Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 9

 

የ2013 ዓ.ም የክረምት


በጎ ፈቃድ መርሓ-ግብር
 
መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት

የፕሮግራሙ ዋና አዘጋጅ፡- ዘ-ኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሴሽን

ሐምሌ 2013 ዓ.ም


 

አጋር አካላት
§ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ
§ የአዲስ አበባ ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ
§ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር
§ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን
§ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር
§ ሰላም ሚኒስቴር
§ ትምህርት ሚኒስቴር
§ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት
§ ቀይ መስቀል
§ የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

ፈፃሚ
§ የኢትዮጵያ ወጣቶች ትስስር መረብ በጎ ፈቃደኞች
§ የተሳታፊ በጎ ፈቃደኞች ብዛት 200
§ የተጠቃሚዎች ብዛት 20.000.00
§ ቀጥተኛ 13.000.00
§ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ 7000.00

የ2013 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ መርሓ-ግብር መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት YNE  


 
 

መግቢያ
የበጎ ፈቃድ ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ በሀገራችን
ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት እየተሰጠውና በአገልግሎቱም
ጥራትና ተደራሽነት አንፃር ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረ
መሆኑ እሙን ነው። በተለይም ክቡር ጠቅላይ
ሚኒስትራችን ዶክተር ዐቢይ አህመድ ባሳዩት የበጎነት
ልብ እና ተሳትፎ ምንያት ሌሎች አመራሮችም
ለተግባሩ ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን ሰፋፊ
ስራዎች በመስራት ላይ እንደሚገኙ የሚታይ ነው።
ይሁንና ከተለመደው የበጎ ፈቃድ ተግባር ባሻገር
ዘመናዊ በሆነ መልኩ በጎነትን ለመከወን በሚያስችል መንገድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ትስስር መረብ
“ዲጂታል ቮለንተሪዝም” የተሰኘ ልዩ የበጎ ፈቃድ እድል ለህብረተሰባችን ይዞ መጥቷል፡፡

የ2013 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ መርሓ-ግብር መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት YNE  


 
 

የበጎ ፈቃድ ተግባራት

1, የትምህርት ድጋፍ አገልግሎት {Tutorial Service}


§ ለመጀመሪያ ደረጃ እና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች
2, የቋንቋ ተምህርት
§ አፋን ኦሮሞ ፣
§ ትግርኛ ፣
§ ግዕዝ ፣
§ እንግሊዝኛ … ወዘተ
3, የአስተሳሰብ ግንባታ (Mind-set) ስልጠና
4, ስብዕና ግንባታ ስልጠና
5, ሴቶችን የማብቃት ስልጠና (women Empowerment)
6, የማማከር - (በቁማር፣ በሱሶችና ሌሎችም ጉዳዮች)
7, አቅመ ደካማዎችን የመንከባከብ ፣ የመከታተል
8, እህቴን ወደ ዩኒቨርሲቲ እሸኛለሁ
9, የበይነ-መረብ ቤተ-መጻሕፍት ወመዛግብት (Digital Library)
10, Youth Abroad (ኢትዮጵያዊ ወጣቶች በዉጪ ሀገራት)
11. የበጎ ፈቃድ ፅንሰ-ሀሳብ ስልጠና በበጎ-ፈቃደኞች ለአባላት መስጠት
12. የደም ልገሳን አስመልክቶ ስላለው አሉታዊ አስተሳሰብና ግንዛቤ ከሚመለከተው አካል ጋር በጋራ
በመቀናጀት ህብረተሰቡ ትክክለኛውን ግንዛቤ እንዲያገኝ ማመቻቸት።
13. የማህበራዊ ትሥሥር ገፆቼን ከአላስፈላጊ ልጣፎች (ፖስቶች) አፀዳለሁ
14. የሰላም ትምህርትና ውይይቶች

15. አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ ግንዛቤ የማስጨበጥና እነሱንም አሳታፊ የሆኑ ተግባራትን ማከናወን

16. በንፅህና አጠባበቅ ዙሪያ የግንዛቤ ፈጠራ ተግባራትን ማከናወን

17. በሁሉም ዘንድ ኃላፊነትን የመወጣት ስሜትን መገንባትና ማስረፅ

የ2013 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ መርሓ-ግብር መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት YNE  


 
 

ምርጥ የኢትዮጵያ ወጣቶች የትስስር መረብ አባላት!


