Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 25

የአበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል

(ቲሹ-ካልቸርና ግሪን-ሀውስ)

ምስ/ጎጃም ቢቸና ከተማ

የፕሮጀክቱ ባለቤቶች፡አቶ ሄኖክ ኑርልኝ፤ዳዊት አስረስና ተክለዓብ በትሩ

ቀበሌ፡ 03

የካፒታል መጠን፡13950000 ብር

የፕሮጀክቱ ዓይነት፡ ምርት

ፕሮጀክቱ የሚተገበርበት ቦታ ስፋት፡9500 ካ.ሜ

ታህሳስ 2015 ዓ.ም

ቢቸና-ኢትዮጵያ
ቀን፡- 04/05/2015 ዓ/ም

አመልካች፡ ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት


ቢቸና

ጉዳዩ፡- የኢንቨስትምንት ቦታ እንዲሰጠን ስለመጠየቅ


በብቸና ከተማ አስተዳዳር 01 ቀበሌ ነዋሪ የሆንን አቶ ሄኖክ ኑርልኝ፤አቶ ዳዊት አስረስ
እና አቶ ተክነዓብ በትሩ ባለን የተለያዩ የቢዝነስ ሀሳቦና አቅም መሰረት ከተማ ማስዋብና
አረንጓዴ ስራ ለመሰማራት ወስነን ወደ ስራ በመግባችን እና ለከተማው ሆነ ለእኛ አገልግሎት
የሚሰጥ ደረጃውን የጠበቀ አበባ ልማት በመገንባት በውስጡም እንደ ውጭ ዛፎች፤አበቦች፤
ሳሮች፤ቀደምት ዝርያዎችን ወዘተ የሚሆን ደረጃውን የጠበቀ አበባ ልማት ለመገንባት በቂ
ዝግጅት ያደረግን ሲሆን ይህንንም ለመስራት ያለንን ሀብት ከራሳችንና ከብድር ተቋማት
በማሟላት በሂደት ላይ ስንሆን ለመስራት በፕሮጀክቱ ፕላንና እቅድ መሰረት 9500 ካሬ
ሜትር ቦታ በላይ የሚሸፍን በመሆኑ የፈለግንውን ቦታና ስፋት ተፈቅዶልን ለመገንባት
ያሰብለውን አረንጋዴና አበባ ልማት እንድንገነባ ስንል የተለመደ ትብብራችሁን
እንጠይቃለን፡፡
"ከሠላምታ ጋር"
የፕሮጀክቱ ባለቤቶችና ተጠሪዎች
ስም ስልክ አድራሻ ፊርማ
አቶ ሄኖክ ኑርልኝ 0912899065 ቢቸና 01 …………….
አቶ ዳዊት አስረስ 0920757243 ቢቸና 01 …………….
አቶ ተክነዓብ በትሩ 0913522526 ቢቸና 01 …………….

የኤችዲቲ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል የፕሮጀክት መረጃ


የፕሮጀክት ርዕስ፡ ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ማቋቋሚያ የፕሮጀክት

 የዒላማ ምርት: ምርት


 የሚተገበርበት ቦታ፡- ቢቸና ከተማ 03 ቀበሌ ከበ/ዘ/ከ/መ/ት/ቤት በስተደቡብ ገባ ብሎ
 የፕሮጀክት ጂኦግራፊያዊ ሽፋን: 9500 ሜ²
 ጠቅላላ የጠያቂዎቹ ድርሻ ገንዘብ መጠን 4185000 ብር
 ጠቅላላ የሚጠየቅ የብድር ገንዘብ መጠን 9765999 ብር
 ጠቅላላ የገንዘብ መጠን 13,950,000 ብር
 የድርጅት አይነት: ምርትና እና የሂደት ማዕከል

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 0|ገ ፅ


ማውጫ

ርዕስ ገፅ
1. መግቢያ 3

1.1 የፕሮጀክቱ አይነትና አቅርቦት 4

1.2 የፕሮጀክቱ ዓላማ 5

1.3. የፕሮጀክቱ ጥንካሬ፤ምቹ አጋጣሚና አዋጭነት 6

2. የፕሮጀክቱ አጀማመርና ትግበራ ምዕራፍ 13

2.1 የግንባታ እና የስራ ማሰኬጃ ዋጋ 20

2.2.የፕሮጅክቱ አዋጭነት ደረጃ 20

2.3. የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ 21

3.የፕሮጀክቱ ባለ ድርሻ አካላት 22

4.የማጠቃለያ 23

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 1|ገ ፅ


ስለፕሮጀክቱ አጭር መግለጫ

ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ወደ አገልግሎት ከመግባቱ በፊትና በኋላ ሊሰጥ የታቀደውና ያካተታቸው


በከተማችን ውስጥ ያሉ ችግሮችን እና አስፈላጊ መሰረታዊ ነገሮችን በማጤንና ለህብረተቡም
ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የታሰበ ሲሆን በመጀመሪያ የፕሮጀክቱ አይነትና
አቅርቦት ፕሮጀክቱ ሲታቀድ በከተማው ውስጥ ያለውን የአረንጓዴ ልማት ችግርና የከተማ
ውበት ለመቅረፍ እና በተመጣጠነ ዋጋና ጥራት ባለው መልኩ ለተጠቃሚው ተደራሽ ማድረግ
ሲሆን ፕሮጀክቱ ሊጀመር የታቀደበት ካፒታል 13950000 ብር ሲሆን አረንጓዴ ልማቱ
በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር ለመግባትና ለሌሎችም በአማካይ ለ80 ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ
የስራ እድል የሚፈጠርበት ፕሮጀክት ነው፡፡ ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድረግ ያለው ምቹ
ሁኔታዎች እና አዋጭነት ከተማው ሰፈና ይህንን ስራ ፈላጊ የህዝብ ቁጥር መጨመርና
ለማህበረሰቡ የጠበቀ በቴክኖሎጅ የታገዘ የአበባ ልማት ማስፈለጉና ሌሎችም ሲሆኑ
የፕሮጀክቱ አጀማመርና የተግበራ ምዕራፍ ለግንባታው ሂደት ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች
እና ጥራት ባለው ማቴሪያል ተጠቅሞ ወደ ተፈለገው አገልግሎት ለመግባት በስነ ምግባር
የታነጹ ባለሙያዎችን በመቅጠር ወደ ተግባር መግባት ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ የሚመጡ
ስራውን አደናቃፊ ነገሮችና ማቃሊያ ዘዴዎች ከሚመለከታቸው ጽ/ቤትጋር በመሆን
እሚከናወኑ ሲሆኑ በማጠቃሊያም አጠቃላይ የፕሮጀክቱን ሃሳብ አላማና ውጤቱ ተገልጾል፡፡

