Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 20

በወጀብ ፡ በአውሎ ፡ ንፋስ ፡ በማዕበል ፡ ስንናወጥ

ወጀቡን ፡ የሚገስጽ ፡ ማዕበሉን ፡ የሚያሰኝ ፡ ጸጥ


ኢየሱስ

አዝ፦ ሥራህ ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫ x) ፡ ጌታ ፡ ሆይ


ሥራህ ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫ x) ፡ ጌታ ፡ ሆይ

እኛን ፡ ያስጨነቀውን ፡ ማዕበሉን ፡ የሚረግጥ


በውኃ ላይ ፡ የሚራመድ ፡ እኛንም ፡ የሚያራምድ
ኢየሱስ

አዝ፦ ሥራህ ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫ x) ፡ ጌታ ፡ ሆይ


ሥራህ ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫ x) ፡ ጌታ ፡ ሆይ

በእጥፍ ፡ የነደደውን ፡ እቶኑን ፡ የሚያበርድ


በእሳት ፡ ውስጥ ፡ የሚራመድ ፡ እኛንም ፡ የሚያራምድ
ኢየሱስ

አዝ፦ ሥራህ ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫ x) ፡ ጌታ ፡ ሆይ


ሥራህ ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫ x) ፡ ጌታ ፡ ሆይ

ኢየሱስ (፬ x)

አምነንህ ፡ አላፈርንም ፡ ጠብቀን ፡ አልከሰርንም


ኢየሱስ ፡ የእኛ ፡ ጌታ ፡ ሁሉንም ፡ የረታህ (፬ x)
እግዚአብሔር ፡ አለልኝ ፡ በቃ
እርሱ ፡ ይበቃኛል ፡ በቃ (፪ x)

እግዚአብሔርን ፡ ሚበልጥ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ አለ ፡ ወይ
ከእኔ ፡ አምላክ ፡ የሚሻል ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ አለ ፡ ወይ (፪ x)

ሌላ ፡ ሌላ ፡ አለ ፡ ወይ (፬ x)
ሌላ ፡ ሌላ ፡ አለ ፡ ወይ (፬ x)

አለልኝ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ (፬ x)
ጌታ ፡ አለልኝ (፫ x)

የልቤ ፡ ፍሰሃ ፡ ነህ ፡ ፍሰሃ ፡ ነህ ፡ ፍሰሃ


የነፍሴ ፡ ደስታ ፡ ነህ ፡ ደስታ ፡ ደስታ (፪ x)

አለኝ ፡ አንድ ፡ ተስፋ ፡ ከንቱ ፡ የማይጠፋ


ኢየሱስ ፡ ይባላል ፡ ነፍሴን ፡ ይመልሳል (፪ x)
አለኝ ፡ አንድ ፡ ተስፋ ፡ ከንቱ ፡ የማይጠፋ
ኢየሱስ ፡ ይባላል ፡ ነፍሴን ፡ ይመልሳል (፪ x)
ነፍሴን ፡ ይመልሳል (፬ x)

አለልኝ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ (፬ x)
ጌታ ፡ አለልኝ (፬ x)
ልዑል ፡ ሆይ ፡ ከልዑሎችም ፡ በላይ ፡ አንተ ፡ ልዑል ፡ ነህ
መተከያም ፡ መለኪያ ፡ የለውም ፡ ለልዑልናህ
ለልዑልናህ (፫ x)
ለልዑልናህ (፫ x)

በዙፋን ፡ ላይ ፡ ላለው ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ይሁንለት


በማደሪያው ፡ ላይ ፡ ላለው ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ይሁንለት
ይሁንለት (፬ x)

ታናናሾች ፡ ታላላቆች ፡ ሁሉ ፡ ቅዱሳኑም ፡ የምትፈሩት


አምላካችንን ፡ አክብሩት (፪ x)

አምጡ ፡ ምሥጋናውን ፡ አምጡ


አምጡ ፡ ክብሩን ፡ አምጡ
አምጡ ፡ ክብሩን ፡ አምጡ
እስኪ ፡ አምጡ ፡ ምሥጋናውን ፡ አምጡ
አምጡ ፡ ክብሩን ፡ አምጡ
አምጡ ፡ ክብሩን ፡ አምጡ
ምሥጋናውን ፡ አምጡ ፡ ክብሩን ፡ አምጡ
ምሥጋናውን ፡ አምጡ ፡ ክብሩን ፡ አምጡ