ይህ የወጣቶች የትስስር መረብ በአዎንታዊነት ሀሳብ እና አቋቋም ለወገናችን ይጠቅማል የምንለውን
መልካም ሀሳብ፣ ንግግር እና ተግባር የምናጋራበት፣ የምናሳይበትና የምንሰራበት መድረክ ነው።
ይህ የወጣቶች የትስስር መረብ የኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሴሽን ኢኒሼቲቭ ሲሆን ህጋዊ
አቋቋም ይዘን ለህዝባችንና ለራሳችን የሚጠቅም ለውጥ ለማምጣት እየሰራን ነው። በመሆኑም
የሚጠቅም ሀሳብ፣ እይታ እና እውቀት እንዲሁም መልካም አጋጣሚ በዚህ የትስስር መረብ
በማጋራት የበኩላችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ አሳስባለሁ፡፡

ከዚህ በመቀጠል “የዲጂታል ቮለንተሪዝም” ስራችንን ለሁለት ወር የምንሰራ ሲሆን በዚህም


ለህብረተሰብ እና ለራሳችን ጠቃሚ ተግባር እንፈፅማለን። “የዲጂታል ቮለንተሪዝም” ሀሳብና
ተግባር በአይነቱ ለየት ያለ እና በትግበራ አንፃርም የመጀመሪያ ሲሆን ሀሳቡ በዚህ የኢትዮጵያ
ወጣቶች የትስስር መረብ የተቀመረ ሀሳብ ነው። “በዲጂታል ቮለንተሪዝም” የበጎ ፈቃድ
አገልግሎት በጎ ፈቃደኞች የቦታ እና የጊዜ ገደብ ሳይኖርብን ከየትኛውም የአለማችን ክፍል ሀሳብን
እውቀትን መልካም አጋጣሚን በማጋራት በበጎ ፈቃድ ተግባር መሣተፍ ያስችለናል።

4 minutes)

የ2013 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ መርሓ-ግብር መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት YNE  


 
 

ዝርዝር የበጎ ፈቃድ ተግባራት


1, የትምህርት ድጋፍ አገልግሎት {Tutorial Service}
ለመጀመሪያ ደረጃ እና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚሰጥ
ተማሪዎችን ከማስጠናት አንፃር በርካታ በጎ ፈቃደኞች የተሰማሩ ሲሆን “በዲጂታል
ቮለንተሪዝም” አንፃር ቤተሰብ ፣ ተማሪው ፣ አስጠኚው የሚካተቱበት ይሆናል፡፡ ይህንንም
በማደረጋችን በክረምት ወቅት ከፍለው የትርፍ ጊዜ የትምህርት ድጋፍ ማግኘት ለማይችሉ
ወገኖቻችን እንደርሳለን

2. የቋንቋ ትምህርት (ኢትዮጵያ ወደፊት የተለያዩ የሥራ ቋንቋዎች ሊኖሯት ይችላል፡፡ ይህን
ታሳቢ በማድረግ ወጣቶች ኢትዮጵያዊ ቋንቋዎችን እንዲሁም አለም አቀፋዊ ቋንቋዎችን መማር
አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡
“ቋንቋዎች የሚያቀራርቡን፣ የሚያስማሙን፣ የሚያዋድዱን እንጂ የሚያጣሉን መሆን የለባቸው!”
በሚል የተነሳው የኢትዮጵያ ወጣቶች ትስስር መረብ “በዲጂታል ቮለንተሪዝም” አንፃር የቋንቋ
ስልጠናዎች በማከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም በታቀደው የክረምት የበጎ ፈቃድ
መርሓግብር ኢትዮጵያዊ ቋንቋዎችን በስፋት በመማማር ሀገራዊ አንድነትና ሰላም ላይ የበኩላችንን
አሻራ እናበረክታለን!
§ ኦሮምኛ ቋንቋ ፣
§ ትግሪኛ ፣
§ ግዕዝ ፣
§ እንግልዝኛ እና ሌሎችም
3-4 የማይድ ሴት ፣ የአስተሳሰብና አመላካከት ለውጥ ስልጠና
§ በኢትዮጵያ ወጣቶች ትስስር መረብ የዲጂታል የበጎ ፈቃድ ሂደት ውስጥ ሌላው እና
ዋነኛው በበጎ ፈቃድ ልንሰጥ የተዘጋጀነው የአዕምሮ ውቅር እና የአመለካከት ለውጥ
ስለጠና እንዲሁም የግል ስብዕና ግንባታ ስልጠናዎች ነው፡፡ በዚህ የሁለት ወር የክረምት
የበጎ ፈቃድ ተሳትፎ በዲጂታል አኳሀን ለወጣቶች ፣ ለህብረተሰባችን ከላይ የተዘረዘሩትን
ስልጠናዎች አንሰጣለን
5. ሴቶችን የማብቃት (women Empowerment) ስልጠና
§ የሴቶች ማጎልበት (ወይም ሴትን ማጎልበት የተሰኘው ስልጠና) ሴቶችን የማብቃት ሂደት
ነው፡፡ የሴቶችን አመለካከት ለውጥ ላይ መስራት አቅማቸውን ማጎልበት በትምህርት
፣ በግንዛቤ ፣ በማንበብ እና በስልጠና ከፍ ማድረግን ጨምሮ በበርካታ መንገዶች
በመጠቀም በተለይም ልምዱ እና ዝግጅቱ ባላቸው በጎ ፈቃደኞች ሴቶችን የማጎልበቻ
የ2013 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ መርሓ-ግብር መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት YNE  
 
