Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 11

ኤል ዳድ ሜታል ወርክ እና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

EL DAD METAL WORK AND TRADING P.L.C


መመስረቻ ጽሁፍ
አንቀጽ አንድ
ምስረታ
በሰነዱ ስር ፊርማችንን ባሰፈርነው መካከል በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ የንግድ ሕግ
የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ልዩ እትም አዋጅ ቁጥር 1243/13 መሠረት በዚህ የመመስረቻ ጽሁፍ
የሚገዛና ዓላማውም ከዚህ በታች በአንቀጽ 4 ሥር የተመለከቱትን የንግድ ሥራ ተግባራት
ማከናወን የሆነ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለመመስረት ስምምነት ተደርጓል፡፡
አንቀጽ ሁለት
የአባላቱ ስም፣ ዜግነትና አድራሻ
ተ.ቁ ስም ዜግነት አድራሻ
ከተማ ክ/ከተማ ወረ የቤ/ቁ.

1 አቶ ዮናስ ሙሉአለም በዳሶ ኢትዮጵያዊ አ.አ ልደታ 03 515
2 አቶ ሳሙኤል ሙሉአለም በዳሶ ኢትዮጵያዊ አ.አ ልደታ 03 515
3 አቶ ሚኪያስ ሙሉአለም በዳሶ ኢትዮጵያዊ አ.አ ልደታ 03 515
4 ወ/ሪት ማህሌት ሙሉአለም በዳሶ ኢትዮጵያዊ አ.አ ልደታ 03 515
5 አቶ በላይአብ በቀለ ጆፌ ኢትዮጵያዊ አ.አ ን/ስ/ላ 01 አዲስ

አንቀጽ ሶስት
የማህበሩ ስምና ዋና መስሪያ ቤት
3.1 የማህበሩ ስም ኤል ዳድ ሜታል ወርክ እና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (EL DAD
METAL WORK AND TRADING P.L.C) ነው፡፡

3.2 አባላቱ ወደፊት በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ ቅርንጫፍ

የመክፈት መብታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የተመዘገበው የማኀበሩ ዋና መስሪያ ቤት


በአዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የቤ/ቁ.315 ውስጥ ነው፡፡
አንቀጽ አራት
የማህበሩ የንግድ ሥራ ዓላማዎች
ማህበሩ የተቋቋመበት ዓላማዎች
1. የብረታ ብረት ኢንዱስትሪዎችን በማቋቋም ምርቶቹን ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣
2. የብረታ ብረት ምርቶችን በማሰባሰብና ከውጭ አገር በማስመጣት ለገበያ ማቅረብ፣
3. የኢትዮጵያን ቡና፣ የቅባትና የጥራጥሬ እህሎችን በውጭ አገራት ማስተዋዋቅና ኤክስፖርት ማድረግ፣

