Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 3

የሙስና ወንጀሌ ምንነትና ሌዩ ባህሪያት

በሀገራችን በፍትህ ስርዓት ከሚታወቀው የህግ አይነት አንደ የወንጀሌ ህግ ነዉ፡፡ የተሇየዩ ዴርጊቶችን
በህግ ወንጀሌ በማዴረግ ሌዬ ሌዬ የወንጀሌ ህጎች ያለ ሲሆን ሇምሳላ የኢ.ፌ.ዱ.ሪ የወንጀሌ ህግ፤ የፀረ
ሽብር ህግ ፤ የህገ ወጥ ሰዎች ዝውውር ህግ፤የሙስና ወንጀልች ህግ እና ላልች ህጎች ይገኛለ፡፡ የዚህ
ጽሁፍ ዓሊማ አጠቃሊይ ወንጀሌ ምንነትና የሙስና ሌዬ ባህርን የሚመሇከተ ነው፡፡ ስሇሆነም ወንጀሌ
ማሇት ምን ማሇት ነዉ? የሙስና ወንጀሌ ትርጉሙ ምንዴነው? የሙስና ወንጀሌ ከላሊው ወንጀሌ
አንጻር ሌዩ ባህራያት ምን እንዯሆነ ሇመዲሰስ ተሞክሯሌ ፡፡
ሀ/ የወንጀሌ ትርጉም
አንዴ ዴርጊት ወንጀሌ ነው ሇማሇት በወንጀሌ ህጉ በተጠቀሰው መሰረት ሶስት ፍሬ ነገሮች መሟሊት
አሇበት፡፡ አንዯኛው ፍሬ ነገር (element) በህግ የተከሇከሇ ዴርጊት መሆን አሇበት፡፡ ዴርጊቱ በህግ
እንዱያዯርግ ወይም እንዲያዯርግ የሚገሌጽና ይህንን ግዳታ የተሊሇፈ ሰው ሊይ ቅጣት የሚጥሌ መሆን
አሇበት፡፡ በ1996ዓ.ም የወጣ የወንጀሌ ሀግ አንቀጽ 2 ስሇ ህጋዊነት መርህ ሲገሌጽ፣ የወንጀሌ ህግ ስሇ
ሌዬ ሌዬ ወንጀልችና በወንጀሌ አዴራጊዎች ሊይ ስሇሚፈፀሙት ቅጣቶችና ጥንቃቄ እርምጃዎች
በዝርዝር እንዯሚዯነግግ ይገሌጻሌ፡፡ ፍርዴ ቤቱ ሕገወጥነቱ በህግ ያሌተዯገገን ዴርጊት ወይም ግዴፈት
እንዯ ወንጀሌ ሉቆጥረዉ እና ቅጣት ሉወስንበት አይችሌም፡፡ ፍርዴ ቤቱ በህግ ከተዯነገጉት በቀር
ላልች ቅጣቶችንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን ሉወስን አይችሌም በማሇት ያስቀምጣሌ፡፡ ስሇሆነም አንዴ
ሰው የፈጸመዉ ዴርጊት በህግ የተከሇከሇ ካሌሆነና የተከሇከሇ ሆኖም ቅጣትን የማይወስን ከሆነ የወንጀሌ
ዴርጊት አይሆንም፡፡ ሁሇተኛዉ ፍሬ ነገር በህግ የተከሇከሇ ዴርጊትን መፈጸምን የሚመሇከት ነዉ፡፡
በተመሳሳይ ህግ አንቀጽ 23 ሕገወጥነቱና አስቀጪነቱ በህግ የተዯነገገዉን ዴርጊት መፈጸም ወንጀሌ ነዉ
ይሊሌ፡፡ በህጉ መሰረት ዴርጊት ማሇት በሕግ የተከሇከሇዉን ማዴረግ ወይም በሕግ የታዘዘዉን
