Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 16

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ሥርዐተ ቅዳሴ

2014 ዓ.ም
◌ አመሠራረት እና እድገት
◌ የኢትዮጵያ ሥርዓተ ቅዳሴ መግቢያ
◌ አወቃቀር እና ሥርዓት
◌ ልዩ ባሕርያት
◌ ተምሳሌታዊነት (ትዕምርታዊነት)
አመሠራረት እና እድገት
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከቀደምት አብያተ
ቤተክርስቲያናት ውስጥ የምትመደብ ናት።

• ከ4ኛው ክፍለ ዘመን እስከ 1959 ዓ.ም በቅብጥ ቤተክርስቲያን ስር


ትተዳደር ነበር።

• ለቅዱስ ቁርባን ብዙ የምስጋና ሥርዐት ካላቸው አብያተ ቤተክርስቲያናት


አንዷ ስትሆን የምትጠቀመው ቋንቋም ግዕዝ ነው።
ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ . . . ?
ሦስት መላ ምቶች አሉ ፡

1. ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ (ሐዋ 2:38)


2. ቅዱስ ማቴዎስ ለኢትዮጵያውያን ሰብኳል!
3. በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ (ሐዋ 8 : 26- 38)
• ኢትዮጵያውያን ክርስትናን ከመቀበላቸው በፊት የአይሁድ እምነት
ተከታዮች እንደመሆናቸው መንፈሳዊ ዜማቸው የዕብራይስጥ
እንደነበር ይነገራል።

• ይህ እምነት እና የዕብራይስጥ ዜማ ምኒልክ ቀዳማዊ ኢየሩሳሌም


ደርሶ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ ይዟቸው ከመጣው 318 ሌዋውያን
እንደተወረሰ ይነገራል ።

• ቅዱስ ፍሬምናጦስ (አባ ሰላማ) ወደ ግብጽ ሄደው የኢትዮጵያ ሊቀ


ጳጳስ ተደርገው ተሹመው ሲመጡ የቅብጥ ቤተክርስቲያን ዜማ እና
ቅዳሴ አምጥተው ለሕዝቡ ካስተማሩ በኋላ በፊት የነበረው
የዕብራይስጥ ዜማ በአዲሱ ተተክቷል።
• ከቅዱስ ፍሬምናጦስ ቀጥሎ ደግሞ የዘጠኙ ቅዱሳን ወደ
ኢትዮጵያ መምጣት አስተዋጽኦ አድርጓል።

• ከዘጠኙ ቅዱሳን ውስጥ አብዛኞቹ በዜግነት ሶሪያዊ ሲሆኑ


ብዙ መጽሐፍትና እና የሥርዓት መጽሐፍትን አምጥተው
ተርጉመውልናል ።

• በዚህም ምክንያት 5 የሚሆኑ የቁርባን ምስጋናዎችን ከሶርያ


እና ከቅብጥ ቤተክርስቲያን የወረስን ሲሆን የተቀሩት 15
ቅዳሴዎች ግን እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ባሉ ሃገር በቀል
ሊቃውንት የተደረሱ ናቸው።
• በግራኝ አህመድ ወረራ እና በዮዲት ጉዲት ምክንያት ብዙ መዛግብት መጥፋታቸው ሥርዓቱን ለማጥናት ከባድ ቢሆንም
የቤተክርስቲያን ሊቃውንት እነዚህ የተቀበልናቸውን ዜማዎች መሠረታቸውን ሳይለውጡ በሊቁ ቅዱስ ያሬድ አማካኝነት
ሀገር በቀል ዜማ ለመሆን በቅተዋል።
የኢትዮጵያ ሥርዐተ ቅዳሴ መግቢያ
የኢትዮጵያ ሥርዐተ ቅዳሴ
• የኢትዮጵያ ሥርዓተ ቅዳሴ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ ሀገር በቀል
ቢሆንም እንኳን ውብ እና ልዩ ያደረጉትን ሦስት ተጽእኖች ማንሳት
ተገቢ ነው።
• የቅዱስ ማርቆስ ፣ ያዕቆብ ዘስሩግ ፣ ቅዱስ ባስልዮስ እና የጌታችን
ወንድም የሆነው ያዕቆብ ቅዳሴያት የተተረጎሙት ከቅብጥ እና ሶሪያ
ቤተክርስቲያን ነው።

• የኢትዮጵያ የቅዳሴ ድርሳናት ውስጥ ወደ 20 የሚጠጉ አኮቴተ ቁርባን


(የቁርባን ምሥጋናዎች) አሉ። ከ20ዎቹ ውስጥ ግን በግልጽ የሚታወቁ
እና በቤተክርስቲያን ሥርዐተ ቅዳሴ ላይ የተካተቱት 14ቱ ናቸው ።

• ከ14ቱ ቅዳሴዎች ውስጥ ደግሞ ሦስቱ (የሐዋርያት ቅዳሴ ፣ የጌታችን


ቅዳሴ እና የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ) ከውጪ ተተርጉመው የመጡ
ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ የኢትዮጵያን የሥነ መለኮት ልኅቀት እና ውበት
የሚያሳዩ ሀገር በቀል የቁርባን ምስጋና ናቸው፡፡
አወቃቀር እና ሥርዓት
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሦስት ዋና ዋና
የሥርዓተ ቅዳሴ ክፍሎች አሏት።

• ቅዳሴውን የሚቀድሱ ካህናት እና ዲያቆናት 5 ናቸው። ይህም የታቦር ተራራ ላይ


የተገኙትን 5 ሰዎችን ለማስታወስ ነው።

• የሚቀድሱት 7 ከሆኑ 7ቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያንን ያመለክታል። 13 ከሆኑ 12ቱ


ሐዋርያትንና ጌታችንን ምሳሌ በማድረግ ነው ።
• በቅዳሴው ሥርዓት 5 መሥዋዕቶችን ለእግዚአብሔር እናቀርባለን።
• ሥርዓተ ቅዳሴ ከሌላው የቤተክርስቲያን ሥርዓቶች ለየት የሚለው እነዚህን ሁሉ መሥዋዕቶች በአንድ ጊዜ ማድረግ
የሚችል ሥርዓት ስለሆነ ነው።

• በዚህ ሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት 5ቱ የስሜት ሕዋሶቻችን ሥርዓተ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ ።


ልዩ ባሕርያት
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብዙ መለያ ጸባያት አሏት
የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያክል ፡
ተምሳሌታዊነት (ትዕምርታዊነት)
• የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከሌሎች ቤተክርስቲያናት ለምሳሌ ከምሥራቅ አብያተ ቤተክርስቲያናት ሮማን ካቶሊኮች
እና ፕሮቴስታት አብያተ ቤተክርስቲያናት አንጻር ለብሉይ ኪዳን ትምህርት አጽንኦት ትሰጣለች ብሎ Wikipedia
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ይገልጻል።

የክርስቶስ ምሳሌ ነው።


ክርስቶስ የተወለደባትን ለማስታወስ ነው።
መባዕ እና ወይኑ የሚፈተትበት ክርስቶስ መስዋእት የሆነበት ምሳሌ ነው።
ኢያሱ እና እስራኤላውያን በኢያርኮ ግንብ መዞራቸውን ምሳሌ አድርጎ ነው
❖ ሙሴ በተቀደሰው መሬት ላይ ጫማ ማውለቁን ምሳሌ አድርገን በተቀደሰችው መቅደስም እኛም
ጫማ እናወልቃለን!

You might also like