Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 76

ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ጥንታዊ
የኤዞፕ ተረቶች

አንደኛ መጽሐፍ

አዘጋጅ = መለሰ ማሩ (መሳይ)

ሐምሌ = 2012

1
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነዉ!


© አዘጋጅ = መለሰ ማሩ(መሳይ)
All Rights Resereved.

የመጀመሪያ ዕትም ሰኔ 2007


ሁለተኛ ዕትም ሰኔ 2010
ሦስተኛ ዕትም ሐምሌ 2012

ወገግታ አሳታሚ

+ 251-911-51-94 37

+ 251-929-32-75-75

+ 251-919-17-47-03

2
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

መቅድም

ኤዞፕ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ600 ዓ.ዓ ቀደም


ብሎ የኖረ ኢትዮጵያዊ ፈላስፍ፣ ተረት አዋቂና ድንቅ የሞራል
መምህር እንደነበር መዛግብትና የታሪክ ባለሞያዎች
ይናገራሉ፡፡ ከአስገራሚ ፍልስፍናዎች እስከ ጣፋጭ ተረቶች
ድረስ ለዓለም ሕዝብ አበርክቶ ያለፈዉ ይህ ታላቅ ሰዉ
ምንም እንኳን ታሪኩ ከትዉልድ ሀገሩ ኢትዮጵያ ይልቅ
ረዥም ዘመን እንደኖረባት በሚነገርላት ግሪክና ሊቃዉንቶቿ
ዘንድ ብዙ የተነገረ ቢሆንም ከእናት ሀገሩ በኩልም ቢሆን
እንደ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን ባሉ ዕዉቅ ጠበበብት መዘከሩ
አልቀረም፡፡ ይህ እዉቅ ፈላስፋና የተረቶች አዋቂ የሆነ ሰዉ
ለምድራችን ያበረከተዉ ብዙ ድንቃድንቅ ሥራዎች እንዳሉት
ቢገመትም አስከአሁን ድረስ ግን በይበልጥ የሚታወቀዉና
አድናቆትን ያገኘዉ በጣፋጭ ተረቶቹ በኩል ነዉ፡፡

በዘመናችን የኤዞፕ ተረቶች በተደጋጋሚ በምሳሌያዊ


ማስተማሪያዎችና በታሪክ ንግርቶች ሲቀርቡ ይስተዋላሉ፡፡
ይህም መሆኑ በቀላሉ እንዳይረሱና አስተማሪነታቸዉ ለሁሉም
እድሜ ክልል እኩል እየጣፈጠ የሚደርሱና ተወዳጅ
3
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በእያንዳንዱ


ሰው አዕምሮ ውስጥ አስገራሚ ጥበቦችን እየፈጠሩ ምስል
ከሳች በሆነ የእንስሳቶች ትዕይንት እያዝናኑ ፤ ከብልጠታቸው
ብልሃትን፣ ከሞኝነታቸው ታላቅነትንና ታናሽነትን ፣ከስህተታቸው
መታረምን ፣ ከኃያልነታቸው የበላይነትን ፣ እንዲሁም
በጠቅላላዉ በአሸናፊነትና በተሸናፊነት ስሜት እያዝናኑ
የሚያስተምሩ ታሪኮች ናቸዉና ለማንም ሰዉ ከመነበብ
አያሰለቹም፡፡

ይህ የኤዞፕ ተረት ወደ አማርኛ ሲተረጎም ፤ ከዚህ


ዘመንና ከማኅበረሰባችን ሥነ ልቦና ጋር ተስማሚነት
ያላቸውን ምሳሌያዊ አነጋገሮች አካቶ ለአዲሱ ትዉልድ
ተስማሚ እንዲሆንና ለኢትዮጵያውን ልጆች እንዲመጥን
ተደርጎ በታላቅ ጥንቃቄና የኃላፊነት ስሜት የተዘጋጀ ነዉ፡፡

በኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ ፍቅርን መተሳሰብን ግብረገብንና


እዉነተኛ ቅንነትን እንዲማሩ፤ብሎም በብልኁና በአስተዋዩ
ፈላስፋ ኤዞፕ ጣፋጭ ተረቶች በኩል ዕልፍ ቁምነገሮችን
እንዲጨብጡ ይህንን ዘመን አይሽሬ ድንቅ መጽሐፍ
ያነቡ ዘንድ በታላቅ ክብር ተጋብዘዋል፡፡

4
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

TITLE page nō

ርዕስ ገጽ ቁጥር

1. THE WOLF AND THE CRANE


ሽመላና ተኩላው………………………….…… 9
2. THE ANT AND THE DOVE
ጉንዳንና ዋኔ ………...………………....……12
3. THE ANTS AND THE GRASSHOPPER
ሙዚቀኛዋ እንጭራሪና ሠራተኛዋ ጉንዳን ……… 14
4. THE CROW AND THE PITCHER
የተጠማው ቁራና የውኃ ማሰሮ……………........17
5. THE NORTH WIND AND THE SUN
የሰሜኑ ንፋስና ፀሐይ ….……………………. 19

5
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

6. THE TWO TRAVELERS AND BEAR


አደገኛው ድብና ሁለት መንገደኞች….….……. 21
7. THE GOOSE AND THE GOLDEN EGG
የወርቅ እንቁላል የምትጥለው ዶሮ እናስግብግቡ ሰው….... 23
8. THE ASS IN THE LIONS SKIN
የአንበሳ ቆዳ የለበሰው አህያ .…...…………. 26
9. THE WOLF AND THE LAMB
ተኩላውና ሪማው …………………………… 28
10. THE FOX AND THE GRAPES
ቀበሮውና የወይን ዘለላው …………………. 30

11.MERCURY AND THE WOODMAN

ሜርኩሪውና ዛፍ ቆራጩ …...……………… 33


12. THE FOX AND THE GOAT
ቀበሮውና የፍየል ሙክቱ …….……………… 37

6
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

13. THE DOG AND HIS REFLECTION


ውሻውና ጥላው ……….…………….……… 42
14. THE FROG AND THE MOUSE
የአይጥና የእንቁራሪት ጓደኝነት ………………… 39
15. THE FOX AND THE STORY
ቀበሮውና ሽመላው …………….………….……. 44
16. THE WOLF IN SHEEP’S CLOTHING
የበግ ቆዳ የለበሰው ቆዳ ተኩኩላ ……….….……. 48
17. THE LION, THE ASS, AND THE FOX
አንበሳ ቀበሮና አህያ ……………………..…….. 51
18. THE FOX WITHOUT A TAIL
ጅራተ ቆራጣው ቀበሮ ……………..…………… 53
19. THE TRAVELERS AND THE PURSE
መንገደኞቹና የወርቅ ቦርሳው …………………… 56
20. THE FOX AND THE CROW
ጥበበኛው ቁራ …………………………………. 59
7
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

21. THE STAGE AND HIS REFLECTION


በቀንዶቹ ውበት የተደነቀው አጋዘን ……………… 62
22. THE MOTHER AND THE WOLF
ቂሉ ተኩላና ብልኋ እናት …….…………………. 64
23. THE LION AND THE MOUSE
አንበሳ እና አይጥ ………………………………. 66
24. THE WOLF AND THE GOAT
ተኩላና ፍየል ……….………….………………. 68
25. THE FARMER AND HIS SONS
ገበሬዉና የወይን ማሳዉ ……………….………. 70
26. The cooks fight
የዶሮዎች ጸብ …….………………….…..… 73
27. Bird and chiken

አንዲት ወፍና ጫጩቶቿ ……………..…… 75

8
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE WOLF AND THE CRANE

ሽመላውና ተኩላው

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ተኩላ ምግቡን ፍለጋ


ሲሄድ አንድ የሞተ እንስሳ አገኘ፡፡ ስጋውንም ተስገብግቦ
ሊውጥ ሲሞክር ከስጋው ጋር የተቀላቀለ አጥንት በጉሮሮው
ተሰነቀረበት፡፡

9
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

አጥንቱን ከጉሮሮው ለማውጣት ብዙ ሙከራ አደረገ፡፡ ነገር


ግን የተሰነቀረው አጥንት ከጉሮሮው ሊወጣለት አልቻለም፡፡
በመሆኑም የተሠነቀረውን አጥንት ሊያወጣለት የሚችል ኃይል
አጥቶ እያጓራ መጮህ ጀመረ፡፡

በአካባቢው የነበረች ሽመላ ወደ ሚጮኸው እንስሳ ቀርባ


ስታይ ከጉሮሮው አጥንት ተሠንቅሮበት የሚሠቃይ ተኩላ
ተመለከተች፡፡ ተኩላውም ባያት ጊዜ ሽመላዋን “እባክሽን ይህንን
አጥንት ከጉሮሮዬ እንዲወጣልኝ እርጂኝ ውለታሽን እከፍላለሁ ሲል
ተጽኖዉን አሰማ፡፡

ሽመላዋም እረጅ መንቆሯን ከተኩላው አፍ ዉስጥ ከትታ


የተሠነቀረውን አጥንት በማውጣት የተኩላውን ሕይወት ከሞት
አተረፈችለት፡፡ ተኩላውም እፎይታ ተሰማው፡፡

ሽመላዋም በል እንግዲህ የድካም ዋጋዬን ክፈለኝ


አለችው፡፡ ተኩላም ከሞት ያተረፈችውን ሸመላን ክዶ ዞር በይ
መንቆርሽን ከተኩላ አፍ አስገብተሽ በሠላም ማውጣትሽ ሳይበቃሽ
ውለታዬን ክፈለኝ ትያለሽ ከዚህ አካባቢ እርቀሽ ጥፊ በማለት
አባረራት፡፡