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 2|ገ ፅ


1. መግቢያ
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከነበራት ኋላቀርነትና ድህነት ተላቃ በኢኮኖሚም ሆነ በተለያዩ ማህበራዊ
እሴቶች እያደገች የምትገኝ ሀገር እንደመሆኗ ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ዜጎች በተለያዩ
የሥራ መስኮች በመሳተፍ የዚህ እድገት ተቋዳሽ መሆን እንደሚያሰፈልጋቸው አከራካሪ
ጉዳይ አይደለም፡፡

የሀገራችን እድገት በማፍጠን ረገድ ጉልህ አስተዋጾ ከሚያበረክቱ የኢኮኖሚ ክፍሎች ውስጥ
ደግሞ ዋናውና በመጀመሪያ ደረጃ የሚገኘው ግብርናው ሲሆን ከተማ ውበትና አረንገዋዴ
ልማት ደግሞ የማይተካ ድርሻ አለው፡፡ በተለይም በእንደዚህ አይነት ፕሮጀክቶች
መሳተፋቸው የፕሮጀክቱ ውጤታማነት እጅጉን የሚጨምር ይሆናል፡፡ በመሆኑም በዚህ ቦታና
ጊዜ መገንባቱ ተጠቃሚውን ከእዛው ከማህብረሰቡ ዘንድ በማዳረስ በቀላሉ አመች መሆኑ
አጠያያቂ ጉዳይ አይሆንም፡፡

በተለይን በአሁኑ ስዓት በወረዳችን ያለውን ስራ አጥነትና ድህነት ለመቀነስ ወደ ተሻለ ደረጃ
ሊያሸጋግራቻው የሚችለውን መንገድ በማጥናትና በመገንዘብ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች
በመሳተፍና የኢኮኖሚ አድማሳቸውን ማስፋፋት ግድ ይላቸዋል በመሆኑም ይህ የፕሮጀክት
ፕሮፖዛል ጹሁፍ ሲዘጋጅ የአበባ ልት ብቻ ሳይሆን የላንስድኬፕ ማስዋብ ስራዎችንም
በመስራትና ሌሎች በአካባቢው ያሉ ዝርያዎችንም በማላመድ ወሳኙ የፕሮጀክቱ ግባቱ
የሚያስችል ግንባታ ላይ ለማተኮር በንድፍ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን በተግባር ዙሪያም ስለአፈጻጸሙ
ጠቃሚ አስተያየትና የአሰራር መርሆችን አካቶ የያዘ ተግባርና መመሪያ በመሆኑ በአግባቡ
ተግባር ላይ እንዲውል ከተደረገ በመጀመሪያ የፕሮጀክቱ ባለቤት በመቀጠልም በመስኩ
የሚሰማሩትን ባለሙያዎችን እና ሰራተኞችን እንዲሁም ተገለጋዮችን የአካባቢውን
ህብረተሰብ በአስተማማኝ መልኩ ተጠቃሚ ያደርጋል የሚል ሙሉ እምነት አለን፡፡ አንድ
የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ሲቀረጽ በሁለተናዊ መልኩ የተዋጣለት ሊሆን የሚችለውና ተግባራዊ
ለማድረግ አመች የሚሆነው ከፁሁፍ ባሻገር በባለድርሻ አካላት ጠቃሚ አስተያየት
በመስጠትና ገንቢ ምክሮችን በመለገስ ለሚሳተፉ ግለሰቦችም ሆነ መንግስታዊ ተቋማት
አስተዋጾቸውን በአወንታዊ መልኩ የምንቀበለው በመሆኑ ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 3|ገ ፅ


1.1 የፕሮጀክቱ አይነትና አቅርቦት

ፕሮጀክቱ በመግቢያው እንደተጠቀሰው ዘርፈ ብዙ አግልግሎት የሚሰጥ የአበባ ልማት


መክፈትና ተያያዠነት ያለው አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይታሰባል፡፡

ፕሮጀክቱ በዚህ መልኩ ተቋቁሞ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የድርጅቱን ባለቤትም ሆነ


የአካባቢውን ማህብረሰብ ለተሻለ መንገድና በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያደርግ ይገመታል፡፡