ጌታን ፡ ነዉ ፡ የታወቀ ፡ በዓለም ፡ ዝናው ፡ የገነነ


ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ የሚሰግድለት ፡ ምላስ ፡ ሁሉ ፡ የሚያወራለት

ለዚህ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ እሰግዳለሁ (፫ x)


ለዚህ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ እኖራለሁ (፫ x)
ለዚህ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ እግዛለሁ (፫ x)

መጸለይ ፡ አለልኝ ፡ በቃ
እጸልያለሁኝ ፡ በቃ
ለእግዚአብሔር ፡ ነገርኩት ፡ በቃ
ለእግዚአብሔር ፡ ሰጠሁት ፡ በቃ

ከጸሎት ፡ ሚበልጥ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ አለ ፡ ወይ
ከጸሎት ፡ የሚሻል ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ አለ ፡ ወይ (፪ x)
ሌላ ፡ ሌላ ፡ አለ ፡ ወይ (፬ x)

ትልቅ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ አእምሮ ፡ ሊሸከመው ፡ ከሚችለው ፡ በላይ (፬ x)


ኦ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ትልቅ (፫ x)
ኦ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ትልቅ (፫ x)
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ትልቅ ፡ ነው (፪ x)

ትልቅነትህን ፡ ያላየ ፡ ማነው (፫ x)


ትልቅነትህን ፡ ያልሰማ ፡ ማነው (፫ x)
እኔስ ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን
ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ አንተ ፡ መብለጥህን
እኔ ፡ እንኳን ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን
ከነገሮች ፡ በላይ ፡ አንተ ፡ መብለጥህን

እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን
ከሁኔታዎች ፡ አንተ ፡ መብለጥህን
አንተ ፡ እኮ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪ x)
አምላኬ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪ x)

በሠማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ላለኸው


ምሥጋናዬ ፡ ይኸው ፣ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው
በሠማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ላለኸው
አምልኮዬ ፡ ይኸው ፣ አምልኮዬ ፡ ይኸው

አይመረመርም ፡ ከፍ ፡ ማለቱ ፡ የእርሱ ፡ ልቀቱ ፡ ጌታዬ


አይመረመርም ፡ ተወዳዳሪ ፡ አቻ ፡ ማጣቱ ፡ ጌታዬ
አይመረመርም ፡ ውበት ፡ ቁንጅና ፡ ድምቀት ፡ ማማሩ ፡ ጌታይ
አይመረመርም ፡ ግርማ ፡ ሞገሱ ፡ አስፈሪነቱ ፡ ጌታዬ
ሃ ፡ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፬ x)
አይመረመርም ፡ የርህራሄው ፡ የምህረቱ ፡ ብዛቱ
አይመረመርም ፡ ቸርነቱ ፡ ይቅር ፡ ማለቱ ፡ ጌታዬ
አይመረመርም ፡ ፍቅሩ ፡ ጥልቀቱ ፡ ወርዱ ፡ ስፋቱ
አይመረመርም ፡ ሰውን ፡ መውደዱ ፡ አዳኝነቱ ፡ ጌታዬ
ሃ ፡ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፬ x)

ትልቅ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ አእምሮ ፡ ሊሸከመው ፡ ከሚችለው ፡ በላይ (፬ x)


ኦ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ትልቅ (፫ x)
ኦ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ትልቅ (፫ x)
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ትልቅ ፡ ነው (፪ x)

ትልቅነትህን ፡ ያላየ ፡ አለ ፡ ወይ? (፫ x)


ትልቅነትህን ፡ ያልሰማ ፡ አለ ፡ ወይ? (፫ x)
እኔኮ ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን
ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ አንተ ፡ መብለጥህን

እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን
ከሁኔታዎች ፡ አንተ ፡ መብለጥህን
አንተ ፡ እኮ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪ x)
አምላኬ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪ x)

የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የምድር ፡ ፈጣሪ


በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነዋሪ
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች (፪ x)
የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች (፪ x)
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች (፪ x)
ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች (፬ x)

