤል ዝም አለ … እናት አቀፈችው

/ከወራት በኋላ/

ሲን 28

ውጪ እነ ዳንኤል ግቢ ማታ

ሰማዩ ላይ ብዙ ደመና እናያልን ደመናው ጥቁር ነው ጨረቃ በደመና ውስጥ ተሸፍናለች … ዳንኤል ተኝቶ ወደ ሰማይ እያየ ነው

ዳንኤል V/o

ዛሬ ከተለየችን ብዙ ወራት ሆናት… እሷ ተሸፍና ቀርታለች እንደ ማትመለስ ይሰማኛል


ከደመና በላይ ተሸሽጋለች … ለብዙ ሰዎች ሂወት መለወጥ ተሰዶ ያልተመለሰች ብርሀን ነች… እኔ ብላ እሷ
መኖር ብችልም ልረሳት ግን አልችልም

23
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሰማዩን እያየ ነው

ሲን 29

ውስጥ የዳንኤል ጎደኛው ቢሮ ቀን


ዳንኤልና ጎደኛው ውል ሲፈራረሙ ይታያል የተወሰኑ የድርጅቱ ሰራተኞች እናያለን፡፡ ዳንኤልና
ጎደኛው ተፈራርመው ተጨባበጡ
ጎደኛው

/በፈገግታ ዳንኤልን እያየው/

አቶ ዳንኤል አብረንህ በምስረታችን በጣም ደስተኛ ነን …


ዳንኤል

/በስስ ፈገግታ/

እኔም …
በድጋሚ አጨበጨቡ

ሲን 30

ውስጥ የክፍለ ሀገር መንገድ ቀን


የሆነች ላንድ ክሮዘር መኪና እየተናደች እናያለን ዳንኤል መኪናዋን እየነዳት እናያለን የገጠር

ሲን 31

ውጪ … መንገድ ቀን /ሽሺንዳ ውሽ ሽያ/

በአካባቢው ጥቅጥቅ ያለ ደን እናያለን ደኖቹ መሀል ብዙ ዘንባባዎች እናያለን አንድ ወጣት

እያለከለከ እየሮጠ ነው፡፡ በጣም በተደካመ ስሜት ውስጥ ነው እየሮጠ ያለው ከኋላውሰው መሆን 140 /

እየሮጠ እየተከተለው ነው፡፡ በእጁ መሳሪያ ይዟል፡፡ ልጁ በጣም በተዳከመ ስሜት በጉልበቱ ወደቀ ሰው መሆን እየሮጠ ሄደ
ልክ እንደደረሰ ልጁን በተንበረከከበት በጫማ ጥፊ መታው ልጁ ወደ ኃላ ተዘርግቶ ወደቀ… ከአፍንጫው ደም እየፈሰሰው ነው…

ሰው መሆን

/አፍጦ እያየው/

ሁለተኛ ቀና ብላ ታያታለህ …
ልጁ

/በተደካመ ስሜት/

አይ … ይቅርታ …
ሰው መሆን

/አፍጦ እያየው/

እየውልክ በሷ የመጣብኝን ሰው እደፋዋለው… አይደለም ቀና ብለህ ልታያት ይቅርና …እሷ ባለፈችበት ቦታ


እልፋለው ብትል አልቅህም

ልጁ

24
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

በሁለተኛ ስህተት አልሰራም … የዛሬን ብቻ ማረኝ


ሰው መሆን በንዴ በሀይል በቦክስ መታው

ሲን 32

ውጪ የመኪና መንገድ ቀን /ቪቨንዳ/

የመኪና መንገዱ ዳር እና ዳር ፍጹም ተፈጥሮዋዊ ዛፎችጥቀጥቅ ባለ ሁኔታ እናያለን…

አንዳንድ ደኖች ውስጥ በዛፎቹ እና በትልልቅ ዛፎች የተሸፈኑ ደኖች እናያለን፡፡ እዝራ ጭረት(23) በእጁ እንኳዋን ደህና መጣህ
የሚለውን ቃል ተዘበራርቆ ደህና መጣህ እንኩዋን

የሚለውን ጹሁፍ አፅፎ ደረቱ ላይ ይዞታል … ፈገግ ብሎ ቁሟል… የዳንኤል መኪና


ስትመጣ እናያታለን … መኪናዋ ከአዝራ ጭረት አጠገብ ቆመች … ዳንኤል በመስኮት እዝራን ጠራው … እዝራ ወደ እሱ
ሄዶ
ዳንኤል

ሰላም … ሰው መሆን ልኮህ ነው?

እዝራ

/በፈገግታ/

አዎ… እንኳን ደህና መጣህ


ዳንኤል

/ጹሁፉን ካየው በኋላ በፈገግታ/

ጹሁፉ ግን እንደዛ እያደለም ከሚለው


እዝራ
በጣም ስለቆየህ … ደክሟቸው ቦታ ተቀያይረው ነው… አስፈቅደውኛል
ዳንኤል በስሱ ሳቀ … በሩን ከፈተለት እርቅ ጫማውን አመለቀ
ዳንኤል
እረ በናትህ መኪና ውስጥ ለመግባት ጫማ ታወልቃለህ
እዝራ
አይ እስከገባ ነው… ውስጥ አረገዋለው

( እዝራ ገብቶ በሩን ዘጋው… ዳንኤል ፈገግ አለ )

ዳንኤል

/መኪናዋን እየነዳች/

ቀልድ ትችላለህ … ለማንኛውም … የት ነው የምንሂደው .. ምራኝ

እዝራ
አይ እኔ ሙሉ ኢትዮጵያን ካልሆነ አንተን ብቻ አልመራም …
ዳንኤል ሳቀ…
እዝራ

25
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ለማንኛውም … ከባድ ሰው እንዳልመሰልህ ብዬ ነው … እዝራ ጥረቱ እባላለው


አንድ ላባቱ እናቴ እንኳን ብዙ ልጆች አሏት
ዳንኤል
ዳንኤል …

( የሆነ መታጠፊያ እናያለን ) …

እዝራ

/በእጁ ምልክቱ እያሳየው/

ወደ ግራ
ዳንኤል መኪናዋን ወደ ግራ አጥፍ ካደረጋት

ሲን 33

ውጪ የሻይ ቅጠል እርሻ አካባቢ ቀን


የሻይ ቅጠሉ እርሻ በርቀት ይታያል … እርሻው እጅግ በጣምያምራል … ሰፊና ሁሉም በአንድ አይነት
አበቃቀል የበቀሉ ናቸውስራተኞቹ የሉም … ዳንኤል እና እዝራ አንድ ዳገታማ ቦታ
ላይ ቁመው እርሻውን እያዩ ነው፡፡ ዳንኤል ተገርሟል፡፡
ዳንኤል
በጣም ደስ የሚል እና ሰፊ ነው
እዝራ
አዎ … እናተ በአንድ ብርጭቶ የምጠጡት ይሒን የሚያክል የሻይ ቅጠል እርሻን ነው
ዳንኤል በስሱ ፈገግ አለ

ሲን 34

ውስጥ የዳንኤል ከፍል ካምና ማታ


ክፍሉ በጣም የሚያምር ክፍል ነው፡፡ ሰው የለበትም በሩ ተከፈተ … ዳንኤል እና እዝራ ገቡ፡፡ ዳንኤል ክፍሉን አየው …
ዳንኤል
እሺ በጣም አመሰግናለሁ
እዝራ
በቃ ደና እደር ጠዋት እዛው እርሻ ቦታ እንገናኝ …
ዳንኤል
በል ደና እደር

( እዝራ ወጣ )

( እዛው የሻይ ቅጠሉ ማሳ ላይ በጣም በሚያምር ሁኔታ ከተራራዎች ጀርባ ፀሀይ ስትወጣ እናያለን )

( ደመና /ጉም/ ተራራዎቹ ጫፍ ላይ ወድቆ እናያለን )

26
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሲን 35

ውጪ … የሻይ ቅጠሉ ማሳ ምሳ ሰዓት


የሻይ ቅጠሉ ማሳ ላይ የተለያዩ ሰዎች እናያለን … ሰዎቹ እራቅ እራቅ ብለው ቁመው ሻይ ቅጠል እየቀነጠሱ እናያለን በእጃቸው
ቅርጫት ይዘዋል … እዝራ ጭረቱ አንድ ቦታ ሆኖ እየቀነጠ እናያለን… በእጃቸው ቅርጫት ያዘዋል …ሁሉም ወንዶች የፍርሃት
በሚመስል ስሚት አጎንብሰው ነው የሚቀነጥሱት … ሰው መሆን የደበደበው ልጅ ፊቱ አፍንጫው ቀልቶ አይኑ ጠቁሮ እናየዋለን…
ዳንኤል … የሻይ ቅጠሉን ማሳ በተለያየ ሁኔታ ሲያነሳ እናያለን… የሚያነሳቸው ፍሬሞች በጣም ደስ ይላሉ… ዞር ሲል እንዴት ወፍ
የሻይ ቅጠል ላይ ስታርፍ አያት …ወደ ወፏ ካሜራው ፍሬም አስተካከለ ልክ ሊያነሳ ሲል በሁሉ ነገሩዋ ሂለንን እምትመስል ሲት
ናት ሳባ በታም በሚያምር ሁኒታ ቅርጫቷን እንደያዘች ወፏን ከልላ ገባች፡፡ ዳንኤል ወፏን ለማንሳት በስራው ፍሬም ውስጥ አንስት
ዳንኤል ወዲያውኑ ያነሳውን ፎቶ አያቶ ደነገጠ በለማመን አይነት ስሜት ቀና አለ …ሳባ ቆማለች

እዝራ
/ጮክ ብሎ/
ሁላችሁም ምሳ ብሉ … የምሳ ሰዓት ደርሷል ( ሰዎቹ መተረማመስ
ጀመሩ … ዳንኤል ያየውን ባለማመን አይነት ስሜት … ፍፁም ደስታ እና
ግራ መጋባት በተቀላቀለበት አያት ስሜት እያየ ነው ሄለን በሁሉ ነገሯ የምትመስል ሴት … ቁማለች
ሰባ ሁሉ ነገሩዋ ሄለንን ነው የሚመስለው … መልኩዋ ከሄለን በምንም አይለይም … ሳባ ቀና ስትል
ዳንኤልን ካየችው በፍርሀት አይነት ስሜት ካየችው በኋላ አንገቷን አቀረቀር… በመሀላቸው ሰፊ
እርቀት አለ ሰራተኞቹ በመሀላቸው መተላለፍ ጀመሩ )

ዳንኤል

/ካሜራውን ጥሎ ወደ ሳባ እየለ

( በጣም በፍጹም ደስታ እየጮኸ )

ሔለን … ሔለን
በመሀላቸው ብዙ ሰዎች ሲርመሰመሱ እናያለን …ዳንኤል ሰዎቹ ሳባን ከልለውታል … ዳንኤል ሰዎችን እየገፈታተረ አልፎ
ሳባ የነበረችበት ጋር ሲደርስ ሳባ የለችም … እዝራ ግራ በመጋባት አይነት ስሜት እያየው ነው፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ዳንኤልን
እያዩት ነው

ዳንኤል

/በፍጥነት ዙሪያውን እያየ በጭሆት/

ሔለን… ሔለን
እዝራ

/ወደ ዳንኤል ሄዶ/

ምን ሁነሀል? ማን ነች ሔለን?

ዳንኤል

/በሚያሳዝን እብደት በሚመስል ስሜት/

በሔወት አለች … አልሞተችም … እዚህ አይቻታለው


እዝራ

/ግራ እየገባው/

ማንን?

ዳንኤል

27
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

/የደስታ እንባው እየወረደ … ሳያረጋጋ/

ሔለንን ….

እዝራ

/ግራ በመጋባት/

ማነች?

ዳንኤል የእዝራን እጅ እየጎተተ በፍጥነት ወደ ካሜራው ወስደው ካሜራው ላይ የሳባ ፎቶ ቅርጫት ያዘ


እየለቀመች ያለው ይታያል፡፡ እዝራ አየው ደነገጠ እዝራ በፍጥነት ካሜራውን ያዘ ዝቅ ብሎ ማሳ ውስጥ ቁጭ
ብላ፡፡ ዳንኤል የደስታ ለቅሶ እያለቀሰ አጎንብሳ ቁጭ ብላ

አዝራ

/በችኮላ ስሜት/

እየውልህ ስማኝ … የአንተ ስሜት አልገባኝም … ግን … ይቺን


ልጅ ማየት አቁም አለበለዚያ ሰው መሆን አይለቅህም

ዳንኤል

/እያለቀሰና እየተናደደ/

ማነው ሰው መሆን? እኔ እኮ ፍቅረኛዋ ነኝ … ልታገባኝ ቃል ገብታልኛለች

እዝራ

/በንዴት/

እየውልህ እሱ ወንድሟ ነው … አሁን ይሄንን ስሜትህን ካወቀ ዝም አይልም


ዳንኤል ግራ በመጋባት በተበሳጨ ስሚት እዝራን አየው

ሲን 36

ውስጥ የሰው መሆን ቤት ቀን


ሰው መሆን የሰራተኞች መኖሪያ ካምፕ ውስጥ ያለ ጥሩ የሆነ ቤት ነው፡፡ ሰው መሆን የምግብ ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ብሏል
ምግብ እየበላ ነ ው፡፡ ሳባ ከፊት ለፊት ተቀምታ እየበላች ነው

ሰው መሆን

/አጎንብሶ በሚያስፈራ ሁኔታ እያያት/

ሳባ ከዚ በኋላ … እኔ ሀፍት የለኝም የምኖረውም የምሰራውም አንቺን ለመጠበቅ


እና ለማኖር ነው… ስለዚ ያንን ስራ ተይው
ሳባ

/ልስልስ ባለ ነፃ ባለመሆን ስሜት/

አውቃለው … ግን እዛ መስራት የፈለኩት እዚ ስሆን እየጨነቀኝ ስለሆነ እና

28
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

እዛ በጣም ደስ የሚል ቦታ ስለሆነ እንጂ ለሳንቲሙ ብዬ አይደለም


ሰው መሆን

አንደኛ ካደረሱብሽ ጥቃት በኋላ የገጠመሽ የመርሳት

በሽታሽ ማገገም አለብሽ በዛ ላይ ጠላቶቻችን እንኮዋን ቢመጡ አታቂያቸውም


እንደገና ገና ለገና ሰዎች እንቺን አዩሽ ብዬ…እየተጋጨው ነው… ደሞ እመኚኝ
ከዚም በኋላ አንቺን እንዲያናግሩሽም እንዲያዩሽም አልፈልገም… ማንም ይሁን ማንም
በአንቺ ከመጡብኝ ወደዋላ አልልም ድጋሚ መሰደድ እና መግደል አልፈልግም
ሳባ በእሽታ እራሷን ወዘወዘች … ሰው መሆን ካያተት በኋላ … አጎረሳት