10
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች፡-

 ሰዎች ችግራቸውን እስኪወጡ ድረስ ሰዎችን ይለማመጣሉ፡፡

ችግራቸው ሲያልፍ ግን ሰውን ተመልሰው ማየት ይጠላሉ፡፡

ከእንደዚህ አይነት ሰዎች ተጠንቀቁ ደግ ለዋለላችሁ ክፉ

አትመልሱ፡፡

11
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

The aent and the Dave

ጉንዳንና ዋኔ

አንዲት ጉንዳን ወደ ወንዝ ወርዳ ውኃ ትጠጣ ነበር ነገር


ግን የተመቻቸ የውኃ መጠጫ ቦታ ባለማግኘቷ ተንሸራትታ ውኃ
ውስጥ ገባች፡፡ ውኃው ደራሹ ማዕበል ሞልቶ ስለነበር ጉንዳኗን
ከወንዙ ጅረት ጋር እየጋጨ ክፉኛ ያንገላታት ጀመር ከዛፍ ላይ
ሆና የጉንዳኗን ስቃይ የምትመለከት አንዲት ዋኔ ነበረች፡፡
12
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ጉንዳኗን ክፉኛ ከሚያንገላታት የውኃ ማዕበል ልታድናት አሰበች፡


፡ በውኃው በላይም እየበረረች አንድ የዛፍ ቅርንጫፍ ቆርጣ
ጣለችላት፡፡ ጉንዳኗም ዋኔም የጣለችላትን ቅርንጫፍ ተጠቅማ
የውኃውን ማዕበል መሻገር ቻለች፡፡ ለዋኔዋም ትልቅ ምስጋና
አቀረበች፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን ዋኔዋ ከዛፍ ላይ እንደተቀመጠች


አንድ አዳኝ ዋኔዋን በቀስት አነጣጥሮ ሊመታት ሲዘጋጅ ጉንዳኗ
ተመለከተች፡፡ ዋኔዋ የተነጣጠረባትን ቀስት አላየችም ነበር፡፡
ጉንዳኗም ክፉኛ የአዳኙን እግር ነከሰችው ባለቀስቱ አዳኝም
ደንግጦ ቀስቱን ጣለው የቀስቱን መውደቅ የሰማችው ዋኔም
ከዛፍ ቅርንጫፍ ላይ ተነስታ በረረች፡፡

ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች፡- በጎነት ቁጥር የሌለው


ደስታ ነው ዋኔዋም በረረች ከሞት አመለጠች፡፡ ቅን ስሩ
በክፉ ቀን ስንቅ ይሆናችኋል ዋኔም ጉንዳኗን ከማዕበሉ
በማዳኗ ጉንዳኗ ዋኔዋን አዳነቻት፡፡

13
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE ANTS AND THE GRASSHOPPER

ሙዚቀኛዋ አንበጣና ሠራተኛዋ ጉንዳን

በአንድ በረሃማ ቦታ አካባቢ አንበጣና ጉንዳን ተጎራብተው


ይኖሩ ነበር፡፡ አንበጣ ፌንጣ መሣይ በራሪ እንስሳ ስትሆን ጉንዳን
ደግሞ በመሬት ተራማጅ እንስሳ ነች፡፡ አንበጣ በጣም ዘፈን

14
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ወዳድ በመሆኗ ክረምት ከበጋ ጊዜዋን በመዝፈን ታሳልፍ ነበር፡


፡ በአንድ ወቅት ታዲያ ቀንም ሆነ ሌሊት መዝፈን የሚያስደስታት
አንበጣ የበጋውን ወራት በሙሉ ቤቷን ዘግታ ስትጨፍር ከረመች፡
፡ የበጋውም ወራት ተጠናቆ የክረምቱ ወራት መጣ፡፡

እንጭራሪትም የበጋው ወራት በሙሉ ስትዘፍንና ስትጨፍር


በማሳለፏ ለክረምት የሚሆናትን ጥራጥሬና ትላትል አልሰበሰበችም
ነበር፡፡ የክረምቱም ወቅት በጣም ከባድ የሆነ ዝናብ ማስተናገድ
ጀመረች የዛፍ ቅጠሎችን አረገፋቸው የመሬት ውስጥ ትላትሎችንና
ዝንቦችን ጎርፍ ጠራርጎ ወሰዳቸው፡፡

አንበጣም በክረምቱ ኃያልነት በጣም ተቸገረች፡፡ የዕለት


ምግቧንም ጭራ ለመብላት ተሳናት፡፡ ችግሯም እየጠና በመምጣቱ
ጎረቤቷ ጉንዳንን ጥራጥሬ ለመበደር ተገደደች፡፡ ወደ ጎረቤቷ
ጉንዳንም ቤት በመሄድ የክረምቱ ወራት እስኪያልፍ በቤቱ ውስጥ
ምንም አይነት የጥራጥሬም ሆነ የትላትል ባለመኖሩ ረሃብ
ሊገድለኝ ነው ክረምቱ ሲያልፍ የምከፍለው ጥራጥሬ አበድሪኝ
አለቻት፡፡

ጎረቤቷ ጉንዳንም አንበጣ በጋውን ወራት ምን ስትሰራ


እንዳሳለፈችው ስለምታውቀው የበጋውን ወራት ምን ስትሰራ
አሳለፍሽውና አሁን ቸገረሽ አለቻት፡፡ አንበጣም ሌቱንም ቀኑንም
ስዘፍን የበጋውን ወራት አሳለፍኩት አለቻት፡፡ ጉንዳንም በንዴት
15
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

እየመለከታችት ስትዘፍኝ ካስለፍሽማ እስክስታ ስትመኝ መክረም


ነዋ በማለት መለሰችላት፡፡ እንጭራሪትም እያዘነች ወደ ቤቷ
ተመለሰች፡፡

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች፡-

በዕቅድና በስርዓት ኑሩ::

ዝናብ ሳይዘንብ ቤት መስራት ነው፡፡

ችግር ሳይመጣ አስቀድሞ ማሰብ ብልኅነት ነዉ፡፡

16
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE CROW AND THE PICTHER

የተጠማው ቁራና የውኃ ማሰሮ

አንድ በበረሃ አካባቢ የሚኖር ቁራ ውኃ ለመጠጣት ወደ


ወንዝ ሲሄድ ውኃው ሁሉ ደርቆ ነበር፡፡ በአካባቢ ምንም አይነት
የሚጠጣ ውኃ ያለበትን አካባቢ ማፈላለግ ጀመረ፡፡

17
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ነገር ግን በአካባቢው ያሉት ወንዞች ደርቀው ነበር፡፡ ውኃ አግኝቶ


እስካልጠጣ ድረስ ግን መፈለጉን ላለማቋረጥ ወስኖ ፍለጋውን
ቀጠለ፡፡

በአንድ መንደር አካባቢም ደርሶ በሰማይ ሲያንዣብብ


አንድ ማሰሮ ተቀምጦ ተመለከተ፡፡ ወደ ማሰሮውም በተስፋ ወርዶ
ሲያይ ከማሰሮ ትንሽ ውኃ አየ ለመጠጣት ሞከረ ነገር ግን
የማሰሮው አንገት ጠባብ በመሆኑ ቁራው እንደፈለገ አንገቱን
አስገብቶ ለመጠጣት አልቻለም፡፡ በመሆኑም በጣም ተቸገረ፡፡
የውኃው ጥምም እየበረታበት መጣ፡፡

አሁንም ተስፋ ሳይቆርጥ የማሰሮውን ውኃ ሊጠጣበት


የሚችልበትን ዘዴ ማሰብ ጀመረ፡፡ ከዚያም በአካባቢው ጠጠር
ያለን ከአከማቸ በኋላ ማሰሮው መክተት ጀመረ፡፡ ማሰሮውም
በጠጠር እየሞላ ሲመጣ ከስር የነበረው ውኃ ከጠጠሩ ጋር ወደ
ላይ ቀረበለት፡፡ ቁራውም ከብዙ ጥረት በኋላ የማሰሮውን ውኃ
መጠጣት ቻለ፡፡

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች፡- ማጣት የፈጠራ እናት ናት ችግር


ብልሃትን ይወልዳል ይባላል፡፡ እናንተም ችግር ሲገጥማችሁ
በዕድላችሁ ከማዘን ለችግራችሁ መፍትሄ መፈለግ አለባችሁ፡፡

18
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE NORTH WIND AND THE SUN

የሰሜኑ ነፋስና ፀሐይ

ከዕለታት አንድ ቀን የሰሜን ንፋስና ፀሐይ ተገናኝተው


ሲጨዋወቱ ከሁለታችን በጥንካሬ ማን ይበልጣል መባባል ጀመሩ፡
፡ የሰሜን ነፋስ የራሱን ኃያልነት እየዘረዘረ ተናገረ፡፡ ፀሐይም
እንዲሁ ኃያል መሆኗን ስትገልጽ አንድ ጋቢ የለበሰ ሰው በመንገድ
ሲያልፍ ተመለከተ፡፡ ሁለቱም ኃይላቸውን በዚህ ሰው ላይ
ለመሞከር ተስማሙ፡፡ የሰሜኑ ነፋስም ፀሐይን “ኃያል መሆኔን
ዛሬ ላሳይሽ፡፡” በማለት መንገደኛውን ሰው በአውሎ ነፋስ
19
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ያዋክበው ጀመር፡፡ መንገደኛውም ሰው አደገኛው አውሎ ነፋስ


የለበሰውን ጋቢ እንዳይነጥቀው አጥብቆ መያዝ ጀመረ፡፡ ነፋሱ
ጋቢውን ለመንጠቅ ኃይሉን ጨመረ፡፡ መንገደኛውም የነፋሱን
አደገኛነት እየጨመረ ሲሄድ እርሱም ጋቢውን ይበልጥ አጥብቆ
በመያዝ ሊለቅለት አልቻለም፡፡