አሇማዴረግ ነዉ፡፡ ሶስተኛ ፍሬ ነገር የሀሳብ ክፍሌ ወይም ሞራሊዊ ፍሬ ነገር የሚመሇከት
ነዉ፡፡በወንጀሌ ህግ አንቀጽ 23(2) ሊይ አንዴ ወንጀሌ ተዯረገ የሚባሇዉ ወንጀለን የሚያቋቁሙት ሕጋዊ
፣ ግዙፋዊ እና ሞራሊዊ ፍሬ ነገሮች ተሟሌተዉ ሲገኙ ብቻ ነው፡፡ ሞራሊዊ ፍሬ ነገር ሲባሌ የወንጀሌ
ዴርጊት የተባሇዉን ዴርጊት አዴራጊዉ ሆን ብሇዉ አስበዉ ዉይም በቸሌተንነት ስሇመፈጸሙ
የሚመሇከት ሲሆን ይህም የሚረጋገጠዉ ከተፈጸመዉ ግዙፋዊ ዴርጊት አፈጻጸምን በማመዛዘን ነዉ፡፡
በመሆኑም ወንጀሌ ዴርጊት የሚባሇዉ ዴርጊትን የሚከሇክሌ ህግ፣ በህግ የተከሇከሇ ዴርጊት መፈጸምንና
በህጉ በተጠቀሰዉ የሀሳብ ክፍሌ አይነት አስበዉ ወይም በቸሌተኝነት የተፈጸመ ሲሆን ነው፡፡
ሇ/ የሙስና ወንጀሌ
የሙስና ወንጀሌ ትርጉም በሙስና ወንጀልች ህግ ሊይ በግሌጽ ትርጉም አሌተሠጠም፡፡ ማንኛውም
የመንግስት ወይም የህዝባዊ ዴርጅት ሰራተኛ ወይም ላሊ ማንኛውም ሰው በ2007ዓ.ም የወጣዉን አዋጅ
ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 2 ስር የተመሇከተዉን የሙስና ባህርይ የሚያሟሊ ወንጀሌ በፈጸመ ጊዜ
ሇወንጀለ የተዯነገጉ የቅጣት ዴንጋገዎች ይፈጽመብታሌ ይሊሌ፡፡ ማንኛውም የመንግስት ወይም የህዝባዊ
ዴርጅት ሰራተኛ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የማይገባ ጥቅም ሇራሱ ሇመግኘት ወይም ሇላሊ ሰው
ሇማስገኘት ወይም በላሊ ሰው መብት ወይም ጥቅም ሊይ ጉዲት ሇማዴረስ በማሰብ በተሰጠዉ ኃሊፊነት
ወይም ተግባር ማዴረግ የሚገባዉን እንዲያዯርግ ወይም ማዴረግ የማይገባዉን እንዱያዯርግ ከላሊ ሰው
ሊይ ጥቅም የተቀበሇ ወይም የጠየቀ ወይም በማናቸውም ላሊ መንገዴ ሇራሱ ወይም ሇላሊ ሰው ጥቅም
ሇማስገኘት የተሰጠዉን ስሌጣን ወይም የህዝብ አዯራ ያሊአግባብ የተገሇገሇ እንዯሆነ፤ ወይም ሇላሊ ሰው
ሇማስገኘት ወይም በላሊ ሰው መብት ወይም ጥቅም ሊይ ጉዲት እንዱዯርስ ሇማዴረግ በማሰብ
ሇመንግስተ ወይም ሇህዝባዊ ዴርጅት ሰራተኛ የማይገባ ጥቅም ሇመስጠት ቃሌ የገባ፣ያቀረበ፣የሰጠ ወይም
ሇማቅረብ የተስማማ እንዯሆነ፤ ወይም በአግባቡ ሇተፈጸመ ወይም በአግባቡ ሇወዯፊት ሇሚፈጸም
የመንግስት መስሪያ ቤት ወይም የመንግሰት ሌማት ዴርጅት ወይም የህዝባዊ ዴርጅት ስራ የማይገባ