ሲን 37

ውስጥ የዳንኤል ክፍል ቀን


ዳንኤል የሔለንን ፎቶዎች ለእዝራ እያሳየው እናያለን እዝራ በጣም በመገረም ነው የሚያየው … ዳንኤል በጣም በተረበሸ ስሜት
ውስጥ ነው፡፡

እዝራ

/በጣም በመገረም/

ሔለን ማለት ሳባ ነች? … እሺ እሱ ይሁን እንዴት … ስታይህ እረሳችህ …

ዳንኤል

/ግራ በመጋባት/

እኔ እንጃ … በሔወት ትኑር ትሙት እናውቅም ነበር …


እዝራ
እዚ ከመጣች አምስት ወር ቢሆናት ነው አሁን እንዳልከኝ

… ሔለን ከናተ ከተለየች ደሞ ዘጠኝ ወር … ስለዚ የሆነ ሴራ አለ ማለት

ነው … ሰው መሆን እህቱ ብትሆን ኑሮ እዚ አካባቢ 15 ዓመት ሲኖር ሊያመጣት

ይገባ ነበር፡፡በዛ ላይ እሱ እህት እንዳለው አናውቅም ነበር


ሁለቱም ተያዩ
ዳንኤል

/ግራ በመጋባት/

ቆይ እኔ ለምን ለህግ አላመለክትም


እዝራ
አይሆንም … እየሁልህ … የሆነ ጊዜ ሲያወራት እንደሰማሁት ከሆነ እሷ
የመርሳት ችግር አለባት … ስለዚ አንተን ብትረሳህስ … ከሱ ጋር
መሆን ብትፈልግስ … እና በቃ … እኔ በድብቅ እረዳኃለው

… ያለውን ነገር እንወቅ አለበለዚያ ግን ሕይወትህ አደጋ ላይ ይወድቃል

29
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ዳንኤል

/እየተናደደ/

ለምን አይገለኝም
እዝራ
እየውልህ ምንም ነገር ሳትፈጥር ከምትሞት መልስህ እሷን ያንተ ካረካት በኋላ ሙት መጀመሪያ …
በተለያዩ አጋጣሚዎች … እንድታስታውስህ አድርጋት … እመነኝ ያኔ ሁሉም ነገር ቀላል ነው… ለሷ
ስትል… ይሄንን አድርግ ምን አልባት ጥላት ከሆነ እሷንም ሊጎዳት ይችላል

ዳንኤል

/በረጅሙ ከተነፈሰ በኋላ/

እሺ … ግን እርዳታህን አፈልጋለው

እዝራ
አንተ ብቻ … ሁሉንም ነገር ከእሱ እና ከሌሎች ሰዎች እይታ ውጪ አድርገው
ዳንኤል በእሽታ እራሱን ወዘወዘ

ሲን 38

ውጪ ማሳ ላይ ቀን
የተለያዩ ሰዎች ማሳው ላይ እየለቀሙ ይታያሉ … ሰው መሆን ወደዛ ወደዛ እያለ ሲቆጣጠር እናያለን፡፡
ሰው መሆን

/ወደ አንድ ሰራተኛ እያየ/

አተ በርታ እንጂ … ፈዘሀል እኮ


( ልጁ በፍጥነት ሲስራ እናያለን፡፡ ሰው መሆን ዞር ሲል ሳባ ቅርጫቷን ይዛ ልትለቅም ስትገባ አያት፡፡
ተነዶወደ ሳባ ሄዶ… ሳባ አየችው፡፡ ዳንኤል እና እዝራ ወደ ማሳው ሲሄዱ እናያለን )

ሰው መሆን

/ደርሶ እየተቆጣት/

እዚ ስራ አቁሚ ብዪሽ እሺ ብለሽኝ አልነበር ለምን መጣሽ


ሳባ

/ግራ እየገባት/

እኔን .... መቼ?

ሰው መሆን

/እየተበሳጨ/

ቅደም
ሳባ

30
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

/ግራ እየተጋባች/

እንደዚ እንዳልከኝ በእውነት እኔ አላስታውስም …


ሰው መሆን ተበሳጨ ፡፡ ዞር ሲል ዳንኤል እና እዝራን አያቸው ወደ እነ ዳንኤል ሄዳ፡፡
ሰው መሆን

/በስሱ ፈገግ እያለ እጁን ለመጨበጥ እየዘረጋ/

ሰላም አቶ ዳንኤል … እስካሁን ሳላገኝህ በጣም ይቅርታ


ዳንኤል

/ከጨበጠው በኋላ/

ችግር የለውም
ሰው መሆን
በቃ እዝራ አለ … እኔ ቲንሽ ስራ ይበዛብኛል ከእሱ ጋር እየዞርክ የምትፈልገውን ፎቶ
አንሳ
ዳንኤል

/ኮስተር ብሎ እያየው/

እሺ
ሰው መሆን ለ ዳንኤል ጀርባውን ስቶ ሲሄድ እናያለን ዳንኤል ሳባን አያት፡፡

ሲን 39

ውስጥ የእነ ሰው መሆን ቤት /ሳሎን/ ማታ

ሳሎን ሰው መሆን እና እዝራ ጭረቱ ቁጭ ብለው ፊልም እያዩ እናያለን…


ሰው መሆን
/ወደ እዝራ እያየ/
ስማ ይቺ ልጅ እኮ በጣም እያስጨነቀችኝ ነው… ቢያንስ ቤት ውስጥ ብትቀመጥ
ስላም ይሰማኝ ነበር
እዝራ
እኔ … ግን … ወታ እዛ መሆኗ የተሸለ ነው… እንዲያውም … እንዳትጨነቅ
ያደርጋታል…
ሰው መሆን
ይልቅ … ከዚ በኋላ እኔን ተክተህ እንድትቆጣጠራት ያው እንደኔ ሁነህ … ብዙ ስራዎች እየበዙብኝ ስለሆነ
እሷን በመጠበቅ አግዛኝ … ታውቃለህ አንተን እንደ ታናሽ ወንድሜ ነው የማይህ

እዝራ
/በስሱ ፈገግ እያለ/
እሺ… ደስ ይለኛል … ደሞ እሷን መንከባከቡ ባትለኝም የሁለታችንም ግዴታ ነው
ሰው መሆን በደስታ ስሜት እራሱን ወዘወዘና ተያዩ

ሲን 40 ውጪ ጫካ ውስጥ ያለ የእግረኛ መንገድ ጠዋት

31
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ጫካውን በሩቅ እናየዋለን፡፡ ጉም ወደ ዛፎቹ አናት ላይ ወርዶ እናየዋለን፡፡ በጫካው የተዋጡ ጎጆ ቤቶች
ከውስጣቸው የሚወጣ ጢስ ይታይባቸዋል… ቦታው በጣም የሚያምር እና ደስ የሚል የጠዋት ድባብ ያለው
ቦታ ነው፡፡ በእግረኛ መንገዱ ሳባ እየሄደች እናያለን… ሳባ አንገቷን ደፍታ ነው የምትሄደው … ዝናብ እየዘነበ
ነው

/ኤላ አታያይ/

ዳንኤል በዝናቡ በስብሶ ከእግረኛ መንገዱ ዳር ካለ ቦታ ላይ አንድ የዘንባባ ዛፍ ተደግፎ ቁሟል… ወደ መንገዱ ጫፍ
እየተመለከተ ነው ከሁኔታው ሰው እየጠበቀ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ከሚመለከትበት መንገድ ካለው እጥፋት ሳባ ስትመጣ
አየው በጣም በስስት እና በጉጉት ስሜት አያት… ከሰኮንዶች በኋላ ሳባ እሱ ጋር ደረሰች በዝናብ ውስጥ ቁሞ አየችው፡፡

ዳንኤል

/ወደ ሳባ እያየ በስስት/

ሔለን

ሳባ
/ግራ በመጋባት እሱን እያየችው በትህትና/
እኔን ነው ሔለን ያልከኝ?
ዳንኤል
/በስስት እያያት ከተጠጋት በኋላ/
አዎ …ቆይ ምን ሁነሻል
ሳባ
/በትህትና እያየችው/
አይ ተሳስተሀል … የኔ ስም ሳባ ነው
ዳንኤል
/እንባው እያዩ ላይ ግጥም እያለ/
እሺ … ስምሽን ተይው ግን አታውቂኝም
ሳባ ግራ በመጋባት አየችው፡፡ ዳንኤል በተከፋ ስሜት አያት ሄለን ግራ በተጋባ ስሜት አየችው
ሳባ

/ግራ በመጋባት አይነት ስሜት/

ምን አልባት አቅህ ይሆናል…. ይቅርታ አድርግልኝ… እኔ ትንሽ አደጋ ከደረሰብኝ

በኋላ… ያለፈ ታሪኬን ማስታውስ አልቻልኩም ደሞ ለምን ታለቅሳለሁ? አንተ ማን ነህ?

ዳንኤል

/እያለቀሰ እያያት/

ዳንኤል ነኝ … ልታጋቢው እምትፈልገው ዳንኤል…


ሳባ

/በፍጹም ግራ መጋባት ውስጥ ሁና/

እርግጠኛ ነኝ … ተሳስተሀል
የሰው መሆን ድምፅ ሰማች… ዞር ስትል እሷ በመጣችበት አካባቢ በዛፎቹ ተሻግሮ ሰው መሆን እና እዝራ
ሲመጡ ተመለከተች… ደነገጠች … በፍጥነት የዳንኤልን እጅ ይዛ እየጎተተች ወደ ጫካው ውስጥ ገባች ከአንድ

32
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ትልቅ ዘንባባ ግንዱ ስር ዳንኤልን ደበቀችው ፡፡ እሷ እንዳትታይ እሱን ተጠግታው ልጥፍ ብላ በፍርሀት ቆመች
እነ ሰው መሆን እያለፉ ነው

ዳንኤል

/እንባው እየወረደ/

ሔለን
ሳባ ደንግጣ አፉን በእጇ ጥብቅ አድርጋ ያዘችው… እያኑን አትኩራ አየችው… ከአያቱ እንባ እየወረደ አትኩሮ አያት… እነ ሰው መሆን
እያለፉ ነው፡፡ ሳባና ዳንኤል በአትኩሮት እየተያዩ ነው፡፡ ሰው መሆን እነ እዝራ እርቀው ሄዱ

ሳባ

/እጇን ሳትለቀው እያየችው በሹክሽክታ/

የኔ ወንድም እንግዳ ነህ መሰለኝ…እባክህ እኒን አትከተለኝ ለራስህ ስትለ


ሰውመሆን ይጎዳሃል እመነኝ … ሌላው በፍጹም እኔ አንተን አላውቅህም
እጇን ከአፉ ላይ አነሳችው … ብላይ ላይ ያለው ሻርፕ ወደቀ ሄደች … ዳንኤል ግራ በመጋባት ስሜት ውስጥ ሆኖ እያለቀሰ
አያት… እርቃ ሄደች … በአይኑ ሸኛት …ሻርቧን አነሳው … ሻርቧን ሳመው

ሞንታጅ

• ዳንኤል የሳባን ሻርፕ ይዞ ብቻውን የተራራው ጫፍ ላይ ሆኖ የሻይ ቅጠሉን ማሳ እያየ ሲያለቅስ ..

ተራራው አናት ላይ ግብት ያለ ደመና እናያለን

• ዳንኤል ብቻውን በጫካው ውስጥ ባለው መንገድ መሀል የሳባን ሻርፕ ይዞ ሲሄድ እናያለን … ተከፍቷል ዝናብ ነው፡፡

• ዳንኤል እስካርፑን እጁ ላይ አስሮት የሻይ ቅጠሉ እርሻ ላይ ሲያያት ያነሳትን ፎቶ እያየ አልጋው ላይ

ጋደም እንዳለ ሲያለቅስ

• የሻይ ቅጠሉ ማሳ መሀል ብቻውን ቁሟል እሱ እዛው እንደቆመ ሳይንቀሳቀስ … ሌሎቹ ስራተኞች በፎርዋርድ እየፈፀኑ
ማሳው ላይ ሲገኙ እናያለን … ፍርዋርዱ ዝግ ካለ በኋላ ሳባ ማሳ ውስጥ ሆና ያያታል … በጣም በሚያሳዝን ስሜት ነው
የሚያያት … እጁ ላይ ሻርቧ አለ

• ዳንኤል ከተሰጠው ክፍል በረንዳ ላይ በጀርባው ተኝቶ ሰማዩን እየተመለከተ ነው፡፡ በጣም በተረበሸ ስሜት

ውስጥ ነው፡፡ በጠርሙስ የያዘውን አልኮል እየጠጣ እናያለን

ሲን 41

ውስጥ … የእነ ሰውመሆን ቤት/ሳሎን/ማታ

ሳሎን ውስጥ ሳባ ሰውመሆን እዝራን እናያቸዋለን ቴሌቨዥን እያዩ ነው… ትንሽ ሲያዩ ጊዜ ሲያልፍ እናያለን

ዳንኤል o/s

/በጣም በስካር እና በጭሆት ድምፀት/

ሔለን !!! ሔለን

ሦስቱም ደነገጡ … እዝራ በጣም ደነገጠ … ሰው መሆን እና እዝራ ተከታትለው ወጡ … ሳባ ደንግጣ በዝግታ እነሱን ተከትላ
ስትሄድ እናያለን፡፡

33
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሲን 42

ውጪ የእነ ሰው መሆን በር ማታ
ዳንኤል በጣም በስካር ስሜት ጠርሙስ በእጁ ይዞ ቁሟል …እዝራና ሰው መሆን ተከታትለው ወጡ
ዳንኤል

/እየጮኸ በስካር ስሜት/

ሔለንስ !!! ሔለንስ?

