Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 4

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

I. አጠቃላይ መግለጫ
የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
ግብርና ሚኒስቴር የሐር ማሽንና መሣሪያዎች ሠራተኛ የግብርና ልማት

የቅረብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ውጤቶችና ተግባራት


2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-
 የሐር ማሽንና መሣሪያዎችን በመጠቀም ጥራቱን የጠበቀ የሐር ውጤት ለማምረት ነው፡፡
2.2. የሥራ መደቡ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1፡ ለሐር ድህራ-ምርት ሥራ ማሽን ማዘጋጀት
 በየጊዜ የማሽን ፅዳት ስራ ያከናውናል፣ ግሪስና ዘይት ይቀባል፣
 የማሽኑን ደህንነት ያረጋግጣል፣ከአቅም በላይ የሆነ ብልሽት ሲገጥመው ለሚመለከተው ያቀርባል፣ተጠግኖ አገልግሎት እንዲሰጥ
ክትትል ያደርጋል፡፡
 ለሐር ድህራ ምርት ሥራ የሚያገለግሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን፣የአሠራር ስልቶችና ሃሳቦችን በማመንጨት፣
ልዩ ልዩ ምርጥ ተሞክሮዎችን የሚፈለግበትን አማራጮችን ያቀርባል፡፡
ውጤት 2፡ ሂደቱ በማሽን ተጠናቆ በንጽህናና በአግባቡ ማከማቸት
 የተሰበሰበው ኩብኩባ በማድረቂያ ማሽን የማድረቅ ስራ ያከናውናል፣
 ወደ ቦይለሩ ውሃ የመሞላትና የማሞቅ ስራ ይሠራል፣የተዘጋጀውን ኩብኩባ የመቀቀል ስራ ይፈጽማል፣
 የተቀቀለውን ኩብኩባ በሪሊን ማሽን ወደ ክርነት ይቀይራል፣ የከረረውን ክር በቦይለር በፈላ ውሃ ውስጥ በእንፋሉት የማያያዝ
ሰራ ይሠራል፣
 ከሪሊንግ ማሽን የወጣውን ክር ወደ ፐርሚሽን ቸምበር በማስገባት አየሩን የማስለቀቅና የማርጠብ ስራ ይሰራል፣ ከፐርምሽን
ቻምበር የወጣውን ክር ሪሪል ያደርጋል፣
 የተዘጋጀውን ክር በዋይንዲንግ ማሽን ወደ ቦቢን የመገልበጥ ሰራ ይሠራል፤ዋይንድ የተደረገውንም ክር መጀመሪያ ወደ ማሽን
በማስገባት የማክረር ስራ ይሠራል፣
 በመጀመሪያ ደረጃ በማክረሪያ ማሽን የከረረውን ክር ደብል ያደርጋል፤ ደብል የተደረገውን ክር በሁለተኛ ደረጃ ማክረሪያ ማሽን
በማስገባት ማክረርና ወደ ፕፕሮል ይገለብጣል፣
 ከቦይለር የወጣውን ፒፒሮል ወደ ሪዋይንዲንግ ማሽን ይገለብጣል፣
 ከሪዋይድንግ ማሽን ወደ ዋይድንግ ማሽን በማስገባት ወደ ቦቢን የመገልበጥ ስራ ይሰራል፣
 ወደ ቦቢን የተገለበጠውን ክር እስታንድዋሪፕንግ በማስገባት ወደ ቢም ይገለብጣል፣
 በማሽኑ የተመረቱትን ውጤቶ በንጽህና በአግባቡ እንዲቀመጡ ሁኔታዎችን ያመቻቸል፣
 የሥራ ክንውን ሪፖርት ለቅርብ ኃላፊ ያቀርባል፡፡
III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች
3.1. የሥራ ውስብስብነት
 ሥራው የተመረተውን ጥሬ የሐር ምርት አገልግሎት መስጠት ወደሚችልበት ደረጃ ለመለወጥ የሥራ ቅደም
ተከተልን ጠብቆ መሥራትን የሚጠይቅ ነው፡፡ በሥራ ክንውን ወቅት የሚያገጥሙ ችግሮች የተቀቀለውን ኩብኩባ
በሪሊን ማሽን ወደ ክርነት ለመቀየር እንዲሁም ከአንዱ ደረጃ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ለመቀየር የክሩን ጫፍ አለማግኘት ሲሆን
ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎች በማመከርና መረጀ በማለዋወጥ ችግሮቹ ይፈታሉ፡፡
3.2 ራስን ችሎ መስራት
3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 ሥራው ከቅርብ ኃላፊ በሚሰጥ ዝርዝር መመሪያና የሥራ ቅደም ተከተል መሠረት የሚፈፀም ነው፡፡
3.2.2. ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
 ሥራው ተገቢውን የጥራት ደረጃ ጠብቆ በተሰጠው ዝርዝር መመሪያና የሥራ ቅደም ተከተል መሠረት ስለመከናወኑ
በቅርብ ኃላፊው የቅርብ ክትትል ይደረግበታል፡፡