4. የኢትዮጵያን ቡና፣ የቅባትና የጥራጥሬ እህሎችን በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የገበያ መድረክ ላይ በመሳተፍ ሽያጭ
እና ግዥ መፈፀም፣ የኮሚሽን ኤጀንት ሥራዎችን መስራት፣
5. በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት የአባልነት ወንበር በመግዛት የማህበሩን የንግድ ሥራዎች ማከናወን እንዲችል፣
6. የኢትዮጵያን ቡና፣ የቅባትና የጥራጥሬ እህሎችን ከአምራች አርሶ አደሮች ወይም ከአልሚ ባለሀብቶችና
አቅራቢዎች በአውቶግሮውስ እና በቀጥት ግብይት ትስስር ኮንትራት ውል መዋዋል፣ መግዛት፣ ለኢትዮጵያ ምርት
ገበያ ማቅረብ ወይም በቀጥታ ለውጭ ገበያ መላክ፣
7. የቡና፣ የቅባትና የጥራጥሬ እህሎችን ማጠቢያና ማበጠሪያ ኢንዱስትሪ ማቋቋም፣ ከአምራች ቡና መግዛት
መፈልፈል፣ ማበጠርና ማቀነባበር፣
8. ጥሬ ቡና ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወይም በግብይትና ልማት ትስስር ገዝቶ ቆልቶ፣ ፈጭቶ፣ አቀነባብሮና አሽጐ
ለሐገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣ መሸጥ፣
9. ፋብሪካዎችና እና ኢንዱስትሪዎችን አቁቁሞ የተለየዩ ምርቶችን በማምረት በጅምላም ሆነ በችርቻሮ መሸጥ
ኤክስፖርት ማድረግ፣
10. አጠቃላይ አስመጪነት፡- ልዩ ልዩ የውጭ ሀገር ምርቶችን ወደ ሀገር ውስጥ አስመጥቶ መሸጥ፣ ማከፋፈል፣
11. አጠቃላይ ላኪነት፡- ማንኛውንም ምርቶች በማምረትም ሆነ ከአምራቾች በመረከብ ወደ ውጪ በመላክ መሸጥ፣
12. አጠቃላይ የአቅርቦት ሥራዎችን መስራት፣ የተለያዩ ዕቃዎችን ከአስመጪዎችም ሆነ ከአምራቾች በመረከብ
ማቅረብ፣ ማከፋፈል፣ መሸጥ፣
13. የተለያዩ የምግብ ዓይነቶችን ማምረት፣ ማቀነባበር፣ በጅምላም ሆነ በችርቻሮ መሸጥ ኤክስፖርት ማድረግ፣
14. ለተዘጋጁ ምግቦች ማሸገያ የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎችን ማምረት፣ ማከፋፈል፣ በጅምላና በችርቻሮ መሸጥ፣
15. ጠቅላላ የኮንስትራክሽን ስራዎችን መስራት፣(GC)
16. ማንኛውም የኮንስትራክሽን መሣሪዎች በማስመጣት ማከፋፈል፣ ማከራየትና መሸጥ፣ እንዲሁም ለራሱ የሥራ
አገልግሎት ማዋል
17. አጠቃላይ የውሃ ኮንስትራክሽን ሥራ እና መስመር መዘርጋት
18. ለኮንስትራክሽን አገልግሎት የአገር ውስጥ ጥናት ማካሄድ ፣
19. ማንኛውንም የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎችን፣ማስመጣት፣ ማምረት፣ በጅምላ በችርቻሮ መሸጥ፣
20. በኮንስትራክሽን የሙያ ዘርፍ የማማከር፣ የዲዛይንና ጥናት አገልግሎት መስጠት፣
21. አጠቃላይ ብረታ ብረቶችን፣ አልሙኒየም ከውጭ ሀገር ማስመጣት፣ ማከፋፈል፣ መሸጥ፣ ለራሱ አገልግሎት
ማዋል፣
22. ማዕድን መፈለግ፣ ማውጣት፣ ቅርጽ ማስያዝ ለሃገር ውስጥም ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣
23. ከአገር ውጪ ከውጭ ሃገራት መሰል ድርጅቶች በሽርክና መሥራት፣ አሊያም አክሲዮን መግዛት፣ መሸጥ፣
24. ቦንድና አክስዮን መግዛትና መሸጥ፣ በሌሎች ማህበሮች ውስጥ አክሲዮን መያዝ፣
25. የመኪና አካል ለውጥና የጋራዥ ስራዎችን መሥራት፣ መሸጥ፣
26. የውሃ ፓምኘ ጄኔሬተርና የሶላርና ማሽነሪ እና ኤሌክትሪካል ዕቃዎች አቅርቦት፣ እንዲሁም የኤሌክትሮ መካኒካል
ዕቃዎችን ማስመጣት፣
27. የመኪናና የሞተር ብስክሌት እቃዎች አቅርቦት አስመጪና ላኪነት፣
28. ያገለገሉና አዲስ ተሽከርካሪዎች ከውጭ ሀገር ማስመጣትና መሸጥ፣
29. አዲስና ያገለገሉ የተሽከርካሪም ሆነ የማንኛውም ዓይነት ማሽኖች መለዋወጫ ዕቃዎችን ማስመጣት፣ መሸጥ፣
ማከፋፈል፣
30. የመኪና ቦዲ፣ የመኪና ጐማ፣ የመስታወት ምርቶች፣ ጐሚኒዎች፣ ፍሬሞች፣ የመለዋወጫና ተጓዳኝ ዕቃዎች
ማስመጣት ማምረት፣ መስራት፣ ማከፋፈል፣ መሸጥ፣
31. ቁርጥራጭ ብረቶችን (ስክራኘ) ማስመጣት፣ ማከፋፈል፣ መሸጥ፣ መግዛት፣
32. ቡና ማምረት ወደ ውጭ መላክ፣
33. የጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች አበጣሪነት መሥራት መሸጥ እና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣
34. ቡና ቆልቶ ፈጭቶ በማሸግ በጅምላ እና በችርቻሮ መሸጥ ፣
35. ቡና ቆልቶ ፈጭቶ በማሸግ ወደ ውጭ ሃገር መላክ፣
36. ለግብርና ምርቶች ማሸጊያ የሚሆኑ ግብዓቶች (ጆንያ፣ ሸራ፣ ማዳበሪያ የመሳሰሉትን) ማምረት፣ ማከፋፈል፣
መሸጥ፣
37. የነዳጅ ድርጅት ማቋቋም፣ የነዳጅ ማደያ ማከራየት፣ መከራየት፣ መሸጥ፣ መለወጥ፣
38. የማሽነሪ ዘይቶች፣ ቅባቶች እና ነዳጅ ማደያ ስራዎች ላይ መሰማራት፣
39. መድኃኒትና የተለያዩ የህክምና መሣሪያና ማሽኖች እንዲሁም የላብራቶሪ ዕቃዎችን ማስመጣት በጅምላና
በችርቻሮ መሸጥ፣ ማከፋፈል፣
40. የግብርና እቃዎች፣ ኬሚካሎችና ፀረ ተባዮችን፣ ጨርቃጨርቆችን፣ የአሌክትሪክና ኤክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ መኪና