ጥቅም ሇማንኛውም ሰዉ የሰጠ ወይም ከማንኛዉም የመንግስት ወይም ህዝባዉ ዴርጅት ሰራተኛ
የተቀበሇ እንዯሆነ በሙስና ወንጀሌ ፈጻሚነት ተጠያቂ ይሆናሌ በማሇት ይገሌጻሌ (በአዋጁ አንቀጽ
4(2))፡፡ሙስና ወንጀሌን በተመሇከተ በቀጥታ ትርጉም የሚያስቀምጥ ሳይሆን ምን አይነት ዴርጊት
ሲፈጸም በሙስና ወንጀሌ ሉያስቀጣ እንዯሚችሌ የሚገሌጹ ናቸዉ፡፡
ሆኖም ሙስና ከላልች ወንጀልች የራሱ የሆነ ሌዬ ባህርይ ያሇዉ በመሆኑ በአዋጅ የተሇያዬ ዴርጊቶችን
የሙስና ወንጀሌ በማዴረግ በህጉ ተዯንግጎ ይገኛሌ፡፡ የተሻሻሇዉ የፀረ-ሙስና ሌዬ የሥነ ሥርዓትና
የማስረጃ ህግ አዋጅን ሇማሻሻሌ የወጣ አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 2(1)(1) የሙስና ወንጀሌ ማሇት
የሙስና ወንጀልችን ሇመዯንገግ በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 881/2007 የተሰጠዉ ትርጓሜ እንዯሚኖር
ይገሌጻሌ፡፡ የመስና ወንጀልች ማሇት የሙስና ወንጀልችን ሇመዯንገግ በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 881/2007
የተጠቀሱት የህግ ዴንጋጌዎችን በመጣስ የሚፈጸም ወንጀሌ ነዉ፡፡
ሐ/ የሙስና ወንጀልች ሌዬ ባህሪያት
1. ተጠያቂ የሚሆኑ አካሊት በተመሇከተ በሙስና ወንጀሌ ፈጻሚነት የሚጠየቁት የመንግስት መስሪያ
ቤት ፣ የመንግስት ሌማት ዴርጅት እና የህዝባዊ ዴርጅት ስራ ጋር በተያያዘ በህጉ የተጠቀሱ
ዴርጊቶችን በመተሊሇፍ የሚፈጽም የመንግሰት ሰራተኛ ወይም ኃሊፊ ወይም ከእነዚህ ተቋማት ጋር
በተያያዘ የህጉ ዴንጋጌ የተሊሇፈ ማንኛዉም ግሇሰብ የሚመሇከተ ነዉ፡፡ ህዝባዊ ዴርጅት ሲባሌ
በማንኛዉ አግባብ ከአባሊት ወይም ከህዝብ የተሰበሰበ ወይም ሇህዝባዊ አገሌግልት ታስቦ የተሰበሰበ
ገንዘብ፣ ንብረት ወይም ላሊ ሀብትን የሚያስተዲዴር አካሌንና አግባብነት ያሇዉን ኩባኒያ የግሌ
ዘርፍ የሚያካትት ሲሆን፤ የሃይማኖት ዴርጅትን፣የፖሇቲካ ፓርቲን፣ የዓሇም አቀፍ ዴርጅትን እና
እዴርንና ተመሳሳይ ባህሊዊ ወይም ሃይማኖታዊ ይዘት ያሇዉ ማህበርን አያካትትም፡፡
2. ጥቅም ሇማግኘት ወይም ሇማስገኘት ወይም ጉዲት ሇማዴረስ በማስብ የሚፈጸም መሆኑ፤ የሙስና