ሰው መሆን

/ወደ እዝራ እያየ/

ገና እግሩ ሳይቆም ስክሮ ይበጠብጣል


እዝራ

/ወደ ዳንኤል እየሄደ/

በቃ እኔ አስገባዋለው … አንተ ግባ
እዝራ ወደ ዳንኤል ሄዶ … እጂን ያዘው
እዝራ

/በሹኩሽክታ እየፈጠጠበት/

ምን እየሆንክ ነው … ያምሀል
ዳንኤል

/እየጮኸ እየፈጠጠበት/

አዎ ያመኛል … በምወዳት ሔለን አለመታወቄ ያመኛል


ሰው መሆን ግራ እየተጋባ አየው …
ዳንኤል

/ወደ ሰውመሆን እያየ በቁጣ/

ሔለንስ
ሰው መሆን
ማን ነች ሔለን
ዳንኤል

/እዝራን እየታገለው/

አስመሳይ … ስም ቀይረህ ሳባ ብትላላም እሷ ግን መልክዋ አይቀየርም


ሰው መሆን ተናደደ … ወደ ዳንኤል ሄደ እዝራ በጭንቀት ስሜት ዳንኤልን እየታገለው ነው …ሰው መሆን ደርሶ ዳንኤልን
በበክስ መታው … ዳንኤል ተንገዳገዶ … የያዘውን ጠርሙስ ወደ ሰው መሆን ሊሰነዝር ሲል ሳባን ከበር ስትወጣ አያት …
ጠርሙሱን መሰንዘሩን አቆመ … ፈዘዘ … ሳባ በጣም ባዘነ ስሜት በሩን ተደግፋ ቆመች … ሰው መሆን ዳንኤልን እየመታው
ነው … ዳንኤል እየተመታ ቀና ብሎ ሳባን እያየ ዝም ብሎ ፈዞ እያለቀሰ

34
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሲመለከታት እናያለን፡፡ ሰው መሆን እዝራን እየታገለ ዳንኤልን እየደበደበው ነው … ሰው መሆን ዳንኤል የያዘውን
ጠርሙስ ተቀብሎ ጭንቅቅላቱን መታው ዳንኤል ደም በደም ሆነ… ተልፈሰፈሰ … ሰው

መሆን በፍጥነት ወደ ቤት ገባ …እዝራ ተከትሎ ገባ … ዳንኤል ወደቀ … በወደቀበት ቀና ብሎ ሳባን እጅግ በጣም
በሚያሳዝን ስሜት እያለቀሰ አያት … በተደከመ ሁኔታ ውስጥ ነው … ሳባ እንባዋ አይኗ ላይ ግጥም አለ አለቀሰች

ሲን 43

ውስጥ የእነ ሰው መሆን ቤት /ሳሎን/ ማታ

ሰው መሆን መሳሪያ ይዞ ከመኝታ ቤት ወጣ … እዝራ ያዘው


እዝራ

/በጭንቀት/

እባክህ በፈጠረህ … እሱ እኮ በሽተኛ ነው


ሰው መሆን

/በንዴት እየታገለው/

እሱ እኔን ሊበቀለኝ የመጣ ሰው ነው …

( ሳባ ከበሩ ወደ ውስጥ ገባች )

እዝራ
እሱ የአምሮ በሽተኛ ነው … አማንኤል የነበረ ሰው ነው …
ሳባ

/በጭንቀት እና በሀዘን/

አዎ … ትናንትናም እንደዚ እያረገው ሌላ ሰው ቤት ሂዶ ሲረብሽ ነበረ


እና እባክህ ተረጋጋ
ሰው መሆን እየተበሳጨ ወደ መኝታ ቤቱ ገባ

ሲን 44

ውስጥ … የዳንኤል መኝታ ቤት ጠዋት

በመስኮቱ ብርሀን እየገባ ነው…. ዳንኤል ከአንሶላ ውሰጥ ሁኖ እናየዋለን … አይኑ አብጧል … ፊቱ በልዟል … ጭንቅላቱ
ታሽጓል … አይኑን ገልጦ በጀርባው እንደተኛ ነው፡፡በጣም በሚያሳዝን ስሜት ውስጥ ነው …

ሲን 45

ውጪ የዳንኤል ቤት በር ጠዋት
ሳባ ወደ ዳንኤል ቤት በር ሄዳ ስትቆም እናያለን ትንሽ ካመነታች በኋላ በሩን አንኩዋካች … ዝም አለች
አልተከፈተም … ደግሞ አንኩዋኳች … አልተከፈተም …ተመልሳ ልትሄድ ዞር ስትል በሩ ተከፈተ … ቆመች
ዳንኤል አያት … በሩን እንደያዘው ደንግጦ አያት … ሳባ የተመታውን ፊቱን በሀዘን አየችው

35
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሳባ

/በዝምታ ከተያዩ በኋላ/

ወንድሚ አዝናለው … ለሊቱን ሙሉ ስጨነቅ ነው ያደርኩት …


እኔ በጣም ግራ ገብቶኛል … ከረዳኃኝ እና እስክትሄድ ጎደኛዬ ሁነህ …
ተደብቀን እየተገናኘን ስለ አንተ
ባቅ ደኑ ያለኛል … ንፁ ሰው እንደሆንክ አውቃለው … ከእዝራ ብዙ ነገሮችን
ነገረኝ …
ዳንኤል

/በሦስት እያያት ዝቅ ባለ በህመም ስሜት/

ምን ነገረሽ?

ሳባ

/ለማስታወስ እየሞከረች/

አንተ በጣም ንጹህ የሚያስጨንቅህ ያለፈ ታሪክ እንዳለህ ነገረኝ … እና በቃ


አንተን በደንብ ማወቅ እፈልጋለው …ምን አልባት አንተን ሳውቅህ ባለፈ
ታሪኬ ውስጥ መኖርህን እና አለመኖርህን ላረጋግጥ እችላለው …
ዳንኤል ዝም ብሎ አያት
ሳባ

/እጇን ለትውውቅ እየዘረጋች/

እባክህ ጎደኛዬ ትሆናለህ …


ዳንኤል ፈዞ ካያት በኋላ እጁን ዘርጋላት ተጨባበጡ

ሳባ

/በስሱ ፈገግ እያለች/

ሳባ እባላለው
ዳንኤል

/ፈዞ እያያት/

ዳንኤል
ሳባ ካረገችው ቀሚስ ውስጥ እስኪርብቶና ወረቀት አወጣች ዳንኤል ብላ ፃፈች
ሳባ

/በፈገግታ እያየችው/

ምሳ ሰዓት ላይ ምሳ ይዤልህ እመጣለው እስከዛ ግን ከምግብ ቤት ቁርስ አስመጣ


እሺ

36
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ዳንኤል

/በጣም በመገረም እያያት/

እሺ
በፈገግት ካየችው በኋላ ሄደች … ዳንኤል ፈዞ አያት … በአይኑ ሸኛት

ሲን 46

ወጪ የሻይ ቅጠሉ የእርሻ ቦታ ቀን


የሻይ ቅጠሉ የእርሻ ቦታ ላይ የተለመዱ ክንውኖችን እናያለን … ሁሉም ሰራተኞች ስራ እየሰሩ እናያለን ፡፡ ሰው
መሆን ዞር ዞር እያለ ሲያይ እናያለን … ሳባ ማሳው ላይ ሻይ ቅጠሉን እየተንከባከበች እናያለን፡፡ እነዚን
ሁኔታዎች ካየን በኃላ ዳንኤል ወደ ማሳው ሲመጣ እናያለን፡፡ በተደበደበበት ሁኔታ ውስጥ ነው ፊቱ፡፡ ዳንኤል
ወደ ሰው መሆን አጠገብ ሄዶ ሲቆም እናየዋለን፡፡ ሳባ ግራ በመጋባት ዳንኤልን አየችው፡፡ ሰው መሆን ወደ
ዳንኤል ዞረ፡፡

ዳንኤል

/ትንሽ ካየው በኋላ/

ይቅርታ … በረኩት ነገር አዝኛለው


ሰው መሆን

/ቲንሽ ካየው በኋላ/

እነ እዝራ ሁሉንም ነገር ነግረውኛል … እና አትጨነቅ … ስራህን በሰላም ሰርተህ ሂድ


ዳንኤል በእሺታ እራሱን ወዘወዘ … ሰው መሆን ወደ ሌላ ቦታ
ማየት ጀመረ፡፡ ሳባ ዳንኤልን እያየች በስሱ ፈገግ አለች፡፡ ተያዩ

ሲን 47
ውጪ ዳንኤል የሚቀመጥበት ተራራ ቀን
ዳንኤል እና ሳባ ከተራራው ጫፍ ላይ ቁጭ ብለዋል… ከፊል ከፊታቸው የተበላለት ምሳ ሰአን እናያለን፡፡ ዳንኤል ወደ ሻይ
ቅጠሉ ማሳ እየተመለከተ ነው፡፡

ሳባ

/ወደ ዳንኤል እያየች/

የሻይ ቅጠሉ እርሻ ብዙ ቦታ ይበልጥ ውብ እንደሆነ አላውቅም ነበረ …


ዳንኤል

/ወደ ሳባ እያየ/

እኔም ዛሬ ነው በደንብ ያየሁት


ሳባ

/ግራ እየተገባች/

እንዴት … አንተ አይደለህ እንዴ እዚ ያመጣኸኝ እንዴት እስከ ዛሬ አላየከውም?

ዳንኤል

37
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

/ወደ ማሳው እያየ/

ከዚ ትልቅ ማሳ … ከነዚ ሁሉ ሰዎች መሀል … አንቺ ነሽ የምትታይኝ


ሳባ

/በሹፈት ስሜት/

እና የኔ ፊት ከሩቅ ሲታይ ከዚ ማሳ ይበልጣል ማለት ነው

ዳንኤል ሳቀ … እሷም ሳቀች …


ሳባ

/ሳቋን ጨርሳ/

እያሾፍኩብህ አይደለም እሺ … ይልቅ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ … እስኪ ስለ ሄለን አውራኝ


ዳንኤል

/በዝምታ ከየት በኋላ/

በጣም ታፈቅረኛለች … ሁሊም … ታስብልኛለች ለራሷ ሳይሆን ለሰዎች መኖር ምኞቷ ነው


ጎበዝ ደራሲ ነች … ግን የመጀመሪያ መፀሀፏን የመስራት እቅድ ነበራት …
ሳባ

በጣም ደስ ትላለች ..

ዳንኤል
ግን … ስለ ሄለን ለምን ንገረኝ አልሽ
ሳባ
ስለ እሷ ማወቅ ፈልጌ
ዳንኤል
እሺ …አንቺ … ሄለን አይደለሁም ብለሽ እያስብሽ ሊሆን ይችላል … እኔ ግን አንቺ

እሷ ነሽ … ሙሉ ለሙሉ እሷን ትመስያለሽ ቆይ መንትያ እህት አለሽ?

ሳባ
እኔ ገና እንደተወለድኩ የነበረኝ ፎቶ አለ … … የተረሱኝ ብዙነገሮች እንዳሉ ባውቅም … እህት

እንደሌለኝ አውቃለው ሰውመሆን እኛ ቤት ውስጥ ሴት እንደሌለ ነግሮኛል … እህት


እንደሊለኝ በዚ ማርጋገጥ ትችላልህ
ዳንኤል በፍጹም ግራ መጋባት አያት … ከኪሱ የሄለን ፎቶ አውቶ ሰጣት አየችው ግራ ተጋባች፡፡ ወዲያውኑ ተገረመች
ዳንኤል
እሺ … እሷ ማን ነች … ሳባ … ያለሽባትን ችግር በግልፅ ንገሪኝ …
ያለሁበት ሁኔታ ጥሩ አይደለም በጣም እየተጎዳው ነው …

( ሳባ ግራ በመጋባት አየችው … ዳንኤል የመከፋት ስሜት ያነባብባት ጀመረ )

38
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ዳንኤል

/በተከፋ ስሜት ውስጥ ሆኖ/

እንደምትመለሺ ነግረሽኝ ነበር የሄድሽው ታውቂያለሽ እናትሽ ካለ አንቺ መኖር ከብዷታል


ገዳም ገብታለች … ባክሽ … ስምሽን ስለቀየርሽ ብቻ ያለፈ ታሪክሽን መቀየር አትችይም …

( እንባው አይኑ ላይ ቀረረ … ባዘን ስሜት አየችው )

ዳንኤል

/እንባው ወረደ/

አውቃለው … አይደለም ኑረሽ ብትሞቺ እንኩዋን እኔ ካለ አንቺ አግብቶ የመኖር ህልም የለኝም
አግቢኝ እያልኩሽ አይደለም … እኔ ለሄወት መኖርስ ብቻ በቂ ነው …
እየጠየኩሽ ያለሁት ቢያንስ … እኔና እናትሽ እያየንሽ እንኑር

( ሳባ በተረበሸ ስሜት ካየችው በኋላ እንባውን ጠረገችለት … የሱንእየጠረገችለት እሷ አለቀሰች፡፡)

ሳባ

/በተረበሸ ስሜት እያለቀሰች/

እውነት ግራ እየገባኝ ነው… ለምንድን ነው ያለፈ ታሪኬን ማስታወስ የማልችልወ … ቆይ


እሺ እኔ ማን ነኝ …
ዳንኤል

/እንባዋን እየጠረገላት/

አይዞሽ ከዚ በኋላ ያለፈውን ነገር ስለማስታወስ አትጨነቂ … የምልሽ ሁሉ … እንዲያስጨንቅሽ

አልፈልግም … የነገርኩሽን ሁሉ እርሺው እንደገና እንደተወለድሽ አስቢው … ስለ እኔ አትጨነቂ … በቃ አዲስ


ጓደኞች ነን …
እንባዋ እየወረደ በእሺታ እራሷን ወዘወዘች፡፡ ዳንኤል አቀፋት

ሲን 48

ውስጥ … የዳንኤል ቤት ማታ
ዳንኤል አልጋው ላይ ተኝቶ ጣራ ጣራውን እያየ ፈገግ ብሏል

ዳንኤል V/0

እኔና እሷ ድጋሜ እንደ አዲስ ተዋወቅን …


ባለፈ ታሪኳ ውስጥ ባታስታውሰኝም
በሚመጣው ሂወቷ ውስጥ መኖርን ተመኘው
ብርድ ልብሱን ፈገግ እንዳለ ለበሰው

ሲን 49

ውጪ ጫካ ውስጥ ጠዋት

39
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ጫካው በጣም ጥቅጥቅ ያለ ነው… በዛ ውስጥ ትንሽ የእግረኛ መንገድ አለ፡፡ በዛ መንገድ ላይ ሳባ እየሮጠች ስትሄድ
ዳንኤል እየሮጠ ሲከተላት እናያለን … ፊታቸው ላይ ደስታ ያነበባል

ዳንኤል V/0

አውቃለው ሂወትን እንደ አዲስ መጀመር ይከብዳል … ሄለን ባለፈ ታሪኳ ውስጥ
ጠፍታለች … በቃ እኔም እሷን ተከትዬ መጥፋት እና … ድጋሚ መወለድን
እፈልጋለው … አሁን ሄለን ያለችበት አለም ላይ ከደመናው በላይ ሁነን እየኖርን
እንዳለን ይሰማኛል …

ሲን 50

ውጪ ጫካ ውስጥ አንድ ዘንባባ ስር ቀን


ሳባና ዳንኤል ከዘንባባው ዛፍ ስር ተደግፈውት ቁጭ ብለዋል ዳንኤል የሳባን ሻርፕ በእጁ ይዞታል…
ዳንኤል

/በፈገግታ እያያት/

ይሄንን ሻርፕ ታስታውሽዋለሽ?