እና የማሽን ዕቃዎችን፣ እንዲሁም የፋብሪካ ጥሬ እቃ ኬሚካሎችን ማስመጣት፣ በጅምላና በችርቻሮ መሸጥ፣
ማከፋፈል፣
41. የሚዲያ ዕቃዎች እና የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ማስመጣት፣
42. የማዕድን ውሃ ማምረት፣ መሸጥ፣ ማከፋፈል፣
43. የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ማምረት፣ ከውጭ ሃገር ማስመጣት፣ መሸጥ፣ ማከፋፈል፣
44. ሪልስቴት ሥራ፣ ቤቶችና ህንጻዎችን እየሰሩና እየገዙ መሸጥና ማከራየት፣ ቤቶችና ህንጻዎችን ለመሸጥና
ለመግዛትም ሆነ ለማከራየት ውክልና መውሰድ፣
45. በእርሻና በሌሎች የግብርና ስራ ዘርፎች ላይ መሰማራት
46. ልዩ ልዩ የአግሮ እንዱስትሪ ውጤቶች፣ የአበባ፣ የአትክልት፣ ፍራፍሬ ማምረት፣ ማዘጋጀትና ምርቱን ለሃገር
ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣
47. የቀንድ ከብትና የዓሣ፣ የዶሮ እርባታ፣ የሥጋ፣ የወተት ምርት ማምረትና መቀነባበር ለሃገር ውስጥና ለውጭ ገበያ
ማቅረብ፣የእርድ/ ቄራ/ ሥራ መስራት
48. የእህል ሰብል(አዝርዕት) በሰፋፊ እርሻ ማምረትና ምርቱን ለሃገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣ እንዲሁም የአትክልት ዘር
ማስመጣት፣
49. የእርሻ መካናይዜሽን ለእርሻ ሥራ የሚውሉ መሣሪያዎች ግብአቶች ማቅረብና መጋዘንና የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት
መስጠት፣
50. ፋብሪካዎችን በግል እና ከሌላ ኩባንያ/ ግለሰብ/ ጋር በጋራ በመሆን ማቋቋም፣
51. የጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች አበጣሪነት መሥራት መሸጥ እና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣
52. በአስጐብኚነትና በቱሪዝም ወኪልነት መሥራት፣ መዝናኛዎችን መናፈሻዎችን ማቋቋም፣
53. ቦንድና አክስዮን መግዛትና መሸጥ፣ በሌሎች ማህበሮች ውስጥ አክሲዮን መያዝ፣
54. የጅምላና የችርቻሮ የንግድ ስራ ማካሄድ
55. ለውጭም ሆነ ለሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ወኪል ሆኖ መሥራት፣
56. የአየር መንገድ ትኬት በኮሚሽን መሸጥ፣
57. ለተለያዩ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች ጉዳይ ማስፈፀም ሥራ፣
58. የተለያዩ የታሸጉና ያልታሸጉ ምግቦችን፣ የንጽህና ዕቃዎችን ከውጪ ማስመጣት ፣
59. የጽሕፈት መሳሪያዎችን አስመጩነት ስራ ላይ መሰማራት፣
60. የኮስሞቲክስ ዕቃዎችን (የውበት መጠበቂያ) ማስመጣት፣
61. አስጐብና የጉዛ ወኪል ሥራ መስራት፣
62. የመኪና ኪራይ አገልግሎት መስጠት፣
63. በሆቴል፣ በመዝናኛ ሥራዎች መሳተፍ፣ የጭነትና የሰው ማጓጓዣ ትራንስፖርት ሥራት መስራት፣
64. የጉምሩክ አስተላለፊነት ሥራዎችን መሥራት፣
65. የትራንዚት አገልግሎት በመስጠት የባህር እና የየብስ ትራንስፖርትና ሞቢላይዜሽን አገልገሎት መስጠት፣
66. በሀይል ማመንጨት በኢንዱስሪ እና በፋብሪካ የስራ ዘርፍ መሰማራት፣
67. የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን ማስመጣትና ማከፋፈል፣ ማከራየት፣
68. በአየር፣ በባህርም ሆነ በየብስ የትራስፖርት ሥራ ላይ መሰማራት፣
69. የማሽነሪ ዘይቶች፣ ቅባቶች እና ነዳጅ ማደያ ስራዎች ላይ መሰማራት፣
70. ት/ቤት ማቋቋም፣ ትምህርት ቤቶችንና ኮሌጆችን ማቋቋምና የትምህርት ሥራ መሥራት፣
71. ማምረት በአገር ውስጥ የቅመማ ቅመም ግዥ ማካሄድ፣ ወደ ውጭ አገር በመላክ መሸጥ፣
72. የጤና አገልግሎት መስጠት፣ በክሊኒክ፣ በሆስፒታል፣ ላብራቶሪ ወዘተ በጤናና ህክምና አገልግሎት ላይ
መሰማራት፣
73. የጭነትና የሰው ማጓጓዣ ትራንስፖርት ሥራ መሥራት፣
74. የኘሮጀክት ጥናት፣ አስተዳደር አፈፃፀም ሥራ መስራት፣
75. በልዩ ልዩ ኢንቨስትመት መስኮች ውስጥ አክሲዮኖችን መግዛት፣ የውጪ ንግድ ረዳትነት፣ ኮሚሽን ኤጀንትና
ውክልና ሥራ ማከናወን ፣ የጉምሩክ ስራ አጣሪነት/ክሊራንግ ኤጀንት፣ የመጫንና ማራገፍ የማሸግና የጉዞ
ወኪልነት የጠቅላላ ዕቃ አስተላላፊት፣
76. የተለያዩ ከጨርቅ የሚሰሩ ምርቶችን በመፈብረክ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣
77. ብትን ጨርቆችንና የጨርቃ ጨርቅ ስራ ጥሬ እቃዎችን በማስመጣት የተዘጋጁ ምርቶችን ማምረት፣
78. ለድርጅቶችና ትምህርት ቤቶች የደንብ ልብስ ማዘጋጀት፣
79. ጣቃ ጨርቅ፣ ክር፣ ድርና ማግ አልባሳትና ሌሎችም የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶችን በማንጣት በማቅለም
በማኮማተር በማፍካት በማጠናከር ወርድና ቁመትን በመጠበቅ ወይም በማስዋብ ማጠናቀቅ፣
80. ከማህበሩ ዓላማ ጋር ግንኙነትና ተዛማጅነት ያላቸውን ሌሎችን ሥራዎችን በተጓዳኝ መሥራት፣
አንቀጽ አምስት
ካፒታል
5.1 የማኀበሩ ካፒታል ብር 1,000,000.00/አንድ ሚሊዮን ብር/ ሲሆን ይኸው ገንዘብ በጠቅላላ

