Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 1

ቀን 05/05/2015 ዓ/ም

/
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር ጽ ቤት

ሁመራ

ጉዳዩ፡- ጉዳያችን በዲጋሚ ታይቶ ለሁለተኛ ጊዜ መፍትሄ እንዲሰጠን ስለመጠየቅ ይመለከታል

አመልካቾች፡- ከሱዳን ተመላሽ ኮሚቴዎች

አድራሻ፡- ሰቲት ሁመራ ከተማ ቀበሌ 04 ቀጠና 02

ከላይ ስማችንና አድራሻችን የተገለፀዉ ከሱዳን ተመላሽ ኮሚቴዎች ቀደም ስል በ 01/05/2015 ዓ/ም የፃፍነዉን
ማመልከቻ በመጥቀስ ከሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ እና የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ ከተከበሩ ኮ /ል ደመቀ ዘዉዱ
ጋር ደብዳቤያችን አቅርበን የሰጡን መልስ ለኛ አጥጋቢ ሆኖ ባለማግኘታችን ድጋሚ አቤት ለማለት ተገደናል፡፡
በመሰረቱ እኛ ከሱዳን ከስደት ስንመለስ የተሰጠን ተስፋ ብዙ ቢኖርም ለጊዜዉ የሚሆናችሁ ተብሎ ከተሰጠን
ቤትና 15 ኪግ ስንዴ ዉጪ የተረዳነዉ ነገር የለም፡፡ አሁንም ሰቲት ሁመራ ከተማ የምትቀመጡ መሬት
እንደማይሰጣችሁ አዉቃችሁ ተኖግራችሁ ተስማምታችኋል የተባለዉን ጉዳይ እኛ ከስደት ተመላሾች
የምናዉቀዉ ምንም ነገር የለም፡፡ አሁንም ወደ ገጠር ሄዳችሁ ተቀመጡ እና መሬት እንሰጣችኋለን የተባለዉ
እኛን ለሶስተኛ ጊዜ ማፈናቀል ነዉ የሚሆነዉ፡፡ እኛ ዞኑ የሚሰጠዉን መመሪያም ሆነ ዉሳኔ ለመጣስ
እንቸገራለን፡፡ ይህንንም ለማድረግ ፈልገን አይደለም፡፡ ስለዚህ ይህ በእኛ ላይ የተወሰነዉ ዉሳኔ የእኛን ችግር
ማባባስ እንጂ የሚያቀልልን ሆኖ አላገኘነዉም፡፡ ስለዚህ በእኛ ላይ የተወሰነዉ ዉሳኔ እንደገና እንዲታይልንና
ሁመራ ከተማ ተቀምጠን ለጊዜዉም ቢሆን መሬት ተሰጥቶን ችግራችንን የምናቃልልበት መንገድ ቢፈጠርልንና
ከእርዳታ ጠያቂነት እንዲንላቀቅ/እንድንወጣ/ እዲደረግልን በድጋሚ በትህትና እናመለክታለን፡፡

ከሰላምታ ጋር!

አመልካቾች፡- ከሱዳን ተመላሽ ኮሚቴዎች

You might also like