ሳባ

/ካየቻ በኋላ/

አይ … የማን ነው?

ዳንኤል
እዚው ዘንባባ ጋር ነው የተቀበልኩሽ
ሳባ ፈገግ ብላ አየችው

ዳንኤል

/ሻርፑን እየሰጣት/

በይ ከዚ በኋላ ያንቺ ነው
ሳባ

/ሳትቀበለው እያየችው/

አይ ያዘው ማስታወሺያ ይሁንክ


ዳንኤል

/በፈገግታ ካያት በኋላ/

እኒና አንቺ ከዚ በዋላ የልብ ጓደኞች ነን … አንለያየም … ሁሌም


እንገናኛለን… ደሞ ማስታወሺያ የሚሰጠው ድጋሚ የማታገኘው ሰው ሲሆን ነው
ዳንኤል ሰጠት፡፡ ተቀበለችው፡፡ አረገችውና በፈገግታ አየችው
ሳባ

40
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ስለ ማትለየኝ ሁሌም ጎደኛዬ ስለሆንክ አመሰግንአለው


በእሽታ እራሱን ወዘወዘ …በጣም ተያዩ …

ሲን 51

ውስጥ የእነ ሰው መሆን ቤት ቀን


ሰው መሆን እና እዝራ ሳሎን ቁጭ ብለዋል…
ሰው መሆን

/ወደ እዝራ እያየ/

ለማንኛውም … እኔ እስክመለስ የድርጅቱን ሰራተኞች አደራ


ሳባ ከውጪ ፈገግ ብላ ገባች … ሄዳ ደስተኛ በመሆን ስሜት ሁለቱንም ሳመቻቸው
ሰው መሆን

/በፈገግታ እያያት/

አዲስ አበባ አብረሽኝ ልትሄጂ መሆኑን ሰምተሸ ይሆን ደስታው


ሳባ

/ፈገግታዋ ከፊቷ ጠፋ/

እረ እኔ አልሄድም
ሰው መሆን
እሱ እንኩዋን እኔ ከስራ ደርሺ እስከመለስ ጥዬሽ መሄድ አልችልም
ሳባ
/እየከፋት/
እንዴ … እዚህ መሆን ነው የምፈልገው … ደሞ እዝራ አለ …
የሻይ ቅጠሉ እርሻ ቦታም አልሄድም ግን እዚ መሆን እፈልጋለው
ሰው መሆን
እሺ … አይክፋሽ … እስክመለስ … መውጣት የለም ብትወጪም ከእዝራ
ጋር ብቻ ነው … ብቻሽን የትም አትሂጂ
ሳባ

/ፈገግ እያለች/

እሺ …

… ደስ አላት

ሲን 52

ውጪ መንገድ ላይ ጠዋት
ዳንኤል ካሜራውን ይዞ እየሄደ እናያለን፡፡ ፊቱ ላይ ደስታ እየተነበበ ነው፡፡ በአካባቢው ሌሎች ሰዎች እናያለን
ቲንሽ ብቻውን ከተጎዘ በኋላ ሳባ መታ ከኋላው ታስደነግጠዋለች ደንግጦ ቆመ … ሳቀች … እሱም ሳቀ ፀጉሩም ተንጨባሯል
እላዩ ላይ ማበጠሪያ ሽጉጣለች፡፡ በእጇ የምግብ ሳህን ይዛለች

41
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ዳንኤል

/እየሳቀ እያያት/

ፀጉርሽ ምንድን ነው
ሳባ
እያበጠርኩት ሳለ ቶሎ አንተን ማግኘት ፈለኩኝ እና መጣሁኝ …
ዳንኤል

/ግራና ቀኙን ካየ በኋላ/

ደሞ በሰዎች መሀል እንዳንገናኝተባብለን አልነበር … አሁን ሰውመሆን ቢያንስ

ሳባ

/በስሱ እየሳቀች/

ፈራህ እንዴ?

ዳንኤል
አይ … ተደብቀን እንጂ… በግልፅ ለመገናኘት ሁለታችንም አንፈልግም ብዬ ነው …
ሳባ
አትፍራ ሰውመሆን የለም … ከተወሰኑ ቀናት አዲስ አበባ ሄዷል
ሁለቱም ተያይዘው ሲሄዱ እናያለን

ሲን 53

ውጪ ጫካ ውስጥ ጠዋት
ዳንኤልና እና ሳባ ሁለቱም ዘንባባዎች ያሉበት አካባቢ ተቀምጠው ነው የምናያቸው፡፡ ዳንኤል ሳባን እያያት ነው … ሳባሌላ ሌላ ቦታ
እያየች ስታወራ እናያታለን፡፡

ሳባ
እውነት አንተ ጎደኛዬ ከሆንክ ጀምሮ ብዙ ለውጥ
እያየው ነው … የድሮው ህቤቷ
ትዝ ባይለኝም ካንተ ጋር የማሳልፋቸው ጊዜያት
ግን ጊዜ ሰጥቼ ስለማስባቸው ይሁን እኔጃ ሁሌም ትዝ ይሉኛል
ዳንኤል

/ፈገግ እያለ/

እሺ … ደሞ ፀጉርሽን ተሰሪው
ሳባ

ለምን አንተ አትሰራኝም? …

42
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ዳንኤል

የማልችል መሽሎስ ነው ? ነይ ልስራሽ ግን ባለ

ሦስቱን ቁጥርጥር ብቻ ነው የምችለው

( እየሳቀች እግሩ ስር ገባች … ዳንኤል ፀጉሯን እያበጠረ ቁጥርጥር እየሰራት ሦስት ፀጉሮችን ይዞ ሲሰራቸውእናያለን )

ዳንኤል

/እየሰራት እያየችው/

ደሞ ፀጉርሽን ሰርቼ ስጨርስ … አንድ ስጦታ አዘጋጅቼልሻለሁ


ሳባ

/እየከፋት/

ማስታወሻ አይደለም አይደል?

ዳንኤል
አትፍሪ ስጦታ ነው
በደስታ … መስራቱን አቋማ ዞረች …
ዳንኤል

/እየሳቀ እያያት/

ቆይ እንጂ
ሳባ

/በጉጉት እያየችው/

አይ አሁን ሰጠኝ

( ዳንኤል ከኪሱ የሀብል ማስቀመጫ አወጣ፡፡ ደነገጠች ሀብሉን አወጣው … ያ ሀብል ከሄለን ሊሰጣት የነበረው የወርቅ ሀብል ነው
… ሳባ ጉጉቷ ቅዝቅዝ አለ )

ዳንኤል
ከዚ … የተሻለ ስጦታ ለጊዜው አጣው
ሳባ

/መልስ እግሩ ስር ጀርባዋን ሰታ ቁጭ እያለች/

እመሰግናለው እሺ … ግን እኔ የወርቅ ጌጥ አልወድም


ዳንኤል ደስ አለው … በደስታ እያያት እንባው ግጥም አለ ሌላየሀብል ማስቀመጫ አወጣ … የብር ሀብል አወጣ ጀርባዋን ሰታ
እንደተቀመጠች ሀብሉን አንገቷ ላይ አደረገላት ሀብሉን ስታየው ደስ አላት … ጮኸች … ተነሳች

ሳባ

/በደስታ እየዘለለች/

የብር ሀብል እንደምወድ በምን አወክ


ዳንኤል

/በስስት እያያት/

43
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሳባዬ … አንቺ እኮ በሂወት የመኖረው አንቺን ብዪ ነው

ሳባ በደስታ አየችው ጉንጩን ሳመችው .. ቁማ ሀብሉን አየችው ሀብሉን አንዴ ዳንኤልን አንዴ ካየችው በኋላ ፊቷ

ወደ ሀዘን ስሜት ውስጥ ገባች … እንባ አይኗ ላይ ሙልት አለ አለቀሰች


ዳንኤል
/በጭንቀት ተነስታ እያቀፋት/
ምን ሆነሽ
ሳባ
/እያለቀሰች እያየችው/
እኔ የብር ሀብል እንደምወድ የምታውቀው መቼ ነው? … እኔ ሔለን የምትላት ሚስትህ
ነበርኩኝ አይደል
ዳንኤል
/ለማባበል እየሞከረ/
አይ ስላለፈ ሂወትሽ አትጨነቂ እርሺው
ሳባ

/እያለቀሰች/

በሄወት የምትኖረው እንዳለብኝ ለኔ ብለህ ነው አያደል … ለምን … እጠራጠርሀለው


ዳንኤል ሊያባብላት ሞከረ … እያለቀሰች መሄድ ጀመረች
ሳባ
እኔ እኮ እረስቼአለው …ላስታውስህ አልችልም አንተ ግን ለኔ ትኖራለህ
እያለቀሰች እየሄደች ነው … ዳንኤል በጣም በተረበሸ ስሜት ተከተላት

ሲን 54

ውስጥ የሰው መሆን ቤት ቀን


ሳባ እያለቀሰች ሳሎን ቁጭ ብላለች ከአጠገቧ ዳንኤል ቁጭ ብሏል …
ዳንኤል

/አይን ለአይን እየተያዩ/

አሁን እኮ አንቺ ከጎኔ አለሽ … እኔን ስለ ማፍቀር አትጨነቂ


ሳባ

/እንባዋን መቆጣጠር እያቃታት/

እወድኃለው … በጣም ለምጂሀለው … ግን የኔ ስሜት የፍቅር አይደለም … በቃ


እየበደልኩህ እንደሆነ ይሰማኛል

ዳንኤል

/በስስት እያያት/

አልበደልሽኝም … የኔን ስሜት ካለፈ ታሪክሽ ጋር እርሺው … አሁን ሁሉም አዲስ ነው


እስኪ እንደ አዲስ እወቂኝ

44
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

እያለቀሰች በእሽታ እራሷን ወዘወዘች … ዳንኤል እንባዋን ጠረገላት ሁለቱም ተቃቀፉ … እዝራ ጥረቱ አንድ ጥግ ይዞ
ሲያያቸው እናያለን

ሲን 55

ውጪ የመኖሪያ ካምፕ ሰፈር አመሻሽ


ዳንኤል ብቻውን እየሄደ እናያለን … ፊቱ ላይ ስስ የሆነ ደስታ እናያለን

ሲን 56

ውስጥ የእነ ሰው መሆን ቤት ማታ /ሳሎን/

እዝራ ከሳባ ጋር አጠገቧ ቁጭ ብሏል … ሳባም እዝራም ሁለቱም ዝም ብለዋል


እዝራ

/ከዝምታ በኃላ/

አንቺ የእሱ ብቻ ነበርሽ … ሳባ በንግግሬ ይቅርታ ግን አንቺ ያለፈ ታሪክሽን ለማስታወስ ስታይ
እየበደልሽው ነው … በጣም እራስ ወዳድ ነሽ ሳባ ዞር ብላ አየችው
እዝራ

/አተኩሮ እያያት/

እንደገና እሱን ማፍቀር ባትችይስ … እሱን ትተሸ ሌላ ብታገቢስ … አያሳዝንሽም ከሰማሽኝ አንድ ነገር ልንገርሽ
ሰባ በአትኩሮት አየችው … አያት …
እዝራ

/ከዝምታ በኋላ/

ወይ ተስፋ አስቆራጪው … ወዬ ድጋሚ እስክታፈቅረው አጠብቂ፡፡


አብረሽው ሁኚ … ለአንድ ቀን ተለይቶሽ አያቅም ነበር …
ታዲያ አሁን ሁሌም ሲጠብቅሽ እየኖረ እኮ ነው … ደሞ ወደ
እሱ ሂወት ውስጥ በደንብ ስትገቢ ብዙ ነገሮችን ታስታውሺ ይሆናል

( ዝም ብላ ካየችው በኋላ በረጅሙ ተንፈሰችና በማሰብ ስሜት መሬት መሬቱን ማየት ጀመረች፡፡ እዝራ ትከሻውን ነካነካ
አደረገው፡፡)

ሲን 57

ውጪ የሻይ ቅጠል እርሻው ቦታ ቀን


ዳንኤል ፎቶ እያነሳ ነው፡፡ ሰራተኞች ስራቸውን እየሰሩ ነው፡፡ ሳባ በዝምታ ውስጥ ሁና የሻይቅጠሉ እርሻ መሀል ቁማ ፈዛ
ዳንኤልን እያየችው ነው፡፡ ዳንኤል በአጋጣሚ ዞር ሲል አያት ሁለቱም ተያዩ

ሲን 58

ውጪ የመኪና መንገድ ቀን( ሺሺነዳ )

አንድ የህዝብ መኪና በሩቅ ሲመጣ እናያለን … ፡፡ ቆመ፡፡ በሩ ተከፍቶሰው መሆን ከውስጥ ወጣ፡፡ ሻንጣዎችን ይዟል፡፡ እዝራ
ተቀበለው፡፡

45
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሲን 59

ወጪ የሻይ ቅጠሉ እርሻ ቦታ ቀን


እርሻው ቦታ ላይ ሰዎች የሉም … ከእርሻው ጥግ ቲንሽ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ሳባና ዳንኤል ቁጭ ብለው ይታያሉ፡፡የሻይ ቅጠሉ
እርሻ እስከ ጭንቅላታቸው ድረስ ሸፍኗቸዋል፡፡ ሳባ ዝም ብላ አይን አይኑን እያየችው ነው፡፡

