Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 73

Christo et Ecclesiae

1
ማውጫ

ማስረጃ ............................................................................................................... 3

ምልከታ .............................................................................................................. 7

ምሥጢረ ሥላሴ .................................................................................................. 9

አንቀጽ አንድ፡ አንድ ሕልውና ............................................................................ 9

የእግዚአብሔር ልጅ .................................................................................... 11

የእግዚአብሔር መንፈስ .............................................................................. 22

አንቀጽ ሁለት፡ ሦስት አካላት ........................................................................... 25

ወልድ በተለየ አካሉ በግብር ተወላዲ፣ በስም ልጅ ይባላል .............................. 26

መንፈስ ቅዱስ በተለየ አካሉ በግብር ሠራጺ፣ በስም መንፈስ ቅዱስ ይባላል። .. 31

አንቀጽ ሦስት፡ የማይነጣጠል አሰራር ............................................................... 39

የእግዚአብሔር ቃል .................................................................................... 39

የእግዚአብሔር እስትንፋስ........................................................................... 42

ምሥጢረ ሥጋዌ.............................................................................................. 48

አንቀጽ አንድ፡ ትሥጉት ................................................................................... 48

አንቀጽ ሁለት፡ ነገረ መስቀል ............................................................................ 59

ዋቤ መጽሐፍት .................................................................................................. 70

2
ማስረጃ

ሊቀ መዘምራን፣ ክቡር ዳዊት፣ ”እንዲህ ያለው ዕውቀት ለኔ ድንቅ ነው፤


1
ልደርስበትም የማልችል ከፍ ያለ ነው” ሲል በዘመረው መሠረት፣ ትምህርተ መለኮት
2
ከዕውቀት አድማሳችን ባሻገር እንደሆነ እናምናለን። ስለዚህ በዐጉል ምርመራ ከዐቅማችን
በላይ አንንጠራራም። መለኮት በረቂቅነቱ ድንቅ፣ በድንቅነቱም ረቂቅ ነውና ምሥጢሩ
ሰውና መላእክት ተመራምረው የሚደርሱበት አይደለም። በማይጠቅም ምርምር
3
መለኮትን ለማወቅ ብንሞክር፣ በከንቱ እንደክማለን። በፍኖተ አእምሮአችን ወደ
4
መለኮታዊ እውቀት መዝለቅ ስለሚሳነን እግዚአብሔር ራሱ አብርሆቱን ሰደደልን፤
5
የሚሥጢራትን መጋረጃ ቀድዶ የተመሰጠረውን ገሃደ ።

እጅግ አፍቃሪ፣ እጅግም ጠቢብ አባታችን ባሕሪያችንን በሚመጥን፣ ለመረዳት


ግልጥ በሆነ መልኩ ለድነታችን አስፈላጊና በቂ ምሥጢራትን በቅዱሳት መጽሐፍት
6
ገልጦልናል ፤ እኛም እሊህ መጽሐፍት የመጨረሻ ዳኛ መሆናቸውን አውቀን በእምነትና
7 8
በሃሌታ ከመቀበል በስተቀር የምንጨምረውም ሆነ የምንቀንሰው ነገር ሊኖር አይገባም።
መለኮታዊ ጥበብ ”የሃይማኖት ነገር ከዚህ እንዳያልፍ፤ እንዳይተርፍ” ብሎ ያሰመረልንን
ድንበር አንጣስ፤ ይልቅ በፍቅሩ የገለጠልንን እውነት አጥብቀን እንያዝ። ለአሁን
በድንግዝግዝ በምናየው ረክተን፣ በሚመጣው ዓለም ፊት ለፊት ለማየት መናፈቅ አለብን

1
መዝ 139፡6
2
Origen, De Principiis, Book 1: “Our understanding is unable of itself to behold God
Himself as He is.”
3
To apply logic where it is not applicable is illogical.
4
አብርሆት- መገለጥ
5
ገሃድ አወጣ (ገለጠ)
6
Athanasius: “Man can perceive only the hem of the garment of the triune God; the
cherubim cover the rest with their wings.”
7
ሃሌ- ሃሌታ- ስብሐት- ውዳሴ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ)
8
አራቱ የቅዱሳት መጽሐፍት ባሕርያትን ልብ በሉ፡- ግልጽነት፣ አስፈላጊነት፣ ብቁነትና ባለ ሥልጣንነት
St. John of Damascus, The Orthodox Faith, Book 1, Chap.1: “He revealed that which
it was to our profit to know; but what we were unable to bear He kept secret.
With these things let us be satisfied, and let us abide by them, not removing
everlasting boundaries, nor overpassing the divine tradition.”
3
እንጂ እንደ ፍልስፍና ተማሪዎች በምርምር ብዛት አእምሯችንን ማስጨነቅ የለብንም።
የአምላክን ታላቅነት በሰው አእምሮ ከመመዘን ውቅያኖስን በሲኒ መስፈር እጅጉን
ይቀላል። የመለኮትን ምሥጢር ከመመርመር፣ የገለጠውን በእምነት መቀበል ብልህነት
ነው። በአእምሮአችን መስፈርት በመስፈር፣ በኅሊናችን ሚዛን በመመዘን ያምናበጀው
9
ጣዖት እንጂ መለኮት ሊሆን አይችልም። ስለሆነም [ትምህርተ መለኮትን ስናጠና]
የአብርሆት ተማሪዎች እንጂ የአእምሮ ተመራማሪዊች አንሁን። እዚህ እምነት እንጂ
10
ምርመራ አንዳች ፈይዳ የለውም። ሮማውያን ሊቃውንት እንደሚሉት፦ Da fidei quae
11
fidei sunt- የእምነትን ለእምነት።

ሁሉን በቀኖናዊ መጽሐፍት መሠረት፣ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት፣ በመንፈስ


ቅዱስ አጋዥነት እናምናለን፤ እናስተምራለን። ”የለም! የለም! ቅዱሳት መጽሐፍት ብቻ!
የምን የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ነው?” ቢሉ፦ በእርግጥ የእምነታችን መሠረት፣
የሕይወታችን መመሪያ፣ ”ቅዱሳት መጽሐፍት ብቻ” ናቸው፤ ነገር ግን፣ ”ቅዱሳት
12
መጽሐፍትን እኔ ብቻ አውቃለሁ” ማለት እብሪት ነው። ከብዙዎች ጋር የሚያጣላን
የቅዱሳት መጽሐፍት ሥልጣን ሳይሆን የቅዱሳት መጽሐፍት ትርጓሜ ነው። እኛ የራሳችንን
ትርጓሜ ለማጽናት የቤተ ክርስትያንን ትውፊት እንጠቀማለን።

ቅዱሳት መጽሐፍት ታሪካዊ መጽሐፍት ናቸው። ቸር አምላክ በየዘመኑ


የሚያስነሳቸው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ቀድመውን አንብበዋቸው የተረዱትን በጽሁፍ
አውርሰውናል። የእነርሱን ትርጓሜ መመልከታችን ልንሰጥ ካለነው ስሁት ትርጓሜ
እንድንቆጠብ ይረዳናል። ”የኣርዮስ ኑፋቄ ቅዱሳት መጽሐፍትን እና የቤተ ክርስቲያንን
ትርጓሜ ካለማወቅ የተወለደ ነው” እንዲል ቅዱስ አትናቴዎስ። በልዩ ልዩ ጊዜያት የሚነሱ
መናፍቃን ችግር ከቤተ ክርስቲያን ሳይማሩ መምህራን ሊሆኑ መፈለግ ነው። እንግዳ የሆነ

9
Tertullian, Against Praxeas, Chap 18: “Heretics fabricate idols with their words, just
as the heathen do with their hands; that is to say, they make another God and
another Christ.”
10
St. Ambrose, De fide, 1:"Put arguments aside where faith is sought."
11
የአመክንዮን ሥፍራ ጠንቅቀን ማወቅ አለብን
12
ትዕቢት
4
13
ትርጓሜ ሁሉ ስሁት ነው፤ ሲከፋም ኑፋቄ ነው። ፈጠራ የመናፍቁ መለያ ነው።
14
በጥንታዊው ጎዳና መጓዝ ብልህነት ነው።

በሌላ ጽንፍ የቅዱሳት መጽሐፍትን ሥልጣን ከቤተ ክርስቲያን ትውፊት ሥልጣን


የሚያስተካክሉ መኖራቸው እሙን ነው። አበው፣ ”Vox audita perit, littera scripta
manet- በቃል ያለ ይረሳል፤ በመጽሐፍ ያለ ይወረሳል” በሚል መርሕ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ፣
ረድኤት ለክርስቶስ ክብርና ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ብዙ ድርሳናት ደረሱ፣ ብዙ መጽሐፍት
ጻፉ፤ ሆኖም ከቤተ ክርስቲያን ጽሁፎች ውስጥ ቅዱሳት መጽሐፍትን ”ሕጸጽ አልባ” ሲሉ
ለዩ። ቅዱሳን አባቶቻችን ራሳቸው ”በጽሁፋችን ውስጥ ሕጸጽ ቢገኝ የግል ስህተታችን ነው”
15
የሚሉ አይደሉምን? (የግርጌ ማስታዎሻውን ተመልከት)

እስኪ እንጠይቃችሁ፦ ጥንታውያን አበው፣ ”ሕጸጽ አልባ፤ የሃይማኖት መሠረት”


በማለት የለዯቸውን ቀኖናዊ መጽሐፍት የእምነት መሠረት፣ የሕይወት መመሪያ አድርጎ
መያዝ አይገባምን? እነርሱ ቀኖናዊ መጽሐፍትን ለምን ለዩ? ልጆቻቸው ነን የምንል እኛስ
የለዩትን በመደባለቅ ሥራቸውን ለምን እናፍርስ? የከበሩ አባቶቻችን ልጆች ልትሆኑ

13
Philip Schaff, History Of The Christian Church, Volume 3: “Innovation is the
business of heretics not of the orthodox.”
14
Stare super antiquas vias
15
Augustine, Letter 19 (To Gaius): “If you discover in my writing anything false or
blameworthy, you may know that it is bedewed by a human cloud, and you
may attribute that to me as truly my own.”
Augustine, Letter 82 (To Jerome): “…not one of their (sacred scriptures) authors
has erred in writing anything at all. If I do find anything in those books which
seems contrary to truth, I decide that either the text is corrupt, or the translator
did not follow what was really said, or that I failed to understand it. But, when I
read other authors, however eminent they may be in sanctity and learning, I do
not necessarily believe a thing is true because they think so, but because they
have been able to convince me, either on the authority of the canonical writers
or by a probable reason which is not inconsistent with truth.
Thomas Aquines, Summa Theologiae, Part 1, Question 1: “Sacred doctrine…
properly uses the authority of the canonical Scriptures as an incontrovertible
proof, and the authority of the doctors of the Church as one that may properly
be used, yet merely as probable. For our faith rests upon the revelation made
to the apostles and prophets who wrote the canonical books, and not on the
revelations (if any such there are) made to other doctors.”
5
ከወደዳችሁ፣ ፈለጋቸውን ተከተሉ። ጥመትና ሐሰት የለባቸውምና ሃይማኖታችሁ እንደ
ቅዱሳት መጽሐፍት ትምህርት ይሁን።

16
የጥንቶቹ ሊቃውንት ሁሉን በቅዱሳት መጽሐፍት ላይ ይመሰርቱ ነበር፤ የቤተ
ክርስትያንን ትውፊትን ሲጠቅሱ መጽሐፍ ቅዱስን በትክክለኛ መንገድ እንደተረዱና
እንዳስረዱ ለማረጋገጥ ነው። እውነተኛውን እምነት ቅዱሳት መጽሐፍት እና በቤተ
ክርስቲያን ትውፊት ማረጋገጥ የጥንቶቹ ሊቃውንት ልማድ ነው። ይህም ቅዱሳት
መጽሐፍት በራሳቸው በቂና ምሉዕ ስላልሆኑ ሳይሆን ለቅዱሳት መጽሐፍት ስሁት ትርጓሜ
የሚሰጡ በመኖራቸው ነው። ቅዱሳት መጽሐፍት ምሉዕና በቂ መስፈርተ ዓሚን
17
(norma/regula fide) በመሆናቸው የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ድርሻ የቅዱሳት
መጽሐፍት ታማኝ ተርጓሚ፣ ትጉህ አቃቢ መሆን ነው። የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ቅዱሳት
መጽሐፍትን እንደወደድን እንዳናጎሳቁል ጣልቃ ይገባል።

ሰባኪው በቅዱሳት መጽሐፍት መሠረት የቤተ ክርስቲያን ትርጓሜን ተከትሎ


ማስተማሩ የመንፈስ ቅዱስ ረድኤት ካልታከለበት ከንቱ ነው። መንፈስ ቅዱስ ልብን
ካላስተማረ ሰባኪው በከንቱ ይደክማል። ሰው ለጆሮ ይናገራል፤ ልብን የሚያስተምር ግን
በሰማይ አለ። በሚፈሩት ሰዎች ልቡና አድሮ ዕውቀትን የሚገልጽ እግዚአብሔር ነው። በዚህ
መንገድ ሁሉን በቀኖናዊ መጽሐፍት መሠረት፣ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት፣ በመንፈስ
ቅዱስ አጋዥነት እናምናለን፤ እናስተምራለን።

ደራሲው ለሰፊው የማሕበረ ሰብእ ክፍል እንግዳ ይሆናሉ ብሎ ያሰባቸውን ቃላት


ፍቺ በግርጌ ማስታዎሻዎች መልክ አኑሯል። የግርጌ ማስታዎሻዎቹ ከዚህ በተጨማሪ
የመጽሐፉን ጭብጥ ለመረዳት ጠቃሚ መረጃዎችን የሚያቀብሉ ናቸው። በዚህ መሠረት
ተደራሲያኑ የመጽሐፉን የሐሳብ ፍሰት ተከትለው፣ የግርጌ ማስታዎሻዎቹን እያጣቀሱ
እንዲያነቡ ይመክራል።

16
Augustine: “Our concern with any man is not with what eloquence he teaches,
but with what evidence.”
17
የእምነት መለኪያ
6
ምልከታ

ነገሮችን ማወሳሰብ የእውቀታችንን ጡንቻ ፍርጣሜ ለሌሎች እንደማሳያ


ስንጠቀምበት ይስተዋላል። ለአያሌ ጊዜያትም ነገረ መለኮታዊ አቀራረባችን ከተደራሹ
ቁመት በላይ ይሆንና “የተደራሽ ያለህ!” ሲያሰኝ መስማት የተለመደ ነው። ማወሳሰቡም
ሆነ ሽቅብ መሳቡ ክፋት ባይኖረውም አትራፊነቱ ግን የእፍኝ ዝግን ያህል ነው። በሌላ በኩል
ነገር ማወሳሰብ የሀሳብ አቅራቢውን የዕውቀት ውስንነት አሳባቂ ነው። አልበርት
አይንስታይን “በቀላሉ ልታስረዳው ካልቻልክ፣ አልተረዳኸውም ማለት ነው” የሚለው
ለዚያም አይደል!

የተለየ አብርሆት የሚፈልጉትም ቢሆኑ በአተረጓጎም ልዩነት ጎራ አስለይቶ በቃላት


ሲያቧቅስ ዘመን ፈጅቷል፤ ከዚያም አልፎ ህይወት በልቷል። ውጤቱ ለማም ከፋ መጽሐፍ
ቅዱስን ለመተርጎም አስፈላጊ ያደረገው የራሱ የቅዱሱ መጽሐፍ ባሕርይ መሆኑ ልብ ሊባል
ይገባል። ጎርደን ፊ እና ዳግላስ ስቱዋርት፣ ፕሮፌሰር ጆርጅ ላድን ዋቢ አድርገው “መጽሐፍ
ቅዱስ በታሪክ በሰዎች ቃላት የተገለጸ የእግዚአብሔር ቃል” ስለሆነ፣ ከዚህ መንታ ባህርይው
የተነሳ መተርጎም አስፈላጊ እንደሆነ ያስረዳሉ (መጽሐፍ ቅዱስን ለሁለንተናዊ ጥቅሙ
ማጥናት፣ ጎርደን ዲ. ፊ እና ዳግላስ ስቱዋርት(ትርጉም ግርማዊ)፣5) ። መተርጎም አስፈላጊ
የመሆኑን ያህል ትክክለኛውን ትርጉም መከተሉም አንኳር ጉዳይ ነው።

የተለየ አብርሖት የሚፈልጉ ሀሳቦችን ከትክክለኛው ትርጉም በመቅዳት ቀላልና


በሚገባ መንገድ ለተደራሲው ማቅረብ መለኮታዊ ዕገዛን፣ የራስን መፍጨርጨር አደብ
ማስገዛትን ይጠይቃል። ወንድም ሔኖክ በዚህች አነስተኛ ገጽ ባላት፣ ነገር ግን ግዙፍ ነገረ
መለኮታዊ ሀሳቦችንና ሙግቶችን በያዘች መጽሐፍ የቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶች
የትንፋሻቸው ሙቀት አንገታችን ሥር እንዲሰማን በሚያደርግ ሁኔታ አቅርቦልናል።
ምስጢረ ሥላሴን በተመለከተ የግርታውን ግርዶሽ ቀስ እያረገ፣ ሆኖም ግን በአባቶች ቃል
እየሞገተ በመግፈፍ፣ ስለ ስላሴ አካላትም፣ “አብ በተለየ አካሉ በግብር ወላዲ፣ በስም አባት
ይባላል። ወልድ በተለየ አካሉ በግብር ተወላዲ፣ በስም ልጅ ይባላል። መንፈስ ቅዱስ በተለየ
አካሉ በግብር ሠራጺ፣ በስም መንፈስ ቅዱስ ይባላል” በማለት ያስረዳል።

በሌሎችም በሚያነሳቸው ሀሳቦች የሙግቱን ዳርቻ አስፍቶ ሳያንዛዛ፣


ለመሰብሰብ በሚመች ጥቂት ዋና ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሽከረከር በማድረግ ተደራሲውን

7
አማኝ ከስህተት ለመጠበቅ ይታገላል። ጸሐፊው “ከተመሠረተው በቀር … ሌላ መሠረት
ሊመሠርት” (1ኛ ቆሮ. 3፡11) አይዳዳውም፤ ይልቁኑ “በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ”
የታነጹ(ኤፌ.2፡20) የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ተጋድሎ ተጋድሏችን እንድናደርግ
ይጎተጉተናል። እኛም “በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ
ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ”(1ኛ ጴጥ. 3፤15) በተባልነው መሰረት ለመዘጋጀት
ያግዘን ዘንድ፣ ለህይወትም ይጠቅመን ዘንድ እንድናነበው አበረታታለሁ። መልካም ንባብ።

(አበበ አብዲሳ(መ/ር))

8
ምሥጢረ ሥላሴ

አንቀጽ አንድ፡ አንድ ሕልውና

ከሁሉ ይበልጥ፣ አብይና መሠረታዊ ምሥጢር በመሆኑ፣ “የምሥጢራት ሁሉ


ምንጭ“ በመባል ይታወቃል ምሥጢረ ሥላሴ። የክርስትና ሃይማኖትና ህይወት አማክሎተ
18
ምሥጢር ነው። አንዳንዶች እብሪት ጋልቧቸው፣ “ምሥጢር መባል የለበትም“ ሲሉ፣
ሌሎች ደግሞ፣ “ሥላሴ የሚል ስም በቅዱሳት መጽሐፍት አልተጠቀሰምና አስተምህሮው
መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም“ ይላሉ።

ለምን ምሥጢር ተባለ? ቢባል፦ ከዕውቀት አድማሳችን ባሻገር ያለ እውነት


በመሆኑ ነው፤ እግዚአብሔር ግን በቸርነቱ ገለጠልን። በዚህ አግባብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
በአክብሮት እንድንቀበለው፣ በፍኖተ አእምሮ የማይደረስበት መሆኑን እያመለከተች፣
”ታላቅ ምሥጢር” ትለዋለች። ይህም ረቂቅ ምሥጢር የክርስትና አርማ፣ ምልክት ሆኖ
ይኖራል።

ለምን ሥላሴ ተባለ? ቢባል፦ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰውን ልጆች ከአምልኮተ


ጣዖት ለማዳን በቅዱሳት መጽሐፍት በአንድነቱ ሦስትነቱን፣ በሦስትነቱ አንድነቱን
ገልጦልናል። በዚህ መሠረት አንድ አምላክ በሦስት አካላት እንደ ነበር፣ እንዳለና እንደሚኖር
እናምናለን። “ሥላሴ“ የሚለው ቤተ ክርስቲያናዊ ስያሜ ይህን የአንድነትና የሥስትነት
ምሥጢር ያመለክታል። ሥላሴ የሚለውን ስም አለመቀበልህ ከድነት ሊያጎድልህ

18
Catechism of the Catholic Church, Part 1, sect. 1, Chap. 1: “The mystery of the
most holy Trinity is the central mystery of Christian faith and life. It is the
mystery of God in Himself. It is therefore the source of all the other mysteries
of faith, the light that enlightens them. It is the most fundamental and
essential teaching in the hierarcy of the truth of faith… The Trinity is a
mystery of faith in the strict sense.”
9
አይችልም። አንድ አምላክ በሦስት አካላት እንደ ነበር፣ እንዳለና እንደሚኖር ባታምን ግን
ያለ ጥርጥር የዘለዓለም ጥፋት ይደርስብሃል።

ቅዱስ አውገስጢን፣ “እንደዚህ አስተምህሮ ስህተት ጎጂ፣ ምርመራው አድካሚ፣


እውነቱን ማግኘት ጠቃሚ የሚሆንበት አስተምህሮ የለም” በማለት በጥንቃቄና በትጋት
19
እንድንማር ያበረታታናል። ትምህርቱ በይዘቱ ከባድ በመሆኑ ወደ ኋላ አቆይተን
የምናስተምረው ሳይሆን፣ የክርስትና ሃይማኖት ጀማሪያን በሙሉ በቅድሚያ ሊያውቁት
የሚገባ መሠረተ ትምህርት ነው። ምሥጢረ ሥላሴን ሳያምኑ ክርስትና የለም። ለመዳን
የሚፈልግ ሁሉ ምሥጢረ ሥላሴን እውነተኛ አድርጎ ሊቀበል ይገባል፤ የማይቀበል ሁሉ ያለ
ጥርጥር የዘለዓለም ጥፋት ይደርስበታል።

19
St. Augustine, On The Trinity, Book 1, Chap. 3
10
የእግዚአብሔር ልጅ

ምሥጢረ ሥላሴ በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ቢገለጥም፣ በምልአት የታወቀው


20
በመሲሑ መምጣት፣ በዘመነ ሐዲስ ነው። የምሥጢረ ሥላሴ መግቢያ በር፣ “ኢየሱስ
የእግዚአብሔር ልጅ ነው“ ብሎ ማመን ነው። ጌታ ኢየሱስ እግዚአብሔርን፣ “አባቴ“ ራሱን፣
“የእግዚአብሔር ልጅ“ ሲል ገልጧል። ይህንንም እውነት በእጁ ተዓምራት፣ በቃሉ ትምህርት
አረጋግጧል። አብም መጀመሪያ በዕለተ ጥምቀት፣ በኋላም በቅዱሱ ተራራ ላይ፣
21
“የምወደው ልጄ“ በማለት መስክሮለታል። የሃይማኖታችን ሥረ መሠረት፣ ኢየሱስ
የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ማመን ነው። ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችው በዚህ
22
የእምነት ጠንካራ ዐለት ላይ ነው። ይህ በሰዎች ጥበብ የተፈጠረ ትርክት ሳይሆን
23
ኣርያማዊ መገለጥ ነው። ይህ በመናፍቃን የማይበገር እምነት፣ የገሃነም ደጆች
የማይችሉት አሸናፊ እውነት ነው። ይህን በአግባቡ ከተረዳን ከመናፍቃኑ ከበባ አምልጠን፣
በሃይማኖት እንጸናለን።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ይህ መለኮታዊ መገለጥ የሕይወት መገኛ፣


የድነት ምንጭ ነው። ክርስቲያን ነኝ የሚል ሁሉ በዚህ ኋይለ ቃል ይስማማል። ነገር ግን፣
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ማለት ምን ማለት ነው? የሚለውን ጥያቄ መመለስ
ስንጀምር ልዩነታችን ይገለጣል። በዚህም እውነተኛውና ሐሰተኛው ክርስቲያን ይለያል።
እውነተኛው ክርስቲያን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሚባል ብቻ ሳይሆን፣ ኢየሱስ
የእግዚአብሔር ልጅ የተባለበትን ምክንያት ጭምር ከቅዱሳት መጽሐፍት፣ በመንፈስ ቅዱስ
ጸጋ ተረድቷል። ሐሰተኛው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሚባል ከቅዱሳት መጽሐፍት
ቢማርም፣ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የተባለበትን አግባብ ግን አልተረዳም ወይም
አልተቀበለም።

20
ክርስቶስ
21
ማቴ 3፡17፣ 17፡5 2ጴጥ 1፡17
22
ማቴ 16፡16 -Catechism of the Catholic Church, Part 1, sect. 2, Chap. 2: “Moved by
the grace of the Holy Spirit and drawn by the Father, we believe in Jesus and
confess: “You are Christ, the Son of the living God.” On the rock of this faith
confessed by st. Peter, Christ built His church.”
23
2ጴጥ 1፡16
11
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ይህን ቃል አለመቀበል ኢ-አማኒነት፣ ቃሉን
ተቀብሎ ከትርጓሜው ማፈንገጥ ምንፍቅና ነው። አንዱ ከነአካቴው ቃሉን አይቀበልም፤
ሌላው የቃሉን ቤተኛ ትርጓሜ በማባረር፣ መጤ ትርጓሜ ይተካል። ሁለቱም ቃሉ
የሚገልጠውን እውነት አይቀበሉም። ሁለቱም በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስላላመኑ አሁን
ተፈርዶባቸዋል። ከእግዚአብሔር ቅዱስ ቁጣ አያመልጡም፤ ያለ ጥርጥር የዘለዓለም ጥፋት
ይደርስባቸዋል። እንኪያስ እኛም በአንደበታችን፣ “ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው“
እያልን፣ በልባችን የመናፍቃኑን ፈለግ ስንከተል እንዳንገኝ ኢየሱስ በምን አግባብ
የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ልንማር ይገባል።

እግዚአብሔር በሦስት አግባብ አባት ይባላል። በመለኮታዊ ግብሩ የፍጥረታት


24
ሁሉ አባት፣ በጸጋ የክርስቲያኖች ሁሉ አባት፣ በአካላዊ ግብሩ የወልድ ብቻ የባሕርይ አባት
25
ነው። ሦስተኛው ውልደት መጀመሪያ ከጠቀስናቸው በዓይነት፣ በደረጃ በማዕረግም
እጅግ በጣም የላቀና የተለየ ነው። በሥነ ፍጥረት እንደምንማረው በፈጣሪነት ግብሩ
የፍጥረታት ሁሉ አባት፣ በትምህርተ ድነት እንደምንማረው በማዳን ጸጋው የክርስቲያኖች
ሁሉ አባት ቢሆንም የባሕርይ አባትነቱ ግን ተቀዳሚና ተከታይ ለሌለው ለአንዱ የባሕርይ
ልጁ ብቻ ነው።