 

ሰስልጠና እንዲሁም የማማከር ስራ እንሰራለን፡፡ ሴቶችን ማጎልበት ሴቶች ሕይወትን


የሚወስኑ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል

6-7 የማማከር ፣ የመንከባከብ ፣ የመከታተል አገልግሎት


§ በኢትዮጵያ ወጣቶች ትስስር መረብ የማማከር አገልግሎት እንሰጣለን በዚህ የማማከር
አገልግሎት ውስጥ በተለያዩ ሱስ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን እናማክራለን
§ በትምባሆ እና የመጠጥ ሱስ
§ የፖርኖግራፊ ሱስ
§ የቁማር ሱስ ውስጥ ያሉ ወጣቶችና ልምዱ እና ብቃቱ ያላቸውን አማካሪዎችን በመጠቀም
የምንሰራ ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እነዚህን ወጣቶች እንዲሁም አቅመ-ደካማዎችን
የመከታተልና የመንከባከብ ተግባር የምናከናውን ይሆናል፡፡

8, እህቴን ወደ ዩኒቨርሲቲ እሸኛለው

§ ወደ ዩኒቨርስቲ የምትሄድን አንዲ ሴት በተለይም አቅም የሌላትን የሚያስፈልጋትን


የንፅህና መጠበቂየ ቁሳቁስ በማሟላት፣ የትራንስፖርት ወጪ በመሸፈን አንድ እህቴን ወደ
ዩኒቨርርቲ እሸኛለው በሚል ህብረተሰባችንን የምናሳትፍበት ልዩ መርሀግብር ነው፡፡

9, የበይነ-መረብ ቤተ-መፃሕፍት ወመዛግብት (Digital Library)

§ በዚህ ዲጂታል ቮለንተሪዝም የክረምት በጎ ፈቃድ መርሀግብር የማህበራዊ ድህረገፅን


በመጠቀም በየትኛውም አለማቸን ክፍል ለሚገኙ ወገኖቻችንን የሚፈልጉትን መፅሀፍ
በማቅረብ የንባብ ባህላቸውን እንዲያዳብሩ የምናገለግልበት ማዕቀፍ ነው፡፡ በዚህ
አገልግሎት ከ መቶ ሺህ በላይ መጻሕፍቶችን በፒ.ዲ.ኤፍ ያዘጋጀን ሲሆን በልዩ ሁኔታ
ለማገልገልም ተዘጋጅተናል፡፡

10. Youth Abroad

§ ኢትዮጵያዊ ወጣቶች በውጪ ሀገር በተሰኘው የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሀግብራችን


በተለያዩ የአለማችን ክፍል የሚገኙ ወጣት ኢትዮጵያዊያን በዲጂታል ቮለንተሪዝም የበጎ
ፈቃድ ተግባር እንዲሳተፉ በማድረግ እውቀታቸውንና ሀሳባቸውን ለወንድሞቻቸው እና
ለእህቶቻቸው በተዘጋጀው የኢትዮጵያ ወጣቶች ትስስር መረብ አንፃር ማገልገል እንዲችሉ
እናመቻቻለን!

የ2013 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ መርሓ-ግብር መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት YNE  


 
 

§ በውጪ የሚገኙትን ኢትዮጵያዊያንን በችግሮቻቸውና በሚያስፈልጉ ጉዳዮች አንጻር


እንዲወያዩ ፣ መረጃ እንዲለዋወጡ ፣ መልካም አጋጣሚዎችን እንዲያጋሩ ፣
እንዲደማመጡ እና እርስ በእርስም እንዲደጋገፉ የምንሰራበት ልዩ መርሀግብር ነው!

