Dubai

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 11

-

ዱባይ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ውስጥ የምትገኝ በቅንጦት ግዢ፣ በእጅግ ዘመናዊ የስነ ህንፃ አሰራር
እና በህያው የምሽት ህይወት ትዕይንት የምትታወቅ ከተማ ናት።

ከ 7 ቱ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ውስጥ በሕዝብ ብዛት የምትታወቅ እና የኢሚሬትስ ዋና ከተማ

ነች፣ በ 18 ኛው ክፍለ ዘመን እንደ ትንሽ የዓሣ ማጥመጃ መንደር በመሆን የተመሰረተችው

ከተማዋ በ 21 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በቱሪዝም እና በቅንጦት ህይወት ላይ በማተኮር


በአለም ሁለተኛ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎች እና በአለም ላይ ረጅም ህንፃ የሆነውን ቡርጅ ከሊፋን
በመገንባት በፍጥነት ያደገች ከተማ ነች።

በ 1971 ከታላቋ ብሪታንያ ነፃ መውጣትን ተከትሎ የተፈጠረው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ


ፌደሬሽን ካቋቋሙት እና ሀብታም ከሆኑት ከሰባቱ ኢሚሬትስ ከተሞች መካከል አንዷ የሆነችውን
ዱባይን የኢሚሬትስ ዋና ከተማ በማለት ሰይመዋታል።
ዱባይ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች፣ ወደቦች እና የባህር ዳርቻዎች ያሉባት ከተማ ነች። የአካባቢው ህዝብ
በዋነኛነት ሙስሊም ነው። ምንም እንኳን ጉልህ የሆኑ ክርስቲያን፣ ሂንዱ እና የሲክ ማህበረሰቦች ቢኖሩም
ገዥው ቤተሰብ ሙስሊም ላልሆኑ ሰዎች ካለው መቻቻል እና ከተማዋ በንግድ ስራ ላይ ካደረገው ትኩረት
አንፃር፣ የተለያዩ ማህበረሰቦች ተስማምተው ይኖራሉ።

ልክ እንደ አብዛኛው የፋርስ ባህረ ሰላጤ የባህር ዳርቻ፣ ዱባይ ዓመቱን ሙሉ ሞቃታማ የአየር ጠባይ

አላት። በበጋው ወራት እርጥበት ከፍ ያለ ሲሆን የቀረው አመት መካከለኛ ነው . በጣም ቀዝቃዛው

የክረምት ወር ብዙውን ጊዜ ጥር (January) ላይ ሲሆን ዝቅተኛው የሙቀት መጠን

15 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነው። በጣም ሞቃታማው የበጋ ወር ደግሞ july ላይሲሆን ከ 40


° ሴ በላይ ሊሞቅ ይችላል።

የዱባይ ህዝብ ላለፉት ሁለት መቶ ዓመታት ከጥቂት ሺህ የአካባቢው ነዋሪዎች ተነስቶ አሁን ላይ ከሁለት
ሚሊዮን በላይ ደርሷል።
በ 1960 ዎቹ እና 1990ዎቹ መካከል ያገኘችው ተፈጥሯዊ የዘይት ሀብት መሠረተ
ልማቶችን በመገንባት ሌሎች የኤኮኖሚ ዘርፎችን ለማሳደግ ያገለግል ነበር። ከተማዋ ሁለቱን የዓለም
ትላልቅ ወደቦች በተጨናነቀ ዓለም አቀፍ የአየር ጭነት ማእከል በማንቀሳቀስ ንግድ የዱባይ ኢኮኖሚ ዋና
ማዕከል ሆኖ እንዲቆይ አድርጋለች።

የጄበል አሊ ነፃ የንግድ ዞን በ 1980 ዎቹ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ተቋቋመ።