ቅዱሳት መጽሐፍት እግዚአብሔር ከሥነ ፍጥረት ውስጥ ከኪዳኑ ሕዝብ ጋር


ያለውን ልዩ ቁርኝት ለማመልከት የኪዳኑን ሕዝብ “የእግዚአብሔር ልጆች“ በማለት
ይጠራሉ። ከኪዳኑ ሕዝብም የክርስቶስን መሲሃዊ አገልግሎት በጥላነት የመሰሉ የብሉይ
ነገሥታትን “የእግዚአብሔር ልጆች“ በማለት ይለያሉ። በአንዳንድ የቅዱሳት መጽሐፍት
ክፍሎች “የእግዚአብሔር ልጅ“ የሚለው መጠሪያ መለኮትነትን ሳይሆን መሲህነትን ብቻ
የሚያሳይ ነው። አንዳንዶች ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅ ሲሉ መሲህነቱን ለመግለጥ
እንጂ ያ መሲህ መለኮት እንደሆነ አምነው አይደለም። ስለዚህም ኢየሱስን እንደ ተናፈቀው
መሲህ በመቁጠር ሊያነግሱት የፈለጉ፣ መለኮትነቱን በገለጠ ጊዜ ሊገድሉት ሲፈልጉ

24
እግዚአብሔር የሁሉ ቀዳሚ መንስኤ፣ ሉዓላዊ ገዢ፣ መልካም መጋቢ በመሆኑ “አባት“ ይባላል።
ፍጥረታት ሀልዎታቸውን በእርሱ ፍቃድና ኋይል አገኙ።
25
Catechism of the Council of Trent for Parish Priests, Part 1: “God is called Father
for more reasons than one.”
God Is Called Father Because He Is Creator And Ruler
God Is Called Father Because He Adopts Christians Through Grace
The Name Father Also Discloses The Plurality Of Persons In God
12
እናያለን። ሊቃውንተ ቤተ እስራኤል ሊገድሉት እስኪፈልጉ ድረስ ያስቆጣው ከእግዚአብሔር
26
ጋር እኩል መሆኑን መግለጡ እንጂ “መሲሁ ነኝ“ ማለቱ አይደለም።

ለመሆኑ የባሕርይ ልጅ ማለት ምን ማለት ነው? ሥነ ፍጥረታትን፣ “ለይኩን“


27
ሲል ካለ መሆን፣ ወደ መሆን ጠራ (Ex nihilo) እንጂ በቅድምና ከነበረ ነገር አላበጀም።
28
ወልድ ዋሕድ ግን ከአብ ባሕርይ ተወለደ እንጂ ከኪሩቤል፣ ከሱራፌል እንደ አንዱ
አልተፈጠረም። ይህም አብን በመልክ እንዲመስለው፣ በባሕርይ እንዲተካከለው
አድርጎታል። ከብርሃን የሚገኝ ብርሃን እንጂ ሌላ ያልታወቀ፣ ብርሃን ያልሆነ እንግዳ ነገር
እንዳልሆነ ከእውነተኛ አምላክ የሚወለድ እውነተኛ አምላክ ቢባል እንጂ ሌላ ፍጥረት
ሊሆን አይችልም። በዚህ አንቀጽ በቀኖናዊ መጽሐፍት መሠረት፣ በቤተ ክርስቲያን
ትውፊት፣ በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ከብዙ በጥቂቱ አፍታተን የምናስረዳውም ይህን
ታላቅ እውነት ነው።

29
ጌታችን በዘመነ ትሥጉቱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ሲያስተምር የነበሩ
ቀዳማዊ ሰማዕያን እንዴት ተረዱት? ምላሻቸውስ ምንድን ነበር? ክርስቶስስ እንዴት
አስረዳቸው? ፍሰቱን ከትንሹ ወደ ትልቁ በማድረግ በቀዳማይነት የአይሁድን ተቃውሞ፣
ከዚያም የአማኒያንን አቀባበል፣ በመጨረሻም የጌታችንን ማብራሪያ እንመለከታለን።

ለአይሁድ እግዚአብሔርን፣ “አባቴ“ ራሱን፣ “የእግዚአብሔር ልጅ“ ማለት፣


በባሕርይ ከእግዚአብሔር ጋር መስተካከል መሆኑን ተረድተው ነበር። ይህም ቅዱስ
30
አውገስጢን፣ “አርዮሳውያኑ ያልተረዱትን፣ አይሁድ ተረድተው ነበር“ እንዳለው ነው።
ሆኖም በሥጋ ተገልጦ ቢያዩት አምላክነቱን ባለመቀበል፣ “አንተ ተራ ሰው ሆነ ሳለህ፣
31
ራስህን አምላክ ታደርጋለህ“ በማለት ተቆጡ፤ ሊገድሉትም ፈለጉ። ለመሆኑ ልጅነቱ
የባሕርይ ካልሆነ በቀር እንዴት ነው የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል
የሚያደርገው? አስቀድመን እንዳልነው፦ ከብርሃን የሚገኝ ብርሃን እንጂ ሌላ ያልታወቀ፣

26
መሲህ፣ ንጉሥ መሆኑ ለሃገረ ገዢዎቹ ከውልደት እስከ ሞቱ ስጋት እንደሆነባቸው ወንጌላውያኑ
ዘግበዋል። ሊቃውንቱም በሃገረ ገዢዎቹ ፊት ክሳቸውን ሲያቀርቡ ነገሩን ፖለቲካዊ መልክ
ይሰጡታል።
27
Out of nothing
28
አንድያ ልጅ
29
የጌታችንን ምድራዊ ቆይታ ለማመልከት ነው። እንጂ አሁንም ፍጹም አምላክ፣ ፍጹም ሰው ሆኖ
እንደሚኖር ጥያቄ የለውም።
30
St. Augustine, Tractates on John, Tractate 17
31
ዮሐ 5፡18, 10፡33, 19፡7
13
ብርሃን ያልሆነ እንግዳ ነገር አይደለም። የእግዚአብሔርም የባሕርይ ልጅ፣ እግዚአብሔር
ነው። አይሁድ ይህን ከአነጋገሩ በሚገባ ተረድተው ነበር። ስለዚህም እግዚአብሔርን “አባቴ“
በማለቱ፣ “ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል አደረገ“ ሲሉ በቁጣ ተነሱበት።

ጌታችን ከእውርነቱ የፈወሰውን ሰው አቀባበል ተመልከቱ! ጌታችን፣ “አንተ


32
በእግዚአብሔር ልጅ ታምናለህን “ አለው። ያም ሰው መልሶ፣ “አቤቱ! አምንበት ዘንድ
የእግዚአብሔር ልጅ ማን ነው?“ አለው። ጌታ ኢየሱስም፣ “የምታየውና ከአንተ ጋር
33
የሚነጋገረው እርሱ ነው“ አለው። እርሱም፣ “አቤቱ አምናለሁ አለ“ አመለከውም። በቤተ
እስራኤላውያን ዘንድ ስግደት ለልዑል እግዚአብሔር ብቻ መሆኑ ግልጥ ነው። ታዲያ ይህ
ሰው እንዴት ለጌታ ኢየሱስ ሠገደ? ጌታችንስ እንዴት መለኮቱን ገለጠለት? ሰውየው
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ የባሕርይ አምላክ እንደሚያደርገው ተረድቶ ነበር።
በዚህ መሠረት በሥግደት አመለከው። ሐዋርያው ቶማስም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ
34
መሆኑን በዮናስ ምልክት፣ በድለ ትንሣኤ ካረጋገጠ በኋላ፣ “ጌታዬ፤ አምላኬም“ አለው።
35
የነባቤ መለኮት፣ ወንጌላዊ ዮሐንስ፣ ወደ ደረቱ ስለተጠጋጋው ሰው እየተናገረ፣ “እርሱ
36
እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው“ ይለዋል።

እግዚአብሔርን “አባቴ“ በማለቱ፣ “ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል አደረገ“ ሲሉ


ሊገድሉት ለፈለጉ አይሁድ እንደሚከተለው ይመልሳል፤ “አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው
37
ሁሉ፣ ወልድም በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታል።“ ወልድ ሕያው ከሚሆን ከአብ
ስለተወለደ ሕያው ነው፤ የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ እግዚአብሔር ነው። በራስ ሕያው
38
(Self-existant) መሆን የመለኮት ባሕርይ ገንዘብ ነው። ታዲያ፣ “ወልድም በራሱ
ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታል“ ማለት ወልድ ባሕርየ መለኮቱ ከአብ አግኝቷል ከማለት
ውጪ ምን ማለት ሊሆን ይችላል? “ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካከለ“ ሲሉ ለከሰሱት

32
አንዳንድ ቅጆች “የሰው ልጅ“ ይላሉ። ሆኖም የሚበዙ ጥንታውያን አበው “የእግዚአብሔር ልጅ“
በማለት መጠቀማቸው፣ ቀደምት (የጠፉ) ቅጅዎች “የእግዚአብሔር ልጅ“ እንደሚሉ አመላካች
ነው።
33
ዮሐ 9፡35-38
34
ዮሐ 20፡28
35
በቤተ ክርስቲያን ሥነ ጽሁፍ ቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ጎርጎርዮስ የነባቤ መለኮት “Theologian“
በመባል ይታወቃሉ
36
1ዮሐ 5፡20
37
ዮሐ 5፡26
38
God is self-existant. He is existence to all else. There is none self-existant save
God. There is none that exist save by God.
14
አይሁዶች፣ “አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው ሁሉ፣ ወልድም በራሱ ሕይወት እንዲኖረው
ሰጥቶታል“ በማለት አባቱን አክሎና መስሎ መወለዱን ይገልጣል።

ወልድ፣ “የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም


39
የላከውን፦ ትሳደባለህ ትሉታላችሁን? እኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ“ ይላል።
የአብን ሥራ መስራቱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንዴት ያረጋግጣል? ቢባል፦ እርሱ
የሚሰራው መለኮታዊ ሥራ የአባቱ መለኮታዊ ባሕርይ በእርሱ እንደሚኖር እንደሚኖር
ይመሰክራል። ይህ የባሕርይ ልጅነቱ ማረጋገጫ ማሕተም ነው። በዚህ መሠረት ወልድ፣
“የአብ መለኮታዊ ባሕርይ በእኔ መኖሩን ሌላው ቢቀር ስለ ድንቅ ሥራዎቹ እንኳ እመኑ“
ይላል። አብ በወላዲነት የራሱን ባሕርይ ለወልድ ሰጥቶታል፤ ወልድም በረቂቅ ውልደቱ
ባሕርዩን ከአብ ተቀብሏል። አብ በባሕርዩ በወልድ ውስጥ ሕልው ሆኖ ይኖራል፤ ወልድም
በባሕርዩ በአብ ውስጥ ይኖራል። በዚህም መሠረት ወልድ፣ “እኔ በአብ እንዳለሁ፣ አብም
40
በእኔ እንዳለ ስነግራችሁ እመኑኝ“ ይላል። ይህንን፣ አንዱ በአንዱ የመኖሩን ምሥጢር
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን “ሕልውና“ በሚል ቃል ትጠራለች።

ኣርዮስ፣ “ክርስቶስ “የእግዚአብሔር ልጅ“ ቢባል በጸጋ እንጂ፣ በባሕርይ ከአብ


ስለተወለደ አይደለም“ ሲል የባሕርይ ልደቱን ይክዳል። “ባሕርዩ ካለመሆን ወደ መሆን
የመጣ፣ የተፈጠረ እንጂ ከአብ ባሕርይ የወጣ፣ የተወለደ አይደለም“ በማለት ወልድ
በባሕርይ ከአብ የተለየ ነው ይላል። ክርስቶስ ለምን የእግዚአብሔር ልጅ ተባለ? ተብሎ
ቢጠየቅ፣ “ከእግዚአብሔር ስለተወለደ፣ በመልክ ስለሚመስለው፣ በባሕርይ
ስለሚተካከለው ሳይሆን እግዚአብሔር በጸጋው እንደ ልጅ ስለሚያየው ነው“ ይላል።
እንዲህ የሚያስተምሩ ከእምነታችን የተለዩ፣ ከጉባኤያችን የተወገዙ ናቸው። ጸያፍ
ትምህርታቸውም በእኛ ዘንድ የተጠላ ነው።

“ወልድ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ከመፍጠሩ በፊት ፍጥረታትን ሊፈጥርበት


41
የፈጠረው ፍጡር ነው“ የምትል ኣርዮስ ሆይ፤ የወንጌላዊ ዮሐንስን ቃል አድምጥ! “ሁሉ
42
ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ ከተፈጠረው ሁሉ ያለ እርሱ የተፈጠረ ምንም የለም።“
ተመልከት! የሚታየውን፣ የማይታየውን ሁሉ ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ እርሱ ነው፤

39
ዮሐ 10፡36-37 በተጨማሪም ዮሐ 5 ይመልከቱ
40
ዮሐ 14፡11
41
ራሳቸውን “የያሕዌ ምሥክሮች“ ለሚሉ ለዘመናችን ኣርዮሳውያንም ሊነገር ይችላል።
42
ዮሐ 1፡ 3
15
ከተፈጠሩ ፍጥረታት መካከል ያለ’ርሱ ምንም የተፈጠረ የለም። ወልድ ከሥነ ፍጥረት
የሚቆጠር ሳይሆን ፈጣሬ ኩሉ ነው። እንደ ፍጡራን ፍጡር ሆኖስ ቢሆን ከፍጡራን ጋራ
43
ይቆጠር ነበር። ኣርዮስ ሆይ፤ አንተ “ፍጡር“ የምትለውን የእቅፍ ወዳጁ፣ “ፈጣሬ ኩሉ“
ይለዋል። እኒህ ከሐዲያን እንደምን ደፍረው ፈጣሪን ፍጡር ይላሉ? እኛስ ቅዱሳን ሐዋርያት
ባስተማሩት መሠረት በወልድ ፈጣሬ ኩሉነት እናምናለን፤ እናስተምራለን።

ሌሎች ደግሞ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ባሕሪውን ከአብ


ስለሚያገኝ ሳይሆን በግብሩ ለአብ ስለሚገዛ ነው ይላሉ። “እውነተኛ ወላዲነትና ተወላዲነት
በእግዚአብሔር ዘንድ ከሌለ፣ የአብ አባትነት፣ የወልድም ልጅነት እውነተኛ አይደለም“ ይላል
44
አኩዊነስ። አካላዊው ጥበብ [ወልድ]፣ በጠቢቡ ሰለሞን አድሮ፣ “ከውቂያኖሶች በፊት፣
የምድር ምንጮች ከመፍለቃቸው በፊት ተወለድሁ፤ ተራሮች ገና ሳይመሰረቱ
45
ከኮረብቶችም በፊት ተወለድሁ“ ይላል።

ውልደትን እና ሥርጸትን የሚክዱ በምሥጢረ ሥላሴ እናምናለን ይበሉ እንጂ


ዶግማውን ግን ክደዋል። ሦስት አካላት እንዳሉ፣ በመለኮትና በባሕርይ አንድ እንደሆኑ
ያምናሉ። ነገር ግን እውነተኛ የወላዲነት፣ የተወላዲነትና የሠራፂነት ግብር መኖሩን፣ በሦስቱ
46
አካላት አንድ ሕልውና መኖሩን ይክዳሉ። እነዚህ ሰዎች በምሥጢረ ሥላሴ ያምናሉ
ከማለት፣ በሦስት አማልክት ያምናሉ ማለት ይቀላል። የክርስቶስ ልጅነት የባሕርይ ልጅነት
እንደሆነ ከላይ የጠቀስናቸው የሙግት ነጥቦች ያስረዳሉ። ውስጣዊ ግብርና የመለኮታዊ
ሕልውና አንድነትን መካድ ምሥጢረ ሥላሴን መካድ ነው ያልንበትን ምክንያት በተገቢው
ክፍል እናያለን።

አብ ወልድን ከወለደ አይልቀውምን? አይቀድመውምን? አብ አባት በመሆኑ


ከወልድ አይልቅም። ወልድ ልጅ በመሆኑ ከአብ አያንስም። ኣርዮስ ወልድ ተወላዲ ከሚለው
በመነሳት ዘላለማዊነቱን ይክዳል። የሙግት ቅደም ተከተሉ ይህን ይመስላል፤ ”ወልድ ከአብ
ከተወለደ ዘላለማዊነትን ከአብ አይጋራም፤ ይህም ወልድ ያልነበረበት ጊዜ ነበር ማለት
ነው። ወልድ ያልነበረበት ጊዜ ነበር ማለት ደግሞ፣ አብ አባት ያልነበረበት ጊዜ ነበር ማለት
ነው። ልጁ ከመወለዱ በፊት አልነበረም፣ አባቱም ከመውለዱ በፊት አባት አልነበረም።”

43
ሐዋርያው ዮሐንስ፤ የጌታችን የእቅፍ ወዳጅ
44
Thomas Aquines, Summa Theologiae, Part 1, Question 28
45
ምሳ 8፡25-25
46
መለኮታዊ ሕልውና የሚለው ቃል አንዱ አካል በሌላው በባሕርይ መኖር፣ መገኘቱን ያመለክታል
16
ኣርዮስ መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ባለማወቁ፣ ጥያቄ በተፈጠረበት ጊዜም የቤተ
ክርስቲያንን ሊቃውንት ጠይቆ ከመረዳት ይልቅ፣ በሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት
ላይ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረጉ፣ ሳተ፤ ብዙሃንን አሳተ።

ኣርዮስ የማያስተውሉ ደካማ ሴቶች ጋ ይሄድና፣ “ከመውለድሽ በፊት ልጅ


ነበረሽ?” ሲል ይጠይቃል። አከታትሎም፣ “ከመውለድሽ በፊት ልጅ እንዳልነበረሽ ሁሉ፣ አብ
47
ከመውለዱ በፊት ልጅ አልነበረውም” ይላል። እኛም ለኣርዮስ ጥያቄ እናቅርብ፡- አንድ
የፈጠራ ባለሙያ፣ የሚሰራባቸውና የሚጠቀማቸው ቁሶች ሳይኖሩ ፈጠራውን መፈጸም
ይችላልን? ይህ ማለት እግዚአብሔርም ለመፍጠር የግድ የሚሰራባቸውና
የሚጠቀምባቸው ቁሶች ያስፈልጉታል ማለት ነውን? በፍጹም! መፍጠር በእግዚአብሔር
ዘንድና በሰው ዘንድ አንድ እንዳልሆነ ሁሉ፣ ውልደትም በእግዚአብሔር ዘንድና በሰው ዘንድ
አንድ አይደሉም። አብ ወልድን ወለደው በምንል ጊዜ እንደ ሰው መወለድ አድርገው
የሚያስቡ ካሉ ተሳስተዋል። ይህ ልደት እንደ ሰው ልደት አይደለም፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤
አይመረመርም። በሥነ ፍጥረት እንደምናየው ልጅ ከአባቱ ጋር በሥነ ተፈጥሮው እኩል
ነው። ወልድም በመለኮቱ ከአባቱ ጋር እኩል ነው። ሆኖም እንደ ምድራዊ አባትና ልጅ በጊዜ
48
መቀዳደም የለባቸውም። “አብ ከወልድ ተለይቶ የኖረበት ዘመን አለ፤ ኖሮ ኖሮ አባት ሆነ“
ይሉ ዘንድ አይገባም፤ ይኸውም መራባት ነውና። አብ ዘለዓለማዊ አባት፣ ወልድም
ዘለዓለማዊ ልጅ ነው።

የክርስትና እምነት ወልድ ፈጣሬ ኩሉ እንደሆነ ይመሰክራል። ጊዜን፣ ሥፍራን፣


49
ቁስ አካላትን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ፣ የሚታየውንና የማይታየውን የፈጠረ እርሱ
ነው። ታዲያ እንዴት፣ ”አብ ከመውለዱ በፊት ልጅ አልነበረውም ይባላል?” በፊት የጊዜ
አመልካች ነው፤ ወልድ ከመወለዱ በፊት በማለት የትኛውን ጊዜ ልናመለክት እንችላለን?
50
የጊዜ ፈጣሪ ሳይኖርስ ጊዜ እንዴት ሊኖር ይችላል? ኣርዮስ ሆይ፤ እርሱ የጊዜ ፈጣሪና ገዢ
ነው እንጂ ጊዜያዊ ፍጥረት አይደለም። የወልድ ልደት ዓለም ሳይፈጠር፣ ዘመን ሳይቆጠር
ነው። ቅዱስ ዮሐንስ፣ ”በመጀመሪያ ነበር” ሲል ቅድመ ሕልውናውን ያስተምራል።

47
Athanasius, Four Discourses Against The Arians, Discourse 1, chap. 7
48
Origen, De Principiis, Book 1: “God is the Father of His only begotten Son, who
was born indeed of Him, and derives from Him what He is, But with out any
beginning.”
49
Time, Space and Matter
50
ጊዜያዊ መተካካትን በተመለከተ አንቀጸ ዘለዓለም ላይ ማብራሪያ አቅርበናል።
17
”በመጀመሪያ ነበረ” ማለት ጊዜ ሲጀምር እርሱ ነበረ ማለት ነው። ጊዜ ሲጀምር እርሱ ነበር
51
ማለት ዘመን ሳይቆጠር እርሱ ነበር ማለት ነው። እርሱ ከዘመናት በፊት የነበረ አምላክ
መሆኑን እናምናለን።

ወልድም ከአብ ይገኛል፤ አብ ግን ከወልድ አይገኝም። ሆኖም አብ ኖሮ ወልድ


52
የሚጎድልበት ጊዜ የለም። ይህም አባ አትናቴዎስ፣ ”የዘለዓለማዊ ብርሃን ዘለዓለማዊ
53
ነፀብራቅ፤ የዘለዓለማዊ አባት ዘለዓለማዊ ልጅ” እንደሚሉት ነው። ሁለቱም፣ ከመንፈስ
ቅዱስ ጋር ጥንት ሳይኖራቸው፣ ዘመን ሳይቀድማቸው፣ በቅድምና የነበሩ ቀዳማውያን
ናቸው። ይህ ልደት ምሥጢር ነው፤ በሰው ቋንቋና ምሳሌ እናስረዳ እንጂ ከምሳሌዎች ሁሉ
የራቀ ነው። እንደሚገባው መስሎ ሊናገር የሚችል ማንም የለም። የወልድ ከአብ መወለዱ
እንደምንድን ነው? ቢሉ፦ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እርሱ ብቻ ያውቃል። እኛስ
በአእምሮ መርምረን ልናውቅ፣ በአንደበት ተናግረን ልንገልጥ አይቻለንም። ዳግመኛም
ግዙፉ ረቂቁን መርምሮ ማወቅ አይችልም። በዚህ መሠረት ቅዱስ አምብሮስ፣ ”እዚህ ጋ
የእኔ ብቻ ሳይሆን የመላዕክትም ድምጽ ጸጥ ይላል፤ እዚህ ጋ የእኔ ብቻ ሳይሆን
54
የመላዕክትም አዕምሮ ከንቱ ይሆናል” ይላል። በዚህ መሠረት አበው ቅዱሳት መጽሐፍትን
በመከተል ለሃይማኖት ትምህርታችን ወሰን አድርገውለታል።

51
Augustine, Homilies On The Gospels, Sermon 117: “In the beginning was the
Word…. What look you for before the beginning? But if you should be able to
find anything before the beginning, this will be the beginning. He is mad who
looks for anything before the beginning.”
52
Origen, De Principiis, Book 1: “Because His generation is as eternal and
everlasting as the brilliancy which is produced from the sun. For it is not by
receiving the breath of life that He is made a Son, by any outward act, but by
His own nature.”
53
Athanasius, Four Discourses Against The Arians, Discourse 1, chap. 4: “Eternal
Radiance of a Light which is eternal.” Chap. 5: “The etenal offspring of the
eternal Father.”
54
St. Ambrose, Exposition Of The Christian Faith, Book 1, Chap. 10: “Dost thou ask
me how He is a Son, if He have not a Father existing before Him? I ask of thee,
in turn, when, or how, thinkest thou that the Son was begotten. For me the
knowledge of the mystery of His generation is more than I can attain to-the
mind fails, the voice is dumb—ay, and not mine alone, but the angels’ also. It is
above Powers, above Angels, above Cherubim, Seraphim…”
St Hilary of Poitiers, De Trinitate, Book 2: “I look for comfort to the fact that
Archangels share my ignorance, that Angels have not heard the explanation,
18
ሐዋርያው ፊልጶስም፣ ”ጌታ ሆይ፤ አብን አሳየንና ይበቃናል” ባለው ጊዜ፣ ጌታችን፣
”እኔን ያየ አብን አይቶአል” አለው። ምክንያቱንም እያስረዳ፣ ”እኔ በአብ፣ አብም በእኔ አለ”
ይላል። የአብ ባሕርይ በወልድ ሕልው ሆኖ ይኖራል። መለኮታዊ ሕልውና የሚለው ቃል
አንዱ በአንዱ መኖሩን፣ መገኘቱን ያመለክታል። አብ በባሕርይ ወላዲነቱ በወልድ ይገኛል።
ወልድ በባሕርይ ተወላዲነቱ በአብ ይገኛል። ወልድ የሚሠራው መለኮታዊ ሥራ የአብ
ባሕርይ በእርሱ ሕልው ሆኖ መኖሩን ያሳያል። ስለዚህም ”እኔ በአብ እንዲሁም አብም በእኔ
55
እንዳለ ስነግራችሁ እመኑኝ፣ ሌላው ቢቀር ስለ ድንቅ ሥራዎቹ እንኳ እመኑ” ይለናል።
በባሕርይ ከአብ ስለሚወለድ፣ የአብ ባሕርይ በእርሱ ይገኛል። ስለዚህም እርሱ
የሚያደርገውን በሙሉ በእርሱ የሚኖር አብ የሚያደርገው ነው። በባሕርይ ውልደት የተነሣ
የአባት ባሕርይ የልጅ ባሕርይ ነው። የልጅ መለኮታዊ ሥራዎች የአባቱ መለኮታዊ ባሕርይ
በእርሱ እንደሚኖር ያረጋግጣል።

ከዚህም በተጨማሪ ኣርዮሳውያኑ ስለ ወልድ ሰብዓዊ ባሕርይ የሚናገሩ


ክፍሎችን በመጥቀስ ይከራከራሉ። ለምሳሌ፦ ”አብ ከእኔ ይበልጣል” የሚለውን ክፍል
ይጠቅሱና፣ ”እናንተ፣ ”ወልድ በመለኮት ከአብ ጋር አንድ ነው” ትላላችሁ፤ ወልድ ራሱ ”አብ
ከእኔ ይበልጣል” በማለት እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን ላይ ይሳለቃሉ። የሚጠቅሷቸውን
56
ምንባቦች እየዘረዘርን ምካቴ አናቀርብም። ነገር ግን፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሕግና መመሪያ
በመስጠት እንመልስላቸዋለን። ይህም ቀኖናዊ መመሪያ ከሊቀ ሐዋርያት፣ ቅዱስ ጳውሎስ
መልዕክት የተወሰደ ነው። ”እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ጋር
መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቆጠረውም። ነገር ግን የባሪያን ባሕርይ ይዞ፣
57
በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ።”

