Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 4

የሙስና ጥቆማ

ሙስና በርካታ መገለጫዎች ያሉት ቢሆንም፤ ጉቦ፣ ምዝበራ፣ አድልኦ፣ የዝምድና አሰራርና ስጦታዎች ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡

የሙስና ወንጀሎች ከሚሰኙት መካከል ደግሞ፡- በስልጣን አላግባብ መገልገል፣ ጉቦ መቀበል፣ የማይገባ ጥቅም ማግኘት፣
አስታራቂ ሽማግሌ ሆኖ ጉቦ መቀበል፣ የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ስራን በማያመች አኳኋን መምራት፣ አደራ
በተሰጠዉ ንብረት አለአግባብ ማዘዝ፣ በስራ ተግባር የሚፈጸም የመዉሰድና የመሰወር ወንጀል፣ በስልጣን ወይም
በሃላፊነት መነገድ፣ በህገ ወጥ መንገድ መሰብሰብ ወይም ማስረከብና ያላግባብ ጉዳይን ማጓተት ይገኙበታል፡፡

ይሁን እንጅ የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ያለዓለም ፈንታሁን ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከቱትን
ተግባራት ስለመፈጸማቸዉ ከበቂ ማስረጃዎች ጋር እንደሚከተለዉ አጠናቅረን አቅርበናል፡፡

1. ህዳር 15/2013 ዓ.ም ማይጠምሪ ከተማን ከጠላት ነጻ አዉጥን ሙሉ በሙሉ ከተማዋን በተቆጣጠርን ማግስት
ጠዋት ላይ ህዳር 16/2013 ዓ.ም የወቅቱ የ 33 ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል አለምነዉ ሞላ በበርበሬ
ማዳበሪያ የተቋጠረ ገንዘብ ማይጠምሪ ከተማ ላይ ወደ ሺሬ መዉጫ ካለዉ ማደያ ላይ ለአቶ ያለዓለም
ፈንታሁን አስረክቦት ወደ ሽሬ ከተማ ሲጓዝ በአይኔ ተመልክቻለሁ፡፡ ይሁን እንጅ ከዚያ በኋላ ገንዘቡ የት
እንደወደቀ ማዎቅ አልቻልኩም፡፡
2. ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ከደባርቅ ዩኒቨርስቲ የቦርድ በመሆን የመንግስት ስራን በማይመች አኳኋን
በመምራት በግቢው ከሚከናወኑ ከፍተኛ ግንባታዎች ከእያንዳንዳቸው ተቋራጮች አንድ ሚሊየን ብር
በመቀበል የስራ ፈቃድ ወይም የቦርድ ይሁንታ በመስጠት የራስን ጥቅም የማስከበር ስራ ተሰርቷል።

3. ከማይጠምሪ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጠለምት ወረዳዎች የተከዘኑ የግንባታ ብረቶችን ከአካባቢዉ መስተዳደር
ጋር በመመሳጠር እና በማስዎጣት ሸጠዉ ተከፋፍለዉታል፡፡ በዚህ አይብቃ ብሎም፤ ከተማ የማብራት ከፍተኛ
አቅም ያላቸዉን ጀኔሬተሮች ከልዩ ኃይል ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር በክሬን አስጭኖ ሊወጣ ሲል ደባርቅ ላይ
በቁጥጥር ስር ዉሏል፤ አንዱ ግን ከደባርቅ አልፎ ባህር ዳር ደርሷል፤ የት እንደተቀመጠ አይታዎቅም፤ ከዚህም
የባለስልጣኑ እጅ አለበት።
 
4. ያለአግባብ ጉዳይን በማጓተት የደባርቅ ከተማ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉን ነጋዴዎች በእርዳታ ስንዴ መሸጥ
መለወጥ አይቻልም በማለት 13 መኪና ሙሉ ጭነት እንደጫነ ከአንድ ወር በላይ በማገት ኢኮኖሚ እንዲዳቀቅ
አድርጓል። ነገር ግን የሊማሊሞ ዱቄት ፋብሪካ ባለኃብቶች ከ 50 ሺህ ኩንታል በላይ እንዲገዙ በመፍቀድ
ያልተገባ ጥቅም ማግበስበስ ስራ ተሰርቷል።

