Zak New

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 16

56 .

በሽተኛው ድኩላ

(the sick stag

አንድ ድኩላ በድንገት በህመም ተያዘ እስኪሻለውና የቀድሞ ጥንካሬው እስኪመለስ ድረስ የሚያቆየውን
ምግብ ሰብስቦና በአንድ ጫካ ውስጥ በጥሩ ሁኔታ ተመንጥሮ በተደላደለ ቦታ ገብቶ ተኛ፡፡

መታመሙን የሸሙ እንስሳት ስለጤንነቱ ሁኔታ ሊጠየቁት መጡ ሁሉም የራባቸው ስለነበረ የድኩላውን
ምግብ እያነሱ በሉበት፡፡

ልጆች እንግዲህ ምን ትጠብቃላችሁ የአጋዘኑ ዕጣ ወዲያውኑ በርሃብ መሞት ነው፡፡

57 .ምንጭ ውስጥ የተዘፈዘፉ ቆዳና ውሾች

{the dogs and the hides

ጢቂት የተራቡ ውሾች አንድ ፋቂ አንድ ምንጭ ውስጥ የዘፈዘፈውን ቆዳ በድንገት አዩ መልካም ቆዳ
ለተራበ ውሻ ጥሩ ምግቡ ነው፡፡

ቢሆንም ቅሉ ምንጩ ጥልቀት ስላለው ውሾች ቆዳውን በቀላሉ ሊደርሱበት አልቻሉም፡፡ ስለዚህ ምን
እናደርግ ብለው ምክክር ያዙ የተሻለ ብለው ያሰቡት ዘዴ ውሃውን ከምንጩ ጠጥቶ ማስወገድ ነበር፡፡
እናም ሁሉም እኩል ውሃውን መጠጣት ጀመረ፡፡ የሚችሉትን ያህል ቢታገሉም ውሃው ጢቂት እንኳ
ሳይጎል እንደቀደምው ነበር በመጨረሻም ውሾች ብዙ ውሃ በመጠጣት ምክንያት ሁሉም ፈነዱ

የማይቻል ነገር ፈጽሞ አትሞክር

58 .የብረት ድስትና የሸክላ ድስት

{the two pots

ሁለቱ ድስቶች ማለትም የሸክላ ድስትና የብረት ድስት ጉልቻ ላይ ተጥደው በነበረበት አንድ ቀን የብረት
ድስት እስቲ ወጣ እንበልና ውጩን እንይ የሚል ሃሳብ አቀረበ፡፡

የሸክላ ድስት ግን እዚሁ እሳቱ ላይ መቆየት እንደሚሻለው በመናገር እራሱን ሸፋፈነ

“በቀላሉ ተሰባሪ እና ትንሽ ነገር እንክትክቴን እንደሚያወጣው ታውቃለህ ትንሽ መንቀጥቃ ብትንትኔን
ሊያወጣ ይችላል”

“እቤት ውስጥ ተቀምጠህ ምን ታረጋለህ

“አይዞን እኔ እጠንቀቅልሃለሁ በመንገዶችን ላይ ከባድ ነገር ሲያጋጥመን እኔ እመሃል እገባና አንተን


ከጉዳት አድንሃለሁ አለው፡፡

በመጨረሻም የሸክላ ድስት ተረትና ሁለቱ ጎን ለጎን ሆነው ጉዞ ጀመሩ ወዲያ ወዲህ እያሉ እያለፉ
እየተንገዳገዱና በእያንዳንዱ ርምጃ እርስ በእርስ እየተጋጩ ጉዞ ጀመሩ

የሸክላ ድስት ይህን ሁኔታ ብዙም መቋቋም አልቻለም፡፡ አስር እርምጃ ያህል እንኳ ሳይራመዱ
በተፈጠረው ግጭት የሸክላ ድስት አንድ ሺህ ቦታ ተፈረካከሰ

59 .ውሮ እና ዝንጀሮ

{ the monkey and the cat

በአንድ ወቅት አንዲት ድመትና አንድ ዝንጀሮ በቤት እንስሳት እያገለገሉ አብረው በአንድ ቤት ውስጥ
ይኖሩ ነበር፡፡

በጣም የሚዋደዱ ጓደኞች ከመሆናቸውም በላይ በየጊዜው የሚያገኙትን ማንኛውንም የምግብ አይነት
እኩል ተካፍለው ይመገቡ ነበር፡፡

አንድ ቀን ከእሳት ዳር አጠገብ ቁጭ ብለው ምድጃው ውስጥ የለውዝ ፍሬ ሲጠበስ ይመለከቱ ነበር
በአእምሮአቸው የሚመላለስ ጥያቄ ቢኖር ይህን የለውዝ ቆሎ እንዴት ከምድጃው ውስጥ አውጥተው
እንደሚመገቡ ነበር፡፡