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ያለና ፡ የነበረ ፡ የሚመጣ


ሁሉን ፡ የሚገዛ (፪ x)
እያሉ ፡ ቀንና ፡ ሌሊት ፡ አይርፉም (፬ x)

የሠማይ ፡ ሰራዊት ፡ ያገለግሉሃል


በቀን ፡ በሌሊቱ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ይሉሃል (፪ x)
እኔም፡ በአቅሜ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
ሰው ፡ ላረከኝ ፡ ጌታ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ (፪ x)

እያሉ ፡ ቀንና ፡ ሌሊት ፡ አይርፉም (፬ x)

መሆን ፡ እወዳለሁ ፡ ሁልጊዜ ፡ በፊትህ


ተመስገን ፡ እንድልህ ፡ እንዳገለግልህ (፪ x)
መሆን ፡ እወዳለሁ ፡ ሁልጊዜ ፡ በፊትህ
ተባረክ ፡ እንድልህ ፡ እንዳገለግልህ (፪ x)
መሆን ፡ እወዳለሁ ፡ ሁልጊዜ ፡ በፊትህ
ከፍ ፡ በል ፡ እንድልህ ፡ እንዳገለግልህ (፬ x)

ሃሌሉያ ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ (፬ x)
ሃሌሉያ ፡ ሃሌ (፬ x)

አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ተወደስ


በልጆችህ ፡ ተቀደስ
ምሥጋናችን ፡ ለእአምላካችን
ያማረ ፡ ነው ፡ የሁላችን

ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ሃሌሉያ


ክብር ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሃሌሉያ
ሞገስ ፡ ሞገስ ፡ የሌለህ ፡ እኩያ
የሌለህ ፡ እኩያ ፡ የሌለህ ፡ እኩያ (፪ x)

ሃሌሉያ (፫ x) ፡ (ሃሌሉያ)
ሃሌሉያ (፪ x) ፡ ሃሌሉያ
ሃሌሉያ (፫ x) ፡ ሃሌሉያ

ሃሌሉያ ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ (፬ x)
ሃሌሉያ ፡ ሃሌ (፬ x)

በፍቅርህ ፡ ዘይት ፡ ነፍሴን ፡ አረስርሰሃል (፪ x)


ተባረክልኝ ፡ ጌታዬ
በምህረትህ ፡ ዘይት ፡ ነፍሴን ፡ አረስርሰሃል (፪ x)
ተባረክልኝ ፡ ጌታዬ

ሥምህ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው


ደናግሎች ፡ አይተው ፡ ወደዱህ (፭ x)
እኛም ፡ አየንህ ፡ ጌታ ፡ ወደድንህ
መልካም ፡ የመዓዛ ፡ ሽታ ፡ አንተ ፡ አለህ
እኔም ፡ አይቼ ፡ ይህን ፡ ውዴ ፡ ወደድኩህ
መልካም ፡ የመዓዛ ፡ ሽታ ፡ አንተ ፡ አለህ (፫ x)

በፍቅርህ ፡ ዘይት ፡ ነፍሴን ፡ አረስርሰሃል (፪ x)


ተባረክልኝ ፡ ጌታዬ
በምህረትህ ፡ ዘይት ፡ ነፍሴን ፡ አረስርሰሃል (፪ x)
ተባረክልኝ ፡ ጌታዬ

በማለዳ ፡ ምሥጋና ፡ በሌሊትም ፡ ዝማሬ


ሁኔታ ፡ አለወጥህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እስከዛሬ
በማለዳ ፡ ምሥጋና ፡ በሌሊትም ፡ ዝማሬ
ነገሮች ፡ አለወጡህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እስከዛሬ

አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ (፬ x)
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ (፬ x)
ስደክም ፡ ጉልበቴ ፡ ስበረታ ፡ ክብሬ
አንተ ፡ አልተለወጥክም ፡ ኢሄው ፡ እስከዛሬ
ቀናቶች ፡ ሲያልፉ ፡ አመታት ፡ ሲሆኑ
የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ አለ ፡ በዙፋኑ

በማለዳ ፡ ምሥጋና ፡ በሌሊትም ፡ ዝማሬ


ሁኔታ ፡ አለወጥህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እስከዛሬ
በማለዳ ፡ ምሥጋና ፡ በሌሊትም ፡ ዝማሬ
ነገሮች ፡ አለወጡህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እስከዛሬ
አንተ ፡ ነህ ፡ እስከዛሬ (፪ x)

