ጾም እና ጸሎት

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

ጾም ማለት ምንድነው ?

 እራሳችንን በማዋረድ ወደ ጌታ የምንቀርብበት ስራት ነው፡፡

 ጾም ስንል ለተወሰነ ጊዜ አለመብላት አደለም ግን ስጋዊ ፍላጎታችንን ለመቆጣጠር እና ከእግዚአብሄር አንዳች ለመቀበል
ምናደርገው ስርአት ነው፡፡

 ጾም እራሳችንን ለእግዚአብሄር ፍቃድ ሙሉ ለሙሉ እንዳስገዛን የምናሳይበት ሲሆነ የሚያስፈልገንን እንኳን ምግብ
እንደምንተው የምናሳይበት ስርአት ነው፡፡

 ጾም በእግዚአብሄር የተወደደ ቀን ተብሎ ይተራል በብሉይ ኪዳን፡፡

ኢሳ 58፡5

 ጾም ለራስ ትቅም የምናደርግበት እንጂ ለእግዚአሄር ብለን ምናደርገው አደለም፡፡

ዘካ 7፧5-6

እግዚአብሄር እንደሚፈልገው ስንጾም ያሉት በረከቶች


ኢሳ 58 ፡8-9 ኢሳ 58፡11

 ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል

 ፈውስ ፈጥኖ ይሆናል

 የእግዚአብሄርም ጺድቅ በፊትህ ይወታል

 የእግዚአብሄርም ክብር ከኋላ ሆኖ ይጠብቅሃል (የእግዚአብሔር ክብር ደጀን ይሆንልሃል(አዲሱ መ.ት))

 እግዚአብሄርን ትጣራለክ እርሱም ይሰማካል

 ወደ እግዚአብሀር ትጮሀለክ እርሱም እነሆኝ ይልሃል ( ለርዳታ ትጮኻለህ እርሱም ‘አለሁልህ’ ይልሃል(አዲሱ

መ.ት))

 እግዚአብሄርም ሁል ጊዜ ይመራካል

 ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግብሃል ( ፀሓይ ባቃጠለው ምድር ፍላጎትህን ያሟላል(አዲሱ መ.ት) )

 አጥንትህንም ያጠነክራል
እግዚአብሄር በጾማችን ምንድነው የሚፈልገው

1) እራሳችንን ከነገሮችህ አውትተን እሱን ብቻ እንድንመለከት

2) እራሳችንን በማዋረድ ወደ እሱ እንድንቀርብ

3) በፊቱ ቁች ብለን ሃሳቡን እንድንሰማው

4) እራሳችንን እንድናስገዛለት

5) እኛ ጌታ እንዲናገርን ከምንፈልገው በላይ እርሱ ስለነጋችሂን ሊያወራን ይፈልጋል

ጸሎት

እግዚአበሄር ለኛ ከሰጠን ብርቱ ስጦታዎችህ አንዱ ጸሎት ነው፡፡

ሰው በውስቱ ስያዝን፣ሲደሰት፣ሲበረታ፣ሲደኪም፣ሲጎዳ፣ካለበት ነገር ለመውታት ሊሆን ይችላል ብቻ የትኛውም ሁኔታ ውስት ብንሆን
ጸሎት ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት የምናደርግበት መንገድ ነው፡፡

ከእግዚአብሄር ዘንድ ጸጋን የምንካፈልበት መንገድ ነው፡፡

ጸሎት በየትኛውም ሁኔታ ወደ ግራና ወደ ከኝ ማንልበት መሰረታዊ መፍትሄ ነው፡፡

 እግዚአብሄር በዙፋኑ ሆኖ የቅዱሳኑን ጸሎት ለመመለስ ነው። የሚያንኳኳ ሊከፈትለት፣የሚተይክ ሊመለስለት፣የሚፈልግ


ሊያገኝ ፡ ማቲ 7

ጸሎት ለምን እንጸልያለን ?

1) ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት ለማረግ።

2) ህይወታችንን በእርሱ ሀሳብ ውስት እንዲሆን።

3) ህይወታችን ሚከለውም እና ሚከብደውም በጸሎት ሲሆን ስለሆነ።

4) ከ እግዚአብሄር መልስ እና ጸጋን ለመቀበል


ከእየሱስ የምንማረው በተጨነቀ ጊዜ የአምላኩን ፊት እንደፈለገ (ማቲ 26፡39)። በተጨነቅን ሆነ በፈራን ጊዜ የመጀመሪያ
አማራቻችን ጸሎት ሊሆን ይገባል።

“ጥቂት ዕልፍ ብሎ በግንባሩ በመደፋት፣ “አባቴ ሆይ፤ ቢቻል ይህ ጽዋ ከእኔ ይለፍ፤ ነገር ግን እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን አንተ
እንደምትፈልገው ይሁን” ብሎ ጸለየ።”

— ማቴዎስ 26፥39 (አዲሱ መ.ት)

² ወሬኞችም መጥተው፦ ከባሕሩ ማዶ ከሶሪያ ታላቅ ሠራዊት መጥቶብሃል፤ እነሆም፥ ዓይንጋዲ በተባለች በሐሴሶን ታማር ናቸው
ብለው ለኢዮሣፍጥ ነገሩት።

³ ኢዮሣፍጥም ፈራ፥ እግዚአብሔርንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ።

2 ዜና 20

“ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ፥ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፥”

— ነሀምያ 1፥4

You might also like