ይህ ፕሮጀክት የአስፈለገበት ምክንያት በከተማችን ላይም ሆነ በወረዳው አልፎ የሚሄድና


አጎራባች ወረዳዎች ላይ ያለው የአረንገዋዴ እና አበባ ምርት ተጠቃሚዎችም ሆነ ምርቶች
የሚጠቀም በብዛት ስለሚገኙና አገልግሎቱን ይበልጥ በማሳደግ ተጠቀሚነትን በማስፋት
በተለይም የሆቴል፤ፍብሪካ፤አፓርምንቶች፤የገበያ ሞሎች፤መኖሪያ ቤቶች ወዘተ
ባለንብረቶችን ተጠቃሚነት እጅጉን የሚጨምርና የአካባቢውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና
ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታና በተመጣጠነ ዋጋ ለህዝቡ ብሎም ከውጭ የሚገቡ ዝርያዎችን
ለማስቀረት እድልን የሚፈጥር አስተማማኝ አበባና አረንጓዴ ልማት አገልግሎት ተደራሽ
በማድረግ የከተማችንን ገፅታ ለመቀየር ነው፡፡ በመሆኑም ፕሮጀክቱም ተግባራዊ በማድረግ
ይህን ሊበረታታ የሚገባው አላማ ለማሳካት ያስችል ዘንድ፤

 የፕሮጀክቱ ባለቤት
 የሚገኝበት ቦታ
 የታቀደለት አላማ
 ሊሰጡ የሚችል መሰረታዊና ተያያዠ አገልግሎት
 የአዋጭነት ሁኔታ የመሳሰሉት ዝርዝር ይዘቶች እንዲሁም ጉዳዩን ለመፈጸም ያሉት
ምቹ ሁኔታዎችና ስጋቶች ከነአማራጮቹና መፍቴዎች በአጭሩ በዝርዝር
እንደሚከተለው ቀርቧል፡

የፕሮጀክት ባለቤት

ስም አቶ ሄኖክ ኑርልኝ፤ ዳዊት አስረስና ተክለዓብ በትሩ


አድራሻ፡ ብቸና ከተማ 03 ቀበሌ
ስልክ፡ 0912899065/0920757243/0913522526
የስራ መስክ፡ የአበባና አረንጓዴ ልማት

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 4|ገ ፅ


የፕሮጀክቱ ባለቤት እስካሁን በራሳቸው ጥረት ያፈሩትን ሀብትና እውቀት ተጠቅመው
እና ከመንግስት ድጎማና ብድር በመጠቀም ይህን የተቀደሰ አላማ ከግብ ለማድረስ
ቆርጠው የተነሱ ሲሆን ለወደፊቱ ይህን ፕሮፖዛል ጸድቆና የስራ ማከናወኛ መስኩ
የሚፈቀድ ቢሆን የታቀደውን ግንባታ በአጭር ጊዜ አጠናቆ ተገቢውን አገልግሎት
በመስጠትና የካፒታል አቅሙን በማሳደግ የከተማውን ቀጣይ እድል በመልካም ገጽታ
በመቀየር የአካባቢው ተቆርቋሪዎችን በተግባር ማረጋገጥ የሚችል አኩሪ ፕሮጀክት
በመሆኑ ሊበረታታ ይገባዋል፡፡

ፍቃድ የተጠየቀበት የንግድ ዘርፍ

 የአበባና አረንጓዴ ልማት አገልግሎት መስጠት

1.2 የፕሮጀክቱ ዓላማ

ባለቤቱ በዚህ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል መሰረት በሚፈቅደው ቦታ ላይ ደረጃውን የጠበቀ የአበባና


አረንጓዴ መስርቶ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ የባለቤቱን ገቢ ማሳደግ ለስራ ፈላጊዎች፣
ለደበኞች እና ለአካባቢው ባለንብረቶች ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት ለአካባቢው እድገት
ጉልህ አስተዋጾ ማበርከት ነው፡፡

ሊፈጸም የታቀደበት ቦታ ም/ስ/ጎ/ዞን እነ/ወረዳ ቢቸና ከተማ 03 ቀበሌ

የካፒታል መጠን 13950000 ብር

1 አበቦችና አረንጓዴ እፅዋቶች - 6000000 ብር

2 ለመሰረተ ልማቶች- 2000000 ብር

3 ማጓጓዣ መኪና- 1450000

4. ለግንባታ- 300000 ብር

5 ለመገልገያ ግብዓት፣ቁሳቁሶችና ለሰራተኛ ደሞዝ - 1000000 ብር

ለልዩ ልዩ ወጭ- 500000 ብር

ጠቅላላ ድምር- 13950000 ብር

የመፈጸሚያ ጊዜ ፕሮፖዛል ፀድቆ ስራው ከሚፈቅድበት ጊዜ አንስቶ እስከ አንድ ዓመት


ከስድስት ወር ባለው ጊዜ ይሆናል፡፡

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 5|ገ ፅ


የፕሮጀክት አይነትና አመዳደብ ፕሮጀክቱ ከላይ በተጠቀሰውና ከተማው ውስጥ በሚገኘው
9500 ካ.ሬ ሜትር ቦታ ላይ ዘመናዊ የአበባና አረንጓዴ ለማምረት የሚውል የተለያዩ ክፍሎች
ያሉት ግረን ሀውስ ግንባታ የሚገነባ ሲሆን የክፍል ምደባዎችም፤

ሀ/ ለአበቦች ማስቀመጫ 3000 ካ.ሬ ሜትር ቦታ

ለ/ ለአረንጓዴ እፅዋቶች ማስቀመጫ 3000 ካ.ሬ ሜትር ቦታ

ሐ/ አበባና አረንጓዴ እፅዋቶች ማሳያ ቦታ 500 ካ.ሜ ቦታ

መ/ ለአንዳንድ እጽዋቶች ፕሪዘርቮሽን ማድረጊያና ማከማቻ 500 ካ.ሜ ቦታ

ሠ/ ለአበባና አረንጓዴ እፅዋቶች ማራቢያ 500 ሜትር ቦታ

ረ/ የተለያዩ መሳሪያዎች ቢሮና መካዘን 100 ካ.ሬ ሜትር ቦታ እንዲሁም የመሄጃ፤መለያ፤


ክፍት ቦታዎች 1900 ካ.ሬ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን

አጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩት አገልግሎቶችን ሊሰጥ የሚችል ዘመናዊ ግንባታ ገንብቶ