ያለምህረትህ ፡ ምን ፡ አለኝ
ያለ ፡ ይቅርታህ ፡ ምን ፡ አለኝ
ምን ፡ አለኝ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ (፬ x)
ያለምህረትህ ፡ ምን ፡ አለኝ
ያለ ፡ ይቅርታህ ፡ ምን ፡ አለኝ
ምን ፡ አለኝ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ (፮ x)

የምህረት ፡ ደጆችህ ፡ ተከፍተውልኛል


እጅህም ፡ ለእኔ ፡ ተዘርግቶልኛል (፪ x)
እመጣለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ
እገባለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እገባለሁ ፡ እገባለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እመጣለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ
እመጣለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እመጣለሁ ፡ እመጣለሁ

ያለምህረትህ ፡ ምን ፡ አለኝ
ያለ ፡ ይቅርታህ ፡ ምን ፡ አለኝ
ምን ፡ አለኝ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ (፬ x)
የእኔ ፡ መታመኛ ፡ ምህረትህ ፡ ብቻ ፡ ነው
ድፍረት ፡ የሚሰጠኝ ፡ የፍቅር ፡ ፊትህ ፡ ነው (፪ x)
እመጣለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እመጣለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እገባለሁ ፡ እገባለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ
እመጣለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እመጣለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ
እመጣለሁ ፡ እመጣለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ

ተባረክ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ
ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ
ተባረክ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ
ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ (፪ x)

ኢየሱስ ፡ መባና ፡ መሰዋእት


ኢየሱስ ፡ የመዓዛ ፡ ሽታ
ኢየሱስ ፡ አድርጐ ፡ እራሱን
ኢየሱስ ፡ የሰጠኝ ፡ ጌታ
ኢየሱስ ፡ እኔ ፡ አመልከዋለሁ
ኢየሱስ ፡ ቀንም ፡ ሆነ ፡ ማታ

የርህራሄ ፡ አባት ፡ የመጽናናት ፡ ሁሉ ፡ አምላክ


የሆነ ፡ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ
አምላክና ፡ አባት ፡ ይባረክ
የርህራሄ ፡ አባት ፡ የመጽናናት ፡ ሁሉ ፡ አምላክ
የሆነ ፡ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ
አባትና ፡ አምላክ ፡ ይባረክ
ተባረክ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ
ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ (፭ x)

እኔ ፡ እንጃ (፪ x) ፡ ቃል ፡ አገኝ ፡ ይሆን ፡ ወይ


ለመግለጽ ፡ የሚሰማኝን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ስሆን (፪ x)

ሰላም ፡ የሞላበት ፡ ደስታ ፡ የሞላበት


ፍቅር ፡ የሞላበት ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለበት
ሰላም ፡ የሞላበት ፡ ደስታ ፡ የሞላበት
ፍቅር ፡ የሞላበት ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለበት
እግዚአብሔር ፡ ያለበት (፬ x)

የእግዚአብሔር ፡ መንግስት ፡ ጽድቅና ፡ ሰላም


በመንፈስ ፡ የሆነ ፡ ደስታ ፡ ናት (፬ x)
ጸጥታ ፡ ያለበት ፡ እረፍት ፡ የሞላበት
እፎይታ ፡ ያለበት ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለበት

ሰላም ፡ የሞላበት ፡ ደስታ ፡ የሞላበት


ፍቅር ፡ የሞላበት ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለበት
እግዚአብሔር ፡ ያለበት (፬ x)

እኔ ፡ እንጃ (፪ x) ፡ ቃል ፡ አገኝ ፡ ይሆን ፡ ወይ


ለመግለጽ ፡ የሚሰማኝን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ስሆን (፪ x)

አቤት ፡ ፍጥረት ፡ አይቶ ፡ ተደነቀብህ


የእኛማ ፡ እግዚአብሔር ፡ እኩያ ፡ የለህ (፪ x)
አቤት ፡ ፍጥረት ፡ አይቶ ፡ ተደነቀብህ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እኩያም ፡ የለህ (፬ x)
የእኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚሰማ ፡ የሚመልስ ፡ የሚናገር
የእኔ ፡ አምላክ ፡ የሚሰማ ፡ የሚመልስ ፡ የሚናገር