ማስረጃዉ፡- ከፋብሪካዉ ቦታ ጠቦት ዉጭ ላይ የተከዘነዉ የእርዳታ ስንዴ

5. በሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴዉ የተሰበሰበው በጥሬ ገንዘብ 438,000.00 በአይነት 880,000.00 (ዳሽን ቢራ
ለተጎዱ ሰዎች የ 600 ሺህ ብር ግምት ያለዉ ባለ 28 ጌጅ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ በሬ፣ ደብተር) ሌሎች
የፕሮግራሙ ወጭዎች የተሸፈኑት በወረዳዎችና በከተሞች በተመደበላቸው የወጭ ክፍፍል ነዉ። ስለዚህ ጥሬ
ገንዘቡ የት ወደቀ? ምን ላይ ዋለ?

ማስረጃዉ፡- የጋራ አካዉንት የከፈቱት 1. ወ/ሮ ደብረወርቅ ይግዛዉ፣ 2. አቶ ዳኝነት ሙሉሰዉ፣ 3. ወ/ሮ ሶፍያ በሽር፣
ምን ያህል ገንዘብ እንዳለ ኦዲት ይደረግ!

6. በዳባት ወረዳ አለምዋጭ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በመሳተፍ ብርድ ልብስ፣ ብረት ድስት እና ኬንዳ ለመቀበል
ባለፈ መታወቂያ በመያዝ ወደ ዉጭ ሃገር ለመሄድ የሚደረገዉ ቅድመ ዝግጅት በወረዳዉ አሰተዳደር
ተረጋግጧል። ይህን የሚገልጸዉ ደብዳቤም በሰነድነት ተቀምጧል።

የሰነድ ማስረጃዉ፡- ስሙ በስድስት ቤተሰብ ለመረዳት በተራ ቁጥር 54 ላይ ሰፍሯል፡፡


7. ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም በተገኘ ገንዘብ አንድ FSR የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ በመግዛት ለትንሽ
ወንድሙ ሰጥቷል፤ ይህን ተሽከርካሪ በመጠቀም ህገ-ወጥ ሸቀጦችን በመጫን ወደ ትግራይ ክልል እያስተላለፈ
ይገኛል፤

ማስረጃዉ፡-

8. በጎንደር ከተማ ቀበሌ 20 የሚገኘውን ቪላ ቤቱን በአባቱ ስም በማድረግ ያስመዘገበዉ ሲሆን፤ ደባርቅ ከተማ
ስልጣኑን በመጠቀም በ 2012 ዓ.ም በደባርቅ ከተማ 2 ዓመት ሳይሞላዉ በመደራጀት፣ የከተማ አመራሮችን
በማስፈራራት ከአስፋልት ዳር ደረጃ አንድ ቦታ ወስዶ የከተማ ፕላንን በመጣስ በጭቃ ሰርቶ 1.3 ሚሊዮን ብር
በመሸጥ በጎንደር ከተማ ተጨማሪ ቦታ ገዝቷል። ይባስ ብሎም የለመደዉን የአጭበርባሪነት ባህሪዉን
በማጠናከር በእርሱና በባለቤቱ በወይዘሮ ሸዋዬ በጎንደር ከተማ በመኖሪያ ቤት በማህበር ተደራጅቷል።
ማስረጃዉ፡- የጎንደሩ ቪላ ቤቱ

የደባርቁ ጭቃ ቤቱ፡- የቦታዉ ደረጃ አንድ ሲሆን ፕላኑም G፥4 እርሱ የሰራዉ ደግሞ ..
9.  በህልውና ትግሉ ክፉኛ ለተጎዳው የዳባት ህዝብ 210 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት። የአለም የስደተኞች
ድርጅት UNHCR በዳባት ወረዳ ስር ለሚገኙ 35 ቀበሌዎች ለሚያስፈልጋቸው መሠረተ ልማት ማሟያ
የሚሆን ለእያንዳንዳቸው 6 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ 210 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል። ቀበሌዎች
በሚያቀርቡት የልማት እቅድ መሠረት ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸዉም ተገልጧል።

You might also like