አንዳንድ ደካሞች ይህን ምንባብ በመጥቀስ፣ ”ቃል ወደ ሥጋነት፣ መለኮት ወደ


ሰውነት ተለወጠ” ይላሉ። መለኮት በባሕርዩ አይለወጥም፤ ታዲያ እንዴት መለኮት
ተለውጦ ሰው ይሆናል? መለኮት ተለውጦ ሰው ሆነ ብሎ ማሰብ ድንቁርና ወይም ድፍረት

and words do not contain it, that no prophet has espied it and no Apostle
sought for it, that the Son Himself has not revealed it.”
St. Gregory Nazianzen (The Theologian), Orations, Oration 29: “This generation
would have been no great thing, if you could have comprehended it who have
no real knowledge even of your own generation.”
55
ዮሐ 14፡8-11
56
ቅዱስ ኣገስቲን ቀኖናዊ መመሪያ (Canonical Rule) ይለዋል።
57
ፊል 2፡6-7
19
ከዚያም በላይ ስድብና ኀጢአት ነው። በክብሩ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተስተካከለ
እውነተኛ አምላክ፣ ለክብሩ የማይመጥን ሰብዓዊ ባሕርይን በመያዙ፣ “ራሱን ባዶ አደረገ“
ተባለ እንጂ ባሕርየ መለኮቱን ትቶ እንኳን አይደለም። ቅዱስ ቶማስ፣ ከዳሰሰው በኋላ፣
“ጌታዬ፤ አምላኬም“ ያለውም ለዚህ ነው። ሰው ስለ ሆነ ዳሰሰው፤ አምላክ ስለ ሆነ
“አምላኬ“ አለው።

”እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው


እንደማይገባ አድርጎ አልቆጠረውም። ነገር ግን የባሪያን ባሕርይ ይዞ፣ በሰውም አምሳል
ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ።” ወዳጆች ሆይ፤ እነሆ ሁለት ባሕርያት! ባሕርየ መለኮትና
58
ባሕርየ ትስብእት (ሰብዓዊ ባሕርይ)። ባሕርየ መለኮቱ ዘለዓለማዊና ከእግዚአብሔር አብ
ጋር እኩል የሆነበት ነው፤ ባሕርየ ትስብእቱ በዘመናት መጨረሻ የያዘውና ከእኛ ጋር እኩል
የሆነበት ነው። ከእኛ ጋር እኩል የሆነበት ሰብዓዊ ባሕርዩ፣ ከአብ ጋር እኩል ከሆነበት ባሕርየ
መለኮቱ ያንሳል። ክርስቶስ አባቴ ከእኔ ይበልጣል ቢል ይህ አነጋገር ለሰብዓዊ ባሕርዩ
59
የሚስማማ ነው። ቅዱሳት መጽሐፍት በሰብዓዊ ባሕርዩ እንኳን ከአብ፣ ከመላእክት
60
እንደሚያንስ ያስተምራሉ። መላእክት ሥጋውያን አይደሉም፤ አይሞቱም። በዚህም
ከሰው ይበልጣሉ። ክርስቶስ ሞትን ይቀምስ ዘንድ ራሱን ዝቅ በማድረጉ ከመላእክት ጥቂት
አነሰ ቢባልም፣ በባሕርየ መለኮቱ ከአብ ጋር እኩል እንደ ሆነ እሊሁ መጽሐፍት
ይመሰክራሉ። ከመላእክት ጥቂት አነሰ መባሉ ሰው ስለ ሆነ ነው። በባሕርየ መለኮቱ
ከእግዚአብሔር ጋር የተስተካከለ ሲሆን፣ ሰብዓዊ ባሕርይን በመያዙ ራሱን ዝቅ አድርጓል።

የመላእክት ፈጣሪና ገዢ ለድነታችን በተሰገወው ሥጋ ከመላእክት ዝቅ ቢል፣


ፍቅሩን ልናወድስ እንጂ መለኮቱን ልንክድ አይገባም። የሰውን ዘር ከፍ ለማድረግ በያዘው
ሰብዓዊ ባሕርይ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ በባሕርየ መለኮቱ ግን ከአብ እኩል ነው። ስለ ሰብዓዊ
ባሕርዩ የተናገረውን ቃልና በሰብዓዊ ባሕርዩ ያደረገውን ለክርስቶስ መለኮታዊ ባሕርይ
61
እንደተነገረ አድርገን ልንተረጉም አይገባም። በተጨማሪም መለኮታዊ ባሕርዩንና
ሥራውን ከአብ እንደሚቀበል የሚያስተምሩ ክፍሎች፣ አባቱን አክሎና መስሎ ከአባቱ እንደ

58
St Hilary of Poitiers, De Trinitate, Book 1: “He who is man is also God, that He
who died is immortal, that He who was buried is eternal.”
59
አንዳንዴም ምሥጢረ ውልደትን ገላጭ ነው።
60
ዕብ 2፡9
61
Origen, De Principiis, Book 1: “The nature of that deity which is in Christ in respect
of His being the only begotten Son of God is one thing, and that human nature
which assumed in these last times… is another.”
20
ተወለደ የሚያስተምሩ ናቸው እንጂ ከአብ እንደሚያንስ የሚያስተምሩ አይደሉም።
እንግዲህ እንዳንሳሳት ክርስቶስ በመለኮታዊ ባሕርዩ ከአብ ጋር እኩል እንደ ሆነ፣ በባሕርይ
ውልደቱ ባሕርየ መለኮቱንና ሥራውን ከአብ እንደሚቀበል ደግሞም በባሕርየ ትስብእቱ
62
ከአብ እንደሚያንስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሕግና መመሪያ አድርገን መቀበል አለብን።

63
”አባቴና አባታችሁ፣ አምላኬና አምላካችሁ” ያለውን የጌታችንን ቃላት አስቡ!
በባሕርየ መለኮቱ ”አባቴ” የሚለውን፣ ለፍጥረት ሥርዓት እንደሚገባ ”አምላኬ” ብሎ
ይጠራዋል። እንደ መለኮቱ አምላካችን የሆነውን እንደ ቸርነቱ ”አባታችሁ” ይለዋል። ቃል
ሥጋ ባይሆን ኖሮ እንዴት አባቱን ”አምላኬ” ይል ነበር? እንዴትስ አባቱን ”አባታችሁ” ይል
ነበር? አባቱን አምላኩ በማድረግ፣ አምላካችንን አባታችን አደረገ። የባሕርይ ወንድማችን
በመሆን የጸጋ ወንድሞቹ አረገን። ”አባቴ” በማለቱ ፍጹም አምላክ መሆኑን፣ ”አምላኬ”
በማለቱ ፍጹም ሰው መሆኑን እናውቃለን። እግዚአብሔርን “አባቴ“ በማለቱ፣
ከእግዚአብሔር እኩል መለኮት መሆኑን ገለጠ፤ እግዚአብሔርን “አምላኬ“ በማለቱ፣ ከእኛ
እኩል ሰው መሆኑን ገለጠ።

እርሱ ብቻ የአብ የባሕርይ ልጅ በሆነ፣ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር ከአብ


በተወለደ፣ ከአምላክ በተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን በተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ በተገኘ
እውነተኛ አምላክ፣ በህልውናው ከአብ ጋር አንድ በሆነ፣ የተወለደ እንጂ ፍጡር ያይደለ፣
በእግዚአብሔር ልጅ፣ በአንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን። ይህንን የሚፃረር
ትምህርት ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ከተጣለ ዘመናት አልፈዋል። ጌታችን በባሕርየ መለኮቱ
ከአብ እኩል መሆኑን ደጋግሞ ገልጧል። በዚህም መሠረት ሊቃውንቱ ክርስቶስን፣ “Liar,
64
Lunatic or LORD- ወይ ሐሰተኛ፣ ወይ እብድ፣ ወይ ደግሞ ከአብ እኩል ነው“ ይላሉ።

62
St. Augustine, On The Trinity, Book 2
63
ዮሐ 20፡ 17
64
Thomas Aquinas, Comm. On John, Chap 5, Lecture 2
21
የእግዚአብሔር መንፈስ

አብ አባት የተባለው ወላዲ ስለሆነ ነው። ወልድ ልጅ የተባለው ተወላዲ ስለሆነ


ነው። ታዲያ መንፈስ ቅዱስ ለምን መንፈስ ቅዱስ ተባለ? አብ መንፈስ ነው፤ ቅዱስም
ነው። ወልድ መንፈስ ነው፤ ቅዱስም ነው። ታዲያ ለምን አብ “መንፈስ ቅዱስ“ አይባልም?
ወልድስ ለምን “መንፈስ ቅዱስ“ አይባልም? በትምህርተ ሥላሴ፣ “መንፈስ ቅዱስ“
የሚለው ስም የሠራጺነት ግብር አመልካች ነው። ሠረጸ ማለት ወጣ፣ ተገኘ ማለት ነው።
አብ ከማንም አይሠርጽም፤ የማንም መንፈስ አይደለም። ወልድም ከማንም አይሠርጽም፤
የማንም መንፈስ አይደለም። መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ይሠርጻል፤ የአብና የወልድ
መንፈስ ይባላል። ስለዚህም መንፈስ ቅዱስ የሚለው የሠራጺነት ግብር አመልካች ለአብና
ለወልድ አይሆንም። የአብ ስም ተለውጦ ወልድ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባልም። የወልድ
ስም ተለውጦ አብ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባልም። የመንፈስ ቅዱስ ስም ተለውጦ አብ
ወይም ወልድ አይባልም (አንቀጽ ሁለትን ተመልከት)።

ወልድ በባሕርይ ውልደት ከአብ እንደሚገኝ ሁሉ መንፈስ ቅዱስም በባሕርይ


ሥርጸት ከአብና ከወልድ (እንደ ኦርቶዶክሳውያን፦ ከአብ ብቻ) ይገኛል (አንቀጽ ሁለትን
ተመልከት)። ወልድ በባሕርይ ውልደቱ አባቱን አክሎና መስሎ እንደ ተገኘ፣ መንፈስ
65
ቅዱስም በባሕርይ ሥርጸቱ አሥራጺዎቹን (እንደ ኦርቶዶክሳውያ፦ አሥራጺውን) አክሎና
66
መስሎ ተገኝቷል። ወልድ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚባል ሁሉ መንፈስ ቅዱስ
የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይባላል። መንፈስ ቅዱስ የአብና ወልድ መንፈስ በመሆኑ፣
በአብና በወልድ ያለ ባሕርይ በእርሱም ሳይጓደል ይኖራል። ዳግመኛም አብ በወልድና
በመንፈስ ቅዱስ ሕልው እንደሆነ፣ ወልድ በአብና በመንፈስ ቅዱስ ሕልው እንደሆነ፣
መንፈስ ቅዱስም በአብና በወልድ ሕልው እንደሆነ እናምናለን።

65
Tertullian, Against Praxeas, Chap 4: “I believe the Spirit to proceed from no other
source than from the Father through the Son.”
66
Philip Schaff, History of the Christian Church, Volume 3, Section 128: “The
baptismal formula and the apostolic benediction, as well as the traditional
Trinitarian doxologies, put the Holy Ghost on an equality with the Father and
the Son.”
22
መንፈስ ቅዱስ ግዑዝ ሳይሆን ረቂቅ አካል፣ ዝርው ኋይል ሳይሆን እውነተኛ
67
አምላክ ነው። ምሉዕ በኩሉሄ ነው፤ በጊዜና በሥፍራ አይወሰንም፤ በዓለም ሁሉ ምሉዕ
68 69
ነው። ክቡር ዳዊትም በሁሉ ሥፍራ መገኘቱን እያደነቀ ይዘምራል። እማሬ ኩሉ ነው፤
በዕውቀት ይህ ይቀረዋል አይባልም። በዚህ መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ፣ “መንፈስም
70
የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳ ሳይቀር ይመረምራል“ ሲል ጽፏል። ሁሉን ማድረግ
ይችላል፤ የሚሳነው ከቶ የለም። በአብና በወልድ ያለ የአምላክነት ክብር ለመንፈስ ቅዱስም
የባሕርይ ገንዘቡ ነው።

71
ንጉሥ ዳዊት፣ “በእግዚአብሔር ቃል ሰማያት ተሠሩ፤ በአፉም እስትንፋስ
72 73
የከዋክብት ሰራዊት“ ባለው መሠረት (ከአብና ከወልድ ጋር) ፈጣሬ ኩሉ መሆኑን፤ ከሥነ
ፍጥረት አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ እንዳልተፈጠረ እናምናለን፤ እናስተምራለን። ስለዚህ ወልደ
ባርክኤል፣ ታናሹ ኤሊሁ፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጥሮኛል፤ ሁሉን የሚችለውም
74
አምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጥቶኛል“ ይላል። አብ የሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ወልድ የሁሉ
ፈጣሪ ነው፤ መንፈስ ቅዱስም የሁሉ ፈጣሪ ነው። ዳግመኛም አብ ከወልድና ከመንፈስ
ቅዱስ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፤ ወልድም ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ የኖረበት
ዘመን የለም፤ መንፈስ ቅዱስም ከአብና ከወልድ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም።

በቀኖናዊ መጽሐፍት መሠረት፣ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት፣ በመንፈስ ቅዱስ


አጋዥነት ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እናምናለን። ወልድ ከአብ መወለዱ
በቅድምና፣ በመለኮት፣ በማዕረግም ከአብ አያሳንሰውም። መንፈስ ቅዱስ የአብና የወልድ
መንፈስ እንደሆነ እናምናለን። መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ መሥረጹ በቅድምና፣
በመለኮት፣ በማዕረግም ከአብና ከወልድ አያሳንሰውም። አብ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ
ተለይቶ ኖሮ ኖሮ ወልድን የወለደ፣ መንፈስ ቅዱስን ያሠረጸ አይደለም። አብ፣ ወልድ፣
መንፈስ ቅዱስ በመለኮት አንድነት ጥንት ሳይኖራቸው በዘመናት ሁሉ የነበሩ፣ ፍጻሜ

67
በሁሉ ቦታ የሚገኝ
68
መዝ 139፡6-10
69
ሁሉን ዐዋቂ (Omniscient)
70
1ቆሮ 2፡10
71
የአፉ እስትንፋስ፣ የባሕርይ መንፈሱ ነው። መንፈስ ለሚለው ቃል የዕብራይስጥ አቻ ሩአህ፣
እስትንፋስ ወይም ንፋስ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
72
መዝ 33፡6
73
የሁሉ ፈጣሪ
74
ኢዮ 33፡4
23
ሳይኖራቸው የሚኖሩ ናቸው። ከመካከላቸው ወደ ኋላ የሚቀር የለም፤ ቀድምናቸውም
አንዲትና እኩል ናት። በማዕረግ አይበላለጡም፤ በዘመን አይቀዳደሙም። ማዕረጋቸውና
ቅድምናቸው አንድ ነው። ዳግመኛም ወልድ ከአብ በመወለዱ፣ መንፈስ ቅዱስ ከአብና
ከወልድ በመሥረጹ የሦስቱ መለኮት አንድ ይሆናል። የምናምንበት ሃይማኖታችን ይህ
ነው።

24
አንቀጽ ሁለት፡ ሦስት አካላት

“የአብ አካል ለብቻው፣ የወልድ አካል ለብቻው፣ የመንፈስ ቅዱስም አካል


75
ለብቻው ነው” ይላል ቅዱስ አትናቴዎስ። ግልጥ ነው? ጥያቄ የለውም ለተማረ ሰው
ግልጥ ነው፤ እኛ ግን ለማያስተውሉም ዕዳ አለብን። ለመሆኑ “አካል“ ማለት ምን ማለት
ነው? በትምህርተ ሥላሴ “አካል“ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ረቂቅ አካል እንጂ ቁስ
አካል አይደለም። በትምህርተ ሥላሴ “አካል“ የሚታይና የሚጨበጥ ማንነት ሳይሆን፣
76
ራሱን የቻለ ስብእና ያለው፣ እኔ የሚል፣ እገሌ የሚባል ማለት ነው። አብ ከወልድና
ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ እኔነት አለው፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ እኔነት
አለው፤ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ የተለየ እኔነት አለው። በተቃራኒ ሲነገር፦ አብ ወልድ
ወይ መንፈስ ቅዱስ አይደለም፤ ወልድ አብ ወይ መንፈስ ቅዱስ አይደለም፤ መንፈስ
ቅዱስም አብ ወይ ወልድ አይደለም።

77
“አንድ አካል፤ ሦስት ስም“ የሚሉ ሁሉ በቅዱሳት መጽሐፍት የሌለውን
ከልቡናቸው አንቅተው ይናገራሉ። እኒህ ከእምነታችን የተለዩ፣ ከጉባኤያችን የተወገዙ
ናቸው። ጸያፍ ትምህርታቸውም በእኛ ዘንድ የተጠላ ነው። ከእምነታችን ለውግዘት በተገባ
አንደበት እንዲህ ብሎ ለሚናገር ወዮለት! በዚህ አንቀጽ እግዚአብሔር በሰጠን ችሎታ
መጠን በቀኖናዊ መጽሐፍት መሠረት፣ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት፣ በመንፈስ ቅዱስ
አጋዥነት ይህን የምናስረዳ ይሆናል።

75
የአትናቴዎስ የእምነት ቀኖና
76
Philip Schaff, History of the Christian Church, Volume 3, section 142: “Person is
the Ego, the self-conscious, self-asserting, and acting subject.”
77
የጥንት ሰባልዮሳውያንንና በዘመናችን ያሉ ራሳቸውን ”ኢየሱስ ብቻ” ብለው የሚጠሩ መናፍቃንን
ያካትታል።
25
ወልድ በተለየ አካሉ በግብር ተወላዲ፣ በስም ልጅ ይባላል

አስቀድመን እንዳየነው፦ ወልድ ከአብ መወለዱ በቅድምና፣ በመለኮት፣


በማዕረግም ከአብ አያሳንሰውም፤ በተቃራኒው በረቂቅ ልደቱ አብን አክሎና መስሎ
በመገኘቱ በሕልውና፣ በባሕርይ፣ በመለኮት ከአብ ጋር አንድ ነው። ሆኖም በውስጣዊ
ግብር፣ በስም፣ በአካል ከአብ ይለያል። ግልጥ ነው? ጥያቄ የለውም ለተማረ ሰው ግልጥ
ነው፤ እኛ ግን ለማያስተውሉም ዕዳ አለብን።

ወልድ በውስጣዊ ግብር ከአብ ይለያል ማለት ምን ማለት ነው? ሥላሴ ውስጥ፣
አንዱ አካል ከሌላው አካል ጋር ያለው ግንኙነት ውስጣዊ (አካላዊ) ግብር ይባላል። አብ
በአካላዊ ግብር ወላዲ ነው፤ ወልድ ደግሞ ተወላዲ። አብ ቢወልድ እንጂ አይወለድም፤
ወልድ ቢወለድ እንጂ አይወልድም። አብ አምላክ ነው፤ ከአምላክ ግን አይደለም። ወልድ
አምላክ ነው፤ ከአምላክም ነው። አብ በባሕርዩ ከማንም አይደለም፤ አባትነቱ ግን ለወልድ
ነው። ወልድ በባሕርዩ ከአብ፣ ልጅነቱም ለአብ ነው። በዚህ መሠረት ቅዱስ አትናቴዎስ፣
”የዘለዓለማዊ ብርሃን ዘለዓለማዊ ነፀብራቅ፤ የዘለዓለማዊ አባት ዘለዓለማዊ ልጅ” ይለዋል።
78
በአወላለድ ሥራ የወለደ አብና ያልወለደ ወልድ፣ የተወለደ ወልድና ያልተወለደ አብ፣
አንዱ ከአንዱ ይለያሉ።

ወልድ በስም ከአብ ይለያል ማለት ምን ማለት ነው? ስም ግብርን ወደ መረዳት


ያደርሰናል። አብን አብ ያሰኘው የወላዲነቱ ግብር ነው። ወልድን ወልድ ያሰኘው
የተወላዲነቱ ግብር ነው። አብን አብ ያሰኘው ከወልድ ጋር ያለው ግንኙነት ነው። ወልድን
ወልድ ያሰኘው ከአብ ጋር ያለው ግንኙነት ነው። አባት እባል ዘንድ ልጅ ሊኖረኝ ይገባል።
ልጅም እባል ዘንድ ወላጅ ሊኖረኝ ይገባል። አባት መሆን የምችለው ልጅ ሲኖረኝ ብቻ ነው፤
ልጅም መሆን የምችለው ወላጅ ሲኖረኝ ብቻ ነው። ወልድ ልጅ የለውምና አባት
አይባልም። አብ አባት የለውምና ልጅ አይባልም። ወልድ በሚለው ስያሜ አብ
አይጠራበትም። አብ በሚለው ስያሜ ወልድ አይጠራበትም።

78
Athanasius, Four Discourses Against The Arians, Discourse 1, chap. 4: “Eternal
Radiance of a Light which is eternal.” Chap. 5: “The etenal offspring of the
eternal Father.”
26
ወልድ በአካል ከአብ ይለያል ማለት ምን ማለት ነው? አብ ወላዲ እንጂ ተወላዲ
ካልሆነ፣ ወልድም ተወላዲ እንጂ ወላዲ ካልሆነ አብ ወልድ፣ ወልድም አብ አይደለም።
በግብርና በስም አለመወራረሳቸው አካላቱ በያሉበት፣ አንዱ አካል ወደ ሌላው አካል
ሳይፈልስ ጸንቶ መኖሩን ያስረዳናል። አብ በተለየ አካሉ በግብር ወላዲ፣ በስም አባት
ይባላል። ወልድ በተለየ አካሉ በግብር ተወላዲ፣ በስም ልጅ ይባላል። ወልድ በባሕርይ ልደቱ
ከአብ ስለሚገኝ ከአብ ጋር አንድ ነው፤ ነገር ግን ወልድ አብ አይደለም። በሕልውና፣
በባሕርይና በመለኮት ከአብ ጋር አንድ ቢሆንም በግብር፣ በስምና በአካል ከአብ ይለያል።
አብ ወላዲ ነው፤ ወልድ አይወልድም። አብ ልጅ አይባልም፤ ወልድ አባት አይባልም። አብ
79
ወልድ አይደለም፤ ወልድም አብ አይደለም።

አንዳንዶች ክርስቶስ፣ “እኔና አብ አንድ ነን” እንዳለ በማመልከት፣ “እነሆ፤ ወልድ


80
ራሱ አብ እንደሆነ እየተናገረ ነው፤ ክርክራችሁን አቁሙ፤ ወልድ ”አብ ነኝ” እያለ ነው። ”
ይላሉ። በእርግጥ “አንድ ነን“ ማለት እኔ አብ ነኝ ማለት ነውን? በጭራሽ! ማሰሪያ አንቀጹን
በጥንቃቄ ተመልከቱ! ወልድ፣ “እኔና አብ አንድ ነን” አለ እንጂ፣ በመጀመሪያ አካል ነጠላ
አመልካች፣ “እኔና አብ አንድ ነኝ” አላለም። “ነን“ የሚለው ቃል በራሱ የብዝህና አመልካች
አንቀጽ እንደ ሆነ ለመረዳት የሰዋሰው ሊቅ መሆን አይጠበቅብንም። መናፍቃኑ አብና
ወልድ በአካል አንድ እንደሆኑ ለማረጋገጥ የሚጠቅሷቸው ጥቅሶች ሳይቀሩ የአካላቱን
ሁለትነት ያስተምራሉ። “ሥላሴ አንድ አካል ነው“ የሚሉ የርጉም ሰባልየስ ልጆች ይፈሩ፤
ይዋረዱ። ወልድ፣ “እኔና አብ አንድ ነን” ሲል በሕልውና፣ በባሕርይና በመለኮት ከአብ ጋር
81
አንድ እንደ ሆነ፣ በግብር፣ በስምና በአካል ከአብ እንደሚለይ ያስተምራል። እርሱ ተወላዲ
ነው፤ አብ ወላዲ ነው፤ እርሱ ወልድ ይባላል፤ አባቱን “አብ“ ይላል። የአብ አካል ለብቻው፤
የወልድ አካል ለብቻው ነው። በእውነት የተነገረውን አጣሞ መተርጎም የመናፍቃን
ልማዳቸው ነው። የተጻፈውን ፍቀው፣ የሌለውን ይጨምራሉ።

ፊልጶስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አብን አሳየንና ይበቃናል” አለው። ኢየሱስም እንዲህ


አለው፤ “አንተ ፊልጶስ! ይህን ያህል ጊዜ ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን

79
“He is not the Father who is the Son, nor is the Son He who is the Father, nor is
the Holy Spirit He who is the Father or the Son.” Council of Toledo 11
80
ዮሐ 10፡30
81
St. Cyril, Comment on John, Book 1, Chap 2
St. Cyril of Jerusalem, The Catechetical Lectures; Lecture
27
82
አይቷል፤ እንዴትስ “አብን አሳየን” ትላለህ?“ ይህን ምንባብ በመጥቀስ፣ “ወልድ ከአብ
የተለየ አካል ያለው ስለመሰለው ጌታችን ፊልጶስን ሲገሥጽ ተመልከቱ! ከክርስቶስ የተለየ፣
“አብ“ የሚባል ሌላ አካል የለም፤ ወልድ ራሱ አብ ነው፤ ስለዚህ እርሱን ያየ አብን አይቷል”
ይላሉ። ከግንዱ የተለየ ቅርንጫፍ ሕያውነቱን እንደሚያጣ፣ ከምንባቡ የተነጠለ ጥቅስ
ለዛውን ያጣል። ስለዚህ ጥቅሶች ከምንባባቸው ጋር ተገናዝበው መተርጎም አለባቸው።
በተጠቀሰው ምንባብ ጌታ ኢየሱስ፣ ”እኔን ያየ አብን አይቷል፤ እንዴትስ “አብን አሳየን”
ትላለህ?” ያለበትን ምክንያት ሲያብራራ፣ “እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ
ስነግራችሁ እመኑኝ፤ ሌላው ቢቀር ስለ ድንቅ ሥራዎቹ እንኳ እመኑ“ ይላቸዋል። ”እኔን ያየ
አብን አይቷል” ያላቸው፣ እርሱ በአብ፣ አብም በእርሱ ስለሚኖር (ማለትም አንድ ሕልውና
ስላላቸው) እንጂ እርሱ አብ ስለ ሆነ አይደለም። በባሕርይ ውልደቱ ወልድ አብን መስሎና
83
አክሎ በመወለዱ፣ ”የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅ፣ የአካሉ ትክክለኛ ምሳሌ፣
84
የማይታየው አምላክ አምሳል” ይባላል። በባሕርይ ልደቱ አብ በወልድ፣ ወልድ በአብ
85
ይኖራል።

አብ በወላዲነቱ የእርሱ የሆነውን ሁሉ ለወልድ ሰጥቶታል፤ ወልድም


86
በተወላዲነቱ የእርሱ የሆነውን ሁሉ ከአብ ተቀብሏል። የአብ ሕልውና፣ ባሕርይና መለኮት
87
የወልድ ነው፤ ነገር ከአብ የተለየ የራሱ ግብር፣ ስምና አካል አለው። በኦሪት ዘልደት ፣
”ሰውን በመልካችን፣ በአምሳላችን እንስራ… ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ
ፈጠረው” የሚለውን ቃል አስታውሱ! ሕብረ መልካቸው አንድ ባይሆን እንዴት መልካችን

