Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 3

የመዝገብ ቁጥር 0302444

ጥቅምት 01 ቀን 2014 ዓ.ም.

በአ/ብ/ክ/መንግስት

ኦሮሚያ ዞን ደዋ ጨፋ ወረዳ ፍርድ ቤት

ከሚሴ

ከሳሽ፡ ወ/ሮ ዘቢባ የሱፍ

ተከሳሽ፡ ወ/ሮ ለምለም ቅጣው

መዝገብ በቀጠሮ እንዲቆይ ለመጠየቅ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 197/2 እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 205
መሰረት በመኃላ ቃል ተደገፎ የቀረበ አቤቱታ፤

- የተከበረው ፍ/ቤት በመዝገቡ ላይ በሰጠው ብይን የከሳሽ አቤቱታ በይርጋ የተቋረጠ መሆኑን ያረጋገጠ
ቢሆንም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ግን የከሳሽ አቤቱታ በይርጋ አይታገድም በማለቱ
ምክንያት ከሳሽና ተከሳሽ በፍሬ ነገሩ ላይ እንዲከራከሩ ለጥቅምት 01 ቀን 2014 ዓ.ም. ቀጠሮ ተይዟል፡፡
- ሆኖም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት
በመሆኑ ስህተቱ ታርሞ ፍርዱ እንዲሻር ተከሳሽ አቤቱታቸውን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት አቅርበው ችሎቱ ጉዳዩን በመዝገብ ቁጥር …………. ላይ ለማየት ለጥር 04 ቀን 2014 ዓ.ም.
ቀጠሮ ይዟል፡፡
- የፌዴራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የከሳሽ ክስ በይርጋ ይታገዳል ወይስ አይታገድም የሚለውን ጭብጥ መርምሮ
አቋም ከመያዙ አስቀድሞ የተከበረው ችሎት በዚህ መዝገብ የተያዘውን የፍሬ ነገር ጉዳይ ቢመረምር
በተከሳሽ ላይ የማይካስ ጉዳት ይደርሳል፤ የፍ/ቤቱም ጊዜ ይባክናል፡፡
- በዚህ መዝገብ የተያዘ የፍሬ ነገር ጉዳይ እልባት ማግኘት የሚችለውም የፌዴራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት
በይርጋ መቃወሚያው ላይ የመጨረሻ አቋም ሲያሳርፍ ነው፡፡
ስለዚህ በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚጥ ድረስ ይህ መዝገብ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 197/2 መሰረት በቀጠሮ ወይም ተዘግቶ እንዲቆይ እንዲታዘዝ ከፍ ባለ ትህትና
አመለክታለሁ፡፡
የቀረበው በእውነት ነው፡፡
የተከሳሽ ወኪል
ኢብራሂም የሱፍ

የመዝገብ ቁጥር 0302444

ጥቅምት 01 ቀን 2014 ዓ.ም.


በአ/ብ/ክ/መንግስት

ኦሮሚያ ዞን ደዋ ጨፋ ወረዳ ፍርድ ቤት

ከሚሴ

ከሳሽ፡ ወ/ሮ ዘቢባ የሱፍ

ተከሳሽ፡ ወ/ሮ ለምለም ቅጣው

ጣልቃ ገብ አመልካቾች፡ 1 ኛ/

2 ኛ/

3 ኛ/

4 ኛ/

5 ኛ/

6 ኛ/

7 ኛ/

8 ኛ/

በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 41 መሰረት ወደክርክር ጣልቃ ለመግባት እንዲፈቀድ ለመጠየቅ የቀረበ አቤቱታ፤
- ከሳሽ በተከሳሽ ላይ በመሰረተችው ክስ ከአባቷ ከሟች አቶ የሱፍ ኢብራሂም በውርስ የተገኘ በከሚሴ
ከተማ፣ ቀበሌ 03 ውስጥ በ 528 ካሬ ሜትር ላይ ከሰፈረና በምሥራቅ የወ/ሮ ታየች አሊ የመኖሪያ ቤት፣
በምዕራብ የአቶ አህመድ ሱልጣን የመኖሪያ ቤት፣ በሰሜን የአቶ መሐመድ ሰይድ የመኖሪያ ቤት፣ በደቡብ
የወ/ሮ ዘውዴ የመኖሪያ ቤት የሚያዋስኑት እንዲሁም ባለስድስት ክፍል የመኖሪያ ቤት፣ ሁለት ክፍል
ትላልቅ የመኖሪያ ቤት እና 6 ክፍል ሰርቪስ ያለውን ቤት ለመካፈል ጠይቃለች፡፡
- ሆኖም ከሳሽ ለመካፈል የጠየቀችው ቤት የውርስ ሃብት ሳይሆን ሟች አቶ የሱፍ ኢብራሂም በ 1987
ዓ.ም. ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ ወራሾቻቸው በሆኑት ጣልቃ ገቦች የግል ገንዘብ በባዶ መሬት ላይ የተሰራ
የጣልቃ ገብ አመልካቾች የግል ሃብት ነው፡፡
- ከሳሽ ከውርስ ሃብት ላይ ማግኘት የሚገባትን ገንዘብ በተለያየ መንገድ ተቀብላ ከሄደች ከ 10 ዓመታት
በኋላ በባዶ መሬት ላይ በጣልቃ ገብ አመልካቾች የተሰሩ ቤቶችን ስትመለከት ልካፈል ብላ መቅረቧ
ሕጋዊም ፍትሐዊም አይደለም፡፡
- ለክስ መነሻ የሆነው ቤት የጣልቃ ገብ አመልካቾች ነው፡፡
- ቤቱ የጣልቃ ገብ አመልካቾች መሆኑን
1 ኛ/
2 ኛ/
3 ኛ/
4 ኛ/
5 ኛ/
የተባሉ ምስክሮች ቀርበው ማስረዳት ይችላሉ፡፡
ስለዚህ የጣልቃ ገብ አመልካቾች በሆነ ንብረት ላይ እየተካሄደ በሚገኝ ክርክር ላይ ጣልቃ ገብ አመልካቾች
ተሳታፊ ሳይሆኑ የሚሰጥ ፍርድ የጣልቃ ገብ አመልካቾችን መብት የሚጎዳ በመሆኑ የተከበረው ችሎት
ጣልቃ ገብ አመልካቾች ወደክርክሩ ጣልቃ ገብተው ክርክራቸውን እንዲሁም ማስረጃዎቻቸውን አቅርበው
እንዲከራከሩ እንዲፈቀድ በትህትና እናመለክታለን፡፡
የቀረበው በእውነት ነው፡፡

You might also like