በጥሬ ገንዘብ በአባላቱ ተከፍሏል፡፡


5.2 ጠቅላላው ካፒታል እያንዳንዳቸው ብር 1,000/አንድ ሺህ ብር/ ዋጋ ባላቸው 1,000/አንድ

ሺህ / አክሲዮኖች ተከፋፍሏል፡፡
በመስራች አባላት የተያዘው የአክሲዮን መጠን የሚከተለው ነው፡፡
ተ.ቁ ስም የአክሲዮን የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ መዋጮ
ብዛት
1 አቶ ዮናስ ሙሉአለም በዳሶ 300 1,000 300,000.00
2 አቶ ሳሙኤል ሙሉአለም በዳሶ 349 1,000 350,000.00
3 አቶ ሚኪያስ ሙሉአለም በዳሶ 300 1,000 300,000.00
4 ወ/ሪት ማህሌት ሙሉአለም በዳሶ 50 1,000 50,000.00
5 አቶ በላይአብ በቀለ ጆፌ 1 1,000 1,000.00
ድምር 1000 - 1001000100100
0.00

አንቀጽ ስድስት
የአባላቱ ኃላፊነት
አባላት ከላይ የተጠቀሰውን ካፒታል በጥሬ ገንዘብ በሙሉ የተከፈለ መሆኑን በአንድነት እና
በነጠላ አረጋግጠዋል፡፡ ስለሆነም የአባላቱ ኃላፊነት በማኀበሩ ውስጥ ባላቸው አክስዮን መጠን
የተወሰነ ነው፡፡
አንቀጽ ሰባት
የትርፍና ኪሣራ ክፍፍል
አባላቱ በተለየ ሁኔታ ካልተስማሙ በስተቀር ከጠቅላላው ዓመታዊ ትርፍ ሕጋዊ የመጠባበቂያ
ገንዘብ እና ሌሎች ጠቅላላ ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ ቀሪው በአባላቱ መካከል እንደ አክስዮን
ይዞታቸው ይከፋፈላል፡፡ ኪሣራም ካለ በተመሳሳይ ሁኔታ በአባላቱ መካከል ይከፋፈላል፡፡ ሆኖም
በማንኛውም ሁኔታ አባላቱ በማኀበሩ ውስጥ ካለው የአክስዮን ካፒታል በላይ ተጠያቂ ሊሆኑ
አይችሉም፡፡

አንቀጽ ስምንት
ሥራ አመራር
8.1 የማኀበሩ ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባሩ በመመስረቻ ጽሁፍ በዝርዝር የተመለከተ፣