“እነ ከምድጃው ውስጥ በደስታ ዘግኜ አወጣቸው ነበር ሲል ጮሌው ዝንጀሮ ንግግር ጀመረ አንቺ ግን
ለእንደዚህ አይነት ጉዳይ ከእኔ የተሻለ ክህሎት አለሽ አንቺ ጉትተሸ አውጪ እኔ ለሁለተኛና እኩል አከፍላለሁ”
አላት
ውሮ ጥፍራን ( መዳፏን) ዘረጋግታ አመዱን በጥንቃቄ ወደ አንድ ጉን አደረግችና መዳፉን ቶሎ ወደ ኃላ
መለሳችው ከዚያም እንደገና ሙከራ አደረገች በዚህ ሙከራም ከለውዙ ፍሬ ብዙ ወደ ኋላ ወረወረች በሶስተኛ
መከራዎች እጇን እየለበለባት ብዙ ፍሬዎች ወደ ኋላ ለዝንጀሮ አቀበለች ዝንጀሮ ግን እርሷ መዳፈን
እየተለበለበች ወደ ኋላ የምተቀብለውን እያነሳ ይባላ ነበር፡፡

ከዚያም ልክ የቤቱ ጌታ ከውጭ ወደ ቤት ሲገባ ወስለታው ዝንጀሮ ፈትላክ አለ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ


የዝንጀሮና የድመት ጓደኝነት ቀዝቃዛ ቢሮ አብዛኛው ውሎው ካይጦች ጋር ሆነ

60 ውሻውና የጌታው ምግብ

{the dog and his master s dinner

አንድ ውሻ የጌታውን እራት በየቀኑ ለጌታው ማድረስን ስለጠና በቅርጫት ውስጥ ያለው የምግብ
ሽታ ቢፈታተነውም ቅሉ ውሻው ግዴታውን በታማኝነት ያወጣ ነበር፡፡
በመንደሩ የሚኖሩ ውሾች ይህ ውሻ ሁልጊዜ በቅርጫት ይዘት የሚሔደው ነገር ምን እንደሆነ
ወዲያውኑ ደርሶበት ( አወቀ)

ከእርሱ ለመስረቅ በርካታ ሙከራዎችን ቢያደርጉም እርሱ ግን በታማኝነቱን ጠብቆ ለጌታው


ማድረሱን ቀጠለ፡፡
አንድ ቀን የመንደሩ ውሾች በሙሉ አንድ ላይ ሆነው አገኙት ታማኙ ወፍ በሚችለው አቅም
ሁሉ ሊያመልጣቸው ምክር ነበር በመጨረሻ ግን በንግግር ሊያግባቸውና ሊያሳምናቸው ቁሞየታማኙ
ውሻ ትልቅ ስህተት ይህ ነበር ወዲያውኑ ነበር አሳምነውት ምግብ የያዘ ቅርጫቱን እንዲያስቀምጥ
ያደርጉት
ከዚህም ለራሱ አንድ ትልቅ የተጠበሰ ስጋ አነሳና ቀሪውን ተከፍላችሁ ብሉት አላቸው፡፡

61 .አጋዝኑ በጓና ተኩላው

{the stag the sheep and the wolf

አንቅ ቀን አቶ አጋዘን ወ/ሮ በግ ጋ መጥቶ የስንዴ መስፈሪያዋን እንድታውሰው ጠየቃት ወ/ሮ


በግም አቶ አጋዘን ፈጣን ሯጭ መሆኑን በሚገባ ታውቃለች በቅጽበት ሩጫ ከአይኗ ሥር እንደሚሰወር
ትገነዘባለች
ስለዚህ ዋስ ሊሆነው የሚችል እንስሳ እንዳለ ጠየቀችው

“አዋን አለኝ አቶ ተኩል ዋስ ይሆነኛል” ሲል በልበ ሙሉነት መለሰ“ አቶ ተኩላ! በትል ወ/ሮ
በግ በመደነቅ ጠየቀች

“በእንዲህ ያለ ሁኔታ ታምነኛለች ብለህ ታስባለህ ተኩላን እኮ አውቀዋለሁ የሚፈለግውን ነገር


ማንኛውንም ነገር ብድግ አድርጎ ሳይከፍል ይዞ ይሮጣል አንተም ብትሆን እግሮችህን ተጠቅመህ
ታመልጠኛለህ ስለዚህ እኔ ንብረቴን ለመሰብሰብ ያለኝ እድል በጣም አነስተኛ ነው እሱም ቢሆን ሮጬ
ልይዝ ከቻልኩ ነው” አለች