በፍጥነት ወደ ስራ መግባት ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሌሎች አገልግሎቶች በቀጣይነት
እንዲስፋፋ ይደረጋል ተብሎ ይታሰባል፡፡

ይህን ፕሮጀከት በዘመናዊ መልኩ የሚገነባዉ የአበባና አረንጓዴ ልማት ግንባታ ስራዉ
ሲጠናቀቅና አገልግሎት ላይ መዋል ሲጀምር የፕሮጀክቱን ባለቤት የኢኮኖሚ አቅም
በማሻሻልም ሆነ የአካባቢውን ማህበረሰብ ልማት በማፍጠን ረገድ የጎላ አስተዋጾ
እንደሚኖረው ያሳያል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ያስፈለገበት ዋና ምክንያት በከተማችን ቢቸና ብዙ አገልግሎቱን ፈላጊና


ለዚሁ አገልግሎት ወደ አ/አበባ፤አዳማና ባህርዳር የሚሄዱ ብዙ ባለንብረቶች የሚኖሩ በመሆኑ
ይህን ዘመናዊ የአበባና አረንጓዴ በአካባቢው መክፈቱ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ
ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን በቅርበትና በተመጣጠነ ዋጋ ተደራሽ በማድረግ
የህብረተሰቡን እድገት ለማማምጣት የሚያስችል የተሻለ አማራጭ ይሆናል ተብሎ
በመታመኑ ነው፡፡

1.3. የፕሮጀክቱ ጥንካሬ፤ምቹ አጋጣሚና አዋጭነት

ሐ.ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማደረግ ያለው ምቹ ሁኔታና አዋጭነት

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 6|ገ ፅ


 የአበባና አረንጓዴ በዚህ ቦታ የታቀደበት ዋነኛው ምክንያት በከተማውና አጎራባች
ከተማዎችም ውጤታማ የሆነ ደንበኛ መኖሩ እጅጉን አመች በመሆኑ
 የአበባና አረንጓዴ ሊከፈትበት የታሰብው ቦታ አጎራባች ከተሞች ከአ/አበባ ወደ
ባ/ዳርና ጎንደር መተላለፊያ መስመር ኮሪደር ስላሉና በሁሉም አቅጣጫ አመች የሆነ
መንገድ መሆኑን በርካታ አገልግሎት ፈላጊዋች መኖራቸው
 በአካባቢው ሰላምና ጸጥታ የሚያበረታታ አመራርና የአስተዳድር ስርዓት መኖሩ
 ለስራው የሚያስፈልገው ገንዘብ በእራስ አቅም የሚገኝና በመንግስት ድጋፍ በመሆኑ
 የአበባና አረንጓዴ ግሪን ሀውሱን ለመገንባት አስፈላጊውን ቁሳቁስ አሟልቶ የአበባ
ልማት በመክፈት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ከማንኛውም ግለሰብ የይግባኝ
ጥያቄ ነጻ የሆነ ሰፋ ያለ ክፍት ቦታ የሚገኝ መሆኑና
 በከተማው ዙሪያ ላሉ 80 ስራ ፍላጊዎች የስራ እድል የሚፈጥር በመሆኑ

በአጠቃላይ ለስራው የሚያስፈልገው በጀት በጠቅላላ ከላይ እደተጠቀሰው ብር 13950000


ብር፡፡

የበጀት ምንጭ ከራሱ (30%) ከፕሮጀክቱ ባለቤት እና ከመንግስት ብድርና ድጋፍ (70%)
በሚገኝ መነሻ ካፒታል

ፕሮጀክቱ የሚፈጥረው የስራ እድል

ፕሮጀክቱ ሲገነባ የሚፈጥረው የስራ እድል

በጊዜዊ የሚሰሩ ሰራተኛ ብዛት 65

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ወይንም በቋሚነት የሚሳተፈው የሰው ሀይል 15

1. 1 ስራ አስኪያጅ

2. 10 አበባ የሚንከባከቡ

3. 10 የሚያዳቅሉ

4. 2 የክትትልና ድጋፍ ባለሙያ

5. 1 ገንዘብና እንግዳ ተቀባይ

6. 1 ጥበቃ

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 7|ገ ፅ


በድምሩ በቋሚነት 15 የሰው ሀይል በአጠቃላይ 80 የሰው ሀይል ይዞ ነዋሪዎችን መንግሰታዊ
ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሰራተኞች ነጋዴው ማህበረሰብ እና እንግዳ ተደራሾችም
እና ሌሎች በአጠቃላይ በሚፈቅደው ፕሮጀክት ሊገኝ የሚችለው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ
ሀገራዊ ፋይዳ ለዜጎች ስራ እድል መፈጠር

 የከተማውን እድገት ለማፋጠን ትልቅ አስተዋጾ ማበርከቱ


 በሚገኘው ጥቅም ልክ የተሻለ ግብር የሚከፈል መሆኑ
 ኢኮኖያዊ ፋይዳው የፕሮጀክቱ ባለቤት አትራፊ ማድረግና የድርጅቱን ገቢማሳደግ
 ማህበራዊ ፋይዳው የአካባቢውንም ሆነ ሌሎችን ሰዎች ስራ እድል መፍጠር የአካባቢ
ኗሪዎች ዘመናዊ የአበባና አረንጓዴ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው፡፡
 በተለያዩ የስራ ምክንያቶች እንገዶች ሲመጡ አካባቢው ኗሪዎች በተለይም ባለሀብቶች
እንዲሁም ለሁሉም ፈላጊ ማህበረሰብ ዘመናዊ በሆነ መንገድ ማቅረብ መቻል