ፀሐይ ደግሞ በተራዋ ሙቀቷን ቀስ አድርጋ መልቀቅ


ጀመረች፡፡ አሁን መንገደኛው ምንም የሚያስፈራውና
የሚያስቸኩለው ነገር ባለመኖሩ ዘና ብሎ መጓዙን ቀጠለ፡፡
ፀሐይም እየቀደመም በቀስታ ሙቀቷን መልቀቅ ያዘች፡፡
መንገደኛውም ሰው እንደ ነፋሱ የሚያስደነግጥ ነገር ባለመኖሩ
ጋቢውን በማውለቅ ትከሻው ላይ አድርጎ መጓዝ ጀመረ፡፡ ፀሐይ
ቀጠለች፡፡ ያለ የሌለ ኃያል ሙቀቷን ለቀቀችው፡፡ መንገደኛውም
ትከሻው ላይ ያለውን ጋቢ ቀርቶ የለበሰውን ካፖርት አውልቆ
ጉዞውን ቀጠለ ፀሐይም በትዕግስት አሸነፈች፡፡

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች፡- ነገሮችን በኃይል ከማሳመን ይልቅ


በእርጋታና በብልኅነት መጓዝ ትልቅነት ነው፡፡

20
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE TWO TRAVELERS AND BEAR

አደገኛው ድብና ሁለት መንገደኞች

ከዕለታት አንድ ቀን ሁለት ጓደኛሞች እየተጨዋወቱ ይጓዙ


ነበር፡፡ ሞቅ ያለ ሳቅና ጨዋታቸውንም የሰማ አንድ የጫካ ድብ
ከጫካ ወጥቶ ድንገት ከተፍ አለባቸው፡፡
21
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ከሁለቱ ጓደኛሞችም አንደኛው ድቡን ቀድሞ አይቶት ነበርና


የድቡን መምጣት ለጓደኛው ሳይናገር ተሽቀዳድሞ ከትልቅ ዛፍ
ላይ ወጥቶ ተደበቀ፡፡ ሌላኛው ጓደኛው ግን ድቡን የያው ዘግይቶ
ነበርና ምን ማድረግ እንዳለበት አሰበ፡፡ ድብ የሞተ ሰው
አይበላም ሲባል ይሰማ ስለነበር የሞተ ሬሳ መስሎ መሬት ላይ
ተዘርቶ ተኛ፡፡

ድብም ወደ እርሱ በመቅረብ አፉን ጆውንና የጭንቅላቱን


አካባቢ ማሽተት ሲጀምር እርሱም የሞተ ሰው እንደሚሆነው
ትንፋሹን ዋጥ አደረገ፡፡ ድቡም ምንም አይነት የመንቀሳቀስና
የትንፋሽ ስሜት ሲያጣበት ትቶት ሄደ፡፡ ከዛፍ ላይ ተደብቆ
ሲመለከተው የነበረው ጓደኛም የድቡን ከአካባቢ ርቆ መሄድ
ሲያይ ከዛፍ በመውረድ ሁለቱ ጓደኛሞች ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ ዛፍ
ላይ ተሰቅሎ የድቡን ሁኔታ ሲመለከት የነበረውም “ጓደኛዬ ሆይ
ድቡ አፉን በጆሮህ አስጠግቶት ምን እያለህ ነበር?” አለው
ጓደኛውም የድቡን መምጣት ሳይነግረው ዛፍ ላይ ወጥቶ
በመደበቁ የተሰማውን በጓደኛው አለመተማመን ለመግለጽ
“በአደጋ ጊዜ ጥለው ከሚሸሹ ሰዎች ጋር ጓደኛ አትሁን” ብሎ
መከረኝ ሲል መለሰለት፡፡

ውድ የኢትዮጵ ልጆች፡- ከወስላቶች ጋር ጓደኛ አትሁኑ በአደጋ ጊዜ


ጓደኞቻችሁን አትካዱ፡፡

22
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE GOOSE AND THE GOLDEN EGG

የወርቅ እንቁላል የምትጥለው ዶሮ እናስግብግቡ ሰው

አንድ በድህነት የሚኖር ሰው በጎጆው ውስጥ ዶሮዎች


እያረባ የእለት ጉርሱን ከዶዎቹም የሚያገኘውን እንቁላል
በመሸጥ ያገኝ ነበር፡፡
23
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ከዕለታት አንድ ቀን ከሚያረባቸው ዶሮዎች መካከል አንዷ


የወርቅ እንቁላል መጣል ጀመረች፡፡ ዶሮዋ የምትጥለው የወርቅ
እንቁላልም እየሸጠ ሃብታም ሆነ ከተለያዩ ሃገር ለሚመጡ ሰዎች
በውድ ዋጋ እየሸጠ በጣም የከበረ ሀብታም ሆነ፡፡ ዶሮዋ በየቀኑ
አንዳንድ እንቁላል እየጣለች የምትሰጠው ሀብት አልበቃው አለና
ለምን ግን ይህች ዶሮ በቀን አንድ እንቁላል ከመጣል ይልቅ
ሁለት እና ሦስት የወርቅ እንቁላል አትጥልም በማለት ብዙ
እንቁላል በቀን እንድትጥልለት ተመኘ፡፡

ለብዙ ጊዜም ዶሮዋን ሁለትና ሶስት እንቁላል እንድትጥልለት


ከአንድ ቤት ዘግቶባት ይውል ነበር፡፡ ዶሮዋ ግን አሁንም ቢሆን
በቀን አንድ የወርቅ እንቁላል በላይ አትጥልም ነበር፡፡ በዚህነም
አልረካ ያለው ስግብግብ ሰው ዶሮዋን አርዶ ከሆዷ ውስጥ ያለውን
የወርቅ እንቁላል በሙሉ ለመውሰድ አሰበ፡፡

ቢላዋም ይዞ ወደ ዶሮዋ መኖሪያ በመምጣት ዶሮዋን


አረዳት ከሆዷ ውስጥ ግን የወርቅ እንቁላል አልነበረም ይልቁንም
በወርቅ እንቁላል ፈንታ ትንንሽ የእንቁላል አስኳል አገኘ፡፡
ስግብግቡም ሰው በአንዴ ለመክበር ሲቸኩል የዘላለም ሀብቱን
አጣ፡፡

24
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች በሀገራችን አባባል፦

የጅብ ችኩል አፍንጫ ይነክሳል፡፡

አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል፡፡

አተርፍ ባይ አጉዳይ፡፡

እንደሚባለዉ እንዳንሆን ልጆች ለእያንዳንዱ ድርጊት በቅድሚያ

ማሰብ ያስፈልጋል፡፡

25
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE ASS IN THE LIONS SKIN


የአንበሳ ቆዳ የለበሰው አህያ

ከዕለታት በአንድ ቀን አንድ አህያ የአንበሳ ቆዳ ለብሶ


ወደ አንበሶች ዘንድ ሄደ፡፡ በአካባቢው የሚኖሩ እንስሳቶች አንበሳ
መጣብን በማለት ከአካባቢው መሸሽ ጀመሩ፡፡

26
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

አስመሳዩና ኩራተኛው አህያም እንስሳቶቹ እሱን በመፍራት


ከአካባቢ በመሸሻቸው የአካባቢውን ሳርና ቅጠል እየበላ መደሰት
ጀመረ፡፡ በሄዱበት ቦታ እየተከተለ ማሳደዱንና ማሸማቀቁንም
ቀጠለበት፡፡ ኩራቱና ጥጋቡም ከልክ በላይ ሆነ፡፡ በየሜዳውም
እየዞረ የአንበሳን ድምጽ ያገሣ መስሎት የራሱን ጩኸት ማናፋት
ጀመረ፡፡

ይህንን ድምጽ በቅርብ ሆኖ የሰማች ቀበሮም በድፍረት


ወደ አስመሳዩ አህያ ቀርባ “አቶ አህያ ለካ አንተ ኖረሃል አንበሳ
መስለህ ስታሸብረን የነበረ” ከዛሬ ጀምሮ ለሁሉም እንስሳት
እነግርልሃለሁ በማለት ለሁሉም እንስሳት እየዞረች ተናገረች፡፡

አስመሳዩ አህያም አግኝቶ የነበረውን ክብር በጥጋቡ ብዛት


አጣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም በአንበሳው አምሳል ይረብሻቸው የነበሩ
እንስሳቶች አህያዉን በማስወገድ በሰላም ኖሩ፡፡

ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች፦

የራስ ባልሆነ ነገር መኩራት መጨረሻዉ ዉርደት ነዉ፡፡

በሀገራችን ዉሸትና ስንቅ እያደር ይቀላል እንደሚባለዉ፡፡


27
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE WOLF AND THE LAMB

ተኩላውና ሪማው

ከዕለታት አንድ ቀን ተኩላ ምግቡን ለማፈላለግ ወደ ወንዝ


ሲወርድ አንዲት ሪማ ወንዝ ዳር ቆማ ውኃ እየጠጣች ተመለከተ፡
፡ ተውኩላውም ሪማዋን ሰበብ ፈልጎ ለመብላት አሰበና ሪማም
ከምትጠጣበት ከፍ ብሎ ውኃ መጠጣት ጀመረ፡፡ ምክንያትና
ሰበብ ሲፈልግ የቆየው ተኩላም አንች ሪማ ለምንድን ነው
የምንጠጣውን ውኃ የምታደፈርሽብኝ? አላት፡፡ ሪማዋም ኧረ
ጌታዬ እኔ የምጠጣው ከታች ነው አንተ የምትጠጣው ከላይ ነው
እንዴት ውኃ ወደላይ ይሄዳልና ነው ውኃውን የማደፈርስብህ
አለችው፡፡

ተኩላውም ይህ እንደማያዋጣው ሲያውቅ “ባለፈው ዓመት


አባቴን ሰድበሻል!” አለ፡፡ ሪማዋም “ኧረ ጌታዬ ባለፈው ዓመት
እኮ እኔ ገና አልተወለድኩም ነበር” አለችዉ፡፡

ተኩላውም የፈጠረው መላ የማያዋጣው መሆኑን ሲያውቅ


ትንሽ ዝም ብሎ ከቆየ በኋላ አንቺ እንደሆንሽ የፈለገ ቢጠይቁሽ
መቼም መልስ አያልቅብሽ በማለት ዘሎ አነቃትና ቀረጣጥፎ በላት፡

28
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ልጆች፡- ሪማ ማለት የበግ ግልገል ነው፡፡ እሺ!

