Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 1

ወይ በደል

በእለተ አርብ ሥላሴ ሰውን ፈጠሩ በግብራቸው


የተፈጠሩትም አዳም ሔዋን ናቸው
ለጠቅላላው አለም ኃይልን ቢሰጧቸው
አፍርሰው ወደቁ በሰይጣን ተሳስተው
ወይ በደል ወይ ጉዳት
የሁላችን አባት አዳም ያን ጊዜ ጀመረ ለቅሶውን
ተሳስቶ በመብላት እጸ በለስን
ሊወርስ ፈልጎ አምላክነትን
ባልሆነ መካሪ በክፉ ሰይጣን
ወይ በደል ወይ ጉዳት
ከጎኔ ተፈጥረሽ ሔዋን እንኳን ልትረጂኝ ጎዳሽኝ
አንቺ ተሳስተሸ እኔን አሳትሽኝ
በማስመሰል ነግረሽ ስላበላሽኝ
እስከ መቼ ድረስ ሞቼ ቀረሁኝ
ወይ በደል ወይ ጉዳት
አትውቀሰኝ እንጂ አዳም ምን ላድርግ ብለህ ነው ጌታዬ
ሰይጣን አስቶኝ ነው አዬ መከራዬ
እስከመቼ ድረስ እሳት ነው ኑሮዬ
ስለተጣላሁኝ ከቸር ፈጣሪዬ
ወይ በደል ወይ ጉዳት
ያቺን እጸ በልስ ባትቆርጫት ከሰይጣን ጋራ ተማክረሽ
የምድሩ ሳይበቃሽ የሰማይ ሽተሽ
እኔን አዋረድሽኝ አንቺም ተዋረድሽ
ከእንግዲህ ይጥቀምሽ ከንቱ ምኞትሽ
ወይ በደል ወይ ጉዳት
ያን ጊዜ ከገነት ሲወጡ ጸጋቸው ሲገፈፍ ክብራቸው
መጣላት ጀመሩ እርስ በእርሳቸው
አንቺ ነሽ አንተ ነህ ሆነ ነገራቸው
ነገር ግን አይጠቅምም መነዛነዛቸው
ወይ በደል ወይ ጉዳት

You might also like