ወንጀልች ህግን በመተሊሇፍ የሚፈጸሙ ወንጀልች በአብዛሃኛዉ የማይገባ ጥቅም ሇማገኘት ወይም
ሇማስገኘት የሚፈጸሙ ናቸዉ፡፡ የማይገባ ጥቅም ማሇት ተገቢ ያሌሆነ ጥቅም ወይም አግባብ
ባሇሆነ መንገዴ የተገኘ ጥቅም ማሇት ነዉ (በአዋጁ አንቀጽ 2(14))፡፡
2.1 ጥቅም በተመሇከተ በአዋጁ አንቀጽ2(13) ጥቅም ማሇት የሚከተለትን ይጨምራሌ፤
1ኛ. በገንዘብ ወይም በማናቸዉም ዋጋ ባሇዉ መያዣ ወይም በላሊ ንብረት ወይም በንብረት ሊይ
ያሇን ጥቅም (መብት)፤ 2ኛ. ማንኛዉንም ሹሜት፣ ቅጥር፣ ወይም ዉሌ 3ኛ. ብዴርን፣ግዳታን
ወይም ማናቸውንም ዕዲ በሙለም ሆነ በከፊሌ መክፈሌን፣ማስቀረትን፤ ማወራረዴን፤ወይም
ከእነዚህ ነገሮች ነጻ ማዴረግን፤ 4ኛ. ከተመሰረተ ወይም ካሌተመሰረተ የአስተዲዯር፣ የፍትሐብሔር
ወይም የወንጀሌ ክስ ወይም ካስከተሇዉ ወይም ከሚያስከትሇዉ ማናቸዉም ቅጣት ወይም የችልታ
ማጣት በማዲን ወይም ይህን በመሰሇ ዘዳ የሚዯረግን አገሌግልት ወይም ውሇታ፤ 5ኛ.
ማናቸውንም መብት ወይም ግዳታ መፈጸምን ወይም ከመፈጸም መታቀብን፤ 6ኛ. ከተጠቀሱት
ዉጭ በገንዘብ የማይተመን ማናቸውንም ላሊ ጥቅም ወይም አገሌግልት ፤ እና ከተጠቀሱት
ጥቅሞች አንደን ማቅረብን፣ ጥቅሙ የሚገኝበትን መንገዴ ማመቻቸትን ወይም ይህንኑ
በሚመሇከት የተስፋ ቃሌ መግባትን ወይም መቀበሌን ያካትታሌ፡፡
2.2 የሶስተኛ ወገን ጥቅም ወይም መብት ሊይ ጉዲት ሇማዴረስ በማስብ መሆኑ፤
የሙስና ወንጀሌ የሚፈጸመዉ ጥቅም ሇማገኘት ወይም ሇማስገኘት ብቻ ሳይሆን በሚሰራበት
የመንግስት መስሪያ ቤት ወይም ህዝባዊ ዴርጅትን ጥቅም ወይም መብት ወይም የላሊ ግሇሰብ
ጥቅም ወይም መብት ሊይ ህጉን በመተሊሇፍ ጉዲት ካዯረሰ ጥቅም ባያገኝም በሙስና ወንጀሌ
ተጠያቂ ይሆናሌ፡፡
3. ጥቅም የማግኘት ወይም ጉዲት የማዴረስ ሀሳብ በህግ ግምት የሚወሰዴ ስሇመሆኑ፡
ተቃራኒ ማስረጃ ካሌቀረበ በስተቀር የሙስና ወንጀልቹ የተፈጸሙት የማይገባ ጥቅም ሇማግኘት ወይም
ሇማስገኘት ወይም ላሊዉን ሰው ሇመጉዲት መሆኑ በተዯነገገ ጊዜ በዴንጋገዉ የተመሇከተው ግዙፋዊ ፍሬ
ነገር መፈጸሙ ከተረጋገጠ ዴርግቱ የተፈጸመው ተገቢ ያሌሆነ ጥቅም ሇራሱ ሇማግኘት ወይም ሇላሊ