በሀገራችን አያ ጅቦ ሳታመካ ብላኝ፡፡


ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ጅግራ ነሽ ይሏታል፡፡ እንደሚባለዉ
አንዳንዶች ሌላዉን ሰዉ መጉዳት ሲፈልጉ የማይገናኝ ሰበብና
ምክኒያት ይደረድራሉ፡፡

29
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE FOX AND THE GRAPES

ቀበሮዉ እና የወይን ዘለላዉ

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ቀበሮ ከመኖሪያ ዋሻው ወጥቶ


የሚበላ ምግብ ፍለጋ ጉዞ ጀመረ፡፡ ነገር ግን እንደ አጋጣሚ
ቀኑን ሙሉ ሲዞር ቢውልም የሚበላ ነገር ባለማግኘቱ በዕድሉ

30
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

እያዘነ ወደ መኖሪያ ዋሻው ሲመለስ አንድ የሚያምር የወይን


ዛፍ በአንድ ማሳ ውስጥ ተንዥርግጎ አየ፡፡

በዚህ ጊዜ ቀበሮ የሚያስጎመጅ ፍሬ አፍርቶ ያየውን የወይን


ዘለላ ለመብላት በመጎምጀቱ ወደ ወይን ማሳው ዘልሎ ገባ፡፡ ነገር
ገን ቀበሮው የወይን ማሳውን ፍሬ እንደጠበቀው አላገኘውም፡፡
የወይን ዘለላው የሚገኘው ከፍ ባለ ቅርንጫፍ ላይ ነበር፡፡ የወይን
ዘለላውን ለመብላት የቋመጠው ቀበሮም ቁመቱ ወደ
ተንዠረገገው የወይን ዘለላ እሸት ባለመድረሱ የጓጓለትን የወይን
ዘለላ መመገብ የማይቻል ሆነበት፡፡

እየደጋገመ ወደ ወይን ዘለላው ቢያንጋጥጥ ሊደርስበት


አልችል አለ፡፡ ይባስ ብሎም ወደ ወይን ዘለላው ለመድረስ ሲዘል
ወድቆ ተሰበረ፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ከወደቀበት ተነስቶ
የተንዠረገገውን የወይን ዘለላ እሸት በንቀት እያየ እንዲያው
በከንቱ ደከምኩ እንጂ የወይን ዘለላውስ ገና አልበሰለም ነበር
በማለት እንደራበው ወደዋሻው ጉዞውን ቀጠለ፡፡
31
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች፡-

የማይችሉት ነገር ማንኳሰስ ወይም ማጣጣል ራስን መደለል ነው፡፡

ቀበሮው ያፈራውን የሚያስጎመጀውን የወይን ዘለላ የናቀ ማግኘት

ስለማይቻለው እንጅ የወይን ዘለላው ግን በስሎ ነበር፡፡

32
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

MERCURY AND THE WOODMAN

ሜርኩሪውና ዛፍ ቆራጩ

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ዛፍ ቆራጭ ሰው ከወንዝ ዳር


ያለ ዛፍ እየቆረጠ ሣለ ይቆርጥበት የነበረው መጥረቢያ ድንገት
ተወርውሮ ውኃ ውስጥ ገባበት፡፡

33
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ዛፍ ቆራጩም መጥረቢያው ድንገት ውኃ ውስጥ ገብቶ


በመስመጡ በማዘን ከወንዙ ዳር ቁጭ ብሎ ማልቀስ ጀመረ፡፡
የዛፍ ቆራጩንም ሀዘን የሰማ ሜርኩሪ የተባለው የውኃ ውስጥ
አድባር ወደ ዛፍ ቆራጩ ሰው ቀርቦ ለምን ወንዝ ዳር ተቀምጦ
እንደሚያለቅስና በሚያሳንዝን ትካዜ ውስጥ እንዳለ ጠየቀው፡

ዛፍ ቆራጩም መጥረቢያ ወደ ወንዝ ተወርውሮ


ስለገባበትና የሚያወጣለት በማጣቱ መሆኑን ለውኃው ውስጥ
አድባር (ለሜርኩሪው) ገለፀለት፡፡ የዛፍ ቆራጩን ሐዘን የተረዳው
ሜርኩሪም ወደ ውኃው ውስጥ ጠልቆ በመግባት አንድ በጣም
የሚያምር የወርቅ መጥረቢያ ይዞ በመመለስ ለዛፍ ቆራጩ ሰው
የጠፋብህ መጥረቢያ ይህ ነው በማለት የወርቅ መጥረቢያውን
አሳየው፡፡ ዛፍ ቆራጩም ሃቀኛና ታማኝ ሰው ስለነበረ ይህ የእኔ
መጥረቢያ አይደለም በማለት መለሰለት፡፡

የውኃው ውስጥ አድባር ሜሪኩሪም ለሁለተኛ ጊዜ ወደ


ውኃው ውስጥ ጠልቆ በመግባት አንድ ከብር የተሠራ መጥረቢያ
ይዞ ተመለሰ፡፡ ወደ ዛፍ ቆራጩም በመቅረብ ይህስ የአንተ
መጥረቢያ አይደለም ሲል ጠየቀው፡፡

ዛፍ ቆራጩም ይህም የእኔ መጥረቢያ አይደለም፡፡ ሲል


መለሰለት፡፡ ሜርኩሪውም ለሦስተኛ ጊዜ ወደውኃው ጠልቆ
በመግባት ከዛፍ ቆራጩ አጅ አምልጦ ወደ ውኃው ውስጥ
34
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

የገባውን መጥረቢያ ይዞ ተመለሰ፡፡ ዛፍ ቆራጩም በደስታ ይህ


የእኔ መጥረቢያ ነው አለ፡፡ ሜርከኩሪውም በዛፍ ቆራጩ
ታማኝነትና ሃቀኝነት ተደስታ ወደ ወንዙ ውስጥ ጠልቆ በመግባት
በፊት ያሳየውን የወርቅና የብር መጥረቢዎቹን ጨምሮ ሰጥቶ
ሸኘዉ፡፡

ዛፍ ቆራጩም የውኃውን ውስጥ አድባር ሜርኩርን


እያመሰገነ ሦስቱን መጥረቢያዎቹን ይዞ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡
የዛፍ ቆራጩን የወርቅና የብር መጥረቢያ የተመለከተ ጎረቤቱም
ሁለቱን መጥረቢያዎች የት እንዳገኛቸው ጠየቀው ዛፍ ቆራጩም
በውሎው የገጠመውን የሜርኩሪውን የመጥረቢያውን ታሪክ
ለጎረቤቱ ወዲያዉ አጫወተው፡፡

የዛፍ ቆራጩ ጎረቤትም ስግብግብና ቀናተኛ በመሆኑ


ሜርኩሪው ለዛፍ ቆራጩ እንዳደረገለት ሁሉ ለእኔም ያደርግልኛል
በማለት ቤቱ ውስጥ ያስቀመጠውን መጥረበያ ይዞ ወደ ወንዝ
ወረደ፡፡ ስግብግቡ ሰው ይዞት የሄደውን መጥረቢያ አውቆ ወደ
ውኃው ውስጥ በመወርወር ከወንዙ ዳር ተቀምጦ ማልቀስ ጀመረ
የውኃው ውስጥ አድባር (ሜርኩሪ) ለሚያለቅሰው ሰው ተገለፀለትና
አንተ ሰው እዚህ ወንዝ ዳር ተቀምጠህ “ለምን ታለቅሳለህ?”
ሲል ጠየቀው፡፡ ወደ ውኃው ውስጥ መጥረቢያውን አውቆ
የወረወረው አስመሳዩም ሰው ለውኃው ውስጥ አድባር ሜርኩሪ
ድንገት መጥረቢያዬ ወደ ወኃው ውስጥ ነጥቆኝ ወደቀ በማለት
35
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

በሚያሳዝን ሁኔታ ሌላ ንብረት እንኳን የለኝም ይህች መጥረቢያ


ከጠፋች እንጨት በምን መቁረጥ እችላለሁ እባክህ መጥረቢዬን
አውጣልኝ በማለት ለመነው፡፡

ሜርከኩሪም ወደ ወንዙ ውስጥ ጠልቆ በመግባት አንድ


የወርቅ መጥረቢያና አንድ የብር መጥረቢ ይዞ ብቅ አለ፡፡
ሁለቱንም መጥረቢዎች ለአስመሳዬ ዛፍ ቆራጭ እያሳየው የአንተ
መጥረቢያ የትኛው ነው የወርቁ ነው ወይንስ የብሩ በማለት
ጠየቀው፡፡ አስመሳዩ ዛፍ ቆራጭም ስግብግብ ከመሆኑ የተነሳ ገና
የወርቁን መጥረቢያ እንዳየ አዎ እሱ የወርቁ መጥረቢያ የእኔ
ነው አለ፡፡ ሜርኩሪም በዛፍ ቆራጩ ስግብግብነትና ጮሌነት
ተገርሞ ለአንተስ እንኳን የወርቅ መጥረቢያ የብረትም
መጥረቢያ አይገባህም በማለት ሁለቱንም መጥረቢያዎች ወደ
ወንዙ በመወርወር የእራሱንም መጥረቢያ ሳያዋጣለት ከአካባቢው
ተሰወረ፡፡

