Internet Session 1

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 98

የትምህርቱ መመሪያ

የ Microsoft Digital Literacy የማስተማሪያ ተጨማሪ መርጃ መሣሪያ


በonline መረጃን መድረስ

digital ትምህርት
በዚህ የትምህርት ጉዞ ላይ የinternet ፅንሰ
ሐሳብ ምን እንደሆነ እና እንዴት ሊደርሱበት
እንደሚችሉ ያውቃሉ። ከዚህ በተጨማሪ ከ
World Wide Web ጋር እና የድር browser
በመጠቀም እንዴት ሊደርሱበት እንደሚችሉ
እንዲተዋወቁ ይደረጋሉ። ከዚህም በላይ search
engines እንዲሁም እንዴት በውጤታማ
መንገድ ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ እና
እንዴት ውጤታቸውን መመዘን እንደሚችሉ
ሽፋን ይሰጣቸዋል።
የኮርስ ሞጁል አጭር ማጠቃለያ

▪ internet በመጠቀም ምን ማድረግ እንችላለን?


▪ internet ምንድን ነው?
▪ ከ internet ጋር እንዴት መገናኘት ይችላሉ?
internet ሰዎችን
አንዳቸውን ከሌላኛቸው
ጋር በኮምፒውተሮች እና
በመሣሪያዎች ግዙፍ ዓለም
አቀፍ network አማካይነት
እንዲገናኙ ያደርጋቸዋል።
internet በመጠቀም
በመላው ዓለም ከሚገኙ
ሰዎች ጋር መልእክቶችን
መለዋወጥ፣ መረጃን
መድረስ እና መጋራት
ይችላሉ።

5
በቅርብ እና በርቀት
ከሚኖሩ ቤተሰቦች
እና ጓደኞች ጋር
መልእክት
መለዋወጥ
እንችላለን።
በአንድ ቦታ ላይ
አንድ ላይ መሆን
ሳይኖርብን
ከሌሎች ጋር ቢዝነስ
መሥራት
እንችላለን።
በሕይወታችን
አግኝተናቸው
ከማናውቅ ሰዎች
ጋር ጨዋታዎች
መጫወት
እንችላለን።
ዕውቀትን መማር
እና መካፈል
እንዲሁም ሌላ ብዙ
ነገር ማድረግ
እንችላለን።
እግረ መንገድዎን መጠቀም
ሲፈልጉ ወይም በጊዜያዊ
ቦታ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ
ወደ ተንቀሳቃሽ መሣሪያ
ማገናኘት ብዙውን ጊዜ
ይኖርብዎታል። ወደ
internet ያለ ገመድ Wi-Fi
ን በመጠቀም ማገናኘት
ይችላሉ።

