ነሃስ_ብቻ ወይም ነሑሽታን

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

ነሃስ_ብቻ ወይም ነሑሽታን

================

✍️እስራኤል ከግብፅ ባርነት በእግዚአብሔር ክንድ ነፃ ወጥተዉ እግዚአብሔር ከሰማይ እየመገባቸዉ ከአለት ዉሃ
እያጠጣቸዉ ቢመራቸዉም ጠረጠሩት አስመረሩት እንጀራዉንም ይሄ ቀላል እንጀራ አሉ...
“ሕዝቡም በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ፦ በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣችሁን? እንጀራ የለም፥ ውኃ
የለም፤ ሰውነታችንም ይህን ቀላል እንጀራ ተጸየፈ ብለው ተናገሩ።”
— ዘኍልቁ 21፥5

✍️ይህንም ተከትሎ እግዚአብሔር እባቦችን ሰደደ ህዝቡንም ነደፋ ብዙዎችም ሞቱ ከዚያም ህዝቡ ወደ ሙሴ ጮኸ
ሙሴም...
ዘኍልቁ 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት
በሕይወት ይኖራል አለው።
⁹ ሙሴም #የናሱን_እባብ_ሠርቶ_በዓላማ_ላይ_ሰቀለ፤ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ።

✍️እስራኤል በእባብ ሲነደፉ በአላማ ላይ የተሰቀለዉን የናሱን እባብ ባዩ ጊዜ ዳኑ እንደሚል ይህንን ሃሳብ በዮሐ.ወ ምዕ
3 ጌታ ኢየሱስ ኒቆዲሞስን ስለ ዳግም ልደት ባስተማረዉ ትምህርት.....
“ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ #በእርሱ_የሚያምን_ሁሉ_የዘላለም_ሕይወት_እንዲኖረው እንጂ
እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።”
— ዮሐንስ 3፥14-15

✍️የነሃሱን እባብ ያዩ እንደ ዳኑ በመስቀል የተሰቀለዉን ኢየሱስ ያመኑ ሁሉ ይድናሉ የእግዚአብሔር ዋናዉ ሃሳብ ይሄ
ነዉ።

📌 ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ይህን ሙሴ የሰቀለዉን የናሃስ እባብ ከዘመናት በኋላ ላዳናቸዉ ለእግዚአብሔር ክብር
መስጠትን ትተዉ ለናሱ እባብ ያጥኑለት ጀመር ይህንንም እግዚአብሔር ደግ አደረጋችሁ ለማዳን የተጠቀምኩበትን
አከበራችሁት ብሎ እዉቅና አልሰጠዉም ባዕድ ድርጊት ነዉና አልተቀበለዉም፤ የአካዝ ልጅ ህዝቅያስም በይሁዳ በነገሰ
ጊዜ አባቱ ዳዊት እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ።

1)በኮረብታም ያሉትን መስገጃዎች አስወገደ፥


2)ሐውልቶችንም ቀለጣጠመ፥
3)የማምለኪያ አፀዶቹንም ቈረጠ፤
4)የእስራኤልም_ልጆች_እስከዚያ_ዘመን_ድረስ_ያጥኑለት_ነበርና
👉ሙሴ የሠራውን የናሱን እባብ ሰባበረ፤ ስሙንም ነሑሽታን ብሎ ጠራው።” ትርጉሙም ነሀስ ብቻ ማለት ነው።
አንዳች ነገር ማድረግና መፈወስ የማይችል ነሀስ ብቻ።
— 2 ኛ ነገሥት 18፥4

✍️እስራኤላዊያን የነሃሱን እባብ ሲያጥኑለት እንደነበረ ዛሬም በእኛ ዘመን ብዙ ሰዎች የክርስትና እምነት ተከታዮችንም
ጨምሮ የተሰቀለዉ ኢየሱስ ላይ ከማተኮር ይልቅ ቁሳዊ ነገሮች ላይ (የተቀባ ዘይት፣የሚፈውስ ውሃ ፣ተአምር
የሚያደርግ ስዕልና እንጨት) በማለት ፈዋሽህ አምላክህ እግዚአብሔር ነው የሚለውን እውነተኛ ቃል ትተው ልባቸውን
መፈዎስ በማይችሉ ነሁሽታኖች(ዘይት ብቻ ውሃ ብቻ ስዕል ብቻ) ላይ አድርገው እንመለከታለን።
✍️የሚደረጉት ነገሮች ሁሉ ከትያትርነት በዘለለ ምንም ማድረግ ስለማይችሉ የናሃሱን እባብ ህዝቅያስ እንደሰባበረዉ
ዛሬም እኛ አይኖቻችንን ከተሰቀለው ከኢየሱስ እንድናነሳ የሚያደርጉ ቁስ ነገሮች ሁሉ ነሁሽታን ነሃስ ብቻ በማለት
ልናስወግዳቸው ይገባል።

✍️ዘጸአት 15 (Exodus)
26፤... እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና፡ አለ።

✍️ኢሳይያስ 53 (Isaiah)
5፤ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም
ቍስል እኛ ተፈወስን።

✍️ዮሐንስ 3 (John)
14-15፤ ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ
እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።
16፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ
ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
17፤ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።
18፤ በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን
ተፈርዶበታል።

📌 2 ቆሮንቶስ 13
14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

የወንጌል እውነት
Gospel Truth

You might also like