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች፦

ያለፋችሁበትን ገንዘብ አትመኙ::

የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣልና::

36
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE FOX AND THE GOAT

ቀበሮውና የፍየል ሙክቱ


ከዕለታት አንድ ቀን ቀበሮ በጥልቀት ጉድጓድ አካባቢ ሲያልፍ
ሳያስበው ተንሸራትቶ ከጥልቀት ጉድጓድ ውስጥ ወደቀ፡፡

ጉድጓዱም እጅግ ጥልቀት የነበረው በመሆኑ ወደ ላይ


ለመውጣት አደጋች ሆነበት፡፡ ከጉድጓድ ለመውጣት መፍጨርጨርና
37
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

መጮህ ሲጀምር በአካባቢው እያለፈ የነበረ የፍየል ሙክት


ጩኸትን ሰምቶ ወደ ጉድጓድ በመቅረብ ወደ ታች ሲመለከት
ቀበሮ ከውስጥ ሆኖ ሲጮህ ተመለከተ፡፡

ፍየሉም ቀበሮውን አይቶ “ከዚህ ጉድጓድ ውስጥ ምን


ትሠራለህ? ለምንስ ትጮሃለህ?” ሲል ጠየቀው ቀበሮም ፈጠን
ብሎ “የጠጣሁት ውኃ አስደስቶኝ ነው፡፡” ሲል መለሰለት፡፡

የፍየሉ ሙክትም “ውኃ አለ እንዴ?” አለ ወደታች


እየተመለከተ፡፡ ቀበሮውም “ና ጠጣ ይጣፍጣል” አለ፡፡ ፍየሉም
የቀበሮውን ምክር ሰምቶ ወደ ጉድጓድ ዘልሎ ገባ ውኃውንም
የሚበቃውን ያህል ጠጣ፡፡ የፍየል ሙክቱ ልክ እንደቀበሮ ሁሉ
የመውጫው ነገር አሳሳቢ የሆነበት በኋላ ነበር፡፡ እንዴት መውጣት
እንደሚችሉም ቀበሮን ጠየቀው፡፡

ቀበሮም ብልጥ በመሆኑ የአንተ ቁመት ረጅም ስለሆነ


ከታች ሆነህ እኔን ወደላይ ግፋኝ እኔ ከወጣሁ በኋላ የአንተን
ቀንድ ይዤ ወደላይ ጎትቼ አወጣሃለሁ አለው፡፡

ፍየሉም በቀበሮ ሃሳብ ተስማማ ቀበሮው ከፍየሉ ጀርባ ላይ


ሆኖ ጉድጓዱን መውጣት ቻለ፡፡ ቀበሮውም ጥልቁን ጉድጓድ ከወጣ
በኋላ ፍየሉን ማውጣት ትቶ መንገዱን ቀጠለ፡፡

38
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ፍየሉም ምነው ጓደኛዬ እኔንም አውጣኝ እንጂ ሲለው


የአንተ ክብደት ወደ ታች ጎትቶኝ ተመልሼ ጉድጓድ ውስጥ
እንድገባ ትፈልጋለህ በማለት ትቶተት መንገዱን ቀጠለ፡፡

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች፦
በችግር ጊዜ የደረሰላችሁን ሰው ችግራችሁ ሲያልፍ አትርሱ፡፡

39
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE DOG AND HIS REFLECTION

ውሻውና ጥላው

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ውሻ የአጥንት ሥጋ በአፉ


ይዞ ወደ ቤቱ ይሄድ ነበር፡፡ ውሻው በአፉ ያንጠለጠለውን ስጋ
እንደያዘ አንድ የወንዝ ድልድይ ማቋረጥ ጀመረ፡፡ ውሻው

40
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ድንገት ወደ ውኃው ሲመለከት የራሱ ጥላ በትልቁ ተንፀባርቆ


ተመለከተ፡፡

በመሆኑም ውኃው ውስጥ ባየው ትልቅ የአጥንት ስጋ


ገመዠ፡፡ ውሻው ወንዙ ውስጥ ያየው የአጥንት ስጋ አሳስቶች
ስለነበረ ለመቀማት ዘሎ ገባ፡፡ ውኃው ውስጥ ያለውን ውሻም
ያገኘ መስሎት አፉን ከፍቶ ለማነቅ ሲጣደፍ በአፉ የያዘውን
የአጥንት ስጋ ውኃው ወሰደበት፡፡ ሊይዘው አስቦት የነበረው ስጋና
ውሻ ግን አልነበሩም፡፡ ውኃ ውስጥ የተመለከተው የራሱን ጥላ
ነበርና፡፡

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች፡-

የራሳችሁን በጥንቃቄ መያዝ ሳታረጋግጡ የሌሎችን ለመያዝ

አትመኙ፤ የሌሎች የሆነን ነገር ለመቀማት ሲሄድ የራስንም

ማጣት አለና፡፡

41
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE FROG AND THE MOUSE


የአይጥና የእንቁራሪት ጓደኝነት

በአንድ ወቅት እንቁራሪትና አይጥ በጓደኝነት አብረው ይኖር


ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን እንቁራሪት ጓደኛው አይጥን ውኃ
ውስጥ የሚገኘው መኖሪያውን ሊያስጎበኘው ፈለገ፡፡

42
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

አይጥ ግን በውኃ ውስጥ መዋኘት ስለማይቸል የጓደኛውን


የውኃ ውስጥ ጉብኝት ለመቀበል ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ በመሆኑም
እግሩን ከእራሱ እግር ጋር አጥብቆ አስሮ የጓደኛውን ችግር ምንም
ሳይረዳ ወደ ውኃው ውስጥ ይዞት በመግበት መዋኘት ጀመረ፡፡

እግሩ የታሰረው አይጥን በውኃው ውስጥ መዋኘት ባለመቻሉ


ውኃው በአፍሩና በአፍንጫው እየገባ ተንፋሽ ያሳጣው ጀመር፡፡
ጓደኛው እንቁራሪት ግን በውኃ ውስጥ የመኖር ልምድ ስለነበረው
እሱ በውኃ ውስጥ ሆኖ ጓደውን በጀርባው አዝሎ ይጓዝ ጀመረ፡፡

አይጡም በፍርሃት ሕይወቱን ለማትረፍ ውኃው ውስጥ ብቅ


ጥልቅ እያለ መጓዛቸውን ቀጠሉ፡፡ የዚህን አይጥ እንቅስቃሴም
ያየች ጭልፊት ወደ ወንዙ በመውረድ ብቅ ጥልቅ የሚለውን
አይጥ መጭልፉ ከወንዙ ይዛው ወጣች፡፡

በዚህ ጊዜ ከአይጡ እግር ጋር የታሠረውም እንቁራሪት


ከአይጡ ጋር አብሮ ተንጠልጥሎ ወጣ፡፡ ጭልፊትም በአንድ ድንጋይ
ሁለት ወፍ እንዲሉ ሁለቱንም ቅርጥፍ አድርጋ በላቻቸው፡፡

43
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች፦

እናንተን ከማይመስል ሰው ጋር ጓደኝነት አትጀምሩ፡፡

የራሳችሁን ብቻ አይታችሁ ሰዎችን ያለ አግባብ አትበድሉ ለሰው

ያሉት ለራስ ይደርሳልና፡፡

44
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE FOX AND THE STORY

ቀበሮውና ታሪኩ

ከዕለታት አንድ ቀን ቀበሮ ወዳጁን ሽመላ እራት ጋበዛትና


ወደ ቤቱ ወሰዳት፡፡ ቀበሮም ለእራት ግብዣዉ ያዘጋጀው ምግብ
ሾርባ ሲሆን ያቀረበውም በዝርግ ሣህን ነበር፡፡

ስስታሙ ቀበሮ ለተንኮል ነበር የእራት ሾርባውን በዝርግ


ሳህን ያቀረበው፡፡ ዝርጉ የሾርባ ሳህን ለሽመላ የሚመች ባለመሆኑ
እረጅሙ መንቆሯ በዝርጉ ሣህን ላይ የቀረበውን ሾርባ ሊጠጣላት
አልቻለም ነበር፡፡ ቀበሮ ግን በዝርጉ ሳህን ላይ የቀረበውን ሾርባ
ሙጭልፍ አድርጎ ጠጣው፡፡ ሽመላም በቀበሮ ድርጊት እያዘነች
ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡

ሽመላም ከብዙ ቀናት በኋላ ብድሯን ለመመለስ አስባ


ቀበሮውን የእራት ግብዣ ወደ ቤቷ ጠራችው፡፡ ቀበሮም የሠራውን
ተንኮል እረስቶት ስለነበር ወደ ሽመላ ቤት ለግብዣ ሄደ፡፡
ሽመላም ለግብዣው ያዘጋጀው ምግብ በጣም የሚማርክ በመሆኑ
ስለነበር ቀበሮውን ገና በሩቅ ሽታው ምራቁን አስውጦት
እስኪቀርብለት ቸኩሎ ነበር፡፡ ሽመላም የተዘጋጀውን ምግብ