62 .አውራ ዶሮውና ዕንቁው

{the cock and the jewel


አንድ አውራ ዶሮ በትጋት እየጫረ ለእርሱና ለቤተሰቡ የሚበላ ነገር ይፈልጋል፡፡ በዚህ ፍለጋው
ላይ እያለ ከአንድ ሰው የጠፋ የእንቁ ጌጥ ያገኛል፡፡
ያለ ጥርጥር ውድ ዋጋ ታወጣለህ የጠፋበትም ሰው አንተን መልሶ ለማግኘት የተጠየቀውን ዋጋ
ይከፍላል ለእኔ ግን አለም ላይ ካሉ ዕንቁዎች ሁሉ አንዲት የገብስ ፌር ይሻለኛል፡፡
63 .ጨው የተጫነው አህያ

{the ass and the load of salt

አንድ ነጋዴ አህያው ከበድ የጨው ጭነት ጭኖ ከባህር ዳርቻ ወደ ቤቱ ይመለሳል ሁልጊዜም ሲመላለሱ
የሚያቋርጡት አንደ ወንዝ ነበር ይህንን ወንዝ ብዙ ጊዜ ቢያቋርጡ አንድም ቀን አደጋ ደርሶባቸው
አያውቅም አንድ ቀን ግን አህያው ድንገት አዳለጠውና ወንዙ ውስጥ ወደቀ በመጨረሻም ከወንዙ
ውስጥ እንደምንም ሲወጣ ጨው በመሟሟቱ ሸክሙ ቀለለውና ወደ ቤት የሚያደርገው ጉዞ
አስደሳችና ቀላል ሆነለት፡፡
በቀጣዩ ቀን ነጋዴው ሌላ ጨው ሊያመጣ ወደ ባህር ዳርቻው አህያውን ይዞ ሄዶ ሲመለሱ
ትናንትና ወንዙ ውስጥ ሲወድቅ የሆነውን ነገር አስተወሳና ሆን ብሎ ወንዙ ውስጥ ለጥ አለ
ልክእንደትናንትናው ሁሉ ዛሬም የጨው ጭነት ቀነሰ፡፡
በነገሩ የተበሳጨው ነጋዴ ወዲያውኑ አህያውን ወደ መጣበት በመመለስ ሁለት ትልልቅ ቅርጫት
ሙሉ እስፖንጅ ጭነው እንደተለመደው ወንዙ ጋር ሲደርሱ አቶ አህያ ወንዙ ውስጥ ተኛ ከዚየም
ተነስቼ እራመዳለሁ ሲል ተንደፋድፉ አህያው በፊት ከሚያመላልሰው አስር እጥፍ ክብደት ያለው
ሸክም ተሸክሞ በሀዘን ቅስሙ እንደተሰበረ ወደ ቤቱ ተመለሰ

64 ቀበሮ እና ጃርት
አንድ ቀን አንድ ቀበሮ አንድን ትልቅ
ወንዝ በዋና አቋርጦ ከተሻገረ በኋላ በጣም ስለደከመው ከወንዙ ዳርቻ ድካሙን ለማሳለፍ ጋደም አለ፡፡

ወዲያውኑ ደም መጣጭ ዝንቦች መጥተው ወረሩት ቀበሮውም ከድካሙ የተነሳ ሮጦ ማምለጥ ስላልቻለ
እዛው እንደተጋደመ ዝም አለ፡፡አንድ ጃርት መጣና ‹‹እነዚህ ደም መጣጮችን ላባርልህ›› አለው

ቀበሮውም‹‹ ተው ተው ወዳጄ አታባራቸው›› ሲል ተቃወመ

‹‹እንዲያውም አትረባሻቸው እነዚኞቹ የሚበቃቸውን ያህል መጥምጠውኛል አንተ ካባረርካቸው ግን ሌሎች


የተራቡ ይመጡና የቀረች እንጥፍጣፊ ደሜን መጠው ይገላግሉኛል››

65 እረኛውና የዱር ፍየሎች

አውሎ ንፋስና ዝናብ ቀላቅሎ በጣለበት አንድ ቀን የፍየሎች እረኛ ፍየሎቹን ለማስጠለል ወደ አንድ
ዋሻ ውስጥ ይዟቸው ገባ በዋሻውም ውስጥ በርከት ያሉ የዱር ፍየሎች አገኘና ይለምዱልኛል በማለት አስቦ
ከራሱ መንጋዎች ጋር ቀላቅሎ ወደ በረቱ ይዟቸው ሄደ፡፡