82
ዮሐ 14፡ 9-11
83
(Hupostaseoos)
84
ቆላ 1፡15 ዕብ 1፡3
85
St Hilary of Poitiers, De Trinitate, Book 3: “The One is from the Other, and they
Two are a Unity; not Two made One, yet One in the Other, for that which is in
Both is the same. The Father is in the Son, for the Son is from Him; the Son is in
the Father, because the Father is His sole Origin; the Only-begotten is in the
Unbegotten, because He is the Only-begotten from the Unbegotten. Thus
mutually Each is in the Other, for as all is perfect in the Unbegotten Father, so
all is perfect in the Only-begotten Son.”
86
“… The Father has through generation given to the only-begotten son everything
that belongs to the Father, except being Father… Because of that unity the
Father is wholly in the Son and wholly in the Holy Spirit; the Son is wholly in
the Father and wholly in the Holy Spirit; the Holy Spirit is wholly in the Father
and wholly in the Son.” Council of Florence
87
ኦሪት ዘፍጥረት
28
ይላል? ደግሞስ አካላቱ ነጠላ ቢሆኑ እንዴት መልካችን ይል ነበር? ነጠላ አካል ቢሆን በነጠላ
ማሠርያ አንቀጽ ”መልኬ” ባለ ነበር። ሦስቱ የሥላሴ አካላት በመልክ ማለትም በሕልውና፣
በባሕርይና በመለኮት አንድ በመሆናቸው አንዱን ያየ ሌላውን አይቷል።

የማይታየውን አምላክ ማየት ትሻለህ? ክርስቶስን ተመልከት! በእርሱ የመለኮት


88
ምልዓት በሥጋ ተገልጧል ፤ የማይታየው አምላክ ትክክለኛ ምሳሌ ነው። በምሳሌነት
ከሚመስለው የሚያስን አይደለም፤ ነገር ግን መጽሐፍ እንደሚለው፣ ”ትክክለኛ ምሳሌ”
ነው። የአብ መለኮታዊ ባሕርይ አንዳች ሳይጓደል በእርሱ አለ። ባአባቱና በርሱ መካከል
ምንም የሚለይ የለም። የአብ ሁለንተና በወልድ ይታወቃል። ስለዚህም ወልድ፣ ”እኔን ያየ
አብን አይቷል” ይላል። እርሱ ሰብዓዊ ባሕሪን ስለ ያዘ ልናየው ቻልን እንጂ በባሕርየ
መለኮቱ እንደ አብ፣ እንደ መንፈስ ቅዱስ የማይታይ ነው። ቃል ሥጋ ባይሆን፣ በዓይነ
ልቡናችን ብቻ የምናየውን አምላክ እንዴት በዓይነ ሥጋችን እናየው ነበር? በቀድሞ ዘመን
አምላክ በነቢያቱ አድሮ ይናገር ነበር፤ በዘመነ ሐዋርያት ግን እርሱ ራሱ መጥቶ፣ አፉን
89
ከፍቶ ተናገረ። አምላክ በሥጋ ተገለጠ።

90
የዕብራውያን መልዕክት ወልድን፣ “የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የአካሉ
ትክክለኛ ምሳሌ” ይለዋል። ወልድን የአብ አካል ትክክለኛ ምሳሌ በማለት፣ የአብን አካልና
የአካሉ ትክክለኛ ምሳሌ፣ ወልድን፣ ለያይቶ ያስቀምጣል። ይህም የአብ አካል ለብቻው፤
91
የወልድም አካል ለብቻው እንደ ሆነ ያስተምራል። በዚያው ምንባብ አብ ዓለማትን በልጁ
92
እንደፈጠረ እንማራለን። የሰዋሰው ድንቁርና ካልተጸናወተን በቀር በእነዚህ ቃላት የአብ
አካል ለብቻው፣ የወልድ አካል ለብቻው እንደሆነ እንረዳለን። አብ ራሱ ወልድ፣ ወልድም
ራሱ አብ ቢሆን፣ እንዴት አብ ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ተናገረን ይባላል? አብ በወልድ
ፈጠረ መባሉ አብ ከወልድ የተለየ አካል እንዳለው ያመለክታል።

ሊቀ ሐዋርያት፣ ቅዱስ ጳውሎስ፣ ክርስቶስ በባሕርየ መለኮቱ ከአብ ጋር እኩል


93
እንደ ሆነ ያስተምራል። ይህ በራሱ ወልድ ከአብ የተለየ አካል እንዳለው ያስተምራል። ወደ
ንጽጽር የሚገቡ የተለያዩ አካላት መሆን አለባቸው። ስለዚህ፣ ወልድ ከአብ ጋር እኩል እንደ

88
ቆላ 2፡8-10
89
1ጢሞ 3፡16
90
Hupostaseoos
91
John Calvin, The Institutes of the Christian Religion, Book 1 Chap 13
92
ዕብ 1፡1-3
93
ፊል 2፡6
29
ሆነ የሚያሳዩ ምንባቦች ሁሉ፣ ከአብ የተለየ አካል እንዳለው ያስተምራሉ። ቅዱስ ዮሐንስ፣
“በመጀመሪያ ቃል ነበር፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበር“
በማለት ወልድ ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር ጋር የነበረ እግዚአብሔር እንደ ሆነ
ያስተምራል። Nuda verba- ቃሉ ግልጥ ነው፤ ይህን ለማብራራት መሞከር ወደ ፀሐይ
ባትሪ እንደ ማብራት ነው። በሚያበሩ ቃላት ወልድ በመለኮት ከአብ ጋር አንድ፣ በአካል
ከአብ የተለየ እንደሆነ ያስተምራል። ራሱ እግዚአብሔር የሆነ ቃል እግዚአብሔር ከሆነ አብ
ጋር ነበር ማለት ቃል ከአብ የተለየ አካል ነበረው ከማለት ውጪ ምን ማለት ሊሆን ይችላል?

እውነተኛው የክርስትና እምነት ሙሉ የሚሆነው በሦስቱም አካላት (በአብ፣


በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም) ስናምን ነው። ከአካላቱ ውስጥ አንዱን ብንክድ ሁሉንም
እናጣለን፤ በሦስቱ አካላት አምነህ አንዱን ከሌላው ብታሳንስ ሙሉ እምነትህን ከንቱ
ታደርጋለህ። ነገር ግን በሦስትነቱ አንድነቱን፣ በአንድነቱ ሦስትነቱን አምነህ አንዱን አካል
94
ብትጠራ እምነትህ ሕጸጽ የለበትም። ፀሐይ ባልን ጊዜ ያለ ብርሃኗና ያለ ሙቀቷ ከቶ
95
ልናስበው አንችልም። አብ ስንልም ያለ ወልድና ያለ መንፈስ ቅዱስ አይሆንም። አዎ!
ሦስትነታቸው የማይነጣጠል ሦስትነት ነው።

“አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር


የቅንነት በትር ናት። ጽድቅን ወደድህ፤ አመጻን ጠላህ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር አምላክህ፣
96
ከጓደኞችህ ይልቅ አንተን የደስታ ዘይት ቀባህ።” ይህን ታላቅ መሢሃዊ ዝማሬ በአትኩሮት
ተመልከቱ! የቆሬ ልጆች ሁለተኛ አካል ነጠላ ማሠሪያ አንቀጽ በመጠቀም ወልድን
ያወድሳሉ። ስለ አብ ደግሞ በሦስተኛ አካል ነጠላ ማሠሪያ አንቀጽ ያወራሉ። ይህም የአብ
አካል ለብቻው የወልድ አካል ለብቻው እንደ ሆነ ያስተምራል። የእግዚአብሔር እንደ ልቤ፣

94
St. Ambrose, On The Holy Spirit, ll. 2
በዚህ መሠረት ሐዋርያቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ቢያጠምቁ ከሥላሴ እምነት ጋር የሚጻረር
አንዳች ነገር የለውም።
95
Tertullian, Against Praxeas, Chap 18: “Suppose the Sun to say, “I am the sun, and
there is none other besides me, except my ray.” Would you not have remarked
how useless was such a statement, as if the ray were not itself reckoned in the
Son?”
96
መዝ 45፡6-7
30
ክቡር ዳዊት፣ “ጌታዬ ጌታዬን… አለው“ በማለት አብ ከወልድ የተለየ ስብእና እንዳለው
97
ያመለክታል።

መንፈስ ቅዱስ በተለየ አካሉ በግብር ሠራጺ፣ በስም


መንፈስ ቅዱስ ይባላል።

አስቀድመን እንዳየነው፦ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ መሥረጹ በቅድምና፣


በመለኮት፣ በማዕረግም ከአብና ከወልድ አያሳንሰውም፤ በተቃራኒው በረቂቅ ሥርጸቱ
አብና ወልድን አክሎና መስሎ በመገኘቱ በሕልውና፣ በባሕርይ፣ በመለኮት ከአብና ከወልድ
ጋር አንድ ነው። ሆኖም በውስጣዊ ግብር፣ በስም፣ በአካል ከአብና ከወልድ ይለያል።

መንፈስ ቅዱስ በውስጣዊ (አካላዊ) ግብር ከአብና ከወልድ ይለያል ማለት ምን


ማለት ነው? በአካላዊ ግብር አብና ወልድ (እንደ ኦርቶዶክሳውያን፦ አብ ብቻ) አሥራጺ
ናቸው፤ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ሠራጺ። አብና ወልድ ቢያሠርጹ እንጂ አይሠርጹም፤ መንፈስ
98
ቅዱስ ቢሠርጽ እንጂ አያሠርጽም (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት)። አብ ከማንም

97
መዝ 110፡1
98
ፈሉካዊ ንትርክ (The Filioque controversy) የታላቁ ክፍፍል መንስኤ ነው።
Catechism of the Catholic Church, Part 1, sect. 1, Chap. 1: “The affirmation of the
flioque does not appear in the Creed confessed in 381 at Constantinople. But
Pope St. Leo I, following an ancient Latin and Alexandrian tradition, had already
confessed it dogmatically even before Rome, in 451 at the Council of
Chalcedon, came to recognize and receive the Symbol of 381. The use of this
formula in the Creed was gradually admitted into the Latin liturgy (between the
eighth and eleventh centuries). The introduction of the filioque into the
NicenoConstantinopolitan Creed by the Latin liturgy constitutes moreover,
even today, a point of disagreement with the Orthodox Churches. At the
outset the Eastern tradition expresses the Father's character as first origin of
the Spirit. By confessing the Spirit as he "who proceeds from the Father," it
affirms that he comes from the Father through the Son. The Western tradition
expresses first the consubstantial communion between Father and Son, by
31
የማይገኝ፣ ወላዲና አሥራጺ ነው፤ ወልድ ተወላዲና አሥራጺ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ሠራጺ
99
ነው። የአብ ልዩ ግብር ወላዲነት ነው፤ የወልድ ልዩ ግብር ተወላዲነት ነው፤ የመንፈስ
ቅዱስ ብቸኛ ግብር ሠራጺነት ነው።

መንፈስ ቅዱስ በስም ከአብና ከወልድ ይለያል ማለት ምን ማለት ነው? የአካላቱ
ስም ወደ አካላቱ ግብር ይመራሉ። አሥራጺነት የአብና የወልድ የጋራ ግብር ነው። የአብ ልዩ
ግብር ወላዲነት ነው፤ የወልድ ልዩ ግብር ተወላዲነት ነው፤ የመንፈስ ቅዱስ ብቸኛ ግብር
ሠራጺነት ነው። በዚህ መሠረት አብ ወላዲ፣ ወልድ ተወላዲ፣ መንፈሰ ቅዱስ ሠራጺ
ይባላል።

መንፈስ ቅዱስ በአካል ከአብና ከወልድ ይለያል ማለት ምን ማለት ነው? አብ


ወላዲና አሥራጺ እንጂ ሠራጺ ካልሆነ፣ ወልድ ተወላዲና አሥራጺ እንጂ ሠራጺ ካልሆነ፣
መንፈስ ቅዱስም ሠራጺ እንጂ ወላዲ ወይ ተወላዲ ወይ አሥራጺ ካልሆነ፣ መንፈስ ቅዱስ
አብ ወይም ወልድ አይደለም። በግብርና በስም አለመወራረሳቸው አካላቱ በያሉበት፣ አንዱ
አካል ወደ ሌላው አካል ሳይፈልስ ጸንቶ መኖሩን ያስረዳናል።

100
የጌታን ቃል አስቡ! “እኔ አብን እለምናለሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር ለዘለዓለም
የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም የእውነት መንፈስ ነው።“ ይህ አስተዋይ ልብ፣
ትሁትም መንፈስ ላለው የአብ አካል ለብቻው፣ የወልድ አካል ለብቻው፣ የመንፈስ

saying that the Spirit proceeds from the Father and the Son ilioque). It says
this, "legitimately and with good reason," for the eteral order of the divine
persons in their consubstantial communion implies that the Father, as "the
principle without principle," is the first origin of the Spirit, but also that as
Father of the only Son, he is the Son, the single principle from which the Holy
Spirit proceeds. With This legitimate complementarity, provided it does not
become rigid, does not affect the identity of faith in the reality of the same
mystery confessed.”
99
Thomas Aquines, Summa Theologiae, Part 1, Question 32: “There are Five notions
in God: "innascibility," "paternity," "filiation," and "procession." Of these only
four are relations, for "innascibility" is not a relation, except by reduction. Four
only are properties. For "common spiration" is not a property; because it
belongs to two persons. Three are personal notions---i.e. constituting persons,
"paternity," "filiation," and "procession." "Common spiration" and "innascibility"
are called notions of Persons, but not personal notions
100
ዮሐ 14፡16-17
32
ቅዱስም አካል ለብቻው እንደ ሆነ ያስተምራል። ወልድ መንፈስ ቅዱስን “ሌላ” በማለቱ
የአካላቱን መለየት አስረድቷል። ወልድ “አብ… ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል” ባለው መሠረት
አብ የመንፈስ ቅዱስ አሥራጺና ለአኪ እንጂ ራሱ መንፈስ ቅዱስ እንዳልሆነ እንገነዘባለን።
101
በዚያው ምንባብ ወልድ ቃሉን ወደተቀበሉት ከአብ ጋር እንደሚመጣ ያስተምራል።
“ወደ እርሱ እንመጣለን“ የሚለውን የመጀመሪያ አካል ድርብ አንቀጽ ልብ በሉ!
እንመጣለን የሚለው ቃል አብና ወልድ ነጠላ አካል እንዳልሆኑ ያረጋግጥልናል።

የዚህ አንቀጽ እጣሬ እንደሚከተለው ይሰበሰባል፦

ሥላሴ በውስጣዊ (በአካላዊ) ግብር ሦስት ናቸው። አብ ወላዲ፣ ወልድ


102
ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ ነው። አብ ቢወልድ እንጂ አይወለድም፤ አይሠርፅም።
ወልድ ቢወለድ እንጂ አይወልድም፤ አይሠርፅም። መንፈስ ቅዱስ ቢሠርፅ እንጂ
አይወልድም፤ አይወለድም። ስለዚህ ወላዲ የሚሆነው አንድ እንጂ ሦስት አይደሉም፤
ተወላዲ የሚሆነው አንድ እንጂ ሦስት አይደሉም፤ ሠራፂ የሚሆነው አንድ እንጂ ሦስት
አይደሉም። አንድ ወላዲ አብ፣ አንድ ተወላዲ ወልድ፣ አንድ ሠራጺ መንፈስ ቅዱስ።

አብ አይወለድም፤ አይሠርጽም። ወልድ ከአብ ይወለዳል። መንፈስ ቅዱስ ከአብና


103
ከወልድ ይሠርጻል። በባሕርዩ አስገኝ የለውምና አብ የሥላሴ መገኛ መሠረት ፣ የሥላሴ
104
የመጀመሪያው አካል … ይባላል። ወልድና መንፈስ ቅዱስም በቅደም ተከተል የሥላሴ
105
ሁለተኛና ሦስተኛ አካል ይባላሉ። ይህ ማለት በአካላቱ መካከል መቀዳደም አለ ማለት
106
እንዳልሆነ በቀደመው አንቀጽ ተምረናል። አብ ቢያስገኝ እንጂ ከማንም አይገኝም። አባት

101
ዮሐ 14፡23
102
“It is the Father who generates, the Son who is begotten, the Holy Spirit who
proceeds.” Lateran Council 4
103
Origen, De Principiis, Book 1, Chap 2
St. Augustine, De Trinitate, Book 4, Chap. 20
104
The first person of Trinity
105
Tertullian, Against Praxeas, Chap 13: “As Christ came, and was recognised by us
as the very Being who had from the beginning caused plurality (in the Divine
Economy), being the second from the Father, and with the Spirit the third…”
106
Catechism Of The Council Of Trent For Parish Priests, Part 1: “When we say that
the Father is the first person, we are not to be understood to mean that in the
Trinity there is anything first or last, great or less… But since the Father is the
beginning without beginning we truly and unhesitatingly affirm that He is the
first person.
33
107
የሌለው አባት፣ አስገኚ የሌለው አስገኚ ነው። ወልድ ቢወለድ እንጂ አይወልድም፤
አይሠርፅም። መንፈስ ቅዱስ ቢሠርፅ እንጂ አይወልድም፤ አይወለድም። የሦስቱ አካላት
108
ግብር ከአንዱ ወደ ሌላው አይተላለፍም።

ሥላሴ በአካላዊ ስም ሦስት ናቸው። የአካላቱ ስም ወደ አካላቱ ግብር


ይመራሉ። አብን አብ ያሰኘው የወላዲነቱ ግብር ነው። ወልድን ወልድ ያሰኘው የተወላዲነቱ
ግብር ነው። መንፈስ ቅዱስን መንፈስ ቅዱስ ያሰኘው የሠራፂነቱ ግብር ነው። አብን አብ
109
ያሰኘው ከወልድ ጋር ያለው ግንኙነት ነው። ወልድን ወልድ ያሰኘው ከአብ ጋር ያለው
ግንኙነት ነው። መንፈስ ቅዱስን መንፈስ ቅዱስ ያሰኘው ከአብ እና ከወልድ ጋር ያለው
ግንኙነት ነው። ወላዲው አብ፣ ተወላዲው ወልድ፣ ሠራጺው መንፈስ ቅዱስ ይባላል። የአብ
ስም ተለውጦ ወልድ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባልም። የወልድ ስም ተለውጦ አብ ወይም
መንፈስ ቅዱስ አይባልም። የመንፈስ ቅዱስ ስም ተለውጦ አብ ወይም ወልድ አይባልም።
ይህም ስማቸው አይፋለስም፣ አይለወጥም በየስማቸው ጸንተው ሲመስገኑ ይኖራሉ
እንጂ። አብ አብ ነው እንጂ ወልድ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይደለም፤ ወልድ ወልድ ነው
እንጂ አብ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ
አብ ወይም ወልድ አይደለም። በሦስትነት ስማቸው አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ
የተባሉትም በአንድነት ስማቸው አንድ እግዚአብሔር ይባላሉ።

ሥላሴ በአካል ሦስት ናቸው። አብ ወላዲ እንጂ ተወላዲ ካልሆነ፣ ወልድም


ተወላዲ እንጂ ወላዲ ካልሆነ አብ ወልድ፣ ወልድም አብ አይደለም። በግብርና በስም
አለመወራረሳቸው የሥላሴ አካላት በያሉበት፣ አንዱ አካል ወደ ሌላው አካል ሳይፈልስ ጸንቶ

107
Origen, De Principiis, Book 1: “Unbegotten God is made Father of the only
Begotten Son.”
The unbegotten Father, “The Principle without principle” Council of Florence, “The
source and origin of the whole divinity.” Council of Toledo 6
108
The 4th Lateran Council: “The Father is from none, the Son from the Father
alone, and the holy Spirit from both equally, eternally without beginning or
end; the Father generating, the Son being born, and the holy Spirit proceeding;
consubstantial and co-equal, co-omnipotent and co-eternal.”
109
Gregory Nazianzen (The Theologian), Orations, Oration 29: “The very fact of
being unbegotten or begotten, or proceeding has given the name of the
Father to the first, of the Son to the second, and of the Holy Spirit to the third.”
34
110
መኖሩን ያስረዳናል። አብ በተለየ አካሉ በግብር ወላዲ፣ በስም አባት ይባላል። ወልድ
በተለየ አካሉ በግብር ተወላዲ፣ በስም ልጅ ይባላል። መንፈስ ቅዱስ በተለየ አካሉ በግብር
ሠራጺ፣ በስም መንፈስ ቅዱስ ይባላል። አብ በተለየ አካሉ አንድ እንደሆነ እናውቃለን፤
ወልድ በተለየ አካሉ አንድ እንደሆነ እናውቃለን፤ መንፈስ ቅዱስ በተለየ አካሉ አንድ
እንደሆነ እናውቃለን። እሊህ ሦስቱ አካላት ፈጣሪ እንጂ ፍጡራን አይደሉም። ለአብ
የአባትነት ስም፣ የአባትነት ክብር አለው፤ ለወልድ የልጅነት ስም፣ የልጅነት ክብር አለው፤
ለመንፈስ ቅዱስም የሠራጺነት ስም፣ የሠራጺነት ክብር አለው። አብ ወልድን ወይም
መንፈስ ቅዱስን ለመሆን አይለወጥም፤ ወልድም አብን ወይም መንፈስ ቅዱስን ለመሆን
አይለወጥም፤ መንፈስ ቅዱስም አብን ወይም ወልድን ለመሆን አይለወጥም። ሆኖም
በባሕርይ ክብር፣ በሥልጣን፣ በፍቃድ አንድ ናቸው።

ስለምን እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዙ ምስክሮችን በመጥቀስ እንደክማለን? አብ


ራሱን “እኔ“ ይላል፤ በዚህ የራሱ ስብእና ወይም አካል እንዳለው እናያለን። በወልድና
በመንፈስ ቅዱስ፣ “አንተ“ እና “እርሱ“ ይባላል፤ በዚህም ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ
ስብእና ወይም አካል እንዳለው እናያለን። ወልድ ራሱን “እኔ“ ይላል፤ በዚህ የራሱ ስብእና
ወይም አካል እንዳለው እናያለን። በአብና በመንፈስ ቅዱስ፣ “አንተ“ እና “እርሱ“ ይባላል፤
በዚህም ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ ስብእና ወይም አካል እንዳለው እናያለን። መንፈስ
ቅዱስ ራሱን “እኔ“ ይላል፤ በዚህ የራሱ ስብእና ወይም አካል እንዳለው እናያለን። በአብና
በወልድ፣ “አንተ“ እና “እርሱ“ ይባላል፤ በዚህም ከአብና ከወልድ የተለየ ስብእና ወይም
111
አካል እንዳለው እናያለን። የሥላሴ ገጻት በየአካላቸው ሦስት ሲሆኑ በመለኮት አንድነት
ጸንተው ይኖራሉ።

የአካላቱ ስም ወደ አካላቱ ግብር ይመራሉ። በግብርና በስም አለመወራረሳቸው


የሥላሴ አካላት በያሉበት፣ አንዱ አካል ወደ ሌላው አካል ሳይፈልስ ጸንቶ መኖሩን (በሌላ
ቃላት አብ ወልድ እንዳልሆነ፣ መንፈስ ቅዱስም አብ ወይም ወልድ እንዳልሆነ) ያስረዳናል።

110
Catechism of the Council of Trent for Parish Priests, Part 1: “The Name Father
Also Discloses The Plurality Of Persons In God.”
111
በእርግጥ አንዳንዴ በዓላማ ራሳችንን በሦስተኛ አካል ነጠላ አንቀጽ ልናመለክት እንችላለን።
ለምሳሌ፦ ቅዱስ ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮ 12 ስለ ራሱ እንደ ሦስተኛ አካል ሲያወራ እንመለከታለን።
ጌታ ኢየሱስም ይህን ዓይነት አነጋገር ያዘወትር ነበር። ነገር ግን መቼም ቢሆን ስለ አብና ስለ
መንፈስ ቅዱስ በአንደኛ አካል ነጠላ አንቀጽ አውርቶ አያውቅም።
35
112
አብ የወልድ አባት ካልሆነ ታዲያ ለምን አባት ተባለ? ወልድስ ከአብ የተወለደ ካልሆነ
ታዲያ ለምን ልጅ ተባለ? ወላዲው አብ፣ ተወላዲው ወልድ ከተባለ፣ ወላዲው ከተወላዲው
የተለየ አካል ነው። ከሐዲያኑ፣ “ወልድ ራሱ አብ ነው፣ አብ ራሱ ወልድ ነው” በማለት፣ ከአብ
እውነተኛ አባትነትን፣ ከወልድ እውነተኛ ልጅነት ይቀማሉ። የአካላቱ ስም ወደ አካላቱ ግብር
113
የሚመሩ ቢሆኑም ስሁታኑ ከስሞቹ ትርጉማቸውን በመንሳት ደካሞችን ያታልላሉ። አብ
የሚለው ስም አብ የተባለው አካል ወላዲ መሆኑን ይገልጣል፤ ወልድ የሚለው ስም ወልድ
የተባለው አካል ተወላዲ መሆኑን ይገልጣል። ወላዲው ተወላዲ አይደለም፤ ተወላዲው
114
ወላዲ አይደለም። እንግዲህ፣ አብ ሲባል የሰማን ሁላችን፣ በከሐዲያኑ ሳንታለል፣
በእውነተኛ አባትነቱ፣ ወልድ ሲባል የሰማን ሁላችን፣ በከሐዲያኑ ሳንታለል፣ በእውነተኛ
ልጅነቱ እንመን።

ይህን ሙግት ሲሰሙ የዘመናችን ሰባሊዮሳውያን፣ “Only Jesus“፣ “በጣም ጥሩ!