45
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ማቅረብ ጀመረች፡፡ ምግቡ ቀርቦ እስኪበላ ቸኩሎ የነበረው ቀበሮ


ምግቡ ይቀርባል ብሎ ያሰበው በዝርግ ሳህን ነበር፡፡

ሽመላ ግን ምግቡን በአንገተ እረጅሙ ኩልኩልት /ማሠሮ/


አቀረበች፡፡

ቀበሮም ከአንገተ ጠባቡ ኩልኩልት /ማሠሮ/ አንገቱን


ለማስገባት ቢሞክር የማይቻል ሆነ፡፡ ቀበሮ ቆሞ ምራቁን
ሲያዝረበርብ ሽመላ ያንን አንገት እረጅም መንቆሯን ወደ

46
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ኩልኩልቱ /ማሰሮው/ እያስገባች እያስወጣች ምግቡን ሙጭልፍ


አድርጋ በላች፡፡

ቀበሮውም በሠራው ተንኮል ቅጣቱን ተቀብሎ ምግቡን


ለመብላት እንደቋመጠ ምንም ሳያገኝ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች፡-

ብድር በምድምር ይላችኋል ይሄ ነው፣ በሰው ክፉ ስትሰራ


በእናንተም እንደሚደርስ አስታውሱ ምክንያቱም ሰው የዘራውን
ያጭዳል፡፡

47
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE WOLF IN SHEEP’S CLOTHING


የበግ ቆዳ የለበሰው ቆዳ ተኩኩላ

ከዕለታት አንድ ቀን በእረኛው ትጋት በግ ማግኘት ያልቻለ


አንድ ተኩላ የመንጋውን በግ እረኛ ለማታለል አሰበ፡፡ በመሆኑም
የበግ ቆዳ ለብሶ መንጋውን በግ ተቀላቀለ፡፡ እረኛውም ቀኑ መሸት
48
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ባለ ጊዜ የበግ መንጋዎቹን ወደ ማደሪያ ጎረኖ ወስዶ በደንብ


አጥብቆ ዘግቶ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ ተንኮል ያሰበው ተኩላም የበግ
ቆዳውን ለብሶ ከመንጋው ጋር ተቀላቅሎ ወደ ጎረኗቸው ገባ፡፡
ነገር ግን ጎረኗቸው ከውጭ በጥብቅ በመዘጋቱ መውጫው ከባድ
መሆኑን ተረዳ፡፡

የተኩላው ሃሳብ የበግ እረኛው ሌሊት እንቅልፍ ሲወስደው


ጠብቆ የጎረኖውን በግ በሙሉ ለመብላት ነበር፡፡ ነገር ግን
መግቢያውን እንጂ መውጫውን ያላሰበው ተኩላ ቦሩ
እንደተዘጋበት ከመንጋው ውስጥ ሆኖ መጨነቅ ጀመረ፡፡ በዚያን
ቀን ምሽት የበጎቹ እረኛ ከጠቦት ግልገሎቹ አንዱን ለማረድ አስቦ
ስለነበር ነበር የሰላ ቢላዋውንም ይዞ ወደ በጎቹ በረት በመግባት
የጠቦቶቹን ወገብ እየጨበጠ ደህና ስጋ የያዘውን ጠቦት መምረጥ
ጀመረ፡፡

ተንኮለኛው ተኩላም ለምዱን እንደለበሰ ቆሞ እንደ በጎቹ


መመረጥ ጀመረ፡፡ እረኛው ደህና ስጋ የያዘውንም ጠቦት
ሲያማርጥ በአጋጣሚ የተኩላውን ወገብ ጨበጠው፡፡ ተኩላውም
ወፈር ያለ በመሆኑ ደህና ስጋ የያዘ መሰለውና ወደ ቤቱ እየገተቱ
ይዞት ሄደ፡፡ ቤቱ እንደደረሰም በስለት ቢላዋ አንገቱን ባረከው፡

49
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

የበጎቹ እረኛም ተኩላውን ከባረከ በኋላ ቆዳውን ለመግፈፍ


ሲዘጋጅ ያረደው የበግ ጠቦት ሳይሆን የበግ ቆዳ ለብሶ የቆመውን
ተኩላ መሆኑን ተረዳ፡፡ ተኩላውም በተንኮሉ ሕይወቱን አጣ፡፡

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች፡-

ጎሮኖ ወይንም በረት ማለት የበጎች ማደሪያ ማለት ነው፡፡

አንድ ሥራ ስታስቡ መጀመሪያችሁን ሳይሆን መጨረሻችሁን


አስውሉ፡፡

እበልጥ ሲሉ ከመበለጥ ፣ እበላ ሲሉ ከመበላት ፣ እሠርቅ ሲሉ


ከመሠረቅ ተጠንቀቁ፡፡

50
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE LION, THE ASS, AND THE FOX

አንበሳ ቀበሮና አህያ

ከዕለታት አንድ ቀን አንበሳ ቀበሮና አህያ በጓደኝነት


ተስማምተው ለአደን ወደ ጫካ ወረዱ፡፡ ቀኑንም ሙሉ ያደኑትን
ግዳይ ከሰበሰቡ በኋላ አንበሳ አህያን ጠርቶ የተሰበሰበውን ሥጋ
እንድታካፍል አዘዛት፡፡

አህያም ስጋውን ሶስት ቦታ ላይ እኩል ለከፋፈለች በኋላ


አንበሳን የመረጥከውን ውሰድ አለችው፡፡

አንበሳም በአህያዋ ድርጊት በጣም በመቆጣት አንክትክት


አድርጎ በላት፡፡ በኋላም ወደ ቀበሮው በመዞር “በል አንተ
አካፍለን?” አለው፡፡ ቀበሮውንም ጥሩ ጥሩውን ስጋ በአንድ ቦታ
ከቆለለ በኋላ በሌላ በኩል ደግሞ ትንንሽ ቅንጥብጣቢ ስጋዎችንና
አጥንቶችን በማስቀመጥ አንበሳን የመረጥከውን ውሰድ አለው፡፡

አንበሳም ቀበሮውን እንደዚህ ማካፈልን የት ተማርከው


ብሎ ቢጠይቀው በአህያው ላይ የደረሰውን በማየት ሲል
መለሰለሰት ይባላል፡፡
51
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ይህ ታሪክ የእንስሳቶችን የበላይነትና የበታችነት ለማሳየት


እንዲሁም ተረቱን ለማሳመር ሲባል እንጂ አህያ ስጋ በል እንስሳ
አይደለችም፡፡

ውድ የኢትዬጵያ ልጆች፦

ከሌሎች የሚማሩ እጅግ ብልሆች ናቸው፡፡

52
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE FOX WITHOUT A TAIe

ጅራተ ቆራጣው ቀበሮ

አንድ በጉብዝናው የሚታወቅ የቀበሮዎች አለቃ ነበር፡፡


ከዕለታት አንድ ቀን ለአደን ወደ ጫካ ሲሄድ አዳኞች ጅራቱን
በወጥመድ ያዙት፡፡ ቀበሮው ከአዳኞች ወጥመድ ለማምለጥ
ጥረት አደረ ገነገር ግን የቀበሮውን ጅራት የያዘው ወጥመድ በ

53
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ጣም አደገኛ ነበር፡፡ በመሆኑም አደገኛው ወጥመድ ጅራቱን


የማይለቀው መሆኑን ተገነዘበ፡፡ ቀበሮው የነበረው ብቸኛ
አማራጭ ጅራቱን ቆርጦ ሌላውን አካሉን ማዳን ነበር፡፡

በዚህም ምክንያት ጅራተ ቆራጣ ሆነ፡፡ በኋላ ግን አንድ


ሃሳብ እየተመላለሰ ይረብሸው ጀመር፡፡ ምክንያቱም እንዴት
የቀበሮዎች ሁሉ አለቃ ጅራተ ቆራጣ ሆነ የሚለው የጓደኞቹ
ቀልድና ሹፈት ታሰበው፡፡ ሃፍረቱም ለሁልጊዜ
እንደማያስቀምጠው ተረዳ፡፡

ከዚህም የተነሳ አንድ ቀን ዘመዶቹንና የቀበሮን ዝርያ


በሙሉ ስብሰባ ጠራ፡፡ እንዲህ አለ “ጅራታችን ምንም
ማይጠቅመን ለጠላቶቻችን ወጥመድ የሚያጋልጠን ጥቅም
የሌለው አካል በመሆኑ መቆረጥ አለበት” በማለት የጅራን ጥቅም
አልባነት እየገለጸ ማስተበበል ጀመረ፡፡

የጅራቱ ቆራጣውንም ቀበሮ ሃሳብ በጥሞና ሲከታተል የቆየ


አንድ ቀበሮ ተነስቶ የተከበረው አለቃችን “የአንተ ሀሳብ
ገብቶናል!” የራስህ ጅራት ቢቆረጥብህ ለምን የእኛ እንዲቆረጥ
ታስባለህ? በማለት አሳፍረው፡፡ ጅራተ ቆራጣው ቀበሮም ሀፍረቱን
ተከናንቦ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡

54
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች፦

በእናንተ ላይ የደረሰ ክፉ ነገር በሌሎችም ላይ እንዲደርስ


አትመኙ፡፡

55
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE TRAVELERS AND THE PURSE