3.3. ተጠያቂነት
3.3.1. ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /Responsibility for Impact/፣
 ሥራው የሐር ትልን የማሽኑንና የመሳሪያዎቹን ደህንነት ጠበቆ ጥራት ያለው የሐር ደህረ-ምርት ማምረትን
የሚጠይቅ ሲሆን ሥራው በሚፈለገው ጥራትና ደረጃ ባይከናወን በማሽኑና በመሣሪያዎቹ ደህንነት እና በሐር
ድሀረ-ምርት ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል፣ተቋሙ ከሐር ምርት የሚያገኘውን ገቢ ያሳጣል፣ በሥራ ክፍሉ
የሥራ አፈጻጸም ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል
3.3.2. ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣
 የለበትም፡፡
3.4 ፈጠራ
 ሥራው የሐር ድህራ ምርት ሥራን ለማሻሻል አዳዲስ ሃሳቦችን በማመንጨት፣ ልዩ ልዩ ምርጥ ተሞክሮዎችን
በመፈለግ አማራጮችን በማቅረብ መሥራትን የሚጠይቅ ነው፡፡
3.5. የሥራ ግንኙነት /Work Communication/
3.5.1 የግንኙነት ደረጃ
 ሥራው በውስጥ ከቅርብ ኃላፊ፣ከሥራ ክፍል ሠራተኞች ከምርምር ወይም የሐር ትል እርባታ ላይ ከተሠማሩ
ተቋማት ጋር ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡

3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ


 ሥራው ዝርዝር የሥራ መመሪያ ለመቀበልና የሥራ ሪፖርት ለማቅረብ ፣ ልምድና መረጃ ለመለዋወጥና የተሻለ
ተሞክሮ ለማግኘት ነው፡፡
3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ
 ሥራው በሚያካሄድበት ጊዜ ከሥራ ጊዜው 25 በመቶ የሥራ ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡
3.6 ኃላፊነት
3.6.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት
 የለበትም፡፡
3.6.2 ኃላፊነት ለንዋይ
 የለበትም፡፡
3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት
 ከምፕዩተር፣ ጠረጴዛና ሐር መሳሪያዎች በብር እስከ 150,000.00 ንብረት በኃላፊነትና ተጠያቂነት መያዝ
የሚጠበቅበት ይሆናል፡፡
3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
 ሥራው ሥራው የሐር ትልን የማሽኑንና የመሳሪያዎቹን ደህንነት ጠበቆ ጥራት ያለው የሐር ደህረ-ምርት
ማምረትን ፤ ምርት ሥራን ለማሻሻል የአሠራር ስልቶችና ሃሳቦችን ማመንጨት፣ ልዩ ልዩ ተሞክሮዎችን በመፈለግ
አማራጮችን በማቅረብ የአዕምሮ ሥራን ይጠይቃል፡ ይህም ከሥራ ጊዜው 25 በመቶ ይሆናል፡፡
3.7.2. ሥነ-ልቦናዊ ጥረት
 ሥራው የተቀቀለውን ኩብኩባ በሪሊን ማሽን ወደ ክርነት ለመቀየር እንዲሁም ከአንዱ ደረጃ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ለመቀየር
የክሩን ጫፍ በቀላሉ የማይገኝ ሲሆን የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት ትዕግሥት፣የሥነልቦና ዝግጅነትን፣
ቁርጠኝነትንና የሥራ ትጋት ጥረትን የሚጠይቅ ነው፡፡

3.7.3. የዕይታ ጥረት፣


 ሥራው በሐር ድህራ ምርት ሥራ ወቅት እያንዳንዱን ደረጃ ሂደት በትኩረት አይቶ መሥራት በጣም ከፍተኛ
የዕይታ ጥረትን የሚጠይቅ ሲሆን ይህ ከቀን የስራ ሰዓቱ 25% ይሆናል፡፡
3.7.4 የአካል ጥረት
 ሥራው ለማከናወን 45 በመቶ በመቆም፣25 በመቶ ጎንበስ ቀና በማለት፣ 25 በመቶ በመቀመጥና በእግር በመጓዝ
10 በመቶ የሚከናወን ይሆናል፡፡
3.8. የሥራ ሁኔታ
3.8.1. ሥጋትና አደጋ
 ሥራው የመቆረጥ፣ የመውደቅና የመሰበር፣ በኤሌክትሪክ የመያዝ፣ ከባድ የአካል ጉዳት የሚያደርሱ ጉዳቶች
ሊያስከትል የሚችል ነው፡፡
3.8.2. የሥራ አካባቢ ሁኔታ
 ሥራው በአብዛኛው ከፍተኛ ድምጽ ያለበት አካባቢ የሚከናወን ስለሆነ የጤና መታወክን ሊያስከትል ይችላል፡፡

3.9. እውቀትና ክህሎት፣


3.9.1. ትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት አይነት
10+3 በቴክስታይል ኢንደስትሪ

3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ


የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
0 ዓመት

የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ ፊርማ ቀን


መጠሪያ

You might also like