06

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 1

ቀን 06/01/2014 ዓ/ም

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ትምህርት ጽ/ቤት

ሁመራ

አመልካች፡- መ/ር ሙሉዓለም በፈቃዱ አድራሻ፡- ሰቲት ሁመራ ከተማ ቀበሌ 03 ቀጠና 02

ጉዳዩ፡- ቅሬታ ማቅረብን ይመለከታል

በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረዉ ከላይ ስሜና አድራሻዬ የተጠቀሰዉ መምህር በሰቲት ሁመራ ከተማ የሰቲት ሁመራ ከተማ
አጠቃላይ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የፊዝክስ መምህር ሆኜ ማገልገሌ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን በአሁን ሰዓት የሲቪል ሰርቪስ
ህግና ደንብን ባልተከተለና በሚፃረር መልኩ ለእኔ የዳቦ ስም በመስጠት የሰቲት ሁመራ ከተማ ት /ት ጽ/ቤት ከስራ እንዲለቅ
አድርጓል፡፡ ይህን ጉዳይ ከዚህ ቀደም ያሳወቅሁ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን አሁን ይህን ቅሬታ ለማስገባት የፈለኩበት ዋናዉ
ምክንያት የሰቲት ሁመራ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር የሆነዉ መምህር በላይ ፈለቀ በ 04/01/2015 ዓ/ም
የት/ቤቱን መምህራን ሰብስቦ ለመምህራኑ የሚታዉቁት ለሃይስኩል የሚመጥን እዉቀት ያለዉ የፊዝክስ መምህር ካለ እንዲመጣ
ብታደርጉ እዚህ ይቀጠራል ከማለቱም ባሻገር አሁን የማስተዋዉቃችሁ መምህር ወንድሜና የፊዝክስ መምህር ነዉ እኔ 11 ኛን እና
12 ኛን ፍዚክስ አስተምራለሁ ወንዲሜ ደግሞ 9 ኛን እና 10 ኛን ያስተምራል ብሎ ለመምህራን መናገሩ መምህራንም እሱ እያለ
በምል ሃሳብ ቅሬታ ስለነበራቸዉ መጥተዉ ነግረዉኛል፡፡ ይህ ጉዳይ ስጀመር ሁለት ወንድማማቾች በአንድ መስሪያ ቤት በሲቪል
ሰርቪስ ህግ አይፈቅድም፡፡ መግባትም ማስገባት ማሰራትም አይቻልም፡፡ ምናልባት የከተማዉ ት /ት ጽ/ቤት አዲስ የራሱ ህግ ካለዉ
እሱን አላዉቅም በቀጣይ እናንተ የሚታጣሩት እና አግባብ ያለዉ ዉሳኔ እንደምትሰጡ ከዞኑ ጽ /ቤት ጠብቃለሁ፡፡ በተጨማሪ እኔ
የፊዚክስ መምህር ሆኜ ማገልገሌ እየታወቀና በግልጽ በአሻጥር እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ ሌላ የፊዚክስ መምህር ፍለጋ
ማስታወቂያ ማስነገር አግላይና ከት/ት ስርዓት ጋር የሚፃረር እንዲሁም የትምህርትን ስራ ሆን ተብሎ ከጥቅም ጋር
በማስተሳሰር የተደረገ ግልጽ ክህደት ስለሆነ እና ከምለዉ በላይ አእምሮዬን የሚነካና ሰዉና ሀገር አልባ እንደሆንኩ
ስለተሰማኝ እና ቅር ስላለኝ ቅሬታየን በዚህ መልኩ በትህትና አቀርባለሁ፡፡

ከሰላምታ ጋር!

መ/ር ሙሉዓለም በፈቃዱ

ግልባጭ

 ለሰ/ሁ/ከ/ሲ/ሰ/ጽ/ቤት
ሁመራ
 ለሰ/ሁ/ከ/ት/ት/ጽ/ቤት
ሁመራ

You might also like