Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 2

★ እሁድ ጥቅምት 6/2015

➢ መግቢያ
● በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ለምን በስመ አብ ወወልድ ወምንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ብለን እናማትባለን? አንድ
አምላክ የምናመልክ ከሆነ ለምን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ብለን እንላለን?
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ስላሴ ናቸው! ሥላሴ ደግሞ አንድም ሶስትም ናቸው ብለን ስለምናምን ነው ነገር ግን
የምናመልከው 1 አምላክ ብቻ ነው። ለምሳሌ
ጸሀይ፦ ፀሀይ 1 ናት ነገር ግን በውስጧ 3 ነገሮች አሏት እነርሱም፦ 1ኛ ሙቀት፣ 2ኛ ብርሀን፣ 3ኛ እራሷን የቻለች አካል ናት
ነገር ግን ፀሀይ 1 እንጂ 3 ናት አንልም እንደዛ ሁላ እኛም የምናመልከው አምላክ 1ነው ግን ስናማትብ በአብ በውልድ
በመንፈስ ቅዱስ ብለን እናማትባለን።
➢ ለምን እናማትባለን?
❖ እምነታችንን መመስከራችን ነው
❖ ስናማትብ ሠይጣን ከእኛ ይርቃል
❖ የመድኋኔዓለም መከራ መስቀሉን አናስባለን
❖ መስቀልን ስናይ ኢየሱስ ክርስቶስን እናስባለን(ኢየሱስ ክርስቶስ አምሳያ ይናያለን፤ ኢየሱስ ክርስቶስን እናያለን)።
➔ ትምህርት
"መዝ 122፥1"=ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ እንዲህ ሲል ተናግሯል ''ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ ''
የእግዚአብሔር ቤት እግዚአብሔርን ላመኑ, ለእኛ ለሠዎች የተዘጋጀ ቤት ነው። ጌታችን መድኋኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ለመሰቀል 1 ሳምንት ሲቀረው እሁድ ለታ በአህያና በውርንጭላ ከቤተ-ገሊላ ተነስቶ 2 mile ያክል ተጉዟል በጉዞው ላይ
ግማሹን መንገድ ዳገት ግማሹ መንገድ ደግሞ ለጥ ያለ ነበር! ዳገቱን ጠንከር ባለችው በጠንካራዋ አህያ ለጥ ያለውን
ደግሞ በውርንጭላ ላይ ሆኖ ተጉዟል ደቀ-መዛሙርቱ ደግሞ ሆሳዕና በአርያም እያሉ ልብሳቸውን ሳይቀር መሬት ላይ
እያነጠፉ አህያዋ ላይ እያረጉ በደስታ ያመሰግኑት ነበር ለጥ ያለው መሬት ላይ ሲደርሱ በውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም
ሲደርሱ በእናታቸው ጀርባ የታዘሉ ህጻናት እንኳን ሳይቀር ይናገሩ ነበር ያጨበጭቡ ነበር። ጌታችን በመንገድ ላይ 3 ቦታዎች
ላይ አልቅሷል! ጌታችንን በእዛ ያሉት ካህናት እና ሽማግሌዋች ይጠሉት ነበር ምክንያቱም አንተ ሆሳዕና ልትባል አይገባህም,
አንተ መድኋኒታችን ልትባል አይገባህም አንተ ሀይማኖታችንን ታረክሰዋለህ ይሉት ነበር ጌታችን መድሓኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ያለቀሰው እስራኤል ትልቅ መከራ ሊመጣባት ስለነበር ነው። ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን
ለእስራኤል እንዲህ አላት፦"እኔ አንችን ላድንሽ ነበር የመጣሁት ነገር ግን አንች አልተቀበልሽኝም አላት" ትልቅ መከራ
እንደሚመጣባትም ተናገረ። እነሱ ግን ይሰድቡት ነበር። በዛን ዘመን መስቀል ላይ የሚሰቀለው ወንበዴ ነው፥ መስቀሉንም
ያንቋሽሹት ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክ የተሰቀለበት መስቀል ስለሆነ እኛ እናደርገዋለን በመስቀልም እናምናለን።
*እግዚአብሔር አምላክ እንደተናገረው በ70 ዓ.ም እስራኤል እስራኤል ተቃጠለች መልሳም የተገነባችው በ1945 ዓ.ም ነው።
ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ-መቅደሱ ሲገባ ቤተ-መቅደሱ ገበያ ሆኖ ነበር ብዙ ሽያጮች ነበሩ ግማሹ
በግ፣ፊየል የተለያዩ ነገሮችህ ሲሸጡ በአንድ በኩል ደግሞ ገንዘብ በተለያዩ ዕቃዎች የለዋወጡ ነበር ምግቦች ብዙ ነገሮችም
ይሸጡ ነበር! ጌታችንም ሁሉንም ዘረጋግፎ አበላሽቶ ሁሉንም አስወጣቸው ሁሉንም ካስወጣ በውሃላ እንዲህ አለ"ይህች
የተቀደሰች ስፍራ የአባቴ ናት ይችን ይፁህ ቤት እናንት ወደ ወንበዴዎች መነሀርያ አደረጋችኋት" አላቸው። ሌላኛው ቅዱስ
ዳዊት በመዝሙሩ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ ያለው በዚህ ምክንያት ነው።
➢ ወደ ቤተ-ክርስቲያን ስንመጣ የምንጠቀመው ጥቅም፦
❖ ስጋ ወደሙን ስንቀበል
❖ ስጋ ወደሙን ስንቀበል በረከት እናገኛለን
❖ ስጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ የዘለዓለም ህይወት አለው ስላለ
❖ መንፈሳችንን ለማረጋጋት
❖ መጥፎ ሀሳብን ትተን ጥሩ ጥሩውን ብቻ ለማሰብ
❖ ህይወታችንን ለመቀየር (ለመለወጥ)
❖ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት፦ በፀሎት፣በምስጋና በተለያዩ ነገሮች ማለትም ከእግዚአብሔር ጋር ሊያገናኙን
ከሚችሉ ነገሮች በሙሉ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለወላዲቱ ድንግል


ወለመስቀሉ ክቡር!

You might also like