ከዚያም የዱር ፍየሎችን ከራሱ ፍየሎች አስበልጦ ይንከባከባቸው ጀመር በርከት ያለ መኖ እያቀረበ
ለራሱ ፍየሎች ግን አነስተኛ እና ለመኖር ብቻ የሚያበቃ መኖ ይሰጣቸው ነበር፡፡በቀጣዩ ቀን ዝናቡ አባራና
ሁሉንም ፍየሎች እየነዳ ወደ መስክ ይዟቸው ወጣ የዱር ፍየሎች ግን ወዲያውኑ ከመንጋው ተለይተው ወደ
ዱሩ መገስገስ ጀመሩ፡፡

በዚህ ጊዜ እረኛው ‹‹እንደዚያ ተንከባክቤ እና መግቤ አሳድሬ እንዴት ትታችሁኝ ትሄዳላችሁ›› ሲል


ቅሬታውን ተናገረ

‹‹ከመንጋህ ጋር ተቀላቅለው ይኖራሉ ብለህ ጠብቀህ ከሆነ ተሳስተሃል እርግጥ ነው የራስህን ፍየሎች
በድለህ እኛን ደህን አድርገህ እንደተከባከብከን እንረዳለን ነገ ደግሞ ሌሎች ፍየሎች ስታገኝ እኛን ትተህ እነሱን
ትንከባከብና እኛን ታስርበናለህ›› አለው፡

66 አሳ አጥማጁና ትንሸዋ አሳ
The fisherman

አንድ ምስኪን አሳ አጥማጅ ኑሮውን የመሰረተው አሳ በማጥመድ ስለሆነ ሁል ጊዜ ማለዳ ማለዳ እየተነሳ አሳ
ያጠምዳል፡፡

አንድ ቀን ታዲያ መጥፎ ዕድሉ ሆነና ከአዲት ትንሽዬ አሳ በቀር ምንም አሳ ሳያጠምድ ዋለ እናም ይህቺ
ትንሽዬ አሳ ወደ ቅርጫቱ ውስጥ ሊያስቀምት ሲል ‹‹ እባክህ አሳ አጥማጅዬ ልቀቀኝ እንደምታየኝ ትንሽ ነኝ
እኔን ወደ ቤትህ ብትወስደኝም አረባህም ሳድግና ትልቅ ስሆን ግን የተሸለ የሚያጠግብ ምግብ እሆንሃለሁ››
አለችው ሆኖም ግን አሳ አጥማጁ አሳዋን በፍጥነት ወደ ቅርጫቱ እያስቀመጠ ‹‹እንዴት ሞኝ ይሆናል ብለሽ
ታስቢያለሽ የቱንም ያህል ትንሽ ብትሆኚ ከምንም ትያሻያለሽ አላት፡፡

67 የአረጀ አንበሳ እና ቀበሮ


አንድ በርጅና ምክንያት ጥርሶቹ እና ጥፍሮቹ ስለደከሙበት እንደ ወጣትነቱ ዘመን በቀላሉ አድኖ ምግብ
ማግኘት ተሳነው፡፡ እናም በርሃብ ምክንያት ታመመ፡፡

ከዚያም መታመሙን ሁሉም ጎረቤቶች እንዲያውቁለት አደረገና ዋሻው ውስጥ ተኝቶ ጠያቂዎችን
መጠባበቅ ጀመረ

አዝነው ሊጠይቁት የመጡትን እንስሳትን እያነቀ ይመገባቸው ጀመር፡፡ቀበሮም ሊጠይቀው መጥቶ ነበር
ሆኖም ከዋሻው ራቅ ብሎ በመቀመጥ ‹‹እንዴት ነው ተሻሎት እንዴ›› ሲል በትህትና ጠየቀ

‹‹ኧረ በጣም አሞኛል ግባና ትንሽ ቆይተህ ሂድ›› አለውቀበሮውም ‹‹ስለ ግብዣህ አመሰግናለሁ ገብቼ
ባጫውትህ ደስ ይለኛል ሆኖም ግን በዋሻህ በር ላይ ማየው የእንስሳት ዱካ ወደ ውስጥ ሲገቡ እንጂ ሲወጡ
አያሳይም አስቲ ባክህ ንገረኝ ጠያቂዎችህ በየት በኩል ነው ወጥተው የሚሄዱት››?