,
እዚያ ላይ የተመሰረቱ እንቅስቃሴዎች የአልሙኒየም ማቅለጥ የመኪና እና የሲሚንቶ ማምረትን
ያካትታሉ። እንደ ጀበል አሊ ያሉ በርካታ ነፃ ዞኖች የውጭ ኩባንያዎች በዱባይ የአገር ውስጥ አጋር
ሳያስፈልጋቸው እንዲሠሩ ያስችላቸዋል።
ሰፊ አውራ ጎዳናዎች፣ ሞቃታማ የአየር ጠባይ እና ኑሮዋ ዓመቱን ሙሉ በአየር ማቀዝቀዣ ላይ
የተመሰረተው ዱባይ በእግር ለሚንቀሳቀሱ እንግዶች ምቹ ከተማ አይደለችም። በዚህም ምክንያት
የተሸከርካሪዎች ትራፊክ በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አዳዲስ ድልድዮች፣ መንገዶች እና ሙሉ
በሙሉ አውቶሜትድ የሆነ አሽከርካሪ አልባ የሜትሮ ባቡር መስመር በመዘርጋቱ በከተማው ውስጥ
ያለውን መጨናነቅ አቅልሎታል።

በመዳፍ ቅርጽ የተሰራው Palm Jumeirah ፣ ሰው ሰራሽ የባህር ዳርቻ


ደሴት በዱባይ ዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ፣ የግል መኖሪያ ቤቶች እና ሆቴሎች ያረፉበት ስፍራ ነው።
ደሴቱ ከአየር ላይ ሲታይ በቅጥ የተሰራ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል። ከዋናው መሬት ጋር በድልድይ የተገናኘው
ሰፊው ግንድ የደሴቱ መግቢያ ሆኖ ያገለግላል።
ፓልም ጁሜይራህ በዱባይ መንግስት ባለቤትነት የተያዘ የሪል እስቴት ኩባንያ ነው። ማስተር ፕላኑን
ያዘጋጀው በሄልማን ሁርሊ ቻርቫት ፒኮክ የአሜሪካው የሥነ ሕንፃ ግንባታ ድርጅት ነው። ደሴቶቹ
የተሠሩት በአብዛኛው ከፋርስ ባሕረ ሰላጤ ወለል ላይ ከተፈለፈለ አሸዋ ነው። የተቀረው በክፍተት
በድንጋይ ተሸፍኗል።

ቪላ ቤቶች፣ አፓርታማዎች፣ ሱፐርማርኬትች እና ሆቴሎች በዚህ ደሴት ላይ ተገንብተዋል። በ 21


ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አስርት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 10,000 ሰዎች በፓልም
ጁሜይራ ውስጥ ይኖራሉ ተብሎም ይገመታል።

ፓልም ጁሜራህ በዱባይ ከሚገኙት ተመሳሳይ ቅርጽ ካላቸው ሦስት ሰውሰራሽ የባህር ደሰቶች

የመጀመሪያው እንዲሆን ታስቦ የነበረ ቢሆንም የተቀሩት በትልቅነታቸው የሚታወቁት  Palm


Jebel Ali Palm Deira
እና  ባለው የገንዘብ ማጠር ምክንያት
ሳይጠናቀቁ እስካሁን ድረስ ቆይተዋል።
ዱባይ ቆንጆ ሰው ሰራሽ ደሴቶች የቱሪስት መስህብ ብቻ አይደለችም -
ዋና የምህንድስና መገኛም
ጭምር እንጂ ።
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ነዳጁ ለዘላለም እንደማይቆይ ያውቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ሼክ መሀመድ
ያለፔትሮሊየም መኖር የምትችል ከተማቸውን አለም አቀፍ ደረጃ ያለው የቱሪስት መካ ለማድረግ
ያለፉትን ሁለት አስርት አመታት ሲሰሩ ቆይተዋል።

. ..
የፓልም ደሴቶች እጅግ አስደናቂ የሆነ የምህንድስና ፕሮጀክቶች ናቸው። እ ኤ አ በ

2001 ፣ ሞቃታማ ከሆነውና እና ጥልቀት ከሌለው ከገልፍ ውሃ በስተቀር በዱባይ የባህር ዳርቻ
ምንም ነገር አልነበረም።

ትንሹን ደሴት እንኳን ለመጨረስ አሥር ዓመታት ፈጅቷል .