ሳባ

/አትኩራ እያየችው/

እረስታኛለች ብለህ .. ጥለህኝ ስላልሄድክ በጣም አመሰግናለው እሺ

ዳንኤል
ባክሽ እንደዚ አትበይኝ

ሳባ በስሱ ፈገግ አለች፡፡ ዳንኤል በስሱ ፈገግ አለ፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዞ .. እየተያዩ ነው … በድንገት ዞር አሉ .. ሰው መሆን እና
እዝራ ሲያልፉ አይ ደነገጡ፡፡ዝቅ አሉ፡፡ ዳንኤል ከስር እሷ ላዩ ላይ ተኛች ሳባ ደንግጣ እነ ሰው መሆኑን እያየች ነው

… ዳንኤል

ፈዞ እሷን እያያት ነው
ኤላ አተያይ
ከሻይ ቅጠል እርሻ ዳር ሰው መሆን እየሄደ ነው … ሰው መሆን በድንገት እነ ሳባ ወዳሉበት ቦታ ዞር አለ፡፡ ኮስተር ብሎ በጥርጣሪ ካየ
በኃላ በዝግታ ወደ እነ ሳባ ሄደ፡፡

ኤላ አተያይ
ሳባ በም ደንግጣ ትንፋሷን ፀጥ አድርጋ በፍርሀት እያየችው ነው በደረቷ ደረቱ ላይ ልጥፍ ብላ ተኝታለች፡፡
ኤላ አተያይ
ሰው መሆን ወደነ ሳባ በዝግታ እየሄደ ሳለ በድንገት የሆነች ግልገል በግ ብቅ አለች … አያት በስሱ ፈገግ ብላ በግልጋሏን ካነይት በኋላ
ተመልሶ ሄደ ሳባ በጭንቀት ስታየው ከቆየች በኋላ በረጅሙ ተነፈሰች፡፡ ዞር ብላ ወደ ስሯ ስትመለከት ዳንኤል ፈዞ እያያት ነው፡፡ ዞር
ባለችበት ቅስፈትበጣም ተጠጋግተዋል፡፡ በዝግታ ወደ ጉንጩ ጠጋ ብላ ሳመችው፡፡ በጡቷ ደረቱ ላይ እንደተኛቸች እናያለን፡፡
በፍቅር ስሜት እየተያዩ ነው፡፡ እጁን ወደ ግራና ቀኝ ዘርጋው … እጁን ተከትላ በፍቅር ስሜት ጭብጥ አደረገችው፡፡ ከደረቱ ላይ
ወርዳ በጀርባዋ ተኛች ቀና ብሎ ሻርቧን ከላይ ላይ ሳብ አድረገው የሸሚዙ ቁልፍ ከፍታ ብሎ ደረቱ ይታያል፡፡ ሻርፑ የወደቀበት
አካባቢ ሸሚዙ ሲጣል እናያለን፡፡ እግሩ ከእግሯ ሲጠላለፍ እናያለን፡፡ ሸሚዝና ሻርቧ ያለበት ቦታ ላይ የእነሱን ሁሉንም ልብሶች
እናያለን፡፡

ምንታድ
• ዳንኤል እና ሳባ በዘንባባዎች መሀል እጅ ከእጅ ተያይዘው ሲሄዱ ዝናብ እየዘነበ ነው በዝናብ ውስጥ ሁለቱም ፈገግ
ብለዋል

• ዳንኤል የቤቱ ግቢ ላይ በጀርባው ተኝቶ ሰማዩን ሲመለከት ከአጠገቡ ሳባ ሰማዩን ስትነለከት

46
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

• ዳንኤል የዘንባባ ዛፍ ተደግፎ ቁጭ ብሎ የዘንባባ ቅንጣሽ ይዞ የዘንባባ ቀለበት ሲሰራ እናያለን

• ሳባና ዳንኤል ብርድ ልብስ ውስጥ ሆነው ሲያወሩ ሲስቁ ሲደሰቱ እናያለን … /የእነሱን ንግግርና ሳቅ
አንሰማም/በመስኮቱ በኩል የሚገባው ብርሀን ቤቱ ውስጥ በጣም ደስ የሚል ውበት ፈጥሯል

ሲን 60

ወጪ ዘንባቦች የበዙበት አካባቢ ቀን


ቦታው ቲንሽ የእግረኛ መንገድ አለው መሬቱ ላይ የአበባ በታኞች እና እቅፍ አበቦች በሚያምር ሁኔታ ተደርድረዋል ፡፡ ዳንኤል
የሚያምር አለባበስ ለብሶ ከአበባ ሴትአፑ መሀል ቁሟል ወደ መንገድ እያየ ነው፡፡ ሳባ በጣም የሚያምር አለባበስ ለብሳ ከእግረኛ
መንገዱ ቲንሽ እራቅ ብሎ ካለ እጥፋት ብቅ አለች ፡፡ የአበባውን ሴት አፕ አየች በመገረም አየችው ደስ አላት አበባውን እያየች
መሀል ገብታ ከፊቱ ቆመች፡፡ ዳንኤል በፍቅር ስሜት ሲያያት ከቆየ በዋላ ተንበረከክና ቀና ብሎ አያት፡፡ በእጁ በዘንባባ የተሰራ
ቀለበት እናያለን ቀለበቱን ወደ ሳባ ከፍ አደረገው

ዳንኤል

/ፈቷን አትኩሮ እያየው/

እባክሽ አግቢኝ
ሳባ በመገረም እና ደስ በሚል ስሜት አየችው ዳንኤል በጣም በፍቅር ስሜት እያያት ነው፡፡
ሳባ
አውቃለው ይሄ የአንተ ብቻ ህልም ሊመስልህ ይችላል አሁን የአንተ ብቻ ህልም አይደለም በኔ ሂወት ውስጥ ትናትን
አላስታውሰውም ግን ዛሬ አንተ ከኔ ጋር ስላለህ ትናትን አለማስታወሲ አያስጨንቀኝም፡፡ የኔም ህልም የአንተ ብቻ
የሚመስልህ ህልምን መኖር ነው ፡፡ እና ባክህ አግባኝ

// ወደ ዳንኤል ተጠጋች ፡፡ ዳንአል በደስታ አያት ፡፡ ቀለበቱን አረገላት ደስ አላት ሁልቱም ለረጅም ሰከንዶች ተቃቀፉ፡፡
ከዛ በስስት ተያዩ//

ሳባ
ግን እኮ ዘንባባ ስለሆነ ቀለበቱ ይደርቃል
ዳንኤል

/በስስት ካያት በዋላ/

በሚደርቀው የዘንባባ ቀለበት ውስጥ የሚለመልም ፍቅር አለ፡፡


በቃ ሁሉም ነገር በኔና ባንቺ ስሜት ውስጥ ይጸድቃል እንጂ አይጠወልግም፡፡
ሳባ

/በፍቅር ስሜት/

እኔ ባዶነት ይሰማኝ ነበር አሁን ግን እግዚያብሄር አንተን ሰቶኛል ሙሉ ነኝ፡፡ ሁሌም አብረን መኖር እመኛለው.... ዳኒዬ
በቃ እወድሀለው

/በጣም በሚያምር ስሜት ተያዩ/

ሲን 61

ውጪ የሰውመሆን ቤት ቀን

47
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሰው መሆን የካምፑ ቤት በረንዳ ላይ ሁኖ እየተመለከተ ነው ከተወሰነ ቆይታ በኋላ ሳባ እና እዝራ ሲመጡ እናያለን፡፡ ሳባ
የለበሰችው ከዳንኤል ጋር ቀለበት ስታረግ የለበሰችውን ልብስ ነው፡፡ሁለቱም ሰው መሆን ጋር ደርሰው ቆሙ፡፡

ሰው መሆን

/ኮስተር ብሎ እያያቸው/

ከየት ነው
ሳባ

/የዘንባባ ቀለበቷን በጭንቀት እየነካካች/

አይ … ዝም ብለን እየዞርን
ሰው መሆን
እሺ … አንቺ ግቢ …
እዝራ ግራ በመጋባት አይነት ስሜት አየው … ሳባ በመደናገጥ ስሜት ወደ ቤት ገባች
ሰው መሆን

/በሚያስፈራ ስሜት እያየው/

ይቺ ልጅ በተደጋጋሚ ከዳንኤል ጋር ታይታለች የሚባለው እውነት ነው?

እዝራ

/በፍርሀት ስሜት ካየው በኋላ/

አይ … አይመስለኝም
ሰው መሆን

/ቀና ብሎ እያየው/

አንተና እሱን ከሳባ ጋር ያያችው ሰው ነው የነገረኝ … እየዋሸከኝ እንደሆነ በትክክል


አውቃለው
እዝራ

/መሬት መሬቱን እያየ/

እኔ የማውቀው … በአጋጣሚ ሲገናኙ ሰላም ተባብለው እንደሚያልፉ ብቻ ነው


ሰውመሆን

/በንዴት ከተቀመጠበት በጭሆት እየተነሳ/

አሁንም አትዋሸኝ
እዝራ ደነገጠ … ሰው መሆን የእዝራ ፊት ተጠግቶ አፈጠጠበት
ሰው መሆን

/በሽቆ እያየው/

አንተ ካሳደጉት ውሻ አትሻልም … የበላህበትን ቤት


አስደፍረሀል …

48
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

( አንገቱን አቀርቅሮ በንዴት በሽቶ ዝም ብሏል )

ሰው መሆን

/እያፈጠጠበት/

እውነት እዛ ከወደክበት አንስቼ እዚ ያመጣሁክን እኔን ከካድከኝ


ነብስህን ከስጋህ ነው የማካክዳት
እዝራ አንገቱን እንደቀረቀረ … እናያለን

ሲን 62

ውስጥ የሰው መሆን ቤት ቀን


ሳባ በጣም በተረበሸ ስሜት የበሩን ጥግ ያያ እያዳመጠች እናያለን ስታዳምጥ ከቆየች በኋላ በጣም በተጨነቀ ስሜት ሶፋ
ወንበሩ ላይ ሄዳ ቁጭ አለች

ሲን 63

ውስጥ የዳንኤል ቤት /መኝታ ቤቱ/ ማታ

ዳንኤል አልጋው ላይ ተኝቷል ኮርኔስ ኮኔርኒሱን እያየ በደስተኝነት ስሜት ተኝቷል፡፡ ስልኩ ጠራ ስልኩን አየው፡፡ ግራ
ተጋባ
ዳንኤል

/ግራ በመጋባት/

ሄሎ

ሰው መሆን o/s
/በተቆጣ ስሜት/
እስከ ነገ ይሄን ቦታ ጥለህ ካልወጣሀ እመነኝ አገልሀለው …ከሳባ ጋር የፈጠርከውን ግንኙነት
ሰምቻለው
ዳንኤል

/በዝምታ በኋላ ለተኛበት ተነስቶ/

ልተገለኝ ትችላለህ … ነገር ግን በህይወት እያለው እኔ ብቻ የተፈጠረችን ሴት ልትነጥቀኝ አትችልም

ሲን 64

ውስጥ የሰውመሆን ቤት ማታ/ሳሎን/

ሰው መሆን ካፓርት ለብሶ እየተንጎራደደ ስልክ እየጠራ ነው ፊቱ ላይ የመናደድ ስሜት ይነበባል … ካለሽ
ተቀምጦ እናያለን

ሰው መሆን

/እየተናደደ በብስጭት/

ቆይ አንተ ማን ነህ?

ዳንኤል o/s

49
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ይሄን መጠየቅ ያለብኝ እኔ ነኝ አንተ እራስህ ማን ነህ?

ሰው መሆን

/እየተናደደ/

የኔን ማን መሆን አሳይአለው … ጠብቀኝ


ሰውመሆን በንዴት ስልኩን ዘጋው፡፡ በፍጥነት መሳሪያውን አነሳው፡፡ ሳባ ከክፍሏ ወጣች፡፡ አየችው ደነገጠች፡፡ ሰውመሆን ክላሹን
አንስቶ በፍጥነት ከቤቱ ወጣ፡፡ ሳባ ደንግጣ እየሮጠች ወደ እዝራ ክፍል ገባች፡፡

ሲን 65

ውስጥ የእዝራ ክፍል ማታ


የእዝራ ክፍል በሐይል ተበርግዶ ተከፈተ … እዝራ አልባው ላይ ወቶ ሊተኛ ሲል ባለበት ሁኔታ ደንግጦ ወረደ፡፡ ሳባ በፍጥነት
ገብታ ስታወራ እናያለን፡፡ ድምፅ እንሰማም፡፡ እዝራ ደነገጠ፡፡ ወዲያውኑ ስልክአወጣ ሲደውልና ሲያወራ እናያለን፡፡

ሲን 66

ውጪ የካምፑ መኖሪያ ሰፈር ማታ


ሰው መሆን በጣም በተቆጣ ስሜት ክላሹን ይዞ በፍጥነት እየተራመደ ሲሄድ እናያለን

ሲን 67

ውስጥ የዳንኤል መኝታ ቤት ማታ


የዳንኤል መኝታ ቤት ሰውመሆን በሀያለኛው በሩን በርግዶገባ … ክላሹን ደቅኖ በተቆጣ ስሜት ነው የገባው፡፡ መኝታ ቤት
ውስጥ ዳንኤል የለም፡፡ ሰውመሆን ተናደደ፡፡

ሲን 68

ውጪ መንገድ ዳር ማታ
ዳንኤል የመጣበት መኪና ቁማለች እዝራ እና ዳንኤል ውሰጥ ናቸው ፡፡ የመኪናው አንደኛው በር ክፍት ነው፡፡
ሳባ

/በውጥረት ውስጥ ሆና/

አሁን ሁለታችሁም በፍጥነት ከዚ ሀገር ውጡ


ዳንኤል
አንቺ ካልገባሽ የትም አልሄድም … ድጋሚ ልለይሽ አልፈልግም
ሳባ
/በንዴት እየጮኸች/
ይገልሀል
ዳንኤል
/እየተናደደ/
ይግደለኛ

ከርቀት መሳሪያውን ይዞ ሰው መሆን እየሮጠ ሲመጣ እናያለን


ሳባ

50
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

/ዞር ብላ ሰውመሆን ካየች በኋላ ተጨንቃ/

እባክህ … አምልጡ
ዳንኤል

/እየተበሳጨ/

ድጋሜ ላንለያይ ቃል ተገባብተናል …


ሰው መሆን ከነበረበት እርቀት እየቀረበ እየሮጠ ሲመጣ እናያለን፡፡ሳባ በጣም ተጨነቃለች፡፡ እዝራ ዞር እያለ ሰውመሆንን እያየው
ነው
ሳባ