ሰው ሇማስገኘት ወይም ሦስተኛ ወገንን መብት ወይም ጥቅም ሇመጉዲት እንዯሆነ ይገመታሌ፡፡ በህጉ
መሰረት ክስ የቀረበበት ሰዉ የሙስና ወንጀሌ በመተሊሇፍ የፈጸመው ግዙፋዊ ነገር ወይም ዴርጊቱ
ከተረጋገጠ፤ ያዯረሰዉ ጉዲት ወይም ያገኘዉ ጥቅም አስበዉ እንዯሆነ ህጉ ግምት ይወስዲሌ፡፡ ሆኖም
በሙስና ወንጀሌ የተከሰሰ ሰው በላሊ ማስረጃ የቀረበበት ክስ ማስተባበሌ ይችሊሌ፡፡
4. በህግ አግባቡ ሇተሰራዉ ስራ ጥቅም መቀበሌ ወይም መስጠት በሙስና ወንጀሌ የሚያስጠይቅ
መሆኑ ላሊ ሌዬ ባህረይ ነዉ፡፡ ማንኛዉ የመንግስት ወይም የህዝባዊ ዴርጅት ሰራተኛ በህግ
የተጣሇበት ግዳታ ከመፈጸሙ በፊት ይሁን ከፈጸመ በኃሊ ጥቅም ያገኘ እንዯሆነ በህጉ የማይገባ
ጥቅም በመቀበሌ የሙስና ወንጀሌ ያስጠይቃሌ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ግታዉን ሇተወጣዉ ሰራተኛ
ጥቅም የሰጠ ማንኛዉ ግሇሰብ በሙስና ወንጀሌ ያስቀጣሌ፡፡
5. በሙስና ወንጀሌ ሌዬ በሚያዯርገዉ ተጎጂ መንግሰት ወይም ህብረተሰቡ መሆኑ ወይም የአክሲዮ
ባሇቤቶች መሆናቸዉ ነዉ፡፡ ምንም እንኳን ጉቦ መስጠት አይነት ጉዲይ የግሇሰብ ተጎጂ ሉኖር
የሚችሌ ቢሆንም በሙስና ወንጀሌ ቀጥታ ተጎጂ የሚሆነዉ አብዛሃኛዉ ማህበረሰቡ ነዉ፡፡ ሙስና
ዉስብስብ ከሚያዯርጉት አንደ ቀጥተኛ ተጎጂ ግሇሰብ ባሇመኖሩ ምርመራ፤ ክስ እና የፍርዴ ሂዯት
አስቸጋሪ ያዯርገዋሌ፡፡ ላሊዉ ጥቅም ሰጪ ይሁን ጥቅም ተቀባይ በስምምነት የሚፈጽሙ በመሆኑ
የምርመራ ሆነ የክስ ሂዯት አስቸጋሪ ያዯርጋሌ፡፡ ስሇሆነም ህብረተሰቡ የሙስና ዴርጊት ሁለም
ህብረተሰብ የሚጎዲ ተግባር በመሆኑ ሙስና በመዋጋት ሁለም የዴርሻዉን መወጣት አሇበት፡፡
በአጠቃሊይ ወንጀሌ ሇማሇት ዴርጊትን የሚከሇክሌ ህግ፣ የተሇከሇ ዴርጊት መጸምንና በህግ
የተከሇከሇ ዴርጊት የፈጸመበት የሀሳብ ክፍሌን በአንዴነት ተሟሌቶ ሲገኝ ስሇመሆኑ ተገሌጸሌ፡፡
የሙስና ወንጀሌ በሙስና ወንጀሌ ህጉ የሚከሇከለ ተግባራት የገሇጸ ሲሆን የሀሳብ ክፍሌ
በተመከሇተ በህግ ግምት የሚወሰዴ ነዉ፡፡ የተከሇከለ ተግባራት በህጉ ከተዯነገጉት መካከሌ
ስሌጣን አሇአግባብ መገሌገሌ፤ የመንግስት ስራ በማይመች አኳኃን መምራት፤ ጉቦ መስጠት
ወይም መቀበሌ እና ልልች ይገኛለ፡፡

You might also like