መንገደኞቹና የወርቅ ቦርሳው

56
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሽማግሌና ወጣት በአንድ ላይ


እየጠጨዋወቱ ሲጓዙ አንድ የተጠቀለለ ቦርሣ መንገድ ላይ ወድቆ
አገኙ፡፡

ወጣቱ መንገደኛም ፈጠን ብሎ የወደቀውን ቦርሣ


በማንሳት በውስጡ የያዘውን ዕቃ ተመልከተ፡፡ ቦርሳውም በወርቅ
የታጨቀ ነበር፡፡

ወጣቱ መንገደኛም ቦርሳው በወርቅ የታጨቀ መሆኑን


ሲያይ ወደላይ እያንጋጠጠ “ኦ! አምላኬ ለሕይወቴ
የሚያስፈልገኝን ገንዘብ ሰጠኸኝ” አለ፡፡

ሽማግሌው መንገደኛም “ምነው ልጄ ለሁለታችንም ሰጠን


በል እንጂ ለአንተ ብቻ ነው እንዴ የሰጠህ” አሉ፡፡ ወጣቱ
መንገደኛም ቦርሳውን ጠበቅ አድርጎ ያዘ “አብረን አየነው እንጂ
ቀድሜ ያነሳሁት እኔ ነኝ ማየት ምን ጥቅም አለው ቀድሞ
ማንሳት ነው እንጂ” አለ፡፡

ሽማግሌውም እንደፈቀድከው ይሁንልህ በማለት


እየተጨዋወቱ መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡ ነገር ግን ብዙ አልተጓዙም
ፈረሰኞቹ ከኋላቸው እየሮጡ ሌባ ሌባ በማለት ወደነሱ ሲገሰግሱ
ተመልከቱ፡፡ ወጣቱ መንገደኛም ወደ ሽማግሌው በመዞር “ጉዳችን
ፈላ አባቴ ችግር ላይ ልንወድቅ ነው?” አለ፡፡

57
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ሽማግሌውም ቆጣ ብለው “ምነው አንተ ጉዴ ፈላ በል


እንጂ እንዴት ጉዳችን ፈላ ትላለህ የአነሳኸው አንተ ችግሩም
ጉዱም የአንተ በል እንዲህ ቻለው” ብለውት መንገዳቸውን ቀጠሉ፡
፡ ወጣቱም በፈረሰኞቹ ተይዞ ወደ ከተማ በመሄድ ለፍርድ ቀረበ፡

ዉድ የኢትዬጵያ ልጆች፡-

ለእያንዳንዱ ነገር ቀድሞ ከመናገርና ያለ ጥንቃቄ ከመተግበር


ተቆጠቡ ይህ ታሪክ አስተዋይ መሆን ሚመክር ታሪክ ነው፡፡

58
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE FOX AND THE CROW

ጥበበኛው ቀበሮና ቁራ

ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ቀበሮ ምግቧን ፍለጋ


ወጣ ብላ ዞር ስትል አንድ ቁራ ከትልቅ የዛፍ ቅርንጫፍ
59
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ላይ ተቀምጦ በአፉ ሙዳ ስጋ ይዞ ተመለከተች ቀበሮም


በአፉ የያዘውን ስጋ ለመቀማት በማሰብ ዘዴ ማፈላለግ
ጀመረች፤ ወደ ቁራም ቀና ብላ እየተመለከተች “አያ ቁራ
መረዋ ድምጽህ የሚያምር አንተ ከሌሎች እንስሳት ሁሉ
የተለየህ ነህ፡፡

ንጉሥነት የሚገባህ ለአንተ ነበር፡፡ የምታኮራ ነህ”


በማለት ማሞጋገስ ጀመረች፡፡ ቁራም ቀበሮ በነገረችው
ክብርና ሞገስ ተደስቶ የሚያምረውን ድምጹን ለማሰማ
አፉን ከፈተ፡፡ በዚህ ጊዜም በአፉ ነክሶ ይዞት የነበረውን
ሥጋ መሬት ላይ ጣለው፡፡ ቀበሮም ትንሽ አዕምሮ ቢያድልህ
ምናለበት እንኳን ንጉሥነት ምንም አይገባህም በማለት
የወደቀላትን ስጋ ይዛ ወደ ዋሻዋ ተመለሰች፡፡

60
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ውድ የኢትዮጲያ ልጆች፦

ባልሰሩት ነገር መኩራራትና አጉል ሙገሳን መፈለግ


የራስን ነገር ያስጥላልና ከዚህ ተጠንቀቁ፡፡

61
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE STAGE AND HIS REFLECTION

በቀንዶቹ ውበት የተደነቀው አጋዘን

ከዕለታት አንድ ቀን አጋዘን ወደ ወንዝ ወርዶ ውኃ ሲጠጣ


ኩልል ብሎ ጥርት ባለዉ ምንጭ ላይ የራሱን ውበት እስከ ግርማ
ሞገሱ ተመለከተ፡፡ ባለው ግርማ ሞገስ ከቀንዶቹ ጀምሮ ማድነቅ
ጀመረ የቀንዶቹ ርዝመትና ውበታቸው በጣም አስደንቆታል፡፡
62
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ከትንሽ ቆይታ በኋላ ግን እግሮቹን ተመለከተ፡፡ እግሮቹ


እንደ እንዝርት ቀጫጭን መሆናቸው አየ፡፡ በድንገት አንበሳ
ተወርዉሮ ሊያንቀው ሲመጣ አየና በእነዚያ አስቀያሚ ቀጫጭን
እግሮቹ ተፈትልኮ አመለጠ፡፡ አንበሳው እየተከተለ አባረረው
አጋዘኑም ቀንዶቹ በጫካ ውስጥ በተተበተቡ አረጎች መሃል ገብተው
ተቀረቀሩበት፡፡ እነርሱንም ከሃረጎቹ ለመንቀልም ብዙ ታገለ ነገር
ግን አልሆንልህ ብሎት ሲለፋ አንበሳ ደረሰና ዘሎ ተጎመረበት፡፡

የአጋዘኑም የመጨረሻ ቃል “እንደዚያ ሳያቸው ያሳፈሩኝ


እግሮቼ ከአደጋ ሲያድኑኝ የተመካሁባቸው ቀንዶቼ ግን ለጠላት
አጋለጡኝ” የሚል ነበር፡፡

ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች፡-

አንዳንዴ መልክ ከቁም ነገር ጋር ሲሆን መልካም ነው፡፡ ነገር ግን

ውበትን ከቁም ነገር አብልጦ ራስን እንደትልቅ መቁጠር በጎ

አይደለምና ይልቁንም ባላችሁ ነገር ላይ ተጠቀሙ፡፡

63
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE MOTHER AND THE WOLF

እናትዬዉ እና ቂሉ ተኩላ

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ የተራበ ተኩላ ምግቡን ፍለጋ


በመንደር ውስጥ ገብቶ መዞር ጀመረ፡፡ ተኩላው ከአንድ ቤት
ውስጥም የህፃን ልጅ ለቅሶ በመስማቱ ወደ ግድግዳው ተጠግቶ
ማድመጥ ጀመረ፡፡

64
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

የህፃኑን ልጅ ለቅሶም ለማስቆም እናቱ “አንተ ልጅ


ለቅሶህን ካላቆምክ ለተኩላው ነው የምሰጥ” ስትል ሰማ፡፡
ተኩላም ከግድግዳው ተጠግቶ የሚያለቅሰውን ልጅ አውጥታ
ትሰጠኛለች በማለት መጠባበቁን ቀጠለ፡፡

ተኩላው የልጅ ለቅሶ እየጨመረ በሄደ ቁጥር አሁን አሁን


ልጁም ለቅሶውን አላቆም ሲል እናትየዉም በመጨረሻ “አይዞህ
የእኔ ልጅ ዝም በል ይህ ተኩላ ነው አይደል የሚያስፈራራህ አባትህ
ሲመጣ ግድል ያደርገዋል፡፡” የሚለዉን ቃል ሲሰማ ቂሉ ተኩላ
ከግድግዳው ተጠግቶ አምሽቶ እያዘነ ወደ ጎሬው ተመለሰ፡፡

ዉድ የኢትዬጵያ ልጆች፡- ያልሆነ የማታምኑበትን ተስፋ


አትጠብቁ የዘመኑ ሰዎች ተስፋ ለመስጠት ቀልጠፎች ናቸው ነገር ግን
ከተስፋ መስጠት የዘለለ እምነት ያላቸው ትንሾች ናቸው፡፡

65
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE LION AND THE MOUSE

አንበሳ እና አይጥ

ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት አይጥ በመንገድ ስታልፍ


አንድ አንበሳ ተመለከተች፡፡

አንበሳውን በጣም ትፈራው ስለነበር ደፍራ ለመቅረብ


ፈራች፡፡ ነገር ግን አንበሳው ኃይለኛ እንቅልፍ ወስዶት ስለነበር
ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንደ ሌለው አየች፡፡ ወደ ጭራው
አካባቢም ተጠግታ ብትነካው አንበሳው አልሰማትም ነበር፡፡
አይጧም በድምጹ ሞገድ የምትፈራውን አንበሳ ተኝቶ ስታገኘው

66
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

በላዩ ላይ ወጥታ መጫወት ጀመረች፡፡ ብዙም በጀርባው ላይ


እየተረማመደች መጫወቷን ቀጠለች፡፡

አንበሳውም ድንገት ከእንቅልፍ ባንኖ በመነሳት በጀርባው


ላይ የምትጫወተውን ቀበጧን አይጥ ለቀም አድርጎ ያዛት፡፡
አይጧም በአንበሳው መዳፍ ውስጥ ሆና አንበሳው እንዲለቃት
ተማፀነችው፡፡ በሚያሳዝን ድምፅ ከዕለታት አንድ ቀን ውለታውን
እመልሳለሁ አለች አንበሳም በአይጧን በንቀት “አንችም ብሎ
ውለታ መላሽ በይ ከዚህ ሂጂ በማለት ከመዳፍ ለቀቃት፡፡”