/እየተጨነቀች በውጥረት ውስጥ ሁና/

እሱ እኮ ወንድሜ ነው … ጥዬው ልሄድ አልችልም


ዳንኤል

/ከመኪናው በንዴት እየወረደ/

እንግዲያውስ አንቺም እኔ ሚስቴ ስለሆንሽ ጥዬሽ ልሄድ አልችልም


ሳባ … በጣም ተረበሸ ስሚት አንዴ ሰው መሆንን በርቀት ወደነሱ እየሮጠ ሲመጣ አይተው ዞር ብላ ዳንኤልን ካየችው በኋላ
በፍጥነት ወደ መኪናው ውስጥ ገባች፡፡ ዳንኤል በፍጥነት የመኪናዋ ሹፌር ቦታ ላይ ገባ፡፡

/ኤላ አላያይ/

ሰው መሆን ክላሹን እየሮጠ ወደ መኪናዋ ሲተኩስ እናያለን


ኤላ አተያይ
ዳንኤል እዝራ ሳባ በውጥረት ውስጥ ናቸው፡፡ ዳንኤል መኪናዋን ሊያስነሳ ሲል ሞተሩ እምቢ አለው፡፡ እየተተኮሰባቸው ነው
ኤላ አተያይ
ሰውመሆን ወደ መኪናዋ በቅርብ እርቀት ሁኖ እየተኮሰ ሲሮጥ እናያለን
ኤላ አተያይ
ዳንኤል መኪናዋን ሊያስነሳ ሲታገል እናያለን እዝራና ሳባ ወደ ሰው መሆን በጭንቀት ዙረው ሲመለከቱ እናያለን ሰው መሆን
ቀርቧል ዳንኤል ግንባሩን አልቦታል በጭንቀት ውስጥ ሁኖ የመኪናዋን ቁልፍ ሲሞከረው ተነሳ በፍጥነት ነዳት መኪናዋ ሄደች ሳባ
መኪናዋ ውስጥ ሁና በተረበሸ ስሜት ሰውመሆን አየችው እዝራ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡ ዳንኤል ላቡን ከተነፈሰ በኋላ ጠረገ

ኤላ አተያይ
ሰውመሆን በጣም በተበሳጨ ስሜት መኪናዋ ስትሄድ አያት … ተናዷል ስልኩን በፍጥነት አወጣ፡፡ በፍጥነት ደወለ፡፡

ዳንኤል o/s

የሚገባኝን አግኝቻለው … ብዙ በኋላ አትልፋ


ሰው መሆን

/የእልህ እንባ እየተናነቀው/

እሺ አሁን ልለምንህ … ተሸነፊያለው እሷን ምንም እንዳታረጋት … እባክህ

ዳንኤል o/s

አሁን እውነት ለሷ ያዘንክ አይመስልም ሌባ

51
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ስልኩ ተዘጋ … ሰውመሆን በህል እንባ ሲተናነቀው እናያለን

ሲን 69

ውጪ አዲስ አበባ መግቢያ ጠዋት


የዳንኤል መኪና እየተነዳች እናያለን እዝራ ከዋለኛው ወንበር ላይ ተኝቷል፡፡ ሳባ በተደከመ ስሜት ከዳንኤል አጠገብ ቁጭ
ብላለች፡፡ ዳንኤል በጣም በተደከመ ስሜት እየነደነው ወደ አዲስ አበባ ደህና መጣችሁ የሚል ታፒላ እናያለን ዳንኤል በፈገግታ ሳባን
ካያት በኋላ በዘንባባ ቀለበት አውቶ ሰጣት የደረቀውን አውልቃ አዲሱን አረገችው፡፡ ፈገግ ብላ አየችው

ሲን 70

ውስጥ የድሮው የዳንኤልና የሄለን ቤት ቀን


ቤቱ ሰው የለበትም የዳንኤል የሄለን ፎቶዎች እንደተሰቀሉ ነው ቤቱ ተከፈተ ዳንኤል ሳባና እዝራ ገቡ፡፡ ሳባ የእሷን መልክ እና
የዳንኤልን ፎቶዎች አየች፡፡ እዝራ ቤቱን አየው፡፡

ዳንኤል

/ሳባን ጉንጯን ከሳማት በኋላ/

እንኩዋን ወደ ቤትሽ በሰላም መጣሽ


ሳባ

/አንዴ እሱን አንዴ ፎቶዎችን ካየች በኋላ/

ፎቶዎቹ ያምራሉ
እዝራ

/የወሽት በመብሰቅ /

ግን የኔ ፎቶ የለም
ዳንኤል

/እየሳቀ/

አይዞህ ከዚ በኋላ ይኖራሉ


ሁሉም ሳቁ

/ከአንድ ወር በኋላ/

ሲን 71

ውስጥ የዳንኤል ጎደኛው መሳፍንት ቤት ማታ


ቤቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ ቤት ነው፡፡ ጠረጴዛ ላይ የተለያዩ ምግቦችና መጠጦች እናያለን፡፡ እዝራ ዳንኤል ሳባ መሳፍት ሆነው
ጠረጴዛውን ከበው ቁጭ ብለዋል፡፡ ሁሉም እየሳቁ እየበሉ እየጠጡ ነው፡፡

መሳፍንት
እውነት ዳንኤል እድለኛ ነው …
እዝራ

52
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

እኔ ነኝ እንጂ እድለኛ ያልሆንኩት … ለፍቅር ስል ከኢንቨርስቲ ተጭሬ እዝራ ጭረቱ አንድ ላባቱ
የሚል ስያሜ ይዜ ከሀገር ሀገር ብሰደድም የእነ ዳኔን ፍቅር እንጂ የራሴን አላገኝሁትም

ሁሉም ሳቁ
እዝራ

/ሳቃቸውን ከጨረሱ በኋላ/

ለነገሩ … የማፈቅራት ልጅ ተጭራ ወታ የት እንደሄደች ሰጣት እኔም መማር ከብዶኝ


ተጫርኩኝ … ምን አለፋችው የኔ ፍቅር ጭረት በጭረት ነው
በድጋሚ ሳቁ
እዝራ
አሁን እሷ ሌላ እንደገባች ሰምቻለው ይገርመኛል እኔና አባቴን ብዙ ጊዜ ሴቶች

ይክዱኛል አይወዱንም.. እኛ ግን እንወዳችዋለን

በድጋሚ ሁሉም ሳቁ

እዝራ

/የመጠጥ ብርጭቆውን ከፍ እያደረገ/

አሁን እባካችሁ መጠጡን ከፍ አደረጉት


መሳፍንት

/ሳባን እያየ/

ከፍ አርጌው እንጂ?

ዳንኤል
አይ እሷ ይቅርባት … ዛሬ ተመርምራ የሁለት ወር እርጉዝ እንደሆነች ተነግሮናል

መሳፍንት እዝራ
/በደስታ/ /በደስታ/
በጣም ደስ ይላል እንኩዋን ደስ ያላችው

ዳንኤል

/መጠጡን ከፍ እያደረገ/

አሁን ለሚስቴ ለልጄና ለናንተ ክብር ችርስ

( ሁሉም ከፍ አድርገውት ብርጭቆውን አገጩት ሳባ በደስታ ካየቻቸው )

ሲን 72

ውጪ መንገድ ላይ ቀን

53
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሰውመሆን ካፓርት አድርጎ ከፍያ አጥልቆ አጎንብሶ አንድ ጥግ ቆሟል… ወደ አንዴት መኪና እየተመለከተ ነው መሳፍንት ከመኪናዋ
ፊት ካለ ህንፃ ሲወጣና ወደ መኪናዋ ሲሄድ እናያለን፡፡ ሰው መሆን በፍጥነት ተራመደ መሳፍንት መኪናዋን ከፍቶ ገባ፡፡ ሰው መሆን
በፍጥነት ሂደ ሁለተኛውን በር ከፍቶ ወደ መኪናዋ ገባ፡፡ ሰው መሆን ከወገቡ ሽጉጥ አወጣና ከልሎ ደቀነበት፡፡ መሳፍንት ደነገጠ

መሳፍንት

/በድንጋጤ/

ምንድን ነው?

ሰውመሆን
ዳንኤልን የምታገናኝ አንተ ብቻ እንደሆንክ አውቃለው በፍጥነት ወደሱ ውሰደኝ መሳፍንት
ደነገጠ

ሲን 73

ውጪ የዳንኤል ቤት ግቢ ቀን
ዳንኤል ስልክ እያወራ ወደ ግቢው ሲገባ እናያለን … የሳሎኑ በር ገርበብ ተደርጎ ተከፍቷል፡፡
ዳንኤል

/ስልክ እያወራ እየሄደ/

እሺ … እስከዛ ከእዝራ ጋር ሁን … ካሜራ ይዤ መውጣት ብቻ ነው

ሳባ o/s

ቶሎ በል … ቁልፍ … ከበሩ ስር አስቀምጫ

ስልኩን እያወራ በሩን ተመለከተ ….በሩ ገርበብ ተደርጎ ተከፍቷል ዳንኤል በሩን እያየ በጥርጣሬ ስሜት እየሄደ እናያለን

ዳንኤል

/ወደ በሩ በጥርጣሪ እያየ/

እሺ …
ስልኩን ዘጋው … በዝግታ ወደ በሩ ሄዶ

ሲን 74

ውስጥ የዳንኤል ቤት ቀን
የዳንኤል ቤት ውስጡ ዝም ባለ ሁኔታ የአንዲት ሴት የለቅሶ ድምጽ ብቻ ይሰማል … ሴቷ ጀርባዋን ሰታ ቁማለች በእጇ የፎቶ
ፍሬም ይዛለች፡፡ ዳንኤል በዝግታ ወደ ውስጥ ገባ የሴቷን የለቅሶ ድምፅ ሰምቶ ዞር አለ፡፡ ከኋላዋ ብትንትን ያለ ፀጉር ያላት ሴት
ናት፡፡ ስቅ ስቅ ብላ እያለቀሰች ነው ዳንኤል በፍርሀት ጠጋ እያለ ነው፡፡

ዳንኤል

/በአትኩሮት እያያት/

ማን ነሽ?

ሴቷ በዝግታ በጣም በተጎዳ ሁኔታ ዞር አለች፡፡ ፊቷ በጣም የተጎዳ ነው፡፡ ጉንጯ ላይ ጠባሳ አለ … እንባ በጉንጫ እየወረደ ነው
የያዘችው ፎቶ የሄለንና የዳንኢልን ፎቶ ነው … እርጅም የአረቦችን ቀሚስ አርጋለች፡፡ እርጉዝ ነች፡፡ ሔለን በእንደዚ አይነት ፍጹም
በተጎዳና በተንገላታ በሚመስል ሁኔታ ውስጥ ሁና እናያታለን እያለቀሰች በዝግታ ዞር ብላ ዳንኤልን አየችው … ዳንኤል በተረበሽና
ግራ በተጋባ ስሜት ድርቅ ብሎ አያት

ሔለን

54
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

/በተዳከመ ድምፀት እንባ እየወረዳት/

ዳኔዬ …. ሔለን ነኝ

ዳንኤል … በፍጹም ድንጋጤ ውስጥ ሁኖ እያያት ነው … ሔለን ወደ ዳንኤል ከሄደች በኋላ አቀፈችው፡፡ እረጅም ሰከንድ
ካቀፈችው በኋላ ቀና ብላ ፊቱን አየችው

ዳንኤል

/በተረበሸ እና ግራ በታገባ ስሜት/

ሳባ እየቀለድሽብኝ ነው?...

ሔለን

/ግራ በመጋባት እንባ ከአይኗ እየወረደ ፊቱን እያየችው/

ምን ሁነህብኛል? … እኔ እኮ ሔለን ነች … አልናፈኩህም ብዙ ኔዜ እኮ ነው የተለያየ ነው ዳንኤል ድርቅ


ብሎ ሔለንን እያያት … እንባ አይኑ ላይ ሙልት አለ

ሔለን

/እያለቀሰች/

ይሄን ያህል ጊዜ ስጠፋ እኮ ፈልጌው አይደለም ሽፍቶቹ … ሁሉንም ገለው


እኒንና ሦስት ሴቶችን አስገድደው ደፈሩን … ሁለቱ እዛው ሞቱ … ከሸፍቶቹ አንዱ
ይሄን ያህል ጊዜ አንድ ቤት ውስጥ አሽጎብኝ ሚስቱ አድርጎ አኖረኝ
ዳንኤል ፍጽም ድርቅ ባለበት ስሜት ውስጥ ሁኖ እንባ ከአይኑ ወረደ
ሔለን

/እያለቀሰች እያየችው/

ቀን በቀን አስብአለው … … ደውዬ እንኳን ላገኝኅ


አልችልም …ሁሉም ንገር ጨለማ ነበር በስቃይ ውስጥ ሁኜ አንተን ነው የማስብህ
ዳኒዪ ናፍቀኀኛል ቆይ እሺ ምን ሆንክ አልተረዳሃኝም
ዳንኤል

/እንባ እየፈሰሰው … አይን አይኗን እያየ/

ምን ብዬ አወራለው … እኔ ሳቅፍሽ ነው የኖርኩት … ከታለየሽኝ ከተወሰነ ጊዜ በኋላም


እስከ ዛሬ ከኔ ጋር ነበርሽ … አሁን እኔ ነኝ የሞትኩት
ሔለን

/ግራ በመጋባት እያየችው/

ምን እያልክ ነው? አልገባኝም?