ስዕል፡ የአበባና አረንጓዴ ልማቱ እቅድ ውጤት እይታ

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 8|ገ ፅ


ስዕል፡ የአበባና አረንጓዴ ልማቱ ግሪንሀውስ እቅድ ውስጣዊ እይታ

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 9|ገ ፅ


ስዕል፡ የአበባና አረንጓዴ ልማቱ ማስቀመጫና ድቅያ እቅድ ውጤት እይታ

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 10 | ገ ፅ


ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 11 | ገ ፅ
ስዕል፡ የአበባና አረንጓዴ ልማቱ አንዳንድ እጽዋቶች እቅድ ውጤት እይታ

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 12 | ገ ፅ


የፕሮጀክት መግለጫ እና አጠቃላይ እይታ
ስለ ፕሮጀክቱ
የታቀደው አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት በምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቸና ከተማ ቀበሌ 03 ውስጥ
በሚገኘው አካባቢ በድምሩ 9,500 ሜትር ካሬ ቦታ ላይ ይገነባል። የተጠቀሰው ቦታ ከከተማ
ዋና መንገድ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ከ20-30 ሜትር መንገድ ላይ የሚገኝ ነው፡፡

ቢቸና ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ጋር በጥሩ ሁኔታ የተገናኘው በመንገድ ጥሩ የትራንስፖርት


አገልግሎት ነው። በቢቸና በኩል የሚያልፍ የአስፓልት መንገድ አለ፣ እሱም ከተለያዩ
የገጠር ከተሞች እና ክልሎች ማለትም ከባህር ዳር እና ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን እና ደቡብ
አቅጣጫ ስለሚገኝ ለስራው አመቺ ይሆናል፡፡

የታቀደው ፕሮጀክት የአበባና አረንጓዴ ልማት ግንባታ ነው ስለዚህ የከተማውን መሬት


ክሊራንስ ከቢቸና ከተማ የቤትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በመጠየቅ የታቀደው አበባ ልማት
ፕሮጀክት መስራት ይቻላል፡፡

የስራ ሂደት/እርምጃዎች
ሀገራዊ ደረጃውን የጠበቀ አበባና አረንጓዴ ለመገንባት የሚያስፈልጉ አስፈላጊ እርምጃዎች
የሚከተሉት ናቸው።

የመሬት ይዞታ ማግኘት


የአዋጪነት ጥናት መስራት
የገበያ እና የፋይናንስ ትንተና እና ትንበያዎች
በባንኮች ወይም ባለሀብቶች የገንዘብ መዝጋት
ዲዛይን መስራትና ማረጋገጥ
የጣቢያ ቅኝት ማጠናቀቅ, የእጽዋት፤ሕንፃዎች ንድፍ, የሜካኒካል
መገልገያዎች, የኤሌክትሪክ አገልግሎቶች እና ስርዓት መዘርጋት.
እንደ የግንባታ የውሃ መስመሮች, የኤሌክትሪክ መስመሮች እና የፍሳሽ
ማስወገጃዎች, ቢሮ, የጉልበት ካምፕ ያሉ ስራዎችን ለማንቃት ማቀድ;
አቀራረብ እና የውስጥ መንገዶች
የሰራተኛ መቅጠር ሂደት
ግብይት

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 13 | ገ ፅ


የቦታ እና ካርታ ስራ በተመለከተ
የታቀደው የፕሮጀክት ቦታ በቢቸና ከተማ 03 ቀበሌ ይገኛል። የተጠቀሰው ቦታ ከቢቸና
ከተማ ማዕከል በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ 500-1000 ሜትር በመንገድ ላይ ይገኛል፡፡

ምስል: የተከበበችው ቦታ ፕሮጀክቱ የታሰበበት ሳተላይት ላይ እይታ

Pt, E:(m.), N:(m.), Z:(m.), Height(m.)

1, 412971.74, 1154323.38, 2528.50, 2533.45

2, 412896.52, 1154284.03, 2520.00, 2525.02

3, 412863.28, 1154233.38, 2518.40, 2523.50

4, 412882.79, 1154207.16, 2516.00, 2521.04

5, 412920.57, 1154210.61, 2516.00, 2521.22

6, 412971.42, 1154234.87, 2521.50, 2526.32

7, 412960.49, 1154258.11, 2521.00, 2526.26

8, 412994.65, 1154303.37, 2520.00, 2524.57

ምስል: የፕሮጀክቱ ኮርዲኔትና ትሪያንጉሌሽን ጂፒኤስ ፕላን

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 14 | ገ ፅ


የፕሮጀክቱ ቦታ ባዶ መሬት ነው. የታቀደው የፕሮጀክት ቦታ ከግለሰብ ድርጅትና ማንኛውም
ይዞታ ነፃ ሲሆን በለጋሽ ድርጅቶች፤እስታዲየም፣መኖሪያ ቤትና ክፍት ቦታዎች የተከበበ
ነው. ከታች እንደሚታየው የፕሮጀክቱ ቦታ የቅርብ ጊዜ ፎቶዎች:

ምስል፡ ፕሮጀክቱ የታሰበበት ቦታ አሁን ላይ ያለበት ሁኔታ በፎቶ

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 15 | ገ ፅ


ምስል፡ ፕሮጀክቱ የታሰበበት ቦታ አሁን ላይ ያለበት ሁኔታ በፎቶ

የድርጅት የሰው ኃይል እና የሥልጠና መስፈርቶች


ሪዞርቱ ለአገልግሎት ስራው የሰው ሃይል 80 ሰዎችን በግዜያዊና ቋሚነት ይፈልጋል።

የፕሮጀክቱ ድርጅታዊ መዋቅር የተነደፈው ሁሉንም አስፈላጊ የሰው ሀይል በትክክለኛው


ክፍል ውስጥ በማካተት ነው. በድርጅታዊ መዋቅር አናት ላይ የፕሮጀክቱን አጠቃላይ

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 16 | ገ ፅ


እንቅስቃሴ የመቆጣጠር ሃላፊነት ያለው ዋና ሥራ አስኪያጅ ይኖራል. እንደ ማዕከሉ ባህሪ
እና በእያንዳንዳቸው ስር የሚሰራው ስራ መጠን የሚቆጣጠረው ለጠቅላላ አመራሩ ተጠያቂ
በሆነው ክፍል ኃላፊ ነው።