68 አህያው እና አንበሳው

አህያ እና አንበሳ አብረው አደን ሊወጡ ተስማሙ የሚያድኑትን እንሰሳ ፍለጋ ላይ እያሉ የዱር ፍየሎች
ወደ አንድ ዋሻ ውስጥ እየሮጡ ሲገቡ ተመለከቱ፡፡ከዚያም እንዴት ሊያጠምዷቸው እንደሚችሉ ዕቅድ ነደፉ

አህያው ወደ ዋሻው ውስጥ በመግባት ፍየሎችን ከዋሻው ውስጥ እንዲወጡ እንዲያደርግና እበሳው
ድግሞ እዋሻው በር ላይ ቆሞ በክርኑ እየሰባበረ እንዲያስቀራቸው ተስማሙ፡፡
በርግጥም ዕቅዳቸው በሚገባ ሰምሯል አህያው ወደ ዋሻው ውስጥ በመግባት ከመጠን በላይ በማናፋትና
በርግጫ በመማታት የዱር ፍየሎች ላይ ሽብር በመንዛት ፍየሎቹ በርግገው ወደ ውጭ እንዲወጡ አደረገ
አንበሳው እዋሻው በር ላይ ሆኖ እያንዳንዱን እየያዘ አና እየሰባበረ አስቀራቸው፡፡

አህያውም ከዋሻው ውስጥ ወጥቶ ‹‹አየህ አይደል እንዴት በድንጋጤና በፍርሃት ፈርጥተው እንደወጡ
እንዳደረኳቸው›› አለው፡፡
‹‹አዎን አይቼያለሁ አንተ እና ባህሪህን አስቀድሜ ባላውቅ ኖሮ እኔ እራሴ በሩጫ ልፈረጥጥ ነበር››፡፡

69.እረኛውና አንበሳው

አንድ እረኛ አንድ ቀን በጎቹን መቁጠር ጀመረ ወዲያውኑ ከመንጋው አንድ እንደጠፋበት አወቀ፡፡በንዴትና
በቁጣ ሌባውን ካገኘሁ የሚገባውን ቅጣት እንደሚሰጠው በኃይል እየጮኸ በጉራ ደነፋ፡፡እንደ እረኛው ግምት
ከሆነ የበጉ ሌባ ተኩላ እንደሚሆን አለተጠራጠረም፡፡
እናም ተኩላውን ፍለጋ ወደ አንድ ኮረብታ ላይ ወደ ሚገኝ ዋሻ ለመሄድ ወሰነ፡፡ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ግን
ጁፒተር ለተባለው ጣኦት ሌባውን ካስገኘለት ጥጃ እንደሚሰዋለት ቃል ገባ፡፡ምን ዓይነት ተኩላ ሳያገኝ ብዙ
ከተንከራተተ በኋላ በአንድ ኮረብታ አጠገብ ባለዋሻ አንድ ትልቅ አንበሳ በጉን ይዞ ተመለከተ፡፡
በታላቅ ድንጋጤ መሬት ላይ ወረዶ ተንበረከከና ‹‹ጁፒተር የሰው ልጅ የሚጠያቀውን አያውቅምና
ጠቦቴን የሰረቀውን ካገኘው ጥጃ እሰዋለሁ ብዬህ ነበር አሁን ግን ሌባውን ከአጠገቤ እንዲርቅ ካደረከው አንድ
ወይፈን እሰዋልሃለሁ አለው፡፡
70 ዝንጀሮውና ግመሉ
The monkey and the camel
ለንጉስ አንበሳ የንግስ ክብረ በዓል በተዘጋጀው ሥነ-ሥርዓት ላይ አቶ ዝንጀሮ የዳንስ ትርዒት እንዲያሳይ
ተጠየቀ በርግጥም ያሳየው የዳንስ ችሎታ አስደናቂ ነበር እንስሳት በሞላ ዝንጀሮው ባሳየው የደዳንስ ፀጋና
ችሎታ በጣም ተደሰቱ ለአቶ ዝንጀሮ የተቸረው ምስጋናና ሙገሳ አቶ ግመል ሲመለከት ቅናት አደረበት፡፡
እናም ከዝንጀሮው የተሻለ ባይሆንም እንኳ የዝንጀሮን ያህል መደነስ እንደሚችል እርግጠና ሆነ፡፡
ወዲያውኑ ወደተሰበሰቡት እንስሳት መሃል ገብቶ በኋላ እግሩን በማንሳት መደነስ ጀመረ፡፡ በጣም አስቸጋሪ
እግሮቹና ሲረግጥ ገልጃጃ አንገቱን ሲያጠማዝዝ የሚያስቅ ሞኛ ሞኝ መሰለ የተሰበሰቡትን እንስሳት
ግመሉከባባድ ኮቴዎቹ እንዳይረጋግታቸው መከላከል አስቸጋሪ ሆነባቸው ጭራሽ አንደኛው ትልቁን ወደ ላይ
ብድግ አድርጎ ወደ ንጉሱ አፍንጫ አቅራቢያ ሲያደርስ እንስሳቱ በሙሉ በንት ጦፈው እየጠገፈታተሩ ከመሃል
በመውጣት ወደ በርሃ አባረሩት፡፡
ይህን ድርጊት ቀበሮ በድንገት ተመለከተና በሳቅ ተንከተከተ፡፡“አንበሳው በሕይወት ያለ ቢሆን ኖሮ የተለየ
ታሪክ ይሆን ነበር የእርሱ ጥፍር ከእናንተ ከጠቅላላችሁ ጥርሶች የበለጠ የሰላ እንደሆነ ያሳያችሁ ነበር” አለ