2
በዓለም በ1989 ለመጀመሪያ ጊዜ
የተፈጠረው ድረገጽ በጣም ቀላል
ነበር። ምንም ዓይነት ሚዲያ
ወይም styles የሌሉበት
ዝምብሎ ጥቁር እና ነጭ ጽሑፍ
ያለው ብቻ ነበር። ዘመናዊ
ድረገጾች ይበልጥ በየጊዜው
መስተጋብራዊ እና የበለፀጉ
እየሆኑ በመሄድ ላይ ናቸው።
ለተለያዩ ጥቅሞች የሚውሉ
ድረገጾች አሉ። የአንድን ግለሰብ
የግል ጦማር ከማንበብ ጀምሮ
እስከ ጉዞ ለማድረግ ቲኬቶችን
ማስመዝገብ እስከሚያስችልዎት
የተለያዩ ድረገጾችን ማግኘት
ይቻላል። 29
የinternet የተለመዱ ጠቀሜታዎች
1. በመላው ዓለም ከሚገኙ ሰዎች ጋር መልእክቶችን
መለዋወጥ፣ መረጃን መድረስ እና መጋራት ይችላሉ።
2. በአንድ ቦታ ላይ አንድ ላይ መሆን ሳይኖርቦት ከሌሎች ጋር
ቢዝነስ መሥራት ይችላሉ።
3. በሕይወትዎ አግኝተዋቸው ከማያውቁዋቸው ሰዎች ጋር
ጨዋታዎች መጫወት ይችላሉ።
4. ዕውቀትን መማር እና መካፈል እንዲሁም ሌላ ብዙ ነገር
ማድረግ ይችላሉ።
ይሞክሩት፦ Wi-Fi በመጠቀም የ
Windows 10 መሣሪያን ወደ internet
ማገናኘት
የእርስዎን ኮምፒውተር የ Wi-Fi connection status
ይፈትሹ።
ከ network ጋር ተገናኝተዋል?
ለመቀላቀል የሚያስችልዎት መዳረሻ ያልዎት networks አሉ?
ኮምፒውተሩ “online” ነው ማለት ምን ማለት ነው
a) ኮምፒውተሩ ሙሉ በሙሉ ኃይል ተሞልቷል።
b) ኮምፒውተሩ ከ internet ጋር ለመገናኘት በመጠባበቅ ላይ ነው።
c) ኮምፒውተሩ ከ internet ጋር ተገናኝቷል።
d) ኮምፒውተሩ በርቷል።
ኮምፒውተሩ “online” ነው ማለት ምን ማለት ነው
a) ኮምፒውተሩ ሙሉ በሙሉ ኃይል ተሞልቷል።
b) ኮምፒውተሩ ከ internet ጋር ለመገናኘት በመጠባበቅ ላይ ነው።
c) ኮምፒውተሩ ከ internet ጋር ተገናኝቷል - ትክክል! online መሆን ማለት በ internet ላይ የሚገኙ
ግብዓቶችን ሊደርሱባቸው ይችላሉ ማለት ነው።
d) ኮምፒውተሩ በርቷል።
የዕውቀት መፈተሻ - መገናኘት
ከሚከተሉት ቃላት መካከል የትኛው internet አይመለከትም?
a) ግዙፍ
b) መተግበሪያ
c) network
d) ዓለም አቀፍ
የዕውቀት መፈተሻ - መገናኘት
ከሚከተሉት ቃላት መካከል የትኛው internet አይመለከትም?
a) ግዙፍ
b) መተግበሪያ - ትክክል! internet መተግበሪያ አይደለም። network ነው።
c) network
d) ዓለም አቀፍ
ከሚከተሉት መካከል የትኛው ወደ internet ለማገናኘት የሚያስችል ገመድ አልባ አማራጭ ነው?
a) ኢተርኔት
b) Wi-Fi
c) ራውተር
d) ሞደም
ከሚከተሉት መካከል የትኛው ወደ internet ለማገናኘት የሚያስችል ገመድ አልባ አማራጭ ነው?
a) ኢተርኔት
b) Wi-Fi - ትክክል! Wi-Fi ገመድ አልባ አማራጭ ነው።
c) ራውተር
d) ሞደም
የኮርስ ሞጁል አጭር ማጠቃለያ

▪ በ internet እና በድር መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?