አሁን ከቅዱሳት መጻሕፍት ባሳየኸኝ መሠረት፣ ከእንግዲህ በኋላ ሦስት አማልክትን
እንድትሰብክ ጠይቅኻለሁ” በማለት ይመልሱልናል። ይህ ከቶ አይሆንም! በሦስትነቱ
ለማመን አንድነቱን፣ በአንድነቱ ለማመን ሦስትነቱን መካድ የለብንም። እግዚአብሔር
በቸርነቱ የሰውን ልጆች ከአምልኮተ ጣዖት ለማዳን አንድነቱን እንደገለጠልን ሁሉ
ሦስትነቱንም ገልጦልናል። ሐሰተኞች፣ “በቅዱሳት መጸሐፍት አንድና ሦስት ስለምናገኝ
ሦስቱም (አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ) አንድ ናቸው ማለት ነው” ይላሉ። ስለ አንድነቱ

112
Tertullian, Against Praxeas, Chap 9: “Does not the very fact that they have the
distinct name of Father and Son amount to a declaration that they are distinct
impersonality?”
113
St Hilary of Poitiers, De Trinitate, Book 2: “They deceive their hearers by
emptying terms of their meaning, though the Names remain to witness to the
truth.”
Thomas Aquines, Summa Theologiae, Part 1, Question 28: “The Father is
denominated only from paternity; and the Son only from filiation. Therefore, if
no real paternity or filiation existed in God, it would follow that God is not
really a Father or Son but only in our manner of understanding and this is the
Sabellian heresy.”
114
Ibid, Chap 10-11
36
የተገለጠውን በማጉላትና ስለ ሦስትነቱ ከተገለጠው ጋር በማጣላት አንድነቱን ይዘው፣
115
ሦስትነቱን ይክዳሉ።

“አብ አምላክ፣ ወልድ አምላክ፣ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው። ሆኖም አንድ
116
አማልክ እንጂ ሦስት አማልክት አይደሉም“። አንድ አምላክ ማለት ነጠላ አካላዊ አምላክ
117
ማለት አይደለም። ሦስት አካላት ማለት ሦስት አማልክት ማለት አይደለም።
እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን አንድ አምላክ በሦስት አካላት እንደ ነበር፣ እንዳለና
እንደሚኖር ታምናለች። ሐሰተኞቹ፣ አንድ መለኮት የሚለውን የቅዱሳት መጽሕፍት
አስተምህሮ፣ ሦስት አካላት የሚለውን የቅዱሳት መጽሐፍት አስተምህሮ ለመቃወም
ይጠቀሙበታል።

“አብ አምላክ ነው፤ ወልድ አምላክ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው። ሆኖም
118
አንድ አምላክ እንጂ፣ ሦስት አማልክት አይደሉም“ ይላል ቅዱስ አትናቴዎስ። ስለ
መለኮት አንድነት የሚናገሩ ክፍሎችን አካላቱን ለመደባለቅ እንደተነገሩ አድርገን
ልንተረጉም አይገባም። ደግሞም ስለ አካላቱ ሦስትነት የሚናገሩ ክፍሎችን መለኮትን
ለመከፋፈል እንደተነገሩ አድርገን ልንተረጉም አይገባም። እኛስ ስለ አንድነቱ የተገለጠውን
በማጉላት ሦስትነቱን፣ ስለ ሦስትነቱ የተገለጠውን በማጉላት አንድነቱን አንክድም።
አካላቱን ሳንደባልቅ፣ መለኮታዊ ህልውናውንም ሳንከፍል በሦስትነቱ አንድነቱን፣

115
Tertullian, Against Praxeas, Chap 13: “Very well! you say, I shall challenge you to
preach from this day forth (and that, too, on the authority of these same
Scriptures) two Gods and two Lords, consistently with your views. God forbid,
(is my reply). For we, who by the grace of God possess an insight into both the
times and the occasions of the Sacred Writings, especially we who are followers
of the Paraclete, not of human teachers, do indeed definitively declare that
Two Beings are God, the Father and the Son, and, with the addition of the Holy
Spirit, even Three, according to the principle of the divine economy, which
introduces number, in order that the Father may not, as you perversely infer,
be Himself believed to have been born and to have suffered, which it is not
lawful to believe, forasmuch as it has not been so handed down.”
116
የአትናቴዎስ የእምነት ቀኖና
117
One God not uni-personal God (Latin: Non in Unum). We do not confess 3 Gods,
but 1 God in 3 persons. God is one but not solitary.
Tertullian, Against Praxeas, Chap 26
St. Ambrose, On The Holy Spirit, Book2, Chap. 1
118
የአትናቴዎስ የእምነት ቀኖና
37
በአንድነቱም ሦስትነቱን አምነን አንድ አምላክን እናመልካለን። የእግዚአብሔርን መገለጥ
ያለማመንታት፣ በእምነት እንቀበላለን። Fides praecedit intellectum, intellectus
119
merces est fidei- እምነት ማስተዋልን ይቀድማል፤ ማስተዋል የእምነት ሽልማት ናት።
በዚህ መሠረት እምነት ፍኖተ ጥበብ (semitae sapientiae) ትባላለች።

119
St. Augustine, Homilies On The Gospels, Sermon 67: “If you are not able to
understand, believe, that you may understand. Faith goes before;
understanding follows after.”
38
አንቀጽ ሦስት፡ የማይነጣጠል አሰራር

አስቀድመን እንዳልነው፦ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በሕልውና፣ በባሕርይ፣


በመለኮት አንድ ናቸው እንጂ በውስጣዊ ግብር፣ በስም፣ በአካል ይለያያሉ። ሆኖም
በፍቃድ፣ በአሠራርና በፍርድም አይነጣጠሉም። ሦስቱን አካላት በሦስት ስም
ብንጠራቸውም፣ አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አንላቸውም። አብ ፈጣሪ ነው፤
ወልድ ፈጣሪ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ ነው። ሆኖም አንድ ፈጣሪ እንጂ ሦስት ፈጣሪያን
አይደሉም። ይህም የሚሆነው አብ በአካላዊ ቃሉ (በወልድ) እና በአካላዊ እስትንፋሱ
(መንፈስ ቅዱስ) ስለሚሠራ ነው። መዝሙረኛው፣ “በእግዚአብሔር ቃል ሰማያት ተሠሩ፤
120
በአፉም እስትንፋስ የከዋክብት ሰራዊት“ እንዲል።

የእግዚአብሔር ቃል

ወልድ “የእግዚአብሔር ቃል“ ይባላል። የእግዚአብሔር ቃል ማለት ምን ማለት


121
ነው? ቃል ሲባል ዝርው ቃል ሳይሆን እውነተኛ አካላዊ ቃል ማለት ነው። ሀይፖስታቲክ
ሎጎስ ይሉታል ግሪካውያን ሊቃውንት። ይህ ቃል ራሱን የቻለ ስብእና ያለው፣ እገሌ የሚባል
አካል ነው እንጂ በአየር የሚፈስ፣ ተሰምቶ የሚያልፍ ድምጽ አይደለም። ይህ ቃል ድምጽ
ሳይሆን አካል፣ ንግግር ሳይሆን እውነተኛ አምላክ ነው። ለባዊ ከሆነ አብ፣ ነባቢ የሆነ ወልድ
122
ይገኛል። የሰው ነፍስ ልብነቷ ቃልነቷን እንደሚያስገኝ፣ አብ ወልድን ያስገኛል። የአብ
ጥበብ፣ ሃይል፣ ቀኝ እጅ፣ ክንድ… እርሱ ነው። ወልድ ለምን “የእግዚአብሔር ቃል“ ተባለ?

120
መዝ 33፡6
121
St Hilary of Poitiers, De Trinitate, Book 2: “The Word is a reality, not a sound, a
Being, not a speech, God, not a nonentity.”
122
Thomas Aquines, Exposition of the Apostles’ Creed, Article 2: “The soul by its act
of thinking begets the word, so also the Son of God is the Word of God.”
39
ቢባል፦ አብ በወልድ ቃልነት ስለሚናገር። ወልድ ለምን “የእግዚአብሔር ሐይል“ ተባለ?
123
ቢባል፦ አብ በወልድ ሐይልነት ስለሚሠራ፣ ስለሚፈጥር፣ ስለሚገዛ።

ጌታ ኢየሱስ፣ “እውነት እላችኋለሁ፤ አብ ሲሠራ ያየውን ብቻ እንጂ ወልድ ከራሱ


124
ምንም ሊያደርግ አይችልም፤ አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ያደርጋል“ ይላል።
“አብ ሲሠራ ያየውን ብቻ እንጂ ወልድ ከራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም” ማለት፣ “አባት
እንደ ብልህ ሠራተኛ ሰርቶ ያሳየውን ልጁ በጥንቃቄ በማየት ከተማረ በኋላ አባቱ ሲሠራ
እንዳየው መልሶ ይሠራል” ማለት ነውን? በፍጹም! እንደዚያ ቢሆን ወልድ “ፈጣሬ ኩሉ“
125
ባልሆነ! (ሁሉ በእርሱ ሆነ፤ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም) ወይ ደግም፣
“አባት ልጁ ሊሠራ ላለው ሥራ ንድፈ ሐሳብ ያኖርለታል፤ ልጁም አባቱ ያዘጋጀለትን ንድፍ
126
በማስተዋል እያነበበ አካል ይሰጠዋል“ ማለት ይሁን? እንዲህም አይደለም።

ጌታችን፣ “እኔ በአብ እንዳለሁ፣ አብም በእኔ እንዳለ ስነግራችሁ እመኑኝ፤ ሌላው
127
ቢቀር ስለ ድንቅ ሥራዎቹ እንኳ እመኑ።“ ባለው መሠረት ወልድ በአብ እንዳለ፣ አብም
128
በወልድ እንዳለ እናምናለን። የአብ ባሕርይ በወልድ ሕልው ሆኖ ይኖራል። የወልድ
ባሕርይ በአብ ዘንድ ሕልው ሆኖ የሚኖር ነው። አብ በወልድ ውስጥ ለመኖሩ ምን
ማረጋገጫ? አለ ቢሉ፣ ወልድ፦ “እኔ በአብ እንዳለሁ፣ አብም በእኔ እንዳለ… ስለ መለኮታዊ
ሥራዎቹ እንኳ እመኑ“ ባለው መሠረት ወልድ የሚሠራው መለኮታዊ ሥራ የአብ
መለኮታዊ ባሕርይ በእርሱ ሕልው ሆኖ መኖሩን የሚያረጋግጥ ነው።

“እውነት እላችኋለሁ፤ አብ ሲሠራ ያየውን ብቻ እንጂ ወልድ ከራሱ ምንም


ሊያደርግ አይችልም፤ አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ያደርጋል።“ አብ በባሕርዩ

123
Origen, De Principiis, Book 1, Chap 2: “By the power of God is to be understood
that by which… He appoints, restrains, and governs all things.”
St. Cyril of Alexandria, Comment on John, Book 1, Chap. 5: “When the Father
works the Son will work as being His natural and essential and hypostatic
power. Likewise when the Son works, the Father too works, as a source of the
creating Word.”
124
ዮሐ 5፡19
125
ዮሐ 1፡3
126
St. Augustine, Tractates on John, Tractate 19: Chap 5፡19-30
St. Augustine, Tractates on John, Tractate 18: Chap 5፡19
St. Basil, De Spiritu Sancto, Chap. 5
127
ዮሐ 14፡10-11
128
ተገኝቶ
40
በወልድ ውስጥ በመኖር ያሳየዋል። ወልድ ራሱ ቢሠራም ከራሱ አይሠራም፤ አብ ራሱ
129
ባይሠራም በሌላው ይሠራል። በዚህም አይነት መንገድ ሲሠሩም አንድነታቸውን
ይጠብቃሉ። ወልድ ተወላዲ ስለሆነ፣ “ከራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም።“ አባቱን
መስሎና አክሎ ስለተወለደ፣ ”አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ያደርጋል።”

አብ በውስጣዊ ግብር የወልድ ወላዲ ስለሆነ ውጫዊ ግብሩን በወልድ


130
ይከውናል። ወልድ በውስጣዊ ግብር ከአብ ተወላዲ ስለሆነ ውጫዊ ግብሩን ከአብ
ይከውናል። ይህም ወልድ ራሱ፣ “የምነግራችሁ ቃል ከራሴ አይደለም፤ ነገር ግን ሥራውን
የሚሠራው በእኔ የሚኖረው አብ ነው“ እንዳለው ነው። ጌታችን ይህን ሲል መናገሩን፣
መሥራቱን እየካደ አይደለም፤ ነገር ግን በእርሱ አካላዊ ቃልነት አብ ስለሚናገር፣ በእርሱ
131
አካላዊ ሐይልነት አብ ስለሚሠራ ነው። “ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ተናገረን“ ይህ
ክፍል ወልድ የአብ መፍጠሪያ ሐይል፣ መናገሪያ ቃል እንደ ሆነ ያስተምራል። ይህን
መለኮታዊ ድምጽ ልብ በሉ! “የምነግራችሁ ቃል ከራሴ አይደለም“ በማለት አብ በወልድ
አካላዊ ቃልነት እንደተናገረ፣ “ሥራውን የሚሠራው በእኔ የሚኖረው አብ ነው“ በማለት
አብ በወልድ አካላዊ ሐይልነት ዓለማትን እንደ ፈጠረ፣ እንደሚገዛ፣ ተዓምራትን
እንደሚያደርግ ገልጧል። አብ የሚሠራውን ሁሉ በወልድ ይሠራል፤ ወልድ የሚሠራውን
ሁሉ ከአብ ይሠራል። ወልድ፣ “ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ“ ሲል ከአብ
132
እንደሚሠራ ገልጧል።

129
St. Hilary of Poitiers, De Trinitate, Book 9
130
ውስጣዊ ግብር አካላዊ ግብር ማለት ነው። በውስጣዊ ግብር አብ ወላዲ፣ ወልድ ተወላዲ፣
መንፈስ ቅዱስ ሠራጺ ነው። ውጫዊ ግብር መለኮታዊ ግብር ማለት ነው። ይህም ሦስቱ
የሥላሴ አካላት በአንድ መለኮት የሚከውኑት ነው። በዚህም ምክንያት የሥላሴ ውጫዊ ግብር
የማይነጣጠል ነው ይባላል።
131
ዕብ 1፡2
132
ዮሐ 10፡32
41
የእግዚአብሔር እስትንፋስ

አብና ወልድ በውስጣዊ ግብር የመንፈስ ቅዱስ አሥራጺ ስለሆኑ ውጫዊ ግብርን
በመንፈስ ቅዱስ ይከውናሉ። መንፈስ ቅዱስ በውስጣዊ ግብር ከአብና ከወልድ
ስለሚሠርጽ ውጫዊ ግብሩን ከአብና ከወልድ ይከውናል። “እግዚአብሔር ግን ይህን
133
በመንፈሱ አማካይነት ለእኛ ገልጦልናል።“ ይህ ምንባብ አብ በመንፈስ ቅዱስ
ምሥጢራትን እንደሚገልጥ ያስተምራል። “የአብ የሆነው ሁሉ የእኔ ነው፤ እንግዲህ፣ የእኔ
ከሆነው ወስዶ እንድታውቁ ያደርጋል“ ይህ ምንባብ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ
እንደሚገልጥ፣ እንደሚሠራ ያስተምራል። የሥላሴ ውጫዊ ግብር በውስጣዊ ግብሩ
መሠረት ነው። አብ በውስጣዊ ግብሩ ባሕሪውን ለወልድ በወላዲነት፣ ለመንፈስ ቅዱስ
በአሥራፂነት እንደሚሰጥ ሁሉ በውጫዊ ግብሩም የሚያደርገውን ሁሉ በወልድ በኩል
በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ይከውናል [The Father acts through the Son in the
Holy Spirit]።

ምንም እንኳ አብ በአካላዊ ቃሉ (በወልድ)፣ በአካላዊ እስትንፋሱ (በመንፈስ


ቅዱስ) ቢተገብርም ግብሩ አንድ መለኮታዊ ግብር ነው። ጌታ ኢየሱስ አብ በእርሱ ሆኖ
ከሚሠራው ውጪ አንዳች ከራሱ እንደማያደርግ እያመለከተ፣ “አብ ሲሠራ ያየውን ብቻ
እንጂ ወልድ ከራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም፤ አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ
134
ያደርጋል“ ይላል። ፍጹም ነጠላ የሆነ አሠራር! “ወልድ ከራሱ ምንም ሊያደርግ
አይችልም“ እስኪባል ድረስ የወልድ ሥራ ሁሉ አብ በወልድ ሆኖ የሚሠራው ነው፤ “አብ
የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ያደርጋል“ እስኪባል ድረስ አብ የሚሠራውን ሁሉ
በወልድ ሆኖ ይሠራል። ጌታችን፦ መንፈስ ቅዱስ አብና ወልድ በእርሱ ሆነው ከሚሠሩት
ውጪ አንዳች በራሱ እንደማያደርግ እያመለከተ፣ “እርሱ ከራሱ አይናገርም… የአብ የሆነው
135
ሁሉ የእኔ ነው፤ እንግዲህ፣ ከእኔ ወስዶ እንድታውቁ ያደርጋል“ ይላል። ፍጹም ነጠላ የሆነ
አሠራር! መንፈስ ቅዱስ “ከራሱ አይናገርም“ እስኪባል ድረስ የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ
ከአብ በወልድ በኩል በሥርጸት የሚቀበለው ነው። ክርስቶስ፣ መንፈስ ቅዱስ “ከእኔ ወስዶ
እንድታውቁ ያደርጋል“ ባለው መሠረት፣ “እግዚአብሔር በመንፈሱ አማካይነት ለእኛ

133
1ቆሮ 2፡10
134
ዮሐ 5፡19
135
ዮሐ 16፡13-15
42
136
ገልጦልናል“። ልብ በሉ! አካላቱ ሦስት ቢሆኑም እንደ ተለያዩ ሦስት አካላት አይሰሩም።
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ በውስጣዊ ግብር፣ በስምና በአካል ቢለያዩም፣ በሕልውና፣
በባሕርይ፣ በመለኮት አንድ ናቸው። በፍቃድ፣ በአገዛዝና በፍርድም የማይነጣጠሉ ናቸው።

እንግዲህ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የሚፈጽሙት ፈቃድ፣ የሚሠሩት ሥራ ከአብ


ጋር ሆነው ያሰቡት፣ የመከሩት፣ ያቀዱትንና የፈቀዱት መሆኑን እናስተውላለን። በሰው
ቋንቋ አሰብ፣ መከሩ፣ አቀዱ፣ ፈቀዱ ብንል አንዱ የማያውቀውን ሌላው ሚያሳውቀው ሆኖ
ሳይሆን አንድ ፍቃድ፣ አንድ አሳብ እንዳላቸው ለማመልከት ነው። ፍቃዳቸው አንድ ነው፤
ሥራቸው አንድ ነው። አብ፣ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ ፍቃድ የለውም። ወልድ፣
ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ ፍቃድ የለውም። መንፈስ ቅዱስ፣ ከአብና ከወልድ የተለየ
ፍቃድ የለውም። አብ፣ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ ራሱ ብቻውን የሚሠራ
አይደለም። ወልድ፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ ራሱ ብቻውን የሚሠራ አይደለም።
መንፈስ ቅዱስ፣ ከአብና ከወልድ ተለይቶ ራሱ ብቻውን የሚሠራ አይደለም። አብ
በማይለይ ምክር፣ በአንዲት ፍቃድ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሰማይንና ምድርን፣
የሚታየውንና የማይታየውን ፈጠረ። አብ ፈቃዱ ፍቃዳቸው በሚሆን በወልድና በመንፈስ
ቅዱስ ሁሉን ይሠራል። ዳግመኛም ሦስት ሲሆኑ በረከትን በመስጠት፣ ምሥጋናን በመቀበል
አንድ ናቸው።

ክበበ ፀሐይ ብርሃንና ሙቀትን እየላከ መኖሩን ያሳውቃል እንጂ እንደ ብርሃን፣
እንደ ሙቀት የሚላክ አይደለም። አብ ወልድንና መንፈስ ቅዱስን ይልካል እንጂ የሚላክ
137
አይደለም። አስቀድመን እንዳልነው፣ በውስጣዊ ግብር፦ አብ አይወለድም፤
አይሠርጽም። ወልድ ከአብ ይወለዳል። መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ይሠርጻል። ስለዚህ
አብ የሥላሴ መገኛ መሠረት እና የሥላሴ የመጀመሪያው አካል ይባላል። ወልድና መንፈስ

136
St. Cyril of Alexandria, Comment on John, Book 1, Chap. 5: “The Father and Son
co-work, not as separate.”
137
St. Augustine, De Trinitate, Book 2, Chap. 3: "The Father alone is never described
as being sent." Book 4, Chap. 20: “"The Father, when known by anyone in time,
is not said to be sent; for there is no one whence He is, or from whom He
proceeds."
Thomas Aquines, Summa Theologiae, Part 1, Question 43: “The very idea of
mission means procession from another, and in God it means procession
according to origin, as above expounded. Hence, as the Father is not from
another, in no way is it fitting for Him to be sent; but this can only belong to
the Son and to the Holy Ghost, to Whom it belongs to be from another. “
43
ቅዱስም በቅደም ተከተል የሥላሴ ሁለተኛና ሦስተኛ አካል ይባላሉ። ይህ ማለት በአካላቱ
138
መካከል መቀዳደም አለ ማለት አይደለም። በውጫዊ ግብር፦ አብ ይልካል፤ አይላክም።
ወልድ በአብ ብቻ ይላካል። መንፈስ ቅዱስ በአብም በወልድም ይላካል። አብ በወላዲነቱ
ወልድን ይልካል፤ በአሥራጺነቱ መንፈስ ቅዱስን ይልካል። ወልድ በአሥራጺነት መንፈስ
139
ቅዱስን ይልካል። ሆኖም ስለ ክርስቶስ ሰብዓዊ ባሕርይ የተነገሩ ነገሮችንና በሰብዓዊ
ባሕርዩ የከወናቸው ሥራዎችን ስለ መለኮታዊ ባሕርዩ እንደተነገሩና በመለኮታዊ ባሕርዩ
እንደተገበሩ ልናስብ አይገባም።

አብ ይልካል በምንልበት ጊዜ በሥላሴ አካላት ውስጥ ታናሽና ታላቅ አለ ለማለት


ሳይሆን አብ በአካላዊ በቃሉ (በወልድ) እና በአካላዊ እስትንፋሱ (በመንፈስ ቅዱስ)
140
መሥራቱን ለማመልከት ነው። አብ በአካላዊ ቃሉ (በወልድ) እና በአካላዊ እስትንፋሱ
(በመንፈስ ቅዱስ) ይሠራል። ጌታችን “ይህን ያህል ጊዜ ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን?
እኔን ያየ አብን አይቷል፤ እንዴትስ “አብን አሳየን” ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ፣ አብም በእኔ
እንዳለ አታምንምን? የምነግራችሁ ቃል ከራሴ አይደለም፤ ነገር ግን ሥራውን የሚሠራው
በእኔ የሚኖረው አብ ነው። እኔ በአብ እንዳለሁ፣ አብም በእኔ እንዳለ ስነግራችሁ
141
እመኑኝ“ ባለው መሠረት፣ የክርስቶስን ትምህርትና መለኮታዊ ሥራ ያዩና የተረዱ ደቀ
መዛሙርቱ አብን በወልድ ሕልው ሆኖ ሲሠራ እንዳዩ ይቆጠራል። የወልድን መለኮታዊ
ሥራ ከተመለከትክ የአብን ሥራ ተመልክተሃል ማለት ነው።

138
አንቀጽ አንድ
139
Thomas Aquines, Summa Theologiae, Part 1, Question 43: “Not each person
sends, but that person only Who is the principle of that person who is sent; and
thus the Son is sent only by the Father; and the Holy Ghost by the Father and
the Son.“
140
Catechism of the Catholic Church, Part 1, sect. 2, Chap. 3: “In their joint mission,
the Son and the Spirit are distinct but inseparable. When the Father sends His
Word, He also sends His Breath.”
Thomas Aquines, Summa Theologiae, Part 1, Question 43: “The mission of a
divine person is a fitting thing, as meaning in one way the procession of
origin from the sender, and as meaning a new way of existing in another;
thus the Son is said to be sent by the Father into the world, inasmuch as He
began to exist visibly in the world by taking our nature; whereas "He was"
previously "in the world."…. “The Son may proceed eternally as God; but
temporally, by becoming man, according to His visible mission, or likewise by
dwelling in man according to His invisible mission.“
141
ዮሐ 14፡9-11
44
“አብ ሲሠራ ያየውን ብቻ እንጂ ወልድ ከራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም፤ አብ
የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ያደርጋል።“ አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ያደርጋል፤
መንፈስ ቅዱስም ያደርጋል። ወልድ የሚያደርገውን ሁሉ አብ ያደርጋል፤ መንፈስ ቅዱስ
ያደርጋል። መንፈስ ቅዱስ የሚያደርገውን ሁሉ አብ ያደርጋል፤ ወልድ ያደርጋል። አብ
ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ተነጥሎ የሚያደርገው ነገር የለም። ወልድ ከአብና ከመንፈስ
ቅዱስ ተነጥሎ የሚያደርገው ነገር የለም። መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ተነጥሎ
የሚያደርገው ነገር የለም። ይህን እውነት እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን የማይነጣጠል
142
አሰራር ትለዋለች።

“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ በአሰራር የማይነጣጠሉ ከሆነ የተሰገወው፣


የመስቀል መከራም የተቀበለው አብ ነው?“ ተብለን እንጠየቅ ይሆናል። ጥያቄው ታሪካዊና
ታሪክን ካለማወቅ የመነጨ ነው። ርቱዓን አበው የማይነጣጠል አሰራርን ባስተማሩ ጊዜ
143
ከሚነሱ ጥያቄዎች አንዱ ይሄ ነው። (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት) የተሰገወው
144
ወልድ ነው፤ ትሥጉቱ ግን የሥላሴ ሥራ ነው። ቃል ሥጋ ሆኖ የሰራውን ሥራ ያዩና
የተረዱ የአብንና የመንፈስ ቅዱስን ሥራ እንዳዩ፣ በወልድ ቤዛነት፣ አብና መንፈስ ቅዱስ
አዳኝ እንደ ሆኑ እናምናለን። ይህ እውነተኛ የክርስትና እውነት ነው።

142
The Doctrine Of Inseparable Operation
143
St. Augustine, Letters, Letter 11(To Nerbidus): “I am surprised at your finding it
hard to understand why the Son is said to have become man, and not the
Father, or even the Holy Spirit, for according to Catholic Faith, the Trinity is
proposed to our belief and believed -and even understood by few saints and
holy persons- as so inseparable that whatever action is performed by It, must
be thought to be performed at the same time by the Father and by the Son
and by the Holy Spirit. Consequently, the Father does not do anything which
the Son and the Holy Spirit does not do also; the Son does not do anything
which the Father and the Holy Spirit does not do also; nor does the Holy Spirit
do anything which the Father and the Son does not do also.”
144
Thomas Aquines, Summa Theologiae, Part 3, Question 3: “The act of
assumption proceeds from the Divine power, which is common to the three
Persons, but the term of the assumption is a Person. Hence what has to do
with action in the assumption is common to the three Persons; but what
pertains to the nature of term belongs to one Person in such a manner as not
to belong to another; for the three Persons caused the human nature to be
united to the one Person of the Son.
45
ጌታችን “የምነግራችሁ ቃል ከራሴ አይደለም፤ ነገር ግን ሥራውን የሚሠራው
በእኔ የሚኖረው አብ ነው“ ባለው መሠረት፣ አብ የሚሠራውን ሁሉ በወልድ እንደሚሠራ፣
ወልድም፣ በባሕርየ መለኮቱ፣ የሚሠራውን ሁሉ ከአብ በተቀበለው ባሕርይ እንደሚሠራ
እናምናለን። አብ በወላዲነቱ ባሕርዩን ለወልድ ሰጥቷል፤ ወልድም በረቂቅ ውልደቱ ባሕርዩን
ከአብ ተቀብሏል። አብ በባሕርዩ በወልድ ውስጥ ይኖራል፤ ወልድም በባሕርዩ በአብ ውስጥ
ይኖራል። አብ በባሕርዩ በወልድ ሆኖ ዓለማትን በእርሱ እንደፈጠረ፣ በክርስቶስ ዓለምን
145
ከራሱ ጋር አስታረቀ፤ ዓለምን በእርሱ አዳነ።