የፍየል ግልገሉ
The Wolf and Kid
በአንድ ወቅት አንድ ትንሽዬ የፍየል ግልገል ነበር፡፡ ብቅ ብቅ ያለው ቀንዱ ራሱን ትልቅ ፍየልና ራሱን
መጠበቅ እንደሚችል ተሰማው፡፡ እናም አንድ ቀን አመሻሽ ላይ መንጋው ከግጦሽ ወደ ቤት መመለስ ሲጀምር
እናቱ ስትጠራው ችላ ብሎ ለምለሙን ሳር መንመቱን ቀጠለ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጭንቅላቱን ቀና አድርጎ
ቢመለከት መንጋው ጥሎት ሄዷል፡፡ እናም ብቻውን ቀሪ ፀሐይም ወደ ማደሪያዋ እየጠለቀች ነበር፡፡

ረጃጅም ጥላዎችም በምድር ላይ አጠሉ፡፡ ትንሽዬ ለስላሳ ንፋስም የሚያስፈራ ድምፁን በሰሩ ውስጥ
እየተሻለ

ትንሹ ግልገልም ስለ አደገኛ ተኩላ አስቦ መንቀጥቀጥ ጀመረ፡፡ እናቱን እየተጠራ መሄድ ጀመረ ግማሽ
ያህል ርቀት እንኳ ሳይጓዝ ከክለምች ዛፎች አጠገብ ተኩላ ቆሞ ነበር፡፡

ቢሆንም ግን አንድ ጭላንጭል ተስፋ እንዲለው ተረዳ “አያ ተኩላ አለ እየተንቀጠቀጠ” ልትበለጥ
እንደሆነ አውቅያለሁ ግን ከዛ በፊት ዋንሽንት ተጫወትልና የምችለውን ያህል ትንሽ መደሰት እፈልጋለሁ፡፡

ተኩላ ከመባል በፊት በትንሹ በዕሁዘቃ የመዝናናቱን ሀሳብ ወደደው እናም የሽንቱን አንስቶ መጫወት
ጀመረ ግልገሉም ወደያ ወዲህ በደስታ መሽከርከር ጀመረ፡፡
በዚህ ጊዜ መንጋው ወደ ማደሪያቸው አቅራቢያ እየተቀረቡ ነው፡፡ ፀጥ ብለው የምሽት ዓየር የተኩላው
የዋሽንት ድምፅ ሩቅ ድረስ ይሳካ ነበር የእረኛው ውስጥ ጀሮአቸውን ቀሰሩ ተኩላውን በለስ ሲቀናው
የማጫወተውን ዜማ መሆኑን አስትሮለ እናመው ወዲያውኑ ወደ ግጦሽ ሥፍራ ተመልሰው መገስገስ ጀመሩ፡፡

የተኩላው ዜማ በድንገት ቀጥ አለ ውሸቱ እያስደሰት ግልገሉን ለማስደሰት ሙዚቃ መጫወቴ ቂል ነጥ


ሲል ራሱን ወቅሰ የገዛቴ ራሴን

አንድ ልጅ ከአንድ ማሰሮ ውስጥ ጥቂት ንፍሮ እንደወሰደ ተፈቀደለት፡፡

ይሁን እንጂ እርሱ ጥብጥ ሙሉ ዞግኖ እጁን መልስ ማውጣት ተሰራው ከዘገነው አንዩትም ፌሬ
መተው ያልፈቀደው ልጅ ሙሉውን ይዞ መውጣት አልሆነለትም፡፡