ሥጋዬን ፡ አልነጭም ፡ ፊቴን ፡ አልቧጭርም


አምላኬን ፡ ለማግኘት ፡ ብዙ ፡ አልቸገርም
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ስለው ፡ አቤት ፡ የሚለኝ
ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ያለኝ

የእኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚሰማ ፡ የሚመልስ ፡ የሚናገር


የእኔ ፡ አምላክ ፡ የሚሰማ ፡ የሚመልስ ፡ የሚናገር
የሚናገር ፡ የሚናገር ፡ የሚሰማ ፡ የሚመልስ
የሚናገር ፡ የሚናገር ፡ የሚነግረኝ ፡ የሚነግረኝ
የሚያወራኝ ፡ የሚያወራኝ

አቤት ፡ ፍጥረት ፡ አይቶ ፡ ተደነቀብህ


የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እኩያም ፡ የለህ (፬ x)
አቤት ፡ ፍጥረት ፡ አይቶ ፡ ተደነቀብህ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እኩያም ፡ የለህ (፮ x)

በየት ፡ ሃገር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር


ሰው ፡ ጥሎ ፡ የሚያወቀው ፡ እግዚአብሔር (፬ x)
እግዚአብሔር ፡ አይጥልሽም
እግዚአብሔር ፡ አይተውሽም
እግዚአብሔር ፡ አይረሳሽም (፪ x)
እግዚአብሔር ፡ አይጥልህም
እግዚአብሔር ፡ አይተውህም
እግዚአብሔር ፡ አይረሳህም (፪ x)

ዝም ፡ በሉ ፡ ዝም ፡ በሉ
በኩራት ፡ አትናገሩ (፫ x)
እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው
ስራውን ፡ ሚመዝን ፡ ነው (፫ x)
የእኔ ፡ አምላክ ፡ አዋቂ ፡ ነው
ስራውን ፡ ሚመዝን ፡ ነው (፫ x)

እግዚአብሔር ፡ አይጥለንም
እግዚአብሔር ፡ አይተወንም
እግዚአብሔር ፡ አይረሳንም (፪ x)
እግዚአብሔር ፡ አይጥለንም
እግዚአብሔር ፡ አይተወንም
እግዚአብሔር ፡ አይረሳንም (፪ x)

ሁሉም ፡ በየጓዳው ፡ ችግሩን ፡ እያየ


አንተን ፡ ለማመስገን ፡ እንደምን ፡ ዘገየ (፪ x)

ምድር ፡ ሆይ ፡ ደስ ፡ ይበልሽ
ሠማያትም ፡ ዘምሩ ፡ ኮረብቶች ፡ አጨብጭቡ
ተራሮች ፡ እልል ፡ በሉ
እግዚአብሔር ፡ ችግረኛውን ፡ አስቧል ፡ የተጐዳውን (፪ x)

ዝም ፡ በሉ ፡ ዝም ፡ በሉ
በኩራት ፡ አትናገሩ (፫ x)
እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው
ስራውን ፡ ሚመዝን ፡ ነው (፫ x)
የእኔ ፡ አምላክ ፡ አዋቂ ፡ ነው
ሥራውን ፡ ሚመዝን ፡ ነው (፫ x)
ሥራውን ፡ ሚመዝን ፡ ነው (፮ x)

ጻድቅ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ስራህ ፡ ትክክል


የማታደላ ፡ የማትበድል
ለታላቅነትህ ፡ ፍጻሜ ፡ የለው
አቤት ፡ ጌታም ፡ ሆይ ፡ ስራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው

ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናህን ፡ ይናገራል (፫ x)


ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናህን ፡ ይናገራል (፫ x)

ደግሜ ፡ ደጋግሜ ፡ እባርክሃለሁ


ምሥጋና ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው
ማለዳ ፡ በምሥጋና ፡ አፌን ፡ እከፍታለሁ
ከአንደበቴ ፡ ፍሬ ፡ ለአንተው ፡ እነግራለሁ

ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናህን ፡ ይናገራል (፫ x)


ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናህን ፡ ይናገራል (፫ x)

አዝ፦ እጅግ ፡ የሚምር ፡ የሚራራ


አምላክ ፡ ነውና ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ይድረሰው ፡ ምሥጋና ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ይድረሰው ፡ ምሥጋና (፪ x)

እንኳንስ ፡ ምረሀኝ ፡ ቀርቶልኝ ፡ አበሳ (፪ x)


እኒስ ፡ ምሥጋናዬን ፡ ሁልጊዜው ፡ አልረሳ (፪ x)
ምህረትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ጠንክራለችና (፪ x)
ኃይሌ ፡ ታድሶልኝ ፡ ቆምኩኝ ፡ እንደገና (፪ x)

አዝ፦ እጅግ ፡ የሚምር ፡ የሚራራ


አምላክ ፡ ነውና ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ይድረሰው ፡ ምሥጋና ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ይድረሰው ፡ ምሥጋና
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ይድረሰው ፡ ምሥጋና (፬ x)

ማዳኑን ፡ አስታውቆ ፡ ጽድቁንም ፡ ገለጠ (፪ x)


ከእኛ ፡ መተላለፍ ፡ ምህረቱ ፡ በለጠ (፪ x)
በሞገሱ ፡ ጋሻ ፡ እየከለለን (፪ x)
ከአዳነን ፡ በኋላ ፡ ምህረቱ ፡ ያዘን (፪ x)

አንድ ፡ ላይ ፡ ተስማሙ ፡ እውነትና ፡ ምህረት (፪ x)


መግባትም ፡ ተቻለን ፡ እግዚአብሔር ፡ ካሌበት (፪ x)
ጻድቅ ፡ ፈራጅ ፡ ሲሆን ፡ እንከን ፡ የሌለበት (፪ x)
አልፈረደብኝም ፡ ምህረቱ ፡ አይሎበት (፪ x)

አዝ፦ እጅግ ፡ የሚምር ፡ የሚራራ


አምላክ ፡ ነውና ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ይድረሰው ፡ ምሥጋና ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ይድረሰው ፡ ምሥጋና
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ይድረሰው ፡ ምሥጋና (፪ x)
ጌታ ፡ እልሃለሁ ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ (፪ x)
አምላክ ፡ እልሃለሁኝ ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ (፪ x)
አንተን ፡ አመልካለሁ ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ (፪ x)

ይገባሃል ፡ የአንደበቴ ፡ ቃል
ይገባሃል ፡ የአፌ ፡ ምሥጋና
ይገባሃል ፡ ልዘምርልህ
ይገባሃል ፡ ላገለግልህ

እኔ ፡ አምላክ ፡ እልሃለሁኝ ፡ አንተን ፡ አአመልካለሁ (፭ x)


እስከዛሬ ፡ ተመስገን ፡ ብያለሁ ፡ ተባረክ ፡ ብያለሁ ፡ አሃ
ከፍ ፡ በል ፡ ብያለሁ ፡ እስከዛሬ ፡ ተመስገን ፡ ብያለሁ
ተባረክ ፡ ብያለሁ ፡ አሃ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ብያለሁ

ደግሞ ፡ ዛሬ ፡ ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል
ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል
ደግሞ ፡ አሁን ፡ አሁን ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ጌታ
አሁን ፡ ምን ፡ ልበል
ደግሞ ፡ ዛሬ ፡ ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል
ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል

ይገባሃል ፡ የአንደበቴ ፡ ቃል
ይገባሃል ፡ የአፌ ፡ ምሥጋና
ይገባሃል ፡ ላገለግልህ
ይገባሃል ፡ ልዘምርልህ

ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፬ x)
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፬ x)
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፬ x)
ሌላ ፡ ነገር ፡ አይደለም ፡ ነፍሴን ፡ የሚያረካት
አምላክ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ናና ፡ በመገኘትህ ፡ አርካት
ሌላ ፡ ነገር ፡ አይደለም ፡ ነፍሴን ፡ የሚያረካት
አምላክ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ናና ፡ በመገኘትህ ፡ አርካት (፭ x)