▪ የድር ጣቢያ ምንድን ነው?
▪ የድር browser ምንድን ነው?
ድሩን ለማሰስ የድር browsers
መጠቀም
1. በድር ላይ ካለ ይዘት ጋር ለመድረስ እና መስተጋብር
ለመፈጸም እንደሚያስችል መሣሪያ እንደ Microsoft
Edge ያለ የድር browser በመጠቀም በድር ላይ digital
ይዘትን መድረስ።
2. የድረገጽ URL ወደ የድር browser ላይ በመጀመሪያ
በመተየብ የድር browser በመጠቀም በድረገጾች መካከል
ዳሰሳ ማድረግ።
ለደኅንነት አስተማማኝ በሆነ መንገድ የ
online ግብይቶችን ማጠናቀቅ
1. በመጀመሪያ የ online ፍለጋን ማድረግ እና የሚፈልጉትን
ምርት ለይቶ ለማወቅ መፈለግ እና አስተማማኝ የሆነን
ሻጭ ማግኘት እና የት ሊገዙት እንደሚችሉ ማወቅ።
2. እየፈለጉ ያሉትን ምርት ወይም አገልግሎት በተመለከተ
በሌሎች የተጻፉ ግምገማዎችን ማንበብ።
3. ግዢ ከመፈጸምዎ በፊት ከጥቂት የተለያዩ የድር ጣቢያዎች
ወይም ሻጮች ዋጋዎችን እና ፖሊሲዎች ማነጻጸር።
4. Account ለመፍጠር የእርስዎን መረጃ በሚያጋሩበት ጊዜ
ይጠንቀቁ እና ጣቢያው ለደኅንነት አስተማማኝ እና
የሚታመን መሆኑን ያረጋግጡ።
5. ከኢ-ኮሜርስ መድረስ ዋስትና፣ ተመላሽ ገንዘብ፣ መላኪያ
ፖሊሲዎች ጋር ራስዎትን ያስተዋውቁ።
ወደ World Wide Web ለመድረስ፣ ይህንን መጠቀም ይኖርብዎታል፦
▪ Notepad
▪ Microsoft Edge
▪ Microsoft Word
▪ Microsoft Windows
ወደ World Wide Web ለመድረስ፣ ይህንን መጠቀም ይኖርብዎታል፦
▪ Notepad
▪ Microsoft Edge - ትክክል! Microsoft Edge የድር ማሰሻ መተግበሪያ ነው።
▪ Microsoft Word
▪ Microsoft Windows
የዕውቀት መፈተሻ ጥያቄ - ድርን ማሰስ
ከሚከተሉት የ browser features መካከል የትኛው በተመሳሳይ window ውስጥ በርካታ ድረገጾችን እንዲከፍቱ
ያስችልዎታል?
a) Tabs
b) ተወዳጆች
c) ታሪክ
d) የአድራሻ bar
የዕውቀት መፈተሻ ጥያቄ - ድርን ማሰስ
ከሚከተሉት የ browser features መካከል የትኛው በተመሳሳይ window ውስጥ በርካታ ድረገጾችን እንዲከፍቱ
ያስችልዎታል?
a) Tabs - ትክክል! Tabs በተለያዩ ድረገጾች መካከል እንዲንቀሳቀሱ እርስዎን ያስችልዎታል።
b) ተወዳጆች
c) ታሪክ
d) የአድራሻ bar
ከሚከተሉት መካከል የትኛው click በሚደረግበት ጊዜ አዲስ ድረገጽን ይከፍታል?
a) hyperlink
b) ድረገጽ
c) URL
d) tooltip
ከሚከተሉት መካከል የትኛው click በሚደረግበት ጊዜ አዲስ ድረገጽን ይከፍታል?
a) hyperlink - ትክክል! hyperlink ወደ ድረገጽ የሚያደርስ ሊንክን ያከማቻል።
b) ድረገጽ
c) URL
d) tooltip
በሌሎች ደንበኞች ተሞክሮዎች ላይ በመመርኮዝ ከሚከተሉት መካከል የትኛው ስለ አንድ ምርት መረጃን ለእርስዎ
ሊያቀርብልዎት ይችላል?
a) የምርት መመለስ ፖሊሲ
b) የፍለጋ ታሪክ
c) የመላኪያ ፖሊሲዎች
d) የምርት ደረጃ አሰጣጦች
በሌሎች ደንበኞች ተሞክሮዎች ላይ በመመርኮዝ ከሚከተሉት መካከል የትኛው ስለ አንድ ምርት መረጃን ለእርስዎ
ሊያቀርብልዎት ይችላል?
a) የምርት መመለስ ፖሊሲ
b) የፍለጋ ታሪክ
c) የመላኪያ ፖሊሲዎች
d) የምርት ደረጃ አሰጣጦች - ትክክል! የምርት ደረጃ አሰጣጦች ስለ አንድ ምርት ደንበኞች ያላቸውን
ሐሳቦች ያሳያል።
ኢ-ኮሜርስ ግብይቶችን
ጨምሮ online ማድረግ
የምንችላቸው በርካታ
ነገሮች አሉ። ድሩ
ግዢዎችን እንድንፈጽም
እና ከኣኛ ኮምፒውተሮች
ላይ በቅፅበት በሚባል
ደረጃ online ግብይቶችን
እንድንፈጽም ያስችሉናል።