ከአባላቱ መካከል ወይም ከውጭ በአባላቱ በሚመረጥ፣ የሥልጣን ዘመኑ ላልተወሰነ ጊዜ


በሆነ አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ ይመራል፡፡ በዚህ መሠረት አቶ ሳሙኤል ሙሉአለም በዳሶ
የመጀመሪያው የማኀበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተመረጠዋል፡፡ ምክትል ሥራ
አስኪያጁም አቶ ዮናስ ሙሉአለም በዳሶ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
8.2 የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር

8.2.1 የዘርፍ ሥራ አስኪያችን ይሾማል፣ ይሽራል፣ ተግባራቸውን ዘርዝሮ ይሰጣል፣


ይቆጣጠራል፤
8.2.2 ማኀበሩን በመወከል ይፈርማል፤
8.2.3 ለማኀበሩ ቴክኒካዊና አስተዳደራዊ ተግባሮች ኃላፊ ነው፤
8.2.4 የጠቅላላ ጉባዔዎችንና የቦርዱን ውሳኔዎች ሥራ ላይ ያውላል፤
8.2.5 ለማኀበሩ የሚከፈል ገንዘበ መቀበል፣ የማኀበሩን ዕዳዎች መክፈል፣ ማናቸውም የሐዋላ
ወረቀት የተስፋ ሰነድ፣ የባንክ ሰነድ ማዘጋጀትናና በጀርባ ላይ መፈረም፣ ማደስና
መክፈል እንዲሁም የጭነት ማስታወቂያ ደረሰኞች፣ የቦንድ ሰርተፊኬቶችን ወይም
ማናቸውንም ሰነዶች ማፅደቅና ከጀርባው መፈረም፤
8.2.6 የማኀበሩን ወኪል ወይም ሠራተኛ ይቀጥራል፤ ያሰናብታል፣ ክፍያውን፣ ደሞዙን
ጉርሻና ሌሎች ከመቀጠርና ከመሰናበት ጋር የተያያዙ ሁኔታዎችን ይወስናል፤
8.2.7 ለማኀበሩ ንግድ በመልካም ሆኔታ መካሄድ የሚጠቅሙ ግዢዎች ሽያጭና የእነዚህን
ማዘዣዎች ይወስናል፤
8.2.8 ከማኀበሩ ንግድ ጋር የተያየዙ ማናቸውንም የንግድ ልውውጥ በተመለከተ ከሶስተኛ
ወገኖች ጋር ውል ይዋዋላል፤ ጨረታ ይጫረታል፡፡
8.2.9 በማናቸውም ፍ/ቤት ማኀበሩ ከሳሽ፣ ተከሳሽ ወይም ጣልቃ ገብ በሚሆንበት ጉዳይ
ሁሉ ማኀበሩን በመወከል አስፈላጊውን ይፈጽማል፤ አስፈላጊ ሲሆን ጠበቃ ይወክላል፡፡
8.2.10 በማህበሩ ስም የሚንቀሣቀስም ሆነ የማይንቀሣቀስ ንብረት ይገዛል፣ ይከራያል፣
የኪራይ ውል ይዋዋላል፣ ውል ያድሳል፡፡
8.2.11 የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጅ በጋራ በመሆን በማህበሩ ስም
የባንክ ሂሣብ ይከፍታሉ፣ ሂሣቡን በፊርማቸው ያንቀሣቅሳሉ፣ ገንዘብ ወጪ ገቢ
ያደርጋሉ፣ ወጪ የሚደረጉ ቼኮች ላይ ይፈርማሉ፣
8.2.12 የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጅ በጋራ በመሆን በማህበሩ ስም
ተመዝግቦ የሚገኘውን የሚንቀሣቀስም ሆነ የማይንቀሣቀስ ንብረት ወይም የ 3 ኛ
ወገን ንብረት በዋስትና በማስያዝም ሆነ ያለዋስትና ከባንክ፣ በግለሰብ፣ ከአበዳሪ
ተቋማት ገንዘብ ይበደራሉ፣ የብድርና የመያዣ ውል ይዋዋላሉ፣ ፈርመው
ይቀበላሉ፣
8.2.13 የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጅ በጋራ በመሆን የማህበሩን
የሚንቀሣቀስም ሆነ የማይንቀሣቀስ ንብረት ሶስተኛ ወገን ከባንክ ለሚበደረው
ብድር በዋስትና ያሲይዛሉ፣
8.2.14 የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጅ በጋራ በመሆን በማህበሩ ስም
ተመዝግቦ የሚገኘውን የሚንቀሣቀስም ሆነ የማይንቀሣቀስ ንብረት ያከራያሉ፣
ይሸጣሉ፣ ይለውጣሉ፣
8.2.15 ማህበሩን በመወከል አዲስ የሚቋቋሙ ወይም በተቋቋሙ የንግድ ማህበራት ውስጥ
በመስራች አባልነት እና/ወይም በአባልነት የመመስረቻ ጽሁፍ እና ሌሎች የቃለ
ጉባኤ ሰነዶች ላይ ይፈርማል፣ ድምፅ ውሳኔዎችን ያሳልፋል አክሲዮኖች ይገዛል፣
ከምክትል ሥራ አስኪያጅ ጋር በጋራ ይሸጣል እንደ አስፈላጊነቱ ውሳኔ ይወስናል፡፡
8.2.16 ማኀበርተኞች ሊቀበሉትና ሊያፀድቁት እንዲችሉ የሂሣብ ወጪና የገቢ መዝገብ
በደንቡ እንዲያዝ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡
8.2.17 የማኀበሩ ዓላማ ግቡን እንዲመታ አስፈላጊ መስሎ በታየው ጊዜ ከላይ ከተገለጹት
ተግባራት መሀል ማናቸውን በሌላ ሶስተኛ ሰው እንዲፈጸም በማኀበሩ ስም ውክልና
መስጠት ይችላል፡፡
8.2.18 በማንኛውም ጊዜ ምክትል ሥራ አስኪያጁ ዋና ሥራ አስኪያጁን ተክቶ ይሰራል፡፡
አንቀጽ ዘጠኝ
ኦዲተር
ማኀበሩ በአባላቱ የሚመረጡ ኦደተር/ኦዲተሮች/ ይኖሩታል፡፡
አንቀጽ አስር
ካፒታል ስለመጨመር