ፓልም ጁሜይራህ የመጀመሪያው እና ትንሹ የሆነው ደሴት ግንባታ ከተጠበቀው በላይ አመታትን
ያስቆጠረ ቢሆንም ዛሬ ግን ሰፊ የገበያ ማዕከሎች እና የቅንጦት ሆቴሎች መናኸሪያ ነው።
በዱባይ ውስጥ ትልቁ ፌስቲቫል የዱባይ የገበያ ፌስቲቫል ሲሆን ይህ የኤምሬትስ ህዝብ ምን ያህል መግዛት
እንደሚወድ በግልፅ ያሳያል።

ዱባይ የንግድ ከተማ ናት። ለጉብኝት የሄደ ሰው በቀላሉ መገበያየት እንዲችል በማሰብ በገበያ ማዕከሎቿ
ውስጥ የተለያዪ ነገሮችን ለገበያ ታቀርባለች። ከነዚህም መካከል
የወርቅ እና የአልማዝ ጌጣጌጥ፣ የፋርስ ምንጣፎች፣ የአረብ ቡና ማፍያዎች፣ የኤሌክትሮኒክ
ዕቃዎች፣ከግመል ወተት የተሰሩ ቸኮሌቶች እና የዱባይ ቅመሞች ይገኙበታል።

የወርቅ ሀብል ወይም አምባሮች ለመግዛት ከዱባይ የተሻለ ቦታ የለም። በግብር ፖሊሲያቸው ምክንያት
እዚህ የጌጣጌጥ ዋጋ ከሌሎች ከተሞች ያነሰ ነው። ከወርቅ ጌጣጌጥ በተጨማሪ የአልማዝ እና

የፕላቲኒየም ጌጣጌጦችን በተመጣጣኝ ዋጋ መግዛት ይችላሉ .


ቡና አፍቃሪዎች በዚህ መራራ ግን መንፈስን በሚያድስ የአረብ ቡና ጣዕም ያልተለመደ ደስታ ያገኛሉ።
ብዙውን ጊዜ የጣዕሙን ሚዛን ለመጠበቅ ከአንዳንድ ጣፋጭ ምግቦች ጋር ተያይዞ ይቀርባል። እዚህ
ያለው ቡና በጠንካራ ጣዕሙ ይታወቃል።

በዱባይ መደብሮች ውስጥ ያሉት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ከብዙ ገበያዎች በአንፃራዊነት ርካሽ ናቸው።
ከስማርትፎኖች፣ ታብሌቶች፣ ላፕቶፖች፣ ኤልኢዲ ቲቪዎች፣ ካሜራዎች፣ ወዘተ ሁሉም ነገር የበለጠ
ተመጣጣኝ ሆኖ ይታያል።

በአለም ላይ ትልቁ የአበባ መናፈሻ ከከተማው ወጣ ብሎ ይገኛል። የፓርኩ ማእከል እጅግ አስደናቂ

የሆነው እና ከአበባ የተሰራው ኤ380 ኤሚሬትስ አውሮፕላን ነው።


አትክልቱ ብዙ ምግብ ቤቶች፣ የሚያማምሩ የመጫወቻ ቦታዎች አሉት።
በዱባይ ታዋቂው የምሽት የበረሃ ውስጥ አዳር አንዱነው። በተለይ ሌሊቱን በባህላዊ ቤዱዊን ካምፕ
ውስጥ ለማሳለፍ ለሚፈልጉ ታስቦ የተሰራ ሲሆን ከበረሃ ሰማይ ስር በመተኛት መዝናናት ይችላሉ።
ጣፋጭ የአረብ እራት ከተለያዩ ምግቦች፣ ጣፋጮች እና ሌሎችም ጋር ተዘጋጅቶ በእሳቱ ዘሪያ አንድ ላይ
በመሰባሰብ ምሽታችን ያማረ እንዲሆን ማድረግ እንችላለን።