ዳንኤል በጣም በተሰበረ ስሚት አያት

Fillsh back in
ሲን 20

ውስጥ ጎዳ ቀን

55
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

የሔለን እናት የሀዘን ልብስ ለብሰው … ፀጉራቸውን ሲላጩ ዳንኤል በተሰበረ ስሜት ሲያያቸው

ሲን 35

ውጪ የሻይ ቅጠሉ ማሳ - ምሳ ሰዓት

ዳንኤል ካሜራ ሊያነሳ ሲል ሳባ የካሜራው ፍሬም ውስጥ ስትገባ … ዳንኤል በድንጋጤ ሲያያት

ሲን 53

ውጪ ጫካ ውስጥ ጠዋት
ዳንኤል ደስ አለው … በደስታ እያያት … እንባው ግጥም አለ ሌላ የሀብል ማስቀመጫ አወጣና የብር ሀብሉን
አደረገላት

ሲን 59

ውጪ የሻይ ቅጠሉ ማሳ ላይ ቀን
ዞር ባለችበት ቅፅፈት በጣም ተጠጋግተዋል … ከደረቱ ላይ በጡቷ ተኝታለች ሲተያዩ ከቆዩ በኋላ ጉንጩን
ሳመችው … የሁለቱንም ልብሶች ከተኙበት የሻይ ቅጠል እርሻ ላይ ተቀምጠው እናያለን

ሲን 71

ውስጥ የዳንኤል ቤት ማታ
ሁሉም መጠጣቸውን ከፍ አድርገው ይዘዋል … ሳባ ፈገግ ብላ እያየቻቸው ነው
ዳንኤል
አሁን ለሚስቴ ለልጄና ለናንተ ክብር ችረስ
ብርጭቆውን ሲያጋጩት እናያለ

Fillsh back u

ሲን 74

ውስጥ የዳንኤል ቤት ቀን
ዳንኤል በጣም እያለቀሰ ቁሟል … ሔለን ተስፋ በቆረጠና ግራ በተጋባ ስሜት እያየችው ነው
ዳንኤል

/እያለቀሰ እያያት/

እኔ አንቺን እንደገኘሁሽ ነው የማውቀው


አቀፋት ስቅ ስቅ ብሎ አለቀሰ ከተወሰነ ሰከነዶች በዋላ … በሩ ተከፈተ ሳባ ገባች … ዳንኤል እና ሔለን ተቃቅፈው አየች፡፡
ሳባ በትንትን ባሉ ፀጉር የተሸፈነው የሔለንን ፊት እያየች ደነገጠች ሔለንም ቀና ብላ ሳባን አየቻት ሳባ ፊንት ሰርታ ወደቀች

/የኦዲስ አበባ ከተማ ከምሽት ወደ ንጋት ትታያለች/

ሲን 75

ውስጥ የእነ ዳንኤል ቤት ጠዋት


ሔለን ዳንኤል …መሳፍንት ሰውመሆን እዝራ በጣም በተጨነቀ ስሜት ቁመዋል … ሰውመሆን የሄለንን እናት ፎቶ ይዟል

56
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሰው መሆን

/ከተወሰነ ጭንቀት በኋላ/

አዎ የሳባም እናት እሷ ነች … ነገር ግን አንድ ሳባን


እንደወለደች ነው እኛ የምናውቀው
ሔለን

/በጣም በተከፋ ስሜት/

እናቴ ለአንድ ቀንም ቢሆን መንታ እህት እንዳለኝ ነግራኝ አታውቅም ነበር …
ሰውመሆን

/ሔለንን እየተመለከተ/

አባታችን ክፋ ሰው ነበር ብዙ ሴቶችን ያገባል … ነገር ግን የሚያገባው


ልጁ ወልዳውለታ ከቤቱ እንዲወጡ ነው፡፡ልጆቻቸውን እንጂ እነሱን ፈልጎ አያውቅም ምን አልባት
ከዚ ጋር የተገናኘ ሊሆን ይችላል የናትሽ ሚስጥር

ሔለን … ሰውመሆን መሳፍንት እዝራ በጭንቀት ውስጥ ናቸው


ሔለን

/በተሰበረ በተጎዳ ሁኔታ/

እሺ … አባታችንስ የት ነው ያለው?

ሰው መሆን

/በዝምታ ካያት በኋላ/

ገድየዋለው … እናቴን እንደገደለብኝ ሳውቅ ገድየው እንደ


ባሪያ ያሣደጉዋትን ሳባን ብቻ እወዳት ስለ ነበረ ይዤያት
ጠፋሁ … እኔንና እሷን የአባቴ
ዘመዶች ገለነው ሊበቀሉን ይፈልጉ ነበር … ሳባን የእሱ ዘመዶች በመኪና
ገጭተው ሊገሏት ፈልገው በአጋጣሚ ተረፈች ከዛ በኋላ ነው
ትምህርቷን አቋርታ እኒ ጋር ያመጣዋት
ከዳንኤል መኝታ ቤት አንድ ዶክተር ወጣ … ሔለንና ዳንኤል ወደ ዶክተሩ ሔዱ … ዶክተሩ ጋወኑን እየቀየረ
ዶክተሩ

/ወደ ሄለን እያየ/

በቃ መዳኒቷን ወስዳለች የሚብስባት ከሆነ ወደ ሆስፒታል ውሰዷት …


አሁን ሔለንን ማውራት ትፈልጋለች፡፡
ዳንኤል
እሺ አመሰግናለው …
ዶክተሩ ወጣ

57
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሲን 76

ውስጥ የዳንኤል መኝታ ቤት ጠዋት


ሳባ በጣም በተረበሸ ስሜት ተኝታለች … በሀዘን ስሜት ውስጥ ነች በሩ ተከፈተ … ሔለን ገባች፡፡ ሳባ በዝግታ ወደ ሔለን
አየች … ሔለን ወደ ሳባ ከተጠጋች በኋላ አልጋዋ ጫፍ ተቀመጠች

ሔለን

/በስሱ ፈገግ ብላ/

አንቺን የመሰለ እህት እያለኝ ነው … እህት እንደሌለው ብቻዬን ያደኩት …


ሳባ
/እያለቀሰች/
እውነት ለአንድ ቀን መንታ እህት እንዳለኝ ተነግሮኝ አያቅም …
ሔለነ

/እያለቀሰች/

አይዞሽ በኛ በህይወት አጋጣ ውስጥ እንደዚ ሆነ


የሆነውን ነገር እንርሳው … አሁን ተገናኝተናል ቢያንስ
አይቺሻለው … በዳኔኢልና ባንቺ ሂወት ውስጥ ስለተፈጠረው ሁሉ
አታስቢ

( እጅ ለእጅ ተያያዙ )

ሳባ

/እያለቀሰች/

በድየሻለው
ሔለን

/እያለቀሰች የሳባን እንባ እየጠረገች/

አውቀሽ ነው የበደልሽኝ … ዳንኤልስ አውቆ ነው በአንቺም በሱም አልፈርድም … ግን በቃ


እንዳልኩሽ በኛ ሂወት ውስጥ እንደዚ ሆነ ማንንም ልከስ ማንንም ልወቅስ አልችልም
ሳባ ከተኛችበት ተነስታ እዛው ባለችበት እንደተቀመጠች ሔለንን አቀፈቻት ለረጅም ሰኮንዶች ተቃቀፉ … ሔለን እንዳቀፈቻት
አለቀሰች ሳባም እንዳቀፈቻት አለቀሰች

ሲን 77

ውጪ ቤተ ክርስቲያን ቀን
ቤተ ክርስቲያን ግቢ ውስጥ የተለያዩ ምእመን እናያለን … ሄለን እና አንድ አባት ከቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ካለ ወንበር ላይ ተቀምጠዋል
ቄስ

/ወደ ሔለን እያዩ/

መለኩሴ እኮ ደብር የለውም … ምን አልባት እሳቸውም የገቡበትን ገዳም


ቀይረው ይሆናል … ስለዚ አትልፋ

58
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሔለን

አባ … እሳቸውን ማግኘት ግድ ነው? ልጃቸው በሔወት እንዳለች ሊያውቁ ይገባል

ቄስ

/ትንሽ ካሰቡ በኋላ/

እሺ … እንግዲያውስ ወለተ ማርያም … እንጦስ ገዳምእንዳሉ አውቃለው ነገር


ግን ወተም ሊሆን ይችላል
ሔለን አየቻቸው …

ሲን 78

ውጪ የእንጦስ የሴቶች ገዳም ቀን


የእንጦስ የሴቶች ገዳም በጣም በሩቅ ትታያለች፡፡ ገዳሟ ሀይቅ መሀል ያለች ገዳም ነች፡፡ ዳንኤል ሳባ ሔለን ሰውመሆን ግራ
በመጋባት እናያችዋለን ከነሱ ፊት አንዲት መለክሴ በቁጣ ሲናገሩዋቸው እናያለን

ሞለክሴዋ

/በቁጣ እያዬቸው/

ምነው … እግዜአብሄርን የተጠጋን ሰው ልብ ልታሸብሩ ነው … እዚ ድረስ የመጣችሁት


ልጆቼ እሳቸው እግዜአብሔርን እያገለገሉ ነው … ተሳልማቸው ሒዱ
ሁሉም ግራ በመጋባት ቁመዋል … መሎክሴዋ ሂደው ከሌላ ሁለት ሞለክሴ ጋር ሲያወሩ እናያለን፡፡ ድምፃቸውን
እንሰማም … ሔለን ተስፋ በቆረጠ ሁኔታ ዞር ስትል እናቷን አበበችን የሙልክሴ ልብስ ለብሳ የፀሎት መፅሀፍ ይዛ
አየቻቸው ሔለን አለቀሰች ሁሉም በሔለን እይታ ሲያዩ መለኩሲዋነ አበበችን አዩዋቸው…
ሔለን

/እያለቀሰች እናቷን አንገቷን አቀርቅራ ልታልፍ ስትል/

እማ

እናት በድንጋጤ ቀና አሉ ፡፡ ቆሞ፡፡ ሳባን እና ሔለንን አዩ ደነገጡ … በቆሙበት እንባ አይናቸው ላይ ከረረ

Fillsh back in

ሲን 79

ውስጥ የገጠር ማዋለጃ ቦታ ቀን


ቦታው ደሳሳ ቦታ ነው … ቤቱ በጣም የሚያስጨንቅ ቤት ነው እናት በተዳከመ ሁኔታ መደቡ ላይ ተኝታለች … ነጭ ቀሚሷ በደም
ርሷል፡፡ አንድ አዋላጅ እጇን የነካትን ደም በጨርቅ እየጠረገች ነው፡፡ ሁለት ሴት ህፃናት መደቡ ላይ ይታያሉ ….

እናት

/ወደ አዋላጇ በተዳከመ ስሜት እያየች/

አባታቸው መንታ እንደተወለደላት አውቋል?

አዋላጅ
አይ አላወቀም … ምጥ ላይ እንደሆንሽ ለሰው ልኬበታለው

59
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

እናት

/በተጨነቀ ስሜት/

እየመጣ ነው እንዴ?

አዋላጅ

አዎ … ምነው ?

እናት

/በሚያሳዝን ስሜት/

እባክሽ … እሱ ከመጣ ልጆቼን ወስዶ እኔን ያባርረኛል …

አዋላጅ

/ግራ በመጋባት/

እና … እኔ ምን ላርግ
እናት
ልጆቼን ይዤያቸው ልጥፋ
አዋላጅ ግራ በመጋባት አየቻት
አዋላጅ

እሱ ጨካኝ እንደ ሆነ እና ለኒም የማይመለስ እንደሆነ እያወቅሽ … እንዳስጠፋሁሽ ሲያቅ ዝም አይለኝም ?

እናት በጣም በመጨነቅ አየቻት አለቀሰች … ልጆቿብ አየቻቸው


እናት

/እያለቀሰች/

እባክሽ የወላድ መሀን አታርጊኝ … እባክሽ …አዋለጇ አዘነች … ስታስብ እናያለን


አዋላጅ
አንድ ነገር ልተባበርሽ … አንዷን ውሰጂያት
እናት
/እያለቀሰች/
እንዴት ብዬ … አንዷንስ ለማን ጥዬ
( ከውጪ የጥይት ተኩስ ተሰም )
አዋላጅ
/በችኮላ እያየቻት/
አሁን እየመጡ ነው ወስኚ
እናት
/እያለቀሰች/
እሺ… አንዷንም ቢሆን ስጪኝ
አዋላጇ አንዷን ሴት በፍጥነት በፎጣ አንስታት ወደ ጎዳ አስገባቻት፡፡ አስገብታት እንደተመለሰች የእነ ሔለን አባት ወደ ውስጥ ገቡ
መሳሪያ ይዘዋል በጣም የሚያስፈራ ተክለ ሰውነት አላቸው፡፡ እንደገቡ ሳባን እንደተወለደች አዩዋት

አባት

60
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

( በተበሳጨ ስሚት)

ሴት ነች እንዴ
አዋላጅ
አዎ
አባት

/ወደ እናት እያዩ/

ወንድ መስሎኝ ጥይት ሳባክን ይቺ እርኩስ ያለመደብኝን ሴት ወለደች …

( እናት እያለቀሰች ነው )

አባት
ብትሆንም ዘሬ ነች … የወንዶቹ አሸከር ትሆናለች …
እናት

/እያለቀሰች/

ስለፈጠረህ … ልጄን ስጠኝ


አባት

/ምራቃቸውን ወደ መሬት ከተፉ በኋላ/

ከዚ በኋላ ልጄን እንዳትይ … ከዚ አካባቢ


ካየሁሽ በህይወትሽ ፍረጂ … እገላግልሻለው እኒ ሲቶችን ወይ ባሪያ ሁነው ወይ ከአፈር በታች
ሁነው ነው ማየት እምፈልገው በናተ ነው ወጣትነቲን በስቃይ ያሣለፍኩት

( እናት አለቀሰች …)

አባት

/ወደ አዋላጇ እያዩ/

በይ አንቺ ህፃኗን ይዘሽ ተከተይኝ


እናት ስቅ ስቅ ብላ እያለቀሰች ነው፡፡ አዋላጅ አንዴ እናትን አንዴ ህፃኗን ካየች በኋላ ህፃኗን ይዛት ከአባት ጋር
ተከታትለው ወቱ እናት በመረረ ሀዘን አለቀሰች

Fillsh back u

ሲን 78A

ውጪ ገዳም ቀን
እናት በጣም በተረበሸ ስሜት እያለቀሱ ነው፡፡ ሁሉም እያለቀሱ ነው
እናት

61
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

/ወደ ሔለን እያየች እያለቀሰች/

እንዴት ብዬ የኔን ጭካኔ ልንገርሽ እንዴት ብዬ እህትሽን ገረድ ሊያረጋት ላስብ


ሀረመኔ ሰው ትቻት እንደመጣው ልንገርሽ እስካሁን በስቃይ ውስጥ ነበርኩኝ …
እግዜአብሔርን ደስተኛ ሁኜ ያገለገልኩበት ጊዜ አልነበረም
ሁሉም እያለቀሱ ነው
እናት