10.1 የማኀበሩ ካፒታል በጥሬ ገንዘብ በሙሉ የተከፈለ ጠቅላላ ብር 1,000,000.00/አንድ

ሚሊዮን ብር/ ነው፡፡


10.2 ከማኀበሩ አባላት ቢያንስ የካፒታሉን ¾ ድርሻ የያዙት ሲስማሙ የኩባንያውን ካፒታል

አንድ ጊዜ ወይም ብዙ ጊዜ ማሳደግ ይቻላል፡፡ በዚህ ጊዜ አከሲዮኖች በተጨማሪነት


የሚመደቡት ማኀበርተኞች ቀደም ሲል በነበራቸው የአክሲዮኖች ድርሻ መጠን ልክ
ይሆናል፡፡ የካፒታል ጭማሪ የኢትዮጵያ ንግድ ሕግ በሚፈቅደው በማንኛውም መንገድ
መሆን ይችላል፡፡
አንቀጽ አስራ አንድ
አክስዮኖች
11.1 አክስዮኖች በአባላት መካከል ያለምንም ገደብ ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡እንዲሁም የሟች አባል

አክስዮኖች ያለምንም ገደብ ወራሽነታቸውን ላረጋገጡ ወራሾች ይተላለፋሉ፡፡


11.2 አክስዮኖች ከማኀበሩ ውጪ ለሌላ ሰው ማስተላለፍ የሚቻለው በቅድሚያ ቢያንስ

ቢያንስ ከማኀበሩ ካፒታል 75% የያዙትን አባላት ስምምነት ማግኘት ሲቻል ነው፡፡
የአባላቱ ስምምነት ካልተገኘና አክስዮን ማስተላለፍ የፈለገው አባል በሀሳቡ ከፀና
ለሽያጭ የቀረበውን አክስዮን የመግዛት ቅድሚያ የሚሰጠው ከአባላቱ መካከል ቀደምት
ለሆነው ይሆናል፡፡ ከአንድ በላይ ቀደምትነት ያላቸው ሰዎች አክስዮን ለመግዛት
ያላቸውን ቅድሚያ መብት ለመጠቀም የፈለጉ እንደሆነ ከመሀከላቸው በጨረታ አሸናፊ
ለሆነው አባል ይሸጣል፡፡
11.3 ከላይ በተመለከተው ሁኔታ የተደረገ የአክስዮን ማስተለለፍ በጽሁፍ መሆን ያለበት ሲሆን

