Document

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ውስጥ ለውጥን የሚያደናቅፈውን ሂደት ስለማስቆም

✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ለሀገር፣ ለህዝበ ሙስሊሙ እና ለተቀረው ኢትዮጵያዊ በሚመጠቅም መልኩ
ለማደራጀት የሁሉም ፍላጎት እና ጥረት እንደነበር ይታወቃል፡፡ መንግስትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ የድርሻውን ሲወጣ ቆይቶ በሚያዚያ
23 2011 በተካሄደው ጉባኤ ይህንን ግዙፍ ኃላፊነት ይወጣሉ ተብለው ለታሰቡ አካላት በሙሉ ድጋፍ ሙሉ ኃለፊነቱን በጋራ በመስጠት
ወደመስመር እንዲገባ መደረጉ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በአዲስ መልክ ለማቋቋም ኃላፊነቱን የተረከቡት እነዚሁ አከላት በአጠቃላይ በሀገር፣
በህዝብ እና በመንግስት ሲጠበቅ የነበረውን ሪፎርም ማሳካት አለመቻላቸውን ተረድተናል፡፡ ምንም እንኳን ሪፎርሙ በከፍተኛ ጉጉት
እንደመጠበቁ ከፍተኛ ግፊት ሊደረግባቸው ቢገባም ግዜውን ጠብቀው በአቅማቸው ልክ እንዲፈፅሙት ሲባል ብዙሀኑ በዝምታ
ሲጠብቃቸው ቆይቷል፡፡ ይሁንና በዝምታ ውስጥ መርጋትና ስራቸውን መከወን ተስኗቸው ተቋሙን የማሻገርና የተሰጣቸውን ኃላፊነት
መወጣት እንደተሳናቸው አሁን ምስክር በማይፈልግ መልኩ በተግባር እያረጋገጡ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም አልፎ አስተዳደራዊ ብቃት እና
አባታዊ ጥበብ በጎደለው መልኩ ለሀገርና ለህዝብ የውጥረት መነሻ በመሆን ወደአዲስ ሂደት እንዲገባ ምክንያት ሆነው በታሪክም
በህዝብም ይቅር የማይባሉበትን ስህተት እየፈፀሙ ነው፡፡

ዝርዝር ጉዳዮችን በቀጣይ የማወሳ ሆኖ በኢትዮጵያ ውስጥ በአዋጅ እውቅና የተሰጠው የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን መንፈሳዊ ህይወት
በሚመለከት በበላይነት ሊመራ የሚጠበቀው ምክር ቤቱ ለዚህ ኃለፊነት የሚመጥን የሞራል፣ የአቅም እና የዝግጁነት መለኪያዎችን
በማያሟላ ሂደት ውስጥ መቆየቱ፣

ምክር ቤቱ አንድ ተቋም ሊኖሩት የሚገቡት የህግ፣ የመዋቅር፣ የአሰራር ሂደትና በስራ ሂደቶች ሊኖር የሚገባው የስራ ግንኙነት ፈጥረው
ጠንካራ ተቋም እንዲሆን ማድረግ አለመቻላቸው አመራሮቹም በተደጋጋሚ በታየው መልኩ ይህንን የማድረግ አቅምና ፍላጎት
እንደሌላቸው ማረጋገጥ መቻሉ፣

ምክር ቤቱ እንዲያስብ የሚፈለገው እንደ ሀገር ሆኖ ሳለ፣ የሚመለከተው ስለ አጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መሆን ሲገባው፣
በሀገር ደረጃ ያሉ መልካም እድሎችን እየተጠቀመ ለሀገር መስራት ሲጠበቅበት ጠባብና ከፋፋይ በሆኑ ጉዳዮች ውስጥ እራሱን ቀብሮ
ህዝቡንም ወደዚያ ጉድጓድ ለመክተት ብቻ የሚታትር ሆኖ በመገኘቱ፣

መጅሊሱ እንደ ሀገራዊ ተቋምነቱ ለሀገር የሚበጁ ፕሮጀክቶችን ነድፎ ህዝቡን በማስተባበር ማሰራት ሲጠበቅበት የአለመግባባትና የስጋት
አጀንዳዎችን በመቅረፅ ከትርፍነቱ ኪሳራው ወደሚያመዝንበት ደረጃ በመድረሱ፣

እና በቀጣይ በዝርዝር በምመለስባቸው ምክንያቶች በሚያዚያ 23 የተዋቀረው የሪፎርም ቡድን ስራው አለመሳካቱን ሁላችንም ልንረዳ
በምንችልበት ደረጃ ደርሷል፡፡

በመሆኑም፡-
በዚህ የሪፎርም ሂደት የህዝቡን የዘመናት ጥያቄ መልስ ለማስገኘት በቀና መንፈስ ረጅም ርቀት በመጓዝ ድጋፍ ሲያደርግ የነበረው
መንግስት እንደ ሀገር ከሚጠበቁ ሁሉን አቀፍ ሪፎርሞች መካከል በመጅሊሱ ውስጥ ሪፎርሙ ሊሳካ ያልቻለባቸውን እና ለዚህም በግልፅ
የሚታዩ ከለውጥ እና ለከአንድነት ተቃራኒ የሚሰብኩና የሚሰሩ አካላትን በአጭር ግዜ እራሳቸውን ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ
እንዲያደርግ፣

ለምክር ቤቱ ጠንካራ መሆኑ በህግ፣ በአስተዳደር፣ በሌሎች ሙያዎች ሲረባረቡ የነበሩ ባለድርሻዎች በሙሉ ይህ ድካማቸው በጥቂት
ጠንካራ ተቋም እና የህዝቡን አንድነት በማይፈልጉ አካላት ምክንያት እንዲኮላሽ ባለመፍቀድ አስፈላጊውን ድርሻቸውን እንዲወጡ፣

ከምንም በላይ የምክር ቤቱን እውን መሆን በማለም በትግልም በትእግስትም ትልቅ ሚና ያላችሁ ሙስሊሞች በቀጣይ ቀናት የሚኖሩ
ሂደቶችን በቅርበት ተከታትሎ ተቋማችን ረጅም ርቀት ተጉዞ ሳለ በግለሰቦች ጤናማ ባልሆነ ፍላጎት ምክንያት በአጭር እንዳይቀር
የድርሻሁን መወጣት እንደሚጠበቅባችሁ ለማስታወስ እወዳለሁ፡፡

በስተመጨረሻም

ሀገራችን አሁን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ እና የሁላችንንም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ባሉበት ሰአት ለሀገርና ለህዝብ አጋር መሆን ቢሳናችሁ
አጀንዳ በመፍጠርና የእርስበእርስ ፀብ ውስጥ ለማስገባት የምትሰሩ ምንም አይነት አባታዊ፣ ኃይማኖታዊ እና የመሪነት መንገድ ልታሳዩን
ያልቻላችሁ የመጅሊሱ ግዚያዊ አመራሮች ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ የመጨረሻ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

https://www.facebook.com/1502018196725865/posts/2801852256742446/

You might also like