Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 18

ውሳኔ

ድርሰት፡ ኡሩሱላ ናፍላ


የምስል ዝግጅት፡ ቩሲ ማሊንዲ
ትርጉም፡ ናትናኤል ወርቁ
©ነሐሴ 2012 የአዘጋጁ መብት በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ታተመ፡ በይሁን የማስታወቂያ ሥራ


አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር፡ +251-921-45-44-42
ኢሜል፡- wnati00@gmail.com
https://t.m https://t.me/melkamteret
ውሳኔ ገፅ : 1

በመንደራችን ውስጥ ብዙ ችግሮች


ነበሩብን፡፡ ከብቸኛዋ ቧንቧችን
ውሃ ለመቅዳት ለሰዓታት ረጅም
ሰልፎችን እንሰለፍ ነበር፡፡
ውሳኔ ገፅ : 2

በሰዎች የሚቸረንን የምግብ


እርዳታ እንጠብቅ ነበር፡፡
ውሳኔ ገፅ : 3

በሌቦች እንዳንዘረፍ ቤታችንን


በጊዜ እንዘጋለን፡፡
ውሳኔ ገፅ : 4

በችግር ምክንያት ብዙ ልጆች


ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ፡፡
ውሳኔ ገፅ : 5

ሴት ልጆች ወደ ሌሎች መንደሮች


በመሄድ በሰው ቤት ተቀጥረው
ለመስራት ይገደዳሉ፡፡
ውሳኔ ገፅ : 6

ብዙ ወጣት ልጆች ካለምንም ሥራ


ከተማውን ሲያስሱ ይውላሉ፡፡
እድለኞቹ ደግሞ በሰዎች እርሻ
ላይ ተቀጥረው ይሠራሉ፡፡
ውሳኔ ገፅ : 7

ንፋስ ሲነፍስ አላግባብ የተጣሉ


ወረቀቶች ዛፎችንና አጥሮችን
ያለብሷቸዋል፡፡
ውሳኔ ገፅ : 8

በግዴለሽነት የተጣሉ ሰባራ


ጠርሙሶች የሰዎችን እግሮች
ይቆርጣሉ፡፡
ውሳኔ ገፅ : 9

አንድ ቀን የከፋ ችግር ገጠመን፡፡


አንዱና ብቸኛው የውሃ ጉድጓዳችን
ተሟጦ ማከማቻው ባዶ ሆነ፡፡
ውሳኔ ገፅ : 10

አባቴ በየቤቱ እየሄደ የመንደሩን


ሰዎች ስብሰባ ጠራ፡፡
ውሳኔ ገፅ : 11

የመንደሩ ሰዎች በአካባቢያችን


በሚገኘው ዛፍ ስር ተሰብስበው
መወያየት ጀመሩ፡፡
ውሳኔ ገፅ : 12

አባቴ ብድግ ብሎ “ችግሮቻችንን


ለመቅረፍ በጋራ መሥራት
ይኖርብናል” አለ፡፡
ውሳኔ ገፅ : 13

የስምንት አመቱ አቡቲ


በተቀመጠበት የዛፍ ቅርንጫፍ
ላይ እንዳለ “እኔ በፅዳት ሥራ
ማገዝ እችላለሁ አለ፡፡”
ውሳኔ ገፅ : 14

አንዷ ጎረቤታችን “እኔ የጓሮ


አትክልቶችን መትከል እችላለሁ፣
ሴቶች እህቶቼም ያግዙኛል”
አለች፡፡
ውሳኔ ገፅ : 15

ሌላ ሰው ተነሳና “ወንዶቹ የውሃ


ጉድጓድ እንቆፍራለን” አለ፡፡
ውሳኔ ገፅ : 16

በመጨረሻው ሁላችንም በአንድ


ድምፅ “ህይወታችንን መለወጥ
አለብን” ብለን ጮኽን፡፡ ከዛን ቀን
ጀምሮ ሁላችንም ችግሮቻችንን
ለመቅረፍ በጋራ መሥራት
ጀመርን፡፡

You might also like