ማናጀር

አቴንዳት ምስ/አስኪያጅ

ምርትና
ገንዘብ ያዥ የሰው ሀይል ደንበኞች አያያዝ ጥበቃ
እንክብካቤ ክፍል

ጉልበት ሰራተኛ የጥራት ቁጥጥር

ቻርት: የፕሮጀክቱ አደረጃጀት ሰንጠረዥ

2. የፕሮጀክቱ አጀማመርና ትግበራ ምዕራፍ


እያንዳንዱ ግንባታ ፕሮጀክት በቂ ክትትል ካልተደረገለት እንዲሁም የአሰራር ሁኔታዎች
በቅርብ እርቀት ሆኖ መከታተል ካልተቻ በአግባቡ ስራውን ማስኬድ እንደሚገባና ደረጃውን
በጠበቀ መልኩ የሰው ሀይል በመመደብና የስራ ዝርፍ በመስጠት የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን
በማቅረብና በመቆጣጠር የፕሮጀክቱን ትርፋማነት መጨመር፡፡

በዚህ መሰረት የዚህ ፕሮጀክት አስፈላጊ ሁኔታዎችና የክዋኔ ሂደቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 በመጀመሪያ በሚከፈተው የአበባና አረንጓዴ ተያያዠ የአገልግሎት ዘርፎች ውስጥ


ተጠቀሚ ሊሆኑ የሚችሉ ደበኞችን ፍላጎትና ፍሰት በተመለከተ ገብያ በማጥናት
 በመቀጠል የአበባና አረንጓዴ አገልግሎት የሚከፈትበትን 9500 ካ.ሬ ቦታ ተገቢውን
የዲዛይንና ፕላን ፐሮፖዛል በባለሙያ አስርቶ በማቅረብ የግንባታ ሂደቱን ማስፈቀድና
በተበጀተለት በጀት አስፈላጊውን ቁሳቁስ በማቅረብ የቴክኔሎጅ ውጤት የሆኑትን
የግንባታ ግባቶች አቅርቦ ግንባታውን ማስጀመር
 በመጨረሻም ግንባታዎችን ተከታትሎ በፕሮጀክት የተነደፉ ስራዎችን ብቃት ባላቸው
ባለሙያዎች ገንብቶ በብቃትና በስነ-ምግባር የተሞሉ ሰራተኞችን በመቅጠር ስራውን
ማስጀመር ዋነኞች ሲሆኑ እነዚህንም እንደሚከተለው በዝርዝር እንመለከታለን

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 17 | ገ ፅ


 የመጀመሪያውን የገብያ ጥናት ተግባር በተመለከተ በአንድ የንግድ ስራ መስክ
ከመሳተፋችን በፊት ስራው አዋጭነው ወይንስ አይደለም ተፈላጊነቱስ ምን
ያህል ነው ዘላቂነቱና አስተማማኝነቱስ በሚሉት መሰረታዊ መመዘኛዎች
አስገብቶ መመልከት ተገቢ ነው ምክንያቱም በእነዚህ መስፈርቶች ተለክቶ
ውጤታማነቱን ካልተረጋገጠ ኪሳራው ስለሚያመዝን፡፡
 የመስሪያ ቦታ በተመለከተ ጥሩ የመስሪያ ቦታ አስቀድመን ካዘጋጀን የአበባና
አረንጓዴ ምንጭ የሆኑትን ቦታ ገንብቶ ምን ያህል ዘላቂ ጥቅም እንዲሚሰጥ
መርዳት በመሆኑም ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡
 ህንጻው ተግንብቶ ካለቀ በኋላ የአበባና አረንጓዴ ልማት ሂደቱን በጠበቀና
በእውቀትና በስነ-ምግባር በታነጹ ባለሙያዎች ስራውን መስራትና መቆጣጠር
ይገባል፡፡

ፕሮጅክቱ እነዚህን ጠቃሚ ሂደቶች አልፎ ከግብ ከደረሰ በኋላ አስፈላጊ እቃዎችን እና የሰው
ሀይል ስምሪት በፍጥነት በማሟላት አበባና አረንጓዴ ልማት እና ሌሎች አገልግሎቶች
ለደበኛውና ለተጠቃዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ባለው ሁኔታ ማቅረብ መቻል

አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች


እነዚህ ከታች የተጠቀሱት ማቴሪያል የአበባና አረንጓዴ ልማት ምቹና ቀልጣፋ የሚያደርጉ
ግብኣቶችና የሌሎች እቃዎች ስብስብ ናቸው፡፡ለምሳሌ የውች ዝርያዎቸ፤ሀገርኛ
እጽዋቶች፤ ማስቀመጫዎች፤ ግሪን ሀውሶች፤አውቶማቲክ ማጠጫዎች ወዘተ
የመሳሰሉት ነገሮች ለስራው መቅናት በጣም አስፈላጊና ወሳኝ እቃዎች ናቸው፡፡

