Professional Documents
Culture Documents
05
05
////
በን ስ ላ ክ ከ የወረዳ 05
/ ///
ሥራ አስኪያጅ ጽ ቤት የግ ህ ተ ቡድን
መግቢያ
ድህነትና ኋላቀረነትን ታርክ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ የታቀዱ የበጀት ዓመቱ የልማት ግቦች፤ የእድገትና
ትራንስፎርሜሽን እቅድና የተዛማጅ ልማት ግቦች ስኬታማ ለማድረግ መንግስት በማዘጋጃ በታዊ ዘርፎች ሰፍኖ የቆየውና የተበታተነ
፤ጥራት የጎድለውን አስተዳደርና የቁጥጥር ስርአት ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድርግ አዲስና የተቀናጀ አስተዳደርና ቁጥጥር ስርአት
መዘርጋት በማስፈለጉ በፌደራል ህገ መንግስት አንቀጽ 92 መሰረት ማንኛውም ዜጋ ንፁህና ውብ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት
እንዳለው ይደነግጋል፡፡ በዚህ መሰረት የመኖሪያ ቤቶች፤ንግድ ተቋማትና የልየ ልዩ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ በሚፈለገው ደረጃ ጥራቱን
የጠበቀ እንዲሆን እና በተቀመጠላቸው ስታንዳደርድ መሠረት አገልግሎት መስጠት እንዲቻል ለሁሉም ተመሳሳይ ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ
በተለይም ግንዛቤው በደንብ እንዲሰርፅ አስፈላጊ በመሆኑ በወረዳውም ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ጽ/ቤት በግንዛቤና ህብረተሰብ ተሳትፎ ቡድን
በስራ አስኪያጅ ሆኖ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡ ከዚህም በመነሳት በወረዳችን ይህንን አሰራር የተጠናከረ እና የተደራጀ ለማድረግ እና
የህብረተሰቡን ጤናና ውበት በሚገባ ለማረጋገጥ ከባለ ድርሻ የስራ ሂደቶች ጋር ተቀናጅቶ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ ከባለድርሻ ስራ
ሂደቶች ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል የትስስር ሰነድ በሚከተለው መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡
1. ራዕይ
አዲስ አበባን ብሎም ወረዳ 05 በ 2017 ዓ.ም የአፍሪካ ሞዴል ከተማ ሆና ማየት፡፡
2. ተልዕኮ
የወ 05 ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የህብረተሰቡንና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ መሰረት በማድረግ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አሰባሰብ ስራን በመከታተል እና በመቆጣጠር
በመሰብሰብ በማጓጓዝ እና የወረዳውን ነዋሪ ግንዛቤ በማሳደግ ዘመናዊና ዘላቂነት ባለው መልኩ አገልግሎት በመስጠት ከተማዋን ጽዱ ማድረግ ነው፡፡
3. እሴቶችና የእምነቶች መገለጫዎች
የትስስሩ ዓላማ
በጽ/ቤታችን ከሚገኙ የስራ ሂደቶች መካከል ከስራ ሂደታችን ጋር የስራ ግንኙነት ያላቸውን በመምረጥ በተደራጀ እና
በተቀናጀ መልኩ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ መንቀሳቀስ፤ የጥራት ደረጃውን እና ፍትሃዊነቱን የጠበቀ አገልግሎት
በመስጠትና ተከታታይነትና ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትል በማድረግ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር የራሱን ጤና በራሱ
መጠበቅ የሚችል ጤናማ እና ምርታማ ማህበረሰብ መፍጠር ነው፡፡
የትስስሩ ግብ
ከባለድርሻ ስራ ሂደቶች ጋር በመቀናጀት፤ በተልዕኮ ዙሪያ የሚረባረብ አመራርና ባለሙያ በመፍጠር፡የማስፈፀም አቅምን ቀጣይነት
ባለው ሁኔታ በመገንባት እና ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመርና በማስፋፋት ንፁህና ማራኪ አካባቢ መፍጠርና የወረዳው ነዋሪ ፅዳቱ
የተጠበቀ ምርታማ እንዲሆን ማድረግ፡፡
የትስስሩ ወሰን
በ 2014 ዓ.ም በንፋሰ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር በስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ስር በሚገኙ እና ከስራ ሂደታችን ጋር
በስራ በሚያገናኙን የስራ ሂደቶች መካከል ይሆናል ፡፡
ሥራ ሂደቱ የሚያከናወናቸውን ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ እና ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን ከተለያዩ አካላት ጋር
ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ አስፈላጊ በመሆኑ ይህን የትስስር ሰነድ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኗል፡፡
ቆሻሻ ከምንጩ እንዲቀንስ የደረቅ ቆሻሻ ማህበራት ለመልሶ መጠቀም የሚውሉ ደረቅ ቆሻሻዎችን በዓይነት እንዲለዩ
ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
በሕገ ወጥ ቆሻሻ አጣጣል ላይ በንግድ ተቋማት ላይ ለሚወሰደው ሕጋዊ እርምጃ ድጋፍ ማድረግ እና ህገ ወጥ ቆሻሻ
እንዳይፈጠር መከታተል፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የግ/ህ/ሰ/ተሳትፎ የስራ ሂደት ጋር ትስስር የፈጠሩ አካላት
ተ.ቁ የስራ ሂደቶች ስም ስም ፊርማ የተሳሰሩበት ቀን
1 ከደረቅ ቆሻሻ መሰብሰብና ማጓጓዝ አገልግሎት
የስራ ሂደት
2 ከመልሶ መጠቀምና ዑደት ማድረግ
የስራ ሂደት