/ወደ ሳብ እያዩ እያለቀሱ/

እኔኮ እናትሽ አይደለሁም


ሳባ

/እንባዋን መቋቋም እየከበዳት/

እንደዚ አትበይ

እናት
/እንደ እብድ እየጮኸች/
እላለው እኔ ጨካኝ ነኝ … በመሀፀኔ አቅፊሽ በእጄ ያልዳበስኩሽ ጨካኝ ነኝ … ከእህትሽ ነጥዬ
ያኖርኩሽ ጨካን ነኝ
ሞለክሴዎቹ በፍጥነት መተው እናትን ያዟቸው እናት እየጮከች /ጨካኝ ነኝ/ እያሉ በመለኩሴዎቹ እየተጎተቱ ሂዱ … ሳባና ሔለን
እናትን እያዩ ስቅ ስቅ ብለው እያለቀሱ ነው
ሲን 80
ውስጥ የሞለክሴዎች ማረፊያ ቀን
እናት በመለኩሴዎቹ ትግል እየተጉተቱ ወደ ውስጥ ገቡ … እያለቀሱ ነው
ሲን 81
ውጪ የገዳሙ ግቢ ቀን
ግቢ ውስጥ የተለያዩ ምዕመናት ይታያሉ፡፡ ዳንኤል እና ሰው መሆን ቁመዋል ሰው መሆን እንባ እየተናነቀው ነው፡፡
ሰውመሆን
/በእልህ ስሜት እንባ እየተናነቀው/

ያንን ክፉ አባታችንን አይደለም አንድ ሞት አስር ጊዜ


ብገለውም አረካም
ዳንኤል

( በሀዘን )

አይዞህ … እኔ ግን እስከ ዛሬ ስላልተረዳሁክ ይቅርታ


ሰውመሆን
ሁለታችንም እውነትን ስንከተል ተገፋፍተናል … ስለኔ አትጨነቅ … ግን ካጠፋሁ ይቅርታ
እርሶ በእርስ ተያዩ

ሲን 82

ውጪ የሞለክሴዎቹ ቤት የውጪ በር ቀን
ሳባ እና ሔለን ከአንዲት ሞለክሴ ጋር በራፍ ላይ ቁመዋል እያለቀሱ ነው ሞለክሴዎ እያበበላቻቸው ነው

62
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሳባ

/እያለቀሰች/

እባክዎትን እናቴን በደንብ ልያት

ሞለክሴ 2

አይሆንም ይሄንን እንደ እሳቸው ፍቃድ ነው ይደ አብራችው


ትሄዳላችው ወይ ሞለክሴዋ እዚ ይቀራሉ
ሔለን እያለቀሰች ዝም እንዳለች ነው

ሲን 83

ውስጥ የሞከክሴዎቹ ማረፊያ ቀን

እናተ በጣም በሚያሳዝን ስሜት ዝም ብለው ከአይናቸው እንባ እየወረደ እያለቀሱ እናያለን፡፡ መለኩሴ 1 ከፊታቸው

ሁነው እናያለን
ሞለክሴ

/ወደ እናት እያዩ/

አሁን መወሰን አለበዎት … በነሱ ሰላም አታው እግዜአብሄርን ማገልገል ካልቻሉ


አብረዋቸው ከገዳሙ አስተዳደሪ ተሰውረው ሂዱ … አይ እግዚአብሄርን
ላገልግል ይሄ የዲያቢሎስ መንፈስ ሊያስተኝ ነው ብለው ካሰቡ ደሞ ያነሱና ያሰናብቷቸው
ሁለቱም ዝም አሉ

ቢን 84

ውጪ የምለክሴዎቹ ማረፊያ በር ቀን

ሳባ ሄለን ዳንኤል ሰውመሆን ከሞለክሴ 2 ጋር ቁመዋል አሁንም ሳባና ሔለን እያለቀሱ ነው … ከተወሰነ ሰከንድ በኋላ እናት ከቤቱ
ወተው ቆሙ፡፡ ሳባ እና ሔለን ወደ እናት መሔድ ጀመሩ

እናቱ
/በጣም በስስት እያያቸው/
ልጆቼ እንዳታቅፉኝ

ሳባና ሔለን ግራ በመጋባት ቆሙ ሞለክሴ 1 ወተው እነ ሳባና ከናት መሀል ቆሙ

እናት
አሁን ይሄን ሁሉ በቸርነቱ ያደረገን አምላክ እያመሰገንኩት ልኑር በሱ ቸርነት አይደል
ያየዋችው
ሔለን
/በጣም በተረበሸ ስሜት/
ከኛ ጋር አትሄጂም
እናት

/ሔለንን እያየቻት/

ከእግዜያብሄር እቅፍ ውስጥ ነኝ … ከእቅፋ ወጥቼ እናትን ብከተል ወደ እሱ አልመለስም

63
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሳባ
/እያለቀሰች/
እሺ አንዴ ልቀፍሽ
እናት
/እያለቀሰች/
አንቺ ማቀፍ እኮ የዚ አለም ትልቁ ፍላጎቴ ነበር ባቅፍሽ ብስምሽ ደስ
ይለኛል … ግን አንቺን ሳቅፍሽ ከእግዚአብሄር እቅፍ ውስጥ መውጣት ያምረኛል …
ሞለክሴ 1
/እያዘኑ/
በቃ ሂዲ
ሳባና ሔለን አለቀሱ ሰውመሆን ሳባን ዳንኤል ሔለንን ይዘው ለመሄድ ሲሞክሩ ሁለቱም እየታሉዋቸው ሲያለቅሱ እናያለን
እነ ዳንኤል ተረብሸው እየጎተቱዋቸው ነው

ሳባ ሔለን
/እየታገለችው እያለቀሰች እየጮሕች/ /እያለቀሰች/
እቀፊኝ … እናቴ እቀፊኝ ….. ደህና ሁኚ እናቴ እወድሻለው

እናት በጣም በተሰበረ ስሜት ደሳሳዋ የሞለክሴዎቹ ቤት


በራፍ መግቢያ ጋር እንደቆሙ እያለቀሱ በአይናቸው ሸኙዋቸው
ሞንታጃ

• የእናት የድሮው ቤት ዝግ ከነበረበት ሲከፈት … ሳባ ስትገባ … ከእሷ ጋር ዳንኤል እና ሰውመሆን ሲገቡ ሳባ

የናቷን ፎቶ አንስታ ስስም

• ሔለን የእሱ ቤት ውስጥ ሁና እረጅም አጀንዳ ላይ ስፅፍ … እናያለን

• ዳንኤል ብቻውን ሁለት መታጠፊያ ያለው ቦታ ላይ ግራ በመጋባት ቁሞ እናያለን

• አንዲት ህፃን ልጅ እግሯን ከፍታ ቁማ አንድ ታዳጊ ህፃን ልጅ በእሷ እግር ሎጬ ኳስ ሲያሾልክ

• ሔለን መሳቢያ ስከፍት ብዙ በዘንባባ የተሰሩ ቀለበት ደርቀው ስታይ እናያለን

ሲን 85

ውስጥ የእነ ዳንኤል ቤት ማታ


ዳንኤል ከመሀላቸው ሁኖ ሔለን በቀኝ ሁነው የአልጋውን ትራስጌ ታደግፈው ቁጭ ብለዋል
ሔለን
/በስሱ ፈገግብላ/
ወደዚ ስመጣ የላከኝና ያስመለጠኝ መጀመሪያ የደፈረኝ ሽፍታ ነው … እኔ አሸንፊው ነበር በቃ ሂጄ ያለኝ …
ያረገዝኩት ልጅ የሱ ነው
እና ሲልከኝ እኔን የለወጥከኝ ሴት አንቺ ነሽ እርግጥ እኔ ማንንም አልገደልኩም ሽፍታ የሆንኩት ወድጄ
አይደለም ካመንሽኝ … አንድ ቀን መተሸ ልጄን አሳይኝ ብሎኝ ነበር … እኔ ከንግዲ የኖርኩለት ፍቅር ሳይሆን
የልጄ አባት ሚስት ነኝ የልቤን ሳይሆንም እግሬ ተገዶ ወደ ገባበት ቤት ልሂድ

ዳንኤል
/በተከፋ ስሜት እያያት/
ምን እንደምል አላውቀም … ሁሉም ባዶ ሆኖብኛል
ሳባ ከኔ አርግዛለች … አንቺ ስትጎጂ ማየት እና ተመልሰሽ

64
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ስትሄጂ ማየት አልፈልግም


ሔለን
/አትኩራ እያየችው/
እግዜአብሄር በኔም በአንተም በሳባም አይፈርድም ይሄ የልባችንን ስንከተል የደረሰንበት ቦታ ነው
ዳኔዬ በሆነው ሁሉ ራስህን እንዳትወቅስ የኔን አለም ከሌላ ያፅናልኝ ያንተንም ፍቅር ከምወዳት እህቴ ጋር
ለዘላለም ያኑርልኝ

ዳንኤል
/በሀዘን እየተረበሸ/
እወድሻለው
ሔለን
/አቀፈችው/
እኔም ሁሌም እወድአለው አልረሳህም
ተቃቀፉ ለረጅም ሰከንድ ተቃቀፉ

ሲን 86

ውስጥ የእነ ዳንኤል ቤት ጠዋት


የእነ ዳንኤል ቤት ሳሎን ላይ አንድ መዝገብ እናያለን መዝገቡ ላይ የታጠፈ ወረቀት እናያለን ጁስ እና ኩረስ ምግቦች እናያለን፡፡
ዳንኤል በእንቅልፍ ስሜት ከመኝታ ቤቱ ወጣ ወደ ሳሎን ሲገባ እናያለን ዳንኤል በአጋጣሚ በፀሀፉን አየው ሄዶ ወረቀቱን አንሳት
ዘርግቶ ማንበብ ጀመረ

ሔለን V/O

ደና አደራችው ኩርስ ብሉ እሺ ዳንዬ አቅፌህ ልሰናበትህ አልቻልኩም ሁሉንም ነገር እየሸሸሁት ነው ግን ከኔ


የስደት ታሪክ ሰዎች እንዲማሩ እፈልጋለው … ይሄንን መፅሀፍ አስታመው አደራ … የመጽሀፉ ማስታወሻነቱ
ለአንተ ለምወዳት እህቴና ለናቴ ይሁን ብዬ ሰጥቺያችዋለው ዳንኤል አለቀሰ/ የዚ መጽሀፍ ማስታወሻ/ የሚለው
ቃል ተሰማው

ሔለን/የሱን/ V/O

ማስታወሻ እኮ የሚሰጠው ድጋሚ ለማታገኘው ሰው ነው


እያለቀሰ እየሮጠ ወጣ፡፡

ሲን 87

ውጪ የእነ ዳንኤል መንደር ጠዋት


ሦስት ህፃናት ኢንፎርም አድርገው እየሄዱ ነው ዳንኤል እየሮጠ ከግቢው ወጣ… ልክ እንደወጣ እንደ
አውሮፕላን በሰማይ ላይ ሲሄድ ህፃናቱ ወደላይ እያዩ እየሮጡ እጅና አፋቸውን እየነካኩ ድምጽ እየፈጠሩ
ተከተሉት
የህፃናቱ የጋራ ድምፅ
/አውሮፕላኑን አንጋጠው እየተመለከቱ/
አባ … ባ … ባ … አባ … ባ… በ............
ዳንኤል ቆመ ቀና ብሎ አውሮፕላኑን አየው

ሲን 88

ወጪ በርሀማ ስፍራ ቀን
ቦታው እጅግ በጣም በርሀማ ስፍራ ነው አሸዋማ ቦታ ላይአንዴት ብቻዋን በአቧራ የምትሄድ መኪና እናያለን

65
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ሲን 89

ውጪ የሻይ ቅጠሉ ቦታ ተራራው ላይ ቀን


ሳባ ከዳንኤል እግር ስር ሁና ፀጉሯን ሦስት ጥልፍልፍ እየተሰራች ነው ዳንኤል አየሰራት ነው … እንደ ህፃን ልጁ እየተጫወቱ
እናያለን፡፡

ዳንኤል V/O
የኔ የሳባ የሄለን ሔወት ልክ እንደዚ ፀጉር
ስራ ጥልፍልፍ ነበረ … የኔና የሳባ ሔወት አሁን
ከደመና በታች ነው … ዳግም ላንገናኝ የታተመውን
መጽሀፏን ማስታወሻ
ሰታን የሄደችውን የሔለን መጽሀፍ የብዙዎችን ሂወት
ቢለውጥም … እሷ ግን አሁንምከደመና በላይ እኛን እያሰበች እየኖረች እንደሆነ አስባለው …
ለኛ ስትል ያለችበት ቦታ ያስጨንቀኛል ሁሌም ስለ እሱዋ
አስባለው ታሳዝነኛለች ድጋሚ ላገኛት ባልችልም ባለችበት ቦታ
እግዚያብሄር ይጠብቃት
ህፃኑ እየተጫወተ ነው … ዳንኤል የሳባን ፀጉር ሦስትዬሽ እየሰራ ነው ሰማዩ ጥረት ያለ ነው የሻይ ቅጠሉ እርሻ ይታያል

ተፈጸመ

እግዜያብሄር የተመሰገነ ይሁን


ከደመና በላይ

66
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

song
ሳባ
እናቴ የልቤ አለም … የልጅነቴ ሀሳብ
እንዴት ሳይሽ ልጠሸ … የነብሴ እረሀብ
እስቲ አንዴ አቅፈሽኝ … ሺ ዘመን ልርካበት
ይሄ ነበር እኮ … ያልረሳሁት ምኞት
ሔለን
እኛ ያንቺ ጌጦች … መንገድ አገናኘን
አንድ ጎጆ አሞቅን … አንድ ህመም ታመምን
ተለያይተን ሳለ … አንድ ላይ አለምን
ህልማችን ሲፈታ … አንድ አዳም
ዳንኤል
ለካስ ሁለት እግር … ሁለት መንታ ናቸው
እኔ አንድ መስሎኝ … አለሜን ስከተል

እንጉርጉሮ

ከንክርዳድ ለይቶ አቤል ልቡን ሲከፍት

የዋህ በግ ነበረ ለእግዚያብሄር አክብሮት የሰጠው መስዋት

አንተ የንክርዳድ ዘር ባቤል ደም የጸደክ

አትመልስም አሉ ባህር እየወሰድክ

የእኔ እንጉርጉሮ የእኔ መራር ዜማ

ላንድ ቀን አይደለም ባይኔ እንባ እሚደማ

የእናት ሀዘን ከፍቶ ጸጉሯን ብትላጭ

ሃዘን አይረሳም በክፉ ቀን ምላጭ

……………………………/…………………………….

67
ጉንጉን ብሩክ ሞላ

ከደመና በላይ ካለው ጥቁር ሰማይ

መቼ ይሆን እኔ አይንሽን እማይ

68

You might also like