ጭብጥ፦ ወልድ የእግዚአብሔር ልጅ በመሆኑ በሕልውና፣ በባሕርይ፣ በመለኮት


ከአባቱ ጋር አንድ ነው። ይህ እውነት፣ ”ወልድ በባሕርይ ከአብ ያንሳል” የሚሉ
አርዮሳውያንን ጸጥ ያሰኛል። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የክርስቶስ መንፈስ
በመሆኑ በሕልውና፣ በባሕርይ፣ በመለኮት ከአብና ከወልድ ጋር አንድ ነው። ይህ እውነት፣
146
”መንፈስ ቅዱስ ሕጹጽ ” የሚሉ መቅዶንዮሳውያንን ጸጥ ያሰኛል። ወልድ የእግዚአብሔር
ልጅ በመሆኑ በውስጣዊ ግብር፣ በስምና በአካል ከአብ ይለያል። መንፈስ ቅዱስ
የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የክርስቶስ መንፈስ በመሆኑ በውስጣዊ ግብር፣ በስምና በአካል
ከአብና ከወልድ ይለያል። ይህ እውነት፣ ”ሥላሴ በአካል አንድ ናቸው” የሚሉ
ሰባሊዮሳውያንን ጸጥ ያሰኛል። ወልድ የእግዚአብሔር ልጅ በመሆኑ አብና እርሱ በፍቃድ፣
በአገዛዝና በፍርድም የማይነጣጠሉ ናቸው። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር መንፈስ፣
የክርስቶስ መንፈስ በመሆኑ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በፍቃድ፣ በአገዛዝና በፍርድም
የማይነጣጠሉ ናቸው። ስለዚህም ቅዱሳን አበው፣ ”አንድ ሕልውና”፣ ”ሦስት አካላት”፣
”የማይነጣጠል አሰራር” ይላሉ።

“የምሥጢረ ሥላሴ መግቢያ በር ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ ማመን


ነው“ ለምን እንደምንል አያችሁ? የቤተ ክርስቲያን ሥረ መሠረት ”ኢየሱስ የእግዚአብሔር
ልጅ ነው” ብሎ ማመን ነው። በዚህ የእምነት ጠንካራ ዓለት ላይ የተተከለችውን እውነተኛ
ቤተ ክርስቲያን የገሃነም ደጆች የሆኑ መናፍቃን አይችሏትም። በአንጥረኞች እጅ፣
በሐሰተኞች ቃላት የሚበጁ ጣዖታት በእውነተኛው አምላክ ፊት መቆም አይችሉም፤
በነፋሳት ጽናት፣ በማዕበላት ብዛት አትናወጥም። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ይህን

145
2 ቆሮ 5፡19 ዮሐ 3፡17
146
ያነሰ
46
በአግባቡ ከተረዳን ከመናፍቃኑ ከበባ እናመልጣለን። ይህ በመናፍቃን የማይበገር እምነት፣
የገሃነም ደጆች የማይችሉት አሸናፊ እውነት ነው።

አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ በውስጣዊ ግብር፣ በስምና በአካል ሦስት ቢሆኑም
በሕልውና፣ በባሕርይ፣ በመለኮት አንድ በፍቃድ፣ በአሠራር፣ በፍርድ የማይነጣጠሉ
በመሆናቸው አንድ አምላክ ይባላሉ። የአብ ሥራ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው።
አብ፣ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ ራሱ ብቻውን የሚሠራ አይደለም። አብ በቃሉና
በእስትንፋሱ ይሠራል። የአብ ፍቃድ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ፍቃድ ነው። አብ፣ ከወልድና
ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ ፍቃድ የለውም። የአብ መንግሥት የወልድና የመንፈስ ቅዱስ
መንግሥት ነው። ሦስት መንግሥታት የሉም ወይም አንዱን መንግሥት ተከፋፍለው
አይገዙም ወይም በፈረቃ አይገዙም ወይም አንዱ በአንድ መንገድ ሌላው በሌላ መንገድ
አይገዛም። የማትከፈል፣ የማትፋለስ መንግሥት አንዲት ናት። በማይከፈል መንግሥት
ሦስቱ አንድ ናቸው።

እንግዲህ ይህን የተማርን ሁላችን በመናፍቃኑ ድር እንደሚጠመዱ ደካሞች


አንሁን። ከደህንነታችን በላይ ምን የከበረ ነገር አለ? ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ፣
የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ ሆነ እንድታምኑ ዘንድ፣ አምናችሁም በስሙ ሕይወት
147
እንዲኖራችሁ ይህ ተጽፎአል። በእርሱ የማያምን በእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ስላላመነ፣
148
አሁኑኑ ተፈርዶበታል። ክርስቲያናዊ እምነት በክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅነት ማመን
149
እንጂ በደፈናው በክርስቶስ ማመን ብቻ አይደለም። ሐዋርያት ያስተማሩት፣ አባቶች
የጠበቁት፣ ቤተ ክርስቲያን የተቀበለችው፣ እኛም የምናምንባት፣ በጠላቶች ፊት የማይበገር
የክርስትና ሃይማኖት ይህ ነው። ይህች ትምህርት ከሐዋርያት ተገኝታ፣ በአበው ተጠብቃ፣
በቤተ ክርስቲያን ጸንታ ትኖራለች። ይህንን የማይቀበሉ የተረገሙ ናቸው፤
ትምህርታቸውም የተረገመ ነው። ዳግመኛም የእግዚአብሔር ጠላት፣ የክርስትና ባለጋራ
ናቸው። ይህንን እንዲህ ያመኑ ግን ብፁዓን ናቸው። ለሥላሴ ውዳሴ፣ ስብሐት፣ ክብረት
በውነት ይገባል፤ ዛሬም፣ ዘወትርም ለዘለዓለሙ። አሜን።

147
ዮሐ 20፡31
148
ዮሐ 3፡19
149
St Hilary of Poitiers, De Trinitate, Book 1: “The very center of a saving faith is the
belief not merely in God, but in God as a Father, not merely in Christ, but in
Christ as the Son of God; In Him, not as a creature, but as God the creator,
born of God.”
47
ምሥጢረ ሥጋዌ 150

አንቀጽ አንድ፡ ትሥጉት

እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ሰው እንደ ሆነ እናምናለን፤ እናስተምራለን።


ሰዎች መለኮትን ያዩት ዘንድ የበቁ እስኪሆኑ ድረስ በሰው ባሕርይ ተገለጠ፤ ልበ ንጹሃን
151
በተደሞ ፈዘዙ። ወልድ እንዴት ሰው ሆነ? ምሥጢሩን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር
እርሱ ብቻ ያውቃል። እኛ በአእምሮ መርምረን ልናውቅ፣ በአንደበት ተናግረን ልንገልጥ
አይቻለንም። የእግዚአብሔር ፍቅር የተገለጠበት፣ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችበት
የሥጋዌ ምሥጢር ረቂቅና ጥልቅ ነው። ይህም ምሥጢር የክርስትና አርማ፣ ምልክት ሆኖ
152
ይኖራል። በዚህ ክፍል በቀኖናዊ መጽሐፍት መሠረት፣ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት፣
በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት መድኅን ቃል ሰው የመሆኑን ነገር መናገር እንጀምራለን።
እግዚአብሔር በሰጠን ችሎታ መጠን እንናገር እንጂ ተናግሮስ ለመጨረስ አይቻለንም።
ዳግመኛም ሕሊና መርምሮ ሊያውቀው ያልቻለውን፣ ቃል ገልጦ ሊናገረው እንዴት
ይቻለዋል? ይህን ክቡር ሥራ እፈጽም ዘንድ እኔ ማን ነኝ? የአነጋገር ስልት አላውቅም፤
አንደበቴ አልተቃኘም። ነገር ግን፣ Caelitus mihi vires- ረድኤት፣ ጉልበቴ ከአርያም ነው።

አይሁድ፣ “ተራ ሰው ሆነህ ሳለህ፣ ራስህን አምላክ አደረግህ“ በማለት ሊወግሩት


153
ፈለጉ፤ እኛ አምላክ ሰው እንደሆነ አምነን ተቀበልን። እርሱ ራሱን አዋርዶ፣ የባሪያን
መልክ በመያዝ ሰው ሆነ እንጂ ሽቶ፣ ቀምቶ ከእግዚአብሔር ጋር የተካከለ አይደለም።
በምድር ያሉ እንደዘበቱበት፣ እንደሰደቡት፣ በሰማይ ሁሉ ያመልኩታል፤ ይሰግዱለታል።

150
አምላክ ሰው የመሆኑን ምሥጢር ቤተ ክርስቲያን “ምሥጢረ ሥጋዌ“ ወይም “ምሥጢረ
ትሥጉት“ ስትል ትጠራለች።
151
በመደመም፣ በመደነቅ
152
Catechism of the Catholic Church, Part 1, sect. 2, Chap. 2: “Belief in the true
Incarnation of the Son of God is the distinctive sign of the Christian faith.”
153
ዮሐ 10፡33
48
በሥጋ ወገኖቹ ወደሚሆኑ መጣ፤ እነርሱ ግን አልተቀበሉትም፤ በተቃራኒው ሽሙጥ፣
መከራ፣ ሞት አደረሱበት። ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጅ
154
የመሆንን መብት ሰጣቸው፤ ወንድሞቼም አላቸው።

155
“ወደ ምድር መጣ” ቢባል በነበረበት ሥፍራ ባልነበረበት ሁኔታ መገለጡን
ለማመልከት እንጂ የነበረበትን በመልቀቅ፣ ባልነበረበት ሥፍራ መገኘቱን ለማስተማርስ
አይደለም። ስለዚህ ባልተገኘበት እንዲገኝ፣ ጠፈርን አቋርጦ እንደመጣ ልናስብ አይገባም።
156
ወደ ዓለም ከመምጣቱ በፊት በዓለም ነበረ፤ ዓለሙም በእርሱ ሆነ። በመለኮቱ ምሉዕ
157 158
በኩሉሄ ነው፤ በጊዜና በቦታ ሳይወሰን ይኖራል። ሰው በመሆኑ በጊዜና በቦታ ተወሰነ።
ዘመን ተቆጠረለት፤ ሥፍራ ተነገረለት። ከዘመናት በፊት የነበረ እርሱ ትንሽ ሕፃን ሆነ።
ሰማይና ምድርን የመላ እርሱ በበረት ተጣለ። ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ አንድነት ሳይለይ
159
ከሰማይ ወረደ፤ የባሪያን መልክ በመያዝ ከእኛ ጋር ሆነ። አማኑኤል።

ሰማይ ምድር የማይወስነው፣ በድንግል ማሕፀን አደረ። ኋላም የእርግዝናዋ


ወራት ተፈጽሞ የሚወለድበት ቀን ሲደርስ ከሰማይ በታች፣ ከምድር በላይ በአራቱ መዓዘን
ተከበበ፤ በአጭር ቁመት፣ በጠባብ ደረት ተወሰነ። እንደ ሰው ሁሉ በየጥቂቱ አደገ።
በየጥቂቱ ያደገው መለኮት አይደለም፤ መለኮት በሰማይ በምድርም ምሉዕ ነውና።
160
በመለኮቱ ሰማይና ምድርን ይወስናል እንጂ አይወሰንም። ባሕርየ ሰብእን ከመያዙ
በፊት በጌትነቱ በምልአት ነበረ፤ ሰው ከሆነ በኋላም በጌትነቱ በምልአት ይኖራል። ባሕርየ
ሰብእን በያዘ ጊዜ ከመለኮታዊ ምላቱ አልተወሰነም። በባሕርየ ሰብእ በማሕፀን ሳለ
በባሕርየ መለኮቱ በሰማይ በምድር ምሉእ ነው።

ወደ ምድር መምጣቱ፣ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከድንግል ማርያም ያለ ዘርዐ


161 162
ብእሲ ፣ ያለ ሩካቤ መወለዱ ነው። የድንግልን ሆድ መግፋት ባየ ጊዜ ዮሴፍ በልቡናው

154
ዮሐ 1፡12
155
ዮሐ 1፡9
156
ዮሐ 1፡10
157
በሁሉ ቦታ የሚገኝ
158
Catechism of the Catholic Church, Part 1, sect. 2, Chap. 2: “In assuming a true
humanity, Christ’s body was finite.”
159
ኢሳ 7፡14
160
የሰውን ባሕርይ
161
ያለወንድ ዘር
49
አዘነ፤ በዘር የፀነሰችም መሰለው። የጌታችን እናት ግን እንዲህ ያለ ነውር አታውቅም።
163
እንኪያስ ያለ ዘር፣ ያለ ሩካቤ እንዴት ጸነሰች? ለወላዲቷም ትንግርት ነበር። ሊቀ
መልአኩም ሊያብራራው አይችልም። እንዲያው በደፈናው ይህ ታላቅ ምሥጢር በሃይለ
164 165
ልዑል እንደሚፈጸም ተናገረ እንጂ።

አንዳንዶች ከንቱ ፍርሃት አደናብሯቸው ጌታችን ከድንግል ማርያም ሥጋ


166
መንሳቱን ይክዳሉ። ይህ ፍርሃት ከጥንተ አብሶ ጣጣ የተወለደ ነው። እሊህ ስሁታን፣
“ጌታችን ከድንግል ማርያም ሥጋ ነሥቷል ካልን፣ ጥንተ አብሶ (የውርስ ኋጢአት) ነበረበት
ለማለት እንገደዳለን“ ይላሉ። ለመሆኑ “ከድንግል ሥጋ ነሣ“ ማለት፣ “በድንግል ተፀነሰ፤
ከድንግል ተወለደ“ ከማለት ውጪ ምን ማለት ሊሆን ይችላል? “ሥጋ ነሣ“ የሚለው ቃል
167
ከዚህ የዘለለ ትርጓሜ የለውም። “ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች“
የሚለውን የመጽሐፍን ቃል ትቶ፣ ደፍሮ ጌታችን ከድንግል ማርያም ሥጋ መንሳቱን
የሚክድ ቢኖር ይመለስ። ዳግመኛም ድንግል ጸንሣ፣ ወልዳው እንዴት ከጥንተ አብሶ ነፃ
ሆነ? ለሚለው ጥያቄ በድንግል ተፀንሶ፣ መወለዱን መካድ መፍትሄ አይሆንም።
ያልተገለጠልንን ለመመለስ የተገለጠልንን መካድ፣ “የቆጡን ላውርድ ብላ የብብቷን
ጣለች“ ይሆንብናል። እንኪያስ የጌታችን ልደት ያለ ጥንተ አብሶ እንዴት ተፈጸመ?
ምሥጢሩን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እርሱ ብቻ ያውቃል። እኛም ቅዱሳት መጽሐፍት
የተናገሩትን ሳንጠራጠር በእምነት እንቀበል እንጂ ይህ እንደምን ተደረገ? አንበል!

የመድኋኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ “እውነተኛ ያይደለ፣ ምትሐት ነው“ የሚሉ


አሳቾች ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕብረት የላቸውም። እሊህ እንደምንስ ክርስትያን
ይባላሉ? እንደ እነርሱ አነጋገር ከሆነ ሕማማቱ፣ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ድነታችንም ሁሉ ሐሰት
ነው። ሥጋው ምትሓት (መስሎ መታየት) ከሆነ፣ ሕማማት ሞቱም እውነተኛ አይደለም፤
ሞቱ እውነተኛ ካልሆነ፣ ድነታችን በውነት አይደለም። ሰው መሆኑም በወሬ ብቻ ይሆናል።
ምሥጢረ ሥጋዌው ሐሰት ከሆነ፣ ነገረ መስቀሉ ሐሰት ነው፤ ነገረ መስቀሉ ሐሰት ከሆነ፣

162
መናፍቁ ሰሬንተስ ኢየሱስን ማርያም ከዮሴፍ በሕገ ተፈጥሯዊ ሩካቤ እንደወለደችው
ያስተምራል።
163
ለቅድስት ማርያምም
164
በልዑል ሃይል
165
ሉቃ 1፡35
166
The problem of original sin.
167
ኢሳ 7፡14
50
168
ድነት የለም። ጌታችን ከድለ ትንሣኤው በኋላ የሥጋውን እውነተኝነት በመጠራጠር
169
መንፈስ ያዩ ለመሰላቸው ደቀ መዛሙርቱ፣ “ዳሳችሁ እዩ!“ በማለት የሥጋውን ቁስ
አካልነት ያረጋገጠላቸውን ፈለግ በመከተል በእውነተኛ ሥጋ መምጣቱን ለሚጠራጠሩ
170
ቅዱስ ዮሐንስ፣ “ዳሰነዋል!“ ሲል ያረጋግጥላቸዋል። “የክርስቶስ ሥጋ ምናባዊ ነው“
171
የሚሉ ኖስቲካውያን ይፈሩ፤ ይዋረዱ! የኢየሱስ የእቅፍ ወዳጅ፣ ሐዋርያው ዮሐንስ፣
“በዓይኖቻችን አይተነዋል፤ በእጆቻችን ዳሰነዋል“ ሲል ኑፋቄያቸውን አፈረሰ። ደግሞስ
172
ምናባዊ ሥጋ እንዴት ሊገረዝ ይችላል? እንዴትስ ትንሣኤው ለትንሣኤያችን ምስክር
173
ሊሆን ይችላል? እንኪያስ እስከ ዛሬ የሞት ሥልጣን አልጠፋም፤ ትንሣኤም የለም።

ሰው ሆነ ሲባል በሐሰት፣ መስሎ በመታየት አይደለም። በውነት ሰው ሆነ፤ በሐሰት


በምትሐት አይደለም። በሐሰት ያይደለ፣ በውነት ስለ እኛ መከራን ተቀበለ። ግርፋቱ
ይሰማው ነበር፤ እጅና እግሩ ሲቸነከሩ ይሰማው ነበር። የክርስቶስን ሥጋ ምትሀት የሚሉ
ሰዎች፣ ሕማማት መከራውን ከንቱ ያደርጋሉ፤ የማዳን ሥራውን ያራክሳሉ። ዳግመኛም
በውነት እኛን ካልመሰለ፣ እንዴት ወንድሞቹ እንባላለን?

ነፍስ ከሥጋ የከበረች መሆኗ ከክርክር ቀጠና ውጪ ያለ እውነት ነው። ስለዚህ


Nullo contradicente- ያለ ምንም ተቃርኖ፣ “ነፍስ ከሥጋ ትከብራለች“ እንላለን።
እንኪያስ እውነተኛ ሥጋ ይዞ ሰብዓዊ ነፍስ ብትጎድለው ሰው የመሆኑ ፍጹምነት ወዴት
አለ? ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምክንያታዊት ነፍስና ቁስ አካላዊ ሥጋ በመያዙ “ፍጹም ሰው“
174
ትለዋለች። “አምላክ በሥጋ ተገለጠ“ የሚለውን ሃይለ ቃል አፋዊ ትርጓሜ በመስጠት

168
Thomas Aquines, Summa Theologiae, Part 3, Question 5
St. Augustine, Qq 83, qu 13
St. Cyril of Jerusalem, The Catechetical Lectures; Lecture 4
169
ሉቃ 24፡37-39
170
1ዮሐ 1፡1
171
ይህ አስተምህሮ የክርስትና እና የኘላቶኒዝም ቅይጥ ነው። ዋነኛው አስተምህሯቸው፣ “ቁስ አካል
ሁሉ እኩይ ነው፤ መንፈሳዊ አካል ሁሉ ሰናይ ነው“ የሚል ነው። ከዚህ ስህተታቸው የተነሳ
ክርስቶስ በቁስ አካላዊ ሥጋ መገለጡን ይክዳሉ። ከኖስቲካውያን በተጨማሪ ማኒና ተከታዮቹ
“የክርስቶስ ሥጋ ምናባዊ ነው“ ብለው ያስተምራሉ።
172
ሉቃ 2፡21-24
173
1ቆሮ 15
174
Augustine (Fulgentius),De Fide ad Petrum, 14: "Firmly hold and nowise doubt
that Christ the Son of God has true flesh and a rational soul of the same kind
as ours, since of His flesh He says (Lk. 24:39): 'Handle, and see; for a spirit hath
not flesh and bones, as you see Me to have.' And He proves that He has a soul,
51
ሥጋን ያዘ እንጂ ምክንያታዊት ነፍስ አልያዘም የሚል ካለ፣ እስኪ ልጠይቀው፦ ነብየ
እግዚአብሔር፣ ክብር ሙሴ፣ ሰባ ነፍሳት ወደ ግብጽ ወረዱ ሲል ሥጋ የሌላቸው መናፍስት
175
ወደ ግብጽ መውረዳቸውን እየተረከ ነው? በእነዚህ ክፍሎች ብቻ ሳይሆን በተለያዩ
ምንባባት ሰዎች “ነፍሳት“ እና “ሥጋ“ ተብለው እናያለን። የክርስቶስ ምክንያታዊት ነፍስ
ሰብዓዊ እውቀት አላት። በዚህ መሠረት በሥጋ በቁመት፣ በምክንያታዊት ነፍሱ በጥበብ
176
በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር። የክርስቶስ ምክንያታዊት ነፍስ ሰብዓዊ ስሜት
177
አላት። በዚህ መሠረት ነፍሱ አዘነች ። የክርስቶስ ምክንያታዊት ነፍስ ሰብዓዊ ፍቃድ
አላት። በዚህ መሠረት፣ “የእኔ ፍቃድ ሳይሆን የአንተ ፍቃድ ይሁን“ አለ። በምሥጢረ ሥላሴ
እንደምንማረው አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ በፍቃድ ፍጹም አንድ ናቸው። ወልድ፣
ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ ፍቃድ የለውም። በምሥጢረ ሥጋዌ ደግሞ ወልድ ሁለት
ፍቃድ (መለኮታዊ እና ሰብዓዊ ፍቃድ) እንዳለው እንማራለን። ኾኖም ሰብዓዊ ፍቃዱ
178
ለመለኮታዊ ፍቃዱ ያለምንም ተቃርኖ ይገዛል። የክርስቶስ ምክንያታዊት ነፍስ ሰብዓዊ
እውቀት፣ ስሜትና ፍቃድ አላት።

“ቃል ሥጋ ሆነ እንጂ ቃል ሥጋና ነፍስ ሆነ አልተባለም“ የምትል ፊደላዊ ተርጓሚ


ሆይ፤ እስኪ ልጠይቅህ፦ መልስልኝ! “ቃል ሥጋ ሆነ ብቻ ነው የተባለው“ ስትል ደም፣
አጥንት፣ ጸጉር፣ ጥፍር… እንዳለው ትክዳለህ? መጽሐፍ ይህን ሁሉ ቆጥሮ አልተናገረም፤
“ቃል ሥጋ ሆነ“ አለ እንጂ። ከኋጢአት በቀር በሰው ያለው ሁሉ ገንዘቡ የሚሆን ፍጹም ሰው

saying (Jn. 10:17): 'I lay down My soul that I may take it again.' And He proves
that He has an intellect, saying (Mt. 11:29): 'Learn of Me, because I am meek
and humble of heart.' And God says of Him by the prophet (Is. 52:13): 'Behold
my servant shall understand.'"
175
ዘጸ 1፡5
176
ሉቃ 2፡52
177
ማቴ 26፡38
178 th
The 6 Ecumenical Council (Constantinople 3): “In accordance with what the
prophets of old taught us concerning Christ, and as He taught us Himself, and
the symbol of the holy fathers has handed down to us, we confess two natural
will in Him and two natural operations.” Christ’s human will “does not resist or
oppose but rather submit to His Divine and Almighty will.”
St. Augustine, Contra Maximus: “When Christ says ‘not what I will, but what Thou
wilt’ He shows Himself to have willed something else that did His Father; and
this could only have been by His human heart.”
52
ነው። “ከኅጢአት በቀር በሁሉ ነገር ወንድሞቹን መሰለ“ የሚለውን የመጽሐፍ ቃል ትቶ፣
“በሥጋው ብቻ መሰለን“ የሚል ስሁት ነው።

መለኮት ፍጡር አይደለም፤ አይለወጥም። “ያልፋል“ “ይለወጣል“ በማይባል


ባሕርይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል። እንኪያስ እንዴት መለኮት ተለውጦ ሰው ይሆናል?
መለኮት ተለውጦ ሰው ሆነ ብሎ ማሰብ ድንቁርና ወይም ድፍረት ከዚያም በላይ ስድብና
ኀጢአት ነው። ከዚህ የሚበልጥ ምን ድንቁርና፣ ምንስ ድፍረት አለ? መንፈስ ቅዱስ
ገልጦለት ቅዱሳት መጽሐፍትን የተማረ እንዲህ ብሎ ያስብ ዘንድ ፈጽሞ አይደፍርም።
በክብሩ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተስተካከለ እውነተኛ አምላክ፣ ለክብሩ የማይመጥን
(infra dignitatem)፣ የተዋረደ፣ የተናቀ ባሕሪን በመያዙ “ራሱን ባዶ አደረገ“ ተባለ እንጂ
ባሕርየ መለኮቱን ትቶ እንኳ አይደለም። ሰው የሆነው ያልነበረውን ባሕርይ በመያዝ እንጂ
179
ከባሕርየ መለኮቱ በመለወጥ አይደለም። ሰው ከሆነም በኋላ፣ አሁንም በጌትነቱ ጸንቶ
ያለ ነው፤ ባሕርየ መለኮቱ ሰው ወደ መሆን አልተለወጠም።

“አምላክ ሰው በመሆን ተለወጠ“ የሚሉ ደፋሮች ይናገሩ ዘንድ ይህን ክሕደት


ከየት አገኙት? ሰው ብቻ ከሆነማ በሞተ ጊዜ ሞትን እንደምን ድል በነሣ ነበር? እኛንስ
እንደምን ባዳነ ነበር? ይህ ከሰው ኀይል በላይ ነውና። እርሱ ሞቶ ሞትን ድል የነሳ ፍጹም
አምላክ፤ ፍጹም ሰው ነው። ሰው በሆነ ጊዜ ከባሕርዩ አልተለወጠምና በመለኮታዊ ሥራ
አምላክ መሆኑን ገለጠ። ማዕበል ፀጥ ማሰኘቱ፣ በባሕር ላይ መሔዱ፣ አጋንንትን
ማውጣቱ፣ ሙታንን ማስነሳቱ፣ ኋጥያትን ማስተሰረዩ ምንድን ነው? ለባሕርየ መለኮቱ
እንደሚገባ ተአምራትን ያደርጋል እንጂ ከነቢያት እንደ አንዱ በጸጋ አላደረገም። በባሕርይ
180
ሥልጣኑ (Arbitrio Suo) ድንቅን ያደርጋል። ጌታችንን “አምላክ ያደረበት ሰው እንጂ
የባሕርይ አምላክ አይደለም“ የሚሉ ውጉዛን ናቸው። እኛስ እንደ አብ፣ እንደ መንፈስ ቅዱስ
መለኮት ሳለ፣ እንደ እኛ ሰው እንደሆነ በውነት እናምናለን። አምላክ እንደ መሆኑም
181
መዠመሪያ ሰብአ ሰገል፣ ኋላም እግረ ተማሪዎቹ ሰገዱለት። ሥነ ፍጥረት፣ መላእክተ

179
The Roman Catechism, Part 1, Article 2: “The same person, remaining God as He
was from eternity, became man, what He was not before.”
180
On His own authority
181
ደቀ መዛሙርቱ
53
182
ጽልመት ሁሉ ይታዘዙታል። በአዲስ ባሕርይ ቢገለጥም በመለኮቱ ልዕልና ለዘለዓለሙ
ጸንቶ ይኖራል። “አምላክ ሰው በመሆን ተለወጠ“ የሚሉ አምላክን ያይደለ ራሳቸውን ጎዱ።

ምሥጢረ ሥጋዌ ያለመለወጥ፣ ያለመቀላቀል ተፈፀመ እንጂ ባሕርየ መለኮት


ባሕርየ ትስብእት ወደ መሆን አልተለወጠም፤ ዳግመኛም ባሕርየ ትስብእት ከባሕርየ
መለኮት ጋር አልተቀላቀለም። ሁለት ባሕርያት እያንዳንዳቸው ያለ መቀላቀል፤
በየገንዘባቸው ጸንተው ይታወቃሉ። ቅዱሳት መጽሐፍት ከሥጋዌ በኋላም ስለ አምላክነቱ፣
ስለ ሰውነቱም ይናገራሉ። ይህ ባሕርየ መለኮቱ ወደ ባሕርየ ትስብእት አለመለወጡን፣
183
ሁለቱ ባሕርያት አለመቀላቀላቸውን ማስረጃ ነው።

በመለኮቱ አብና መንፈስ ቅዱስን በመልክ እንደሚመስል፤ በባሕርይ


እንደሚተካከል፣ በትስብእቱ እኛን በመልክ ይመስላል፤ በባሕርይ ይተካከላል። ከእኛ ጋር
የሚተካከልበት ባሕርዩ ከአብ ጋር ከሚተካከልበት ባሕርዩ እጅጉን ያንሳል። ፍጡር ከፈጣሪ
ጋር እንዴት ይስተካከላል? መለኮትና ትስብእት በባሕርይ አንድ ናቸው ብሎ እንደመናገር
ያለ ድፍረትስ ምን አለ?