በዚህም ምክንያት ሙሉውን ይዞ መውጣት ስላልቻለ ተናደደና ማልቀስ ጀመረ፡፡

እናቱም “ልጅ ግማሽ ያህሉ ይበቀሃ በዚህም እጅህን በቀላሉ ማውጣት ይቻላሃል፡፡

ምናልባት ሌላ ጊዜ ተጨማሪ ጥቂት እንድትዘግን ይሬቀይሃል”

ባንዴ ብዙ ለመውሰድ አትሞክር

The Graf and the bull


ትንኟና ወይፈኑ
አንዲት ትንኝ በአንድ የግጦሽ መስክ ላይ ስትበር ቀሮችን ከአንድ የወይፈን አንደኛው ቀንድ ላይ
አረፈች፡፡

ትንሽ ጊዜ ከቆየች በኋላ ለመሄድ ተዘጋጀች፡፡ ይሁን እንጅ ከመነሳቷ በፊት የወደፊትን ቀንድ ለማረፍ
ስለተቀበች ይቅርታ ጠየቀችው፡፡

“በመሄድ ደስ ሊልህ ይገባል”

“ለኔ ሁሉም ያው ነው ሲል ይመልስለት ጀመር” ቀንዱ ላይ እንዳረፍሽ እንኳ አላውቅም ነበር፡፡

ከጎረቤታችን ዕይታ ይልቅ እና ራሳችንን ታላቅ ክብር አለን፡፡

The lion and the ass


አንበሳውን አህያው
አንድ ቀን አንድ አንበሳ በአንድ የእግር መንገድ በኩራት እየተራመደ ስለ አራዊት በአክብሮት መንገድ
ይስቁበት ጀመር እርሱ እያለፈ ሳለ አንድ አህያ በንቀት አንዴ አናፋ፡፡

አንበሳው ንዴት (ቁጣ) ተሰማው እናም ራሱን ዞር አድርጎ ቢመለከት ማን ድምፅ እንዳሰማ
ተመለከተና ፀጥ ብሎ መንገዱን ቀጠለ፡፡

ለቂል የጥፍሩን ቆሻሻ ያህል ክብር አልሰጠውም ነበር፡፡ “በቂሎች አስተያየት ቅር አትሰኝ ችላ በላቸው”

The Farmer and The Strok


ገበሬውና ሽመላ
አንዲት የዋህና ታማኝ ፍጥረት የሆነችው ሽመላ አዲስ በተዘራ የእርሻ ማሳ ላይ ተገኝታ እንድትበላ
በአሳ አውጪ ወፎች ተጋበዘች፡፡ይሁን እንጅ ድግሱ በአሳዛኝ (በአስከፊ) ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡ ሁሉም በማሳው ላይ
የተሰማሩ ወፎች በነበረው መረብ ውስ ወደቁ ሽመላ ገበሬው እንዳላየች እንዲህ ስትል ተማፀነችው፡፡

“እባክህን እንድሄድ ፍቀድልኝ እንደምታውቀው እኔ ከታማኞችና መልካም ባህሪ ካላቸው የስመላ


ቤተሰብ ነው የመጣሁት በዚያ ላይ ደግሞ እኔ አሳ አቢጨዋቹ ሊሰርቁ እንደሆነ አላውቅም ነበር” ስትል
አስተዛዝና ለመነችው፡፡

“አንቺ መልካም ልትሆኚ ትችያለሽ” ሲል ገበሬው ንግግር ጀመረ፡፡ ነገር ግን እኔ የያዝኩት ከሌቦቹ ከአሳ
አውጪዎች ጋር ነው፡፡ ስለዚህ ከእነርሱም ጋር ቅጣቱንም ትጋሪያለሽ

“ጓደኛህ ግን እንሆነ ንገረኝና ጫን እንደሆነ እነግርሃለሁ”

The kid and the wolf


የፍየል ግልገሉና ተኩላው
አንድ ከብት አርቢ አንድን የፍየል ግልገል ጉዳት እንዳደርስበት አስቦ ከበጎች ማደሪያ የሳር ክዳን ጣሪያ
ላይ አኑሮት ሄደ፡፡

ይህ ፈንጠዥ ትንሽዬ የፍየል ግልግል ከጣራው ጫፍ ላይ ሆኖ ወዲያ ወዲህ ሊመለከት አንድ ተኩላ
ሲያልፍ አየና በልቡ ይዞት የነበረውን ስድብና ዜዝ ሁሉ ተናገረበት “ሰምቼሃለሁ” አለ ተኩላው “በተናገርከው
ሁሉ ቂም አልይዝብህም” አንተ እዛ እላይ እስከላሥ ድረስ የተናገርከው አንተ ሳትሆን ጣሪያው ነው አለው፡፡
“ሁልጊዜ በድፍረት ልትናገረው የማትችለውን ነገር በማንኛውም ጊዜ አትናገር”
Aesop and the Ass

“The next time you write a table about me” said the donkey to Aesop “make me say
something wise and sensible”

“Something sensible from you!”