ኦውድ፣ አረብኛ ኡድ፣ ባለገመድ የሙዚቃ መሳሪያ በመካከለኛው ዘመን እና በዘመናዊ እስላማዊ ሙዚቃ

"
ውስጥ ታዋቂ ነው። ስሙ በአረብኛ ቀጭን እንጨት "ማለት ሲሆን ይህ ደግሞ የእንቁ ቅርጽ ያለው
ሰውነቱን ለመሥራት የሚያገለግሉትን እንጨቶች ያመለክታል። በዚህ የበረሀ ውስጥ አዳር ትክክለኛ
ሙዚቀኞች የአረብ ሙዚቃዎችን በዚህ መሳሪያ በመታገዝ ለቱሪስቶች ያቀርባሉ።
በግንባታው ወቅት ቡርጅ ዱባይ በመባል የሚታወቀው ቡርጅ ካሊፋ (“ የካሊፋ ግንብ” ) በይፋ

የተሰየመው የአቡ ዳቢ መሪ ሼክ ካሊፋ ኢብን ዛይድ አል ነህያንን ለማክበር ነው። ግንቡ ጥር 4 ቀን

2010 በይፋ የተከፈተ ቢሆንም አጠቃላይ የውስጥ ክፍል በወቅቱ አልተጠናቀቀም ነበር።

የተለያዩ የንግድ፣ የመኖሪያ እና የመስተንግዶ ሥራዎችን ለመሥራት የተገነባው ግንብ በ 163


ፎቆች እና በ 2,717 ጫማ (828 ሜትር ) ከፍታ ላይ ይገኛል። የተነደፈው ቺካጎ

-
ውስጥ በሚገኘው በስኪድሞር፣ ኦዊንግስ እና ሜሪል የስነ ህንፃ ድርጅት ነው።

ቡርጅ አል አረብ በዱባይ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ከተማ ውስጥ የሚገኝ የቅንጦት ሆቴል ነው።

በ Jumeirah  ሆቴል ቡድን የሚተዳደረው ይህ ሆቴል ምንም እንኳን ከጠቅላላው

ቁመቱ 39% የሚሆነው ሰው ሊይዝ በማይችል ቦታ የተሰራ ቢሆንም፣ በዓለም ላይ ካሉ


ረጃጅም ሆቴሎች አንዱ ነው።
ቡርጅ አል አረብ ከጁመይራ ባህር ዳርቻ280 ሜትር ርቃ በምትገኘው አርቲፊሻል ደሴት ላይ
ሲገኝ ከዋናው መሬት ጋር ድልድይ የተገናኘ ነው። የመዋቅሩ ቅርፅ የተነደፈው የመርከብን ሸራ ለመምሰል

ነው። ከመሬት በላይ 210 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል።

ዱባይ የፓልም ትሪ ደሴቶችን የገነባችው ለቱሪስቶች የባህር ዳርቻን ለመጨመር ነው። ዱባይ ፀሐያማ
የአየር ጠባይ እና የባህር ዳርቻዎች በመሆኗ የምትታወቅ ቢሆንም የቱሪስቶችን ቁጥር በሦስት እጥፍ

ለማሳደግ እና በዓመት ወደ15 ሚሊዮን ለማድረስ ከ 72 ኪሎ ሜትር በላይ የባህር ዳርቻ

ያስፈልጋል። መፍትሄው በ 2006 ሲጠናቀቅ የዘንባባ ዛፍ ቅርጽ ያለው ግዙፍ ደሴት መገንባት

ነበር በባህር ዳርቻው ላይ56 . .ኪ ሜ ደሴቱ የተነደፈችው በራሷ ውስጥ ያለች ከተማ
እንድትሆን ነው፣ የገበያ ማዕከላትን፣ ሬስቶራንቶችን፣ ሆቴሎችን እና የመኖሪያ ንብረቶችን ያሳያል።

You might also like