ከብዙ ግዜም በኋላ አንበሳ በአዳኞቹ ወጥመድ ተይዞ


ሲያጓራ ከርቀት ሆና ያች አይጥ ተመለከተች፡፡ ወደ አንበሳውም
በመምጣት አንበሳውን ጠላልፎ የያዘውን ወጥመድ በጥርሷ
በጣጥሳ አስለቀቀችለት፡፡ ወደ አንበሳም ቀና ብላ “ያኔ ውለታህን
አንድ ቀን እመልሳለሁ ስልህ ስቀህብኝ ነበር ዛሬ ግን እኔም ብድር
ለመመለስ ቻልኩ” አለችው፡፡

ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች፡-

አንድ ነገር ትንሽ ነው ብላችሁ አትናቁ ምን ጊዜ የመልካም ዋጋው

መልካምነትን ማግኘት ነው፡፡

ከብር የሚገባውን ክብር ስጡ፡፡ ጥሩ መስራት ድንቅ ነው፡፡

67
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE WOLF AND THE GOAT

ተኩላና ፍየል

ከዕለታት አንድ ቀን የተራበ ተኩላ የዕለት ምግቡን


ለማፈላለግ ሲዘዋወር ከገደል አፋፍ ላይ ቅጠል የሚለቃቅም ፍየል
ተመለከተ፡፡ ወደ ፍየሉም ቀና ብሎ ሲመለከት ፍየሉ በጣም
የሚያምርና ጮማ የተላበሰ ስጋ እንዳለው አሰበ፡፡ ወደ ፍየሉም
68
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

እያየ “እንተ ሞኝ ፍየል ምነው በዚህ ደልዳላው ሜዳ ላይ


የሚያምር ለምለም ሳርና ቅጠል ሞልቶ ከገደል አፋፍ ላይ
ተሰቅለህ መከራህን የምታይ ብትወድቅስ ምን ልትል ነው? አለዉ”
ፍየሉም ለደህንነቱ ያሰበ አዛኝ መሳይ መሆኑን ተረድቶ፡፡ አዛኝ
መሳይ ቅቤ አንጓች በማለት ተሳለቀበት፡፡

ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች፡-

አዛኝ ቅቤ አንጓች ማለት ምን ማለት ነው መምህራችን፣ ወላጆቻችን

፣ አስጠኚያችሁን በመጠየቅ መልሱን በክፍት ቦታ ላይ ሙሉ

ከዘመኑ አስመሳይ ሰዎች ፤ በምላሳቸው ከሚያታልሉና ከእንደነዚህ

አይነት ክፉዎች ተጠንቀቁ፡፡

69
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

THE FARMER AND HIS SONS

ገበሬውና ልጁ

በአንድ አካባቢ ሰፊ የወይን ማሳ የነበረው አንድ ገበሬ


ይኖር ነበር፡፡ በሕይወት ዘመኑ ሙሉ የወይን ማሳውን
እየተንከባከበ ይተዳደር ነበር፡፡ የገበሬው ልጆች ግን መስራት
70
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

አይወዱም ይልቁንም በተንዥረገገው የወይን ማሳ ያለን ወይን


እየተመገቡ ከመኖር ውጪ አባታቸውን በሥራ አያግዙትም ነበር፤

ከዕለታት አንድ ቀን አትክልተኛው አባታቸው ልጆቹን


ከያሉበት ቦታ አስጠራቸው፡፡ አባታቸውም የመሞታቸው ጊዜ
ተቃርቦ ስለነበር በአልጋ ላይ ተኝቶ አገኙት፡፡ በአልጋው ዙሪያም
ከበው አባታቸውን መመልከት ጀመሩ፡፡

አትክልተኛው አባታቸውም ልጆቹን ከእንግዲህ በኋላ


የመሞቻዬ ጊዜ ተቃርቧል በመሆኑም በወይን አትክልታችን
ውስጥ ለናንተ ለልጆቼ የቀበርኩት ወረቅ ስላለ እርሱን አውጥቻለሁ
እንድትጠቀሙበት ልነግራችሁ ነው ያስጠራኋችሁ በማለት
አስረድቷቸው ብዙ አልቆየም ሞተ፡፡

የአትክልተኛውም ልጆች አባታቸው እንደሞተ ሳይውሉ


ሳያድሩ በማሳው ውስጥ የተቀበረውን ወርቅ ለማግኘት የወይኑን
ማሳ ከዳር እስከዳር ግልብጥብጡን አውጥተው ቆፈሩት፡፡ ወርቅ
የሚባል ነገር ግን አላገኙም፡፡ ከትንሽ ወራት ቆይታ በኋላ
የአትክልት ቦታውን እንደገና ግልብጥብጡን አውጥተው ቆፈሩት
ወርቅ የሚባል ነበር ግን በአትክልት ቦታው እንደሌለ ተረዱ፡፡

71
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

የአትክልት ቦታውን ግን በደንብ ገለባብጠው ስለቆፈሩት


የወይን ማሳው እጥፍ ድርብ ኖኖ አፈራላቸው፡፡ ከዚያን ጊዜ
ጀምሮ የከበሩ ባለሃብቶች ሆኑ፡፡

ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች፡-

የአባታቸውንም በዘዴና በብልሃት ለልጆቹ መልካም ነገር

ማስተማሩን ተረዱለት ::

ብልህ አባት ለልጆች የሚያስተምረው በብልሃት ነው የአባት

ምክር ከወርቅ የከበረ አልማዝ ነው፡፡ ስራን ሳይንቁ መስራት

የትልቅ ሃብት ባለቤት ያደርጋል::

72
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

የአንበሳው ድርሻ
The lion share

ከረጅም ዓመታት በፊት አንበሳ፣ ቀበሮ፣ ተኩላና ውሻ


በአንድነት ለአንድ ዓላማ ተሰማሩ፡፡ ምንም ያግኙ ምንም
ያገኙትን አንድ ላይ ተከፋፍለው ለመብላት ተስማሙ::

73
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

አንድ ቀን ተኩላ አንድ አጋዘን አድኖ እንደገደለ ጓደኞቹን


በፍጥነት መጥተው እንዲከፈሉ ጠራቸው፡፡ ማንም ሳይጠይቀው
አንበሳ ራሱን የግብዣው አውራ አድርጎ በመሾም አድሎ
በሚታይበት ሁናቴ በአጋዘኑ ዙሪያ የተሰበሰቡ እንግዶችን መቁጠር
ጀመረ፡፡
‹‹አንድ እኔ እራሴ አንበሳው! ሁለት ተኩላው ሶስት ቀበሮ እና
ደግሞ ውሻው አራተኛ ይሆናል ማለት ነው›› አለና አጋዘኑን
በጥንቃቄ አራት ቦታ እኩል ከፋፈለ፡፡

“እኔ ንጉስ አንበሳና ነኝ” አለ ከፋፍሎ እንዳበቃ “እናም


የመጀመሪያ መደብ ይገባኛል ሁለተኛውም መደብ ለእኔ ሊሆን
ይገባል፡፡ ምክንያቱም ከሁላችሁ ጠንካራ እኔ ነኝና ይህም የእኔ
ነው ምክንያቱም እኔ ከሁላችሁም የበለጠ ጎበዝ ነኝ ከዚያም
የቀረበው መደብ ላይ ያፈጠጡ አራዊትን በቁጣ እየገላመጠ
‹‹ከእናንተ መሃል ስለቀረው አንድ መደብ የመብት ጥያቄ
የሚያነሳ ካለ›› ብሎ አንዴ አጉረመረመና ያለምንም ምክንያት
ጥፍሮቹን ዘረጋግቶ፡፡ ‹‹አሁን የመናገሪያው ጊዜ ነው›› በማለት
አጉረመረመ፡፡

ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች ፦
ከእኩያ ጋር መዋል ከእኩያ ጋር መስማማት ብልህነት ነዉ፡፡

74
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

አህያ እና ተኩላ
The donkey and wolf

,
አንድ አህያ ከአንድ ደን አጠገብ ሳሩን እያጋጠ ሳለ አንድ
ተኩላ ወደ እርሱ እያደባ ሲመጣ ጥላውን ተመለከተ እናም
ተኩላው ምን እንደሳበ የገባው አህያ ራሱን ለማዳን ዘዴ
ማውጠንጠን ጀመረ፡፡

75
ጥንታዊ የኤዞፕ ተረቶች

ልክ እግሩን እንደተጎዳ ማንከስ ጀመረ ተኩላው አጠገቡ


እንደደረሰ ለምን እንደሚያነክስ ጠየቀው አህያውም ሲመልስ
እሾህ ወግቶት እንደሆነ ከነገረው በኋላ ‹‹እባክህን ንቀልልኝ››
ሲል በህመም ስሜት እያቃሰተ ለመነው ቀጠል አደረገናም
‹‹ካልነቀልክልኝ ስትበላኝ ጉሮሮህ ላይ ጉዳት ያደርስብሃል››
አለው
ተኩላው ጉሮሮው ላይ ምንም ጉዳት ሳይደርስ አህያውን
ለማጣጣም ስለፈለገ የአህያውን ምክር በበጎ ተቀበለ፡፡
እናም ከአህያው እግር እሾሁን ለማውጣት ሲሞክር አህያው
ባለ በሌለ ኃይሉ በርግጫ ከነረተው በኋላ ሽምጥ በመጋለብ
እራሱን አዳነ፡፡

ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች ፦
የሚጎዳን ነገር ወደ እኛ በሚመጣበት ጊዜ ከመደናገጥና
ከመፍራት ይልቅ ተረጋግቶ ማሰብና ነገሮችን በጥበብ መመልከት
ይበጃል፡፡

76

You might also like