ስዕል፡ ለአበባና አረንጓዴ ቤቱ የሚያስፈልጉ የእጅ መስሪያ ማቴሪያሎች

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 18 | ገ ፅ


ስዕል፡ ለአበባና አረንጓዴ ቤቱ የሚያስፈልጉ ማጠጫ መሽኖች

ስዕል፡ ለአበባና አረንጓዴ ቤቱ ፕራስቲክና ማስቀመጫ ማምረቻና ማሸጊያ ማሽን

ስዕል፡ ለአበባና አረንጓዴ ቤቱ እቃ፤አበባና ሌሎች ነገሮች ማመላለሻ መኪና

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 19 | ገ ፅ


2.1 የግንባታ እና የስራ ማሰኬጃ ዋጋ

የአበባና አረንጓዴ ልማት ግንባታው በ8000 ካ.ሜ ቦታ ላይ የሚያርፍ ሲሆን እያንዳንዱ


አስፈላጊ ክፍል በምን ካፒታል ሊገነባ እንደሚችል ከላይ በተጠቀስው ግንባታው ከሚጠይቀው
ጠቅላላ የካፒታል መጠን ውስጥ 30 እሚያክለው ተቀናሽ ሲሆን 40 ደግሞ ለእያንዳንዱ
ተጨማሪ እቅድ ተመላሽ የሚሆን ወይም ዋጋው ቢያድግ በተጨማሪነት ወይም አዳዲስ
ምርቶችን ለመጠቀም እንዲያስችል በማድረግም ውስጥ በማስገባት የተዘጋጀ ነው፡፡

በዚህም መሰረት ለአበባና አረንጓዴ ልማት እና ሌሎች አገልግሎቶች የሚያስፈልገው ገንዘብ


ለልዩ ልዩ ስራ ማስኬጃ የሚውለውን ወጭ በጠቅላላ ብር 13950000 ብር ጠቅላላ ስራውን
አጠናቅቆ አስፈላጊ የሰው ሀይል እና ቁሳቁስ በማሟላት ስራ መጀመር እንደሚችል በመገመት
ፕሮጀክቱ እንቅስቃሴውን የሚጀምር ይሆናል፡፡

2.2.የፕሮጅክቱ አዋጭነት ደረጃ

-ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልግ ጠቅላላ መነሻ ወጪ---------------- 13950000 ብር

-ፕሮጀክቱ ወደ ስራ ሲገባ ሊያስገኝ የሚችለው ገቢ የአበባና አረንጓዴ ልማት ግንባታ ተጠናቆ


ስራ ሲጀመር በአማካይ በቀን 100 አበባና አረንጓዴ እጽዋቶችን አምርቶ ቢሸጥ በትንሹ
20000 ብር ገቢ ቢያስገኝ እና በወር 26 ቀን እሁድን ሳይጨምር ቢሰራ *26*በ12 በወር
የዓመቱ ገቢ 6240000 ብር ያስገኛል ማለት ነው፡፡ከዚህ ጥቅል ገቢ ውስጥ ለሰራተኞች
ደሞወዝ በአማካኝ 400000 በአመት ብር ቢያወጣ በአመት ለመብራት ለስራ ማስኬጃና
ለግብር ብር 1350000 ለ5 ዓመት ባንክ ወለድና ተመላሽ 2550000 ብር ቢከፍል፡፡ በድምሩ
ወጭው ብር 4300000 ብር ይሆናል፡፡

በዚህ መሰረት ከጠቅላላ ገቢው ብር 6240000 – 4300000 ብር = 1940000 ብር


የሚደርስ የአንድ አመት የተጣራ ትርፍ ሊያስገኝ ይችላል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት
ደግሞ በመጀመሪያው አንድ ዓመት ይህን ያህል ገቢ ካስገኘና ተጨማሪ የሰው ሃይል
ከያዘ በቀጣይ አመት ከዚህ እጅግ የተሻለ የሰው ሃይል ጥሩ ገቢ እንደሚያስገኝ ማሳያ
ነው፡፡ በአጠቃላይ የመኪና ጋራዡ እና ልሎች አገልግሎቶች ለግለሰቡ ትልቅ የገቢ
ምንጭ ነው ብቻ ማለት ሳይሆን ለማህብረሰቡም ትልቅ የስራ እድል የሚፈጥርና
ከምርቱም ተጠቃሚ የሚያደርግ አዋጭ የሆነ ፕሮጀክት መሆኑን ያሳያል፡፡

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 20 | ገ ፅ


2.3. የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ

ፕሮጀክቱ በአካባቢው ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ

 በአካባቢው ላይ የሚፈጥር ምንም አይነት አሉታዊ ተፅዕኖ የለውም


 የሚጣሉ የአካባቢ ምርቶች የሚያስከትሉት ብክለት አልፎ አልፎ ሊከሰት
እሚችል ቢኖርም በሳይንሳዊ ሂደቶች ይፈታሉ

የተጽኖዎች ማቃለያ መንገድ

-ዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገጃ ዘዴወች መጠቀም

-ለአበባ ልማት ቤቱ አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግ ማለትም መያዝ

-በአጠቃላይ የስራ ግቢውን እና የአካባቢውን ጽዳት መጠበቅ እና ጸጥታውን ማስጠበቅ

-በሰራተኞችና ተጠቃሚወች ላይ በጤና ላይ ጉዳት እሚያደርሱ ነገሮችን የተለያዩ


ማስታወቂያወችን በመለጠፍ ማንኛውንም ሰው እንዳይጠቀሙ ማድረግ

-ለምሳሌ ማጨስ ክልክል ነው፤እፅ መጠቀም ክልክል ነው የመሳሰሉትን አዘል


መልክቶችን

--የእሳት አደጋ መከላከያ ከህንጻው ጋር እንዲኖር ማደረግ

የአካባቢ ተጽዕኖን መለየት፣ ትንበያ እና ትንታኔ


የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ በጥናቱ አካባቢ የታቀዱት ተግባራት ሊደርሱ የሚችሉ
ተፅዕኖዎችን መለየት፣ መተንበይ እና መገምገምን ያካትታል። እነዚህ ተግባራት ለፕሮጀክት
ግንባታ እና አጠቃቀሙ ስኬታማነት የሚያስፈልጉትን ሁሉንም ድርጊቶች ያካትታሉ.
የአካባቢያዊ አካላት የመነሻ መስመር አቀማመጥ ባለፈው ምእራፍ ውስጥ ተመዝግቧል ፣
የአሁኑ ምዕራፍ ግን በግንባታው /በአሠራር ደረጃዎች ውስጥ ሊኖሩ ስለሚችሉ ተፅእኖዎች
ይናገራል።