በአክስዮን መዝገብ ካልተመዘገበ ዋጋ አይኖረውም፡፡ የምዝገባ አስፈላጊነት አክስዮንን


በሚመለከት ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡
አንቀጽ አስራ ሁለት
የማኀበሩ አባላት መብትና ግዴታዎች
12.1 እያንዳንዱ አባል የሚከተሉት መብቶች ይኖሩታል፡፡
ሀ. በማናቸውም የአባላት ስብሰባ ላይ የመካፈል፣
ለ. በማናቸውም ስብሰባ ላይ በያዘው የአክስዮኖች ብዛት መጠን ድምጽ የመስጠት፣
ሐ. በዋናው መሥሪያ ቤት ውስጥ ያሉ የቆጠራ ውጤቶችን፣ የወጪና ገቢ ምዝገባዎችና የኦዲተር
ሪፖርቶች የመመርመርና መዝግቦ የመያዝ፣
መ. በሕግ፣ በማኀበሩ መመሥረቻ ጽሁፍ የተመለከቱትን መብቶች የመጠቀም፡፡
12.2 ከላይ የተመለከተው የአባላት መብት እንደተጠበቀ ሆኖ፣
ሀ. ማኀበሩ ለአንድ አክስዮን ከአንድ በላይ ንብረት አይቀበልም፡፡ ስለሆነም በዚህ መሠረት የአክስዮን የጋራ
ባለንብረቶች ቢኖሩ የአባልነት መብታቸውን ሊጠቀሙበት የሚችሉት ከመካከላቸው አንድ
እንደራሴ በመሾም በቻ ነው፡፡
ለ. ከአክስዮኖች ጋር የተያያዙ መብቶች አክስዮኑን ይከታተላሉ፡፡ የአክስዮን ባለቤት በመሆን የተፈጥሮ
ሰውም ሆነ በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል በደንቡ መሠረት በመብቶቹ ሊገለገል ይችላል፡፡
በአንፃሩም የአክስዮን ባለቤት መሆን ለዚህ መመሥረቻ ጽሁፍና በአግባቡ ለሚተላለፉ የአባላት
ውሳኔዎች ተገዢ የመሆን ውጤቶች ያስከትላል፡፡
ሐ. የሟች ማኀበርተኞች ወራሾም ሆኑ ወኪሎች በማኀበሩ ንብረቶች ላይ ማህተም እንዲደረግ ወይም
እንዲታሸግ የማድረግ መብት አይኖራቸውም፡፡ ስለሆነም በመብታቸው በሚጠቀሙበት ጊዜ ሁሉ
የመመስረቻ ጽሁፍና በአግባቡ የሚተላለፉ የማኀበርተኞች ውሳኔዎች ሁሉ በነሱም ላይ
ተፈጻሚነት አለቸው፡፡
አንቀጽ አስራ ሶስት
ያለ ስብሰባ ስለሚተላለፉ ውሳኔዎች
13.1 ጉባዔ እንዲሰበሰብ ሕግ ወይም የማኀበሩ መመስረቻ ጽሁፍ በማያስገድድበት ጊዜ ዋናው

ሥራ አስኪያጅ ድምጽ ሊሰጥበት የተፈለገውን ጉዳይ ለእያንዳንዱ አባል በጽሁፍ በመላክ


በጉዳዩ ላይ አባላት በጽሁፍ ድምጽ እንዲሰጡበት መጠየቅ አለበት፡፡
አንቀጽ አስራ አራት
ስብሰባዎች
14.1 የማኀበሩ የሂሣብ ዓመት ከተዘጋ አራት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የማኀበሩ ጠቅላላ ጉባኤ መጠራት
አለበት፡፡
14.2 ዋናው ሥራ አስኪያጅ ዓመታዊ የማኀበርተኞች ስብሰባ ከመደረጉ በፊት ከ 24 ቀን ባላነሰ ጊዜ አስቀድሞ
ለአባላት በአደራ ደብዳቤ የስብሰባውን ጥሪ ማሳወቅና ለውሳኔ ወይም ለውይይት ያቀረበው ሃሳብ ምን
እንደ ሆነ በግልጽ ማስረዳት አለበት፡፡
14.3 ኦዲተር ወይም በዋናው ገንዘብ ከግማሽ በላይ የሚወክሉ ማኀበርተኞች በማንኛቸውም ጊዜ የማኀበሩ
ጠቅላላ ጉባዔ እንዲሰበሰብ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
አንቀጽ አስራ አምስት
ምልአተ ጉባዔ
15.1 የማኀበሩ ስብሰባ ሊካሄድ የሚችለው ከዋና ገንዘብ 75% በላይ ያላቸውን የሚወክሉ ማኀበርተኞች
ስብሰባው ላይ ሲገኙ ነው፡፡
15.2 በዚህ ዓይነት ስብሰባዎች ላይ ውሳኔዎች የሚተላለፉት በድምጽ ብልጫ ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ ስድስት


የኦዲተር ሥልጣንና ተግባር
16.1. ኦዲተሮችና ረዳት ኦዲተሮች በሕግ፣ በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ የተጠቀሱትን ሥልጣኖችና ግዴታዎች
አሏቸው፡፡
16.2. ማንኛውም ኦዲተር ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ሥልጣኖችና ግዴታዎች ይኖሩታል፣
ሀ. የማህበሩን መዛግብትና ሰነዶችን መመርመር፣
ለ. የማኀበሩን ንብረት እና የሂሳብ ማመዛዘኛ ትርፍና ኪሳራውንም የሚያሳዩትን መዛግብት
ትክክለኛነት ማረጋገጥ፣
ሐ. የማህበሩን ሥራ አስኪያጅ የሰጠው ሪፖርት የማህበሩን ትክክለኛ ገጽ የሚያሳይ መሆኑን
ማረጋገጥ፣
መ. ሥራውን ለማከናወን አስፈላጊ ነው ብሎ የሚያሳዩትን መዛግብት ትክክለኛነት ማረጋገጥ፣
ሠ. በዓመታትና በማናቸውም ጉባኤ መገኘት፣
ረ. ሌሎች ግዴታዎችንም መፈፀም፣
አንቀጽ አስራ ሰባት
የጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣን

17.1 የማኀበሩን ዋና ሥራ አስኪያጅ መግለጫ ሰምቶ ተቀባይነት ያለው ሆኖ ካገኘው

ያፀድቃል፡፡
17.2 የማኀበሩን ሂሣብ ተቆጣጣሪ/ኦዲተር/ ዓመታዊ መግለጫ መርምሮ ተገቢውን እርምጃ

ይወስድል፡፡
17.3 የማኀበሩን ዋና ሥራ አስኪያጅ ይሾማል በቂ ምክንያት ሲኖር በንግድ ሕጉ በተደነገገው

መሠረት ይሽራል፡፡
17.4 ለዋና ሥራ አስኪያጅ ሊከፈል የሚገባውን የአገልግሎት ዋጋ ይወስናል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ

ዋና ሥራ አስኪያጅ አባል ቢሆንም አይካፈልም፡፡


17.5 የማኀበሩን የሥራ አፈፃፀም በሚመለከት ለዋናው ሥራ አስኪያጅ መመሪያ ይሰጣል፡፡

17.6 ማህበሩን ለማስፋፋት ወይም ለማፍረስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያኘው ውሣኔ ይሰጣል፡፡

17.7 ስለ ዓመታዊ ትርፍ አከፋፈል ውሣኔ ይሰጣል፡፡


አንቀጽ አስራ ስምንት
የማኀበሩ የበጀት፣ የሂሣብ መግለጫና
ሕጋዊ የመጠባበቂያ ገንዘብ
18.1 የማኀበሩ የሂሣብ ዓመት በየዓመቱ ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ ሰኔ 30 ቀን ይፈፀማል፡፡ ስለሆነም
የመጀመሪያው የሂሣብ ዓመት የመመስረቻ ጹሁፍ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ
ይሆናል፡፡
18.2 በየሂሣቡ ዓመት መጨረሻ የማኀበሩን ንብረቶች ዕቃዎች የሚያሳይ ሚዛን በዋናው ሥራ አስኪያጅ
ይዘጋጃል፡፡ ይህም ሚዛን እንዲፀድቅና እንዲመረመር ለኦዲተሮችና ማኀበርተኞች ይተላልፋል፡፡
18.3 የማኀበሩን ዓመታዊ ሁኔታ፣ የሂሣብ ሚዛን፣ የትርፍና የኪሣራ ሁኔታ፣ የንብረት ቆጠራዎችና የዋና ሥራ
አስኪያጅ/ወይም/ የኦዲተር ሪፖርት የሚያሳዩ ሰነዶች በየጊዜው ለአባላት ይላካሉ፡፡
18.4. በንግድ ሕጉ አንቀጽ 539 እንደተደነገገው በተጣራው ትርፍ ላይ በየዓመቱ መጠባበቂያ የሚሆነውን
ቢያንስ አምስት በመቶ እየተነሳ ይቀመጣል፡፡ ይኸው መጠባበቂያ ከማኀበሩ ዋና ገንዘብ አንድ አስረኛ
እጅ ሲደርሱ ግዴታ መሆኑ ይቋረጣል፡፡
አንቀጽ አስራ ዘጠኝ
ስለመፍረስ
19.1. ማኀበሩ በንግድ ሕግ፣ አዋጅ ቁጥር 1243/13 አንቀት 181 መሠረት በቂ በሆኑ ምክንያቶች በፍርድ
ቤት ውሳኔ ይፈርሳል፡፡
አንቀጽ ሃያ
የማጠቃለያ ድንጋጌ
በመመስረቻ ጽሁፍ በግልጽ ያልተካተቱ ጉዳዮች በንግድ ሕጉ መሰረት ይወሰናሉ፡፡
አንቀጽ ሃያ አንድ
የማኀበሩ የሥራ ዘመን
አባላቱ በተለየ ሁኔታ ለመወሰን ያለው መብት እንደተጠበቀ ሆኖ ማኀበሩ የተቋቋመው ላልተወሰነ
ጊዜ ነው፡፡
ተ.ቁ. የመስራች አባላት ስም ፊርማ
1 አቶ ዮናስ ሙሉአለም በዳሶ
2 አቶ ሳሙኤል ሙሉአለም በዳሶ
3 አቶ ሚኪያስ ሙሉአለም በዳሶ
4 ወ/ሪት ማህሌት ሙሉአለም በዳሶ
5 አቶ በላይአብ በቀለ ጆፌ

You might also like