Exclaimed Aesop
“What would the world think? People would call you moralist and me the donkey”
“በሚቀጥለው ጊዜ ስለ እኔ ተረት ስተጽድ” አለች አህያት ኤዞፕ
“ስሜት የሚሰጥና ብልህነትን እንድናገር አድርገኝ”
“አንዳች ስሜት የሚሰጥ ነገር ካንቺ” ኤዞፕ ተደነቀ!
“እና ዓለም ምን ያስብ ይመስላል አንቺን ፈላስፋ እኔን ደግሞ አህያ ብለው ይጠሩሃል”
በዘመነ ኤዞፕ የነበሩ አንዳድ ሙህራንና ኤዞፕ ላይ ጥናት ያደረጉ ሊቃውንት..ከብዙ በጥቂቱ

1 ሜትሪየስ
አቴናዊ ተነጋሪ /Oratcr/
ግሪክ
2 ፌድረስአቴና- ግሪክ 444 ተወለደ
393-ሞተ
ፈሎሠፈርናከሀብታም ቤተሰብ የተወለደ የፊዚክስ ሊቅ
3 ዊልሃምክንተን አንገሊዝ 14 22 እስከ 1491 ዓ ም
ነጋዴ ዲፕሎማት ጸሐፊና አታሚ
4 ሠር ሮጀርእንግሊዝ ለንደን 1616-1704
ፖለቲክሻን ደራሲ ተርጓሚና የጋዜጣ አዘጋጅ
5 ላፎንቴን 1621-1995 ዓ.ም
ፈረንሳይ
የተረት መፅሐፍት አዘጋጅ
6 ሄርደቱስ ትውልደ ቦታ ሀሊካመሳስ ግሪክ
የሞተበት ቦታ ጣሊያን
ተወለደ 484 ዓ.ዓ
የሞተበት 425 ዓ.ዓ
7 ሶለን 630-560 አመት
ግሪክ አቴንስ
ገጣሚ አማካሪ ህግ አርቃቂ
8 ክሮስየስ 560-546 በሊዲያ የነገሰ
ምዕራብ እስያ የተወለደ
ሞቱ ና የኖረበት ዘመን አይታወቅም
9 ሆሚር በሎኒያ ተወለደ..በሎስ - ግሪክ ሞተ
የትውልድ ዘመኑ በትክክል አይታወቅም፡፡ ይልቁንም ከጻፋቸው ሁለት ድንቅ መጽሐፍቶቹ የዘመን
ግምት ብቻ ተሰጥቷቸው ከ 800 ዓ.ዓ ገደማ ተብለው ይገመታሉ እንጅ በውል አይታወቁም
10 አሪስቶፋነስ በጥንታዊት አቴና ተወለደ
የትያትር ፀሀፊ ሲሆን 427-386 ኖረ
በዶለፊን ሞተ
11 ሶፍክለስ 495-406 ኮለንስ አቴና ግሪክ ተወለደ
የትራጀዲይ ትያትር ፀሀፊ
12 ዩሪፒዶስ ካልሚስ ደሴት ግሪክ ተወለደ
ትያትር ፀሀፊ ከ 480 406 ኖረ
13 አፍስጦን /ፕላቶ/
427-328 ኖረ
ፈላስፋ
13 አሪስጣጣሊስ /አርስቶትል/
384-322 ስታጅሪያ ተወለደ
ፈላስፋ
በግሪክ ቻልሲስ ሞተ
14 ሶቅራጠስ /አይፓቼ ግሪክ/ 470-399
በአቴና - ግሪክ ሞተ
ፈላስፋ

ይህንን መጽሐፍ ለማዘጋጀት በጣም በዙ ሊንኮችንና መጽሀፍትን የተጠቀምን ሲሆን አብዛኛወቹን መጽሐፍት
በየመሐሉ የጠቀስን በመሆኑ እዚህ ላይ ማብራራቱን አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም ፡፡
መጽሐፍ አንድ ተጠናቀቀ

የዚህንመጽሐፍቅጽ ሁለት

በቅርብ ቀን !!

You might also like