 ተጽዕኖን የመለየት እና የመተንበይ ሂደት


 በፕሮጀክቱ የህይወት ዘመን ሁሉ የተፅዕኖ ምንጭን ወይም መንስኤን መለየት
 የአካባቢ አስተዳደር እቅድ (EMP) በመጠቀም ተጽዕኖ የመቀየር እድልን መገምገም

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 21 | ገ ፅ


የብክለት ምንጮች
በአበባና አረንጋዴ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ ወቅት የሚፈጠሩት ብክለቶች በግንባታውም
ሆነ በተግባራዊ ደረጃዎች ጠጣር፣ ፈሳሽ እና ጋዝ ናቸው። እንዲሁም የብክለት መፈጠር
ቀጣይ, ወቅታዊ ወይም ድንገተኛ ሊሆን ይችላል.

ተጽዕኖ መለየት
ተፅዕኖዎቹ እና ትንበያዎቻቸው ከግምት ውስጥ የሚገቡባቸው የአካባቢ ጉዳዮች አሳሳቢ
ሲሆኑ በዋናነት፡-

 የመሬት ፣ የውሃ እና የአየር አከባቢ


 የጩኸት አካባቢ
 ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮት
 የትራፊክ ተጽእኖ
 ተጽኖዎቹ እንደ ተፈጥሮ፣ አቅም እና ትልቅነት እንደ አወንታዊ ተፅእኖዎች እና
አሉታዊ ተፅእኖዎች የበለጠ ሊመደቡ ይችላሉ።

የግንባታ ስራዎች የአካባቢ ገጽታዎች


ከግንባታ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዙ ዋና ዋና የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች፡-

 ቆሻሻዎችን ማመንጨት, ማከማቸት እና ማስወገድ;


 በማሽነሪዎች, በመሳሪያዎች እና በተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ምክንያት የአየር
ብክለት; የቆሻሻ ውሃ ማመንጨት እና ማስወገድ;
 እንደ ውሃ ፣ ኤሌክትሪክ ያሉ ሀብቶች ፍጆታ መጨመር
 በሌሎች የግንባታ ስራዎች ምክንያት የአፈር መሸርሸር.
ከላይ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ችግሮችና ስጋቶች ለመቀነስ ሳይንሳዊ ሂደቶችንና የከተማ ውበትና
ፅዳት መመሪያ በመከተል የሚተገበሩ ይሆናል፡፡

3.የፕሮጀክቱ ባለ ድርሻ አካላት


 የፕሮጀክቱ ባለቤት እና ሰራተኛ
 የጸጥታ አካላት
 የአካባቢው አስተዳደር
 ንዑስ መዘጋጃ ቤቱ ጽዳት እና ውበት የስራ ሂደት እና ልሎች
ያልተጠቀሱ አካላት ጋር በመተባበር ችግሩን ማቃለል

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 22 | ገ ፅ


4.የማጠቃለያ
ፕሮጀክቱ ሲጠና ምን ያህል ካፒታል እንደሚያስፈልግው እና ምን ምን አመቺ
ሁኔታወች እንዳሉ እንዲሁም ፕሮጀክቱ ከፋይናስ አንጻር ምን ያህል አዋጭ ሊሆን
እንደሚችል እና ምን አስቸጋሪ ሁኔታወች ሊገጥም እንደሚችል በተቻለ መጠን
በዝርዝር ለመዳሰስ ጥረት ተደረጓል፡፡ይህ ብቻ አይደለም የችግሮች ማቃለያ
መንገዶችን እና የመፍትሄ አቅጣጫወች ለማሳየት ተሞክሯል፡፡

በመሆኑም እንደ አጠቃላይ ከተዳሰሰው የጥናት ሁኔታ መረዳት የሚቻለው ሊገነባ እና


ሊከፈት የታቀደው የአረንጓዴ እና አበባ ልማት እና ሌሎች አገልገሎቶች በአስቸኳይ
በማዘጋጀት ስራ ማስጀመር እና በተሻለ ሁኔታ ከማንቀሳቀስ የሚያግዱ እንከን
ካለመኖሩ ባሻገር በተለይም በአሁኑ ወቅት ሀገራችን በተሸለ ሁኔታ የእድገት ጎዳና
ላይ የምትገኝ እንደመሆኗ መጠን እና በከተማችን እሚገኘውን አገልግሎት ፈላጊ ወደ
ተሻለ ተጠቃሚነት ደረጃ ለማስቀየር እና በተለያዩየ ሥራ ምክንያቶች እሚመጡ
እንግዶችን፣አልፎ ሀጂዎችም ማረፊያ ችግር ለማትረፍ የአገልግሎት ተደራሽነት
ለማሻሻል ቴክኖለጅውን ለማስፋፋት የህብረተሰቡን የቴክኖሎጅ ተጠቃሚነት ፍላጎት
ለማርካት መንግስት ከያዘው እስትራቴጅካዊ እቅድ አንጻር ይህ ፕሮጀክት ከተጠቀሰው
የከተማ ቦታ ላይ ተፈቅዶ ስራው ቢጀመር አዋጭ መሆኑን አሳይቷል፡፡

ኤችዲቲ አበባና አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል 23 | ገ ፅ

You might also like