Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 4

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

I. አጠቃላይ መግለጫ
የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
ግብርና ሚኒስቴር የሐር ትል መኖ ሠራተኛ የግብርና ልማት

የቅረብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ውጤቶችና ተግባራት


2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-
 የሐር ትል መኖ በማልማት ጥራቱን የጠበቀና ጤናማ የሐር ምርት እርባታ እንዲመረት ማስቻል ነው፡፡
2.2. የሥራ መደቡ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1፡ ጥራቱን የጠበቀ የሐር ትል መኖ ማምረት
 ኮሌጁ ለሚያካሄዳቸው የሐር ትል ልማት ሥራዎች የሚሆኑ የመኖ ልማት፣አያያዝና አጠቃቀም አስመልክቶ ዓመታዊ
የሥራ መረሐ-ግብር ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣
 በኮሌጁ ውስጥ ለሚገኙ የሐር ትል እርባታ መኖ በወቅቱና በበቂ መጠን ጥራቱን ጠብቆ መመረቱንና የተመረተውም
ምርት በአግባቡ ወቅቱን ጠብቆ ለሐር ትል መሠራጨቱን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
 ለሐር ትል መኖ የሚውሉትን ዝሪያዎች ምርትና ምርታማነትን ጨመሮ የሚመረትበትን ዘዴ እየጠና ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ
ያደርጋል፡፡
 በተለያዩ የእድሜ ደረጃ ላሉ ትሎች የመኖ ልማት መረሐ-ግብር በማውጣት እንዲዘጋጅ ያደርጋል::
 ለአከካባቢ አየር ተስማሚ የሆኑ የሀር ትል መኖ ዘሮችን/ቁርጥራጮች ዓይነት ይመርጣል፣ እንዲዘራ/እንዲተከል
ያደርጋል፣ ያሳርማል፣አጠቃላይ የእንክብካቤ ሥራዎችን ክትትል ያደርጋል፣
 ለሐር ትል መኖ ልማት የሚውሉ መሣሪያዎች ወጪ በማድረግ በአግባቡ መያዛቸውንና ሥራ ላይ መዋላቸውን
ይከታተላል፣ይቆጣጠራል ሥራ ሲጠናቀቅ ንጽህናቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲመለሱ ያደርጋል::
III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች
3.1. የሥራ ውስብስብነት
 ሥራው ምርትና ምርታማነትን የሚጨምሩ፣ ጥራትን የጠበቁ፣ለአካባቢ አየር ተስማም የሆኑ የሐር ትል መኖ በተለያዩ የእድሜ
ደረጃ ላሉ ትሎች ማልማትን የሚጠይቅ ነው፡፡
 በሥራ ክንውን ወቅት ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ዝርያዎች አለማግኘት ሲሆን ልምድ ያላቸውን
ባለሙያዎች በማመከርና መረጀ በማለዋወጥ ችግሮቹ ይፈታሉ፡፡

3.2 ራስን ችሎ መስራት


3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 ሥራው ከቅርብ ኃላፊ በሚሰጥ ዝርዝር መመሪያና የሥራ ቅደም ተከተል መሠረት የሚፈፀም ነው፡፡
3.2.2. ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
 ሥራው ተገቢውን የጥራት ደረጃ ጠብቆ በተሰጠው ዝርዝር መመሪያ መሠረት ስለመከናወኑ በቅርብ ኃላፊው የቅርብ
ክትትል ይደረግበታል፡፡
3.3. ተጠያቂነት
3.3.1. ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /Responsibility for Impact/፣
 ለሐር ትል ጤና ተስማም መኖ ማልማት የሚጠይቅ ሲሆን ሥራው በሚፈለገው ጥራትና ደረጃ ባይከናወን በእርባታው
ቀጣይነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል፡፡ በሥራ ክፍሉ የሥራ አፈጻጸም ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል

3.3.2. ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣


 የለበትም፡፡
3.4 ፈጠራ
 ሥራው በባሕርይው ለሐር ትል ጤና ተስማም መኖ ለማልማት የአሠራር ስልቶችና ሃሳቦችን በማመንጨት፣ ልዩ ልዩ
ተሞክሮዎችን በመፈለግ አማራጮችን በማቅረብ መሥራትን የሚጠይቅ ነው፡፡
3.5. የሥራ ግንኙነት /Work Communication/
3.5.1 የግንኙነት ደረጃ
 ሥራው በውስጥ ከቅርብ ኃላፊ፣ከሥራ ክፍል ሠራተኞች፣ከቀን ሠራተኞች፣በውጭ ከምርምር ወይም የሐር ትል
እርባታ ላይ ከተሠማሩ ሌሎች ተቋማት ጋር ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡

3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ


 ሥራው በውስጥ ዝርዝር የሥራ መመሪያ ለመቀበል፣ ሥራን ለመከታተል፣የሥራ ሪፖርት ለማቅረብ ፣ልምድና መረጃ
ለመለዋወጥ ወይም ተሞክሮ ለማግኘትና ነው፡፡
3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ
 ሥራው በሚያካሄድበት ጊዜ ከሥራ ጊዜው 40 በመቶ የሥራ ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡
3.6 ኃላፊነት
3.6.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት
 የለበትም፡፡
3.6.2 ኃላፊነት ለንዋይ
 የለበትም፡፡

3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት


 ወንበር፣ ጠረጴዛና በብር እስከ 20,000.00 ንብረት በኃላፊነትና ተጠያቂነት መያዝ የሚጠበቅበት ይሆናል፡፡
3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
 ሥራው ለሐር ትል ጤናና ለአካባቢ አየር ተስማም የሆኑ የሐር ትል መኖ ለማልማት የአሠራር ስልቶችና ሃሳቦችን
በማመንጨት፣ ልዩ ልዩ ተሞክሮዎችን በመፈለግ አማራጮችን በማቅረብን ይጠይቃል፡፡ ይህም ከሥራ ጊዜው 25 በመቶ
ይሆናል፡፡
3.7.2. ሥነ-ልቦናዊ ጥረት
 የሃር ምርቱ ውጣታማ ስለመሆኑና የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት የሚያስችል የሥነልቦና ዝግጅነትን፤
ቁርጠኝነትንና የሥራ ትጋት ጥረትን የሚጠይቅ ነው፡፡
3.7.3 የዕይታ ጥረት፣
 ሥራው ለሐር ትል መኖ የሚያገለግሉና ሲተከሉ ወይም ሲዘሩ የሚጸድቁና የሚበቅሉ ቁርጥራጦችን/ዘሮችን በትክክል
አይቶ ለመምረጥ፣ ትሎቹ የሚመገቡት ቅጠል በታባይና በበሽታ አለመጠቀቱን ለማረጋገጥ መለስተኛ የዕይታ ትኩረትን
የሚጠይቅ ሲሆን ይህ ከቀን የስራ ሰዓቱ 25 30% ይሆናል፡፡
3.7.4 የአካል ጥረት
 ሥራው ለማከናወን 20 በመቶ በመቆም፣ 20 በመቶ ጎንበስ ቀና በማለት፣60 በመቶ በመቀመጥና በእግር በመጓዝ 10
በመቶ የሚከናወን ይሆናል፡፡
3.8. የሥራ ሁኔታ
3.8.1. ሥጋትና አደጋ
 ሥራው የመቆረጥ፣ የመውደቅና የመሰበር ጉዳቶች ሊያስከትል የሚችል ነው፡፡
3.8.2. የሥራ አካባቢ ሁኔታ
 ሥራው በአብዛኛው አቧራ፣ የቅጠል ሽታና ሙቀት ያለበት አካባቢ የሚከናወን ስለሆነ በአካላት ላይ ከፍተኛ የጤና
መታወክን ሊያስከትል ይችላል፡፡

3.9. እውቀትና ክህሎት፣


3.9.1. ትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት አይነት
10+3 በእጽዋት ሳይንስ ወይም በተፈጥሮ ሀብት አያየዝ ወይም በደን ሳይንስ

3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ


የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
0 ዓመት

የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ ፊርማ ቀን


መጠሪያ

You might also like