በአርያም ክብር፣ ምስጋና የሚቀበል አምላክ፣ ሰው በመሆን ሕማማትን፣ ሞትን


ተቀበለ። በውኑ አምላክ ይታመም ዘንድ ግዙፍ ነውን? በባሕርየ መለኮቱ ፈጽሞ ሕፀፅ
የለበትም፤ በሕማም፣ በሞት ድል አይነሣም። ሕይወትን ይሰጣል እንጂ ፈጽሞ አይሞትም።
መለኮት ይደክማል፣ ይታመማል፣ ይሞታል ሊባል አይቻልም። መተኛት፣ ረኋብ፣ ጥም፣
ድካም፣ ሕማማት፣ ሞት የባሕርየ ትስብእት ገንዘብ ናቸው። በባሕርየ ትስብእቱ ተራበ፤
ተጠማ፤ መንገድ በመሄድ ደከመ፤ በግርፋት ቆሰለ። በዚህ ሁሉ ፍጹም ሰው መሆኑን
አስረዳ።

በሥጋው ሞተ እንጂ በመለኮቱ ትንሳኤና ሕይወት ነው። በመለኮቱ ሞት


እንደሌለበት፣ ሕማም ሞትን ድል እንደሚነሣ፣ በሥጋ ቢሞትም በመለኮቱ ሥልጣን
እንደተነሣ እናውቃለን። ሞትን የማያይ ሰው ማነው? ሥጋውን ከመቃብር፣ ነፍሱን ከሲኦል
የሚያድን ማነው? አንድ ራሱን ሊያድን ያልቻለ ዓለምን ሁሉ ሊያድን እንደምን ይችላል?
ሞትን ድል መንሳት እንደኛ ያለ የደካማ ሰው ሥራ አይደለም። ይህ ከሰው አቅም ፈጽሞ

182
ርኩሳን መናፍስት
183
ከ451 ጀምሮ በኬልቄዶናውያንና በተዋሕዷውያን መካከል የነበረው አለመስማማት በ1973
በአቡነ ሽኖዳ መሪነት እልባት ያገኘ በመሆኑ በመሆኑ በዚህ ርዕስ ላይ ጠልቀን የምንገባ
አይሆንም።
54
የራቀ ነው። በዚህ መሠረት ሰው ሆኖ ወደዚህ ዓለም በመጣ፣ በሞተ፣ ከሙታን ተለይቶ
184
በመነሣት የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን በኋይል በገለጠ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን፤
እንታመናለን።

በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ ነው፤ በሰውነቱ ከእኛ ጋር አንድ ነው። ሆኖም ክርስቶስ
ሁለት አይደለም። “ከእግዚአብሔር የተወለደው ሌላ፣ ከድንግል የተወለደ ሌላ“ በማለት
ክርስቶስን ልንከፍለው፣ ሁለት ልናደርገው አይገባም።

ከአብ በተወለደው በቀዳማዊ ልደቱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፤ ከድንግል


በተወለደው በዳኋራዊ ልደቱ የሰው ልጅ ይባላል። ሆኖም ከእግዚአብሔር አብ የተወለደ
እርሱ ዳግመኛ ከድንግል በሥጋ የተወለደ ነው እንጂ “ከእግዚአብሔር የተወለደው ሌላ፣
ከድንግል የተወለደ ሌላ“።

“ከእግዚአብሔር የተወለደው ሌላ፣ ከድንግል የተወለደ ሌላ“ የምትሉ


ንስጥሮሳውያን ሆይ፤ ልጠይቃችሁ፦ እግዚአብሔር አብ “የምወደው ልጄ“ ያለው ከሁለቱ
ማንን ነው? በምድር ላይ የቆመውን አይደለምን? በምድር ላይ የቆመውስ ከድንግል
የተወለደ አይደለምን? እንኪያስ “ከእግዚአብሔር የተወለደው ሌላ፣ ከድንግል የተወለደ
ሌላ“ ማለትን ከየት ተማራቹ? ከእግዚአብሔር የተወለደው ሌላ፣ ከድንግል የተወለደ ሌላ
አይደለም፤ በበረት የተወለደው ሌላ፣ ሰብአ ሰገል የሰገዱለት ሌላ አይደለም። እኛስ
አስቀድሞ ዓለም ሳይፈጠር በመለኮቱ ከአብ በተወለደ፤ ዳግመኛም እኛን ለማዳን በኋላ
ዘመን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በእግዚአብሔር ልጅ እናምናለን።

“የሰው ልጅ ማን ነው?“ ለሚለው ጥያቄ ትክክለኛው መልስ፣ “የሕያው


185
የእግዚአብሔር ልጅ ነው“ የሚል ነው። የሰው ልጅ ማለት ምን ማለት ነው? በሰፊው
ትርጓሜ ከሰው የተወለደ ሁሉ የሰው ልጅ ሊባል ይችላል። በዚህ አግባብ ቅዱሳት
መጽሐፍት፣ “ይዋሽ ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፤ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ
186
አይደለም“፤ “ከብል የሚቆጠር የሰው ልጅ“ ይላሉ። በቅዱሳት መጽሐፍት ቃሉ አንዳንዴ
የተለየ ሥነ መለኮታዊ አመልክቶት ይኖረዋል። በዚህ አግባብ ቅዱሳት መጽሐፍት፣ የጠላትን
ራስ የሚቀጠቅጠውን የሴቲቱን ዘር፣ ለአሕዛብ በረከት የሚያመጣውን የአብርሃም ፍሬ፣

184
ሮሜ 1፡3-4
185
ማቴ 16፡13-16
186
ዘኅ 23፡19 ኢዮ 25፡6… ከዚህ በተጨማሪ በብዙ ምንባቦች ከሰው የተወለዱ የሰው ልጆች ሲባሉ
እናነባለን።
55
187
የአባቱን የንግሥና መንበር የሚወርሰውን የዳዊትን ልጅ ፣ ጌታችን እና መድሃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ የሰው ልጅ ይላሉ። ጌታ ኢየሱስ፣ “ሰዎች፣ የሰውን ልጅ ማን
188
ይላሉ?“ ሲል የጠየቀውን ጥያቄ ለእግረ ተማሪዎቹ ፣ “እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?“
በማለት የግል መልሳቸውን ይጠይቃቸዋል። በዚህም መሠረት “የሰው ልጅ ማን ነው?“
የሚለው ጥያቄ “ኢየሱስ ማን ነው?“ የሚል ትርጉም አለው። የሰው ልጅ (ኢየሱስ)
የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ከቅድስት ድንግል ማርያም በመወለዱ የእግዚአብሔር ልጅ
የሰው ልጅ ሆኗል። በዘመናት መጨረሻ ከድንግል ያለ አባት የተወለደው፣ በዘለዓለማዊ
ውልደቱ ከአብ ያለ እናት የተወለደ ነው።

መልአከ እግዚአብሔር፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ “ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ


189
የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል“ ባለው መሠረት የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ እንደ ሆነ
190
በማመን፣ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ“ በማለት እናመልከዋለን።
191
ሐዋርያው ጳውሎስ፣ “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ“ ቢል
ባሕርየ መለኮት ሥጋና ደም ስላለው እንዳልሆነ ግልጥ ነው። እንኪያስ ለምንድን ነው?
ባሕርየ መለኮት ከሰብዓዊ ባሕርይ ጋር ያለ መለወጥ፣ ያለ መቀላቀል እና የለ መከፋፈል
በአንድ አካል ስለሚኖር ነው። ጌታችን፣ “የሰው ልጅ ኀጢአትን ለማስተስረይ ሥልጣን
192
አለው“ ቢል ኀጢአትን የሚያስተሰርየው የሰው ልጅ በተባለበት ባሕርይ (በሰብዓዊ
ባሕርዩ) ሆኖ ሳይሆን፣ ሰብዓዊ ባሕርዩ ኀጢአትን ይቅር ከሚል ባሕርየ መለኮቱ ጋር በአንድ
አካል በመሆናቸው ነው።

ወልድ ሁለት ልደታት እንዳሉት እናምናለን፤ መዠመሪያ ከአባት ያለ እናት


193
ተወለደ፤ ዳግመኛም ከእናት ያለ አባት ተወለደ። በምድር አባት የሌለው ነው፤
በሰማይም እናት የሌለችው ነው። ከእኛ በሚለይበት ልደት እናት የለውም፤ የእኛን
በሚመስለው ልደት አባት የለውም። ሁለቱም ልደቱ በሰው ልብ ከመመርመር የራቀ ነው።
በቀዳሚ ልደቱ የእግዚአብሔር ልጅ፣ በዳግማዊ ልደቱ የሰው ልጅ ይባላል። ከአብ አብን

187
ዘፍ 3፡15. 26፡4 ሉቃ 1፡32
188
ደቀ መዛሙርቱ
189
ሉቃ 1፡35
190
ማቴ 16፡16
191
ሐዋ 20፡28
192
ማር 2፡10 ማቴ 9፡6…
193
St. Augustine, Homilies on The Gospels, Sermon 76
Gregory Nazianzen, Oration 29; Theological Oration 3
56
አክሎና መስሎ በመወለዱ ፍጹም አምላክ ነው፤ ከድንግል ማርያም የሰውን ባሕርይ
በመካፈል፣ መጀመሪያ በፅንሰቱ፣ በኋላም በልደቱ ፍጹም ሰው ሆነ። ስለዚህ “ፍጹም ሰው፣
ፍጹም አምላክ“ ይባላል።

194
ቅድስት ማርያም በውነት ወላዲተ አምላክ ናት። አምላክን የወለደች ናት
ብንልም፣ ባሕርየ መለኮትን እንዳስገኘች አናምንም፤ አናስተምርም። በምሥጢረ ሥጋዌ
እንጂ በሌላ አምላክን ወለደች አንልም። መለኮታዊ ባሕርዩና ሰብዓዊ ባሕርዩ ያለ
መቀላቀል፣ የአቋም ሽረትና ፍልሰት ሳይኖርባቸው፣ ፈጽሞ ሳይለያዩና ሳይከፋፈሉ በአንድ
አካል በመጣመራቸው ማርያም የአምላክ እናት ትባላለች። ዳግመኛም በመለኮቱ ጥንት
የለውምና ከድንግል ስለ ተወለደ፣ መገኘቱ ከዚህ ወዲህ ነው አንልም። እንደ መለኮቱ
የድንግል ማርያም ፈጣሪ ነው፤ እንደ ሰውነቱ የማርያም ልጅ ነው። “ድንግል ፈጣሪዋን
ወለደችው፤ እርሱም እናቱን ፈጠረ። ከእርሷም ራሱ የፈጠረውን ሥጋ ያዘ“ እንዳለ ኤፍሬም
195
ዘሶርያ። ዳግመኛም እርሱ ፍጡር እንደ ተባለ ብትሰማ እንደኛ ፍጹም ሰው በመሆኑ
እንጂ አርዮስ እንደሚለውስ ሆኖ አይደል።

አስቀድመን “የምሥጢረ ሥላሴ መግቢያ በር ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው


ብሎ ማመን ነው“ ብለን ነበር፤ አሁን ደግሞ “የምሥጢረ ሥጋዌ መግቢያ በር ኢየሱስ
የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ ማመን ነው“ እንላለን። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ
ነው ብሎ ማመን በምሥጢረ ሥላሴ ላይ ከሚነሱ መናፍቃን ብቻ ሳይሆን በምሥጢረ
ሥጋዌ ላይ ከሚነሱ መናፍቃን ይታደጋል። ኦ ታላቅ ቃለ እምነት! ኢየሱስ የእግዚአብሔር
ልጅ ነው። ይህ እውነት ከመናፍቃኑ ጋር በምንገጥመው ተጋድሎ ጋሻና ጦራችን ነው። በዚህ
ጠንካራ ዓለት ላይ የቆመች ቤተ ክርስቲያንን የገሃነም ደጆች አይችሏትም።

ሕማምና ሞት ለመለኮት ሲነገር ብትሰማ ባሕርየ መለኮት ከባሕርየ ሰብእ ጋር


የአንድ አካል ገንዘብ ስለ ሆነ እንጂ መለኮትስ ሕማም የለበትም። ስለዚህ ሕማምና ሞት
ለባሕርየ መለኮቱ እንደ ተነገረ አታስብ፤ ከመለኮቱ ጋር የአንድ አካል ገንዘብ ስለሆነ ስለ
ትስብእት ተነገረ እንጂ። ሞትን ያጠፋ ዘንድ ባሕርየ መለኮት ከባሕርየ ሰብእ ጋር የአንድ
አካል ገንዘብ ሆነ። ሆኖም አንዱ ክርስቶስ አምላክ እንደመሆኑ ተአምራትን ያደርጋል፤
ሰውም እንደ መሆኑ መከራ ይቀበላል። መለኮት ከትስብእት ጋር የአንድ አካል ገንዘብ

194
“የጌታ እናት“፣ “ወላዲተ አምላክ“፣ “እመ አምላክ“፣ “እመ ብርሃን“…
195
ቅድስት ማርያም እመ አምላክ መባል የለባትም ያለው መናፍቅ (ንስጥሮስ) በጉባኤ ዘኤፌሶን
(431) ተወግዞ ነበር።
57
በመሆኑ ታመመ ተባለ እንጂ የሚታመምስ ሆኖ አይደለም። ለሥጋ እንደሚገባ ታመመ፤
ለመለኮት እንደሚገባ ሞትን ድል ነሣ።

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካል አንድ ነው። እርሱ አንድ ብቻ እንደሆነ እመኑ።
ወደ ሁለት መከፈል የለበትም። የማይከፈለውን አንከፍልም። አካሉን መክፈል ክሕደት
ነው። በምሥጢረ ሥጋዌ ባሕርየ መለኮት እና ባሕርየ ትስብእት የአንድ አካል ሁለት
ባሕርያት ሆነዋልና። የምናምንባት፣ ተስፋ የምናደርጋት፣ የምንወዳት ሃይማኖት ይህች
ናት፤ እንኖርባታለን፤ እንሞትባታለን፤ እንነሣባታለን።

58
አንቀጽ ሁለት፡ ነገረ መስቀል196

197 198
አምላክ ለምን ሰው ሆነ? የሚለውን ጥያቄ የኒቅያ ጸሎተ ሃይማኖት (325)፣ “ስለ
199
እኛ፣ ስለ ሰዎች፣ ስለ መዳናችን “ በማለት ይመልሳል። የፍጥረታት ሠራዒ ቃል፣ ሥጋ
በመሆን የፍጥረታት አዳኝ ሆነ። ፍጥረተ ዓለም በእርሱ ሆነ፤ ዳግመኛም አድኅኖተ ዓለም
በእርሱ ተፈጸመ። በእርሱ የሚለው ቃል ለፈጣሪነቱ ብቻ ሳይሆን ለአዳኝነቱም ይነገራል።
200
እግዚአብሔር ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ዓለምን አዳነ። እኛም በእግዚአብሔር ልጅ
ፈጣሪነትና አዳኝነት እናምናለን፤ እንታመናለን።

የሰው ልጅ መዳን፣ አለመዳኑ ለእግዚአብሔር ምኑ ነው? ከመዳኑ ምን


ይጠቀማል? ባይድንስ ምን ይጐድልበታል? መጀመሪያስ ለምን ፈጠረው? መለኮት በራሱ
ለራሱ ብቁ ነው። ከፈጠራቸው ፍጥረታት አንዳች አያሻውም። ታዲያ ለምን ፈጠራቸው?
የራሱን እውነት፣ የራሱን መልካምነት፣ የራሱን ውበት በእነርሱ ውስጥ፣ በእነርሱ ላይ፣
201
በእነርሱ በኩል ይገልጣል ዘንድ።

196
ጌታ ኢየሱስ ከመጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ፣ ያደረገውና ያስተማረው ሁሉ
በምሥጢረ ትሥጉቱ እና በነገረ መስቀሉ ይተረጐማል። ዳግመኛም በነገረ መስቀሉ የትሥጉቱ
ዓላማ ስለ ተፈጸመ፤ ምሥጢረ ትሥጉት በነገረ መስቀል ይተረጐማል። (Catechism of the
Catholic Church, Part 1, sect. 2, Chap. 2: “All that Jesus did and taught, from the
beginning until the day when He was taken up to heaven is to be seen in the
light of the mysteries of Christmas and Easter.”) በዚህ መሠረት ስለ ትሥጉቱ ዓላማ
የሚያወራውን ይህን ንዑሥ ክፍል ነገረ መስቀል ስንል ሰይመነዋል።
197
St. Anselm: “Cur Deus Homo?”
198
የእምነት ቀኖና
199
ኢየሱስ! ይህ ስም የትሥጉቱን ምሥጢር እና ዓላማ ይገልጣል። ትርጉሙ፣ “እግዚአብሔር ያድናል”
ማለት ነው።
200
ዕብ 1፡2, ዮሐ 3፡17
201
Catechism of the Catholic Church, Part 1, sect. 1, Chap. 1: “All creatures bear a
certain resemblance to God, most especially man, created in the image and
likeness of God. the manifold perfections of creatures - their truth, their
goodness, their beauty all reflect the infinite perfection of God. Consequently
we can name God by taking his creatures perfections as our starting point, ‘for
from the greatness and beauty of created things comes a corresponding
perception of their Creator’"
59
እኛ በእርሱ ላይ በማመጽ ጠላቶቹ ስንሆን፣ እርሱ ሰው በመሆን ከእኛ ጋር
ዝምድናን መመሥረት ለምን አስፈለገው? ቅዱስ ዮሐንስ፣ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ
የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ
መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአል” ባለው መሠረት፣ የኩነተ ሥጋዌ ስር መሠረት
የእግዚአብሔር ፍቅር፣ ድምድማቱ የምእመናን ድነት ነው። መጀመሪያ በምሥጢረ
ትሥጉቱ፣ በኋላም በነገረ መስቀሉ ፍቅሩን ለዓለም ገለጠ። “የክርስቶስ መስቀል
202
እግዚአብሔር ፍቅሩን ለዓለም የሰበከበት ምስባክ ነው“ እንዲል አባ አውገስጢን። በዚህ
ዓላማ ማንም ግድ ሳይለው በራሱ፣ በአብና በመንፈስ ቅዱስ ፍቃድ ሰው ሆነ።

እግዚአብሔር ሰውን ሊፈጥር በወደደ ጊዜ፣ ከፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ አልቆና


203
አክብሮ፣ በራሱ መልክ (Imago Dei) ፈጠረው። በዚህ መሠረት ሰውን በሥነ ፍጥረት
ላይ እንደራሴ አድርጐ ሾመው፤ ሰውም በእግዚአብሔር መልክ የፍጥረታት ገዢ ሆነ። ይህም
ክቡር ዳዊት፣ “በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛህለት“
204
እንዳለው ነው። ሰው ለእግዚአብሔር አገልጋይ፣ ለፍጥረታት ገዢ በመሆኑ “የፍጥረታት
205
ዘውድ“ ይባላል። መኖሪያው በገነት፣ በነፍስ፣ በሥጋው ክቡር ነበር። በአእምሮ ከንቱነት፣
በስሜቱ ርኩሰት፣ በልቡናው አሉታዊ ፈቃድ አልነበረም። ዳግመኛም ልብሰ ብርሃንን
ተጎናጽፎ ነበር። ከሁሉ በላይ ከእግዚአብሔር ጋር ሕያው ግንኙነት ነበረው።

ሰው ክፉን በመውደድ፣ የማይገባውን በመምረጥ የእግዚአብሔርን ሥልጣን


ተጋፋ። የእግዚአብሔርን አምላካዊ ፍቃድ ከማገልገል፣ በራሱ ፍቃድ መኖር መረጠ።
በዚህም የውድቀት ምዕራፍ አሃዱ አለ። ኀጢአት አዳምን እና ሔዋንን ከእግዚአብሔር
ለያቸው። ከእግዚአብሔር መለየታቸው ደግሞ የችግራቸው፣ የፍዳቸውና የመርገማቸው

Peter Lombard, The sentences, Book 1, distiniction 1, Chap 3: “So great is His
goodness that He, as the Supreme Good, wanted others to sharers in His
blessedness, by which He is eternally blessed; He saw that this could be shared
and suffer no diminution at all.”
202
አትሮንስ (ፑልፒት)
203
ዘፍ 1፡27
204
መዝ 8፡6
205
Peter Lombard, The sentences, Book 1, distiniction 1, Chap 4: “Just as man was
made for God, that is, to serve Him, so the world was made for man, namely to
serve him. And so man was placed in the middle, so that he might serve and be
served; that he might take both and all might redound to the good of man;
both the obedience which he receives and that which he extends.”
60
ሁሉ መነሻ ምንጭ ነው። ከውብ መኖርያቸው መፈናቀል፣ የባሕርያቸው ጉስቁልና አሉታዊ
206
ፍርሃታቸው ሁሉ የዚህ ውድቀት ክትያ ነው። እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ እነርሱን መስለውና
አክለው የሚወለዱ ልጆቻቸው ሁሉ የውድቀታቸው፣ የበደላቸው፣ የብክለታቸው እና
የቅጣታቸው ተካፋይ ናቸው። ከባሕሪው መጎስቀል የተነሣ ሁሉ ጽድቅን ማረግ የተሳነው
207
(ሙውት)፣ ሥጋዊ፣ የአጋንንት መጠቀሚያ መሣርያ፤ የእግዚአብሔር ጠላት ሆነ።
ብክለት የአዳም ልጆች ሁሉ የባሕርይ ገንዘባቸው በመሆኑ፣ ከአዳም ከወረሱት ኀጢአት ሌላ
የግልና የቡድን ኀጢአት በመጨመር የሰው ልጆች በደልና ዓመፅ በየ ጊዜው እየበዛና እያደገ
ሄደ። ከእግዚአብሔርም ተጣልተውና ተለይተው ይኖሩ ነበር።

ፍቅረ እግዚአብሔር የሰጠን ክብር ይታወቅ ዘንድ የቀደመውን የባሕርያችንን


መዋረድ መናገር አለብን። ፍትሐ እግዚአብሔር በፍትሃዊ ዳኝነቱ፣ በማይሻር ውሳኔው
የሞት ፍርድ ስለበየነብን የሰው ልጅ በችግርና በመከራ ይኖራል፤ ባለ አእምሮ ሲሆን
አእምሮ በሌላቸው በእንስሳት ይመላለሳል፤ ለአጋንንት መዘባበቻ ሆነ፤ በመጨረሻም
ሥጋው ወደ መቃብር፣ ከሥጋው ጋር የማትፈርስ፣ የማትበሰብስ ነፍሱም ወደ ሲዖል
208
ትወርዳለች። በሲዖልም የእጦትን እና የስቃይን ድርብ ቅጣት ይቀበላል። ከዚህ የተነሣ
209
የአዳም ልጆች በሞት ፍርሃት፣ በርደተ መቃብርና በርደተ ሲዖል ተዋጡ።

ከዚህ የሞት ብያኔ ማን ሊያድነን ይችላል? ነቢያት? ራሳቸው የአዳም ዘር


በመሆናቸው ባለዕዳ ነበሩና ለራሳቸው መድሃኒት ፈላጊዎች ናቸው። በዚህ መሠረት
በተሰጣቸው ሀብተ ትንቢት ስለሚመጣው እውነተኛ አዳኝ አስቀድመው በማሳወቅ፣
ምጽአቱን ይጠባበቁ ነበር። መላእክት? ጥፋተኛው ሰው በመሆኑ የሌላ ፍጥረት አዳኝነት
ማሰብ የማይሆን ነገር ነው። በተጨማሪም፣ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ሲጣላ
የእግዚአብሔር ከሆኑት ጋር ተጣልቶአል። በዚህ ምክንያት ከእግዚአብሔር ፍትሃዊ ብያኔ
አፈንግጠው እኛን ሊረዱን አይችሉም። እንደውም ከመላእክት ውስጥ የአንደኛው መልአክ
210
ሥራ ሰው ተመልሶ ወደ ገነት እንዳይገባ በር መጠበቅ ነበር።

እንኪያስ ማን ያድነን? ሞትን በሕይወት መቀየር የሚቻለው፣ ከውድቀት


የሚያነሣ እግዚአብሔር ነው። ድነት በእግዚአብሔር ብቻ ነው (in solo Deo salus)። ኢ-

206
መዘዝ፣ ውጤት
207
ኤፌ 2፡1-3
208
Punishment of loss and punishment of pain
209
ርደት (ፍርሃት)
210
ዘፍ 3፡24
61
ውሱን ከሆነ ቅጣት ነፃ ሊያወጣን የሚችለው ኢ-ውሱን መለኮት ብቻ ነው። የውድቀት
ምዕራፍ ከፋቹ (የመጀመሪያው ኀጢአት) ሆነ ከዚያ በኋላ በአዳም እና በልጆቹ የተፈጸሙ
211
በደሎች ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ የተፈጸሙ ናቸው። የበደልነው እርሱን ብቻ ነው።
ይህን በማለት ኀጢአታችን እንደየ ዓይነቱ፣ እንደየ ደረጃው የሚጎዳው ሌላ አካል መኖሩን
በመካድ ሳይሆን፣ መለኮታዊ ክብር መናቁን ለማጉላት ነው። በዚህ መሠረት ኅጢአት
laesa Majestas- ታለቅ ክህደት ይባላል። ኀጢአትን ክፉ የሚያደረገው በማኅበረ-
ሰብዓችን የሚያደርሰው አስከትሎት ሳይሆን መለኮታዊ ክብር መናቁ ነው።