61
የኮርስ ሞጁል አጭር ማጠቃለያ

▪ Search engines ለምን አስፈላጊ ናቸው?


▪ Search engine በመጠቀም በድሩ ላይ እንዴት ይዘትን ማግኘት ይችላሉ?
▪ የአንድን የ online የይዘት ምንጭ ተአማኒነት እንዴት መገምገም ይችላሉ?
▪ online ስለምናገኛቸው መልእክቶች በተመለከተ በጥንቃቄ ማሰብ ለምን አስፈላጊ ነው?
በፍለጋ ውጤቶች እና በድር
ላይ ያሉ ይዘቶች ውስት
ሲያስሱ፣ ሊያገኙ
ስለሚችሉት ይዘት ዓይነቶች
ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ
አስቀድሞ ማወቅ አስፈላጊ
ነው። ማንም ሰው በድር
ላይ ይዘትን መፍጠር
ይችላል፣ ስለዚህ ያገኙትን
ሁሉንም ነገር ማመን
አይችሉም።

77
በየዕለቱ የሚያጋጥሙን
በርካታ ዓይነት ሚዲያዎች
አሉ። ከጋዜጣ ጀምሮ እስከ
መጽሔት ብሎም እስከ
መጣጥፎች፣ መረጃ እና
መልእክቶች ሁሉም
በዙሪያችን ይገኛሉ። ነገሮችን
እንደ እውነት ከማየታችን
በፊት እነዚህን መልእክቶች
እንዴት መመዘን
እንደምንችል ማወቅ
አስፈላጊ ነው።