አንዳንዶች ፡ ገንዘብ ፡ ይላሉ


አንዳንዶች ፡ ዝና ፡ ይላሉ
አንዳንዶች ፡ ዘመድ ፡ ይላሉ
አንዳንዶች ፡ ዕውቀት ፡ ይላሉ
እኔ ፡ ግን ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ
አንተው ፡ ነህ ፡ የምትበልጠው (፪ x)

እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ለሰዎች ፡ ሁሉ ፡ መፍትሄ ፡ ያለህ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ለሰዎች ፡ ሁሉ ፡ መፍትሄ ፡ ያለህ
ነፍሴ ፡ ወደደችህ ፡ ወዴት ፡ ትገኛለህ
ስፍራውን ፡ አሳየኝ ፡ የት ፡ ታሰማራለህ (፪ x)

ብርና ፡ ወርቅ ፡ አያጓጓኝም


ልቤን ፡ አይነካኝም ፡ ዓይኔን ፡ አይስበኝም
የሚያጓጓኝ ፡ የእግዚአብሔር ፡ መንግሥት ፡ ነው
ርሃቤ ፡ ጥማቴ ፡ ጽድቁ ፡ ነው ፡ ጽድቁ ፡ ነው (፪ x)

አንተን ፡ ነው ፡ ነፍሴ ፡ የተጠማችው


አንተን ፡ ነው ፡ ነፍሴ ፡ የተመኘችው
የአንተን ፡ ስጦታ ፡ መፈለግ ፡ ትታለች
አንተን ፡ እራህን ፡ ትፈልጋለች
የአንተን ፡ በረከት ፡ መፈለግ ፡ ትታለች
አንተን ፡ ራስህን ፡ ትፈልግሃለች

ምን ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ አለ
ከዚህ ፡ ፀሐይ ፡ በታች
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ነው ፡ እንጂ
ለሰዎች ፡ የሚበጅ (፪ x)
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ለሰዎች ፡ የሚበጅ
ነፍሴ ፡ ወደደችህ ፡ ወዴት ፡ ትገኛለህ
ስፍራውን ፡ አሳየኝ ፡ የት ፡ ታሰማራለህ (፪ x)

መዝገቤ ፡ እኮ ፡ አንተ ፡ ጋር ፡ ነው
መዝገቤ ፡ በሰማይ
መዝገቤ ፡ በአለበት
ልቤስ ፡ በዚያ ፡ አይደል ፡ ወይ (፫ x)

ነፍሴ ፡ ወደደችህ ፡ ወዴት ፡ ትገኛለህ


ስፍራውን ፡ አሳየኝ ፡ የት ፡ ታሰማራለህ (፪ x)
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ለሰዎች ፡ ሁሉ ፡ መፍትሄ ፡ ያለህ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ለሰዎች ፡ ሁሉ ፡ መፍትሄ ፡ ያለህ

አይዞሽ ፡ በርቺ ፡ ግድ ፡ የለም (፪ x)


ሁሉም ፡ ያልፋል ፡ እንደማያልፍ ፡ የለም
ጨለማው ፡ ሲያልፍ ፡ ሌሊቱ ፡ ሲነጋ
ሁሉም ፡ አለው ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ዋጋ

አይዞህ ፡ በርታ ፡ ግድ ፡ የለም (፪ x)


ሁሉም ፡ ያልፋል ፡ እንደማያልፍ ፡ የለም
ጨለማው ፡ ሲያልፍ ፡ ሌሊቱ ፡ ሲነጋ
ሁሉም ፡ አለው ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ዋጋ
ሁሉም ፡ አለው ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ዋጋ (፬ x)

አይዞሽ ፡ በርቺ ፡ ግድ ፡ የለም (፪ x)


ሁሉም ፡ ያልፋል ፡ እንደማያልፍ ፡ የለም
ጨለማው ፡ ሲያልፍ ፡ ሌሊቱ ፡ ሲነጋ
ሁሉም ፡ አለው ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ዋጋ

አይዞህ ፡ በርታ ፡ ግድ ፡ የለም (፪ x)


ሁሉም ፡ ያልፋል ፡ እንደማያልፍ ፡ የለም
ጨለማው ፡ ሲያልፍ ፡ ሌሊቱ ፡ ሲነጋ
ሁሉም ፡ አለው ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ዋጋ
ሁሉም ፡ አለው ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ዋጋ (፬ x)

You might also like