3

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

የመምህሩ መምሪያ አደራደር

1. የትምህርት ዓይነት፡- የአማርኛ ቋንቋ


2. ክፍል ፡- 7 ኛ
3. ዝግጅት ቁጥር፡- 3
4. የትምህት ርዕስ፡- -የክርክር መመሪያ
5. ትምህርቱ የሚገኝበት
5.1 በተማሪው መማሪያ መጽሃፍ፡- ገጽ 18
5.2 በመምህሩ ማስተማሪ መጽሃፍ፡- ገጽ 20
6 .የትምህርቱ ዓላማ፡- ከዚህ የሬድዮ ትምህርት በኋላ ተማሪዎች፡-
 የክርክር መመሪያን ተከትለው ክርክር ያካሒዳሉ
7 .የትምህርቱ ፍሬ ሃሳቦች
 ክርክር ሁለት ተቃራኒ ሃሳብ ባላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች መካከል የሚደረግ የሃሳብ ሙግት
ነው፡፡
 ተከራካሪን ማክበር፣ ሰዓት ጠብቆ መናገር፣የዳኛን ውጤት ማክበር… የክርክር መመሪዎች
ናቸው፡፡

8 .ክዋኔ
8.1 ከስርጭት በፊት
 የዕለቱን የሬድዮ ትምህርት ርዕስ በሰሌዳ ላይ ይጻፉላቸውና የቀደመ ዕውቀታቸውን
ተጠቅመው ስርጭቱ ከመጀመሩ በፊት ሃሳባቸውን እንዲገልጹ ያድርጉ፡፡
 ከሬድዮ የሚተላለፈውን ትምህርት የሚከታተሉበት ማስታወሻ ደብተር እና
እስክሪፕቶ እንዲያዘጋጁ ያድርጉ፡፡
8.2 በስርጭት ወቅት
 ተማሪዎች የዕለቱን ትምህርት በጥሞና እንዲከታተሉ ያድርጉ
 ከሬድዮ መምህሩ የተማሪዎችን ተሳትፎ በሚጠይቁ ተግባራት ተማሪዎችን ያሳትፉ
 ትምህርቱ በሚተላለፍበት ወቅት ዋና ዋና ነጥቦችን በሰሌዳ ላይ ይጻፉላቸው

8.3 ከስርጭት በኋላ


 በዕለቱ ከተላለፈው ትምህርተ በተማሪዎች የሚነሳ ጥያቄ ካለ ማብራሪያ ይስጡ
 ስለ ክርክር ምንነት ተጨማሪ ማስታወሻ እና ማብራሪያ ይስጡ
 በተማሪዎች መማሪያ መጽሃፍ ገጽ 18 ተግባር ሁለተኛ ጥያቄን መሰረት አድርገው
በክፍል ውስጥ ክርክር እንዲያካሂዱ ያድርጉ፡፡
9. የክለሳ ጥያቄዎች

ጥያቄ፡-1. ክርክር ምንድን ነው?

መልሱ፡ - ክርክር በሁለት ሰዎች መካከል ወይም ቡድኖች መካከል የሚደረግ አሸናፊና

ተሸናፊ ያለው ስርዓታዊ የሃሳብ ሙግት ነው፡፡

ጥያቄ 2. በቅድመ ክርክር ወቅት አንድ ተከራካሪ ምን ምን ነገሮችን ማከናወን አለበት?

መልሱ፡- መረጃ ማሰባሰብ፣ መረጃ ማደራጀትና መለማመድ

10. የማስተማሪያ ስልት

 ገለጻ
 ውይይት
 ጥያቄና መልስ

You might also like