የእግዚአብሔር ማዳን ለምን አስፈለገ? እያንዳንዷ ኀጢአት የእግዚአብሔርን


አምላካዊ ሥልጣን ትጋፋለች። እያንዳንዷ ኀጢአት ኢ-ውሱን የሆነውን መለኮታዊ ክብር
ትንቃለችና ኢ-ውሱን ቅጣት ይገባታል። የኀጢአት መዘዝ ዘለዓለማዊ ቅጣት መሆኑ ለዚህ
ነው። የተበደለው ኢ-ውሱን መለኮት ነው፤ ስለዚህ በዳዩ ኢ-ውሱን ቅጣት ሊቀበል
ይገባዋል፤ ኀጢአተኛው በውሱን ማንነት ኢ-ውሱን ቅጣት ተቀብሎ ስለማይጨርስ፣ ቅጣቱ
ዘለዓለማዊ ይባላል። ከዚህ ኢ-ውሱን ቅጣት ነፃ ሊያወጣን የሚችለው ብቻውን ኢ-ውሱን
የሆነ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ዳግመኛም ቅዱስ ጳውሎስ፣ “በዋጋ ተገዝታችኋልና
ለራሳችሁ አይደላችሁም“ ባለው መሠረት፣ የትኛውም አካል ከዘለዓለም ሞት ቢቤዠን፣
ለተቤዠን አካል አገልጋዮች እንደምንሆን ግልጥ ነው። ከፍጥረታችን የእርሱ ነበርንና
በቤዛነት ወደ ራሱ ሊመልሰን የተገባው እርሱ ብቻ ነው።

እግዚአብሔር ሊያደርግ ያለውን አድኅኖተ ዓለም ከጥንት ጀምሮ በልዩ ልዩ


ጊዜያት በትንቢቶችና በምሳሌዎች ለአባቶቻችን ተናግሮ ነበር። ቀስ በቀስ፣ ደረጃ በደረጃ
በትንቢት ላይ ትንቢት፣ በምሳሌ ላይ ምሳሌን በማከታተል በምሥጢረ ሥጋዌና በነገረ
መስቀል ለሚፈጸመው ድነተ ዓለም እንዲዘጋጁ አድርጓል። በዚህ መሠረት ቅዱሳን አበው
212
ዘብሉይ ይህን ማዳን በመናፈቅ ይጠባበቁ ነበር።

ምን ትንቢት ተነግሮ፣ ምንስ ምሳሌ ተመስሎ ነበር? ቢሉ፦ ምን ያልተነገረ


ትንቢት፣ ምንስ ያልተመሰለ ምሳሌ አለ? የብሉይ መጽሐፍት ስለ ክርስቶስ ያልተናገሩበት
ምን አንቀጽ ይገኛል? ጌታችን ራሱ፣ “መጽሐፍት ሁሉ ስለ እኔ ይመሰክራሉ“ የሚል
አይደለምን? እንኪያስ ከቅዱሳት መጽሐፍት ክርስቶስን መፈለግ፣ ከባሕር ውስጥ ውሃ
እንደመፈለግ ነው።

211
መዝ 51፡4
212
የብሉይ አባቶች
62
ከጥልቅ ባሕር ጥቂት ውሃ እንደሚጠጣ ሰው፣ ከብዙ ጥቂቱን፣ እንደ ጉርሻ
ሳይሆን እንደ ቅምሻ እነሆ! ወንጌላዊ ዘብሉይ፣ ቅዱስ ኢሳይያስ እግዚአብሔር ከድንግል
በመወለድ ከሰዎች ጋር እንደሚኖር፣ ስቅዩ አገልጋይ በመሆን ስለ ሕዝቡ ኀጢአት መስዋዕት
እንደሚሆን በሀብተ ትንቢት ተናግሮ ነበር። ሆኖም እግዚአብሔር በእርሱ አድሮ ተናገረ
213
እንጂ ከራሱ አንቅቶ አይደለም። ለሕዝበ እስራኤል የተሰጡ የመሥዋዕት ሕግጋት
በምሥጢረ ሥጋዌ እና በነገረ መስቀል የሚፈጸመውን ድነት ልዩ ልዩ ገጽታ በምሳሌነት
ያሳያሉ።

ትንቢቱ በቤተ እስራኤል፣ እምነቱ በቤተ ክርስቲያን አለ። በአይሁድ ዘንድ


“ይወርዳል፤ ይወለዳል“ ተባለ፤ ፍጻሜው ግን በቤተ ክርስቲያን ታመነ። መዠመሪያ በቤተ
እስራኤል ተነገረ፤ ኋላም በቤተ ክርስቲያን ታመነ። እነሱ ጥላውን፣ እኛ አካሉን ያዝን።
እስራኤል ዘነፍስ ከእስራኤል ዘሥጋ በዚህ ይለያል።

[ኑሮ ይባል ከተባለ] በእንዲህ ዓይነት ኹኔታ እየኖርን ሳለን፣ ሕጸጽ አልባ ጥበቡ
የወሰነው የቀኑ ቀጠሮ ሲደርስ፣ ሥላሴ እኛን ከመርገም፣ ከፍዳ፣ ከዘለዓለም ኩነኔ ለማዳን
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰጠን። በእርሱ ላይ ብናምጽም በቸርነቱ ብዛት ወደ እርሱ
214
አቀረበን እንጂ ፈጽሞ አልተወንም። የዓለም ሠራዒ ቃል፣ ሥጋ በመሆን ዓለም ሊያድስ
መጣ።

ኀያል አምላክ በድካመ ሥጋ ለምን ተገለጠ? እኛን ያድን ዘንድ፣ ለእኛ ብሎ


አይደለምን? ሰው ሆይ፤ በፍቃድህ ከተወዳጀኸው ሞት ያድንህ ዘንድ የክብር ጌታ ለአንተ
215
ብሎ የመከራ ሰው ሆነ! ሰው ሆይ፤ የባሕርይ አምላክ ለአንተ ብሎ ባሪያ ሆነ! መከራን
ተቀብሎ፣ ሙቶ አንተን ሊያድን እንጂ ምልአት ሊሆነው አምላክ የባሪያን መልክ አልያዘም።
ይህን ሰምቶ የማያመሰግን ማን አለ? የሰውን ድነት የሚወዱ ደጋግ መላዕክት
ያመሰግናሉ፤ በአካለ ነፍስ ያለ የቅዱሳን ማሕበር ያመሰግናል፤ በአካለ ሥጋ ያለች ቤተ
ክርስቲያን ታመሰግናለች።

የመድሃኒታችን ሙሉ የሕይወት ታሪክ የማዳን ሥራ ነው። ከውልደት እስከ


እርገት ያደረገውና ያስተማረው ሁሉ ለእኛ ድነት ነው። ከሙላቱ በበረከት ላይ በረከት

213
ኢሳ 7, 9, 53
214
ዓለምን የሠራ
215
ስቅዩ አገልጋይ (The suffering servant)
63
216
እያከታተለ አትረፈረፈን። ከእነዚህም ከብዙ ጥቂቱን የጊዜ ቅደም ተከተላቸውን መሠረት
በማድረግ መዘርዘር እንጀምራለን። እንደ ጉርሻ ሳይሆን እንደ ቅምሻ እንዘርዝር እንጂ
ዘርዝረንስ ለመጨረስ አይቻለንም።

መዠመሪያ በኩነተ ሥጋዌ በእርሱ ድኽነት እኛ ባለጠጎች እንሆን ዘንድ እርሱ


217
ሀብታም ሆኖ ሳለ ለእኛ ሲል ድኻ ሆነ። የሰው ልጆች የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ
የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ሆነ። ሰዎችን ያድን ዘንድ ሰው ሆኖ መጣ። በትዕቢታችን
የወደቅን እኛን ያድን ዘንድ ራሱን አዋረደ፤ በአዳም ኅጥእ የሆንን እኛ በእርሱ እንጸድቅ
ዘንድ ዳግማዊ አዳም ሆነ።

ቀድሞ የሰው ክቡርነት በእግዚአብሔር መልክ (Imago Dei) በመፈጠሩ ይነገር


ነበር። አሁን ደግሞ አምላክ በመልኩ ተገልጦ እስኪሞትለት ድረስ የከበረ እንደሆነ ተሰበከ።
በዚህም ከቀደመው ይልቅ የሚበልጥ መምሰልን መሰለን። ከቀደመው የሚበልጥ ፍቅርና
ክብር ሰጠን። ሲፈጥረን ራሳችንን ሰጠን፤ ሲያድነን ግን ራሱን በመስጠት ነው።

ወልድ ሰው መሆኑ ጥቂት ክብር ያስገኘልን አይምሰለን! ይህንን ለመላእክት


አላደረገም። የመጣው መላእክትን ለመርዳት ሳይሆን ሰው በመሆን፣ ሰውን ለመርዳት
ነው። መላእክትን ትቶ፣ ወደ እኛ መጥቶ ባሕሪያችንን ባሕርዩ አደረገ። አብን በመልክ
የሚመስለው፣ በባሕርይ የሚተካከለው እርሱ ወንድሞቹን ከኋጢአት በቀር በሁሉ
218
መሰላቸው።

ዳግመኛም እርሱ ራሱ መጣ እንጂ ዙፋኑን ከበው ከሚቆሙ ከመላእክት ወገን


አንዱን አላከም። ነገር ግን፣ በአዳም ትእቢት ምክንያት ተዋርዶ የነበረ የሰውን ባሕርይ
ያከብር ዘንድ በሚያስደንቅ ትሕትና ሰው ሆነ። አምላክ ሰውን ሊያድን መውረድ፣
መወለዱን ያዩ ደጋግ መላእክት በደስታ አመሰገኑ።

መጥምቁ ዮሐንስ፣ “በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው፣ መንፈስ ሲወርድና በርሱ


ላይ ሲያርፍ የምታየው እርሱ ነው“ በተባለው መሠረት ሰው እንደመሆኑ በመንፈስ ቅዱስ
ተጠመቀ፣ አምላክ እንደመሆኑ በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃል። ሰው በመሆኑ መንፈስ

216
ዮሐ 1፡16
217
2ቆሮ 8፡9
218
ዕብ 2፡16-17
64
ቅዱስን ገንዘቡ እንደ አደረገ ቢነገርም፣ አምላክ እንደመሆኑ በታመኑት ሰዎች ሁሉ መንፈስ
ቅዱስን ያሳድራል።

ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ባሕርይ፣ አንድ ሥልጣን፣ አንድ ፍቃድ ገንዘቡ
ነው። ሁሉን በባሕርይ ሥልጣኑ ያከናውናል። ቅዱሳን አበው Uno animo et voca una-
በአንድ ልብ መካሪነት፣ በአንድ ቃል ተናጋሪነት- እንዳስተማሩት በመንፈስ ቅዱስ መጠመቁ
219
እኛ በእርሱ ሆነን የቅዱሱ ቅባት ተካፋዮች እንሆን ዘንድ እንጂ ለሌላ አይደለም።

220 221
ፍጹም በሆነ ገቢራዊ መታዘዝ ጽድቅን ሁሉ ፈጸመልን። በዚህም በእርሱ
እንጸድቅ ዘንድ ተቻለን። ዳግመኛም ፍለጋውን እንድንከተል አብነት ሆነን። በአዳም
አሉታዊ ፍቃድ ኀጢአት እና ክትያው ወደ ዓለም ገባ፤ በክርስቶስ ፍጹም መታዘዝ ኋጥኡን
222
በሚያጸድቅ በእግዚአብሔር የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቃሉ። ይህም ታላቁ ነቢይ፣
223
“ብዙዎቹን ያጸድቃል፤ መተላለፋቸውንም ይሸከማል“ እንዳለው ነው።

ነባቤ መለኮት፣ ወንጌላዊ ዮሐንስ፣ “አንድያ ልጁ አብን ገለጠው“ ባለው መሠረት


ዓለም በእርሱ አብን አወቀ። እርሱ ካልገለጠለት በቀር አብን የሚያውቅ የለም። ያለ እርሱ
የብሉይ ነቢያት፣ የሐዲስ ሐዋርያት ስለ እግዚአብሔር አንዳች ማለት ባልቻሉ ነበር፤ እርሱ
የአስተርዕዮአቸው ምንጭ፣ የስብከቶቻቸው አቀባይ ነው። እርሱ አብን የምናይበት
ብርሃናችን፣ የምናውቅበት ጥበባችን ነው። ያለ እርሱ ነገረ ድነት ብቻ ሳይሆን ትምህርተ
224
መለኮት የለም። ስለዚህ “ብርሃኔና መድሃኒቴ“ እያልን እንዘምራለን።

ዳግመኛም የክርስቶስን ትምህርትና መለኮታዊ ሥራ ያዩና የተረዱ ደቀ


መዛሙርቱ አብን በወልድ ሕልው ሆኖ ሲሠራ እንዳዩ ይቆጠራል። በዚህ መሠረት ጌታችን፣
”እኔን ያየ አብን አይቶአል” ይላል። አብን መግለጡ በቃልና በትምህርት ብቻ ሳይሆን
በእውነትና በተግባር ጭምር ነው።

219
St. Athanasius, Orat. 4 Chap. 36, Discourse 1, Chap. 12
220
Active obedience
221
ሮሜ10፡4
222
ሮሜ 4፡5, 5፡12-21
223
ኢሳ 53፡11
224
መዝ27፡1
65
ሥጋን ይዞ የቀረ አይደለም፤ ሕማምና ሞትን ተቀበለ እንጂ። ስቃይ ያልተለየው
225
በመሆኑ የሕማም ሰው ተባለ። በሞቱ ብቻ ሳይሆን በሕይወቱ ሙሉ በተቀበለው መከራ
ቤዛ ሆኖናል። “አገልግሎቱን በመራብ ጀመረ፤ ሆኖም እርሱ የሕይወት እንጄራ ነው።
አገልግሎቱን በጥም ፈጸመ፤ ሆኖም እርሱ የሕይወት ውሃ ነው። ተጨነቀ፤ ሆኖም እርሱ
እረፍታችን ነው። “አጋንንት አለበት“ ተባለ፤ ሆኖም አጋንንትን ያስወጣል። አለቀሰ፤ ሆኖም
እንባችንን አበሰ። ግብር ከፈለ፤ ሆኖም እርሱ ንጉሥ ነው። በሠላሳ ዲናር ተሸጠ፤ ሆኖም
ዓለምን ተቤዠ። እንደ በግ ለእርድ ተነዳ፤ ሆኖም እርሱ መልካም እረኛ ነው። ሞተ፤ በሞቱ
226
የሞትን ኋይል አጠፋ።“

ያልተቀበሉት መከራ ያደርሱበት ዘንድ ፈቀደላቸው፤ በደረሰበትም መከራ


የተቀበሉትን አዳነ። ይሁዳ አሳልፎ ሰጠው፤ የካህናት አለቆች አስያዙት። ክብርን እንደ ሸማ
የተጎናጸፈ እርሱ ዕርቃኑን በመስቀል ላይ ተንጠለጠለ። የማይታይ እርሱ ራቁቱን መስቀል
ላይ ታየ። ዠርባው ለግርፋት አልመለሰም። ንጹሐን እጆቹ፣ ክቡራት እግሮቹ ቆሰሉ፤
ተቸነከሩ። የዼንጤኑ ሰው ጲላጦስም በስላቅ “Jesus Nazarenus Rex Iudaeorum-
ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ“ የሚል ጽሕፈት በመስቀሉ ላይ አኖረ። ይህን ብታይ ፀሐይ
ብርሃኗን ነሣች፤ ፍጡራን ሁሉ በጨለማ ተያዙ። በዚህ ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቃድ በእጁ
227
ተከናወነ።

ፍጥረታት ሁሉ በእርሱ ዘንድ ኢምንት ናቸውና እግዚአብሔር የሁላችንን በደል


228
በእርሱ ላይ ጫነው። እርሱም ሁሉን በብቻው ደም አዳነ። በእኛ ፈንታ፣ “አምላኬ፤
አምላኬ፤ ለምን ተውኸኝ“ አለ። በውነት ለእኛ የሚገባ ሞትን በፍቃዱ እርሱ ተቀበለ።
በእርሱ ኋጥእ መባል እኛ ጻድቃን እንባል ዘንድ ኋጢአት የሌለበትን እርሱን ኋጥእ አሰኘው።
ዕዳ፣ በደል የሌለበት እሱ መካራ መቀበሉ ለዚህ ነው።

ሞት የነፍስ ከሥጋ መለየት መሆኑ እሙን ነው። ክርስቶስ ስለ እኛ እንደ እኛ


ሞተ፤ ነፍሱን ከሥገው በፍቃዱ ለየ። ወደ መቃብር መውረዱ በሥጋ ነው እንጂ በነፍሱ
አይደለም። ነፍሱ ከሥጋው ባትለይ እንዴትስ ሞተ ይባላል? መጽሐፍ እንደሚለው፣
“ነፍሴን በአንተ እጅ እሰጣለሁ“ ብሎ ነፍሱን ከሥጋው ለየ። ሥጋ ከመለኮቱ ሳይለይ

225
ኢሳ 53፡3
226
ታላቁ ጎርጎርዮስ
227
ኢሳ 53፡ 10
228
ኢሳ 53፡6
66
በመስቀል ላይ ቀረ፣ በመቃብር አደረ፤ ነፍሱም ከመለኮት ሳትለይ ወደ ሲኦል ወረደች።
ነፍሱ ከሥጋው ስትለይ መለኮቱ ግን ከሁለቱም አልተለየም።

ክቡር ዳዊት፣ “ነፍሴን በሲዖል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ


229
አትተወውም“ ሲል በተነበየው መሠረት፣ ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን ነፍሱን ከሥጋው
አጣምሮ ከሞት የተነሣ። ትንሣኤ የሞት መቀልበስ ነው። ሞት የነፍስና የሥጋ መለያየት
230
ከሆነ፣ ትንሣኤ የሁለቱ ዳግም መጣመር ከመሆን ውጪ ምን ሊሆን ይችላል? ሞትን
ገድሎ ከመቃብር ወጣ። ትንሣኤው የሞትን መሞት ያረጋግጣል። ከሞት እጅ መውጊያ፣
መግደያውን ቀማ፤ በግዛቱ የነበሩትን ነጻ አወጣ።

ሥጋችን ከምድር አፈር ያበጀውን በመበደሉ ወደ አፈር እንዲመለስ ተፈርዶበት


ነበር። “አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ“ የተባለ ሥጋችን በከርሰ መቃብር ተጥሎ
እንዳይቀር ቃል ሥጋ በመሆን፣ ወደ ከርሰ መቃብር ገባ፤ በዚያም ሞትን ድል ነሥቶ ወጣ።
ከሙታን ተለይቶ በተነሣ ጊዜ ፈርሶ፣ በስብሶ መቅረትን ፈጽሞ አጠፋ። ነፍሳችን ተድላ፣
ደስታ ካለበት ከገነት ተሰዳ፣ በሲዖል ከአጋንንት ጋር ቢያያት ከሰማያዊ ዙፋኑ ወረደ፤ በበረት
ውስጥ ተወለደ፤ የሲዖልን መሠረት አናውጦ፣ የገነትን በር ከፍቶ ከአስመለጣት። ነፍስን
በሲዖል፣ ሥጋን በመቃብር ረግጦ ከሚገዛው ሞት ነፃ አወጣን፤ ፃዕረ ሞትን አጠፋ። በሞት
ፍርሃት ፈንታ የትንሣኤን ተስፋ ሰጠን።

የቀድሞ የባሕሪያችንን መዋረድ አስቡ! የዲያቢሎስ ማታለል ሰውን ወደ መሬት


231
የመለሰች ናት። በእርሷም ሞት የባሕርይ ዕዳ (Debitum naturae ) ሆነን። በዚህም
ከእግዚአብሔር ተለይተን፣ በዲያቢሎስ ተረግጠን፣ ለሞት እጅ ሰጥተን ነበር። ውርደታችንን
ይሽር ዘንድ በተሸነፈ ባሕሪያችን ተገልጦ ድልን አቀዳጀን። በመለኮቱ ኀይል ዲያቢሎስን
አልተዋጋም፤ በሥጋ ድል አደረገው እንጂ። ሞትን በሥጋ ያጠፋ ባይሆን ባልተደነቀ ነበር።
ነገር ግን ባሕሪያችንን ያከብር ዘንድ የሕማም ሰው በመሆን ዲያቢሎስን ድል ነሣ።

ኋጢአትንና ክትያውን ሻረ፤ ኩነኔ፣ ጉስቁልና፣ መርገምን አጠፋ፤ ዲያቢሎስን ድል


ነሣ፤ ሥራውን አፈረሰ፤ ሲኦል ታወከ፤ ገነት ተከፈተ፤ ደጋግ መላእክት በሰው መዳን በደስታ

229
መዝ 16፡10
230
አንቀጸ ትንሣኤ
231
Debt of nature
67
ዘመሩ። በአዳም ካጣነው አትረፍርፎ መለሰልን። ይህም ሊቀ ሐዋርያት፣ ቅዱስ ጳውሎስ፣
“ኀጢአት በበዛበት ጸጋ አብልጦ የተትረፈረፈ ሆነ“ እንዳለው ነው።

ልብ በሉ! ክርስቶስ በእኛ ፈንታ በመሞት አዳነን እንጂ መለኮታዊ ፍርድ


አልተሻረም። በዚህም የእግዚአብሔር ፍርድና ፍቅር ተፈጸመ። በክርስቶስ የማዳን ሥራ
መለኮታዊ ፍርድ ሳይሻር መለኮታዊ ፍቅር ተገለጠ። በክርስቶስ መስቀል ካልሆነ
ከእግዚአብሔር ቁጣ መዳን ፈጽሞ የማይታሰብ ነው።

ስለ ዓለም ሁሉ የተሠዋ፣ ዓለሙን ሁሉ ከኋጢአት ያነፃ በግ እርሱ ነው።


የደመነፍስ ፍጥረታት መስዋዕትነት ለሰው ልጅ ካሳ መክፈል እንዴት ይችላል? በእርሱ፣
“የመሥዋዕቱ በግ ከወዴት አለ?“ የሚለው የዘመናት ጥያቄ ተመለሰ። “የመሥዋዕቱ በግ
232
ወዴት አለ?“ ለሚሉ Ecce agnus Dei- እነሆ የእግዚአብሔር በግ። የሚሠዋ አማናዊ
በግ እርሱ፤ የሚሠዋ እውነተኛ ካህን እርሱ ነው። ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም
መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው። እንደ በግ መሥዋዕት፣ እንደ ካህን መሥዋዕት አቅራቢ
በመሆን እኛን ከራሱ፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታረቀን።

እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ለማዳን የመረጠው መንገድ ፍቅሩን እና ጥበቡን


ይገልጣል። ዳግመኛም፣ “እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ፣ ዓለምን
ያዳነበት ጥበብ ይበልጣል።“ የክርስቶስ መስቀል የእግዚአብሔርን ጽድቅ፣ ምሕረት፣ ፍርድና
ፍቅር የሚገልጥ እንጂ የእግዚአብሔርን ክብር የሚቀንስ አይደለም። የክርስቶስ መስቀል
ብስራት እንጂ መርዶ አይደለም።

233
ክርስቶስ ፀሐየ ጽድቅ ነው። ወደ ቅዱስ አባቱ የሚያደርስ ጎዳና እርሱ ነው፤
ተድላ ነፍስ ወዳለበት የሚያገባ በር ነው። የተዘጋ የገነትን ደጅ የከፈተልን እርሱ ነው።
ስለዚህ “Salvator mundi- መድሃኒ ዓለም“ ይባላል። በእርሱ መስቀል ሲኦል ተነዋወጠች፤
መሠረቶቿም እፈርስ እፈርስ አሉ፤ ገነት ተከፈተ፤ የሰው ልጅ አመለጠ፤ ዓለም ከሲዖል
ተፋታ፤ ከሰማይ ታረቀ፤ ርኩሳን መናፍስት ታወኩ፤ ደጋግ መላእክት ደስ ተሰኙ።

“ይህን የሚያክል ብስራት ምን አለ? እግዚአብሔር በምድር፣ ሰው በአርያም፣ ያ


ረጅም ጦርነት አከተመ፤ በእግዚአብሔር በሰው መካከል እርቅ ሆነ፤ ዲያቢሎስ ተረገጠ፤
ሞት ተሻረ፤ ገነት ተከፈተ። እኝህ ነገሮች ጭራሽ የማይገቡን ነበሩ፤ ነገር ግን በምልዓት

232
ዮሐ 1፡36
233
የጽድቅ ፀሐይ
68
ተሰጡን። ይህም ለድካማችንና ለልፋታችን አይደለም፤ በእግዚአብሔር የተወደድን ስለሆን
234
እንጂ።“ ዓይን ያላያት፣ ዦሮ ያልሰማት፣ በሰው ልቡና ያልታሰበች፣ እግዚአብሔር በፍቅሩ
ያዘጋጃት ብጽእና ይህች ናት።

ዳግመኛም መላእክትን አስከትሎ ይመጣል። ለጻድቃን ሊፈርድላቸው፣ በኋጥአን


ሊፈርድባቸው ዳግም ይመጣል። አዎ! የሕማም ሰው የክብር ጌትነቱን ሊገልጥ ዳግም
ይመጣል። ኦ ታላቅ ተስፋ! የቅዱሳን ክብር፤ መንፈሳዊ ፌሽታ። ጌታ ኢየሱስ ዳግም
ይመጣል። ይህ የሙሽራይቱ [የቤተክርስቲያን] ተስፋ፣ የፍጥረታት ናፍቆት ነው። ለእርሱ
ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።

234
Thomas Aquinas, Catena Aurea, Intro
69
ዋቤ መጽሐፍት

Ambrose, De Fide. Trans. by H. De Romestin. New York: Christian


Literature Publishing, 1896

Anselm. Cur Deus Homo. New York: Forgotten Books Press, 2017.

Aquinas, Thomas. Summa Theologia. England: Cambridge


University Press, 2007.

Athanasius, Apologia Contra Arianos. Trans. By M. Atkison. New


York: Christian Literature Publishing, 1892.

Augustine of Hippo. The Trinity. New York: New City press, 2003.

Basil The Great. On The Holy Spirit. Crestwood. New York: St.
Vladimir’s Seminary Press, 2001.

Cyril Of Alexanderia. On The Unity Of Christ. Crestwood. New York:


St. Vladimir’s Seminary Press, 2005..

Gregory Of Nazianzus. Theological Orations. Crestwood. New York:


St. Vladimir’s Seminary Press, 2002.

Hilary Of Poitiers. On The Trinity. Independent Publishing, 2012.

Leo the Great. Letter 28: to Flavian (The Tome). Trans. by Charles
Lett Feltoe. New York: Christian Literature Publishing, 1895.

Lombard, Peter. The Sentences Book 1: The Mystery of the Trinity.


Trans. by Giulio Silano. Toronto: Pontifical Institute of
Mediaeval Studies, 2007.

70
Maximus. On The Cosmic Mystery Of Jesus Christ. Crestwood. New
York: St. Vladimir’s Seminary Press, 2003.

Origen, De principiis. Trans. by Frederich Crombie. New York:


Christian Literature Publishing, 1885.

Shenouda III. The Nature of Christ. Cairo: Dar El-Tebaa El-Kawmia,


1991.

Tertullian, Contra Prassea. Trans. By E. Evans. London 1948.

71

You might also like