11. የበጎ ፈቃድ ፅንሰሀሳብ ስልጠና ለአባላት እንሰጣለን

12. የደም ልገሳ

§ የደም ልገሳን አስመልክቶ ስላለው አሉታዊ አስተሳሰብ ግንዛቤ ከሚመለከተው አካል


ህብረተሰቡ እንዲያገኝ ማመቻቸት፡፡ በዚህም ሰዎች በእውቀት ደማቸውን እንዲለግሱ
መስራት

13. ማህበራዊ ትሥሥር ገፆቼን ከአላስፈላጊ ነገሮች አፀዳለሁ

§ በአሁኑ ጊዜ ሰዎች በቀላሉ ሀሳባቸውን የሚገልፁበትና መልዕክት የሚያስተላልፉበት


መድረክ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በተራቀቀና በቀላል ሁኔታ በእጃቸው ያለበት ሁኔታ ነው
ያለው፡፡ በዚህ እድል በመጠቀም አንዳንዱ ለመልካም ፣ አንዳንዱ ደግሞ ለመለያየት ፣
ለጥላቻ፣ ሰላምን ለማደፍረስ ይህንኑ የማህበራዊ ሚዲያ የሚጠቀም መሆኑ ግልፅ ነው፡፡
ታዲያ “በዲጂታል ቮለንተሪዝም” መርሀግብራችን ማህበራዊ ትስስር ገፄን “ከአላስፈላጊ
ነገሮች አፀዳለሁ!” በሚል መሪ ቃል ከማህበራዊ የትሥሥር ገፆቻችን በተለይም
ከፌስቡክ ላይ የጥላች ንግግርን የሚነዙ መልዕክትና ምስል የሚያጋሩትን በማስወገድ
ህብረተሰባችን የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ሰፊ ንቅናቄ እንፈጥራለን፡፡

14. የሰላም ትምህርትና ውይቶች

§ ስለሰላም ማወቅ አይበቃም ሰላምን መኖር እና ሰላማዊ ስብዕና መያዝ እንጂ ፡-


በኢትዮጵያ ወጣቶች ትስስር መረብ ህብረተሰባችንን በተለይም ወጣቱን ክፍል ስለ ሰላም
እና ስለሰላማዊ ስብዕና በተለያዩ ውይይቶችና ስልጠናዎች በማሳተፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ
ሰላማዊ ህብረተሰብን በመገንባት ሂደት ውስጥ ተሳታፊ እንሆናለን፡፡

15. አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ ግንዛቤ የማስጨበጥና እነሱንም አሳታፊ የሆኑ


ተግባራትን ማከናወን

• የአካል ጉዳት ያለባቸው ግለሰቦችን በተመለከተ ከአስተሳሰብ፣ እነሱን ለመግለፅ


ከምንጠቀማቸው አገላለፆችና ሌሎችም መታረም የሚገባቸው ነጥቦች ላይ ግንዛቤ መፍጠር እና
የአካል ጉዳት ያለባቸውን ግለሠቦች ያሳተፈ ተግባር ማከናወን

የ2013 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ መርሓ-ግብር መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት YNE  


 
 

16. በንፅህና አጠባበቅ ዙሪያ የግንዛቤ ፈጠራ ተግባራትን ማከናወን

• የአካባቢያችንን እና የከተማችንን ብሎም የሀገራችንን ንፅህና ለማስጠበቅ የግንዛቤ ፈጠራ


ተግባራትን ማከናወንና ሁሉም በየአካባቢው ለአካባቢው መቆሸሽ ምክንያት ባለመሆን
አርዓያነት ያለው ተግባር እንዲያከናውን ማስገንዘብና አስተሳሰቡን ማስረፅ ብሎም ማስተግበር

17. በሁሉም ዘንድ ኃላፊነትን የመወጣት ስሜትን መገንባትና ማስረፅ

• ለምሳሌ ማንኛውም የመሠረተ ልማት አውታር እንዲሁም ሥራ ከራሳችንም አልፎ ለልጅ


ልጅ እንዲተርፍ በጥራት እንድንገነባ፣ በአግባቡ እንድንጠቀምበት፣ ከጉዳት እንድንጠብቅና
መሠል በጎ ባሕሎችን በሁሉም ልብ ዉስጥ ማስረፅ።

በመጨረሻም አጋር አካላት ይህንን ጅምር በመደገፍ አብራችሁን እንድትሰሩ እየጠየቅን


በህብረተሰባችን ዘንድ ልናመጣ ያለምነውን አዎንታዊ ለውጥ ከልብ እንድትደግፉ እንዲሁም ይህን
ዲጂታል ማኅበረሰብ በልኩ እና በአንፃሩ በመድረስ ለምናደርገው ርብርብ በእውቀት የሆነ አብሮነት
ጊዜውን የሚመጥን ምለሽ እንድትሰጡን ከልብ እንጠይቃለን።

#እንደርሳለን
#ኢትጵያ #ተስፋ #አላት

ከኢትዮጵያዊ ክብርና ሰላምታ ጋር

ልዩነህ ታምራት
የኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሴሽን ፕሬዚደንትና
የኢትዮጵያ ወጣቶች ትስስት መረብ ኢንሼቲቭ ጠንሳሽ
ስልክ +251923706307
Email:-abusun17@gmail.com
Facebook:-­‐  Youth  Network  Ethiopia  

የ2013 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ መርሓ-ግብር መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት YNE  


 

You might also like