80
ይሞክሩት፦ Bing ን በመጠቀም ቀላል
keyword ፍለጋን ያከናውኑ
የእርስዎን ተወዳጅ ምግብ ለመፈለግ search
engine ይጠቀሙ።
ምን ዓይነት የፍለጋ ውጤቶችን አገኙ?
ስለ እነዚህ ውጤቶች ምን ነገር አስገርሞታል?
ይሞክሩት፦ በ Bing የተገኙ የፍለጋ
ውጤቶችን ያነጻጽሯቸው
የሬይነር ተራራን ቁመት ለማግኘት search engine
ይጠቀሙ። በአጠገብዎ ጓደኛ ወይም የክፍል ተማሪ
ካለ፣ መጀመሪያ ማን መልሱን ማግኘት እንደሚችል
ያወዳድሯቸው።
የትኛው የፍለጋ ቃል ትክክለኛውን መልስ ለማግኘት
አግዟል?
አጋዥ ያልነበሩ የፍለጋ ቃላት ነበሩ?
የሚፈልጉትን ቃል እንዲያገኙ ያግዝዎት የፍለጋ ቃል
ጠቋሚ ሐሳቦች ነበሩ?
የተለያዩ የሚዲያ ቅርጾችን ማብራራት
እና መመዘን
1. የተለመዶ የሚዲያ ቅርጾችን ማለትም ጋዜጦችን፣ ቲቪ፣
ሬዲዮ እና የታተሙ መጽሐፎች ጨምሮ እና እንደ email፣
ኢ-ቡክስ፣ የ online ጨዋታዎች እና መተግበሪያዎች
የመሳሰሉ ተጨማሪ የቅርብ ጊዜ ዕድገቶች እንዳሉ
ጠንቅቀው ይወቁ።
2. ዝምብሎ ከመምጠጥ ይልቅ ሚዲያን ማንበብ
የሚያስችልዎትን ክኅሎቶች ያጎልብቱ።
3. ዝምብሎ በስንፍና እንዳሉ ከመቀበል ይልቅ መልእክቶችን
ህን ብሎ በመመዘን እና ስለ እነርሱ በጠያቂነት በማሰብ
የሚዲያ መሠረተ ትምህርት ክኅሎቶችን ያጎልበቱ።
4. በጥንቃቄ የተመረመረ አዲስ መረጃን ማግኘትን ከግምት
ያስገቡ።
በጥንቃቄ የተመረመረ አዲስ መረጃን
ማግኘትን ከግምት ለማስገባት የሚቀርቡ
ጥያቄዎች
1. ጥያቄ አንድ፦ መልእክቱን ማን ፈጠረው?
2. ጥያቄ ሁለት፦ የእኛን ትኩረት ለመሳብ ምን ዘዴዎች ጥቅም
ላይ ውለዋል?
3. ጥያቄ ሦስት፣ ይህን መልእክት የተለያዩ ሰዎች እንዴት
ትርጉም ሊሰጡት ይችላሉ?
4. ጥያቄ አራት፦ ምን ዓይነት አተያይ፣ የኑሮ ዘይቤዎች ወይም
እሴቶች ተገልጸዋል ወይም ከመልእክቱ ላይ ተቀንሰው
ወጥተዋል?
5. ጥያቄ አምስት፦ ይህ መልእክት እየተላከ ያለው ለምንድነው?
ከ search engine የሚያገኙዋቸው የፍለጋ ውጤቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦
▪ ምስሎች
▪ ድረገጾች
▪ Videos
▪ ሁሉም ከላይ የተጠቀሱት ትክክል ናቸው
ከ search engine የሚያገኙዋቸው የፍለጋ ውጤቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦
▪ ምስሎች
▪ ድረገጾች
▪ Videos
▪ ሁሉም ከላይ የተጠቀሱት ትክክል ናቸው - ትክክል! የፍለጋ ውጤቶች ምስሎችን፣ videos፣ ድረገጾችን ኣና
በርካታ ሌላ ዓይነት ይዘትን ሊያካትቱ ይችላሉ።
የዕውቀት መፈተሻ ጥያቄ - ድርን መፈለግ
ከሚከተሉት ከግምት የሚገቡ ነገሮች መካከል የትኛው የሚዲያ መልእክቶችን እንዲመዝኑ ሊያግዝዎት ይችላል?
a) መልእክቱን ማን ፈጠረው?
b) ከመልእክቱ ተጠቃሚ የሚሆነው ማን ነው?
c) መልእክቱ ለምን ዓላማ እየተላከ ነው?
d) ሁሉም ከላይ የተጠቀሱት ትክክል ናቸው።
የዕውቀት መፈተሻ ጥያቄ - ድርን መፈለግ
ከሚከተሉት ከግምት የሚገቡ ነገሮች መካከል የትኛው የሚዲያ መልእክቶችን እንዲመዝኑ ሊያግዝዎት ይችላል?
a) መልእክቱን ማን ፈጠረው?
b) ከመልእክቱ ተጠቃሚ የሚሆነው ማን ነው?
c) መልእክቱ ለምን ዓላማ እየተላከ ነው?
d) ሁሉም ከላይ የተጠቀሱት ትክክል ናቸው። - ትክክል! በውጤታማ መንገድ ሚዲያን ለመመዘን፣ ስለ
ባለቤቱ፣ ማን ተጠቃሚ እንደሚሆን እና መልእክቱ ለምን ዓላማ እየተላከ እንዳለ ማሰብ ይኖርብዎታል።

You might also like